ባለራዕይ አንባገነኖችን ህግ ያስጣሰ አውራዶሮ!

ገበሬ ነኝ ከቤልጄም

ሰላም ጤና ይስጥልን አንባቢያ !

በዘመናችን በተለይ አሁን ባለንበት እንሰሳት ታምራትን እያሳዮን ይገኛል!

አሁን በቅርብ ከጥቂት አመታት በፊት እንኳን አፍሮ የተባለ ፍየል ልክ እንደ ሰው

ቢራ ይጠጣ ፣ምግብ ይበላ እንደነበር ትዕይንቱን በቴሌቭዥን ተመልክተናል።

በሌላ በኩል ደግሞ ደቡብ ወስጥ እንድ ወደል እህያ ሽክሙን እንደያዘ በአንድ ወንዝ አካባቢ ከዕነ ሽክሙ ይተኛል  ቢደበደብ ቢደበደብ ጭራሽ እንደሞተ ሆኖ በመንፈራፈሩ ባለቤቱ አይ ጣር ይዞት ነው በማለት ሽክሙን ያራግፍና ቢያየው በዛው የሞተ መስሎ በመተኛቱ ጭነቱን ወደሌላ በማዛዎር እዛው ወንዝ አካባቢ ጥሎት ወደ ገበያው ያቀናል ።

ገበሪው ከሄደበት ገበያ እህሉን ሽጦ ወደቤቱ ሲመለስ አህያውን ከቦታው በማጣቱ በዓይኑ አካባቢው ይቃኛል ::

ያየውን በማየቱ ይደናገጥና ሰፈርተኛ ገበያተኛ መንገደኞችን እርዳታ ይጠይቃል፣አህያው ከተኛበት ሆኖ ያገኘው ጅብ ለመብላት ጠጋ በሎ ሊዘነጥለው ሲዳዳ ቆፍጣናው ወደል አህያ ከተኛበት ተፈናጥሮ የጅቡን ማጅራት ነክሶ ትግል ይገጥማል:: ገላጋይ በሌለበት ትግሉ ለረጅም ሰዓት ይቀጥላል!!

አያ ጅቦ ማጅራቱን ክፉኛ ተነክሶ በቆፍጣናው ወደል አህያ በመያዙ አቅም እያነሰው ይመጣና በዛው ያሽልባል ::

ወደል አህያው ግና የለም አለቅም እኔም ከአሳዳሪዪ በተመሳሳይ ቴክኒክ (ዘዴ) ከሽክም ተርፊያለሁ አንተ ግን ወደ ሆድህ ልትከተኝ በመሆኑ አለቅም ያለ ይመስል የኣያ ጅቦን ማጅራት እንደነከሰ ነበር የአህያው ባለቤት የተመለከተው ።

ስዎች ጉድ አሉ በጉድ ብቻ አልቀረም ሥራ ተጀመረ፣በተለምዶ እንደሚባለው እህያን ከጅብ ለማስለቀቅ ሳይሆን ፣ ጅብን ከአህያ ለማስለቀቅ የአህያው ባለንብረትና ገበያተኛው ደፋቀና ማለት ቀጠሉ።

ጅቡ መሞቱን ያረጋገጡት አልሞት ባይ ተጋዳይ ከቀን ጅብ ጋር ተጋጥሞ ያሽነፈወን ወደል አህያ ፣ ለማላቀቅ አሁንም እንደ ጠዋቱ ቢደበደብ ፣ ቢቀጠቀጥ፣ቢባል ፣ቢስራ ወይፍንክች የሽክም ጠላቱ ልጅ ፣በመጨርሻ እሳት አንድደው በሜጫ አፉን በማቃጠላቸው ለያዥ ለገረዥ የታከተው ወደል አህያ መቆም የለም ይበራል ይበራል ይበራል ፣ ለጉድ የተፈጠረው አህያ ወደቤቱ ሰተት ብሎ መግባቱን ስንሰማ ከጉድ ያለፈ ምንም አላልንም ።

በሊላ በኩል ደግሞ ጅብና አንበሳ በያመቱ የሚያደርጉት ጦርነት ከጅብ ስልሳና ሰባ ከአንበሳ አስርና አስራ አምስት ይሞታል።

ታዲያ የተናካሹን አውራ ዶሮ ብሶት እናም የህግ አግባብነት ያልተመለከተው ዳኛ ፣የዶሮው ጤንነት ሳይመረመርና በሽተኛነቱ ሳይረጋገጥ እንዲወገደ መወሰኑ ኢትዮጵያ ወስጥ ያለው ህግ መጣስ ፣ ከመጣስ አልፎ ለህግ ትኩረት ያለመስጠትና ለስረዓቱ አሽቃባጭነት ብቻ የቆመ የአሻንጉሊት ህግ ከመሁኑም ባሻገር በህግ ሞያ ያልሰለጠነ የስረዓቱ አሽቃባጭ ተቀጣሪ እንጂ ዳኛ አለመኖሩን ያረጋገጠ ነው እላለሁ።  ነጻነት የፍትሕ መሰረት ነው።

 

Advertisements

Posted on January 21, 2013, in News, Politics and tagged , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s