ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የድምጻችን ይሰማ ትግላቸውን አንደኛ አመት በቶሮንቶ አከበሩ

ተክለሚካኤል አበበ

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሀይማኖት ነጻነታቸውን ለማስከበር ትግል የጀመሩበትን 1ኛ አመት ቶሮንቶ በሚገኘው ሳላህዲን እስላማዊ ማእከል ትናንት እሁድ ታህሳስ 21 ቀን አከበሩ።Ethiopian muslims held public meeting in Toronto, Canada

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አለማቀፍ ምክርቤታ የቶሮንቶ ቅርንጫፍ ባዘጋጀው በዚህ አንደኛ አመት መታሰቢያ በዓል ላይ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊምና ክርስቲያን ኢትዮጵያዊያን ተገኝተዋል።

በአንደኛ አመት መታሰቢያ ዝግጅቱ ላይ፤ ከጀርመን ተጉዘው የመጡትና፤ በአጼ ሀይለስላሴ ዘመን ህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት አባል የነበሩት ታዋቂው ሙስሊም ሀጂ መሀመድ አህመድ ልጅ፤ አቶ መሀመድ ሀሰን ስለሙስሊሞች ትግል ውጣውረድ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።

ካለፉት ሁለት አመት ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ለማዳከም የተለያዩ ሴራዎችን እንዳቀደ የሚያሳይ ሰነድ ከእጃቸው እንደገባ የተናገሩት አቶ መሀመድ ሀሰን፤ ላለፉት 12 ወራት መንግስት በሙስሊሞች ላይ የሚያደርገው አፈና በዚህ ምስጢራዊ ሰነድ ውስጥ እንደተካተተ ተናግረዋል።

አተ መሀመድ ሀሰን የሙስሊሞችን የአንድ አመት ትግል ሂደት የሚያሳዩና ለትግሉ የተደረገውን አለማቀፍ ድጋፍ የሚያሳዩ የምስል ማስረጃዎችን ለተሰብሳቢዎች ያቀረቡ ሲሆን፤ ተሰብሳቢዎቹ አቶ መሀመድ ባቀረቡት ሀሳብ ላይ ውይይት አድርገዋል።

በዚህ የአንደኛ አመት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የህገመንግስቱ አንቀጽ 27 እንዲከበር ጥሪ ያደረጉ ሲሆን፤ “ድምጻችን ይሰማ፤ ሰላም አጣን ባገራችን፤ መንግስት የለም ወይ” የሚሉ መፈክሮችንም አሰምተዋል።

በዝግጅቱ ላይ  በቶሮንቶ የሚገኙ አገር ወዳድ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያንም ተገኝተዋል።

Advertisements

Posted on January 1, 2013, in Human Right, News and tagged , , , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s