“ያም ሲያማ፣ ያም ሲያማ – ወገኔ ለኔ ብለህ ስማ!”

ከይነጋል በላቸው
yinegal@gmail.com

ይህን ከዚህ በታች የምታገኙትን ዜና የወሰድኩት ከኢትዮጵያን ሪቪው ድረ ገፅ ነው – ዛሬ ማለዳ ነሐሴ 10 ቀን 2005ዓ.ም፡፡ ለሀገራችን አንዳች ጠቃሚ ነገር ይኖረው ከሆነ ብዬRebels seeking to topple Syria President Bashar Assad  እንደገባኝ ተርጉሜ ልኬዋለሁና እንደመላችሁ አድርጉት፡፡ የእንግሊዝኛው ከግርጌ አለላችሁ፡፡ በአንዳንድ ነጥቦች ዙሪያ ከኛዋ ከርታታ ሀገር የነገሮች መገጣጠም ጋር እያወራረስኩ ጥቂት መናገር እያማረኝ በዩሮኒውስ ቲቪ የ‹nocomment› የእንደወረደ አቀራረብ ሥልት ሆን ብዬ ለአንባቢ ትቼዋለሁ – ጥቂት ቦታዎች ላይ ብቻ ግን – እንዲያው ሳት ብሎኝ – አፅንዖት (emphasis) ብቻ በመስጠት ‹ተናግሬያለሁ›፡፡ ደብተራ የጻፈው አሸንክታብ አስመሰልኩባችሁ ይሆን?

አሳድ በአላዋይቶች ጎሣ የትውልድ ከተማ ‹እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ ሊዋጋ› መዘጋጀቱ ተገለጸ – ሪፖርት

በዚህ ሣምንት ‹ዘ ሰንደይ ታይምስ› እንደዘገበው የሦርያው ፕሬዚደንት ባሽር አላሳድ ከሀገሪቱ ዋና ከተማ ከደማስቆ በመሸሽ የመጨረሻውን ፍልሚያ ሊያደርግባት ወዳሰበባት የትውልድ መንደሩ ሊሄድ ማቀዱን ለመረዳት ተችሏል፡፡

አንድ የራሽያን ዲፕሎማት በምንጭነት ጠቅሶ ይህ የዜና ማዕከል እንደዘገበው 22 ወራትን ባስቆጠረው የገዛ ሕዝቡ አመጽ ሳቢያ ከፍተኛ የነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ውጥረት ውስጥ የገባው የሦሪያው ፕሬዚደንት የማይቀርለት ለሚመስለው የመጨረሻ የአልሞት ባይ ተጋዳይ ግብግብ እየተዘጋጀ ነው፡፡

ይሄው ጋዜጣ ያልተረጋገጠ የዜና ዘገባ ጠቅሶ እንዳሠፈረው ፕሬዚደንት አሳድ  “ ምናልባት የተወሰነ የቤተሰቡን አባላት በአላዊት ጎሣ ምርጥ ኃይሎች ጥበቃ ሥር ወደምትገኘውና ቃርዳ(ሃ) ወደምትባለው የአያት ቅድመ አያቶቹ መኖሪያ ከተማ ቀድሞውን አሽሽቶ ሊሆን ይችላል፡፡”

“አሳድ እስከመጨረሻዋ ጥይት ሊዋጋ ዐቅዷል” ሲል ለ‹ዘ ታይምስ› የገለጸው የራሽያው ዲፕሎማት በማስከተልም የአሳድ መንግሥት ቢያንስ ሰባት የሚደርሱ በአብዛኛው ከአላዊት ጎሣ የተዋቀሩ የልዩ ኮማንዶ ባታሊዮን ጦርና ከአንድ የማያንስ     የተወንጫፊና ተምዘግዛጊ ሚሳይል ባታሊዮን በዚሁ የአላዊቶች ጎሣ መኖሪያ በሆነችው ከተማ በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ ማሸመቁን የመካከለኛውን ምሥራቅ የደኅንነትና የፀጥታ ምንጮች በመጥቀስ ገልጧል፡፡

የዜና ምንጮቹ “የአሳድ ኃይሎች የአላዊቶችን ከተማ ከማንኛውም የተቃዋሚዎች ጥቃት ለመከላከል ዙሪያዋንና ከሌሎች ቦታዎች የሚያገናኟትን መንገዶች በሚቀበሩ ፈንጅዎች አጥረዋል፤ ልዩ የጦር ኃይልም ተሠማርቶ ቅኝትና ጥበቃ ያደርግላታል” ካሉ በኋላ አክለው እንደገለጹት የተወንጫፊ ሚሳኤሎቹ ባታሊዮን ጅምላ ጨራሽ የሆነ የኬሚካል ማሣሪያ መታጠቁንም ጠቁመዋል፡፡

ከዚሁ በተያያዘ አላዊቶች ከተደቀነባቸው አደጋ በማምለጥ ጥበቃና ከለላ ሊያገኙ ወደሚችሉባቸው ሥፍራዎች ወደ ሊባኖስና ቱርክ የጋራ ድንበር የሜዲትራኒያን የባህር ዳርቻ አካባቢ ሲጎርፉ መታየታቸው የሁኔታዎችን እየተባባሰ መሄድ እንደሚጠቁም ዘገባዎች አውስተዋል፡፡

በብዛታቸው ከሦርያ ሕዝብ 12 በመቶ (ብቻ) የሚሆኑት አላዊቶች በአብዛኛው የአሳድ ደጋፊና ታማኞች ሆነው ዘልቀዋል፡፡ ከነዚህም አብዛኞቹ በአሳድ መንግሥት ውስጥ ቁልፍ ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎችንና የጦርና የፀጥታ ተቋማትን አመራር መያዛቸው የሚታወቅ ነው፡፡       

የዜና ምንጩ እንደጠቀሰው አላዊቱ አሳድ ጦርነቱን (በእልህ) ለመግፋት ወስኖ በዚያች በጎሣው ከተማ ከመሸገና ጦርነቱን ከቀጠለ ከራሱ ጎሣ የመሠረተው ታማኝ ጦር ለአሳድ ከሚሰስትለት የአካባቢው የአላዊት ሕዝብ ጋር በመተባበር ጦርነቱን ለወራት መቀጠል እንደሚችል የታመነ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

በተያያዘ ዜና ይህ ራሽያዊ ዲፕሎማት የዜና ምንጭ የሦርያው ሕዝባዊ ዐመፅ ከተጀመረ ከማርች 2011 ወዲህ ለበርካታ ጊዜያት ከፕሬዚደንት አሳድ ጋር እንደተገናኘ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የአሳድ መንግሥት በሲቭሉ ማኅበረሰብ ላይ የሚያካሂደውን ጭፍጨፋ የአሜሪካን መንግሥት (በዲፕሎማሲ ደረጃ) የሚቃወመው መሆኑን በማስታከክ “አላዊቶች በጦር ከፍተኛ ሥልጠናና ዘመናዊ መሣሪያም እስካፍንጫቸው የታጠቁ መሆናቸውን፣ ያላቸው ብቸኛ ምርጫም እስከመጨረሻዋ የደም ጠብታ መፋለም መሆኑን አሜሪካዎች ያውቃሉ፡፡” በማለት  የዜና ምንጩ ተጠሪ በአፅንዖት ገልጦኣል፡፡

ጋዜጣው አክሎ እንደዘገበው ይህ ሀገሩን ወክሎ በሦርያ ጉዳይ ከአሜሪካዎች ጋር ይደራደር የነበረው ራሽያዊ ዲፕሎማት ባለፈው ሣምንት አሜሪካ የሦርያውያንን የተቃውሞ ኃይላት የጋራ ግንባር (SNC – Syrian National Coalition) ለሦርያ ብቸኛው ሕጋዊ ወኪል አድርጋ መቀበሏና ዕውቅና መስጠቷ እንዳላስደሰተው ጠቁሟል፡፡

በዚህ የራሽያ ዲፕሎማትና በአሳድ መካከል በተደረገ አንድ የቅርብ ጊዜ ውይይት“ሆስኒ ሙባረክ ከሥልጣን ቢወገድም ግብጽ ግን አለች፡፡ ነገር ግን እኔ ከሥልጣን ብወገድ ሦርያ የምትባል ሀገር ከናካቴው አትኖርም፡፡” በማለት አሳድ ማስጠንቀቁና ማስፈራራቱ ተዘግቧል፡፡

በእስካሁኑ የሦርያ የመንግሥት ይለወጥልን ሕዝባዊ ዐመፅና የርስ በርስ ግጭት በትንሹ ዐርባ ሺህ ሕዝብ ማለቁና ካለቀውም ሕዝብ አብዛኛው በአላዊቶች ግዛት አቅራቢያ በትሬሜሽ፣ በራስታንና በሁላ በሚገኙ የሱኒዎች መንደሮች የሚገኙ ሱኒ ነዋሪዎች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ምንጭ፡- ኢትዮጰያን ሪቪው ዌብሳይት

The Last stand, As Assad prepares to ‘fight to his last bullet’ in Alawite hometown – Report

Syria’s President Bashar al-Assad is reportedly planning an escape from Damascus, preparing for a last stand in his home town, The Sunday Times reported this week.

The embattled leader, facing a lingering 22-month-old uprising against his rule, is preparing for the “worst case scenario,” according to a Russian source who spoke to the newspaper.

The story cites unconfirmed report suggesting Assad “may already have moved members of his family to the town of Qardaha, the family’s ancestral home, where they were being guarded by loyal Alawite special forces.”

Assad plans to “fight to his last bullet” the Russian source told The Times, which highlighted that at least seven largely Alawite commando battalions and up to one ballistic missile battalion had been redeployed to the Alawite territory earlier this month, says Middle East intelligence sources.

They add the missile battalion was equipped with chemical munitions, noting “Assad’s forces mined roads along the border and moved Elite Special Forces to monitor the area,” the newspaper said.

This reflects on recent reports that a flood of Alawites were fleeing to a sanctuary along the Mediterranean coast between Lebanon and Turkey.

Alawites, who make up about 12 percent of the Syrian population, have largely stayed loyal to President Assad. Many occupy key positions in the government and security forces.

If Assad were to take his last battle to his home town, the Russian source told the paper that Assad’s army could “fight on for months with the help of … a sympathetic local population.”

The source is reported to have met with Assad several times since the start of the Syrian uprising, which erupted in March 2011.

“The Americans know that the Alawites are well trained and well equipped and that they have no choice but to fight to the bitter end,” he emphasized, in reference to continued U.S. condemnation of the deadly Syrian army attacks on the civilian population.

The newspaper says the source, who has also been involved in talks with U.S. officials, was disappointed by last week’s American decision to recognize a coalition of opposition forces as the legitimate representative of the Syrian people.

In a meeting between him and Assad, the Syrian leader reportedly said: “Mubarak may have gone but Egypt remains. But if I go, none of Syria remains.”

At least 40,000 people have been killed in violence across the country since the outbreak of an anti-regime revolt, with major attacks reported in Sunni villages, including Tremesh, Rastan and Houla – all of which lie on the eastern edge of Alawite territory.

Source: ethiopianreview.com

 ECADF.COM

Advertisements

Posted on January 1, 2013, in News and tagged , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s