ሕዝባዊ መሰረቱን ያረጋገጠ ታላቅ ተቃውሞ!

ድምፃችን ይሰማ

አላሁ አክበር! የኢትዮጵያ ሙስሊም ዛሬም ጥያቄው ሳይመለስ ቤቱ እንደማይገባ፣ ተቃውሞውንም እንደማያቆም ዳግም ሲያረጋግጥ ዋለ! ለሳምንታዊው የጁምአ ሰላት ቀደም ብሎ በታላቁ አንዋር መስጊድ ቦታ ቦታውን የያዘው ጨዋ ህዝብ የዛሬው አመጣጡ ከቀድሞው የተለየ እንደነበር ያስታውቃል፡፡ ቀደም ባሉት ቀናት ኢቲቪ በመሪዎቻችን ላይ ህግ እና የፍርድ ቤት ትእዛዝ ጥሶ የፈጸመው በደል ውስጡ ድረስ ሰርጎ ተሰምቶታል፡፡ በሰዎች ፊት ላይ ቁጣ ይነበባል፡፡ሕዝባዊ መሰረቱን ያረጋገጠ ታላቅ ተቃውሞ!

አዎ! በዛሬዋ ቀን ሰዎች ወደ ጁሙአ የመጡት ተቃውሟቸውን ለማሰማት ብቻ አልነበረም፡፡ ይልቁንም የትኛውም አይነት የተንኮል ቢላዋ በእነሱና በመሪዎቻቸው መካከል ያለውን የፍቅር ገመድ ሊበጥስ እንደማይችል በማያወላውል ሁኔታ ለማረጋገጥም ጭምር ነበር፡፡ አልሀምዱሊላህ – ተቃውሟቸውንም ያላንዳች እንከን በሰላም ነበር ያጠናቀቁት፡፡ አመት ሙሉ ጨዋነቱን በተደጋጋሚ እያሳየ በተቃራኒው ግን የሚፈጸምበት በደል እየጨመረ እና ድንበር እየታለፈበት እንኳን ስሜቱ ትእግስቱን የማያሸንፍበት ህዝብ በእርግጥም ሊወደስ ይገባዋል!የሰዉ ብዛት እጅግ አስገራሚ ነበር፡፡ ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ ቦታው በሰዎች ተወርሮ ነበር፡፡ ከጎጃም በረንዳ መጠምዘዣ ጀምሮ ወደታች አሜሪካ ግቢን አልፎ ወደሱማሌ ተራ መውረጃ፣ በሴቶች በኩል ወደመርካቶ ዘልቆ ገብቶ ነበር፡፡ በሲኒማ ራስ በኩል የነበረው ቦታም እንዳለ በሰጋጆች ተይዞ ነበር፡፡ ከሌላው ጊዜ ለየት ባለ ሁኔታ መፈክሮች በባነር ጭምር ተዘጋጅተው ነበር፡፡ በሴቶች መስጊድ በኩል ጀግኖች እህቶቻችን የ28ቱ ጀግኖቻችን ፎቶ የታተመበትን ትልቅ ባነር ከፍ ድርገው ይዘው ሲያሳዩ የነበረ ሲሆን ፊልሙ ላይ በግድ ምስክርነት እንዲሰጡ የተደረጉት ኡስታዝ አቡበክርና ካሚል ሸምሱ፣ እንዲሁም የኡስታዝ በድሩ ሁሴን ፎቶዎች በትላልቁ ታትመው በወንዶች በኩል ሲውለበለቡ ታይተዋል፡፡

በዚህ ታላቅ ተቃውሞ የትግሉን መንፈስ የሚገልጹ በርካታ መፈክሮች ተስተጋብተዋል፡፡ በዚህ ታላቅ ተቃውሞ የትግሉን መንፈስ የሚገልጹ በርካታ መፈክሮች ተስተጋብተዋል፡፡ ‹‹አሃዱን አሃድ!››፣ ‹‹ህጉ ተጥሷል!››፣ ‹‹የሐሰት ክስ አይገዛንም!›› ‹‹ኮሚቴዎቻችን አሁንም ህጋዊ ወኪሎቻችን ናቸው!››፣ ‹‹እኛ አቡበክር ነን!››፣ ‹‹እኛ ያሲን ኑሩ ነን!››፣ ‹‹እኛ ካሚል ሸምሱ ነን!›› የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል!

በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ተቃውሞ ካሁን በፊት ሲሞከር እንደነበረው ሁሉ ሰዉን ወደስሜታዊነት ለማስገባት ሲባል 12፣ 13 እና 41 ቁጥር አንበሳ አውቶቡሶች ተቃውሞውን አቋርጠው እንዲያልፉ የተደረገ ሲሆን አላማውም ህዝበ ሙስሊሙ ንዴቱ ገንፍሎ ድንጋይ ሲወረውር ‹‹በህዝብ ንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል!›› የሚል ፕፓጋንዳ ለመንዛት ነበር፡፡ ይርጋ ሀይሌ ህንጻ ላይ ተዘጋጅቶ ሲጠብቅ የነበረው የኢቲቪ ካሜራ ግን ከሰላማዊ ተቃውሞ እና ‹‹አንሰብርም! አንሰብርም!›› ከሚል መፈክር ውጭ አንዳችም የድንጋይ ውርወራ ሳይቀርጽ ወደመጣበት ለመመለስ ተገዷል፡፡ ብዙዎች ተንኮለኝነት የግለሰብ ሳይሆን የመንግስታት ባህሪ መሆኑ በጣም አሳዝኗቸዋል፡፡

በዛሬዋ ጁምአ ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ ከተሞችም የተለያዩ ተቃውሞዎች ተደርገዋል፡፡ ካሁን ቀደም ከፍተኛ ተቃውሞ ሲደረግባት በቆየችው ሻሸመኔ ከተማ ዛሬም ታላቅ የተክቢራ ተቃውሞ ተደርጓል፡፡ በቦታው እጅግ በርካታ የፖሊስ እና ፌደራል ታጣቂ ሀይል የነበረ ቢሆንም ሰላማዊው የሻሸመኔ ሙስሊም ማህበረሰብ ሰላማዊ ተቃውሞውን አሰምቶ በሰላም ተመልሷል፡፡ በደዶላ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ መስጊዶችም ጊዜውን የጠበቀ እና የሞቀ ተቃውሞ ተደርጓል፡፡

መንግስትና አህባሽ መሳጂዶችን በመንጠቅ እና የቁርአን ማቅሪያዎችን በመዝጋት ቢዚ ሆነውባት በነበረችው የኮምቦልቻ ከተማም እንዲሁ ተቃውሞ ተደርጎ ውሏል፡፡ በባቲ ከተማም ቢሆን ከጁምአ ሰላት በኋላ በሴት እህቶች በኩል ጠንካራ የተቃውሞ ስነ ስርአት ተደርጓል፡፡

በሌላ በኩል በሀረርና በጂማ ከተማ ለየት ያሉ ተቃውሞዎች ተስተውለዋል፡፡ በሁለቱም ከተሞች በርካታ መስጊዶች የተሳተፉበት የዱአ ተቃውሞ ስነስርአት ተደርጓል፡፡ በአባ ጂፋሯ ጅማ ለወትሮው ጁምአ በሚሰገድባቸው 40 ያህል መስጊዶች ህዝበ ሙስሊሙ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል አላህ እንዲያነሳው እና ኮሚቴዎቻችንንም አላህ ከተንኮል እንዲጠብቃቸው ዱአ የተደረገ ሲሆን ከሳምንታት በፊት ልጆቿ ደም በጠማቸው ፌደራሎች የተገደሉባት ሀረር ከተማም እንዲሁ በበርካታ መስጊዶቿ የዱአ ተቃውሞ ስነ ስርአት አድርጋለች፡፡

የዛሬው ተቃውሞ ላይ የህዝበ ሙስሊሙ ቁጣም ሆነ ቁጥሩ ከወትሮው ጨምሮ የታየበት ምክንያት መንግስት በፈበረከው ድራማ ኮሚቴውን ለመወንጀል የተደረገው የከሸፈ ሙከራ ብቻ አልነበረም፡፡ አሳፋሪው የፕሮፓጋንዳ ፊልም በህዝቡ ዘንድ አንቱታን ያተረፉ ታላላቅ ዓሊሞችን ክብራቸውን እንኳን ባልጠበቀ መልኩ ‹‹ጂሃድ ሰባኪው›› እያለ ከማብጠልጠሉም በላይ ከሽብር ድርጊት ጋር ለማነካካት መድፈሩ በርካታ እናቶችና አባቶችን ክፉኛ አስቆጥቷል፡፡

ከዚህ ቀደም ‹‹መንግስት ትክክል ሊሆን ይችላል›› የሚል ጥርጣሬ የነበራቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም በኢቲቪው ቅጥፈት እውነት ከማን ጋር እንዳለች ተገልፆላቸዋል፡፡ የነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት የዛሬውን ጁመዓ ከመቼውም በተለየ በህዝብ ጎርፍ እንዲጥለቀለቅ ያደረገ ሲሆን ትግሉም በምንም ሰውኛ ሃይል ላይነቀነቅ ግዙፍ ህዝባዊ መሰረት መጣሉን አረጋግጧል፡፡ በትናንትናው እለት በሪያድ ተደርጎ በነበረው የአባይ ግድብ የቦንድ ሽያጭ ስብሰባ ላይ የመንግስት ልኡካን የገጠማቸውን ተቃውሞ ስናስተውል ከዚህ በኋላ ለመንግስት ይህ ትግል የማይወክለውን የህብረተሰብ ክፍል ለማግኘት ለናሙናም እንኳ የሚከብደው ግዜ እንዳፈጠጠበት ለመረዳት እንገደዳለን፡፡ ታዲያ መንግስት ከህዝብ ጋር እንዲህ ተጣልቶ መዝለቁ ይበጀዋልን?
ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም!

አላሁ አክበር!

ECADF.com

Posted on February 9, 2013, in News and tagged , , , . Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s