በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የአዲስ አበባና አጎራባች ከተሞች ሙስሊም ወደ ቃላቲ ጉዞውን ቀጥሏል

Update: 03:30 AM, November 18, 2012 (via facebook)

Seidhusen Hussen say’s

ክርስቲያን ወገኖቻችን ወደ ቃሊቲ ኮሚቲዮቻችንን ሊዘይር ለመጣው ህዝብ ከቤታቸው ውሀ በባልዲ እና በጄሪካን በማውጣት ሙስሊሙን እያጠጡ ይገኛሉ ምንም እንኳን ETV አሸባሪ ናቸው ቢልም ዉሸትነቱ የተረዱ ክርስቲያን ወገኖቻችን ሙስሊሙን በመርዳትና በማገዝ ላይ ናቸዉ አንዴ ተክቢር በሉላቸው!!

Ethiopian Christians serving water for Ethiopian Muslim protesters

***

(ዘግይቶ በደረሰን ዜና መሰረት፣ ወደ ቃሊቲ ውስጥ መገባት ተጀምሯል፡፡)

ወያኔዎች በሙስሊሙ የሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸውን ተከትሎ የተቀሰቀሰው የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ አመጽ አንደቀጠለ ነው።

አመጹን ለማስቆም እንደተለመደው ወያኔዎች የመረጡት መንገድ መግደል፣ ማሰርና በድብደባ አካላዊ ጉዳት መፈጸም ቢሆንም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች “ወይ ፍንክች” ብለው ተቃውሟቸውን ዘዴ እየቀያየሩ ቀጥለዋል።

የመብት ተሟጋች ሙስሊሞች በሶሻል ሚድያ መረብ እየገለጹት እንዳለው ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በቃሊቲው ማጎሪያ ፊት ለፊት እየተሰባሰቡ ነው። ረፋዱ ላይ የሙስሊሞቹ ቁጥር እጅግ ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል። ሙስሊሞቹ ወደ ቃሊት ማጎርያ እየተመሙ ያሉት የታሰሩ መሪዎቻቸውን ብርታት ለመስጠትና ለአሳሪዎቻቸው (ወያኔዎች) ደግሞ በትግላቸው እንደሚገፉበት ለማሳሰብ ነው።

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ይህ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጽናት ለሌሎችም አርአያ ሊሆን ይችላል እያሉ ነው።

ይህ በዚህ እንዳለ ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ጋዜጠኛ አበበ ገላው በድረ-ገጾች ባሰራጨው ጽሁፉ “ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያነሱት የመብት ጥያቄ በማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊደገፍ ይገባል” ብሏል። አበበ ገላው በዚህ ጽሁፉ ካመላከታቸው እውነታዎች መካከል፣ አሁን በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እየተደረገ ያለው ጣልቃ ገብነት እና አፈና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንና ምዕመናን ላይ ባለፉት 20 አመታት ዉስጥ ሲደረግ የነበረና አሁንም በመደረግ ላይ ያለ ነው ብሏል። የአበበ ገላውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

የሙስሊሞቹን የቃሊቲ ውሎ እየተከታተልን በዚህ ብሎግ ፖስት ላይ እንዘግባለን…ecadforum.com

Advertisements

Posted on November 18, 2012, in News and tagged , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s