የስርአት ለውጥ መፈለግ ቅፅበታዊ ውሳኔ አይደለም!

የአለምገነት አላምረው

የወታደራዊው ስርአት ከተወገደ በሁዋላ የህዝብን ስልጣን በጠመንጃ አስፈራርቶና ዋሽቶ የወሰደው ውጥንቅጡ የጠፋበት ወያኔ መንግስት 21ኛ የጭቆናና የብዝበዛ አመቱን ወደፍፁም አምባገነንነት ተሸጋግሮ አከበረ ፡፡ የአቶ መለስ አገዛዝ የኢትዮጵያውያንን ህዝብ ትግል ውጤት( እነሱ የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው የታገለው ቢሉም) ተጠቅሞ ስልጣን ከጨበጠ ጊዜ ጀምሮ ከዕለት ዕለት ወደ ፍፁማዊ አንባገነንት በመሽጋገር ላይ ይገኛል:: የመንግስት ስልጣን በቤተሰብ በጎጥ በብሔር የተያዘበት ብዙ የአቶ መለስ ወገኖችና ጥቂት ለሆዳቸው ያደሩ የሌሎች ብሄር ተወላጆች የግዙፍ ሀብት ባለቤት ሆነዋል:: በተቃራኔው ደግሞ ከሞላ ጎደል በሙሉ በሜያስብል ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብ በቀን ሶስት ግዜ መብላት አቅቶታል በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩት ደግሞ በያመቱ በከፋ እርሃብ እየተጠቃ ይገኛል::

የህዝብን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን፧የመናገር:የመፃፍ:የመሰብሰብ:በቡድን የመደራጀት:ሀሳብን በአደባባይ ወጥቶ የምግለፅ: በሀገሩ ላይ የመሬት ባለቤት መሆን ያለገደብ መንቀሳቀስ: የፈለገውን እምነት መከተል በሙሉ ተገድበዋል:: የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን: አባላቶችን: ደጋፊዎችን: ምሁሮችን: መምህራኖችን: ጋዜጠኞችን: ዘፋኞችን: ነፃ አሳቢ ዜጎችንና በተለያዩ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ማስፈራራት:በእስር ማሰቃየት: በአካላቸውና በስነልቦናቸው ላይ ጉዳት ማድረስ:ንብረታቸውን መውረስ መዝረፍ ማውደም ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በሰፊው ጨምረዋል::

በሰባዊ መብት:በመልካም አስተዳደር:በህግ የበላይነትና ላይ ግንዛቤ እንዳያገኝና እንዳይኖረው ለማድረግ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች: ነፃ ጋዜጦች: የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ለስልጣኔ ያሰጉኛል በማለት ለህዝቡ እንዳይደርሱ አድርጎዋል:: በብሄርና በጎጥ የተደራጁ ወንበዴ ዘራፊ ድርጅት ማቋቋምና ህዝቡንና ሀገሪቱን ዘርፈዋል:አስርበዋል: የበዪ ተመልካች አድርገውታል:: የብዙ ቤቶች ባለቤት መሆን: ዘመናዊ መኪናዎችን መቀያየር: በመቶ ሚሊዮኖች የሚጨርስ ህንፃና ፋብሪካዎች መገንባት ለወያኔ ብቻ የተፈቀደ እስኪመስል ድረስ አግበስብሰዋል:: ከፍተኛ ሀብት ከኢትዮጵያ ማሸሽና በተለያዩ የውጭ ሀገር ባንኮች መደበቅ ይህም ሳያንስ በባእዳን ሀገር በቢሊየን የሚቆጥሩ ዶላሮችን አውጥቶ ህንፃዎች ገንብተዋል::

የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመረጃ ተቃማትን የግል ጋዜጣዎችን ራዲዮዎች ቴሌቪዥን እና ድህረ ገዕች መረጃዎችን ለህዝቡ እንዳያደርሱ ለማድረግ አታሚ ድርጅቶችን መዝጋት: ፈቃድ መከልከል: ባለቤቶቹን ማስፈራራት: ማሰር: ከሀገር እንዲሰደዱ ማድረግ:: በራዲዮና የቴሌቢጅን የሚሰራጩትን መረጃዎች ከፍተኛ ገንዘብ በማውጥት ሞገዳቸውን ማፈን::

አነዚህ ሁሉ የአምባገነንነት መገለጫዎች ከዐመት ዐመት በመጠናቸውም በይዘታቸውም እጅግ እየጨመሩ ይገኛሉ በቅርቡ በሰሜን አፍሪካ ያየናቸው የህዝብ አመፆች መነሻዎቹ ልክ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ በህዝብ ላይ እየተፈፅሙ ያሉ ከላይ የተዘረዘሩት የህግ የበላይነት አለመስፈን የመልካም አስተዳደር ማጣት በቤተሰብና በዘር የተደራጀ ሙስና ዋነኞቹ ናቸው::

ከስህተታቸው መማር ያልፈለጉት የወያኔ መሪዎች የህዝብን የለውጥ ፍላጎት ለማፈን በተለያዩ መንገዶች እየሞከሩ ይገኛሉ:: በብሄርና በቤተሰብ ተደራጅቶ የህዝብን የለውጥ ፍላጎት ለማስቆም መሞከር አምባገነንነትንና ጭቆናን ከማሳደግ በስተቀር የሚያመጣው ምንም ፋይዳ የለውም:: ምክንያቱም የለውጥ ፍላጎት በቅዕበት የሚመጣ ውሳኔ አይደለም እንደውም የለውጥ ፍላጎት የብዙ ክስተቶች ድምር ውጤት ነው:: ወደዚ ውሳኔ ለመድረስ ብዙ ውጣውረዶችን ያልፋል አማራጮችን ይመለከታል ደካማና ጠንካራ ባህሪያትን ያጠናል ከዛ ወደ ውሳኔ ይመጣል :: አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ የወሰነው” ለውጥ” ነው ስለዚህ ወያኔዎች ብዙ አትድከሙ ለውጥ የማይቀር ነገር ነው::

Posted on November 26, 2012, in Politics and tagged , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s