እስከ መቼ ድርስ ሥርዓት አልባነት

አያና ከበደ ክኖርዌይ /ayanakebede@hotmail.com

 

አያና ከበደ ክኖርዌይ

ሥርዓት ማለት ለሰው ልጅም ሆነ ለአንድ ሀገር የሰላም መመሪያ ነው፡፡ በመሆኑም የሰው ልጆች ከሌሎች ሥነ-ፍጥረታቶች የምንለይበት ለሰው ልጆች ብቻ የተሰጠን ተፈጥሮአዊ ጸጋ ነው።
ሥርዓት የሚገነባው የሰው ልጆች ለራሳችው ጥቅም አድርባይ ሳይሆኑ ለሀገርና ለወገን እንደራሳችው አድረገው ማሰብና መስራትን ይጠይቃል፡ በሀገራችን ኢትዮዽያ ለ፪፩ ዓመታት ተንሰራቶ የኖረው የወያኔ መንግስት ሥርዓትን እንደ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ነው የሚጠቀምበት። በሥነ _መግባር የተገነባ ሥርዓት የመልካም አሥተዳደር መሰርት መሆኑን ስለሚያውቁ የወያኔ ጭፍራዎች የዚህ አይነት ቢያለፍ አይነካቸውም።ቢከተላችውም ወርውረው ይጥሉታል ብል የተሳሳትኩ አይመሥለኝም የነሱ ዋናው ዓላማቸው በዘርና በጎሳ በመከፋፈል ሥርዓት አልባ የሆነውን አገዛዛችውን ማራመድ ነው፡ የፈጸሙት ግፍና በደል በህግ ስለሚያስጠይቃቸው በሰላም ለቀው ይወጣሉ ብሎ ማሰብ የማይሞከር ነው፡ ሰላምና ዲሞክራሲን ለማምጣት የሚሰሩትን ቴረሪሥት ናችው በማለት የተቃውሞ ድምጽ እንዳያሰሙ በማዳክም የራሳቸውን ዓላማ በማራመድ ላይ ይገናኛሉ። በየመስሪያቤቱ ዋና ዋና ቦታ ላይ የሚያስቀምጧቸው በትምህርት ደርጃቸው ለቦታው ብቃት የሌላቸው፣ ከነሱ ቤተሰብ ውስጥ፡ የወጡትን ጆሮ ጠቢወች ለቃል አቀባይነት የሚጠቀሙባቸው፣ ወገንታዊ ካድሪዎች ለሰው ልጅ ርሕራሔ የሌላቸው ጋጠወጦች የሥነ-ምግባር ምንነትን ያልትረዱ የበላይነታቸውን የሚያንጸባርቁ ፀኃይ ላይ እንደ ዋለ መረዋ ገና ሳይነኳቸው የሚጮኹ ናቸው።
ለዚህም ነው መሥማት የተሳናቸው አቶ ስበኅት ነጋ የአቶ መለሥን ሞት ሲያሥተባብሉ የነበሩት መረሳት የሌለበት ነግር ቢኖር ለኣቶ ስብኅት መዋሽት ነውር ኣይደልም ከመጀመሪያ ድግሪቸው እስከ ማስተራቸው የሰሩበት ነው ብል ማንም የሚቃወመኝ ያለ አይመስለኝም።

 

በኢትዮዽያ የዘመን አቆጣጠር ፪፻፬ ዓ.ም መጨረሻ ለይ በሃገራችን የተፈጠረው የድንገተኛ የሁለት ሰዎች (አምባገነኖች) ከዚህ ዓለም በሞት መለየት፣ ለመላው የኢትዮዽያ ሕዝብ የሰላም ጎህ ይቀዳል ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት ላይ ነበር አቶ ሥብሐት የተለመደውን የውሸት ቅኔአቸውን ዘረፍ ዘረፍ ያደረጉት የሞተን ሰው በረፍት ላይ ነው(ናቸው) ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ በማለት የተለመደውን ውሽታቸውን በቮይስ ኦፍ አሜሪካ አሥተላልፈዋል።

በበላይነት የራሣቸውን ጥቅም አሥከብረው፣ በአገር ውስጥ ያሉ አርሶ አደሮችና አርብቶ ኣደሮች በቂ መሬት ሳያገኙ ለውጭ ባለ ሀብቶት መሬቱን በመሸጥ አርሶ ኣደሩን በችጋር ኣረንቛ እንዲማቅቅ በማድረግ አፋናና ጭቆናቸውን በማስፋፋት ላይ ይገኛሉ።

በዚህ ጊዜ ነበር እኔ ካለሁበት የባነንኩት በነደዚህ ዓይነት ወራዶች ነው ኢትዮዽያን ያክል ታላቅ ሀገር የምትመራው በማለት ራሴን ጥያቄ ውስጥ አሥገባሁ። ሀገራችን ለ፪፩ ዓመታት ረግጠውና የህዝብን መብት አፍነው ብዝበዛና ምዝበራን በማካሔድ፡የተለመደውን የውሸት፣ ፕሮፓጋንዳቸውን በተግባር ለማዋል፡ስረዓትን በመጣስ ሌት ከቀን ሲባዝኑ፡ ይታያሉ፡፡

ወደፊት ኢትዮዽያ ምን ምን ያሥፈልጋታል ብለን ለመስራት እራሣችንን እናዘጋጅ። በመጀመሪያ ይህንን ልክሥክሥ ሥርዓት ካለበት ማጥፋት አለብን እነዚህን ማንዘራሽ የኢትዮዽያንነት ፀባይ የሌላቸው ከምድር ገጽ ማጥፋትና በሰላምና በዲሞክራሲ የሚያምን መንግስት ለመመሥረት ሁላችንም የምንችለውን አሥተዋፆ ማድረግ አለብን ድር ቢያብር አንበሣ ያሥር ይባልየለእንዴ::
ኢትዮዽያውያን ስንባል የራሳችንን የማንሰጥ የሰው የማንፈልግ ኩሩዎች፥ በመልከ ፀይም መካከለኛ ቁመት ያለን የራሳችን የሆነ ባህልና ወግ እንዲሁም የራሳችን ፊደል፣የቀንና የዘመን አቆጣጣር ያለን ከሌሎች የዓለም አገሮች የተለየ ትልቅ ታሪክም ያላት ሀገር ያለን ነን ይኸውም የሰው ዘር ለመጀመሪያ የተገኘባት ብቸኛ ሀገር መሆኗን በታሪክ ተዘግቦ እናገኛለን።

በዘመነ ወያኔ ማለትም በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ኢትዮዽያ የምትታወቀው ጭቆናና ኣፈና የበዛባት የሰብአዊ መብት የሌለባት በዓለም ካሉ አግሮች ለብዙ ዓመታቶች በጭቅና ስር ያለችና የሕዝቦቿም የመሰደድ ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን አየጨመረ ያለና በሀገር ውሥጥ ያሉ ጋዜጤኞች ተለቅመው ወደ እሥርቤት በመጣል ላይ ይገኛሉ የነጻሚዲያዎች የመናገርም ሆነ የመጠየቅ መብት የላቸውም። ከጭቆና የተነሳ በመዘጋት ላይ ይገኛሉ የሚዲያ ባለቤቶችም ሥቃይ ስለበዛባቸው አገር ለቀው በየባእድ አገሩ በመንከራተት ይገኛሉ የወያየኔ ዓላማ ምን ይመስላችኋ? መልሱን ለናንተ ልተወው ፟…..?
የወያኔን የወደፊት ሥልት እንዳይቀጥል የኛን ጥረት ይጠይቃል ባንዲራን በመብታቸው ሢቀይሩ እጃችንን አጣምረን መብታችንን ያስወሰድነው እንደፈለጉት ኣደረጉ ነገሩ ያን ጊዜ ነበር በሕብረት መነሣት የነበርብን ላለፈው ክረምት ቤት አይሰራም ለወደፊቱ ግን እምቢ መብቴን አልሰጥም በማለት እንተናነቃቸው እንደ አበበ ገላው ያለንን ኃይል ልንጠቀምበት ይገባናል፡፡

መቼም ቢሆን እነሱ መልካምን ለማሰብም ሆነ ለመሥራት የራቁ መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም፡ ሆን ብለው ታሪክን ለማጥፋትና ጥሩ ሥራን ከመሥራትም መጥፎ ነገርን ለመስራት የተካኑ የጉጅሌጥርቅሞች መሆናቸውን መርሳት የልብንም ከነሱ ሰላምን ማሰብ ከእባብ እንቁላል ዕረግብ መመኘት ማለት ነው፡፡ ድሮ ልጅ እያለሁ አንድ ተርት ሲተረት እሰማ ነበር እረኛ ይቀሳል ድንበር ይፈርሳል ገዳም ይታረሳል የሚል ነበር ግዜው ደረሰልበል? ለነገሩ ድርጊቶቻቸውን ሥንመለከተው ምንም ከረኞች ተግባር አይለይም የሚመሰሩት ለሀገር ሳይሆን የራስን ህልውና ለማሥጠበቅና የራሣቸውን ሆድ ለመሙላት የዘረኛና የአምባገነን ፍላጎታቸውን ለማሳካት የሀገርንና የህዝብን ነጻነትና አንድነት እንዳይኖር ጣልቃ በመግባትና በዘርና በጎሳ በመከፋፈል የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ታጥቀው የተነሱ ናቸው፡፡ ዓላማቸው ግቡን እየመታላቸው ይታያል ዳር ድንበሩ ተደፈረ ብለን ዋይ ዋይ ሥንል ምንም መፍሄ ሣናመጣ ከነካቴው ብለው ለቻይናና ለህንድ ሀብታም ገበሬዎች መሃል አገሩን ቆርሰው ሸጡላችው የኢትዮዽያን ታሪክ ለማጥፋት ዓላማቸውን ከግቡ ለማድረስ ገዳሞችን በማፈራረስ መናኔ መነኮሳት ከገዳሙ በማባረር እንዲሰደቱ ተገደዋል በዚህም ምክንያት በመላው ኣውሮፓ በሥቃይ ላይ የሚገኙ መናኔ መነኮሳት የትየለሌ ናቸው። ጥፋቱን ዕንደ ልማት በማጧጧፍላይ ይገኛሉ።
ውድ የኢትዮዽያ ልጆች ሀገራችን በአሁኑ ጊዜ ያለችበትን አሳዛኝ ሁኔታ ለናንተ ለማሥረዳት ስሞክር ከናንተ የተሻለ ግንዛቤ ኖሮኝ ሳይሆን የበኩሌን ለነዚህ ቆርጦ ቀጥሎች በተደጋጋሚ የማየውን የነሱን ውሽት ይፋ ይውጣ ብየ የማውቀውን ውሸት እንዳትሰሙ አውነትን ለማምጣት ተባብሮ መሥራት ግድይላናል።
አንድ ባለሥልጣን ሰውነት አልባ መሆን ሲጀምር የሚታወቅባቸው ምልክቶች አሉ የመጀመሪያው ምልክት ስልጣንን መከታ በማድረግ አራሱን መካብ የበላይነት ስሜት ማሳየት ለስልጣን ያበቁትን የሕብረተሰቡን ክፍሎች የበታች አድርጎ መመልከት የመሳሰሉት ናቸው ለዚም እንደ ጥሩ ምሳሌ ሊጠቀሱ የሚችሉ መስማት የተሳናቸዉ አቶ ሥብኃት ነጋ እና አቶ በረከት ስምኦን ናቸው።
ለዚህም ነው አቶ በረከት ለ፪፩ ዓመታት ውሸትን በማውራት ታዋቂነትን ያገኙት እውነትን ከተናገሩ ከሥልጣን ይወርዳሉ የተባሉ ይመስል እድሜልካቸውን ውሸት ያውራሉ፡ ይህ የሥነ ምግባር ጉድለታቸው በራስ መተማመንን ሥላሳጣቸው ሁልጊዜ እንደበረገጉ ይኖራሉ አሁንም ከሰሜንና ከደቡብ ለይሥሙላ ብለው ያመጡ አቸውን ኤክስ ጠቅላይ ሚንስተር መጽሓፍ ቅዱስ ዕንደጨበጡት ያንን የውሽት ክህነት በመኃላ አድርገው እንደሚክኗቸው አልጠራጠርም።

እንደህ ነው ክረስቲያን ከገዳዮቼ ጋራ አብሮ የገደለ በድሮ ጊዜ የሀገራችን ክርስቲያኖች አገር ወዳድና በጣም ቆራጦች ነበሩ የጣሊያንን ፋሽሽት ለማሥወጣት ያደረጉትን ማስታወሥ ይቻላል ታቦተፅላቱ ሳይቀር ወደጦር ሜዳ ይዘው የሄዱበት ወቅት እንደነበር ከታሪክ መረዳት ይቻላል ይህን ሥል የሀገራችን ሙሥሊሞችም ማንም ለባንዳ እጅ የሰጠ የለም ነበር ታርኩን ለማንሳት ክርስቲያኖች አልኩ ዕንጅ ሁሉም ኢትዮዽያውያን እጅለጅ ተያይዘው ነበር ዳር ድንበሩን ሳይንካ ይዘው የጠበቁን።

እነዚህ የባንዳ ዝርዮች ዳሯን አስደፈሩት ወደብም አልባ አደርጓት ኢትዮዽያ በማንም ቀኝግዛት ያልተገዛች ሀገር መሆኑን የዓለም ሂስትሪ ያሥረዳል። በአሁኑ ጊዜ ግን የገጠማትን የውስጥ ረገጣ ከቅኝ ግዛትም የከፋ ነው። መቸም ውሸት አይገዳቸው አስራ አንድ በመቶ ዕደገት አሳይተናል በማለት ሁልጊዜ ውሸትን ያስተጋቡልናል፣ ዕድገትማ ቢኖርማ ስንቶቸ እህቶቻችን በየአብ ሀግርሩ እንደወጡ ባልቀሩ ነበረ እኔ እንደሚመስለኝ እድገት የሚሉት በዘረፋ ያጠራቀሙትንና የነሱን ኑሮ ከሕዝብ ጋር በማነጻጸር ወይም ከጫካ ወደ ቤተመንግስት መግባታቸውን እንደ እድገት ቆጥረውት ከሆነ በርግጥም ለነሱ ትልቅ እድገት ነው ሥንቅ እየቀማ ሱቅ እየዘረፈ ላደገ ሌባ ይህንን ሲያገኝ በእድገት ላይ እድገት ማለት ይችላሉ።

ፕሮፌሰሮች ወደ ስደት እረኞች ወደ ቤተ መንግስት መግባቱ እድገት ከተባለ በቀኝ እየሰሙ በግራ መጣል ነው አንጅ ሌላምን መፍቱሄ ይኖራል፡ እሪበል ጎንደር አለ ያአገሬሰው ታድጎ ተሙቷል።

አንዱ እንዲህ ሲል ጓድኛውን ያጫውተዋል ስማ አንተ፣

አቤት፣
እኛኮ የኢትዮዽያ ተምሣሌት ነን፣
እንዴት፣ እንዴት ኾነን፣
ተመልከት እያንዳዱ ቅንጣት ዕንጨት ተባብሮ ችቦን ፈጠረ፡፡
አያንዳንዱ ችቦ ተባብሮ ደግሞ ደመራውን ፈጠረ፣
ያለዕንጨት ችቦ፣ያለችቦም ደመራየለም፣

ትርጉሙን ለናንተው ልተወው ?
በአንድነት ከተንሳን የምንሰራው ስራ ሁሉ ውጤት ይኖረዋል የያንዳንዱ ቅንጣት እንጨቶች ተምሳሌት ለመሆን እንሞክር፡፡ መሖንም ግዳታችን ነው ይህ ካልሆነ ወያኔ የሰጠንን የቤት ሥራ ሳናውቀው እየተገበርንለት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡
ኢትዮጵያንና ሕዝቧን እግዚአብሔር ይባርክ!!
ፀኃፊውን ለማግኘት እና አስተያየት ለመስጠት፣ ayanakebede@hotmail

zhabezha

Advertisements

Posted on December 10, 2012, in Human Right, Politics and tagged . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s