የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመኘውና ማየት የሚፈልገው! ተቃዋሚው መመለስ ያለበት!

ከፈቃዱ በቀለ

መግቢያ

ባለፉት ዐመታት በአንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ምርጫዎች ተካሂደዋል። ከአምስት ዐመት በፊት በኬንያ የተካሄደውንና፣ በሚያዚያ ወር 2011 ዓ.ም ደግሞ በናይጄሪያ የተደረገውንEthiopian flag (Alemayehu G. Mariam)የፕሬዚደንትና የፓርላሜንት ምርጫ ትዝ ሳይለን አይቀርም። ከአንድ ዐመት በፊት ደግሞ በቱኒዚያ የተለኮሰው የሰሜን አፍሪካው የጥቢው አብዮት እየተባለ የሚጠራው ወደ ግብጽና ወደ ሊቢያ፣ ከዚያም ወደ የመን በመሸጋገር የስርዓት ለውጥ ሳይሆን የፕሬዚደንቶችን ለውጥ አስከትሏል። ከአንድ ዐመት በላይ በሰሜን አትላንቲክ የጦር ድርጅትና፣ በሳውዲ አረብያና በካታር የውስጥ ለውስጥ እየተደገፈ የሶርያ የነጻ አውጭ ወታደር እየተባለ የሚጠራው የፕሬዚደንት አሳድን መንግስት ለመጣል የሚደረገው የርስ በርስ ጦርነትና፣ በግምት ለሰላሳ ሺህ ሰዎች መሞት ምክንያት የሆነው ወዴት እንደሚያመራ ከአሁኑ በእርግጠኝነት ለመናገር ያስቸግራል። አንድ በእርግጠኝነት ለመናገር የሚቻለው ነገር ፕሬዚደንት አሳድ ቢወድቁ እንኳን የሶርያ ህዝብ እጣ የጨለመ ይሆናል። የርስ በርሱ ጦርነት ይቀጥላል። ምናልባትም ሶርያ ወደ ሶስት ቦታዎች የምትሽነሸንበት ሁኔታ ይፈጠር ይሆናል። ይህም ማለት የሶርያ ህዝብ የፈለገውን የዲሞክራሲ ምኞቱን በፍጹም አይቀዳጅም ማለት ነው።

በኬንያና በናይጀሪያ የተደረገው የፕሬዚደንትነት ምርጫ ያለውን ስርዓት የበለጠ ያጠናከረ እንጂ የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄ የፈታ አይደለም። በሁለቱም አገሮች ድህነት፣ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ መኖር ባህላዊ የአኗኗር ስልት ሆኗል። በየአራት ወይም በየአምስት ዐመቱ የፈለገውን ያህል ምርጫ ቢካሄድም፣ ምርጫው በሁለቱም አገሮች የሰፈነውን የስራ አጥነት ብዛት ሊቀንስና ድህነትን ሊቀርፍ አልቻለም። የሀብት ክፍፍሉ እንዳለ በመቅረት በሀብታምና በደሃ መሀከል ያለው ልዩነት እንደሰፋና እንደተጠናከረ ነው። የናይጄሪያም ሆነ የኬንያ ህዝብ የየአገሮቻቸው ዕድል ወሳኞች መሆን እልቻሉም። ስለሆነም በሁለቱም አገሮች ያለው ህብረተሰብአዊ ግጭት፣ በተለይም ደግሞ በናይጄሪያ ከሃይማኖት ጋር ተሳቦ የሚካሄደው ተራን ህዝብ በቦምብ መግደል ቀጥሏል። ሁለቱም አገሮች ለረዥም ዐመታት በትርምስ ዓለም ውስጥ እንደሚኖሩ ከአሁኑ በእርግጠኝነት ለመናገር ይቻላል። ምክንያቱም ቀላል ነው። ምርጫ ተካሄደ ቢባልም በመሰረቱ፣ 1ኛ) የኃይል አሰላለፍ ለውጥ አልተካሄደም፤2ኛ) የየመንግስታቱ የመጨቆኛ መሳሪያዎች እልተወገዱም፤ የመንግስቱ መኪና ዲሞክራሲያዊ ይዘት እንዲኖረው በማድረግና በማደስ የህዝብን ጥያቄ መላሽ ሊሆን አልቻለም። 3ኛ) በሁለቱም አገሮች ሰፋ ያለ ህዝቡን የሚያሳትፍ ዲሞክራሲያዊ የኢንስቲቱሽን ሪፎርም አለተደረገም፤ 4ኛ)ሁለቱም መንግስታት የሚመሩበት የኢኮኖሚ ፖሊሲ አዲስ ሀብት የሚፈጥርና፣ ህዝቡን ወደስራ አሰማርቶ የተስተካከለና የተረጋጋ ኑሮ እንዲኖር የሚያደርጉት አይደሉም። 5ኛ) ሁለቱም መንግስታት አሁንም የውጭ ኃይሎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በውስጥ ፖሊሲዎቻቸው ጣልቃ ይገቡባቸዋል። ስለዚህም በሁለቱም አገሮች ያለው የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የባህላዊ፣ የህሊናና የሚሊታሪ ቀውስ ለረዥም ዐመታት እንዳለ ይቆያል፤ ወይም ደግሞ እየተባባሰበት ይሄዳል።

ወደ ስሜን አፍሪካው የጥቢው አብዮት ተካሄደባቸው በሚባሉት ወደቱኔዚያ፣ ሊቢያና ግብፅ ስንመጣ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሁኔታን እንመለከታለን። ከአብዮታዊ ለውጥ ይልቅ የእስላም አክራሪዎች፣ በተለይም ሳላፊስቶች የበላይነትን የሚይዙበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው። ስሞኑን በግብፅ የሚደረገው የጥንት ፒራሚዶች ይውደሙ የሚለው

አደገኛ ቅስቀሳ በተለይም ለክርስቲያኑ የኮፕቲክ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላው የግብፅ ህዝብ አስደንጋጭ ሁኔታን ፈጥሯል። በስልጣን ላይ ያሉት አገዛዞች ኢኮኖሚውን በአዲስ መልክ አደራጅቶ የስራ መስክ ፈላጊውን ወደ ስራ ከማሰማራት ይልቅ ካልጠበቁት አክራሪ ሁኔታ ጋር እንዲጋፈጡ ተገደዋል። አዲስ ሀብትና የስራ መስክ ለመፍጠር ያለመቻላቸውን ወደጎን ትተን፣ ወደ ነፃነት ጥያቄ ስንመጣ ከፕሬዚደንቶች ለውጥ በኋላ የሶስቱም አገር ህዝቦች ነፃነቶቻቸው በረቀቀ መልክ እየታፈነ የመጣበትን ሁኔታ እንመለከታለን። በተለይም ወጣቱና ሴቶች በአዲስ የእስላም እንቅስቃሴ መብታቸው እየተገፈፈ ነው። የፈለጉትን ልብስ እንዳይለብሱና አጋጊጠው እንዳይሄዱ የሚከለከሉበት ሁኔታ ሁሉ እየተዘጋጀ ነው። ሌሎች ሌሎች ነገሮችም፣ የምዕራቡን ሙዚቃ መስማትና ፊልም ማየት የሚከለከሉበት ሁኔታም ሩቁ አይሆንም። ይህ የሚያሳየን ምንድነው? አንድ ህዝብ ለነፃነት በሚያደርገው ትግል አንድ ድል ተቀዳጀሁ ካለ በኋላ ውስጥ ለውስጥ በተደራጁ ኃይሎች፣ ወይም ደግሞ በውጭ ኃይሎች ድጋፍ የራሳቸውን አጀንዳ ተግባራዊ የሚያደርጉ ስልጣንን በመንጠቅ የእንድን ህዝብ የነፃነትና የስልጣኔ ፍላጎት ዝብርቅርቁን እንደሚያወጡትና፣ እንደገና ደግሞ ወደ ሌላ ስቃይ ውስጥ በመክተት በድንቁርናና በድህነት ዓለም ውስጥ እንዲኖር እንደሚያደርጉት ነው።

ከዚህ ስንነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመኘው፣ የሚያልመውና የሚጠይቀው ጥያቄ ግልጽ ነው። የዛሬው የወያኔ አገዛዝ በአንዳች ነገር ቢወድቅ ምኞቴን የሚያሟላልኝ፣ ህልሜን ዕውን የሚያደርግልኝ፣ ነፃነቴን የሚያስከብርልኝና፣ ተከብሬና ተዝናንቼ በአገሬ ውስጥ ለመኖር የሚያስችለኝ የተደራጀ ኃይል አለ ወይ? ካለስ እንዴትና በምንስ ዘዴ ነው ስር የሰደደውን የተወሳሰበ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የጎሳ ችግር፣ የሃይማኖት ጥያቄ፣የሴቶችና የወጣቱን ጥያቄ፣ የባህልና ሌሎችንም መፍታት የሚችለው? እያለ ነው። ወደ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ከመግባታችን በፊት፣ የአገራችን ሁኔታ ምን ይመስላል? የሚለውን እንዳስስ። ይቀጥላል…

ECADF

Advertisements

Posted on November 19, 2012, in News. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s