ስለለውጥ፤ ለውጥን መቋቋም እና መፍራት

ስለለውጥ፤ ለውጥን መቋቋም እና መፍራት
አዘጋጅ በፍቃዱ ዘ ኃይሉ ዘርፍ: Sociopolitics

በበፍቃዱ ኃይሉ

ለውጥን በምናብ ይወዱታል እንጂ በተግባር አይዳፈሩትም – ሰዎች፡፡ የሥርዓት ለውጥ ሲሆን ደግሞ ፍርሐቱ ያይላል፡፡ የፖለቲካ ሥርዓት ለውጥ ሲሆን ደግሞ ከማንኛውም ሥርዓት ለውጥ በላይ ያስፈራል፡፡ የፍርሐት ፖለቲካዊ አንድምታ ከታሪክ አንጻር እየተመለከትን ስለራሳችን ለውጥ እንድናወራ ነው ይህ ጽሑፍ የተጻፈው፡፡

የፍርሐት ዘመን (Reign of Terror፡ 1793-1794)

የመጀመሪያው የፈረንሳይ አብዮት መባቻ ላይ ከፍተኛ ፍርሐት ሰፍኖ ነበር፡፡ አምባገነኑ ሉዊስ 16ኛን ገርስሰው ሰብኣዊ መብት እና ሕገ-መንግስታዊ አስተዳደርን ከአሜሪካ ለመኮረጅ የሞከሩት ፈረንሳውያን እርስ በእርሳቸው ተቀናቃኝነት ባፈሩት የለውጡ መሪዎች ጊሮንዲኖች እና ያቆቢኖች (Girondins and the Jacobins) አንደኛው ሌላኛውን ‹‹የአብዮቱ ጠላት›› በሚል በደም የታጠበ አብዮት በማድረጋቸው 25 ሺሕ ለሚደርሱ ሰዎች እልቂት መንስኤ ሆኗል፡፡ ያንን ጊዜ የፍርሐት ዘመን (The Reign of Terror) በሚል ታሪክ ጸሐፊያን ያስታውሱታል፡፡

እኔ የፈረንሳዩ አቻ ትርጉም ነው ልለው የምለውን ማሕሌት ፋንታሁን የፍርሐት ዘመን በሚል ርዕስ ዞን ዘጠኝ ላይ ከዚህ ቀደም ጽፋዋለች፡፡ ጽሑፏ ያለንበትን የፍርሐት ወቅት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ለመሆኑ ይሄ ፍርሐታችን የፈረንሳይ አብዮት የወለደው የ‹‹ፍርሐት ዘመን›› ጋር የሚያመሳስለው ነገር ይኖር ይሆን በሚል የሚከተለትን ሁለት ክስተቶች ለማስታወስ እንገደዳለን፡፡

ሀ). ቀይ ሽብር

ምናልባትም ለአሁኑ ትውልድ አባት የሚባሉት የ‹‹ያ ትውልድ›› አባላት፣ የሚፈልጉት ለውጥ አቅጣጫውን እንዳይስት እና በየግላቸው መቆጣጠር እንዲመቻቸው ሲባል የሄዱበት መንገድ ሽብር ነበር – ቀይ እና ነጭ ብለው የሰየሙትን ሽብር፡፡

በዚህ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆነ የሽብር ድርጊት ሳቢያ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለው እስከ ግማሽ ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች አልቀዋል፡፡ ሌኒን ‹‹ያለ ቀይ ሽብር ማኅበረሰባዊነት አይገነባም›› ብሏል በሚል በአንድ ርዕዮተ ዓለም እኔ እበልጥ፣ እኔ እበልጥ በሚል እና ደርግ ጊዜያዊ መንግሥት አቋቁሞ ወደካምፑ ይመለስ የሚሉና ሌሎችም አብዮቱን ያቀጣጠሉ ጥያቄዎችን መልስ በመሻት እና በመነፈግ መካከል ለመገዳደል ሳይቀር የሶቪየት ኅብረትን ቀይ ሽብር የሚል ስም የተዋሱት ኢሠፓዎች እና ነጭ ሽብር የሚባል ምላሽ የሰጡት ኢሕአፓዎች ልክ የፈረንሳይ አብዮት ልጆች እንደሆኑት ጊሮንዲኖች እና ያቆቢኖች ‹‹አብዮት ልጆቿን በላች›› ተብሎላቸዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ የቻለው ሲሰደድ የቀረው መፍራት የሚችለውን ያክል የሚፈራበት ታሪክ ተፈጥሯል፡፡ ይህ ፍርሐት በከፊል የተቀረፈው በኢሕአዴግ አፍላ የሥልጣን ዘመን ነበር፡፡

ethiosun.com

Advertisements

Posted on December 23, 2012, in Politics and tagged , , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s