ለካስ ሙት ጀግና ነው!

ለካስ ሙት ጀግና ነው!

ለካስ ሙት ጀግና ነው!

እንደ እርጥብ ሸክላ በድምጽ የተናደ፡
አምባገነን ሲባል አካሉ የራደ።
ሁለት አሰርት አመት ከሰው ተሰውሮ የኖረ በጉድጓድ፡
የሰው አይን ካየው ሲመስለው የሚያነድ።
ሞቶ ጀግና ሆነ ወጣ አደባባይ፡
ራሱ እንኳ ባይሆን ሳጥኑ እንዲታይ።
ምንም ባናውቅ እንኳ ሳጥን ያዘለውን።
በሰው ተከበበ ሊያሳይ ጀግንነቱን።
እንኳን ራዕይ እና በውል ቅዠት አያውቅ፡
አሁን ምን ይባላል ደርሶ መጨማለቅ፡
ከኢትዮጵያ አለፎ ሳውዝ አፍሪቃ መዝለቅ።
ህዝብን አናንቆ አንቋሾ ለኖረ መድዴ ስድ አደግ፡
የሙት አጽሙን ለብሶ ማየት ሲያደገድግ።
ምንኛ ያስጠላል ያንገሸግሽማል፡
የሙት አጽም ለመልበስ ሰው እንዴት ያስባል?
እንደ የዋህ ጅግራ ራብ እንደጠናባት፡
ወያኔ ወጥመድ ውስጥ ዘሎ ላለመግባት፡
መጠንቀቅ ይጠቅማል ዘላቂን መመልከት።
የሙት መንፈስ ኪታ ተካድኖ መታየት፡
ጥቁር ማቅ ጥብቆ ያውም ጉድ ያለበት፡
ትንሽ ውሎ ሲያድር የሚያመጣው ጣጣ፡
እንኳን በይቅርታ በደምም አይወጣ፡
ስለዚህ ወገኔ የደቡብ አፍርቃው፡
ቲ ሸርቱን ጣልና በእግርህ እርገጠው፡
ጨልጦ ለጠጣ የነ ሽብሬን ደም፤ ቆራርጦ ለበላ የነቢዩን ስጋ፡
መሬት ትጸየፈው ትሁን አጋም ቀጋ፡
እያለ ሲራገም ወገን ከዳር አዳር፡
አንተስ ምን ትላለህ ተጠየቅ ተናገር?
አንቺስ እንዴት አሰብሽ?
ጥቁር ትለብሻለሽ ለወያኔ ሰግደሽ
ወይስ?
ሞት ለመለስ ብለሽ፡ የወገኖችሽን፣ እንባ ታብሻለሽ፡
መልሱን ላንተ ትቼ፡ መልሱን ላንቺ ትቼ ልሰናበታችሁ፡
ግን ልብ በሉ፤ ከህዝብ አትጋጩ ወያኔ አይጠቅማችሁ፡
ሆድ አድሮ እንግዳ ነው ሞልቶ አይሞላላችሁ፡
ለሁሌ ደስታ ህሊና ይግዛችሁ።
ደቡብ አፍሪቃ የመለስ ፎቶ የተለጠፈበትን ቲ ሽርት ለመልበስ ለተመለመሉ መልእክቴ ይድረሳችሁ

እግዝአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

እስከ ነጻነት

 

 ecadf.com
Advertisements

Posted on January 21, 2013, in News, Politics and tagged , , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s