የኢሳት አድማጮች አስተያየት

የኢሳት አድማጮች አስተያየት

ከሥርጉተ ሥላሴ 24-11-2-12

ፍለጋ ገባሁ። እርአስ መረጣ … ግን አጣሁ። ስለዚህ ያው ልጠይቀው አሰብኩት አቅም ስላለኝ።  በምልክት እንግባባ ይሆን ብዬም ተግ አልኩ።  ከዘራውን ዘወር አድርጊ ፊቱን ዬ ና – ን ግልባጭ አደባባይ ላይ – ሰገነቱ ላይ – ቀዩን ጃኖ አዘናክቼለት „በላ ልበልኃ“ አልኩታ እኔ ሞኝ።

አዎን ትናንት ማምሻ ላይ ከኢሰአት የአድምጮች ክፈለ ጊዜ የተሰጡትን በሙሉ አዳማጥኳቸው። ያው ትችቱንም የሰማዕት ህጻናትንም ድምጽ የወከለ ለዛውም በሥነ -ግጥም … ተመላለስኩበት። ያቺው ይህቺን ሰባራያን እስኪ … እስኪ … ተዚህ ላይ ይደገም እያልኩ አጣጥምኩት። ያው ሃዘን ሲበዛ ማጣጣም … መራራውን እንደ ጣፋጭ … ዶሮ ማታ ብዬ አሳንጋለውን ዘመን … አዳመጥኩት።

አንድ ሁለት የሚሆኑ አምልኮዊ ፍቅረ ወያኔ የተጠናወታቸው „መጥታችሁ ከዚህ እውነት ካለበት ቦታ ለምን አትዘግቡም? የምተወሩት ያልሆነውን ነው“ የሚልም አዳመጥኩ። እስቲ ሌላው ሁሉ ቀርቶ „ጠቅላይ ሚኒስተሩ ከህማቸው አገግመዋል። በቂ እረፍት ስለሚያስፈልጋቸው ነው እንጂ  እስከ አዲሱ ዓመት ድረስ ሥራቸውን ይጀምራሉ“  ያሉት አቶ በረከት ስሞዖን፤ በረከት ገ/ሕይውት  በአባታቸው መጠራት ስላባቸው … ምላሳቸው ለእህል ለውሃ ሳይደረስ „አለፉ – ሞቱ – ተሰነባቱ“ ሲሉ የት ነበሩ? … ሌላው ሁሉ ይረሳላቸውና … አንድ ትልቅ የመንግሥት ባላሥልጣን በአንድ ሞት እንኳን ስንት ጊዜ ሲቀላመዱ ተሰሙ። እንዲያውም የረገጡት ህዝብ ምን ያህል ጨዋ እንደሆነ ቢያገናዝቡት መልካም ነው። እንጂ ውሸታም! ውሸታም! ውሸታም እያለ ቢና ጢናቸውን አውጥቶ በአደባባይ  ቀልባቸውን በገፈፈው ነበር …

ሌላው ደግሞ ፈሪዎች … ናችሁ እንጂ … እንኳንስ ቴሌቢዥን እስክርቢቶ ፈርታችሁ አይደል እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን፤ እነ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን ያሰራችሁ። መታሰር ብቻ ሳይሆን ድርብ ግፍ እዬተፈጸመባቸው ያለው። „ፍትህና ፍኖተስ“  ስለምን ከህትምት ታገዱ“ ፍትህ“ ስለምን ተቃጠላች… የውሸትም ዓይነት አለው፤ የቅጥፈትም ዓይነት አለው … የትችትም ወግ አለው … ጥጋባቸው በዛ። — እንዲያው እኮ የወያኔና የደጋፊዎቹ  አሰራማ ገፈቱ ምንም እኮ የይሉኝታ ላሂ የሚባል የሌለው መሃን ነው። በጣም ….. የሽብርተኛ ህጉስ … ? እንዲያው ተምን ላይ ይመድብላቸው …

አሁን ወደ ተነሳሁበት። እንዴት ነው ሚዲያና የፖለቲካ ድርጀት ወይንም ንቅናቄ ድብልቅ ያለበት ይመስለኛል ወገናችን። „ኢሰአት ድረስልን በተሎ !“ የሚል ብሄራዊ ጥሪ ጎልቶ አዳምጫለሁ። „ካለ እናንተ ማንም የለንም።“ የሚልም።  ሚዲያ አንደበት ነው። ሚዲያ ዜና ነው። ሚዲያ ወቅታዊ መረጃ ነው። ሚዲያ እውነትን ለባለቤቱ ያስረክባል። ሳይጨምር ሳይቀንስ እንጂ ተዋጊ የፓርቲ ሰራዊት ሊሆን አይችልም። ይህ ከሆነ ሚዲያው ነፃ መሆኑ ቀርቶ ልክ እንደ ኢትቪ የወያኔ ቧ ያለ የቅጥፈት አፍ ነው የሚሆነው።

? ? ? እስኪ ፍቷት የተከበራችሁ የኢሰአት አድምጮች። ስለ መራባችሁም፤ ስለ መታረዛችሁም፤ ስለ መጨቆናችሁም፤ ስለ መታፈናችሁም፤ ስለ መገደላችሁም፤ ፈጽሞ በማይቻልበት ሁኔታ ከቦታው እዬተገኘ ኢሰአት መረጃውን ማዕከላዊ በሆነ መልኩ በወገናዊነት ኃላፊነቱን እዬተወጣ ነው …. የቀረው ነገር … ? ? ?  ናት ወደ ራሳችሁ መመለስ። ራሳችሁን በማዬት – መጠዬቅ።

? ? ?  የተራበ፤ የታረዘ፤ የተጠማ፤ የተገፋ፤ የተረገጠ፤ የታሰረ፤ ጉሮሮው የተዘጋ፤ ሥራ አጣ፤ ቤቱ የፈረሰበት፤ ከኑሮ የተፈናቀለ፤ ህጻናት ልጁን ከ አንቀልባ ላይ የተገደለበት፤ አባወራውን የተቀማ፤ ጉልቻው የፈረሰበት፤ ልጆቹ ከትምህርት የተፈናቀሉበት፤ መሬቱን ተቀምቶ እሱ ባይታዋር ሆኖ ለውጪ ሀገር የተሰጠበት፤ አንጡራ እትብቱ ለባእድ በስጦታ የተሰጠበት፤  ክልሉ የተጣሰበት፤ በፍርድ አድሎ የተፈጸመበት፤ ማንነቱ የተቀጠቀጠበት፤ በትርፍነት የሚገኝ ዜጋ የወያኔ የፊት ለፊት ረድፈኛ ተጠቂ  ? ? ?  ውጪ ያለው ሚዲያ ወይንስ ? ? ? የማከብራችሁ ሀገር ቤት ያለችሁ ወገኖች ተቀራረቡ … ከውስጥ ረመጣችሁ ጋር ? ? ?

ራህብን የሚያወቅው የተራበው ነው። እርግጥ ውጪ ያለው አይሰማውም ማለት አይደለም። ግን ማን እንደ ባለቤቱ። ውጪ ያለው ተራቡ ከሚልና እናንተ ተራብን ብላችሁ በጋራ ብትጮኹ ማነው የሚደመጠው ? ? ? በመዳህኒትዓለም ፊትም ሆነ እንዲሁም ብድርና እርዳታ በገፍ አያጎረፉ ወያኔን ጉልበታም ያደረጉት ኃያላን  ሁሉ የቀረቀሩትን ጆራቸውን ይከፍታሉ። ውጪ ያለው አብሶ አውሮፓ፤ አሜሪካ፤ አውስትራልያ፤ እንዲሁም ኒዊዝላንድ ያለው ወገን በልቶ ያድራል፤ መጠጊያም አለው፤ ነፃነትም አለው። የ እኔ ጌጦች … ውጪ ያለው ጩኽት ተጫማሪ እንጂ ወሳኝ ሚና ሊጫወት የሚቸለው የውስጡ ግፊት ነው። ፍውሰት የሚገኘው የታመመው በሽታውን ሲናገር ብቻ ነው። አፍናችሁ – እቅፍ ድግፍ አድርጋችሁ –  አሽኮኮ አድርጋችሁ ያዛችሁት እኮ የከረፋውን ግፍ … እና እናንተ  እስከ መቼ ? ? ?

የባዛው እሳት ከእራሳችሁ ላይ ነዶ ከእናንተው ዓናት ላይ ነው አመድ የሚሆነው …። በሁሉም ነገር እዬተንገበገባችሁ ያላችሁት እዬተቀጣችሁ ያለችሁት እናንተ ናችሁ። አይደለምን ? ? ? ። ስለሆነም በቃ! ማለት ያለባችሁ እናንተው ናችሁ። ብዙ ናችሁ። ዕልፍ ናችሁ። ዕልፍነታችሁን በተግባር ዕልፍ አድርጉትና ውጤቱን ለኩት። እርግጥ አላስፈላጊ መስዋዕተነት ክፈሉ ማለቴ አይደለም። ግን ለማናቸውም ነገር መንሹ ያለ ከእናንተ እንጂ ከኢሰአት አይመስለኝም።

…. እጅግ የምታናፍቁኝ፤ የምሳሳላችሁም ወገኖቼ እራሳችሁን ጠይቁ። ቁረጡ። ተመካከሩ። ከኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ተከታዮችም የተግባር ምርት ለመማር ተሰናዱ። በተቃዋሚ ፓርቲ የተደራጃችሁትም ምሩን … ለድል አብቁን ብላችሁ አፋጣችሁ ያዟቸው – መሪዎቻችሁን። እናንተም ቢሆን ግዴታችሁን በብቃት ተወጡ —  እነሱን ለመጠዬቅ በቂ መብት እንዲኖራችሁ።

ገፍተው የታገሉት እኮ ብቻቸውን ታሰሩ። አሁን ጋዜጠኛ እስክንድር ስንት ጊዜ ታሰረ? አቶ አንዱአለምስ? 21 ዓመት ሙሉ ተቃዋሚ ነን ብለው ለዘዝ ብለው ስለታገሉ — ለወያኔ የንግድ ፍጆታ ኮረጆውን በመሙላት ብቻ ቀዮዋን በር የማያውቋትም አሉ። ለማንኛውም ተጠ ያዬቁ  – ከፍላጎታችሁ ጋር። ተጠያዬቁ – ከራዕዮቻችሁ ጋር። ተጠያዬቁ – ከነፃነት ምኞታችሁ ጋር። ወያኔ ሚሊዎኖችን ማሰር ስላማይቻል በአንድነት ብትንቀሳቀሱ „ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ነው።“

ሰው ለራሱ ጉሮሮ እራሱ ብቻ ነው። ሲርባችሁ እንጀራን ሁል ጊዜ እራሳችሁ ነው በወጥ አጣቅሳችሁ የምትጎርሱት። የነፃነት ራህብ ከሁሉ የሚልቅ ነው። በቤታችሁ ውስጥ እንኳን ያለውን ነፃነት የምታውቁት እናንተ እንጂ እኔ ወይንም ሌላው አይደለም። ነፃነት – በነፃ ወይንም በርካሽ ዋጋ አይገኝም። የታሰሩትም እንደ እናንተ ትዳር፤ ኑሮ፤ ንጹሕ አዬር እንደ ሰው ያስፈልጋቸዋል። ለእነሱ የወር ማህያቸው በቂ ባይሆንም የጉሮሮ ማርጠቢያ ይሆናል። ግን ለማን ? ? ?  ስትሉ ከመልሱ ጋር ትታረቃላችሁ። ከሰማይ የሚገኝ መና የለም። ካለምንም ጥገኝነት። ወንድ ሴት፤ ሽማግሌ፤ አዛውንት ሳትሉ ከከፋችሁ ቀን ጋር ለመፈታት ድፈሩ።  በቃህን፤  አሁንማ አበዛኽው በሉት – ጎጠኛውን ሙጃ።

ትጠበቃላችሁ! …  ሶስቱ ሚስጢራት ተቆላልፈው — ተያይዘው — ተስማምተው እናንተኑ ይጠብቃሉ።  …  እንዚሁላችሁ አንድነት – በፍቅር፤ ቁርጠኝነት – በፍቅር፤ ድፍረት – በማስተዋል!  ቁልፉን —- ለመፋትት ተሰናዳችሁን  ? ? ?

እግዚአብሄር አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ። ህዝቧንም በበረከት ያጥግብ!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ECADF.COM

Advertisements

Posted on November 25, 2012, in News, Politics and tagged , , , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s