“ለመለስ አለቀስኩ ለምን ቢሉኝ…”

ፓውል ኩልሆ ” The Alchemist” በሚለው መጽሀፉ እንዲህ ጻፈ ፦

ናርሲስ ተወዳዳሪ የሌለው ቆንጆ ወጣት ነበር አሉ፤  ከውበቱ ጋር ፍቅር ስለያዘው  በእየለቱ ወደ አንድ ሀይቅ እየሄደ መልኩን በውሀው ነጸብራቅ ሲያይ ይውላል። አንድ ቀን አጎንብሶMeles Zenawi and Ethiopian history ሲመለከት አሸንራተተውና ሀይቁ ውስጥ ገብቶ ሞተ።

በማግስቱ የጫካ ንግስት ውሀ ለመጠጣት ወደ ሀይቁ ወረደች፤  ነገር ግን በፊት የምታውቀው  የሀይቁ ውሀ ወደ ጨውነት ተለውጦ ለመጠጣት አስቸጋሪ ሆኖ አገኘችው።

የጫካዋ ንግስትም የሀይቋን ንግስት ጠየቀቻት

“ስለምን እንባዎችሽን ታፈሻለሽ? እንባዎችሽ እኮ ውሀውን ጨው አደረጉብን?”

“ምን ላድርግ ብለሽ ነው ናርሲስ እኮ ሞተ”

“አንችማ አልቅሽለት ፣ እኔ እሱን ለማደን በየጫካው እዞራለሁ፣  እሱ ደግሞ ካንጂ ጎን ተደፍቶ ቁንጅናውን ሲመለከት ይውላል።”

“ናርሲሰስ ቆንጆ ነበር እንዴ?” ጠየቀች የሐይቋ ንግስት

“ቆንጆ ነበር ትያለሽ? ስለሱ ውበት ካንች የተሻለ ማን ሊነግረን ይችላል? ካንች አጠገብ አይደለም እንዴ ተንበርክኮ የሚውለው?”

የጫካዋ ንግስት በሀሳብ ተውጣ ለትንሽ ጊዜ ጸጥ አለች።

ቀጠለች  “አየሽ የናርሲሰስን ውበት አንድም ቀን አስተውየው አላውቅም ነበር፣  ነገር ግን እሱ ከጎኔ መጥቶ አንገቱን አዘቅዝቆ ሲመለከተኝ እኔ በእሱ አይኖች ውስጥ የራሴን ውበት መልሼ ስለማየው እደሰት ነበር። ያለቀስኩትም ለዚህ ነው።”

መለስ በተቀበረ በሳልስቱ ኢህአዴግ ደስ ብሎት “ለመለስ ዜናዊ  ያነባህ የኢትዮጵያ ህዝብ ልዩ ምስጋና ይገባሀል” የሚል መግለጫ አወጣ።

የኢትዮጵያ ህዝብም እንዲህ ሲል መለሰ “አይ ኢህአዴግ ያለቀስነው እኮ ለራሳችን ነው። መለስ የውበታችን ማሳያ ነበር ፤ በእሱ ክፋት የኛን ደግነት፣ በእሱ ጥጋብ የኛን ረሀብ፣ በእሱ ውሸት የኛን እውነት፣ በእሱ ጉራ የኛን ትሁትነት፣ በእሱ ስድብ  የኛን ጨዋነት እያየን እራሳችንን እያደነቅን እንጽናና ነበር።”

ኤሎን ሳምሶን ( elonsamson@gmail.com)

ecadf.com

Advertisements

Posted on January 22, 2013, in Politics and tagged , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s