ኦህዴድ ውስጥ የማረጋጋትና የማጽዳት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው

ኢሳት ዜና:- የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት አቶ ሙክታር ከድር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ደረጃ ያለውን አመራር የማጠናከር፣ የማረጋጋትና የማጽዳት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ከፍተኛ ችግር በሚታይበት በምስራቅ ኦሮሚያ እና በሀረሪ ክልል የሚገኙ በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ የኦህዴድ አመራሮች ፣ መምህራንና ርእሰ መምህራን፣ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የድርጅት አባላቶች ከህዳር 27 ጀምሮ ስብሰባ ላይ ናቸው። በሀረሪ ክልል በአሚር አብዱላሂ አዳራሽ መጋቢት 28፣ ቀን 2005 ዓም በኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት በአቶ ረጋሳ ከፍያለው ሰብሳቢነት ስብሰባ ተካሂዷል። በመስራቅ ሀረርጌ ደግሞ መካከለኛ አመራር፣ ርእሰ መምህራንና የድርጅት አባላት የሚሳተፉበት ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል።

ከ700 በላይ የሚሆኑ የኦህዴድ አባላት በተሳተፉበት ስበሰባ ዋነኛ የመወያያ ጉዳዮች ሆነው ከቀረቡት መካከል በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠረው ልዩነት፣ የሙስሊሙ እንቅስቃሴና፣ ትምህርት ቤቶች የአንድ ለአምስት አደረጃጃትን ስለሚተገብሩበት ሁኔታ የሚሉት ይገኙበታል።

የኦሮሞ ህዝብ በብሄር ብሄረሰቦች ቀን ማንነቱን ያስከበረ መሆኑን፣ ኦነግ የሚያቀነቅነው ሀሳብ በአንቀጽ 39 የተከበረ መሆኑ፣ እንዲሁም በአመራሩ መካከል የታዩ ክፍተቶች የተዘጉ መሆኑን ሰብሳቢው ገልጸዋል።

ተሰብሳቢዎች በበኩላቸው “ ይህ በቂ አይደለም ፣ ምስራቅ ሀረርጌ በኦሮሚያ ክልል ስር መሆን ሲገባው በሀረሪ ክልል ሆኗል፣ ቋንቋችን ተግባራዊ ይሁን ከተባለ በሁዋላ እስካሁን ተግባራዊ አልሆንም።” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል።

ኦነግ አመለካከት ያላቸው ሰርጎ ገቦች በቂ የስልጣን ቦታ አላገኘንም በማለት የሚያስወሩት ሀሰት መሆኑንና ኦህዴድ የምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ስልጣን ማግኘቱን ሰብሰባዊው ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል በፕሬዝዳንቱ መታመም ምክንያት ያለፕሬዚዳንት ለ2 አመታት መመራቱና ኦህዴድም ራሱን ችሎ ሊቆም አለመቻሉ ጥያቄ ሆኖ ተነስቷል።

ድርጅቱ ራሱን የማጠናከርና የማረጋጋት ስራ እየወሰደ መሆኑን በስብሰባው የተካፈሉ ስማቸው እንዳይገለጥ የጠየቁ የኦህዴድ አባላት ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ዜናም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ለህክምና ተመልሰው ወደ ውጭ መውጣታቸው ታውቋል። ከአንድ አመት በፊት ጀምሮ በህክምና ላይ የሚገኙት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ህክምናቸውን ሳይጨርሱ ፣ ለአቶ መለስ ዜናዊ ቀብር ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ተደርጎ እንደነበር ይታወቃል። ከፍተኛ የሰውነት መጎሳቆል የሚታይባቸው አቶ አለማየሁ ከሀላፊነት እንዲነሱ በመርህ ደረጃ ውሳኔ ላይ ቢደረስም ፣ እርሳቸውን በሚተካቸው ሰው ላይ በካቢኔ አባላቱ መካካል ስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ ቦታው ክፍት እንዲሆን ተደርጓል።

ባለፈው ሳምንት በአዳማ በተካሄደው የምክር ቤት ስብሰባ ላይ ምክትሉ ሲገኙ ዋናው ፕሬዚዳንት አልተገኙም ነበር። የኦህዴድ መካካለኛ አመራሮችን በመሰብሰብ እያወያዩ ያሉትም ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ ረጋሳ ከፍያለው ናቸው። የኦህዴድ አመራር አባላት እንደገለጡት በድርጅቱ ውስጥ የሚታየው መከፋፋል ከፍተኛ ደረጃ በመድረሱ ስራ መስራት በማይቻልበት ደረጃ ተደርሷል።

ኢህአዴግ በድርጅቶቹ መካካል የተፈጠረውን መከፋፈል ለማስቀረት ከኦህዴድ እና ከብአዴንና ከህወሀት የተውጣጡ 3 ምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትሮችን መሾሙ ይታወሳል።

Admas
 
Posts: 40
Joined: 14 Jul 2007, 14:56
Advertisements

Posted on December 12, 2012, in News and tagged , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s