Blog Archives

የወያኔን ሰላዮችን ከውጭ አለም ማጽዳት

ከእስከ ነጻነት

ኢትዮጵያ የነጻነት ቀንዲል ነች፡እንደ ስበሃት ነጋ ላሉ ባንዳ ወያኔዎች ግን ጣሊያንን አሸንፈን ለመላው የጥቁር ህዝብ የነጻነት ጎህ ቀዳጅ መሆናችን ኩራት ሳይሆን እፍረት ስለሚመስላቸው አገሪቷ ከነሰንደቅ አላማዋ ጥፍታ ማየት የዘወትር ጥረታቸው ነው፡ ሌት ተቅን የሚተጉትም ለዚህ ስለሆነ የኢትዮጵያዊነት ሰሜት ያላቸውን ሁሉ ማሰር፤ መግደል፤ ማጥፋት ዋና ትግባራቸው ነው፡ ይህም ተግባራቸው ከበረሃ እስከ አዲስ አበባ ከዛም ጎረቢት አገሮች ድረስ ዘልቆ አሁን ደግሞ ወደ ምእራብ ሐገራትም መጣሁ እያለ ነው።

ግን አገሪቷም ሆነ ባንዲራዋ ልትጠፋ አትችልም፡ ለጥቁር ህዝብ የነጻነት ጎህ የቀደደች መሆኗን ለማረጋገጥ በርካታ ሃገራት ከቅኝ ግዛት ነጻ ሲወጡ ባንዲራቸውን መሰረት ያደረጉት በኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ላይ ስለሆነ ባለም ዙሪያ ሲውለበለብ ይኖራል እንጂ ባንዳዎች እንደተመኙት ልትጠፋ አትችልም።

ባለፈው አበበ ገላው ላይ የተቃጣው የግድያ ሴራ ከወያኔ አድሎአዊ አገዛዝ፤ ሸሽተን በመጣነው ሁሉ ላይ የተቃጣ ዛቻ ነው በሚል አጠር ያለች ጽሑፍ በእንግሊዘኛ ቋንቋ አቅርቤ ነበር። በዛሬው ጽሁፌ ማተኮር የምፈልገው ወያኔ (ለኔ ወያኔ ማለት ለአላማም ይሁን ለጥቅም የዚህን አገዛዝ እድሜ የሚያራዝም ሁሉ ነው) እንዴት ተሰደን ባለንበት አገር ለማስፈራራት ብርታቱን አገኘ? እንዴትስ የወያኔ አባላት ሰላዮች እና እበላ ባዮች በውጭው አለም በዙ? እንዴትስ መመንጠር እንችላለን የሚሉትን ዝርዝር ጉዳዮች በተመለከተ ይሆናል።

ወደ ውጭ አገር መሰደጃ መንገዶች የታወቁ ናቸው፡ ከደርግ ጅምላ ፍጅት ሽሽት አገራቸውን ጥለው የተሰደዱ ብዙ ናቸው፡ በዘር የተደራጀው እና ዘር በማጥላላትና በማጥፋተ ላይ የተመሰረተው የወያኔ ቡድን ስርዓቱን በኢትዮጵያ ላይ ከጫነ ጀምሮ፡ ወያኔ በህዝቡ ላይ በሚያደርገው ጫና፤ ጭቆናና ግፍ አገራችንን ለቀን ተሰደናል፡ የተሳካልን ነጻው አለም ደርስናል ያልተሳካላቸው በበረሃ አሸዋ ተውጠው ቀርተዋል፡ ባህር ውጧቸዋል፡ ከቀይ ባህር እስከ ቬንዙዌላ የውሃ ጎርፍ ወስዷቸዋል፡ ከባህር እና ካሸዋ የተረፉት በየሀገራቱ እስር ቤቶች ተሰቃይተው ሞተዋል፡የውስጥ አካላቸው ተበልቶ ተወሰዷል፤ በእህቶቻችን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ግፍ እና ስቃይ መናገር አይቻልም፡ የሰው ህሊና ሊያስበውና ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ነው።

እኛስ በዚህ መልኩ ተሰደድን የወያኔ ደጋፊዎች፤ እና ሰላዮችስ እንዴት መጡ?

በስራ፤ በንግድ፤ ወይም በተለያየ መንገድ ከመጡት በተጨማሪ፡ እንደኛው ወያኔ ሊያኖረኝ አልቻለም፡ አሰረኝ፤ ገረፈኝ ብለው የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው ውጭ የሚኖሩ በጣም ብዙ ናቸው፡ በሌላም በኩል ኤርተራዊ ነኝ፡ ብለው በኤርትራውያን ስም፤ ሱማሌያዊ ነኝ ብለው በሱማሌ ስም ጥገኝነት ጠይቀው የተፈቀደላቸው እንዳሉም ይታወቃል፡ እንዳውም የኤርትራውያንን ስደተኞች ተቀብያለሁ እና ሶስተኛ አለም ተረከቡኝ ብሎ ሶስተኛ አገሮች ከተረከቧቸው አብዛኛዎቹ የወያኔ ደጋፊዎች እና የወያኔ ሰላይ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ስደተኞችን ተቀባይ አገሮች አይወቁት እንጂ የህን ጽሁፍ በማንበብ ላይ ያለኸው፤ ያለሽው፡ ጠንቅቀው ያውቁታል።

ለምን የወያኔ ደጋፊዎች፤ ወደ ነጻው አገር መጡ አደለም ጥያቄው፡ ይኸ መንግስት በድሎናል፤ ጨቁኖናል መኖር አልቻንም ብለው የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው፤ ጥያቄያቸው ተቀባይነት ካገኘ በሗላ ከዚሁ ጨቆነን ካሉት መንግስት ጋር አብሮ መስራት፤ የወያኔ ደጋፊዎች፤ ኢምባሲ ጭምር በሚያዘጋጁት ስብሰባ ላይ፤ የድጋፍ ሰልፍ ላይ እንዴት ሊገኙ ቻሉ?

ይህ ብቻ አደለም ከድጋፍ አልፈው የወያኔ አገዛዝ አስመርሯቸው የተሰደዱትን በኬንያ፤ በዩጋንዳ በሱዳን፤ በሶማሊያ፤ በጅቡቲ ሲገሉ እና ሲያሰገድሉ ኖረዋል፡ ያንን ተግበር አሜሪካ፤ ካናዳ እና አውሰትራሊያም ሊሞከሩ እንደሚችሉ፤ መገመት በቻ ሳይሆን አበበ ገላው ላይ የተጠነሰሰው ሴራና የአሜሪካው የፌዴራል ምርምራ ቢሮ (FBI) ማክሸፉ ያላቸውን ዕብሪት በግልጽ ያሳያል።

ይህ ደግሞ በአበበ ገላው ብቻ የሚቆም አደለም ለሌሎቻችንም የሚተርፍ የወያኔ ድግስ ነው ስለዚህ እንዴት ማስቆም አለብን የሚለው ነው ቁም ነገሩ።

ይህንን ለማሰቆም ወይም የወያኔ ሰላዮችን አጋልጦ ለፍርድ ለማቅረብ የፖለቲካ ድርጅቶች ወይም የሲቪክ ድርጅቶች አያስፈልጉም፡ እነሱ ወያኔን ከስሩ ለመንቀል ይንቀሳቀሱ፤ ለዚህ ተግባር ግን የሚያሰፈልገው፡ በወያኔ የዘረኛ አገዛዝ ተማረህ የተሰደድክ፡ ግፋዊ አሰተዳደሩን መቋቋም አቅቶሽ አገርሽን ጥለሽ የወጣሽ፡ በወያኔ የግፍ ቀንበር እህትህን ያጣህ፤ ወንድምሽ እህትሽ በስደት ላይ እያሉ ባህር የዋጠብሽ፡ አንተ ነህ፤ አንቺ ነሽ የምታስፈልጊው፤ የምታስፈልገው። በአንድ ከተማ ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ቁርጠኛ ኢትዮጵያዊ ካለ በቂ ነው፡ በኢትዮጵያ የህግ የበላይነት መከበር ጽኑ አላማ ያለውና በጥቅም ያማይገዛ ህሊና ያላቸው አንድ ወይም ሁለት ባንድ ከተማ ካሉ በጣምበቂ ነው፡ የሚጠበቀው መደባደብ ወይም መሰዳደብ አደለም የሚያሰፈልገው ወያኔ በድሎኛል ብሎ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ ሰው ከወያኔ ቡድን ጋር እየሰራ እና ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም ጥገኝነት የሰጠውን አገር አየስለለ መሆኑን ሪፖረት ማረግ ብቻ ነው።

ማንኛውም ሰው አንድ አገር የፖለቲካ ጥገኝነት ሲጠይቅ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በደለኝ ብሎ መኖር አልቻልኩም ካለና ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ በሗላ ያ መንግስት እስካልተቀየረ ድረስ ከዛ መንግሰት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሊኖረው አይችልም፡ በምንም መልኩ ከዛ መንግስት ጋር ግንኙነቱን ከቀጠለ ከመንግስቱ ጋር ችግር የለበትም ማለት ነው ስለዚህ ወዳገሩ መመለስ አለበት፡ የኽ የኔ አስተያየት ሳይሆን የየሃገራቱ የስደተኛ ህጎች ናቸው።

ስለሆነም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ የተፈቀደለት፡ ወይም ኤርትራዊ፤ ሶማሊያዊ ነኝ ብሎ ጥገኝነት የተፈቅደለት (ወንድ ይሆን ሴት፤ አማራ ይሁን ኦሮሞ፤ ትገሬ ይሆን አደሬ፤ ማንም ይሁን ማ) የወያኔው ኢምባሲ በሚያዘጋጀው ፕሮገራም ላይ የሚሳተፍ፤ የወያኔ ባለስልጣናት በሚጠሩት ስብሰባ ላይ የሚገኝ፤ የወያኔ ደጋፊዎች ወይም ካደሬዎች በሚያዘጋጁት የወያኔ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የሚገኘን፡ ከወያኔ ጋር የንግድ ስራ ጀምሮ ኢትዮጵያ የሚመላለስን ሁሉ ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ማደረግ ያስፈልጋል።

ባለፈው 21 አመት ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት አልተቀየረም ስለሆነም በነዚህ ጊዜያት የወያኔ መንግስት በድሎኛል፤ ሊያኖረኝ አለቻለም ብሎ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ ሰው ሁሉ በምንም መልኩ ከወያኔ ጋር የሚሰራ፡ ወያኔ በሚያዘጋጀው ዝግጅት ላይ የሚገኝ ሁሉ ሪፖርት መደረግ አለበት።

እዚህ ላይ አደራ የምለው እና ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባው ሪፖርት የሚደረገው ነገር እውነት ብቻ እንዲሆን፤ በግል ቂም በቀል፤ ወይም በተወሰነ ዘር ላይ ያነጣጠረ እንዳይሆን አደራ እላለሁ፡፡ ወያኔን ያጠናከረው፡ የተወሰነ ዘር ወይም የወያኔው አባላት ብቻ ሳይሆን እበላ ባይ አጃቢ ጭምር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡ ስለዚህ ሁሉም የወያኔን እድሜ እየለመነ የወያኔን ፍርፋሪ የሚለቃቅም ሁሉ ሪፖርት መደረግ አለበት።

ወያኔን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ከወያኔ ጋር መደባደብ መነታረክ ሳይሆን ሰማቸውን ቢቻል አድራሻና ፎቶገራፋቸውን መዝግቦ መያዝ ነው ከዛ ለሚመለከተው ረፖርት ማድረግ።

ሪፖርት ለማድረግ የግድ የግል ሰማችሁን መጠቀም አይኖርባችሁም፤ ሰሜ አይገለጽ ማለትም ትችላላችሁ፡ ከቤታችሁ ሪፖረት መላክ ካላመቻችሁ ወይም ካልፈለጋችሁ ከህዝብ መጻሕፍት ቤት ኮምፑተር ተጠቅማችሁ ሪፖርት ማድርግ ትችላላቸሁ፡ የህዝብ ቤተ መጻህፍት አባል ለመሆን ክፍያ አይጠይቅም ነጻ ነው፤ የሚጠይቀው መታወቂያ ወይም ባደራሻችሁ በስማችሁ የተላከ ደብዳቤ ብቻ በቂ ነው፡

መልክታችሁ አጭር ነው፡

“እገሌ የሚባል ሰው አዚህ አገር ሲገባ መንግስት ጨቆነኝ አላኖር አለኝ፤ ብሎ ነበር አሁን ግን ጨቆነኝ ከሚለው ከመንግስት ጋር በቀጥታ እየሰራ ስለሆነ ሰላይ ሊሆን ይችላል ወይም የጥገኝነት ጥያቄው የውነት አደለም ብዬ እጠራጠራለሁ ማጣራት ቢደረግ”

ማጣራቱ የናንተ ጉዳይ ሳይሆን የደህንነት ሰራተኞች ጉዳይ ይሆናል፡ ከማንም ሳትማከሩ፤ አዩኝ አላዩኝ ብላችሁ ሳትፈሩ፤ ሚስጥሬ ይባክናል የሚል ስጋት ሳይኖራችሁ ትክክለኛውን መረጃ ለሚመለከተው ክፍል መስጠት የህሊና ነጻነት መጎናጸፍ እና የዜግነት ድርሻን መወጣት ነው፡

ሪፖርት የምታደርጉባቸውም አድራሻዎች

1. በዩናይትድ ሰቴትስ FBI (Federal Bureau of Investigation)https://tips.fbi.gov 2. በካናዳ Canadian Security Intelligence Service:http://www.csis-scrs.gc.ca/cmmn/cntcts-eng.asp 3. በአውስትራሊያ Australian security Intelligence Organization:http://www.asio.gov.au/Contact-Us.html እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

Abbay Media.com

Advertisements

የኢትዮጵያዊያን ትግል

(ከአንዱ ዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ)

eskemechie

June 25, 2013 07:40 am By  Leave a Comment

ክፍል አንድ

የመድረክ የአደባባይ ውይይትን በመንተራስ

የአንድነት ፓርቲ ግምገማዉንና የመድረክ አመራር መልሱን በአደባባይ ማቅረባቸው ታላቅ በር ከፋች ጥረት ነው። አንድነት መድረክን ብቻ ሳይሆን፤ የራሱን አመራር አካላትም ገምግሞ ለኢትዮጵያዊያን ማሳየቱ፤ ብስለቱንና ጥንካሬውን አመልካች ነው። ከመድረክ በኩል የተሠጠውም መልስ፤ በድብቅ ሳይሆን በአደባባይ መውጣቱ የሚያኮራ ነው። እዚህ ላይ አንዱም ሆነ ሁለቱ ትክክል ናቸው ወይንም ስህተተኞች ናቸው ማለቴ አይደለም። ጥረታቸው የሚያኮራ መሆኑን ለመጠቆም ነው። በዴሞክራሲያዊ ማዕከልነት ስምና በፓርቲ አባልነት ግዴታ ማነቆ ልሳናቸው ሳይዘጋ የተጻጻፉበት ምልልስ፤ ትልቅ ትምህርት ለሁላችን ሠጥቷል። እስከዛሬ ያልተለመደው ግልፅነት በሩ ተከፈተለት። ራሳችንን መገምገም ራሳችንን ዝቅ እንደማድረግ ስለሚወሰድና ይኼን ማድረግ እንደተቸናፊነት ስለሚወሰድ፤ ከትናንት ትምህርት የመውሰዱ ሂደት በሩ ዝግ ነበር። አሁን በሩ ተከፈተ። ሀቅ ይረዳል እንጂ ማንንም አይጎዳም። ይኼ ግን ባህላችን አልነበረም። ጥሩ ነገር ስናይ ደግሞ፤ ማንም ይሥራው ማንም ይበል ማለት ተገቢ ነው።

ጉዳዩ የሁላችን ነው

የተወያዩባቸው ጉዳዮች የግላቸው ሳይሆኑ፤ ሁላችን ኢትዮጵያዊያንን የሚነኩና እኩል እንደነሱ ልንወያይባቸው የሚገባ ነው። ትኩረቱ እከሌ እንዲህ አለ፤ ሌላው ደግሞ ይኼን መለሰለት ለማለት ሳይሆን፤ ባደረጉት ምልልስ የተነሱት ነጥቦች በሁላችንም ዘንድ መልስ ፈላጊ በመሆናቸው፤ በየበኩላችን እንድንወያይበት ይገፋናልና የበኩሌን ለመለገስ ነው። አሁንም እንደገና፤ ግልፅ ውይይት ማድረግ በማንኛውም ወቅት የጥንካሬ፣ በተጨማሪም ራስን ደግሞ ደጋግሞ በየደረሱበት ደረጃ መመርመር፤ ለትግሉ ውጤት ያለንን ቁርጠኝነት መለኪያ መሣሪያዎች ናቸው።

ጉዳዩ እንዲህ ነው። መድረክ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዋቀረ የፖለቲካ ድርጅት ነው። የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ ተንትነው አንድ መፍትሔ በማቅረብ፤ የርዕዩተ ዓለም አመለካከታቸው አንድ የሆነ አባላት ያሉበት ድርጅት ነው። በሌላው በኩል በአካባቢ ወገኖቻቸውን በማሰባሰብ የተዋቀሩ ድርጅቶች አሉ። እኒህ ድርጅቶች የአካባቢያቸው ተቆርቋሪ በመሆን አጀንዳቸውን ያማከሉ ድርጅቶች ናቸው። መድረክን ለመፍጠር በሁለቱ ወገን ያሉ ክፍሎች ወይይት አድርገው፤ በኢትዮጵያ በነበረው ሀቅ ተገደው፤ የተወሰነ ስምምነት ላይ ደረሱ። ይህ መድረክ ወደፊት ምን ሊሆን እንደሚችል ያኔ በደንብ ያጤኑት ላለመሆኑ፤ የአንድነት ፓርቲ ግምገማ ግልፅ አድርጎልናል። አሁን ዕድገታቸውን አስመልክቶ ወደፊት ሲሉ፤ በወቅቱ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አስረው ያዟቸውና፤ ከፊታችን ለተደቀነው ውይይት በቁ። ታዲያ ከዚህ ምን እንማራለን?

እውነት ስትፈተን

እያንዳንዳችን መብትና ግዴታችን የሚመነጨው ከኢትዮጵያዊነታችን ነው። መብታችን ሊከበር፣ ኃላፊነታችን ሊጠየቅ የሚገባው፤ በኢትዮጵያዊነታችን ነው። ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በምንኖርባት ኢትዮጵያ፤ ከኢትዮጵያዊነት የተለዬ መብትና ግዴታ የለንም። አማራ ሆኜ በአማራነቴ መብቴና ግዴታዬ፤ በኢትዮጵያ፤ እንደ ትግሬ ወይንም እንደ ኦሮሞ ወይንም እንደ ሶማሌ ሳይሆን እንደ አማራ ይከበርልኝ ብል፤ የምናገረውን የማላውቅ መብት ፈላጊ እሆናለሁ። አማራ መሆኔ የኔ ጉዳይ ነው። ከአማራና ከኦሮሞ መወለዴ የራሴ ቤተሰብ ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያ ስኖር፤ አማራ ወይንም ኦሮሞ፣ ሶማሌ ወይንም አፋር፣ ትግሬ ወይንም ወላይታ መሆን የለብኝም። ኢትዮጵያዊ ብቻ መሆኔ ነው መለኪያው። ከአንዱ ወይንም ከአንዱ በላይ ከሆኑ ቤተሰብ መወለዱ፤ የግለሰቡ የቤተሰብ ትስስር ጉዳይ ነው። ይህ ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ መብቱ ሊጨምርለት ወይንም ሊያስቀርበት አይችልም። ታዲያ ምኑ ላይ ነው ችግሩ? ችግሩ የተከሰተው፤ ከዚህ ወይንም ከዚያ በመወለዴ የቀረብኝ ወይንም የደረሰብኝ ወይንም የሚቀርብኝ ወይንም የሚደርስብኝ ጥቅም ወይንም በደል ነው። ይህ ያለአንዳች ጥያቄ በሀገራችን የተከሰተ ችግር ነው። መለያየት የሚመጣው መፍትሔ ሲታሰብ ነው። መፍትሔው ደግሞ፤ ላንድ ወቅት ወይንም ላንድ ክፍል የሚሰራ ሳይሆን፤ ሁሌም ለሁሉም የሚሠራ መሆን አለበት። ይህ ደግሞ፤ በሕገ-መንግሥቱ፣ በመንግሥቱና በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊከበርና ሊጠበቅ የሚገባው መሆኑ ነው። በዚህ ላይ በአንድነት መነሳት አለብን። በውጭ ሀገር በየተሰደድንበት ቦታ፤ መብታችን በሀገሩ ካሉ ነዋሪዎች በአንዲት ጠብታ ሳታንስ እንዲከበርልን ሽንጣችንን ገትረን እንቆማለን። የሀገሩን ዜግነት ተቀበልንም አልተቀበልንም ልዩነት አናይበትም። ታዲያ ኢትዮጵያ ላይ ምን ልዩነት ተፈጠረ? የሀገሩ ዜጋ በሙሉ እኩልነታቸው የሚመዘገበው፤ የሀገሩ ዜጎች በመሆናቸው ብቻ ነው።

የትግላችን ግብ

ኢትዮጵያዊያን ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ጋር የምናደርገው ትግል፤ ይኼን በጉልበቱ በሥልጣን ላይ ያለን ቡድን ስሙን ስለጠላን ለማስወገድና ሌላ ስም ያለው በቦታው ለመተካት አይደለም። መሠረታዊ የትግሉ መነሻው የዚህ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የፖለቲካ ፍልስፍናውና የአስተዳደር መመሪያው ናቸው። እኒህ የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያዎቹ በሀገራችን ተዘርፍጠው መቀመጥ ቀርቶ ባንዣበቡበት ሁኔታ፤ ወደፊት መሄድ የሚባል ጉዳይ የለም። የትግል እሽክርክሪቱ ተወግዶ ወደፊት እንድንሄድ ከተፈለገ፤ ግልፅ የሆነ ውይይት ማድረግ አለብን። በአሥራ ዘጠኝ መቶ ስድሳዎቹ የነበረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ ዋናው የትግል መስመሩ፤ በገዢዎችና በተገዢዎች መካከል የነበረው ቅራኔ ነበር። በዚህ የተጠቃለሉት የዴሞክራሲያ ጥያቄዎች፤ መሬት ላራሹ፣ የትምህርት ዕድል ለብዙኀኑ፤ ሕክምና ለገጠሬው፣ ኃላፊነት ለፓርላማው፣ የሴቶች እኩልነት፣ በወቅቱ ትክክለኛ ትኩረት ያልተደረገበትና የዘመኑ የሶቪየት ኅብረት ሶሺያሊዝምን መስመር ያንፀባረቀው የብሔሮች እኩልነት ነበሩ ከሞላ ጎደል ሰንደቆቻቸው። በመደብ ትግሉ ጠንካራ አቋም ከነበረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ ተገንጥለው፤“በኢትዮጵያ የብሔሮች ነፃ መውጣት ነው ቅድሚያ ያለው” ብለው የተነሱ ጥቂት ቡድኖች ነበሩ። በዚህ የተመሩ የብሔር ነፃ አውጪ ቡድኖች በሀገራችን ግራ ቀኙን ተሯሯጡበት። ተጨባጭ የነበረው የአድልዖና የጭቆና ክስተት፤ ለትንንሽ መንግሥታት መፍጠሪያ መንገዱን ከፈተ። ለነበረው ሀቅ አንድ ብቻ መፍትሔ ሳይሆን ብዙ መንገዶች ቀረቡ። አንድ ሀገር የሚለው ጉዳይ በአንዳንዶች ዘንድ ተቀባይነት አጣ። በዕርግጥ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ መፍትሔ የፈለገው በሀገራችን ውስጥ የነበረውን የገዢዎችና የተገዢዎች ቅራኔ መፍታት ሲሆን፤ ጥቂቶች ደግሞ የተለዬ መፍትሔ ብለው የያዙት የራሳቸውን ሀገር የመመሥረት አጀንዳ ነበር።

አጀንዳ ያልለወጠ ነፃ አውጪ

ይኼን የመጨረሻውን መንገድ የመረጡት የነፃ አውጪ ግንባሮችን በመመሥረት ጠመጃቸውን አነሱ። በባንዳነት ጣሊያንን በማገልገል የታወቁ የትግራይና የኤርትራ ተወላጆች ልጆች፤ ጠንካራ የሆነ ፀረ-ኢትዮጵያ መርኀ-ግብር ይዘው፤ ኢትዮጵያን የማፈራረስ አጀንዳቸውን በራሳቸውና በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች መመሪያቸው አደረጉ። በከፍተኛ ደረጃ ለዚህ የረዳው ደግሞ፤ የደርግ ደርጋማ ማንነትና የተከተለው መመሪያ ነበር። ሥልጣን ለብቻው መያዝ ዋናው ዓላማው ያደረገው የመንግሥቱ ኃይለማርያም አረመኔ ደርግ፤ ወጣቶችን በመጨፍጨፍ፤ በእውነትና በሕልሙ ጠላቶቼ ናቸው ብሎ የፈረጃቸውን በማሳደድና የራሱ ሰው በላ ቡችሎችን በከፍተኛ ቦታ በማስቀመጥ፤ ሀገራችንን ወደ አዘቅት ከተታት። የዚህ ውጤቱ ለትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሀገሪቱን ወለል አድርጎ ከፍቶ ሀገር ለቆ መሽምጠጥ ሆኗል። ታዲያ የብሔሮች ነፃ መውጣትን ያነገበው ይኼ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ ትግራይን ነፃ ከማውጣት ይልቅ፤ በተፈጠረለት ቀዳዳ ገብቶ ሀገሪቱን ተቆጣጠረ። አጀንዳውን ሳይለውጥ፤ አሁንም የትግሬዎች ነፃ አውጪ ሆኖ አዲስ አበባ ተዘርፍጧል። ባለበት ቦታ ደግሞ የሚሠራው ሀገራችንን መበጣጠስ ነው። ሀገራችንን ሀገር የሚባል ነገር ጠፍቶ፤ የየራሳቸው ብሔር የሚኖራቸው ሕዝቦች ያሉበት ቦታ አድርጓታል። ይህ ነው የትግሬዎች ነፃ አውጪ አጀንዳ። ይኼን ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚታገለው። ታዲያ በየአካባቢያቸው የተዳራጁት የፖለቲካ ድርጅቶች ዓላማቸው ምንድን ነው? የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የሚከተለውን ዓላማ ማራመድ ነው ወይንስ መለወጥ? ሀገራችንን በጋራ ነፃ አውጥተን ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እኩል የምትሆን ሀገር ማድረግ ነው? ይህ ነው መሠረታዊው የመድረክ ምስቅልቅል።

“አትከፋፍሉን። አንድ ነን።”

አንድነት የፖለቲካ ግኘታ ቋምጦ ነበር ከአካባቢ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የተቧደነው። አሁን ጠዘጠዘው። የግድ ከዚህ መላቀቅ አለበት። በአዲስ አበባ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ፤ “አትከፋፍሉን። አንድ ነን።” ነበር ያለው። የኢትዮጵያ የወደፊት ዕድል በሰማያዊ ፓርቲና በመሰሎቹ ወደፊት መጪ ፓርቲዎች እንጂ፤ በነበሩት የነፃ አውጪና የማያፈሩ የቆዩ ፓርቲዎች እጅ አይደለም። የአካባቢ የፖለቲካ ድርጅቶችን ከሀገር አቀፍ የፖለቲካ ድርጅቶች በዋናነት የሚለያቸው፤ የአካባቢ የፖለቲካ ድርጅቶች ሌሎችን አግላይ መሆናቸው ነው። በነዚህ ድርጅቶች ውስጥ፤ በሌሎች አካባቢ የሚኖሩ የሀገሪቱ ዜጎች፤ አባል ሊሆኑ አይችሉም። ስለዚህ ዴሞክራሲያዊም ሆነ ኢትዮጵያዊ አይደሉም ማለት ነው። ከዚህ ተነስተውም፤ እንንቀሳቀስበታለን በሚሉት የራሳቸው ክልል፤ የሀገር አቀፍ የፖለቲካ ድርጅቶችን መንቀሳቀስ በድፍኑ ይቃወማሉ። የርዕዩተ ዓለም ልዩነት ሳይሆን፤ የዚህ አካባቢ ሕጋዊ ተወካዮች እኛ ብቻ ነን ስለሚሉ፤ ከነዚህ ድርጅቶች ጋር ማንኛውንም ዓይነት ስምምነት ለመድረስ፤ በነሱ አካባቢ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ያለማድረግ ቅድመ-ግዴታ ይሆናል። ይኼን የተቀበለ ሀገር አቀፍ ድርጅት፤ አንድም በነዚህ አካባቢ ያሉትን ደጋፊዎቹ የሀገሪቱ ነዋሪዎች ሸጧል ማለት ነው፤ አለያም የሚያደርገውን የማያውቅ ድርጅት ነው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ማኅደር፤ በአካባቢ በተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶችና በሀገር አቀፍ በተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ቅንጣት ታክል ፍቅር የለም። ግንባርማ ቅዠት ነው። ኢሕአዴግም ውሎ አድሮ ሲበጣጠስ፤ ይኼኑ ያሳየናል።

ውሃ ቢያጥቡት

ሥር የሰደደ ቂም ካለው የትግራይ ታሪክ የተያያዘ መነሻ ያለው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ድርጅት፤*1 ኢትዮጵያን ማፈራረስ ዋና ዓላማው ነው። እንደ ኢትዮጵያዊያ ሳይሆን፤ የተገነጣጠልን ሆነን ራሳችንን እንድንመለከት ነው መርሁ። አንዳንድ የአካባቢ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ለምን ሀገር አቀፍ የሆነ ድርጅት እንዳልመሠረቱ ወይንም ሀገር አቀፍ ከሆኑ ድርጅቶች እንዳልተቀላቀሉ ሲጠየቁ፤ የሠጡት መልስ ወንዝ አያሻግርም። ዶክተር መራራ መልሳቸው፤ “እኛ ለኦሮሞ ሕዝብ የቆመ ድርጅት ይዘን ካልተገኘን፤ ሕዝቡ ወደ ኦነግ (የኦሮሞ ነፃነት ግንባር) ይነጉዳል።” ነበር። እንግዲህ የዶክተር መራራ ድርጅት የሚፎካከረው ኦሮሞዎችን ከኦነግ ጋር እንዳይሠለፉ ገንጥሎ፤ በሥሩ ለማድረግ ብቻ ነው። አቶ ገብሩ አሥራትም በበኩላቸው፤ “የትግራይ ሕዝብ የራሱ የሆነ ድርጅት ካላቀረብንለት የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብቸኛ ወኪላቸው በመሆን ያጠቃልላቸዋል።” ይላሉ። በዕርግጥ ቃል በቃል አልተጠቀሱም። መልሳቸው ግን ማንነታቸውን በግልፅ ያሳያል። የአቶ ገብሩ አሥራት አረና የሚፎካከረው ትግሬዎችን በሥሩ ለማድረግ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ጋር ነው። የዶክተር አረጋዊ በርሄና የአቶ ግደይ ዘርዓፂዮን ታንድም እንዲሁ።

የግለሰብ መብትና የቡድን መብት – በግልፅ ከተነጋገርን

በግለሰብና በቡድን መብቶች ዙሪያ ብዙ ስለተጻፈ እዚህ ላይ መተንተኑ አስፈላጊ አይደለም። እግረ መንገዴን ግን የቡድን የምንለው መብት በግለሰብ መብት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የተጠቃለለና በትክክለኛ የዴሞክራሲያዊ ሂደት ብቻውን መቆም የማይችል መሆኑን ማስታወስ እወዳለሁ። አቶ ገብሩ አሥራት፣ ዶክተር አረጋዊ በርሄና አቶ ግደይ ዘርዓፂዮን ትግሬዎችን ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ለመውሰድ ከሆነ የሚታገሉት ለምን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በከለለው በትግራይ ምድር ብቻ ተመዝግበው አይታገሉም? በእውነት ለመናገር፤ ለትግሬዎች ከሀገር አቀፍ በርዕዩተ ዓለም የተመሠረተ የፖለቲካ ድርጅት ሌላ፤ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የበለጠ አረናና ታንድ ይጠቅማሉ? ይኼ ያጠራጥራል። ይልቁንም የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሲወድቅ፤ ትግሬዎች በደል እንዳይደርስባቸው ቦታ መያዣ የተቋቋሙ ድርጅቶች ናቸው። ዶክተር መራራም ሀገራዊ ፍቅር ኖሯቸው ሳይሆን፤ ለሥልጣን ሊያቀርባቸው የሚችለው፤ የአካባቢ የፖለቲካ ድርጅት በመመሥረት ስለሆነ ነው። በተመሳሳይ መልኩ ዶክተር በየነ ጴጥሮስም የዚሁ አባዜ ተጠቂ ናቸው። ታዲያ ዶክተር መራራም ሆኑ ዶክተር በየነ ለምን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በከለለው የኦሮሚያና የደቡብ ክፍል ተመዝግበው አይታገሉም? ይህ እንግዲህ በግልፅ እንነጋገር ከተባለ ነው። ታዲያ ለኔ፤ በመድረክ ውስጥ የታዬው ድራማ ከዚህ በላይ የተገለፀው ነው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ማኅደር የሚሳተፍና በሕዝቡ ላይ እምነት ያለው ግለሰብም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ቀርቦ ሃሳቡን መግለፅና አሳምኖ ተከታዮችን ማግኘት እንጂ፤ በአንድ የተለዬ አካባቢ ቀርቦ፤ ለዚያ አካባቢ ተከላካይና የዚያ አካባቢ ጠባቂ ለመሆን አያስብም።

የመገንጠል ግብ

መገንዘብ ያለብን፤ በሥልጣን ላይ ያለውን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መጣል ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያን ለመገነጣጠል ዓላማቸው አድርገው የሚታገሉ የአካባቢ ድርጅቶች እንዳሉ ነው። እነኚህን ለይቶ ማስቀመጥና ከነዚህ ጋር ሊኖር የሚችለውን ግንኙነት ማጥናት ግዴታ ነው። በዕውነት ግን ከነዚህ ጋር ምን ዓይነት ቅርርብ ሊደረግ ይቻላል? ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከተነሱ ድርጅቶች ጋር የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ለማስወገድ መሠለፍ፤ የራስን አንገት ለማስቆረጥ፤ ከጎራዴ መዛዡ ጋር መስማማት ነው።

*1  የዶክተር አረጋዊ በርሄን የማስተርስና የዶርትሬት ጽሑፍና መጽሐፋቸውን ይመልከቱ። በአፄ ሚኒሊክ ላይ ያስቀመጡት ውንጀላ በግልፅ ተቀምጧል።


የኢትዮጵያዊያን ትግል – ( ክፍል ሁለት )

“ለየብቻችን ተማክለን እንጂ በአንድነት ተዋሕደን አንኖርም።” የሚለው ቅኝት፤

ከሁሉ በፊት ያለው ጥያቄ፤ ኢትዮጵያዊ ነዎት ወይ? ነው። መልስዎ አዎ ከሆነ፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲሉ፤ ምን ማለትዎ ነው? ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? እርስዎ ኢትዮጵያዊነትዎን ሲያስቡ፤ ለግል፣ ለራስዎ የሚሰማዎ ምንድን ነው? ይህ መሠረታዊ ጥያቄ ነው። ለማናችንም ቢሆን መነሻ ወለላችን ይህ ነው። ይኼን ስናጤንና አጢነን ለዚህ የምንሠጠው መልስ፤ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ያለንንና የሚኖረንን ግንኙነት ይወስናል። እናም በአንድነት ለምናደርገው ተግባር፤ ተርጓሚ ነው።

ኢትዮጵያዊነት ለአንድ ኢትዮጵያዊ፤ ጊዜ የማይቀይረው፣ ሁኔታ የማይለውጠው፣ የግል ጥቅም የማያነቃንቀውና ቦታ የማያርቀው የምንነት አካል ነው። ዜግነቱ ብቻ አይደለም። ከዚያ በላይ ነው። ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል በኢትዮጵያዊነቱ የመኖር መብት አለው። ይኼ ደግሞ ሊተገበር የሚችለው፤ አንድ ግለሰብ፤ በኅብረተሰብ የፖለቲካ ተሳትፎው መመዘኛው ኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ሆኖ ሲገኝ ነው። ኢትዮጵያዊ በመሆኑ፤ መብቶቹ ሁሉ ይከበራሉ። አንዱ ኢትዮጵያዊ ከሌላው ኢትዮጵያዊ በማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ ተሳትፎ ብልጫ ወይንም አነስተኛ ድርሻ ሊኖረው አይገባም። የታሪክ አንድነታችን፣ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ያበጀልን ያካባቢ ማነቆ፣ ታሪክን በደንብ መረዳት ግዴታችን መሆኑ፤ ኃላፊነታችን፣ የሌሎች ተመክሮና የዚህ ክፍል ማሳረጊያ እነሆ!

የታሪክ አንድነታችን፤

የእንግሊዝ፣ የጣሊያን፣ የቱርክ፣ የግብፅ፣ የሱዳንና የፈረንሳይ ወራሪዎችን በተለያዩ የታሪካችን ወቅቶች የተጋፈጠው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። ፋሽስት ጣሊያን በኛ ላይ ያደረገውን ተደጋጋሚ ጦርነቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ ነበር ገትሮ የተቋቋመው። በነዚህ ውጊያዎች ቆራጥ የሆኑ አያቶቻችን፤ ከዘርዓይ ድረስ እስከ አብቹ፣ ከበላይ ዘለቀ እስከ ባልቻ አባ ነፍሶ፣ ከአብረሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም እስከ ጣይቱ ብጡል፣ ከታከለ ወልደ ኃዋሪያት እስከ አዳነ አባ ደፋር በአንድነት አኩሪ ተግባር ፈፅመው አልፈዋል። በኤርትራ በኩል፣ በሱማሌ በኩል፣ በሱዳን በኩል ተደጋጋሚ ጥቃቶች ሲመጡብን የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ተሠልፏል። ሽብሬ ደሳለኝ ለአማራ ወይንም ለኦሮሞ፣ ለትግሬ ወይንም ለወላይታ፣ ለሲዳማ ወይንም ለአኙዋክ ሳትል፤ ለኛ ለሁላችን ለኢትዮጵያዊያን ነፃነት ሕይወቷን የሰጠች ኢትዮጵያዊት ነበረች። ከየትኛው የኢትዮጵያ ክልል ከሚኖሩ ወገኖች መወለዷን የሚናገር እስካሁን አላገኘሁም፤ አስፈላጊ አይደለምና! የኔሰው ገብሬ የተናገረው፤ በነበረባት ኢትዮጵያ ያለው በደል፤ ለማንም ኢትዮጵያዊ የማይቻል መሆኑን ነበር። በተጨማሪ ረሃብና እርዛት በአንድ ወገን ሲደርስ፤ ወደ ሌላው አካባቢ በመሄድ ተጠግተዋል። ተመሳሳይ የባህልና የኅብረተሰብ ግንኙነቶችን መጥቀስ ይቻላል። እስኪ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የፈጠረልንን ያካባቢ ማነቆ እንመርምር።

የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ያበጀልን ያካባቢ ማነቆ፤

አሁን ችግራችን፤ ሀገሬን ነፃ አወጣለሁ የሚሉ ኢትዮጵያዊያና የኢትዮጵያን ክፍል አንድ ቆርጠው ነፃ አውጣለሁ በሚሉት መካከል ሊኖር የሚችል ግንኙነት ካለ፤ ምንድን ነው? የሚለው ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ለትግሬዎች ቆሜያለሁ እያለ ኢትዮጵያን እየገዛ ነው። አንዳንዶች ለትግሬዎች አዳላ እያሉ ማሰረጃቸውን በመደርደር ይናገራሉ። በትግራይ ያሉ ወገኖቻችን ደግሞ፤ የለም የራሳቸውን ቤተሰብና ዘመዶች እንጂ በሙሉ የትግራይን ወገን አልጠቀሙም ይላሉ። ማጣፊያው፤ ለእነዚህ መሪዎች የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ጉዳያቸው እንዳልሆነ ነው። እዚህ ላይ የትግራይ ወገናችን የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል በመሆናቸው የችግሩና የመፍትሔው ክፍል ናቸው። ይህ የሚያሳየን፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ ለራሱና ለዘመዶቹ ጥቅም፤ ኢትዮጵያን ለመከፋፈል መነሳቱን ነው። በየክልሉ ያስቀመጧቸው ተቀጥላዎቻቸው የግልና የዘመዶቻቸውን ኪሶች ማሳበጣቸው አብሮ የሚሄድ ነው። በኢትዮጵያዊነታችን የምናምን ደግሞ፤ የምንታገልለትን ማወቅና በግልፅ ማስቀመጥ አለብን። በተጨማሪም ከማን ጋር እንደምንሠለፍ መተለም አለብን። የራሴን ወገኖች ቆርሼ ነፃ ላወጣ ነው የሚል ግንባር፤ ከተቃዋሚ ኢትዮጵያዊያን ይልቅ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ይቀርበዋል። ሲመሽ ከዚህ ቡድን ጋር መቀላቀል ይቀለዋል። ምክንያቱም፤ ሁለቱም ላካባቢያቸው ጉዳይ ቅድሚያ ሠጥተው ነው በኋላ ኢትዮጵያን በያሉበት ተደራጅተው መቀላቀል የሚለው ትርጉም የሚሠጣቸው። ታሪካችን በደንብ መረዳት ከዚህ እንድንጠነቀቅ ይረዳናል።

ታሪክን በደንብ መረዳት ግዴታችን ነው፤

አሁን ባለንበት ዘመን፤ በተለይም የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በፈጠረው የክፍፍል ቀመር እኛ ተመርዘን የቀድሞ አባቶቻችንና ነገሥታትን እንደኛ ያሰሉ ነበር የሚለው ጥሬ አስተሳሰብ ግንዛቤያችንን አሸውርሮታል። በቀድሞ መንግሥታት መካከል የነበረው አመዛኝ አመለካከት፤ ጠንካራ የሆነውን ወገን ማቸነፍ፤ ማቸነፍ ካልቻሉ ደግሞ በጋብቻ ማሰርና መዛመድ ነበር። ለዚህ ነው አጋዚ፣ አገው፣ አማራ፣ ትግሬና ኦሮሞ ነገሥታቶች የነበሩት። የዘር ግንዳቸውን በአባታቸው ቆጠሩት በናታቸው፤ ደማቸው የተደበላለቀ ለመሆኑ ማናችንም ልንጠራጠር አይገባም። በታሪክ የተመዘገበውን የነገሥታት የጋብቻ ትስስር ብናጤን፤ መዛመዱ ሀገር አቀፍ ነበር። ወደ ኋላ ራቅ ብሎ ማየት ይቻላል፤ እስኪ በዘመነ መሣፍንት ጊዜ በጎንደር ብንጀምር፤ ራስ አሊ ልጃቸውን ለካሣ ሲድሩ፣ ካሣ አማራ መሆኑን ጥያቄ ውስጥ አላስገቡትም። ጠንካራ ጎበዝ መሆኑንና በጎናቸው ቢያሰልፉት እንደሚጠቅማቸው ተረድተው ነበር። አፄ ዮሐንስ የወሎውን ራስ አሊ ንጉሥ አድርገው በጋብቻ ሲጠምዱ ዘራቸውን አልቆጠሩም። አፄ ሚኒልክም ደግመውታል። አፄ ኃይለሥላሴም እንዲሁ። በትግሬ፣ በኦሮሞና በአማራ ነገሥታት መካከል፤ በግለሰብ ሥልጣናቸውን የሚያጠናክሩበትን መንገድ እንጂ፤ የደም ቁጥር ተሳስበው ያገለሉበት ወቅት ጎልቶ አይታይም። አሁን እኛ በገባንበት ማንቆ እነሱም ይግቡ ብለን የምናደርገው ትንንቅ፤ ብስለት የጎደለው የግንዛቤ ልልነት ነው። የትግራይ፣ የኦሮሞም ሆነ የአማራ ደም አላቸው ብለን ብንፈርጃቸውም፤ ነገሥታቱ ኢትዮጵያዊ ነበሩ። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መሪ የነበሩት፤ “የአክሱም ሐውልት ለወላይታው፤ የጎንደሩ ግንብ ለኦሮሞው ምን ያደርግለታል?” ያሉ ጊዜ፤ የሀገርን ምንነት ግንዛቤያቸውን ተረዳን። ይህ አባባል፤ በዘመነ መሣፍንት ጊዜ እንኳን፤ የራስን ኃይል ለማጠናከርና ወታደር ለመመልመል መሣሪያ ከመሆን አልፎ ትርጉም አልነበረውም። በአሁኑ ዘመን ሲነገር ደግሞ፤ ተናጋሪው ከዘመነ መሣፍንት በፊት መኖርና መሞት የነበረባቸው፤ ጊዜያቸውን አልፈው የተገኙ ተብለው እንዲወሰዱ ያደርጋል። ይኼን የመሰሉ መሪ ምን ዕቅድ እንዳላቸው ግልፅ ነበር። ከክልሉ ውጪ ያለው ማንኛውም ነገር የሱ አይደለም ማለት ነው። የአክሱም ሐውልት የአሁኑ የትግሬ ነዋሪዎች ነው ብሎ ማሰብ ታሪክን አለማወቅ ነው። ያኔ በዚያ ይኖሩ የነበሩት ማን እንደነበሩ ታሪክን ማገላበጥ ይረዳል። ያኔ በአክሱምና በጠቅላላው የሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል፤ ከአማሮችና ከትግሬዎች በፊት አብዛኛው ነዋሪ አገው እንደነበር ማስረጃዎች ብዙ ናቸው። በመካከላቸው በተደረጉት የጋብቻ ግንኙነቶች፤ የአገው ደም የሌለውን ኢትዮጵያዊ በዚህ ክፍል ማግኘት፤ የአማራ ደም የሌለበት ኢትዮጵያዊ ማግኘት፣ የኦሮሞ ዝንቅ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ማግኘት ቀላል አይደለም። የጎንደር ግንብም ሲሠራ ምን ያህል የኦሮሞ ባለሥልጣኖች በወቅቱ በዚያ ከተማ ይኖሩ እንደነበር ማገናዘብ ያስፈልጋል። አማራዎች ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ኦሮሞዎች ከሰሜን እስከ ደቡብ በተለያዩ ወቅቶች ኖረዋልና! ደም መቁጠሩ የት እንደሚያደርሰን በርጋታ እናስብ። የእኛ ኃላፊነት ምንድን ነው? እንመልከት።

ኃላፊነታችን፤

ኃላፊነታችን የነበረውን ታሪካችንን ተቀብለን፤ ከስኬቱ ሆነ ከስህተቱ ትምህርት ወስደን፣ የወደፊቱን ማስተካከል ነው። እኛ ለትናንቱ ሳይሆን ላለንበት ወቅትና ለነገው ሁኔታ ነው ተጠያቂነታችን። ኢትዮጵያዊ ነኝ ስንልና በኢትዮጵያዊነታችን ስንኮራ፤ በታሪካችን ሁሉም ጥሩ ሥራ እንጂ መጥፎ አልነበረም ብለን አይደለም። እኛ ኢትዮጵያዊ ስለሆን ብቻ ነው። መጥፎም ተደረገ ጥሩ፤ ታሪካችን ነው፤ ኢትዮጵያዊያን ነን። መጥፎ ስለተደረገ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም፣ ዴሞክራሲያዊ መብቴ ስላልተከበረ ሀገሬ ለኔ ምን ታደርግልኛለች፣ የነበረው የኔ አይደለምና አዲስ መጀመር እፈልጋለሁ የሚለው ቁንፅልና ያልበሰለ ግንዛቤ ራሳችንን ጎጂ ነው። አንዳንዶች ከነገሥታቱ እየመረጡ አንዱን ኢትዮጵያዊ ሌላውን የአንድ አካባቢ ተጠሪ ያደርጋሉ። ሌሎች ደግሞ አንዱን አረመኔ ጨፍጫፊ ሌላውን መልዓክ የሚያደርጉ አሉ። ኢትዮጵያዊነትን በአንገት ላይ እንደሚንጠለጠል ጌጥ አድርጎ መመልከት ጎጂ ነው። ኢትዮጵያዊነት የምንነት አካል ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝ ወይንም አይደለሁም እንጂ፤ ኢትዮጵያዊነትን በኪሴ ያያዝኩት ንብረት ነው፤ ስፈልግ ባንገቴ አንጠለጥለዋለሁ አለያም ደብቄ በኪሴ እይዘዋለሁ የምንለው ጉዳይ አይደለም። በመሆንና ባለመሆን መካከል መቆሚያ አጥር የለም። ነህ ወይንም አይደለህም ብቻ ነው። እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ታሪካችን በብዙ ቢሆን ኖሮዎች የተሞላ ነው። አፄ ቴዎድሮስ እንዲህ ቢያደርጉ ኖሮ፣ በዚያ ቦታ እንዲህ ቢወስኑ ኖሮ፣ በዚያ ጊዜ ይኼን ባያደርጉ ኖሮ፣ . . . የምንላቸው ተትረፍርፈዋል። በአፄ ዮሐንስም ዘመን፣ በአፄ ሚኒሊክም ዘመን፣ በአፄ ኃይለ ሥላሴም ዘመን። የሀገራችንን ታሪክ አጥፊዎቹ ሌሎች ናቸው እኛ አይደለንም ለማለት፤ እነሱ ይኼንን ባለማደረጋቸው ነው ወይንም ያንን በመድረጋቸው ነው እያልን፤ ሀገራችን ላለችበት ሁኔታ ወቃሾች ብዙዎቻችን ነን። እስኪ ከ፲ ፱ ፻ ፷ ፮ ዓመተ ምህረት ጀምሮ፤ ስንት አጎምዢ አጋጣሚዎች በዓይኖቻችን ሥር አልፈዋል? ይኼ ቢሆን ኖሮ፣ ያ ቢደረግ ኖሮ፣ . . . የምንላቸው ብዙ ናቸው። አሁንም ከመቼውም የበለጠ አጋጣሚ ከፊታችን ተዘርግቷል። ይኼን አጋጣሚ እንደሌሎቹ ሁሉ አሳልፈን፤ ለነገአዎቹ ቢሆን ኖሮ ካሳለፍንላቸው፤ በታሪክና በነገ ከተወቃሽነት አንወጣም። በሥልጣን ላይ ያለው ቡድን በውስጡ በጣም የተወጠረበት ሰዓት ነው። አንዱ ሌሎቹን ገድሎ ብቻዉን በአቸናፊነት እንስኪወጣ ድረስ፤ በመካከላቸው ትርምስ አለ። ተቀምጠን እነሱ ተባልተው እንስጨርሱ ስንጠብቅ፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ እጅ ሊገባ የሚችለውን ድል አስልፈን እንሠታለን። ተቃዋሚ ክፍሉ በአንድነት፤ የውስጥ መበላላቱን ትቶ፣ በአንድ አጀንዳ፣ በአንድ ድርጅት፣ በአንድ ራዕይ፤ ሥልጣኑንና ምርጫውን ለጠቅላላው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትቶ፤ ከሕዝቡ ጎን ቢሠለፍ፤ የታሪክ፤ የትውልድና የሀገር ኃላፊነቱን ከመወጣት ሌላ፤ እያንዳንዳችን ልባችን ሞልቶ በፈገግታ ቀሪውን የሕይወታችን ጊዜ ማሳለፍ እንችላለን። የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደእስካሁኑ ሁሉ ድርጅቶችን ቀድሞ ከፊት ቆሟል። እሁድ ግንቦት ፳ ፭ ቀን ፳ ፲ ፭ ዓመተ ምህረት የተደረገው ሰልፍ ትልቁ ምስከር ነው። የሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ቢሆንም፤ ጠቅላላ ሕዝቡ የመራውና የሕዝቡ ለመሆኑ አጠያያቂ አይደለም። የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ያን ያህል እንዳልነበሩ ዕውቅ ነውና! ስለዚህ ተጀምሯል። እኛ ተባበርንም አልተባበርንም የኢትዮጵያ ሕዝብ ደወሉን አስምቷል። ይልቁንስ በትልቁ የሀገራችን ጉዳይ እናተኩር። ኢትዮጵያዊ ሆነን እንቆጠር። እስኪ ሌሎች የራሳቸውን ታሪክ በተመለከተ ተመክሯቸውን እንመልከት።

የሌሎች ተመክሮ፤

በአሜሪካ መሥራች አባቶች በመባል የሚታወቁትን መሪዎቻቸው ብናጤን፤ በባርያ ፈንጋይነታቸውና ሠራተኛን በመበዝበዝ የሚታወቁት ባለፀጎች ነበሩ። ዛሬ እኒህ መሥራቾች በነጮችና በአፍሪካዊያን አሜሪካዊያን ዘንድ የማይነኩ ጣዖት ሆነዋል። እኛ የቀድሞ ነገሥታትን እንዴት ነው የምንመለከታቸው? ሪቻርድ ኒክሰን በአሜሪካ የስነ-አስተዳደር ቅጥፈት ተገኝቶባቸው፤ ከፕሬዘዳንትነት ተዋርደው የወረዱ መሪ ነበሩ። የሪቻርድ ኒክሰን የቀብር ስነ ሥርዓት ሲፈፀም፤ የነበረው ድምቀትና አዘኔታ፤ ልክ እንደ አንድ ታላቅ መሪ ነበር። መጥፎ ተግባራቸው የመሪነት የቀብር ስነ ሥርዓቱን አላጓደለባቸውም። ምን ጊዜም የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ነበሩ መባልን አያስቀረውም። ጆርጅ ቡሽ ለብዙ ሺህ አሜሪካዊ ወታደሮችና በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የኢራቅ ተወላጆች እልቀት ምክንያት የሆነውን የኢራቅ ወረራ በውሽት መረጃ አመካኝተው እዝ አስተላልፈዋል። አሜሪካ ከፍተኛ ወጪ በማድረግ ያካሄደችው ይህ ወረራ፤ ምንአልባት ቀጥሎ ለመጣው የምጣኔ ሀብቷ ቀውስ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ሳያደርግ አልቀረም። በዚህ ወረራ ከጠፋው ሕይወት ሌላ፤ የጠፋው ንብረት ቀላል አልነበረም። በተጨማሪም የሕዝቡን መብት በመጋፋት፤ ሕጋዊ ያልሆኑ ፍተሻዎችን፣ እስር ቤቶችን ማቋቋምና ግለሰቦችን ማሰር አከናውነዋል። ይኼን ሁሉ በአሜሪካን በዓለም ዙሪያ ለፈፀሙ መሪ፤ በአሜሪካ ውስጥ፤ ዳላስ ከተማ ከፈተኛ የሆነውን የቡሽ ቤተ መጽሐፍት ወዳጆቻቸው አቋቁመዉላቸዋል። እኛ የራሳችንን እንዴት እያየን ነው?

የዚህ ክፍል ማሳረጊያ፤

“ለየብቻችን ተማክለን እንጂ በአንድነት ተዋሕደን አንኖርም” የሚለውን ቅኝት ዘማሪዎች ከሁለት ወንዝ ይቀዳሉ። የመጀመሪያዎቹ በክፍፍሉ የራሳቸው ሥልጣን ስለታያቸው፤ ከግል የጥቅም ጉጉት አንፃር የሚያከሩ ናቸው። ሁለተኛዎቹ ደግሞ፤ የኢትዮጵያን ታሪክ ካለመፈለግም ሆነ ዕድሉን ስላላገኙ የማያውቁ ናቸው። በማንኛውም መንገድ ቢሆን ራሳቸውን ያላወቁ ናቸው ማለት ይቻላል። አንዳንድ ታሪክ ጸሐፊዎችና ጸሓፊዎችን የሚያዙ ባለጉልበቶች ታሪካቸው እንደፍላጎታቸው እንዲተረክላቸው መጣራቸው አዲስ አይደለም። እኒህ ወገኖች ግን ሁሉን በቁጥጥራቸው ሥር ማድረግ ባለመቻላቸው፤ ታሪክ ከየቦታው እየሠረፀ በመውጣቱ፤ ተመራማሪዎች እያጠናቀሩ አቅርበውልናል። እናም በብዙ ድካም ከተለቃቀሙት ክፍሎች ታሪኩን መረዳት ችለናል። አሁን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የበላይ በሆነበት ወቅት፤ ይህ ቡድን የነበረውን ሆነ አሁን ያለውን በፈለገው እንዲቀረፅለት እየሞከረ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። በሂደቱም ደግሞ የነበረውን ታሪክ መለወጥ የፈለገበት ምክንያት፤ አንድም የራሱን ሕልውና ሕጋዊና ዘለዓለማዊ ለማድረግ፤ ሁለትም የስነ ልቡና ለውጥ ለማምጣት ያለው ጥረት ነው። ስለተጻፈ ግን እውነት አይሆንም። የነበረው ነበር። አሁን ያለንበትን እንጂ የትናንቱን ሀቅ መለወጥ አንችልም። የትናንቱ ሀቅ ደግሞ፤ ትምህርት እንድናገኝበት ከተለያዩ ማዕዘናት መመርመርና መጠናት አለበት እንጂ፤ እንለውጠው ብሎ መነሳት፤ የአምባገነኖች ዓይነተኛ ባህርይ ነው። እኛ የምንታገለው በሀገራችን አሁን ያለው የአስተዳደር ጉድለት፤ ከዕርማት በላይ ስለሆነ መለወጥ አለበት ብለን ነው። ስለታሪካችን የታሪክ ተመራማሪዎች በመስካቸው እንዲከራከሩበት ነፃነቱ እንዲሠጣቸው እንታገልላቸው። ስላሁን ነፃነታችን አሁን እንታገላለን።


የኢትዮጵያዊያን ትግል – ( ክፍል ሶስት )

የሁለት ደረጃ ትግላችን፤

በዚህ ርዕስ በተከታታይ በቀረበው ባሁኑ የሶስተኛው ክፍል፤ በቀጥታና በግልፅ ቋንቋ ምን ማድረግ እንዳለብን አብራራለሁ። በመጨረሻውና አራተኛው ክፍል ደግሞ ከዚህ ወዴት? በሚል መዝጊያን አቀርባለሁ። ኢትዮጵያዊያን አሁን ባለንበት የፖለቲካ ሀቅ፤ ሁለት ደረጃ ያለው ትግል ማድረግ የግድ አለብን። እኒህን በቅደም ተከተል መደረግ ያለባቸው ትግሎች፤ በግልፅ ተረድተንና ተከትለን ካልሄድን፤ ትግላችን የእሬያ ታጥቦ ጭቃነት ነው። እኒህ ትግሎች በፊታችን የተጋረጡ ለመሆናቸውና የግድ ማድረግ ያሉብን ለመሆናቸው፤ ማናችንም ብንሆን ጥርጣሬ የለንም። አንጥረን የለየናቸውና በዚያ ስሌት ያስቀመጥናቸው ለመሆናቸው ግን፤ ጥያቄ አይጠፋም። እንዲያውም ዝብርቅርቅ ያለ ጭጋግ ወጥሮ ይዞናል። ይህን ለማሳየት መጀመሪያ ኢትዮጵያዊያን ያለንበትን ሁኔታ እንመልከት።

ኢትዮጵያዊያንን የማይወክል መንግሥት አዲስ አበባ ላይ ተቀምጧል። ይህ መንግሥት ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነ የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ አስቀድሞ፤ ሀገራችንን ከአንድነት ወደ ልዩነት በመንዳት፤ ለርስ በርስ ትልቅልቅ እያዘጋጀን ነው። በውልድ ኢትዮጵያዊ ይሁኑ እንጂ በተግባር ፀረ-ኢትዮጵያዊ ለመሆናቸው መረጃ የሚጠይቀኝ የለም። ግልፅ ነውና! በእርግጥ እስካሁን በተለያዩ ወገኖቻችን መካከል መጠፋፋቱ አልተከሰተም ብዬ አይደለም፤ መጪው መለኪያ የሌለው የከፋ መሆኑን ለመጠቆም ነው። ድህነቱ፣ በበሺታ ማለቁ፣ ያልተመጣጠነ አስተዳደርና እድገት በተለያዩ ቦታዎች መከሰቱና መደልበቱ፣ የአስተዳደር በደል ጣራ መንካቱ፣ የኑሮ ውድነቱ ማሻቀቡ፣ . . . ወዘተ፤ ባጠቃላይ ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ መሄዱ የተዘገበ ነው። ይኼን እንደ አስተዳደር ብልጠት የተሞሽረበት የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ በዕብሪትና ባለው አቅም እየገፋበት ነው።

በተጓዳኝ የተቃዋሚዎቹን ወገን የተመለከትን እንደሆን ደግሞ፤ አንድ ማዕከል የሌለው፣ አንድ የትግል ራዕይ የሌለው፣ እጅግ በጣም የተበታተነ ክፍል እናያለን። በነዚህ የተለያዩ የተቃዋሚ ወገኖች ውስጥ፤ እጅግ በጣም ቆራጥና ሕይወታቸውን ለወገናቸውና ላገራቸው ለመሥጠት ወደ ኃላ የማይሉ ታጋይ ወጣቶች ሞልተውባቸዋል። የአብዛኛዎቹ የነዚህ ወጣቶች ፍላጎት፤ የኢትዮጵያዊያን ነፃነት፣ የሀገራቸው ብልፅግናና እድገት ብቻ ነው። እነዚህ ወጣቶች፤ ማን ነገ በሕዝቡ ተመርጦ መሪ ይሆናል? ማን ይቸነፋል? የሚሉት በአእምሯቸው ቦታ የላቸውም። በመሪዎቻቸው በኩል የተገላቢጦሽ ነው። አሁንም እነኚህ ወጣቶች በአንድነት ለኢትዮጵያ ለመሠለፍ ዝግጁ ናቸው። መሪዎቻቸው ግን አጥር አበጅተውባቸዋል። የነሱ ድርጅት፣ የነሱ ፍልስፍና፣ እነሱ አጥቂና የበላይ ካልሆኑ፤ ትግሉ አፍንጫውን ይላስ ያሉ ይመስላሉ። እናም “ሌሎቹ ስህተተኞች ናቸው”ብለው ይስብኳቸዋል። ይህ ሊፈርስ የሚችለውና ባንድ ላይ ተሰባስበን ልንታገል የምንችለው፤ የትግሉን ምንነትና መንገድ በአደባባይ ተወያይተንበት ግልፅ ግንዛቤ ስንይዝ ነው። በዚህ ለይስሙላ የተዘረጉት አጥሮች በሙሉ ይፈራርሳሉ። ለዚህም ነው አሁን ካለንበት የፖለቲካ አረንቋ ወጥተን ነገ ትሆን ለምንፈጋት ኢትዮጵያ መንገዱ ሁለት ደረጃ ያለው ትግል ነው የምለው። የተጋዮች በአንድ ወገን መሠለፍ ግዴታ ነው። እነሆ ሁለቱ የትግል ደረጃዎች።

ሁለቱ የትግል ደረጃዎች ምንድን ናቸው?

መልካም። በሁለቱም የትግል ደረጃዎች ውስጥ የአስተሳሰብና የሃሳብ ልዩነቶች አሉ። የሚለያዩበት ቢኖር፤ እንዴት ይስተናገዳሉ በሚባልበት ጊዜ የሚሠጣቸው መፍትሔ ላይ ነው። የመጀመሪያዉን ከመዘርዘሬ በፊት ሁለተኛውን ማስቀደሙ፤ ለግንዛቤ ይቀላልና በሱ ልጀምር።

ሁለተኛው የትግል ደረጃ፤

የሁለተኛው የትግል ደረጃ፤ የእኔ አምራለሁ፣ እኔ አምራለሁ፣ ውድድር ነው። በኔ አምራለሁ አኔ አምራለሁ ውድድር፤ ከፈራጅ ፊት ቀርቦ መልስ መጠበቅ እንጂ፤ እርስ በርስ ማማርን ለማሻሻል ሆነ ለማሳየት ፍጥጫ የለበትም። የሌላውን አለማማር ለማሳደግ ሲሮጡ የራስንም አለማማር ስለሚያባብሱት ሁሉም በዚያ ጎዳና መጓዙን አይወድም። ከጎኑ ያለውን እንዳያምር አደርጋለሁ ብሎ የሚነሳ፤ የራሱ አለማማር ከመጉላቱ ሌላ፤ ያልተነኩት ማማራቸው ወደ ላይ ስለሚወጣ ጉዳቱ እጥፍ ድርብ ይሆናል። እዚህ ላይ አምራለሁ ባዮች የፖለቲካ ድርጅቶች ፈራጅ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። ትግሉም የሰላምና የሃሳብ ትግል ነው። እንግዲህ በዚህ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ፤ የርዕዩተ ዓለም ልዩነት በሕዝቡ ፊት እየቀረበ፤ የምንፋረጅበት ነው ማለት ነው። የዴሞክራሲ ትግል ነው። ሕጋዊ ትግል ነው። ሕጉም የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ነው። በሀገሪቱ ያለው መንግሥት ከተወዳዳሪዎቹ የተለዬና ነፃ የሆነ ነው። እናም በመንግሥቱና በወቅቱ የመንግሥቱን በትር በጨበጠው የፖለቲካ ድርጅት መካከል ግልፅ የሆነ ልዩነት አለ። ይህ እንግዲህ የዴሞክራሲያ አሠራር የሠፈነበት ኅብረተሰብ መኖሩን ያሳያል። ይህን አሠራር የሚያራምዱትና የሚጠብቁት፤ ሕገ መንግሥቱ፤ መንግሥታዊ መዋቅሩና እያንዳንዱ የሀገሪቱ ዜጋ ናቸው። በዚህ ደረጃ ላይ ከተደረሰ፤ ወደ ኋላ የመጓዝ ዕድሉ ሙሉ በሙሉ ይጠፋል ባይባልም፤ በጣም ጠባብ ነው። መብቱን በተረዳ ሕዝብ መካከል፣ ይኼንን መብት በግልፅ ያስቀመጠ ሕገ መንግሥት ባለበት ሀገርና መንግሥታዊ መዋቅሩ ለዚህ አመቺ ሆኖ በተዘረጋበት እውነታ፤ አምባገነኖች የመፈልፈላቸውና ፍላጎታቸውን በሕዝቡ ላይ የመጫናቸው ዕድል የጠበበ ነው። በዚህ ደረጃ ላይ ለመድረስ ግን ትልቅ አጥር መሻገር ይኖርብናል። ይኼውም የመጀመሪያው ትግል ነው። የመጀመሪያውና አስቸጋሪው ትግል በቅድሚያ መደረግ አለበት።

የመጀመሪያው ትግል፤

ከላይ ባስቀመጥኩት የሁለተኛው ትግል፤ የተለያዩ አመለካከቶች ያሏቸው የፖለቲካ ድርጅቶች፤ አመለካከታቸውን በሕዝብ ፊት በማቅረብ፤ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ የሚወዳደሩበት እንደሆነ አሳይቻለሁ። ይኼኛው የመጀመሪያው የትግል ደረጃ ከዚያኛው የትግል ደረጃ በጣም የተለዬ ነው። እዚህ ላይ የርስ በርስ ውድድር የለበትም። ይኼ መሠመር አለበት። እዚህ ላይ የርስ በርስ ውድድር የለበትም። ፈራጅ የለም። እዚህ ላይ የኢትዮጵያዊያን የሕልውና ትግል ነው። ይህ ወደ ሁለተኛው የትግል ደረጃ ለመድረስ ጠራጊ ትግል ነው። ይህ እኔ አምራለሁ እኔ አምራለሁ በማለት የሚኮፈሱበት ሳይሆን፤ ለመጠፋፋት የሚነሱበት የትግል ደረጃ ነው። በእርግጥ፤ እንደማንኛውም የኅብረተሰብ ምርምር ሁሉ አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው ማለት አልችልም። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መሪዎች፤ “ሳንጠፋፋ አብረን እንሥራ ብለው”ሊሠለፉ ይችላሉ ብሎ የሚሞግተኝ እንደማይጠፋ እርግጠኛ ነኝ። እስኪ እኒህን እንመልከታቸው።

በኔ በግል አመለካከቴ፤ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥትና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ያለው ቅራኔ የመጠፋፋት ደረጃ ለይ ስለደረሰ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነቱን የሚያገኘው፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ መንግሥትን አወድሞ ነው እላለሁ። በሌላ በኩል ደግሞ፤ የለም መጠፋፋቱ አያስፈልግም፤ ይህ የትግሬዎች ነፃ አውጪ መንግሥት፤ ሀገራችን ያለችበትን አደጋ ተረድቶ፣ ፈቃደኛ ሆኖ፣ ከተቃዋሚዎቹ ጋር በመተባበር፣ የዴሞክራሲያዊ አሠራርን ተቀብሎ፤ የሽግግር መንግሥት ይመሠርታል የሚሉ አሉ። አይሆንም ብዬ አልከራከራቸውም። የሚሆንበት መንገድ የለም ብዬም ደረቅ አቋም አልወስድም። የመሆን ዕድል አለው። እኔ ግን በሕልሜም አይመጣልኝም። እናም አላምንም። አሁንም በትግሬዎች ነፃ አውጪ መንግሥትና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ያው ትግል፤ የጠፊና የአጥፊ ነው እላለሁ። በዚህ ጎን የሚሠለፉ፤ ቅኝ ተገዢዎችና የቅኝ ገዢዎች፣ ተወራሪዎችና ወራሪዎች፤ ትክክለኛ የሆነና ትክክለኛ ያልሆነ ጦርነት አነሳሾች ናቸው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ትክክለኛ የኢትዮጵያ መንግሥት አይደለም። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሕጋዊ አይደለም። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መሪ ሆኖ ከቀጠለ፤ ሀገራችንን ያጠፋታል። ይኼንን እያልኩ፤ ከዚህ መንግሥት ጋር የሰላም ድርድር ይቻላል የሚል ብዥታ አላራምድም። ኢትዮጵያዊያን ለሕልውናችን ስንል ይኼን መንግሥት ማስወገድና ማጥፋት አለብን። የለም ይህ መንግሥት መጥፋት የለበትም የሚሉ ደግሞ፤ ሀገር ውስጥ በሚደረገው ሕጋዊ ትግል ገብተው፤ በሰላማዊ መንገድ፤ ትክክለኛ መንግሥት ለመመሥረት መታገል አለባቸው። ይህ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ተደምስሶ ኢትዮጵያዊ መንግሥት መመሥረት አለበት ባዮች ደግሞ፤ ሕጋዊም ሆነ ሕጋዊ ያልሆነ የሚባል ትግል የለንም። የትኛው ሕግ? ማንኛውንም መንገድ በመከተል መታገል አለብን። በአንዳንዶች ዘንድ ሰላማዊ ያልሆነ ትግል መልሶ ሌላ አምባገነን ስለሚያመጣ፤ የትጥቅ ትግል ቦታ የለውም የሚሉ አሉ። ለዚህ እኮ ነው ውይይት አድርገን፤ ሀገር አቀፍ የሆነ አንድ ድርጅት ብቻ መሥርተን፤ በማንኛውም መንገድ እንታገል የምለው። የሚያስፈራው ሰላማዊ ወይንም ትጥቃዊ መሆኑ አይደለም። የሚያስፈራው አንድ የራሱ የሆነ ጉልበታም ድርጅት፤ ሌሎቹን ሁሉ ጠቅጥቆ፤ በራሱ አጀንዳ አዲስ አበባ ላይ የተፈናጠጠ እንድሆነ ወይንም ጠመንጃውን ተመክቶ፤ ተገንጥሎ የሄደ እንደሆነ ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥትን፤ አንድነት ያለውና አንድ ብቻ ኢትዮጵያዊ ኃይል፤ በማንኛውም መንገድ ሊጥለው ግዴታ አለብን። የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ ነው። ስለዚህ፤ የታጠቀ አመፅ ለሚያስፈራችሁ፤ አትፍሩ፤ ኢትዮጵያዊና መላ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚሉ ኢትዮጵያዊያንን ያካተተ ስለሚሆን፤ መቼ ደርሶ በሉ! በነገራችን ላይ ስለትግሉ ጥቅል መልክ ለመሥጠት እንጂ ዝርዝሩን በሚመለከት ገና አልጀመርኩም።

የመጀመሪያው ደረጃ ትግል ዝርዝር፤

እንዲህ ነው። ኢትዮጵያዊያን ለሕልውናችን የምናደርገው ትግል አንድ አጀንዳ፣ አንድ መልክ፣ አንድ ማዕከልና አንድ ግብ  ብቻ ነው ሊኖረው የሚገባ። የተለያዩ ማዕከሎች ካሉት፤ ሌላ ትግል በመካከላችን እያዘጋጀን ነው ማለት ነው። አንድ ማዕከል ካላደረግን፤ ተጠፋፊዎች የሆኑ አካላት በመካከላችን አሉ ማለት ነው። ከሁለተኛው ደረጃ ከመድረሳችን በፊት መጠፋፋት ያለብን ክፍሎች አለን ማለት ነው። ይሄ ከታወቀ፤ አጥፊና ጠፊ ባንድ ስለማንሠለፍ፤ ሠፈራችንን ካሁኑ ለይተን መደራጀት አለብን። በዚህ የሕልውና ትግል አንድ ማዕከል ብቻ ሳይሆን አንድ ድርጅት ብቻ እንዲኖር ግዴታ አለ የሚል ነው እምነቴ። ለምን ቢባል፤ የዝንጀሮ መጀመሪያ መቀመጫዬን ነውና! መለያየታችን በሀገር ሕልውና ከሆነ ካሁኑ እንጠፋፋ። የምንለያየው በዴሞክራሲያዊ እምነታችን የመፍትሔ መንገድ ከሆነ በኋላ ከሕዝብ ፊት ስንቀረብ ፈራጁ ስለሚያስተናግደን፤ ቅደም ተከተላችንን እንወቅ። ትግላችን ኢትዮጵያ ሀገራችን ናት ብለን ነው። ትግላችን ኢትዮጵያዊያን ነን ብለን ነው። ትግላችን የሕግ የበላይነት በሀገራችን ይኑር ብለን ነው። ትግላችን የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊ መብት በትክክል ይከበር ብለን ነው። ትግላችን የሀገራችን ዳር ደንበር ይጠበቅና ይከበር ብለን ነው። ትግላችን የኢትዮጵያዊያን አንድነት ይኑር ብለን ነው። ትግላችን ለዚህ ሁሉ ስኬት የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ተወግዶ የኢትዮጵያዊያን መንግሥት ይቋቋም ብለን ነው። በዚህና ለዚህ የምንሰባሰበው ደግሞ፤ እያንዳንዳችን በየኪሶቻችን በያዝናቸው ዘውዶች ልክ የተሰፋ ድርጅት ይዘን በመሰለፍ አይደለም። የግድ አንድና አንድ ድርጅት ብቻ ይዘን ነው። ለዚህ ትግላችን ከአንድ በላይ ድርጅት አፍራሽ ነው። ለምን? ከላይ የተዘረዘሩትን የትግል ዕሴቶቻችንን በአንድ ድርጅት ለማሳካት መነሳት አለብን። ከነዚህ አንዷንም አልቀበልም ያለ የትግሉ አካል አይሆንም። በእርግጥ መጨመር ይቻላል፤ ቁም ነገሩ ግን ሁላችንን የሚያስማሙ መሠረታዊ የትግል ዕሴቶችን በመለየት ላይ ነው። በነዚህ ላይ እንስማማለን የሚል እምነት አለኝ።

የሕልውና ጥያቄ ያለው አንድ መልስ ብቻ ነው። መኖር ወይንም አለመኖር። መኖር ደግሞ አንድ ሕይወት ነው ያለው። የኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ መኖር አንድ ነው። የኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ መኖር ሁለትና ሶስት የለውም። አለን ወይንም የለንም ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ አለች ወይንም የለችም ነው። እንድንኖር ደግሞ በአንድነት አለን ለማለት እንድንችል በአንድነት መሠለፍ አለብን። የአኗኗራችንን ሁኔታ፤ ሕይወታችንን ስናረጋግጥ እንነጋገርበታለን። መጀመሪያ ግን ሕልውናችንን እናረጋግጥ። ይህ ማለት ደግሞ፤ ለሕልውናችን አንድ ሆነን በአንድነት እንታገል ማለት ነው። ታዲያ ሁለትና ሶስት ድርጅቶች፣ ሁለትና ሶስት ማዕከሎች፣ ሁለትና ሶስት የአመራር መዋቅሮች ተልዕኳቸው ምንድን ነው? በእርግጥ ይኼ ቀላልና ግልፅ በሆነ መንገድ ስንመለከተው ነው። ለአንዳንዶች የነበራቸው ታሪክ፣ የከፈሉት መስዋዕትነትና የድርጅታቸው ጥንካሬ እየጎተታቸው ይኼንን መቀበል ይገዳቸዋል። ቁም ነገሩ ግን፤ የተዋደቁለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነቱን አግኝቶ የራሱ ምርጫ እንዲኖረው እንጂ፤ የነሱ ድርጅት የግድ የበላይ ሆኖ ገዢ እንዲሆን አልነበረምም፤ አይደለምም። እንግዲህ እዚህ ላይ፤ በትክክለኛ መንገድ ድርጅታቸውን የትግል መሣሪያ አድርገው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታግለውበታል ከሚለው ቅን አስተሳሰብ በመነሳት ነው። በያዙት ርዕዩተ ዓላማ ጠንካራ እምነት ካላቸው፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እምነት ካላቸው፣ ያደረጉት ተጋድሎ የሕዝብ ነው ብለው ካመኑ፤ የድርጅታቸውን ጉዳይ በሁለተኛው የትግል ደረጃ ለማምጣት የሚያግዳቸው የለም። በሌላ በኩል ደግሞ፤ አባሎቻቸው በድርጅቶቻቸውና በርዕዩተ ዓለሞቻቸው ሙሉ እምነት ያላቸው ከሆኑ፤ ድርጅቱ በሰዓቱና በቦታው ሲመሠረት መምጣታቸው አይቀርም። አለያ ፍርሃት አለ ማለት ነው! ያንን ራሳቸው ይመርምሩ። በብልጠት ቦታ መያዣ አድርገው፣ ካሁኑ መረቦቻቸውን ዘርግተው፣ ድርጅታቸውን አጠናክረው፣ የተጠራቀመ ድልብ ሆነው ለሥልጣን ከሆነ ድርጅታቸውን የሚፈልፉት የሕዝብ ክፍል ለመሆናቸው ጥርጣሬ እንዳሳድር ያደርገኛል። ትግሉ ሕዝቡን የሥልጣኑ ባለቤት ለማድረግ እስከሆነ ድረስ፤ ቅንነት፣ ቆራጥነት፣ መስዋዕትነት፣ እና ከራስ ወዳድነት የራቀ ኢትዮጵያዊነት ነው የሚጠበቀው ከታጋዮች። በተለይም የተሰው ታጋዮችን የትግል ፍሬ መቁጠር ያለብን በሕዝቡ የሥልጣኑ ባለቤትነት መሆን አለበት።

ከዚህ ወዴት?

ከዚህ በላይ በሠፈሩት ከተስማማን፤ መስማማታችንን መጀመሪያ ማስመር ግድ ነው፤ ቀጥሎ ምን ይደረግ ወደሚለው እንሄዳለን። ነገር ግን፤ ከላይ የሠፈረው ቀላልና እንዲያው ባድ ሰው ጽሑፍ ወይንም ባንድ ምሽት የሚካተት ስላልሆነ፤ ሁላችን በያለንበት እንድናብላላውና የየራሳችን የሆነ አቋም ወስደን እንድንወያይ፤ ጊዜ መሥጠት እፈልጋለሁ። ይኼ የኔ የብቻዬ ወይንም የግሌ ጉዳይ አይደለም። ጉዳዩ የሀገራችንና የሁላችን ነው። ያቀረብኩት የራሴን አቋም ነው። ከኔው የተሻለ ሃሳብ ሊኖር ይችላል። ጥሩ የሚሆነው፤ የለም እንዲያ አይደለም፤ ተሳስተሃል ተብዬ የናንተን ደግሞ ባዳምጥ ስለሆነ፤ ተነጋገሩበት። የሀገር ጉዳይ በአደባባይ እንዲህ ወጥቶ ብንነጋገርበት፤ ወደ ጥሩ መፍትሔ አንሄዳለን። ከዚህ ወዴት? የሚለውን በሚቀጥለው አራተኛውና የመጨረሻው ክፍል አቀርባለሁ። (ክፍል አራት – የመጨረሻው ይቀጥላል)

 golgul.com

Obang Metho’s Testimony before the Subcommittee on Africa

Testimony before the Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights and International Organizations. Given by: Mr. Obang O. Metho, Executive Director Solidarity Movement for a New Ethiopia

“Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights”

I would like to thank the Chairman of the Committee on Foreign Affairs, Congressman Edward Royce, and all ranking members of the Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights and International Organizations for this important opportunity to examine the Ethiopian Government’s observance of democratic and human rights principles in post-Meles Ethiopia.

I want to especially thank Congressman Christopher Smith, the Chairman of the Subcommittee on Africa for his extraordinary leadership in bringing the case of Ethiopia to the attention of this subcommittee once again; particularly in light of the many pressing global issues. In 2006, Congressman Smith worked hard to bring this issue all the way from subcommittee to the House, where it faced obstacles and died. I hope this time, something more concrete and productive can be accomplished for the betterment of both our countries.

In 2006, I gave testimony at that previous hearing in regards to the massacre of 424 members of my own ethnic group, the Anuak, in 2003, perpetrated by members of the Ethiopian National Defense Forces. I also testified regarding the ongoing crimes against humanity and destruction of property and infrastructure in the Gambella region of Ethiopia; however, because similar abuses were being perpetrated in other places in the country, I also spoke of the 193 peaceful protestors who were shot and killed as they peacefully protested the results of the flawed 2005 national election and the repression in Oromia. This also included testimony regarding the imprisonment of opposition leaders, including Dr. Berhana Nega, who is sitting next to me today.

Now I am here once again to testify about these same kinds of issues because Ethiopians have only seen increasing restrictions to their freedom and a continuation of government-sponsored human rights violations in every region of the country. This includes the illegal eviction of great numbers of Ethiopians from their ancestral homes and land, causing great hardship to the people. It also includes egregious human rights atrocities in places like the Ogaden [Somali] region, which is blocked from the outside world by the regime. It has obstructed the media from reporting on the great suffering of the people being perpetrated by government forces, which has been described as a silent genocide. Two Swedish journalists were arrested, detained and charged as terrorists before being released last year.  However, the Ogaden is not alone for every region of the country has become a victim to this regime.

Sadly, little, in terms of rights, has changed post-Meles. The only change is that he is no longer here.  Although the rapid decline in freedom and rights was led by Meles, he and his cabinet and ministers established an apparatus of strong-armed control that continues to reach from the top offices of the federal government to rural villages throughout Ethiopia. That infrastructure of repression, which carries out much of the day-to-day enforcement of EPRDF control and the perpetration of human rights violations, is still in place and marks the near achievement of a secretive and chilling plan put into motion in June 1993 under the name: TPLF/EPRDF’s Strategies for Establishing its Hegemony & Perpetuating its Rule[i]which was said to have been given to all their cadres for its execution. An abridged translation of the 68-page Amharic document is now available online.

This plan, based on Marxist ideology, was brought to our attention by one of the members of the TPLF who reported to us strict adherence to this plan by its cadres. The plan aligns closely with the nature of the TPLF when they were still fighting in the bush as well as the Ethiopia of today.

Prior to defeating the brutal Derg regime in 1991, Meles led the Marxist-Leninist based rebel group, the Tigrayan Peoples Liberation Front (TPLF), also so known for its brutality in the bush that the U.S. State Department had classified them as a terrorist group at the time.When they took over power, they formed a new coalition party made up of separate ethnic-based parties. It was called the Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF) and was meant to appear to be a multi-ethnic government but in fact, it has been controlled from the beginning by the TPLF who have never abandoned the goal of perpetual hegemony.

The EPRDF’s structure was based around ethnically defined regions and political parties, but at the grassroots level, all regions and parties, though appearing to be led by leaders of the same ethnicity as the region, were instead pro-TPLF/ERPDF puppets, who implemented their policies. By its nature, this division of Ethiopia by ethnicity was a guise meant to dupe the public and the west by its appearance of being democratic; however, in practice, it has contributed to the prolongation of ethnic-based divisions while strengthening the power of the TPLF, assuring its control of the EPRDF even though Tigrayans are a minority, making up only 6% of the total population. However, this does not mean the TPLF speaks for many Tigrayans who have become disillusioned with the TPLF/EPRDF. 

In short, the TPLF’s plan of revolutionary democracy, which is more closely aligned with the Chinese model than the liberalism of the west, was clearly designed to achieve perpetual hegemony over every aspect of Ethiopian life. In the above-stated plan, they warn that they can achieve their goals “only by winning the elections successively and holding power without let up.” They warn, “If we lose in the elections even once, we will encounter a great danger… [so] we should win in the initial elections and then create a conducive situation that will ensure the establishment of this hegemony.” In 2010, the TPLF/ERPDF successfully accomplished this goal and won their fourth election with an alleged 99.6% of the votes and all but one of the 547 seats in the Ethiopian Parliament.

This also was accomplished through gaining control every sector of society: the media, all aspects of government and civil service, all political space, elections, the judiciary, the passing and interpretation of laws to suit their goals, the financial sector, education, the military, the economic sector, religious groups, civic society, government ownership of all land and government control in the extraction of natural resources. The principles upon which America was founded are absent in Ethiopia despite all the democratic rhetoric.

The TPLF/EPRDF is more in control today than it was in 2006 and continues to hold that power despite the death of their central figure. It has become near to impossible to find any political space for the development of a viable alternative to the TPLF/EPRDF because dissenters, activists or anyone speaking for change will be put in jail. It has become a full-blown autocracy. Anyone who attempts to speak up is silenced. All has been justified by saying that Ethiopia has double digit economic growth and that they have met their millennium goals and that the people are too ignorant to understand how they will eventually benefit; however, the people know that this is not balanced growth but instead has “filled the pockets and bellies” of government supporters as laid out in the 1993 plan. Claims of economic gains also serve to minimize or cover up the reality on the ground of the increased poverty of the majority.  Supporters of the TPLF/EPRDF policies and tactics are rewarded while non-supporters are penalized in a variety of ways. The most marginalized masses are ignored unless they become an impediment to the TPLF/ERPDF plan of exploitation of land or natural resources. Here is an explanation of that strategy from the original TPLF/ERPDF plan:

The combined strength of the State and Revolutionary Democracy’s economic institutions should be used either to attract the support or to neutralize the opposition of the intelligentsia.  We should demonstrate to it that our economic strength could serve its interests, and, in the event of its opposition to us, its belly and pocket could be made empty.

Examples of the practice of the above strategy are rampant. According to a Human Rights Watch[ii] report, following the 2010 election, even humanitarian aid was linked to party membership.

Record numbers of refugees are leaving the country, regardless of the risks, because so little opportunity exists for the average person, let alone for more outspoken dissenters. Laws such as the Charities and Societies Proclamation[iii] have literally closed down civil society, replacing institutions with TPLF/ERPDF controlled look-alike organizations. A vague anti-terrorism law[iv] has been used to silence journalists, editors, democracy activists, religious leaders and opposition members by intimidating them, arresting them or charging and imprisoning them as terrorists. Examples are our heroes of freedom such as Eskinder Nega, Reeyot Alemu and Andualem Arage.

Into this highly controlled milieu, the new Prime Minister, Hailemariam Desalegn, has emerged. He is neither Tigrayan nor is he part of the old guard of TPLF loyalists but instead comes from the South, helping to counter accusations of TPLF domination of the EPRDF. Reportedly, his appointment was hotly contested; however, because he had held the position of Deputy Prime Minister it may have provided the least controversial transition. Insider information reports he has little power and that his actions are all closely monitored by the TPLF central committee. As another means of control, three deputy prime ministers of different ethnicity were appointed and are said to hold more power than the prime minister.  Reports have also surfaced that power struggles within the party leadership have split the top power holders and remain unresolved. These intraparty conflicts could deepen as the next election comes closer, with unpredictable, but possibly dangerous results. Hoping that this problem will resolve on its own is unrealistic and a recipe for disaster.

The TPLF/ERPDF has so effectively constructed a system of repression in Ethiopia that it will likely carry on for awhile; however Meles, the driving force who charmed the west while terrorizing the people, remains their main visionary leader. Billboards around Addis Ababa show his picture and the TPLF/ERPDF continues to elevate his legacy, possibly because no one else within the party has been able to articulate another, more timely or urgently-needed vision. This opens them up to new challenges from the dissatisfied majority that they may not be able to dodge. Intraparty conflicts may also further exacerbate the situation. Add to that pressure from the outside, like from Egypt, neighboring countries or others and the situation may either explode or implode without reforms. Although the TPLF/EPRDF has shown little openness to reforms, with enough pressure from the people and donors like the U.S., it might create a win-win situation to bring about such reforms without violence, chaos and a spillover effect in the Horn of Africa.

The road to democracy and respect for human rights in Ethiopia must be solved by Ethiopians, but the U.S. has a role to play as well. I believe the current U.S. policy of quiet diplomacy will actually contribute to a worse outcome. We should learn from what happened in the Arab Spring, when forces of a frustrated public joined together to oust Egyptian President Hosni Mubarak. It took many by surprise, especially those who had sided with an authoritarian regime rather than the people, thinking Mubarak was so powerful that he could not be brought down. This alliance with an authoritarian regime makes it much more difficult in the aftermath to reestablish a meaningful partnership with Egyptians that goes beyond giving large amounts of foreign aid.

Undoubtedly, many Ethiopians attribute U.S. support to Ethiopia, including partnership in the War on Terror, as a means that has prolonged the life of a repressive, undemocratic regime. Will the U.S. be pro-active in aligning with the people; something that will help sustain a long-term relationship with Ethiopians? Unfortunately, the tendency of most entrenched groups and their supporters, foreign or native, is to continue the status quo without any change; however, in Ethiopia, there is a window of opportunity before the next election in 2015 to set the stage for meaningful reforms. The U.S. and other donor countries should not simply stand by, using the rationale that there is no viable alternative to work with because the TPLF/ERPDF has been so effective in blocking access to political space and will not easily give up on this.  This must be taken into consideration for how can you build an alternative in this kind of repressive environment? You cannot put someone out in the middle of nowhere with no material and tell them to build something. It will not work.

With these limitations in mind, the Ethiopian public, both at home and in the Diaspora, are now working to bring the change. Some of that change can be seen from what happened last week in Addis Ababa when Ethiopians came out in mass numbers to peacefully rally for freedom and justice in Ethiopia based on a call from the newly emerging Blue party. With minimal resources, the Blue party reached out to the public in an inclusive way and the groundswell of response from ethnically, politically and religiously diverse Ethiopians surprised even them. They called on the people and the people answered. Yet, the TPLF/ERPDF warned that Muslims who joined together with Christians and others in the rally were extremists.  This defies the reality on the ground.

For the last year, Ethiopian Muslims have been peacefully rallying in their compound, asking for freedom to practice religion without government interference into their internal affairs. In violation of the Ethiopian Constitution, the TPLF/ERPDF has been choosing their religious leaders, ensuring those leaders were pro-government. The TPLF/ERPDF has done the same within the Ethiopian Orthodox Church leading to the church breaking into two divisions—the government approved church in Ethiopia and the other in exile here in the U.S. – a divide and conquer strategy of gaining hegemony of religious groups addressed in the TPLF/EPRDF master plan of 1993. Within that plan, religious groups were to be “used to disseminate the views of Revolutionary Democracy…and if that is not possible we should try to curtail their obstructionist activities…Without denying them due respect, we should mold their views, curtail their propaganda against Revolutionary Democracy, and even use them to serve our end.”

The TPLF/ERPDF government will do anything to label the Muslims as extremists and radicals to be feared by the west; however, Ethiopian Muslims, Christians and Jews have lived together for thousands of years in harmony. We do not only share the land but we share blood. We are a family. We are brothers and sisters.

In twelve months of rallying, these peaceful Muslim protestors have never destroyed anything or hurt another person. They are not making a stand for Sharia law but instead for a secular state where all people will be free and where there is no government interference in the practice of any religion. Yet, the TPLF/EPRDF fears unity between diverse religious groups. 

Reports have emerged of the TPLF/ERPDF’s intentions to divide people of different religious faith and to alarm the west by staging events themselves while blaming others. For example, inside reports allege that when Ethiopian Muslims were going to rally in front of the U.S. Embassy, they found out that pro-government forces were going to burn the American flag so they called off the entire rally. An eyewitness to the killing of Christians in 2007, reported to be by Muslims in the Oromo region of the country, were recognized by a relative to not be Muslims at all but government supporters.

I personally spoke to that survivor. It preceded the invasion into Somalia and is seen as an attempt to dupe the west. It must be understood that it profits this regime to do violence in the name of their opponents. Here is another example reported in Wikileaks where the U.S. had knowledge that the TPLF/ERPDF government had set the bombs in Addis Ababa several years ago so as scapegoat government opponents. They used it to justify the arrest of Oromo leaders as terrorists and to show a rising incidence of terrorist acts in Ethiopia, even though it was phony. Duping the west into supporting the TPLF/ERPDF was part of their original strategy laid out in the 1993 plan and is part of the reason for becoming a pseudo-democracy.

Division between ethnicities, regions, political parties and religious groups is the lifeblood of the TPLF/ERPDF. For the government to gain power and control, they are trying to alienate the people from each other and spread rumors regarding the makeup of those who are protesting. Just as they are calling Muslims extremists and terrorists, they are now trying to label the Blue party, to separate them from others, by accusing them of being funded by foreigners like Egypt. The fact that Christians and Muslims are rallying together for freedom and justice for all Ethiopians is a real threat to their existence. These kinds of tactics by the government are a sign that the status quo cannot continue and will be challenged in increasing unity among Ethiopians. The donor countries, including the US, should align with the people. This means supporting the people who are working from within and those who are trying to resolve the problem peacefully, without violence.

The proper sequence of reforms is critical to the success of the outcome.

 1. 1.      Intellectual reform must come first, which means the people must have access to information and have the freedom to express it—the first freedom to be attacked by dictatorships and the first that needs to be restored to bring about change.
 2. 2.      The second must be political reform; opening up political space so the choice of the people is reinstated. Then they are free to choose political leaders and groups who represent their interests and the interests of the country. 
 3. 3.      The third is constitutional reform which must rewrite, redefine or reinstate the most inclusive and beneficial relationship between the people and the state in the form of this “constitutional contract”; a contract which upholds the rights of the people and protects the people from the state, similar to African models where it is assumed anyone can become tyrannical so checks and balances must be established to control the power of the government, ensuring participatory democracy. 
 4. 4.      The fourth is institutional reform; meaning reforms of the judiciary, the parliament, the military, civil services, and other institutions where regime cronies are now in control.  Institutions must be independent of the state or party for change to be accomplished and made sustainable. 
 5. Lastly, economic reforms are necessary but will not be inclusive until the other reforms are implemented, making the system more transparent, accountable, and just; unlike in places like Russia, Ivory Coast, Indonesia, Yugoslavia, Cameroon, Rwanda and the Philippines where economic advances were made; yet, regime cronies still controlled the institutions, the political system and the justice system, staging the conditions for a reversal of power and the re-emergence of repression and cronyism.

Poverty and corruption in Ethiopia will also increase the pressure for explosion. Recently, Kofi Annan spoke about the cost of corruption to the African people.  Ethiopia is a primary example.  Although many quote statistics of economic growth in Ethiopia, most of it is in the hands of a few.  Prior to the release of the report by the Global Financial Task Force in their report titled: Illicit Financial Outflows from Developing Countries Over the Decade Ending in 2009, they stated on December 5, 2011 the following in regards to Ethiopia:

“The people of Ethiopia are being bled dry. No matter how hard they try to fight their way out of absolute destitution and poverty, they will be swimming upstream against the current of illicit capital leakage.”[v]

Their report reveals that Ethiopia lost US11.7 billion in illegal capital flight from 2000-2009 and illicit financial outflows from Ethiopia nearly doubled in 2009 to US$3.26 billion—double the amount in the two preceding years—with the vast majority of that increase coming from corruption, kickbacks and bribery. When it comes to transparency, it does not exist in Ethiopia.

Here is another example.  Human Rights Watch found evidence that World Bank money, which was to be used for services, was instead used by the government to displace the people from their land, later given to foreign and crony investors. Five villages in the Gambella region, hard hit with land grabs, accompanied by human rights violations, made an appeal to the World Bank regarding the improper use of its funds. An independent inspection panel investigated the grounds for the appeal for the World Bank.  After meeting with the local people who had been displaced to refugee camps in Kenya and South Sudan, they recommended a full investigation after finding substantial evidence of the misuse of World Bank funds. Now the Ethiopian government has refused to cooperate. All donors to the World Bank should look into this because this is your money. If they have nothing to hide, why would they not allow an investigation?

People on the ground in Ethiopia live in fear of this regime, but many are coming to the point that they can no longer endure life without change and are willing to take a stand.  Prior to the Blue party’s recent rally, a 26-year-old recent graduate sent me his thoughts.  He said:

Obang, it is now just four hours before we go out to rally.  We don’t know what will happen but this may be my last message because the last time I went out I went with three of my friends and I was the only one who came back.  That was seven years ago after the 2005 election. I may be the one not come back this time but I am not afraid. I am looking at it like going into a war zone, but the only difference is the other side has a gun and we have nothing.  If they shoot, I have nothing to deliver. This is the kind of country we live in.  But, we have the moral high ground and this is what is making me go out. I want someone to know.

Ethiopia is a country which relies on the US as its number one supporter and here is one of their brave, but peace-loving heroes, going out not knowing what will happen to him and those with him. Most of you have met Ethiopians here in Washington D.C. as thousands of Ethiopians live and work in this city. They pay taxes to the same government that for too long has overlooked the serial violations of human rights and the emergence of a full-blown dictatorship.

Ethiopians have struggled under dictatorship for 40 years. With the death of Meles and the appointment of Prime Minister Hailemariam Desalegn until the next election in 2015,Ethiopians may have been given the most opportune moment in 21 years for change; however, if Ethiopians—or donor countries genuinely wanting to see democratic reforms—step back, waiting to see what will happen under this new arrangement of power, rather than actively creating a process of change that is owned and managed by the people of Ethiopia, this opportunity will most likely be hijacked and the “system” of repression will continue with the same or new “strongmen” at the helm.  The only acceptable outcome for the Ethiopian people is nothing short of the transformation of Ethiopia to a new society and a New Ethiopia where humanity comes before ethnicity or any other distinctions for no one is free until all are free!

This is a time when the U.S. should use their influence to put pressure on the Ethiopian government for reforms rather than waiting for simmering tensions to explode.  Support for a people-driven process is the best alternative to bring lasting change to Ethiopia, more sustainable peace to the Horn and a better ongoing partnership with the US.

Thank you!

ecadf.com

የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት ግብጽ እና ለስልጣን ጸብ ጫሪው ህውሃት!

(ግርማ ሞገስ)

nile dam

June 20, 2013 06:39 am By  Leave a Comment

የአባይ ጉዳይ ለግብጽ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው። ዛፍ ላይ ሆነህ እንቅልፍ ይወስድሃል? ሸለብ እንኳን ያደርግሻል ዛፍ ላይ ሆነሽ? እነደዚያ ነው የአባይ ጉዳይ ለግብጽ። ይኽ እንቅልፍ ማጣት እና ስጋት ዛሬ የጀመረ አይደለም። ባጭሩ ልተርክ። ሪቻርድ ፓንክረስት በግብጽ የተገኙ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ክርስቶስ ከመወለዱ ከ3 ሺ አመቶች በፊት ጀመሮ የግብጽ ነጋዴዎች በእግራቸው የአባይን ወንዝ ዳርቻ ተከትለው እንዲሁም በቀይ ባህር በነፋስ በሚገፉ ጀልባዎች ዛሬ ኢትዮጵያ (ያኔ የፐንት ግዛት) በሚባለው ግዛት ውስጥ ከሚኖረው ህዝብ ጋር የንግድ ልውውጥ ማድረጋቸውን እና ግዛቱን ምድረ ታ-ኔትጄሩ (Land Ta-Netjeru) ማለትም “ምድረ አማልዕክት” እንደሚሉት እና “የመጀመሪያ አገራችን ነው” ይሉም እንደነበር የኢትዮጵያውያን ድንበር-መሬቶች (The Ethiopian Borderlands) በሚለው መጽሐፉ ዘርዘር አድርጎ ጽፏል። የቅርቡን ብንመለከት ደግሞ በተለይ ከ1813 ዓ. ም. ጀመሮ ግብጽ የኢትዮጵያ ባለቤትነቷን በጦርነት ለማረጋገጥ የዮሐንስን ኢትዮጵያ ከሱዳን ቀላቅላ ለመግዛት በአራት አቅጣጫዎች ወረራዎች ከፍታ ሳይሳካለት ወደ መጣችበት መመለሷን ተክለ ጻዲቅ መኩሪያ “ዐፄ ዮሐንስ እና የኢትዮጵያ አንድነት በሚለው መጽሐፉ በሰፊው ተርኳል። በኃይለስላሴ እና በደርግ ዘመንም ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የጦር መሳሪያ እና ስልጠና በማቀነባበር፣ ገንዘብ በመለገስ፣ በመካከለኛው ምስራቅ አረብ አገሮችን በማስተባበር፣ የአማርኛ ስርጭት ሬዲዮ በመክፈት ድጋፍ ማድረጓን እናውቃለን። ህውሃት ከተጠቃሚዎቹ ተቃዋሚዎች ውስጥ አንዱ ነው። በአባይ ጉዳይ ከጥንት ጀምሮ ግብጽ ከስጋት ነፃ የሆነ እንቅልፍ የለታም። ዛሬም ሆነ ወደፊት ግብጽ የሰላሙን መንገድ ትታ የጸበኛነቱን መንገድ ከመረጠች እንቅልፍ አይኖራትም። ይኽን የግብጽ ጭነቀት እና ስጋት ህውሃት ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ ግንቦት 20 ቀን ጸብ ጫረ። ላብራራ።

የጥናቱን ውጤት ተቀበለችውም አልተቀበለችው ስለ አባይ ጉዳይ በጥናት ላይ የተሰማራው ኤክስፐርቶች ቡድን ሪፖርት እየጠበቀች ሳለች ድንገት ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ. ም. ህውሃት የአባይ ወንዝ የፍሰት አቅጣጫ መቀየሩን ሰበር ዜና ተሰራጨ። የኢትዮጵያ ሽብርተኛው ኢ.ት.ቭ. አስተጋባ። ዜናው ግብጽ ደረሰ። ከጥንት ጀምሮ የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት ግብጽ ተደናገጠች። አምባገነኑ ሞርሲ ከገበባት የውስጥ ችግር ለማምለጥ የህውሃትን ቁስቆሳ ተጠቀመ። አካራሪ የግብጽ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ጋበዞ ‘እኔ ሳልሞት ግብጽ አትጠማም’ አለ። ያጀቡት አክራሪዎችም ‘ግፋ’፣ ‘በርታ’፣ ‘አይዞህ ከጎንህ ነን’ አሉት። ይኽ  ምክክራቸው ዜና ሆኖ አደባባይ ወጣ። ህውሃት ሁካታውን ያልጫረ መስሎ ለኢትዮጵያ ህዝብ ግብጽ ልትወጋህ ነው የሚል ፕሮፖጋንዳ ጀመረ። የቀድሞ አባቶቻችን ድሎች ሳይቀሩ እየተጠቀሱ የቀረርቶ ድምጽ በአዲስ አበባ እየጎላ መጣ። አልባራዳይን የመሰሉት የግብጽ ዴሞክራሲ ኃይሎች የግብጽን መንግስት ወቀሱ። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎችም ቀረርቶው ገደብ ይበጅለት አሉ። የኢትዮ-ግብጽ የጦርነት ሁካታ አነሳሱ ይኽን ይመስል ነበር። ህውሃት የማያስፈልግ ጸብ ጭሯል።

ለመሆኑ ለምን የአባይ ወንዝ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን ተቀየረ? ዜናውስ ለምን ግንቦት 20 ቀን አደባባይ ወጣ? ለዚኽ ጥያቄ አቶ በረከት ስሞዖን ሰኔ 7 ቀን ግድም 2005 የሰጠውን መግለጫ እንመልከት፥ የአባይ ወንዝ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን የተቀየረው በአጋጣሚ እንጂ ህውሃት ሰልጣን ከጨበጠበት ቀን ጋር እንዲገጣጠም ሆን ተብሎ የተደረገ እንዳልሆነ ሊያስተባብል ሞክሯል። ይኽ የበረከት ስሞዖን ማስተባበያ በሽብርተኛው ኢ.ቲ.ቭ. እና በኢሳት ተዘግቧል። የአቶ በረከትን መቀላመድ ወደ ጎን አድርገን እውነቱን ሃቁን እንመልከት። የአባይ ወንዝ ፍሳሽ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን እንዲቀየር ያስደረገው ህውሃት ነው። ዜናው ግብጽ እንዲደርስ ያደረገውም ህውሃት ነው። ግቡም ስልጣን ነው። ላብራራ!

1ኛ) የተለየ አሳቢ እና ከድኽነት ነፃ አውጪህ እኔ ህውሃት ነኝ የሚል መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተላለፍ እንዲችል ሆን ብሎ የአባይ ፍሳሽ የተቀየረበትን ቀን ስልጣን ከጨበጠበት ግንቦት 20 ቀን ጋር አገጣጠመው። የዚኽ እርምጃ ፖለቲካዊ ግብ ህዝቡ እንዲያመልክበት እና ስልጣኑ እንዲጠናከር ነው። ግድብ መገንባት አይደለም ግቡ።

2ኛ) የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ለሆነባት ግብጽ የአባይ ፍሳሽ አቅጣጫ መቀየር ዜና የጦርነት ፖለቲካ ውስጥ እንደሚያስገባት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በምላሹ የኢትዮጵያን ህዝብ በአገር ወዳድነት ስሜት አሳውሮ በሚፈልገው የፖለቲካ አቅጣጫ ለማስጓዝ አስልቶ ነበር። የዚኽም ፖለቲካ ስሌት ግቡ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ ኃይሎች ለመምታት እና ስልጣኑን ለማጠናከር ነበር። በአገር ከሃዲነት እና በሽብርተኛነት ሽፋን። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች ፈጥነው ስላጋለጡት የኢትዮጵያን ህዝብ በአባይ ስሜት አሳውሮ የዴሞክራሲ ኃይሉን ለመምታት የሚያስችለው ጊዜ ሳያገኝ ቀረ። ከሸፈበት።

ግርማ ሞገስ

ግርማ ሞገስ

ህውሃት ከግድቡ ይልቅ ስልጣኑ እንደሚበልጥበት ለአንዲት ደቂቃ እንኳን መዘንጋት አያስፈልግም። ወደፊትም ሌሎች ጸቦች ሊጭር እና ከዚያ ግብጽ ልትወጋን ነው ይልሃል። የዴሞክራሲ ኃይሎች የነፃነት ሰላማዊ ትግላቸውን አጠናክረው በመቀጠል እራሳቸውን ከህውሃት ማጭበርበር እና ጥቃት መጠበቅ አለባቸው።

(girmamoges1@gmail.com)

ወያኔ የፈጠረዉ የፍርሀት ድባብ ሲሰበር . . .

በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚደርሰዉ በደልና መከራ ወለደን ብለዉ ለትግል ጫካ የገቡት ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዉ ከተደላደሉ በኋላ በህዝብ መብትና ነጻነት፤ በአገር አንድነትና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ብሄራዊ ጥቆሞች ላይ ይህ ነዉ ተብሎ ሊነገር የማይችልና ከእነሱ በፊት ከነበሩት መንግስታት ጋር ሲተያይ እጅግ በጣም የከፋ በደል ፈጽመዋል እየፈጸሙም ይገኛሉ። ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዉ የኢትዮጵያን መንበረ ስልጣን ከመቆጣጠራቸዉ በፊት ዕቅድ አዉጥተዉና ተዘጋጅተዉ የመጡት የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፤ በሐይማኖትና በክልል በመከፋፈል በጠመንጃ ኃይል የያዙት ስልጣን በግዜና በህገመንግስት ያልተገደበ መሆኑን ለማረጋገጥና የእኛ ነዉ ለሚሉት የህብረሰተብ ክፍልና ለሚተባበሯቸዉ ሆዳሞች ተቆጥሮ የማያልቅ ሀብት ማጋበስ የሚችሉበትን መንገድ ለመፍጠር ነዉ። የወያኔ መሪዎች ይህንን አገራዊ በደል ያለምንም ተቃዉሞ መፈጸም እንዲችሉ ከአገሩ ይልቅ የተወለደበትን ክልል ብቻ፤ ከብሔራዊ አንድነቱና አጋራዊ ጥቅሙ ይልቅ የራሱን ጥቅም ብቻ የሚመለከትና የእነሱን ኃይለኝነትና የተለየ ጀግንነት እየሰበከ የሚኖር በፍርሀት የተሸበበ ፈሪ ትዉልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

የወያኔ ክፋት፤ ዘረኝነትና “ልማት” በሚል ሽፋን የተደበቀ አገር የማፍረስ ሴራ ከወዲሁ የገባቸዉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ልጆች ከ1997ቱ ምርጫ በፊትም ሆነ በኋላ የወያኔን ገመና ለማጋለጥና የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ፤ ለነጻነቱና ለእኩልነቱ እንዲታገል ለማድረግ እንደሻማ እየቀለጡ ብርሀን ሆነዉ አልፈዋል። ይህ የዕልፍ አዕላፋት የትግል መስዋእትነትና ምሳሌነት ፍሬ እያፈራ መጥቶ በላፈዉ እሁድ ግንቦት 25 ቀን የተካሄደዉንና ወያኔ ከሃያ አመታት በላይ ሲቋጥር የከረመዉን የፍርሀት መቀነት የበጠሰ እጅግ በጣም የሚያበረታታ ትዕይንተ ህዝብ እንዲደረግ አስተዋጽኦ እድርጓል፡፡ ይህ ባለፈዉ እሁድ የተካሄደዉ ሰላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስተባብሩት፤ አቅጣጫ የሚያሳዩትና ጉያዉ ዉስጥ ገብተዉ እያበረታቱ የሚመሩት መሪዎችን ካገኘ እንኳን ምንም አይነት ህዝባዊ መሠረት የሌለዉን ወያኔን የመሰለ ፀረ ህዝብ ሃይል ቀርቶ ለማንም የማይበገር ህዝብ መሆኑን ያስመሰከረ ሰልፍ ነዉ።

በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራዉና የብዙ ኢትዮጵያዉያንን ይሁንታ ያገኘዉ የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ወያኔ ያስረናል ወይም ይገድለናል እየተባለ አላግባብ እየተፈራ በቀጠሮ ሲተላለፍ የቆየዉን ህዝባዊ ትግል ከፍርሀትና እንደ ገመድ ከረዘመ ቀጠሮ ዉስጥ በጣጥሶ ያወጣና የህዝብን የትግል መንፈስ ያነቃቃ ሰላማዊ ሰልፍ እንደነበር በሰልፉ ላይ የታየዉ የህዝብ ስሜትና ለኢትዮጵያ ህዝብ የተላለፉት መልዕክቶች በግልጽ ይናገራሉ። ባለፈዉ እሁድ በተደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የታየዉ ህዝብዊ መነሳሳት ሊበረታታ የሚገባዉና እንዲሁም በአገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵየዉያን የመብትና የነጻነት ትግላቸዉ አካል አድርገዉ ሊቀላቀሉት፤ ሊረዱት፤ሊተባሩትና ህዝባዊ ትግሉ የሚጠይቁዉን አመራር ሊሰጡት የሚገባ እጅግ በጣም አበራታች ጅምር ነዉ። ለትግልና ለመስዋዕትነት ዝግጁ የሆነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ያጣዉ መሪ ነዉ እያልን አግባብ የሌለዉ ጩከት ከመጮህ ይልቅ አገራችንን የምንወድ የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ መሪዎችን በትግል ሂደት ዉስጥ የምንፈጥረዉ እኛዉ እራሳችን መሆናችንን ተረድተን ይህንን የሚያበረታታ ተስፋ የሰጠንን ሰላማዊ ሰልፍ የምናጠናክርበትንና ተከታታይነት ኖሮት ብዙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያካትትበትን መንገድ ልንቀይስ ይገባል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ቢሆን ለመብቱ፤ለነጻነቱና ለአንድነቱ ማናቸውንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ባለፈዉ እሁድ በግልጽ አሳይቷል። አሁን የሚቀረዉ ህዝባዊ ትግሉን የመምራት ታሪካዊ ሀላፊነት የወደቀበት የህብረተሰብ ክፍል ጨርቄን ማቄን ማለቱን ትቶ ወቅቱ የሚፈልገዉን የትግል አመራር መስጠት ብቻ ነዉ።

ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ አንዴ የታጠቀዉን ጠመንጃ በመጠቀም ሌላ ግዜ ደግሞ ፓርላማዉንና የህግ ተቋሞችን ተጠቅሞ ተቃዋሚ ኃይሎችን የሚያጠፋ ህግ በማዉጣት የኢትዮጵያን ህዝብ የፍትህና የነጻነት ፍላጎት ለማፈን ብዙ ጥሯል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ እራሱን “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ” ትዉልድ ብሎ በመጥራት ህዘብ በፍርሃት ጨለማ ዉስጥ እንዲኖር ለማድረግ ብዙ ታግሏል። ቆራጡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ስድቡን፤ ንቀቱን፤ እስራቱን፤ግድያዉንና ስደቱን እንዳመጣጡ መክቶ በፍርሀት ዉስጥ የማይኖር ህዝብ መሆኑን ባለፈዉ እሁድ ለወዳጁም ለጠላቱም በግልጽ አሳይቷል። ይህ እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓም አዲስ አበባ ዉስጥ የታየዉ የትግል መነሳሳት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በማቀፍ ወያኔና በጠመንጃ ኃይል የመሰረተዉ ዘረኛ ስርአቱ እስከተወገዱና ኢትዮጵያ ፍትህ፤ ነጻነትን ዲሞክራሲ የነገሱባት ምድር እስክትሆን ድረስ መቀጠል ይኖርበታል፤ ይህንን ለማድረግ ደግሞ በአገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ እንደ አንድ ሰዉ ቆሞ መታገል ይኖርበታል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

 

የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት ግብጽ እና ለስልጣን ጸብ ጫሪው ህውሃት!

የአባይ ጉዳይ ለግብጽ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው። ዛፍ ላይ ሆነህ እንቅልፍ ይወስድሃል? ሸለብ እንኳን ያደርግሻል ዛፍ ላይ ሆነሽ? እነደዚያ ነው የአባይ ጉዳይ ለግብጽ። ይኽ እንቅልፍ ማጣት እና ስጋት ዛሬ የጀመረ አይደለም። ባጭሩ ልተርክ። ሪቻርድ ፓንክረስት በግብጽ የተገኙ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ክርስቶስ ከመወለዱ ከ3 ሺ አመቶች በፊት ጀመሮ የግብጽ ነጋዴዎች በእግራቸው የአባይን ወንዝ ዳርቻ ተከትለው እንዲሁም በቀይ ባህር በነፋስ በሚገፉ ጀልባዎች ዛሬ ኢትዮጵያ (ያኔ የፐንት ግዛት) በሚባለው ግዛት ውስጥ ከሚኖረው ህዝብ ጋር የንግድ ልውውጥ ማድረጋቸውን እና ግዛቱን ምድረ ታ-ኔትጄሩ (Land Ta-Netjeru) ማለትም “ምድረ አማልዕክት” እንደሚሉት እና “የመጀመሪያ አገራችን ነው” ይሉም እንደነበር የኢትዮጵያውያን ድንበር-መሬቶች (The Ethiopian Borderlands) በሚለው መጽሐፉ ዘርዘር አድርጎ ጽፏል። የቅርቡን ብንመለከት ደግሞ በተለይ ከ1813 ዓ. ም. ጀመሮ ግብጽ የኢትዮጵያ ባለቤትነቷን በጦርነት ለማረጋገጥ የዮሐንስን ኢትዮጵያ ከሱዳን ቀላቅላ ለመግዛት በአራት አቅጣጫዎች ወረራዎች ከፍታ ሳይሳካለት ወደ መጣችበት መመለሷን ተክለ ጻዲቅ መኩሪያ “ዐፄ ዮሐንስ እና የኢትዮጵያ አንድነት በሚለው መጽሐፉ በሰፊው ተርኳል። በኃይለስላሴ እና በደርግ ዘመንም ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የጦር መሳሪያ እና ስልጠና በማቀነባበር፣ ገንዘብ በመለገስ፣ በመካከለኛው ምስራቅ አረብ አገሮችን በማስተባበር፣ የአማርኛ ስርጭት ሬዲዮ በመክፈት ድጋፍ ማድረጓን እናውቃለን። ህውሃት ከተጠቃሚዎቹ ተቃዋሚዎች ውስጥ አንዱ ነው። በአባይ ጉዳይ ከጥንት ጀምሮ ግብጽ ከስጋት ነፃ የሆነ እንቅልፍ የለታም። ዛሬም ሆነ ወደፊት ግብጽ የሰላሙን መንገድ ትታ የጸበኛነቱን መንገድ ከመረጠች እንቅልፍ አይኖራትም። ይኽን የግብጽ ጭነቀት እና ስጋት ህውሃት ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ ግንቦት 20 ቀን ጸብ ጫረ። ላብራራ።

የጥናቱን ውጤት ተቀበለችውም አልተቀበለችው ስለ አባይ ጉዳይ በጥናት ላይ የተሰማራው ኤክስፐርቶች ቡድን ሪፖርት እየጠበቀች ሳለች ድንገት ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ. ም. ህውሃት የአባይ ወንዝ የፍሰት አቅጣጫ መቀየሩን ሰበር ዜና ተሰራጨ። የኢትዮጵያ ሽብርተኛው ኢ.ት.ቭ. አስተጋባ። ዜናው ግብጽ ደረሰ። ከጥንት ጀምሮ የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት ግብጽ ተደናገጠች። አምባገነኑ ሞርሲ ከገበባት የውስጥ ችግር ለማምለጥ የህውሃትን ቁስቆሳ ተጠቀመ። አካራሪ የግብጽ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ጋበዞ ‘እኔ ሳልሞት ግብጽ አትጠማም’ አለ። ያጀቡት አክራሪዎችም ‘ግፋ’፣ ‘በርታ’፣ ‘አይዞህ ከጎንህ ነን’ አሉት። ይኽ ምክክራቸው ዜና ሆኖ አደባባይ ወጣ። ህውሃት ሁካታውን ያልጫረ መስሎ ለኢትዮጵያ ህዝብ ግብጽ ልትወጋህ ነው የሚል ፕሮፖጋንዳ ጀመረ። የቀድሞ አባቶቻችን ድሎች ሳይቀሩ እየተጠቀሱ የቀረርቶ ድምጽ በአዲስ አበባ እየጎላ መጣ። አልባራዳይን የመሰሉት የግብጽ ዴሞክራሲ ኃይሎች የግብጽን መንግስት ወቀሱ። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎችም ቀረርቶው ገደብ ይበጅለት አሉ። የኢትዮ-ግብጽ የጦርነት ሁካታ አነሳሱ ይኽን ይመስል ነበር። ህውሃት የማያስፈልግ ጸብ ጭሯል።

ለመሆኑ ለምን የአባይ ወንዝ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን ተቀየረ? ዜናውስ ለምን ግንቦት 20 ቀን አደባባይ ወጣ? ለዚኽ ጥያቄ አቶ በረከት ስሞዖን ሰኔ 7 ቀን ግድም 2005 የሰጠውን መግለጫ እንመልከት፥ የአባይ ወንዝ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን የተቀየረው በአጋጣሚ እንጂ ህውሃት ሰልጣን ከጨበጠበት ቀን ጋር እንዲገጣጠም ሆን ተብሎ የተደረገ እንዳልሆነ ሊያስተባብል ሞክሯል። ይኽ የበረከት ስሞዖን ማስተባበያ በሽብርተኛው ኢ.ቲ.ቭ. እና በኢሳት ተዘግቧል። የአቶ በረከትን መቀላመድ ወደ ጎን አድርገን እውነቱን ሃቁን እንመልከት። የአባይ ወንዝ ፍሳሽ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን እንዲቀየር ያስደረገው ህውሃት ነው። ዜናው ግብጽ እንዲደርስ ያደረገውም ህውሃት ነው። ግቡም ስልጣን ነው። ላብራራ! (1ኛ) የተለየ አሳቢ እና ከድኽነት ነፃ አውጪህ እኔ ህውሃት ነኝ የሚል መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተላለፍ እንዲችል ሆን ብሎ የአባይ ፍሳሽ የተቀየረበትን ቀን ስልጣን ከጨበጠበት ግንቦት 20 ቀን ጋር አገጣጠመው። የዚኽ እርምጃ ፖለቲካዊ ግብ ህዝቡ እንዲያመልክበት እና ስልጣኑ እንዲጠናከር ነው። ግድብ መገንባት አይደለም ግቡ። በተጨማሪ (2ኛ) የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ለሆነባት ግብጽ የአባይ ፍሳሽ አቅጣጫ መቀየር ዜና የጦርነት ፖለቲካ ውስጥ እንደሚያስገባት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በምላሹ የኢትዮጵያን ህዝብ በአገር ወዳድነት ስሜት አሳውሮ በሚፈልገው የፖለቲካ አቅጣጫ ለማስጓዝ አስልቶ ነበር። የዚኽም ፖለቲካ ስሌት ግቡ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ ኃይሎች ለመምታት እና ስልጣኑን ለማጠናከር ነበር። በአገር ከሃዲነት እና በሽብርተኛነት ሽፋን። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች ፈጥነው ስላጋለጡት የኢትዮጵያን ህዝብ በአባይ ስሜት አሳውሮ የዴሞክራሲ ኃይሉን ለመምታት የሚያስችለው ጊዜ ሳያገኝ ቀረ። ከሸፈበት።

ህውሃት ከግድቡ ይልቅ ስልጣኑ እንደሚበልጥበት ለአንዲት ደቂቃ እንኳን መዘንጋት አያስፈልግም። ወደፊትም ሌሎች ጸቦች ሊጭር እና ከዚያ ግብጽ ልትወጋን ነው ይልሃል። የዴሞክራሲ ኃይሎች የነፃነት ሰላማዊ ትግላቸውን አጠናክረው በመቀጠል እራሳቸውን ከህውሃት ማጭበርበር እና ጥቃት መጠበቅ አለባቸው።

 

 ecadf.com

“ፍትሕ ሁሉን አቀፍ የሆነ መብት ነው”

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም፣ የዓለም አቀፍ ወንጀል ሕግ ባለሙያና መምህር

yacob

June 17, 2013 07:20 am By  Leave a Comment

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም 50ኛ ዓመቱን ለማክበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የመጀመርያ ዙር ተመራቂ ናቸው፡፡

ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አሜሪካ ከሚገኘው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ያገኙ ሲሆን፣ የፒኤችዲ ዲግሪም ያገኙት እዚያው አሜሪካ ነው፡፡ ዶ/ር ያዕቆብ በቀይ ሽብር ምክንያት ከአገር ከመሰደዳቸው በፊት በሕግ አማካሪነትና በጠበቃነት ያገለገሉ ሲሆን፣ በአሜሪካ ከ20 ዓመታት በላይ በማስተማር ሥራ ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ፍርድ ቤት ሩዋንዳ ውስጥ በዓቃቤ ሕግነት ለሦስት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ወደ ማስተማር ሥራቸው ተመልሰው ለሁለት ዓመታት ከቆዩ በኋላ በተመድ ግብዣ በናይጄሪያና በካሜሩን መካከል የነበረውን የወሰን ክርክር ለማየት ተቀጥረው ለሁለት ዓመታት ያህል አገልግለዋል፡፡ በአብዛኛው በሰው እንዲታወቁ ያደረጋቸውን የቅንጅት ጥምረት የ1997 ዓ.ም. የምርጫ እንቅስቃሴና ተዛማጅ ውጤቶች አካል ለመሆን የወሰኑት ይህን ሥራቸውን አቋርጠው እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ በምርጫ 97 ለፓርላማ ተወዳድረው ቢያሸንፉም እንዳብዛኛዎቹ የቅንጅት አባላት ሁሉ ፓርላማ አልገቡም፡፡ ዶ/ር ያዕቆብ ከግል ሥራቸው ውጪ በትርፍ ጊዜ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ ሲሆን፣ በዋነኛነት ዓለም አቀፍ የወንጀል ሕግን ያስተምራሉ፡፡ ሰለሞን ጐሹ እየተካረረ የመጣውን የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤትና የአፍሪካ ኅብረትን ውዝግብ አስመልክቶ አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) በዓለም አቀፍ የወንጀል የሕግ ሥርዓት ውስጥ ያለው ቦታ ምንድን ነው? ፍርድ ቤቱን ለማቋቋምስ ያነሳሳው ምክንያት ምንድን ነው?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- ዘ ሄግ የሚገኘው የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤትን የማቋቋም ሒደት ወደ 80 ዓመት የወሰደ ነው፡፡ የመጀመሪያው ሙከራ የተደረገው የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት እንደተደመደመ ነው፡፡ በቬርሳይል ስምምነት መሠረት የጀርመን የጦር ወንጀለኞችን ለመዳኘት ፍርድ ቤት ተቋቁሞ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ገና ሥራውን ሳይጀምር ጦርነቱን ቀስቅሰው የነበሩት የጀርመን ንጉሠ ነገሥት ስፔን ሄደው የስፔን መንግሥት ለፍርድ ቤቱ ሊያስረክባቸው ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ሥራውን አቋረጠ፡፡ ሁለተኛው መኩራ ደግሞ በኑረንበርግና በቶኪዮ የናዚ የጦር ወንጀለኞችን ለመዳኘት ፍርድ ቤቶችን በማቋቋም ነበር፡፡ እነዚህ ፍርድ ቤቶች በጣም የተዋጣላቸው ነበሩ፡፡ የዓለም አቀፍ የወንጀል ሕግንና ሥርዓትን አስፋፍተዋል፡፡ ቋሚ የሆነ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ለማቋቋም ጥሩ ጠቋሚ ነበሩ፡፡ ሦስተኛው ሙከራ በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ለመዳኘት የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ያቋቋመው ፍርድ ቤትና በዩጎዝላቪያም በተመሳሳይ በፀጥታው ምክር ቤት የተቋቋመው ፍርድ ቤት የያዙትን ጉዳይ አጥጋቢ በሆነ ሁኔታ ማጠናቀቃቸው ነው፡፡

ፍትሕ በመስጠትና ጥፋተኞቹን በመቅጣት የተዋጣለት ሥራ ስለሠሩ ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ አሁን ቋሚ የሆነ ፍርድ ቤት ማቋቋም አለብን ብሎ ተነሳ፡፡ የተመድ አባል አገሮች ሮም ላይ የፍርድ ቤቱን ማቋቋሚያ አርቅቀው እ.ኤ.አ በ1998 ፍርድ ቤቱ የተቋቋመው በዚህ ሁኔታ ነው፡፡ ስለዚህ ፍርድ ቤቱ በዓለም አቀፍ የወንጀል ሥርዓት ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ያለውን ሥልጣን ካየን የሚያረጋግጠው ይህንኑ ነው፡፡ በዘር ማጥፋት፣ በጦር ወንጀል፣ በሰው ዘር ላይ በሚሠራ ወንጀልና የጠብ አጫሪነትን ወንጀል (Aggression) የማየት ሥልጣን አለው፡፡ ፍርድ ቤቱን ያቋቋሙ አባል አገሮች በጦር ትንኮሳ ምንነት ላይ ስምምነት ላይ ስላልደረሱ ትርጉሙ በሮም ሕግ ውስጥ አልተካተተም፡፡ እስካሁንም ድረስ በዚህ ወንጀል የተከሰሰ የለም፡፡ ፍርድ ቤቱ በወንጀሉ ላይ ክስ አይቀበልም፡፡ ነገር ግን አባል አገሮቹና የፀጥታው ምክር ቤት የፍርድ ቤቱን ሥልጣን ሊያስፋፉት ይችላሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ፍርድ ቤቱ ሲቋቋም የበርካታ የአፍሪካ አገሮችን ድጋፍ አግኝቶ ነበር፡፡ ባለፉት 11 ዓመታት ግን አፍሪካና አይሲሲ ከመቀራረብ ይልቅ መራራቅን መርጠዋል፡፡ ፍርድ ቤቱንና አፍሪካን አላግባባ ያለው ችግር መነሻው ምንድን ነው?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- የፍርድ ቤቱ ሥልጣን ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ማስተናገድን ይጨምራል፡፡ እንዲህ ዓይነት ጥሰቶች በአብዛኛው የሚከሰቱት በአፍሪካ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓ ውስጥ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸም አይታይም፡፡ የጦር ወንጀልም ቢሆን አይታሰብም፡፡ በአፍሪካ ውስጥ ግን የተለመደ ነው፡፡ ሌላ ቦታ በሰላማዊ ሠልፈኞች ላይ አይተኮስም፡፡ ምናልባት በእስያ እንደ ማይናማር ያሉ አምባገነን መንግሥታት ይኖሩ ይሆናል፡፡ አፍሪካን የሚስተካከል ግን የለም፡፡ እንደሚባለው ፍርድ ቤቱ የተጠመደው በአፍሪካ ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ እርግጥ እስካዛሬ ድረስ ፍርድ ቤት የቀረቡት አፍሪካውያን ብቻ ናቸው፡፡ ሆኖም በመዝገቡ ብዙ አፍሪካዊ ያልሆኑ በተለይ የእስያ አገሮችን ዜጎች የሚመለከቱ ምርመራዎች አሉ፡፡ መረጃ በማጠናቀር ላይ የሚገኙ አፍሪካዊ ያልሆኑ ብዙ አገሮች አሉ፡፡ አፍሪካውያኑ አዲስ ቅኝ ግዛት ለመመሥረት ያለመ ፍርድ ቤት ነው ሲሉ ግርም ነው የሚለኝ፡፡ ወደ ፍርድ ቤቱ የቀረቡ የአፍሪካውያን ጉዳዮች እኮ የተመሩት በራሳቸው በአፍሪካውያኑ መንግሥታት ነው፡፡ የኡጋንዳ፣ የኮንጎና የኬንያ መንግሥታት ጉዳዩን ለፍርድ ቤቱ አስተላልፈዋል፡፡ ይህን ያላደረገች አገር ሱዳን ብቻ ናት፡፡ ከሰን ልናስቀጣ አልቻልንም፣ አቅሙም የለንም፣ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ይርዳን ብለው ነው ጉዳያቸውን ያቀረቡት፡፡

ሪፖርተር፡- የአፍሪካ አገሮች ጉዳያቸውን ለፍርድ ቤቱ ቢመሩትም ይህ በከፍተኛ ተፅዕኖና ጉትጎታ የተከናወነ እንደሆነ ማስረጃዎች ይቀርባሉ፡፡ የኬንያና የኡጋንዳ መንግሥታት የሐሳብ ለውጥንም ለዚህ ማሳያነት ይጠቅሱታል፡፡ ይህ እርስ በርሱ አይጋጭም ወይ?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- እኔ ምንም የሚጋጭ ነገር አይታየኝም፡፡ አንደኛ ነገር ማስረጃ ካለ ያ ሰው የግድ መከሰስ አለበት፡፡ አለበለዚያ ከፍትሕ ተጠያቂነት ማምለጥ ነው የሚሆነው፡፡ ማስረጃ የለም ካሉ መጀመርያውንም አለማቅረብ ነበር፡፡ ማስረጃ ቀርቦ ዓቃቤ ሕጉ የሚያዋጣ መሆኑን ካመነ በኋላ ክሱን ሊያቋርጥ አይችልም፡፡ በአስተያየት ወይም የፖለቲካ ጥቅም ያመጣል በሚል መዝለል አይቻልም፡፡ የአፍሪካ አገሮች ለምሳሌ የሱዳኑን ፕሬዚዳንት አል በሽር መክሰስ ተገቢ አይደለም በሚል ይከራከራሉ፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ የሰላሙን ድርድር ያበላሸዋል የሚል ነው፡፡ ሰላም ሊገኝ የሚችለው በቅድሚያ ፍትሕ ሲገኝ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ፖለቲከኞቹ ብቻ ሳይሆኑ አንዳንድ የአፍሪካ ልሂቃን የአፍሪካ የፍትሕ አረዳድ ከምዕራባውያን የፍትሕ ሥርዓት ጋር አንድ እንዳልሆነ ያስረዳሉ፡፡ መደበኛ ያልሆነ የፍትሕ ሥርዓትና ማኅበረሰብ አቀፍ መፍትሔዎች የአፍሪካ መለያ እንደሆኑ በመጥቀስ የሚከራከሩም አሉ፡፡ ከዚህ አንፃር ከፍትሕ ይልቅ ሰላም ይስፈን የሚሉ አካላት ተጨባጭ ነጥብ የላቸውም?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- እኔ ያላቸው አይመስለኝም፡፡ ፍትሕ ከሌለህ ሰላም ሊኖርህ አይችልም፡፡ አንተም ተው አንቺም ተይ ተብሎ ወንጀል ሊቀር አይችልም፡፡ ቅጣቱ እኮ ሊዘለልም ይችላል፡፡ ማኅበረሰቡም ይቅርታ ሊያደርግለት ይችላል፡፡ ዋናው ቅጣቱ ሳይሆን ተጠያቂነቱ ነው፡፡ በአካባቢው እርቅና ሰላም እንዲወርድ ከተፈለገ ቅጣቱን መዝለል ወይም በይቅርታ ማለፍ ይቻላል፡፡ ተጠያቂነትን ግን በምንም ዓይነት መንገድ መዝለል አይገባም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለአፍሪካ የተለየ ዓይነት ፍትሕ አስፈላጊ እንደሆነ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ አፍሪካ ከአውሮፓና ከአሜሪካ የተለየ እሴት እንዳለውም ይከራከራሉ፡፡ የፍትሕ አሰጣጡ ሒደት ከአፍሪካ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ሊስተካከል ይገባል በማለት ያስረዳሉ፡፡ አውሮፓም፣ አሜሪካም ሆነ አፍሪካም ያለው ሰው ነው፡፡ የሰው ልጅ ፍትሕ ይፈልጋል፡፡ ፍትሕ ደግሞ ሁሌም አንድ ዓይነት ነው፡፡ ፍትሕ ሁሉን አቀፍ የሆነ መብት ነው፡፡ አፍሪካ የተለየ ፍትሕ የለውም፡፡ የሰው ልጅ ፍላጎት ተመሳሳይ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- አይሲሲ ብሔራዊ የሕግ ሥርዓቶችን በቅድሚያ አሟጦ መጠቀምን ያበረታታል፡፡ የአፍሪካውያን አገሮች ብሔራዊ የሕግ ሥርዓቶች ከአቅምና ከፖለቲካ ጫና ጋር በተያያዘ ችግር ስላለባቸው ይህ ዕድል በጥንቃቄ መታየት አለበት የሚሉ አሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ አይሲሲ ጉዳዮችን እያየ ያለው ለአፍሪካ ብሔራዊ የሕግ ሥርዓቶች በቂ ዕድል ሳይሰጥ እንደሆነ ይተቻሉ፡፡ ለምሳሌ ኬንያ የኡሁሩ ኬንያታን ጉዳይ ራሷ እንድታይ አፍሪካ ኅብረት ጠይቋል፡፡

ዶ/ር ያዕቆብ፡- አይሲሲ ሲቋቋም የነበረው ትልቁ ጥያቄ ሉዓላዊነትን የተመለከተ ነበር፡፡ እንደ አሜሪካ ያሉ አገሮች ፍርድ ቤቱን ያልተቀበሉት ሉዓላዊነታችንን በሌላ አካል አናስደፍርም በሚል ነው፡፡ ሉዓላዊነትን ለማስከበር ሲባል በቅድሚያ ዕድል የሚሰጠው ለየአገሮቹ የሕግ ሥርዓት ነው፡፡ የአገሮቹ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት ፍትሕ ከተሟጠጠ በኋላ ነው ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የሚኬደው፡፡ የአይሲሲ ሕግ የሚለው የአገሮቹ ፍርድ ቤት ፍትሕ ሊሰጥ የማይችል ከሆነ፣ ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም አቅም ከሌለው፣ ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ሊያስተናግድ እንደሚችል ነው፡፡ በአፍሪካ ይህን ነገር ስናይ አንደኛ ድክመትም እያላቸው ለሉዓላዊነት ሲባል የማስተናገድ ነገር አለ፡፡ ሁለተኛ እንደ ኬንያ ያሉ አገሮች ጉዳዩን ለዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ከመሩ በኋላ መልሰው እናስተናግድ ማለታቸው በጣም ግራ የሚያጋባ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዓለም ሕዝብ የሚወክሉ አገሮች የፍርድ ቤቱ አባል አይደሉም፡፡ ከፀጥታው ምክር ቤት አባላት መካከል አሜሪካ፣ ቻይናና ሩሲያ አባል አይደሉም፡፡ ይህ የፍርድ ቤቱን ተቀባይነት ምን ያህል ይጎዳል?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- ችግሩ የሉዓላዊነት ጉዳይ ነው፡፡ በተለይ አሜሪካውያን በሉዓላዊነት ጉዳይ በጣም በቀላሉ ነው ስሜታቸው የሚነካው፡፡ ከተመድ አባልነት ሁሉ መውጣት አለብን በማለት የሚከራከሩ ብዙ አሜሪካውያን አሉ፡፡ በቡድን ተደራጅተው ይህን የሚያንቀሳቅሱ አሉ፡፡ ሉዓላዊነታቸውን ለአንድ የዓለም አቀፍ ድርጅት መስጠት አይፈልጉም፡፡ ሌላው አባል ያልሆኑበት ምክንያት አሜሪካውያን በዓለም ጉዳይ ሁሉ እጃቸውን አስገብተዋል፡፡ ወታደሮቻቸውም ሆነ ዜጎቻቸው ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ አይፈልጉም፡፡ ሆኖም አሜሪካውያን ፍርድ ቤቱን በገንዘብና በተለያዩ መንገዶች ሲደግፉት ደግሞ ይታያል፡፡ በተጨማሪም አባል ካልሆኑት ከቻይናና ከሩሲያ ጋር በመሆን በፀጥታው ምክር ቤት አማካይነት ፍርድ ቤቱን የተመለከቱ የተለያዩ ውሳኔዎችን ይሰጣሉ፡፡ ይኼ ትንሽ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው፡፡

ለምሳሌ ቡሽና ብሌር ብዙ ጊዜ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት መቅረብ አለባቸው እየተባለ ይወራል፡፡ ምናልባትም ይገባቸው ይሆናል፡፡ ቡሽ ያለፀጥታው ምክር ቤት ፈቃድ ነው ኢራቅን የደበደበው፡፡ አሜሪካ ግን ለፍርድ ቤቱ አብዛኛውን በጀት ትመድባለች፡፡ በሌላ በኩል ከእያንዳንዱ አገር ጋር በተናጠል ባደረጉት ስምምነት የአሜሪካ ዜጋን በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እንዳያቀርቡ አስፈርመዋል፡፡ ይህን የአሜሪካ ስምምነት ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ አገሮች ፈርመዋል፡፡ እነዚህን ኃያላን አገሮች ፍርድ ቤቱ ጥቅማቸውን ካልነካ በስተቀር ይፈልጉታል፡፡ በወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ አድኖ እስከመስጠት ድረስ እኮ ትብብር ያደርጋሉ፡፡ ይህ መቶ በመቶ ተቀባይነቱን ባያጠፋውም ትልቅ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ፍርድ ቤቱ ከፀጥታው ምክር ቤት ጋር ቀጥተኛ የሥራ ግንኙነት አለው፡፡ ነገር ግን አብዛኛው የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የፍርድ ቤቱ አባል አይደሉም፡፡ ነገር ግን ራሳቸው የማይገዙበትን ተቋም ሌሎች እንዲቀበሉት የማዘዝ ሥልጣን መስጠት በፍትሕ ላይ እንደ መቀለድ አይሆንም?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- ይኼ እውነትም በፍትሕ ላይ መቀለድ ነው፡፡ ራሳቸው የማይገዙበትን ሕግ በሌላው ላይ መጫን ቀልድ ነው፡፡ ነገር ግን የዓለም አቀፍ ሕግና ፖለቲካ የሚነዳው በኃይል ነው፡፡ ጉልበት፣ ኃይልና ሀብት ወሳኝ ሚና አላቸው፡፡ በሌላው ሕዝብ ላይ ኃያላኑ የመጫን አቅም አላቸው፡፡ ይኼ ፍትሐዊ አካሄድ አይደለም፡፡ የአሜሪካ እውነታ የዓለም እውነታ የሚሆንበት የዓለም ሥርዓት ነው ያለው፡፡ አሜሪካና ሌሎች ኃያላን አገሮች እኮ ዓለም አቀፍ ሕግን እንደፈለጉት ነው እየጣሱ ያሉት፡፡ እንደ አማራጭ እየቀረበ ያለው ነገር አፍሪካ ውስጥ ራሱን የቻለ የአፍሪካ የወንጀል ፍርድ ቤት ማቋቋም ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ በጽሑፍ ደረጃ ተቋቁሟል፡፡ በታንዛኒያ አሩሻ ቢሮ ከፍቷል፡፡ እስከዛሬ ድረስ አንድም ጉዳይ ግን አላስተናገደም፡፡ የአፍሪካ አገሮች ነፃ ፍትሕ ለመስጠት ዝግጁ ናቸው ወይ በሚለው ጥያቄ ላይ ብዙዎች ጥርጣሬ አላቸው፡፡ በአንድ ወቅት አፍሪካዊ ፍርድ ቤት የማቋቋምን ሐሳብ ያነሱት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነበሩ፡፡ የአሩሻውን ቢሮ ጎብኝቼዋለሁ፡፡ በቂ የሰው ኃይል አለው፡፡

ሪፖርተር፡- ፍርድ ቤቱ የአሜሪካን የፖለቲካ ፍላጎት እየተከተለ እንደሚሠራ ይታማል፡፡ ከአሜሪካ ተፅዕኖ ተላቆ ነፃና ፍትሐዊ አሠራር ለመከተል ዕድል ይኖረዋል?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት ከአሜሪካ ተፅዕኖ መላቀቅ የሚችለው ዓለም በሙሉ ከአሜሪካ ተፅዕኖ ሲላቀቅ ነው፡፡ የአሜሪካ የኢኮኖሚ ኃይል ሰፊ ነው፡፡ ዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኗቸው ሰፊ ነው፡፡ በጀት በመመደብ አሜሪካ ቀዳሚ ነች፡፡ አፍሪካውያን ለፍርድ ቤቱ አይከፍሉም ማለት ይቻላል፡፡ ገንዘብ የሚመድቡ ናቸው ደፍረው የሚናገሩት፡፡ ይኼ ከዓለም የፖለቲካ ከባቢ ሁኔታ ጋር አብሮ የሚሄድ ነው፡፡ ተመድ ራሱ ከዚህ የዓለም ሁኔታ ተገንጥሎ አይታይም፡፡

ሪፖርተር፡- የቀድሞው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዦን ፒንግ የቀድሞውን ዋና ዓቃቤ ሕግ ሞሪኖ አካምፖን ከፍርድ ቤቱ ነጥለው በዘረኝነት ከሰዋቸው ነበር፡፡ አዲሷ ዋና ዓቃቤ ሕግ ቤንሱዳ ጋምቢያዊ መሆኗ ለውጥ ያመጣል?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- አፍሪካዊ በመተካቱ የፍርድ ቤቱ ሚና ይለወጣል የሚል እምነት የለኝም፡፡ በኦካምፖ ላይም የተሰነዘረውን ወቀሳ ይኼን ያህል አክብጄ አላየውም፡፡ ፒንግ ይናገር የነበረው የአፍሪካ መሪዎችን ስሜት ነበር፡፡ የአፍሪካ መሪዎችም ሲመቻቸው ፍርድ ቤቱን ይፈልጉታል፡፡ ሳይመቻቸው ሲቀር ደግሞ አይፈልጉትም፡፡ ፍርድ ቤቱ በአፍሪካ ከባድና አሰቃቂ ወንጀሎች እንዳይፈጸሙ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ አሁን አንድ አፍሪካዊ መሪ ከባድ ወንጀል ለመፈጸም ሲያስብ የፍርድ ቤቱን ህልውና ያስታውሳል፡፡ አሁን ማንም መሪ የትም ይሁን የት አሰቃቂ ወንጀል ከፈጸመ ዘ ሄግ የመሄድ ዕድል አለው፡፡ የሮም ስምምነትን ያላፀደቀ አገር ዜጋ እንኳን ከዚህ አያመልጥም፡፡

ሪፖርተር፡- ባልፈረሙት ሕግ የመገዛት አሠራር ከዓለም አቀፍ ሕግ መሠረታዊ መርህ ጋር የሚጋጭ አይደለም?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- እኔ ይኼ አሠራር ትክክል ይመስለኛል፡፡ የሰው ዘር የማጥፋት ወንጀል በሩዋንዳ ቢፈጸምም የሚያመጣው ጥፋት በሩዋንዳ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ አንድን ዘር እስከነጭራሹ ከዓለም ያጠፋል ወይም ለማጥፋት ጥረት ያደርጋል፡፡ ዓለም የአንድ ዘር ባህል፣ ቋንቋና ሃይማኖት በመደምሰሱ ይጎዳል፡፡ የሚጎዳው ያ ዘር ብቻ አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡- ከፍርድ ቤቱ አወቃቀር መካከል በብዛት ጥያቄ የሚነሳበት የዓቃቤ ሕጉ ጽሕፈት ቤት ነው፡፡ ሥልጣንና ተጠያቂነቱ ላይ ቅሬታ ይቀርባል፡፡ አወቃቀሩ ላይ ያለው ችግር ምንድን ነው?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- አወቃቀሩ ላይ የሚታየኝ ችግር የለም፡፡ ከአንድ አካባቢ ብቻ ዓቃቤ ሕጉን መምረጥ ትክክል አይደለም፡፡ አኅጉራቱና አገሮቹ መወከል አለባቸው፡፡ ዓቃቤ ሕጉ ችሎታው፣ ታማኝነቱ፣ ሀቀኝነቱና የፍርድ ዕውቀቱ ተመርምሮ ነው የሚመረጠው፡፡ የመጀመርያው ጣሊያናዊ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ጋምቢያዊት ናት፡፡ በሠራው ሥራ ወይም ሊሠራ ሲገባው በዘለለው ሥራ ተጠያቂ የሚሆንበት ሥርዓት የለም የሚል ቅሬታ ይቀርባል፡፡ ይኼ በዳኞቹም ላይ በተመሳሳይ ይቀርባል፡፡ ሁሉንም ነገር በተጠያቂነት ማካሄድ አይቻልም፡፡

ሪፖርተር፡- የአውሮፓ አገሮች ከአሜሪካ ያልተናነሰ ተፅዕኖ በፍርድ ቤቱ ላይ እንደሚያሳርፉ ይነገራል፡፡ አንዳንድ አፍሪካውያን እንዲያውም ዳግም ቅኝ ግዛትን ለማወጅ ፍርድ ቤቱን እየተጠቀሙ ነው እስከማለት ደርሰዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ፍርድ ቤቱን የአውሮፓ ፍርድ ቤት በማለት ይጠሩታል፡፡ አውሮፓ አግባብነት የሌለው ተፅዕኖ እየፈጠረች ነው ማለት ይቻላል?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- አውሮፓ አግባብነት የሌለው ተፅዕኖ እየፈጠረች ነው ለማለት አልችልም፡፡ አውሮፓውያን እኮ ማንም ዜጋ የሰብዓዊ መብቱ ተጠብቆ እንዲኖር የሚያደርግ የራሳቸው ፍርድ ቤት አላቸው፡፡ እንዲያውም ይህ ፍርድ ቤት ለአውሮፓውያን አያስፈልጋቸውም፡፡ ጫና ለመፍጠርም እየተጠቀሙበት ነው ለማለት አልችልም፡፡ ፍርድ ቤቱ የራሱ ጉድለቶች አሉበት፡፡ ነገር ግን አፍሪካውያኑ አብረው በመሥራት ማስተካከል አለባቸው፡፡ የአፍሪካውያን ቅሬታ ከፍትሕ ሳይሆን ከፖለቲካ አመለካከታቸው የሚመነጭ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ጉዳዮቹን ለፍርድ ቤት የመምራት መብት ለአገሮች ብቻ ሳይሆን ለግለሰብና ለድርጅቶች ጭምር የተሰጠ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ከግለሰቦችና ከድርጅቶች በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ጥቆማዎች ቢቀርቡለትም ቅድሚያ ሰጥቶ የሚከታተለው ከአገሮች የሚመሩ ጉዳዮችን ነው፡፡ ምክንያቱ ምንድን ነው?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- በአገሮች የሚመሩ ጉዳዮች ትኩረት የሚሰጣቸው አንደኛ ማስረጃ በቀላሉ መሰብሰብ ስለሚቻል ነው፡፡ አገሩ ራሱ ስለሚስማማ ያንን ማስረጃ ለማቅረብ ፈቃደኛ ይሆናል፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ፍርድ ቤቱ በራሱ ተነሳሽነት የሚያቀርበው ክስ በአገሮች ተቃውሞ ሊቀርብበት ስለሚችል ነው፡፡ መንግሥት ካልተባበረ ማስረጃ ማግኘት ቀላል አይሆንም፡፡ መንግሥታቱ ራሳቸው የሚያቀርቧቸው ጉዳዮች ለፍትሕ የበለጠ አመቺ ናቸው፡፡ አባል ያልሆነም አገር ጉዳዩ በፍርድ ቤቱ ሥልጣን ሥር ከወደቀ ወደ ፍርድ ቤቱ ሊወስድ የሚችልበትም አሠራር አለ፡፡

ሪፖርተር፡- በአፍሪካ ላይ የተደረገው ትኩረት ከወንጀሎቹ ክብደት አኳያ እንደሆነ በአንድ በኩል ይገልጻል፡፡ በሌላ በኩል በኢራቅ፣ በጋዛ፣ በአፍጋኒስታን፣ በሶሪያና በባህሬን ከአፍሪካ በባሰ ሁኔታ አሰቃቂ ወንጀሎች እንደተፈጸሙ በመጠቆም የፍርድ ቤቱን አድሎአዊነት እንደሚያሳይ የሚቀርብ ክርክር አለ፡፡ በእርግጥ ከባድ ወንጀሎች በአፍሪካ ብቻ ነው የሚፈጸሙት ለማለት ይቻላል?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- በሌሎች አካባቢዎች የሚፈጸሙ ወንጀሎች ለፍርድ ቤቱ ሳያቀርቡ ቀርተው አይደለም፡፡ አፍሪካ ውስጥ በጣም ያነሱ ወንጀሎች ወደ ፍርድ ቤቱ ቀርበዋል፡፡ ልዩነቱ የማስረጃ ጉዳይ ነው፡፡ በሌሎቹ አገሮች ማስረጃ ማግኘት ቀላል አይደለም፡፡ በተጨማሪ ጉዳዮቹ ከሃይማኖትም ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡ ሃይማኖት ለፍትሕና ለክርክር የሚያመች አይሆንም፡፡ ሌሎቹ አገሮች ከአፍሪካ በተለየ ጉዳያቸውን ለፍርድ ቤቱ የማይመሩትም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ በእነኚህ አገሮች የጦር ወንጀል መኖሩ ምንም አጠራጣሪ አይደለም፡፡ ምዕራባውያን እስልምናን ለማጥፋት ይሠራሉ ስለሚባል ጉዳዮቹን በጥንቃቄ ነው የሚያዩዋቸው፡፡

ሪፖርተር፡- ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ተባብራ የመሥራት ታሪክ አላት፡፡ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አባል አገር አይደለችም፡፡ ዋነኛ ምክንያቷ ምንድን ነው?

ዶ/ር ያዕቆብ፡- የኢትዮጵያ አቋም የሚያሳዝንም የሚያሳፍርም ነው፡፡ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕግጋትን በመቀበል በአፍሪካ ውስጥ ቀዳሚነት ነበራት፡፡ የሮምን ስምምነት ኢትዮጵያ በጉጉት መቀበል ነበረባት፡፡ እንደ ወንበዴ መንግሥታት ይህን ዓለም አቀፍ የወንጀል ሕግ አልቀበልም ማለት ተገቢ አይደለም፡፡ ምክንያቱ ተጠያቂ ላለመሆን ይመስላል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለፍትሕ ሥርዓት ትልቅ ከበሬታ ነው ያለው፡፡ ኢትዮጵያ ደቡብ አፍሪካን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ያቀረበችው እኮ የአፍሪካ አገሮች በቅኝ ግዛት ሥር በነበሩበት ጊዜ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የፍርድ ቤቱን ችግር ቀድማ በመረዳት ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ነው አባል ያልሆነችው የሚል ክርክር የሚያቀርቡ አካላት አሉ፡፡ ኢትዮጵያ አባል ሆና የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ በመሆን የአፍሪካን የወቅቱ ጥያቄ ለማስተናገድ ትቸገራለች የሚል ሐሳብም ይቀርባል፡፡ የአጋሮቿ የአሜሪካና የቻይና አባል አለመሆንም እንደተጨማሪ ምክንያት ይነሳል፡፡

ዶ/ር ያዕቆብ፡- እነዚህ ሁሉ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከፍትሕ በላይ ግን ምንም ነገር የለም፡፡ ልማትም ሆነ ሰላም ሊመጣ የሚችለው ከፍትሕ በኋላ ነው፡፡ መረሳት የሌለበት ነገር አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች የፍርድ ቤቱ አባል ናቸው፡፡ አሁን ኢትዮጵያ ፍርድ ቤቱን በመቃወም ቀዳሚ ሥፍራ እየያዘች ነው፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ‘የራሳችን የወንጀል ፍርድ ቤት ማቋቋም አለብን’፣ ‘ይኼ ፍርድ ቤት ዋጋ የለውም’፣ ‘ሰላም ከፍትሕ ይቀድማል’ ይሉ ነበር፡፡ አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ይህንኑ እየደገሙት ይገኛሉ፡፡

ሪፖርተር፡- አፍሪካና ፍርድ ቤቱ የተሻለ ግንኙነት ለመመሥረት ምን ሊያደርጉ ይገባል? ፍርድ ቤቱ በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አማካይነት በይፋ ‘ዘረኛ’ ተብሏል፡፡

ዶ/ር ያዕቆብ፡- የአፍሪካ አገሮች የዲሞክራሲ ይዞታቸውን ሊያስተካክሉ ይገባል፡፡ የውስጥ አስተዳደራቸው በዲሞክራሲ ሲታነጽ ፍትሕን ይቀበላሉ፡፡ ፍርድ ቤቱ በተመድ ውስጥ የፍርድ ቤቱና የአፍሪካ አገናኝ ቢሮ ለመክፈት አቅዶ ተመድም በጀት ለመመደብ ተስማምቶ ነበር፡፡ አፍሪካውያን ሐሳቡን ያልተቀበሉት ሌሎቹ አኅጉሮች ሳይኖራቸው ለምን አፍሪካ ብቻ ይኖረዋል በሚል ነው፡፡ ነገር ግን ችግራቸውን ለመቅረፍ የተሻለ ተቀራርበው መሥራት አለባቸው፡፡ (ምንጭ ሪፖርተር)

goolgule.com

የሙስና ምርመራ እየተወሳሰበ ነው!

“መበላላት እንዳይጀመር ስጋት አለ”

sheraton

June 18, 2013 08:08 am By  Leave a Comment

በጉምሩክና ገቢዎች ባለስልጣን የተጀመረው የጸረ ሙስና ዘመቻ ተከትሎ እየተካሄደ ያለው ምርመራ እየተወሳሰበ መሔዱ ተሰማ። በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ተከሳሾች የሚሰጡት መረጃ መበላላት ያስነሳል የሚል ፍርሃቻ እያስነሳ ነው። “ሰፈር የለየው” የጸረ ሙስና ዘመቻ የፈጠረው ስጋት የሃይል ሚዛን የያዙትንም ስጋት ውስጥ ከትቷል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ የታየው የውስን ሰዎች በድንገት በመበልጸግ ከባለስልጣኖችና ከከፍተኛ የስርዓቱ ሰዎች ቤተሰቦች ጋር በሚከናወን መተሳሰር አማካይነት እንደሆነ ከህዝብ የተሰወረ አይደለም። ሰሞኑንን ይፋ የተደረገው የባንክና የንብረት እግድ እንዳመለከተው የዝርፊያው ሰንሰለት በቤተሰብ የታጠረ መሆኑን ነው።

አቶ መለስ ከድነው ያቆዩትና የሳቸውን ሞት ተከትሎ ከፖለቲካው ልዩነት ጋር በተያያዘ እንደተጀመረ የሚነገርለት የጸረ ሙስና ዘመቻ፣ በመንግስት በኩል “ቆራጥ” አቋም የተያዘበት እንደሆነ ቢነገርም አስጊ ሁኔታ እየተፈጠረ ስለመሆኑ የጎልጉል የጸረ ሙስና ኮሚሽን ምንጮች ይናገራሉ።

እየተካሄደ ካለው ምርመራ በተገኙ ጭብጦች መታሰር የሚገባቸው ባለስልጣናት እንዳሉ የሚጠቁሙት እነዚሁ ክፍሎች፣ ምርመራው እየሰፋና እየጠለቀ ሲሄድ ችግር ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ማሳደሩን አይሸሽጉም።

“የመጨረሻው መጠፋፋት መጀመሪያ ላይ እንዳሉ የሚሰማቸው አሉ” በማለት ለጎልጉል መረጃ የሰጡት ክፍሎች “እየሰፋ የሄደውንና መጨረሻው ወዴት እንደሚያመራ የሚታወቀውን የጸረ ሙስና ዘመቻ የማስቆም ፍላጎት እንዳለ የሚያመላክቱ ሁኔታዎች በቢሮ ደረጃ እየሰማን ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ዘመቻው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት የሚሉ ክፍሎች ስላሉ በሙስና የሚጠረጠሩ ፕሮጀክቶችና ከፍተኛ ግንባታዎችን አስመልክቶ በስፋት መረጃ የሚደርሰው ኮሚሽኑ፣ ከነገ ዛሬ ይመጣብናል በሚል የተፈጠረው መደናገጥ በህገወጥ ሃብት የሰበሰቡትን በሙሉ ስጋት ላይ ጥሏቸዋል። በባንኮች አካባቢ ገንዘብ የማሸሽ፣ ከዶላር ገበያ ራስን የማግለልና የሃይል ሚዛን በመመልከት የመተጣጠፍ ሩጫ በስፋት እንደሚስተዋል የጎልጉል ሰዎች ተናግረዋል።

በሙስናው ሰለባ የሆኑት ቡድኖች አቅማቸውና ትስስራቸው ቀላል ባለመሆኑ፣ የታጠቁ ሃይሎችም ስላሉበት የርስ በርስ መተላለቅ ሊከተል ይችላል በሚል ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚደረግ ያመለከቱት ምንጮች “አቶ መለስ የዘረጉትን ሰንሰለት ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር ችግር እየታየ ነው። መተላለቁ በዚህ ክፍተት ውስጥ ሊከሰት ይችላል” የሚል ስጋት መንገሱን አመልክተዋል።

የሚታወቁ ባለስልጣናትና የክልል አመራሮች “ልማታዊ” ከሚባሉት ኢህአዴግ ሰራሽ ባለሃብቶች ጀርባ ሆነው ፕሮጀክትና ጨረታ በማጸደቅ ምዝበራውን እንደሚመሩ መረጃ ስለመኖሩ የሚናገሩት ምንጮች፣ “በቅርብ ተመስርተው ከፍተኛ ሃብት በሰበሰቡ ሪል ስቴት፣ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች፣ አስመጪና ላኪዎች፣ ሰፋፊ መሬት ለአረብ አገር ባለሃብቶች በማስማማት አየር በአየር የሚጫወቱ፣ በአገሪቱ ከሚታዩት ታላላቅ ግንባታዎች ጋር በተያያዘ ወዘተ ዋናዎቹ ባለስልጣኖችና ቤተሰቦቻቸው ተዋናይ መሆናቸው ይታወቃል። የህወሃት ሰዎች ግንባር ቀደም ናቸው” በማለት የስጋቱን መጠን ይገልጻሉ።

ከአገር ውስጥ በተጨማሪ በአፍሪካና በተለያዩ አገራት የሽርክና ንግድ የከፈቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዳሉ የሚገልጹት የኢህአዴግ የቅርብ ሰዎች “አሁን አመራር ላይ ያሉት የህወሃት ሰዎች የእነዚህን ባለስልጣናት በቤተሰብና ከፍተኛ አቋም በገነቡ ድርጅቶች አማካይነት የተበተቡት ሰንሰለት በቀላሉ መበጠስ ስለማይችሉ የሙስናው ዘመቻ አደጋ ይገጥመዋል። አለያም እርስ በርስ መበታበት ሊከተል ይችላል” በሚል ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቀረጥ ነጻ በማስገባት ከፍተኛ የመንግስት ገቢ ለግል ተጠቅመዋል በሚል በተከሰሱት ሰዎች ላይ እየተካሄደ ባለው ምርመራ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ በከፍተኛ ባለስልጣናት ትዕዛዝ አማካይነት የቀረጥ ነጻ ፈቃድ መስጠታቸውን ለምርመራ መኮንኖች መናገራቸውን የጎልጉል ምንጮች አመልክተዋል።

በዚህም የተነሳ ሸራተንን ተገን ያደረጉት የባለሃብቱ ወኪል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቃቸው ተሰምቷል። በነባር የህወሃት ሰዎች የማይወደዱት እኚሁ የባለሃብቱ ወኪል፣ ወ/ሮ አዜብን፣ አቶ አዲሱ ለገሰና የባለሃብቱ ዋና ሸሪክ የሆኑትን አቶ በረከትን ቢተማመኑም ምርመራው ወደእርሳቸው ሊሄድ እንደሚችል የጎልጉል ምንጮች ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል። አንዳንዶቹ የቀድሞ ሸሪኮቻቸው ስልካቸውን ስለማያነሱላቸው ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውና ከወትሮው የተለየ ያለመረጋጋት እንደሚታይባቸው የቅርብ ሰዎቻቸውን ሳይቀር ሰላም እንደነሳ ለማወቅ መቻላቸውንም ተናግረዋል።

አብዛኛውን የንግድ በሮች በስጋ ዘመዶቻቸውና በአገር ልጆች ተብትበው የያዙት የባለሃብቱ የኢትዮጵያ ወኪል ምርመራ ዙሪያ የሚነሱትን ጉዳዮች ከመጥቀስ የተቆጠቡት ምንጮች፣ በቅርቡ አዲስ ነገር እንደሚሰማ መረጃዎች እንዳሏቸው አመልክተዋል። ለሸራተኑ ሰውና ለሸራተኑ ቡድኖች እጅግ ቅርብ ነን የሚሉ በበኩላቸው “ወ/ሮ አዜብ መስፍንና አቶ አዲሱ ለገሰ እስካልተነኩ ድረስ ሸራተን ሰላም ነው። አቶ ጌታቸውም እዛው ናቸው” ሲሉ የለበጣ ቀልድ ቀልደዋል። እነዚሁ ክፍሎች ቢያንስ “የኤች አይ ቪ/ኤድስ እድሜ ማራዘሚያ እናመርታለን፣ ለወገን እንደርሳለን በሚል ሰበብ በከፍተኛ ማጭበርበር የተፈጸመውን ወንጀል ጉዳይ ዝም አይበሉት” ሲሉ ለጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ አደራቸውን አስተላልፈዋል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

goolgule.com

የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ

“ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ”

ጎልጉል የድረ-ገጽ ጋዜጣ

በነበራቸው የስራ ሃላፊነት በድብቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ቆይተው ለመንግስት ካጋለጡ በኋላ ራሳቸውን ደብቀው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ ምሳ እየተመገቡ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ ተስፋዬ ሰኞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር።

Allegations of Corruption Emerge Against Federal Government Examiners

Former Gambella Regional President, Mr. Omot Obang Olom

በቅርቡ ወደ ፌደራል መንግስት የተዛወሩት የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኡሞት ኦባንግ፣ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር በማደራጀት ለኢህአዴግ ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ አሟሟታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን፤ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ መረጃዎች ናቸው። መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” በሚል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ በ (ጥቅምት 19፤2005/October 29, 2012) መዘገቡ ይታወሳል

ቀደም ሲል የጋምቤላ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ከላይ የተጠቀሰውን የሙስና ወንጀል በማጋለጣቸው ጋምቤላ መኖር ሳይችሉ ቀርተው ራሳቸውን ሸሽገው ለመኖር ተገደው እንደነበር የሚያውቋቸው ለጎልጉል አስረድተዋል።
“አቶ ተስፋዬ ሙስናን በማጋለጣቸው በፍርሃቻ ራሳቸውን ደብቀው ሊኖሩ አይገባም” በማለት ኢህአዴግ ከለላ እንደሚሰጣቸው ቃል በገባላቸው መሰረት ከተሸሸጉበት የወጡት አቶ ተስፋዬ ሰንጋተራ ትንሳዔ ሆቴል ከጋምቤላ ልጆች ጋር መገናኘት ይጀምራሉ።

ባለፈው ሳምንት ከፌዴራል የጸረ ሙስና ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ ከያዙ በኋላ ኮሚሽነሩ በድንገት ለለቅሶ ወደ ጎንደር በመሄዳቸው ቀጠሮው ለሳምንት ይራዘማል። ለሰኞ (ሰኔ10፤2005) አዲስ ቀጠሮ ይይዛሉ።

በስልክ ያነጋገርናቸው ትንሳዔ ሆቴል አካባቢ እንደነበሩና ለጉዳዩ ቅርበት እንዳላቸው የሚገልጹ የጋምቤላ ተወላጅ የስራ ሃላፊ እንዳሉት አቶ ኦሞት ኦባንግ ለአቶ ተስፋዬ ስልክ ደውለው ነበር። አቶ ተስፋዬ ህይወታቸው ከማለፉ ሁለት ቀን በፊት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኦሞት በስልክ ተማጽንዖ አቅርበው ነበር።

አቶ ኦሞት “እውነት ነው ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀጠሮ የያዝከው?” በማለት ይጠይቃሉ

“አዎ! እውነት ነው” በማለት አቶ ተስፋዬ መልስ ይሰጣሉ።

አቶ ኦሞት መልሰው “እንግዲያውስ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከመግባትህና ከማነጋገርህ በፊት ሁለታችን መገናኘት አለብን። የምንነጋገረው ነገር አለ” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። አቶ ተስፋዬ ስለ ስልክ ልውውጡ እንደነገሯቸው የተናገሩት እኚሁ ሰው፣ አቶ ኦሞት በስልክ ደጋግመው በመደወል ያቀረቡትን የ”እንነጋገር” ጥያቄ አቶ ተስፋዬ አልቀበልም ይላሉ።

ጋምቤላ ስራቸውን ለቀው ራሳቸውን ደብቀው የኖሩት በእርሳቸው ምክንያት መሆኑን፣ ፍትህ እንደሚፈልጉ፣ አሁን ለመነጋገር ጊዜው እንዳልሆነ፣ ዘርዝረው ለአቶ ኦሞት መናገራቸውን ያወሱት የጎልጉል ምንጭ፣ ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው አቶ ኦሞት በንዴት ተዛልፈው ነበር።

ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው እንግዲህ አቶ ተስፋዬ ትንሳዔ ሆቴል ሰዎችን በመላላክና በመታዘዝ ከሚኖር አንድ የጋምቤላ ሰው /አቶ ተስፋዬ የሚረዱት በምግባር ጉዳይ የሚታማና ጸበኛ የሚባል ሰው ነው/ አብረው ተቀምጠው ምሳ እየበሉ ሳለ አቶ ተስፋዬ አረፋ ይደፍቃቸዋል። ወዲያው ከተቀመጡበት ተንሸራተው መሬት ይወድቃሉ። ቀጥሎም ሰውነታቸው ይዝልና ኮማ ውስጥ ይገባሉ። ከአፋቸው እየተዝለገለገ የሚወጣው ፈሳሽ በመጨመሩና የተለያየ ርዳታ ቢደረግላቸውም ሊተርፉ ስላልቻሉ ሆስፒታል ተወስደው ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።

አቶ ተስፋዬ ሆስፒታል ከመድረሳቸው በፊት እንደሞቱ የሚናገሩት የጎልጉል ምንጭ አሟሟታቸው ከመርዝ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ በሙስና ወንጀል ላይ ያሰባሱትን መረጃ ለተለያዩ አካላት የበተኑ ስለሆነ እሳቸውን በመግደል ማድበስበስ እንደማይቻል አስታውቀዋል። አቶ ተስፋዬ ሙስና ካጋለጡ በኋላ መሰወራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው። በተያያዘ በጋምቤላ ኢንቨስትመንት ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ውስጥ ከ70በመቶ በላይ የሆኑት የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች የነበሩና የክልል አንድ ተወላጆች መሆናቸው የአቶ ተስፋዬን አሟሟት ይበልጥ ውስብስብ እንዳደረገው አስተያየት እየተሰጠ ነው፡፡

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ “የአቶ ተስፋዬ ሞት አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ” በማለት ስለ አቶ ተስፋዬ ሞትና አሟሟት መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።

“አቶ ተስፋዬ ለእውነት ሲል ሞቷል። ኢህአዴግ ውስጥ በርካታ የወንጀል መረጃ ያላቸው ወገኖች አሉ። እንዲህ ያሉ ዜጎች በየትኛውም ዘመን አይረሱም። የቀን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ስማቸውና ታሪካቸው ከጨዋነታቸው ጋር ተመልሶ ህያው ይሆናል። ሌቦችና ነፍሰገዳዮች ወደ ህግ ሲያመሩ፣ እንደ አቶ ተስፋዬ አይነቶቹ የመጪው ትውልድ ታላቅ ምሳሌ ሆነው እየተወደሱ ህያው ሆነው ይኖራሉ” የሚል አስተያየት የሰጡት አቶ ኦባንግ፤ አቶ ተስፋዬ ያሰባሰቧቸው የሙስናና ተመሳሳይ ወንጀሎች ማሳያ ሰነዶች እጃቸው ላይ ስላለ አቶ ተስፋዬን በመግደልና በማስገደል ወንጀል ማድበስበስ እንደማይቻል ተናግረዋል።

የአቶ ተስፋዬ የቀብር ስነስርዓት ጋምቤላ መፈጸሙን ለመረዳት ተችሏል። ቤተሰቦቻቸውን በማግኘት ሆስፒታሉ ስለ አሟሟታቸው የሰጠውን አስተያየት ጠይቀን ለመረዳት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም።

 

 ECADF.COM

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ (መንግስት ለሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥ አሁንም እንጠይቃለን!)

ሰማያዊ ፓርቲ

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በርካታ ሕዝብ በተገኘበት ደማቅ ሆኖ ተካሂዷል፡፡ ለዚህ ሰልፍ መሳካት ከፍተኛ ድጋፍና አስተዋፅኦ ላደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የመገናኛ ብዙኃንና በሰልፉ ለተሳተፉ ዜጎች እንዲሁም ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ለረዱ የፀጥታ ኃይሎች ፓርቲያችን ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡Blue Party Ethiopia

ከዚህ በተቃራኒ ግን ይህንን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የገዥው ፓርቲ ባለስልጣናትና የመንግስት ተወካዮች የተለመደውን ተልካሻ አስተያየቶች ሰጥተዋል፡፡ የገዥው ፓርቲ ተወካይ ሰልፉን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት “የሐይማኖት አክራሪነት አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ድብቅ አጀንዳው ገሃድ ወጣ” በማለት በሰጡት አስተያየት ፓርቲውን ለማንቋሸሽና ለማራከስ ሞክረዋል፡፡ ይህም ፓርቲውን በእጅጉ ያስቆጣ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ መሰረተ ቢስ ፍረጃ የገዥው ቡድን አባላት ለንግግራቸውና ለሚሰጡት አስተያየት ሚዛን የሌላቸው ከመሆኑ ውጭ በፓርቲው ፕሮግራምም ሆነ እንቅስቃሴ ከአሸባሪነት ጋር የሚያገናኘውን አንዳችም ነገር አልጠቀሱም፡፡ ፓርቲው በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ እና በሕገ መንግስቱ በተሰጠው መብት ተጠቅሞ በሕጋዊ ሥነስርዓት ያደራጀውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በእንዲህ አይነት መንገድ መፈረጅ ሰልፉ ከተጠራበት ዓላማና መንፈስ በእጅጉ የራቀ አስተያየት ሆኖ አግኝቶታል፡፡

ፓርቲው ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ በሰጣቸው መግለጫዎች በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነት መቃወሙ ይታወሳል፡፡ ይህንኑ ጥያቄ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ወደ አደባባይ ይዞ መውጣቱ ሕገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ መሆኑን ይገነዘባል፡፡ ከባለሥልጣኑ የተሰጠው አስተያየት ግን የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ዜጎች በሰላማዊ መንገድ የተቃውሞ ጥያቄ ማቅረባቸውን ገዥው ፓርቲ በበጎ ጎን አለማየቱንና የመብት ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ሁሉ ወደ ሽብርተኝነት ፍረጃ ለመክተት የሚያደርገውን ጥረት የሚያመላክት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በተጨማሪም ገዥው ፓርቲ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ኢትዮጵያውያን ዜጎች እንደሆኑ አድርጎ እንደማያያቸውም ሰማያዊ ፓርቲ ተገንዝቧል፡፡

የመንግስት ተወካይ የሆኑት ባለስልጣን በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት በሰላማዊ መንገድ ተጠይቆና ታውቆ መንግስት ራሱ ያመነውና እጅግ ሰላማዊ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲካሄድ ያደረገን ፓርቲ ውጭ የሚገኙ ኃይሎች ተላላኪ አድርጎ ማቅረብ የአብዬን ወደእምዬ እንደሚባለው መሆኑን እየገለፅን ይልቁንም በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀሰውን ፓርቲያችንን መንግስት ከልቡ ሊቀበለው እንዳልቻለ አስገንዝቦናል፡፡ በተጨማሪም ይህ አባባል ሰማያዊ ፓርቲን የማይመጥን፤ ፓርቲውም በተግባር እያሳየ ያለውን ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚጥስ በመሆኑ አጥብቀን እናወግዘዋለን፡፡ እኝሁ የመንግስት ባለስልጣን በሰላማዊ ሰልፉ የተላለፉት መልዕክቶች ህገ መንግስቱን የሚንዱ ናቸው በማለት በደፈናው ህዝብን ለማታለል ከመሞከራቸው በተለየ የትኛው ሃሳብ የትኛውን የሕገ መንግስት ድንጋጌ እንደሚፃረር ካለማመልከታቸውም በላይ ፓርቲው በፍርድ ቤት ጉዳይ ጣልቃ እንደገባ አድርጎ ለማሳየት መሞከር የመንግስትን ግብር ለሰማያዊ ፓርቲ መስጠት ከመሆኑም ሌላ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ያደርገዋል፡፡

በመጨረሻም የእስልምና እምነት ተከታይ ዜጎቻችን ማንኛውንም የመብት ጥያቄ ከሌሎች ወገኖቻቸው ጋር በሰላማዊ መንገድ የማቅረብ ሕገ መንግስታዊ መብታቸው መሆኑን መንግስትም ሆነ ገዥው ፓርቲ እንዲያውቀው እያሳሰብን፤ ሰማያዊ ፓርቲ ከመንግስትም ሆነ ከገዥው ፓርቲ በሚሰጥ ማንኛውም ማስፈራሪያ ከጀመረው የሰላማዊ ትግል ጉዞ ፍፁም ወደ ኋላ እንደማይል፤ ይልቁንም የተነሱትን የሕዝብ ጥያቄዎች መንግስት በሦስት ወራት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥ አሁንም በድጋሚ ማሳሰብ እንፈልጋለን፡፡

ግንቦት 29 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

 Ecadf.com

ምርመራው ወደ አቃብያነህጉ ተዛወረ!

የሙስናው “ሻርኮች” በዒላማ ውስጥ?berhane

June 3, 2013 08:40 am By  Leave a Comment

* “አዲስ ነገር የለም” ጸረ ሙስና ኮሚሽን

በተለያዩ ከፍተኛ ወንጀሎች በተጠረጠሩ ሰዎች ላይ የተከፈቱ ክሶችን በማፈንና በመመሪያ ፍትህ በማዛባትና በማቋረጥ ወንጀል የተጠረጠሩ አቃቤያነህግ ላይ ምርመራ መጀመሩ ከፍተኛ ድንጋጤ መፍጠሩ ተሰማ። በተለይም ከወንጀል ጋር ቁርኝት እንዳላቸው በህዝብ የሚታወቁ ክፍሎች ክፉኛ መደናገጣቸው ተሰምቷል።

በሙስና የተጠረጠሩት የጉምሩክ ባለስልጣናት፣ ተባባሪ ነጋዴዎችና ደላሎች መታሰራቸውን ተከትሎ ከተፈጠረው ስሜት በላይ ከፍተኛ መደናገጥ የፈጠረው ዜና አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅዳሜ እለት ለንባብ ያበቃው ዜና ነው።

በቅርቡ ከሃላፊነታቸው የተነሱት የፍትህ ሚኒስትር አቶ ብርሀነ ሃይሉና ከአስር በላይ አቃብያነህግ በተለያዩ ጉዳዮች የተመሰረቱ ክሶች እንዲቋረጡ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው መመርመራቸው በትክክል ከተሰራበት ዋንኛ የሚባሉትን የሙስና ወንጀል “ሻርኮች” በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደሚያስችል ከፖሊስ ያገኘነው ጥቆማ ያመለክታል።

“የበርካታ ጉዳዮች ክስ እንዲቋረጥ መደረጉን እናውቃለን” በማለት ለጎልጉል ጥቆማ የሰጡት የፖሊስ አባላት “ይህ ጉዳይ ከተነሳና በትክክል ከተሰራበት የማይጎተት የለም” በማለት በትዕዛዝና በመመሪያ የተቋረጡ የምርመራና የክስ ፋይሎች በርካታ መሆናቸውን ያስረዳሉ።

ተቋማትንና ጉዳዮችን ስም በመጥራት መናገር እንደሚቻል የጠቆሙት ክፍሎች እንዲቋረጡ  የተደረጉ የክስ ሂደቶችን አስመልክቶ ህዝብ ነጻ መድረክ ቢሰጠው የተሻለ እንደሆነ አመልክተዋል። የፌደራል የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የቅርብ ሰው የሆኑ የጎልጉል ምንጭ በበኩላቸው “ኮሚሽኑ የመረጃና የማስረጃ ችግር የለበትም። በርካታ አቤቱታዎች ቀርበውለታል። ግን ሳይፈቀድለት መራመድ አይችልም” በማለት ማነቆው ከላይ እንደሆነ አስረድተዋል።

አሁን ስለተፈጠረው አዲስ ሂደት ሲያስረዱ “አዲስ ነገር የለም” በማለት ፍትህ ሚኒስትሩንና የፍርድ አስፈጻሚ አካላትን በስልክና በቃል መመሪያ በመስጠት ሲያዙ የነበሩት ክፍሎች አስቀድመው የሚታወቁና ኮሚሽኑ ከቁጥር በላይ መረጃ የሰበሰበበት እንደሆነ አመልክተዋል። ከደህንነቱ ጋር በቁርኝት የሚሰራው ኮሚሽኑ ራሱ ውስጥም ተመሳሳይ መነካካት እንዳለበት ጠቁመዋል። ዝርዝር ጉዳዩን ለመናገር አይቻልም ብለዋል።

አዲስ አድማስ አስር አቃቤ ህጉጋን እንደሚታሰሩ ጠቅሶ የዘገበው ዜና እነሆ

በቅርቡ ከስልጣን የተነሱት የፍትህ ሚኒስትር አቶ ብርሃነ ኃይሉና ከአስር በላይ አቃቤ ህጐች በሙስና፣ በሽብርተኝነትና በግድያ ወንጀል በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ የተመሰረተን ክስ ያለአግባብ አቋርጠዋል በሚል በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ምንጮች ገለፁ፡፡ ፖሊስ በሚኒስትሩና በአቃቤ ህጐቹ ቢሮ ባካሄደው ከፍተኛ ብርበራ በርካታ መዝገቦችን ማግኘቱንና ለምርመራ መውሰዱን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በፖሊስ ብርበራ የተገኙት መዝገቦች ያለአግባብ ተቋርጠው እንዲዘጉ የተደረጉ ክሶች ናቸው ተብሏል፡፡

ተከሳሾች ላይ በቂ ማስረጃ ማቅረብ ካልተቻለ ክሶቹን አቋርጦ መዝገቡን መዝጋት የፍትህ ሚኒስትርና የአቃቤ ህጐች ስልጣን መሆኑ ቢታወቅም ከሙስና፣ ከሽብርተኝነትና ከግድያ ጋር የተያያዙት እነዚህ በፖሊስ ብርበራ የተገኙ ከደርዘን በላይ የሆኑ መዝገቦች ግን፣ በቂ ማስረጃ እያለ፣ ያለ አግባብ የተቋረጡ ናቸው ተብሏል፡፡ ምርመራው ተጠናቆ እንዳበቃ በሚኒስትሩና በአቃቤ ህጐቹ ላይ ክስ እንደሚመሰረትም ምንጮች ጠቁመዋል። ለሰራተኞች አቤቱታ ምላሽ ባለመስጠትና በሥራ ድልድል በደል ፈጽመዋል በሚል ቅሬታ ይቀርብባቸው የነበሩት የፍትህ ሚኒስትሩ፤ በተለይ የጥብቅና ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ይታያሉ የተባሉ ችግሮችን እንዲፈቱ አራት የማሳሰቢያ ደብዳቤዎች ተጽፎላቸው እንደነበር ምንጮች ገልፀዋል፡፡ በሚኒስትሩ ላይ ከባለጉዳዮችም የተለያዩ ቅሬታዎች ይሰነዘሩ ነበር ያሉት ምንጮች፤ የታራሚዎች የይቅርታ ጥያቄን ማዘግየትና ተገቢ ምላሸ አለመስጠት በዋናነት እንደሚጠቀስ ገልፀዋል፡፡

በቅርቡ በተካሄደው የኢህአዴግ ዘጠነኛ ጉባኤ ላይ ከፓርቲው መሪዎችና አባላት ለሚኒስትሩ የቃል ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸው እንደነበር ምንጮች ገልፀው፣ ፓርላማም የመ/ቤቱ በርካታ ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡ በኢህአዴግ ዘጠነኛ ጉባኤ ላይ የአገሪቱ ዋና ችግር በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ላይ የሚታይ እንደሆነ መገለፁ ይታወቃል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ ሶስት ሚኒስትሮች በወንጀል ተጠርጥረው ከስልጣን የወረዱ ሲሆን፣ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ከአገር መኮብለላቸው ይታወሳል፡፡

GOOLGULE.COM

የአዲስ አበባ ልጆች አኮራችሁኝ!

እንደልቡ (ዳግም)

“ወጣቱ እንዲህ ሆንዋል እንዲያም ሆንዋል…” ወጣቱን ከማያውቁት ሰዎች የምሰማው የዘወትር መዝሙር ነበር። ወጣቱ ግን ማን እንደሆነ ባገኘው አጋጣሚ አስመሰከረ!!! ነጻነት የሌለው ህዝብ በበረት ዉስጥ እንደታጎረ እንስሳ ነው፣ ይህም ከፍተኛ የመዋረድ ስሜት ይፈጥርና አምሮን ይጎዳል፣ በሞራል ላይ ተመርኮዘን ማድረግ ከሚገቡን ነገሮች ሳናውቅ እንቆጠባለን፣ ውሸታም እና አስመሳይም እንሆናለን… ስለዚህ ነጻነታችንን ማስመለስና በራሳችን የምንተማመን ኩሩ ዜጋ መሆናችንን ማረጋገጥ እጅግ አስፈላጊ ነው።

ይህን የተገነዘቡት በካሊፎርኒያ የፖለቲካ ሳይንስ አስተማሪ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች ስለ ነጻነት፣ ክብርና ሞራል ሲያስተምሩ አይደክማቸውም… እነሆ ለነጻነታቸው ቀናኢ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ በህብረት ስለነጻነታቸው ሲዘምሩ የተመለከቱት ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም ብዕራቸውን አነሱ… እንዲህም አሉ፣

The long youth march to freedom and dignity has begun in Ethiopia. It is beautiful. It is beautiful because it is peaceful. It is beautiful because it is motivated by love of country and love of each other as children of one Mother Ethiopia. It is beautiful because Ethiopia’s youth in unison are shouting out loud, “We can’t take anymore! We need change!” History shall record that on Ginbot 25, 2005 Ethiopia rose from the pit she has fallen into on the wings of her youth.

የፕሮፌሰር አለማየሁን ሙሉ ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Over one hundred thousand young men and women marched in the streets of Addis Ababa

On Ginbot 25, 2005, over one hundred thousand young men and women marched in the streets of Addis Ababa demanding the release of political prisoners, religious freedom, respect for human rights and the Constitution and public accountability.

ECADF.COM

ለደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መዕመናን የቀረበ ጥሪ

ለደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መዕመናን የቀረበ ጥሪ

debreselam

May 29, 2013 07:49 am By  Leave a Comment

የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች ይኸውም ለሥልጣን ያቆበቆቡ እሾም ባዮች ፣ ለጥቅማቸው የቆሙ ግለሰቦች እና ሆድ አደሮች የሀገራችው ፣ የሕዝባቸው፣ የቤተ ክርስቲያኗ ገዳማውያን እና መናንያን  ሐዘንና ሰቆቃ ሳይገዳቸው እኔ ከሞትኩኝ ስርዶ አይብቀል እንዳለችው አህያ የግል ቀቢጸ ተስፋቸውን (ego) ላማሟላት ብቻ ቤተ ክርስቲያኗን ለወያኔ አሳልፈው ለመስጠት መሰናዶአችውን ጨርሰውና ወገባቸውን ጠበቅ እድርገው ተነስተውልህ June 2, 2013ን በትልቅ ጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ (በነገጋችን ላይ ስለ June 2, 2013 ለማታውቁ ወይንም ላልሰማችሁ ለማሰማት ይረዳ ዘንድ….. June 2, 2013 የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ ትቀላቀል ወይንስ አትቀላቀል የሚለው ውሳኔ ይሰጥ ዘንድ የቤተ ክርስቲያኗ የአስተዳደር ቦርድ ስብሰባ የጠራበት ዕለት ነው፤ ስብሰባውም ከቅዳሴ አገልግሎት በኋላ ይከናወናል)።

በኢትዮጵያ ገዳማት እና አድባራት በመነኮሳት እና በመናንያን ወገኖቻችን ላይ የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት የሚፈጽመውን የዘር ማጥፋት እና ማፅዳት፣ የገዳማት እና አብያተ ክርስቲያናት መቃጠል፣ መፍረስ፣ መዘረፍ እና መታረስ ሳይገዳቸው፤ በኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ በተለያዩ ቦታዎችና ግዜያት ለምሳሌ ያህል ከቡዙ በጥቂቱ በሐረር፣ በእርሲ አርባጉጉ፣ በጉራ ፈርዳ፣ በአፋር፣ በጋንቤላ፣ በደቡብ ህዝቦች ከልል፣ በጂማ፣ በአሶሳ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባ በ1997 ከተካሔደው ምርጫ በኋላ፣ በአዋሳ፣ በበደኖ፣ በአርባጉጉ፣ በአርሲ አሳሳ፣ በቤኒሻንጉል ህዝባችን ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ የተናጠል ግድያ፣ አማራው ወልዶ ከሳመበት አርሶ ከቃመበት ቀዬው/ሠፈሩ የዘር ሐረጉ እየተመዘዘ ሲባረር፣ እስራት፣ መከራ፣ ስቃይ፣ ግርፋት፣ እርዛት እና ረሐብ ሲቆላው እያዩ እና እየሰሙ የወገናቸው እና የህዝባቸው ሥቃይ፣ መከራ፣ ሰቆቃ እና ዋይታን ወደጐን በማለት በሌላው ላይ የሚደርሰው ግፍ የማይሰማቸው ካህናት እና መዘምራን የደንቆር ለቅሶ መልሶ ቀልሶ ይሉ ዘንድ አባት ያስፈልገናል በሚል የሐሰት ቅጥፈታቸው፣ የግል ፍላጐታቸውን ለማሟላት እና በወያኔ የተሰጣቸውን የቤት ሥራ ለመስራት ሲሉ ብቻ ቤተ ክርስቲያኗን፣ አንተን እና አንቺን አሳልፈው ሊሸጡህ/ሊሰጡህ የተዘጋጁ ሥለሆነ አንተም ጠንቅቀህ እውነታውን ተረድተህ እና ነቅተህ ቤተ ክርስቲያኗን ልትጠብቅ ይገባሃል።

ህዝበ ክርስቲያኑን እኛ እናውቅልሀለን፣ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ቆመናል፣ አባት ያስፈልግሃል እኛም አባትህ ነን የምንልህን ስማ ካላችሁ ምነው ታዲያ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ተባረው ወደ ጐጃም ሲጋዙ የተጫኑበት አይሱዙ ተገልብጦ አባይ በረሃ ላይ ከ 60ዎቹ 59ኙ ያለቀባሪና ያለአንሺ አስክሬናቸው የአውሬና የአሞራ ሲሳይ ሲሆን በደብረ ሰላም ቤተ ክርስቲያን ፀሎት አልተደረገላቸው፣ የዝቋላ ገዳማት ሲጋዩ፣ የዋልድባ መናንያን ከገዳማቸው ሲባረሩ ምነዋ የኛዋ ደብረ ሰላም በፀሎት አላሰበቻቸውም??? ባለፈው ቦስተን ላይ በደረሰው የሽብርተኞች ጥቃት ለሞቱት ፀሎት ሲደረግላቸው የኛን ግን ረሳናቸው!! ነው ወይንስ የዋልድባ አሳዳጆች የኛን ካህናትም ወዮላችሁ አሏችሁ፤ ካሏችሁ መቼስ ምን ይደረጋል

ፈሪ ለእናቱ ያገለግላል፣

ምጣድ ስትጥድ እንሰቅስቅ ይላል፣ ይባል የለ፤ ለማንኛውም የምንኖረው በ21ኛው ክፍለ ዘመን ስለሆነ በሃገራችን እና በቤተ ክርስቲያንናችን ላይ የሚደርሰውን ጥፋት፣ ውድመት እና ዘረፋ በስማ በለው ሳይሆን በቀጥታ በየእለቱ መከራውን ቀማሽ ከሆነው ህዝባችን ስለምንሰማው ልትሸነግሉን ባትሞክሩ መልካም ነው፤ ይልቁንስ ለእውነት ስለእውነት ቆማችሁ ሃገራችንን እና ቤተ ክርስቲያንናችንን በጋራ ብንታደጋት ለወደፊቱ ይበጀናል ይበጃችኋል።

አንዳንድ ካህናት በቤተ ክርስቲያኗ ዓውደ ምህረት ስብከታቸው ላይ ወደ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ (ሀገር ቤት ያለው በአባይ ፀሐይ እና የፌድራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶ/ር ሺፈራው ተ/ማርያም የሚመራውን ሲኖዶስ (በነገራችን ላይ ዶ/ር ሺፈራው ተ/ማርያም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ናቸው) ከፓትሪያርክ ምርጫ በፊት ሲኖዶሱን ሲመሩት እንደነበረ የሚዘነጉት አይመስለንም) እንግባ እያሉ የሚያደነቁሩን ከቤተ ክርሲቲያን ውጪ ደግሞ የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን ሲኖዶሱ/የኮሌጁ አስተዳደር ከመኖሪያና መማሪያ ግቢ ባባረራቸው ወቅት ተማሪዎቹ የሚበሉት የሚጠጡት የላቸውምና እባካችሁን ለእነርሱ እንድረስላቸው እያሉ የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን የገንዘብ መለመኛ ያደርጓቸዋል። ነገሩ ለበጎ ቢሆነ ባልከፋ ነበረ ነገር ግን በአደባባይ ትክክለኛው ሲኖዶስ ኢትዮጵያ ነው ያለው፣  ሲኖዶስ አይሰደደም እያሉ የሚሰብኩ ነገር ግን ለገንዘብ መለመኛ ሲሆን ሲኖዶሱን ከሰውና ወቅሰው ከስንቶቻችሁ ገንዘብ አንደሰበሰቡ ቤት ይቁጠረው ገንዘቡም ይድረስ አይድረስ ለሰብሳቢው ካህን ትልቅ የጥያቄ ምልክት ? እያኖርኩኝ፤ ከቤተ ክርስቲያኗ አውደ ምህረት ውጪ ሲሆን ግን የተማሪዎቹ መባረር ስህተት ነው፣ ሲኖዶሱም የሚሠራው ሥራ ትክክል አይደለም፣ ጥፋት እየተፈፀመ ነው ብለው ካመኑ፤ ሲኖዶሱንም እያወገዙ ገንዘብ ከለመኑ ታዲያ ምነው ሲኖዶስ አንድ ነው፣ አይሰደድም፣ እሱም ኢትዮጵያ ያለው ነው፣ ትክክልም እየሠራ ነው፣ እሱን ልንከተል ይገባናል አያሉ አውደ ምህረት ላይ ለምን ይሰብካሉ (ባንድ ራስ ሁለት ምላስ ይሏል ይህ ነው)።

እውነታውን አንነጋገር ከተባለ ምነው የአቡነ ጴጥሮስ ኃውልት ሲነሳ በዓውደ ምህረት ላይ አንድ ካህን አልተነፈሰም ያውም የአቡነ ጳውሎስ ኃውልት በሲኖዶስ ውሳኔ እንዲፈርስ ተወስኖ ሳለ፣ የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ከትምህርት ቤቱ ግቢ ሲባረሩ ያውም ምግብ ተከልከለው የእለት ጉሮሮአቸውን አንኳን ለምነው አንዳይዳፍኑ በፖሊስ እየተሳደዱ ባሉበት፣ የዋልድባ መናንያን ቋርፍ በልተው ከሚኖሩባት ገዳማችው እየተባረሩ ወደ ነበሩበት ገዳም ለመመለስ ሲጠይቁ ወደ እዚህ ከምትመለሱ አናታችሁ ማሕፀን ብትመለሱ ይሻላችሗል ሲባሉ፣ በሰደፍ ተደቅትው ሜዳ ላይ ሲጣሉ፣ እንደ ሕፃን በአለንጋ ሲገረፉ በልምጭ ሲለመጡ፣ ከወፍጮ ቤት ገቢ ያሰባሰቧትን 60, 000 (ስልሳ ሺህ ብር) በአደባባይ በመንግስት ታጣቂዎች በጠራራ ፀሐይ ሲዘረፉ፤ ዝቋላ፣ የአሰቦት ገዳም፣ ታሪካዊ መጽሐፍት አና ቅርሶች ያሉባችው ደብሮች እና ገዳማት ሲጋዩ፣ በምዕራብ ጎጃም ጣና በለስ አካባቢ ያሉ አብያተክርስቲያናት እንዲፈርሱ በወያኔ ሲወሰን ምነው አንድም ቀን በቤተ ክርስቲያኗ ዓውደ ምህረት ላይ አልሰበኩ መልሱን ለአንባቢያን እና ለሰባኪያኑ እተወዋለሁ።   የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በተባረሩ ሰሞን አዲስ የተሾሙት ፓትሪያርክ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ (VOA http://amharic.voanews.com) ተጠይቀው ይህ ጉዳይ እኔን አየመለከተኝም ሲሉ የሲኖዶሱ ፀሐፊም ተመሳሳይ መልስ ለኢሳት (Ethiopian Satellite TV/Radio www.ethsat.com) ሲሰጡ እንዲያውም ይባስ ብለው በሌላ ቃለ መጠይቅ እኚሁ የሲኖዶሱ ፀሐፊ ተብዬው አቡነ ህዝቅኤል ስለ ዋልድባ ገዳማውያን እንግልት ጥያቄ ቀርቦላችላቸው “ማርያምን አልሰማሁም” ሲሉ መስማቱ አያሳዝንም። ታዲያ የቤተ ክርስቲያኗ የበላይ ተብዮዎች አያገባንም ካሉ ማ ሊጠየቅ ኖሯል በቅጥፈት እውነትን ለመሸሸግ መሞከሩ ከተጠያቂነት አያድንም፤ ነው ወይንስ የተሾሙት አባት ተብዮዎች ወንበር ለማሞቅ የተቀመጡ ጉዶች ናቸው?? ለነገሩማ ከአነጋገራቸው ለመረዳት እንደቻልነው ምንም ነገር ከመተንፈሳቸው በፊት ከመንግስት አካል ትዕዛዝ/መመሪያ መጠበቅ አለባቸው፣ እህህህ ከማለት ውጪ ምን ይባላል የሚሰብኩትን ወንጌል ሰባኪ ብቻ ሳይሆኑ ፈፃሚም ያድርጋቸው።

ታዲያ የደብረ ሰላሞቹም ካህናት እራሳቸውን አዋቂ ሌላውን አላዋቂ ለማስመሰል ስለ ዮዲት ጉዲት፣ ግራኝ መሀመድ አና ስለ ሌሎችም በቤተ ክርስቲያኗ ላይ ስለደረሱት ጥፋቶች በተደጋጋሚ ሰበኩን፤ አዎ በጣም ብዙ ብዙ ጥፋቶች እና ውድመቶች በዮዲት ጉዲት እና በግራኝ መሀመድ ተፈጽመዋል ይህንን የካደ በደብራችን ማንም ሰው የለም ወይንም አላጋጠመንም ነገር ግን አሁንም ከዛ ባልተናነሰ መልኩ ቤተ ክርስቲያኗን  እያጠፏት እና እያወደሟት ስለሆነ ከእነርሱ ጋራ አንተባበርም፣ ከእነርሱ ጋራ ቤተ ክርስቲያኗን አናጠፋም ነው እያልን ያለነው፤  ካህናቶቹ እያላችሁ ያላችሁት ግን ከአጥፊዎች ጋር ተባበሩ፣ ከአጥፊዎች ጋር እጥፉ ነው፣  ዮዲት ጉዲትም መጥታ ስለ አንድነት እየሰበከች ቤተ ክርስቲያንን ብታጠፋ ከእርሷ ጋር ተባበሩ እያለችሁ ነው፤ አሁንም ደግመን ደጋግመን የምንለው ከአጥፊዊች ጋር አንተባበርም ነው።

ይሁዳ ጌታን አሳልፎ በመስጠቱ ያገኘው ፀፀትና ሐዘን እንጂ ፍሰሐ እና ደስታ አልነበረም እናንተስ እኛን አሳልፎ በመስጠት የምታገኙት ደስታ ምን ይሆን??? መልሱን ለእናንተው እተወዋለሁ።  ለማንኛውም ለሹመቱ ጉጉት ያሎት ጠቀም ያለ ገንዘብም ያዘጋጁ በቅርቡ ሐራ ተዋህዶ አንደዘገበችው ከሆነ ለደብር እልቅና በአነስተኛ ግምት እስከ ብር 80,000 (ሰማኒያ ሺህ) ፣ ለፀሐፊነት አስከ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር ጉቦ መስጠት ይጠበቃል (ለዝርዝሩ ይህን ሊንክ ይክፈቱ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/3506)፤ አሁን አሁን ደግሞ ሰውን አሳልፎ በመስጠት ብቻ ጵጵስና የሚገኝበት ዘመን ላይ አይደለንምና!!! ያውም ካገኙ፤ በቅርቡ ከቤተ ክህነት እንዳፈተለከው ወሬ ከሆነ ሦስተኛ መመዘኛም ተመዟል (መቼም የትግራይ ህዝብ ፈርዶበት በስሙ ይነገዳል) ከትግሬ በቀር ሌላው ቤተ ክህነትን አይረግጥም እየተባለ ነው፤ ታዲያ የኛዎቹ ጉዶች ሌላውን መመዘኛ ብታልፉ ይሄኛው ሳይጥላችሁ አይቀርም (አበስኩ ገበርኩ) ።

አንድነት አንድነት እያሉ የሐሰት ነጋሪታቸውን የሚጐስሙና የውሸት ጥሩንባቸውን የሚነፉ ግለሰቦች ስለ እውነተኛው አንድነት ቢለፉና ቢደክሙ ምንኛ መልካም ነበረ፤ በቅርቡ በአዳባባይና በሚዲያ ወጥተው አማራና ኦርቶዶክሱን አከርካሪውን ሰብረነዋል እያሉን አንዴትስ ነው ከአከርካሪ ሰባሪዎች ጋር አንድ የምንሆነው፤ ይልቁንም የእነርሱ የገደል ማሚቶ ሆኖ የሐሰት ጩኸታችውን ከማስተጋባት ቤተ ክርስቲያናችንን በህብረት ብንሰራ ምንኛ በተሻለ ነበር ይልቁንም በአስራ አንደኛው ሠዓት ላይ የራሳቸውንም ሆነ የቤተ ክርስቲያኗን ሠላምና አንድነት ከሚነሱ አርፈው ቢቀመጡ እንመክራቸዋለን። ለመሆኑ እስቲ አንድነት አንድነት የሚሉትን አንድ ጥያቄ ልጠይቃቸው፤ ባለፈው በዳላስ ቴክሳስ የነበረውን የአንድነት ጉባኤ የበተነው ማነው፣ ጉባኤው ሳያልቅ ከኢትዮጵያ መግለጫ ያወጣው ማነው፣ በሰላም ጉባኤው ላይ የተካፈሉትን ቄሶች መስቀል ነው ያለውስ የህወኃት መስራች የየትኛው አካል ይሆን???? እኛማ የኢትዮጵያን አንድነት እና የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት አጥብቀን እንሻለን እናንተ የምትድግፏቸው ግን ወገኖቻችንን አሳደዷቸው የኢትዮጵያ አንድነት እና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ስላሉ ገደሏቸው፣ ተከብሮና ተፈርቶ የኖረውን ገዳም አትንኩብን ባሉ ገረፏቸው፣ ቀጠቀጧቸው፣ የቤተ ክርስቲያኗን ሀብት እና ቅርስ ዘርፈው ሸጡ፣ ገዳማትን አቃጠሉ፤ ታዲያ አንድነቷን ያሳጣ ሰላሟን የነሳ የትኛው አካል ይሆን???? ጉድ ሳይሰሙ መስከረም አይጠባ ይባል የለ……

እሁድ May 19, 2013 አቡነ ዘካሪያስ በራችስተር ሚኒሶታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ንግስ እና የአዲስ ቤተ ክርስቲያን ግዢ ምርቃት ላይ ተገኝተው በነበረበት ወቅት በተደረገው ስብከት ላይ ባካበቢያችን ሦስት ቤተ ክርስቲያናት ብቻ እንዳሉ እና ሶስቱም በኢትዮጵያ ሲኖዶስ ስር እንዳሉ አድርጐ የተሰበከውን ስብከት አንቀበለውም።  አቡነ ዘካሪያስ የጐጃም ክፍለ ሃገር ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት እናቶችና አባቶች ከልጆቻቸው ጉሮሮ ነጥቀው ለቤተ ክርስቲያን የሰጧትን ምፅዋት ዘርፈው ወደ አሜሪካን በአቡነ ጳውሎስ የተላኩ ናቸው። ይህንንም ከጎጃም አካቦቢ የመጣነው ጠንቅቀን  እናውቀዋለን፣ እርሳቸውም ቢሆኑ ሳይክዱ በኤሚሪካን ድምፅ ራዲዬ ቀርበው በማመን ከልጆቻቸው ለምነው እንደሚከፍሉ ለአቶ አዲሱ አበበ በቃለ መጠይቁ ወቅት የእምነት/ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።  አቡነ ዘካሪያስን፤ አባታችን አባታችን ለሚሉት አንድ ጥያቄ እናስቀምጥላቸው፤ እንደተባለው እና እንዳመኑት የወሰዱትን ከ 1.5 ሚሊየን ብር በላይ ከምን ከተቱት፤ ቤት ሰርተውበት እያከራዩት ይሆን ወይንስ???? እርሳቸውን ብትጠይቁልን??  ሌላው እኚሁ አቡነ ዘካሪያስ በራችስተር ሚኒሶታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ንግስ በኋላ በዕለቱ በበዓለ ንግሱ ላይ የነበሩትን ካህናት እና መዘምራንን ሰብስበው በርቱ የምትሰሩትን መልካም ሥራ እየተከታተልን ነው በማለት ተጨማሪ የቤት ሥራ ሰጥተዋቸዋል፣ ያቺ June 2 ደርሳ ማን ከኢትዮጵያዊያን ማን ከወያኔ እና ከቤተ ክርስቲያን ዘራፊዎች ጋር አንደሚወግን እንተዛዘባለን።

እነሆ ሀገር ወዳድ የሆንከው ኢትዮጵያዊ በሙሉ ይህችን ቤተ ክርስቲያን ከጥፋት ትታደጋት ዘንድ ጥሪያችንን ስናቀርብ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የወያኔን በስመ አባይ ቦንድ ሽያጭን (እዚህ ላይ ወገኔ እንድትገነዘብ የምንፈልገው ሀገር ብትለማ የሚጠላ ማንም እንደሌለ ልብ ይሏል፤ ይሁን እንጂ የሚሰበሰበው ገንዘብ የሚውለው ያንተኑ ወገን ለማፈናቀያ እና ለማሰቃያ እንጂ ለሀገር ልማት ቢውልማ ማን ይጠላ ነበረ!!!) በደቡብ አፍሪካ፣ ሒውስተን ቴክሳስ፣ ሳንዲያጎ ካሊፎርኒያ፣ በኖርዌይ ስታቫንጋር አሳፍረህ እንደመለስክ ዛሬም ይህንኑ እንድትደግም አንቢ ቤተ ክርስቲያኔን ለወያኔ መፈንጫ ገንዘቤን ወገኔን ለማፈኛ አሳልፌ አልሰጥም የምትል ሁላ June 2, 2013 በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን (4401 Minnehaha Ave S. Minneapolis MN) ተገኝተሽ/ህ ድምፅሽን\ህን እንድታሰሚ\ማ።

በመጨረሻም ከአንድ ድረ ገጽ ያገኘነውን ቀንጨብ አድርገን እናካፍላችሁ እና ፅሑፋችንን ለዛሬው በዚሁ እንግታ “ወያኔ መራሹ ዘረኛ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ለማጥፋት ኢላማውን ካነጣጠረ እነሆ 21 ዓመታትን አስቆጠረ። ወያኔ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት በግልፅ የግድ ወታደር ማዝመት አይጠበቅበትም ለምን ቢባል ገና በደደቢት እያለ ያሰለጠናቸውን ልዩ ሃይል መነኩሴ በማስመሰል አሰልጥኖ በመላክ ተልዕኮውን እያሳካ ይገኛል” (ከጥላ መጽሔት)

goolgule.com

Africa Union: Is it a Union of brutal tyrants or the people of African?

Imagine in today’s Africa finding a leader capable of forming a regional organization like OAU. Imagine a leader that stand out as role model for African leadership in the 21stcentury. And, imagine when an African leader would emerge that would earn universal respect like Mandela.

My people, Africa is a play ground for dictators acting like domesticated wolf during the day a hyenas in the night. The few leaders that have the mandate of their people found Africa Union a retreat; a kind of resort to do what they wouldn’t be able to do at home. Shame-on all of them to coddle up with daylight wolves and the hyenas of the nights.

by Teshome Debalke

On the occasion of 50th anniversary of African Union (the former Organization of Africa Unity) another history was made. In a city where the Headquarter of the organization was erected and the country that was the instrument in uniting Africans is occupied by the brutal ethnic tyranny that divides her population by ethnicity and religion; in direct contradiction to the very Charter of the foundation and with the help of the international community.

The visionary leaders that brought about African Unity are replaced by demagogues, corrupt, and brutal tyrants taking the organization down with them. Our own rogue regime not only denies the existence of the nation that is the founding member but, doesn’t recognize the Founding father of the Organization himself. Fifty years later the striking difference between African leaders then and now is telling.

In all honesty, I am sick and tired of being sick and tired of hearing about Africa Union. I don’t know why people make a big deal of an Organization that turned in to good-for- noting; taken hostage by barefaced dictators. The Organization did its work when it was established 50 years ago with clear vision and great leaders of the time to end up into an entertainment hall of mindless dictators financed and built by Chinese Communist Regime.

On the occasion of 50th anniversary of African Union Africa Union a union of brutal tyrants

 

 

 

 

 

No offense to the Chinese regime, but the communist tyranny would do us a great favor if it builds freedom centers for its own people than AU Headquarter to dance with African wolves in order to tap in what is underground in partnership with mindlessly corrupt dictators. For sure a regime that builds on the grave of its own people’s freedom can’t be a friend of Africa. The most expected of the Chinese government is to be a bed fellow with its counterparts for mutual distraction of the people.

Imagine when the clowns couldn’t pitch a few million dollars each from the money they have been stealing to finance the only building that symbolize African Unity. Don’t they have any pride to beg the Chinese authoritarian regime to sell the symbol Africa for cheap as they do the raw materials of their peoples?

I think the regime that occupied Ethiopia would do its counterparts  a favor to sell African Union bond to build a new headquarter and make the Chinese made building a shopping mall to sell cheap Chinese made goods Siyoum Mesfin, the Ethiopia Ambassador in China and Associates import. It would make more sense for a part-time merchant, part-time government and part time beggar regime.

As we speak, 50 years later since the organization was founded the majorities of the member countries of African Union are ruled by brutal and corrupt tyrants brutalizing and robbing their respective people. Their biggest accomplishment is noting more than reducing their respective population in poverty into sub human condition and turn around begging from the international donors and pretending they are running governments. The donors are not helping either.  They handover billions of dollar to tyrants in Africa without asking the hard question as they do the exact opposite at home. It must be the policy of ‘he may be a son of a bitch but he is our son of a bitch’

I am more sick and tired of half a dozen elected leaders of member countries like South Africa, Botswana, and Ghana…too. Wining and dining with brutal and corrupt dictators; going along with them as if everything is nice and dandy with the dictators-for-life, instead of raising the cause of the people of Africa. In fact, during the Libyan uprising to oust Kaddafi the African dictators were embarrassingly showing the true color; refusing to recognize the Transitional Council until the last day of the 42 long years old dictator bit the dust. Even democratically elected leaders sided with Kaddafi instead of the leaders of the revolution. In our own home turf, the Union of Dictators validated the Woyane regime’s 99.64% win in 2010 election as if they don’t know how to count; claiming it is fair and square and decided to dance with the Woyane wolf. These are the kinds of leaders Africans are subjected in the 21st century.

When The Organization of Africa Unity (OAU) was formed it was to fend off the European Colonialists’ aggression in the scramble for Africa’s resources. Fifty years later it turned out to be Africans are still struggling to fend off from African dictators and their partners’ scramble for Africa’s resources. What changed is the color of the dictators from white Europeans to black Africans, from strong national and regional leaders to ethnic peddlers at village level.

Here we are in the 50th anniversary of an organization that supposes to free Africans from exploitation progressing in to the organization of Exploiters/Beggars Country Club. To add salt on the wound the capital city where it was founded and headquartered is occupied by an ethnic tyranny (Woyane) that wouldn’t recognize the Founding father of the Organization, His Excellency Emperor Haile Selase I; the icon and the father of Africa in his own right and time.

In all honesty, to begin with the Organization wouldn’t form if it wasn’t for the visionary leadership of the Emperor himself. But, as our contemporary dictators would have it the best of Africa would overshadow their despicable rule; therefore, they make sure there is noting before and after them as the late Melese Zenawi helplessly undermine great Ethiopian leaders and raise his and his counterparts empty stature in the Club of Tyrants. The genocide craved Bashir of Sudan is a kind of tyrant AU protects from going to jail.

Imagine in today’s Africa finding leaders capable of forming a regional organization like OAU. Imagine a leader that stand out as role model for African leadership in the 21stcentury. And, imagine an African leader to come that would earn universal respect after Mandela. My people, Africa is a playground for dictators acting as domesticated wolfs during the day and hyenas in the night. The few leaders that have the mandate of their people found Africa Union a retreat, a kind of resort to do what they wouldn’t be able to do at home. Shame on all of them dancing with wolves; leaving the people of Africa on the dry.

The degeneration of African leadership is better explained by the late Ethiopian Prime Minster, Melse Zenawi. When he was picked as unofficial representative of African dictators in the world forums AU proven it is a worthless organization.  His skills that earn him the job was begging and making dictators feel righteous. No one can match his skill and legacy. From begging Western nations for basic food and medicine in pretending to feed and cure the people all the way of building infrastructure and a meeting hall for tyrants from Eastern nations; the ‘visionary leadership’ of the late Melse Zenawi unmatched.

The man became a legend in African Dictators’ Club for extorting more money from Western and Eastern donors like no one has done it before. For example, in Climate Change Summit of 2009 in Copenhagen he instigated African dictators to demand 80 billion dollars compensation from industrialized nations for ‘causing draught…famine because of ‘carbon emission’. Dictators that can’t tell the difference between their personal accounts from the public vault let alone understand climate change all of a sudden were lined up to cash in with the new opportunity. Guess who they picked to represent them, Melse Zenawi of Ethiopia.

Quite frankly, the late Melse was exceptionally good maneuvering African tyrants and Western cash cows. He even organized environmental cadres in Addis Ababa and flew them to Copenhagen to demonstrate against ‘Western imperialists’; blaming them for bringing famine and poverty in Africa to force them cough up more money to compensate the ‘African poor’ through dictators’ bank. He was indeed professional extorter in squeezing dollar from donors that earn him his popularity until Journalist Abebe Gelaw interrupted him in front of the world for ever. Melse hasn’t missed a single conference of the rich countries in 20 years where there is money to be gained. In fact, he was the darling of the West they couldn’t do without to feel they are doing something for Africa. The infamous Susan Rise, the US Ambassador to United Nation vows for his wit acting as Ambassador of his regime when in reality he was playing her for a fool to defend him in Washington.

African tyrants learned so much from him they become savvy enough to play the world powers in sustaining their power and robbing their people in collaboration with indigenous and Western professionals covering for them. The cry for democratic rule is sidelined by elaborate diversion of development that filled international Media, thanks for the legendry con man of Africa.

The Mo Ibrahim Foundation that offers The Ibrahim Prize for Achievement in African Leadership tells the story of the African dictators for life. The Prize offers US$5 million over ten years US $200 000 per year for life thereafter and US $200 000 per year available for public interest activities for any tyrant that leave office peacefully. The Criteria is simple; must be a Former African Executive Head of State or Government, must be democratically elected, must be a leader that left office in the last three years, must served only his constitutionally mandated term and must be exceptional leadership.

It looks a very lucrative prize/bribe to ask African dictators to leave power they hold on by the barrel of the gun for too long. It is also embarrassingly insulting to all Africans their leaders wouldn’t budge even when offered bribe to leave the office that doesn’t belong to them.  In politically incorrect language they wouldn’t take the ransom money to release the hostages (African people) they held at gun point. Think about it, how low an organization can go down? Imagine how low expectation Western and increasingly Eastern donors have about Africa to sleep with the Wolves of Africa.

The Prize would be good chunks of money for honest and hard working leader do right. But, for African dictators that steal billions of dollars it is rather pocket change. So far three African leaders received the Prize, according to the Foundation. But, Western governments and organizations continue to defend African tyrants by rewarding them with more money than the reward Prize. Why settle for less when there are more money to be had being a dictator.

To show how small a Prize is for African dictators the late Libyan tyrant Kaddafi comes in mind.  He holds a fortune of over 300 billion dollars managed by his son in European Banks as reported. That is just one chunk, investments in many countries and money stashed by his friends and relatives could be billions more. Obviously, five million sounds for dinner outing to the flamboyant Kaddafi known to spend money like paper. Likewise the Egyptian, the Nigerian, Tunisian…and the rest wouldn’t be impressed with little Prize either.

When it comes to our mini tyrant like the late Melse Zenawi, his Endowment stashed in the name of the people of Tigray worth billions of dollars. For a ‘poor dictator’ that lives on few hundred dollars salary per month according to his wife, Ibrahim Prize could have been a good incentive to vacant power if he ever qualifies for it. But, he is recognized by Western governments as a ‘great leader’ worth a lot more. Why look for chuck change from Ibrahim Prize when donors throw you money as drunken gambler in a strip club. Better yet, his cheerleaders are putting a Foundation for him to award Prizes instead of receiving it.

Dictators are always dictators wherever they may be, it is a historical fact. The problems aren’t the dictators per say but their jackass apologists that legitimize them by adding numbers backwards with their hands in the same cookie jar; insulting supporters on a daily bases as dumb airheads to understand elementary arithmetic.

Let’s take the apologist of Woyane and its supporters. They are conditioned to act like a jackass tied up with Woyane tyranny. They are trained to read backwards to feel good about themselves.   But in reality, besides wearing pants and skirt they are no better than a jackass. Like typical jackass the only thing they demand is anything and from anywhere to fills their belly. They are conditioned not to ask where, why, when how…but take what is given to them like a jackass.

No one knows why Woyane insults its supporters on a daily bases and they accepting it with pride. But, according to psychologist, conditioning is ‘a behavioral process whereby a response becomes more frequent or more predictable in a given environment as a result of reinforcement, with reinforcement typically being a stimulus or reward for a desired response’.

Surprisingly, Conditioning equally works on well educated as much as to uneducated. Therefore, tyrants use it extensively to make a jackass out of the people they call their supporters. Obviously, the well feed jackasses are the role models for the rest. Time-and- time again they failed to understand the public interest can’t be marginalized by size of jackasses’ belly of tyranny dressed up as human beings.  They misunderstood; it isn’t the dress that makes them humans but their behavior.  In their quest to make the population in their image they marginalize and jail those that think critically like human beings.

Anyway you shake-or-bake-it there is noting good that can come out of tyranny and the jackasses that support it. Anyone that tells you otherwise is a jackass of the worst kind that voluntarily shutoff his/her mind to think with the belly, unfortunately, there are many of them out there. Those jackasses that wave their credential on your face are the bigger jackasses of all. What good is a credential but a paper when the belly is doing the thinking?

Recently Ethiopian Satellite Television (ESAT) put out a warning to the jackasses of tyranny (the officials) in a title ‘ኢሳት ጋዜጠኞች ጆሮ ላይ ስልክ ለምትዘጉ ባለስልጣኖች ማሰጠንቀቂያ’. The warning is timely but, there is more than Woyane officials that fart like a loaded jackass every time they are confronted with the hard question.

In my opinion, the worst jackasses of Woyane are the apologist in Diaspora that runs front organizations, Medias… etc.  Their phone must start ringing to come out in public and explain why they are disturbing the peace of the public on behalf of Woyane. The truth is the jackasses in Diaspora that eat the fruit of freedom and prevent their compatriots to do the same on behalf of their beloved tyranny must pay a big price. They are the one that carry tyranny on their shoulder defending it tooth-and-nail. The house of Woyane tyranny is standing because of them. The struggle will be short and sweet when the jackasses of tyranny in Diaspora are forced to come out of the closet they are hiding. As Woyane officials, the Diaspora jackasses will run like a loaded jackasses farting.

Africans in general must standup to the jackasses of their respective tyranny. It isn’t only to free the political space but, the minds and body of the young and old to think critically in order to own our rightful place in the modern world. The jackasses of tyranny are interfering in our quest to own our place in the world community. You can find them in the world stage dressed up to talk with both side of their mouth to defend tyranny; thinking in their bellies than their mind. They must be exposed and challenged in public arena like they would in free societies. Independent Medias in-and-out of Africa must come together to chase out the jackasses to make tyranny history in Africa and Africa Union (AU) tyrants free.

Likewise, Ethiopians and Ethiopia will not only be free from tyranny but, from the jackasses that carry it on their shoulders. There is no if-and-but about it.  Anyone that doubts that reality is a jackass wants to be on the expenses of Ethiopians. The only thing to do is out the jackasses of tyranny in public and, no one can do it better than independent Mass Media like ESAT. Now you know why the jackasses of Woyane are farting on ESAT.

Have you encounter a jackass of Woyane lately?

 

 ECADF.COM

በጥቁር ገበያ የዶላር ዋጋ በሰላሳ ሳንቲም መቀነሱ አነጋጋሪ እየሆነ ነው

በጥቁር ገበያ የዶላር ዋጋ በሰላሳ ሳንቲም መቀነሱ አነጋጋሪ እየሆነ ነው

dollar1

May 23, 2013 03:29 am By  Leave a Comment

በአዲስ አበባ የሚገኙ የጥቁር ገበያ ባለድርሻዎች በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ነጋዴዎች ከሙስና ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በመታሰራቸው በተፈጠረ መደናገጥ መነሻ ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ እያጋጠማቸው መሆኑን ገልፀው፣ የዶላር ምንዛሪ በታሪኩ የሰላሳ ሳንቲም ቅናሽ አሳይቷል።

የከፍተኛ ባለስልጣናቱ በወንጀል የመጠርጠር ዜና ከመሰማቱ በፊት ሃያ ብር ከአርባ ሳንቲም የነበረው የዶላር ምንዛሪ ወደ ሃያ ብር ከአስር ሳንቲም በሳምንት ውስጥ ቀንሷል። በዚህ ቅናሽ ውስጥ አስደንጋጭ የሆነው ክስተት በማንኛውም አይነት ምንዛሪ መጠን ዶላር ወደላይ ሲጨምር ሆነ ሲቀንስ በሰላሳ ሳንቲም የልዩነት ምንዛሪ ውስጥ ወድቆ አለማወቁ መሆኑን ከስፍራው ያገኘነው መረጃዎች ያሳያሉ። በሙስና ከተጠረጠሩ ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች ጋር በተያያዘ ይህ ልዩነት መፈጠሩ አብዛኛው የጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሪ ባለድርሻ አካላትን ማስደንገጡን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ጠቁመዋል።

ባለፉት አራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ የዶላር እጥረት በሀገሪቷ ሲከሰት የጥቁር ገበያ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ተጠቃሚ መሆናቸውን ቢገለጽም፣ ከመንግስት እና ከግል ባንኮች ሰራተኞች የገጠማቸው ችግር ግን እጅግ ፈታኝ እንደነበር አስረድተዋል። ይህም ሲባል፣ ለአንድ የአሜሪካን ዶላር ከአንድ ብር እስከ አንድ ብር ከሃምሳ ሳንቲም የባንኩ ደንበኞች ክፍያ እየፈጸሙ ከፍተኛ መጠን ያለው የዶላር ምንዛሪ ከባንኮቹ ማግኘትን በአማራጭነት በመውሰዳቸው ወደ እኛ ከመምጣት ባንኮንችን ተመራጭ ያደርጉ ነበር። ሆኖም ከፍተኛ መጠን ዶላር የማይፈልጉ ደንበኞች በወቅቱ ስለነበሯቸው ከፍተኛ ተጠቃሚ መሆናቸውንም አልሸሸጉም።

በአሁን ሰዓት ከመንግስት ኪራይ ሰብሳቢ የተለያዩ ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች ወደ እነሱ ይፈስ የነበረው የኢትዮጵያ ብር ለዶላር ምንዛሪ ከፍተኛ ጠቀሜታ የነበረው ከመሆኑ አንፃር አሁን የተፈጠረው ድንጋጤ በከፍተኛ ሁኔታ የጥቁር ገበያውን የዶላር ምንዛሪ ይጐዳዋል። የተፈጠረው ድንጋጤ ግለሰቦችን ሳይቀሩ ማሸማቀቁን ያነጋገርናቸው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አረጋግጠዋል። በስፍራው የተገኙት መረጃዎችም የሚያሳዩት ከመንግስት ከፍተኛ ኪራይ ሰብሳቢ ባለስልጣናት ሰንሰለት ይፈስ የነበረው የኢትዮጵያ ብር ለጊዜ ተቀዛቅዟል። ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ የጥቁር ገበያው አደጋ ውስጥ መውደቁ አይቀርም የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልፀዋል።

ለምን የኢትዮጵያ ብር ወደ ጥቁር ገበያ ይላካል?

በሙስና ውስጥ የተዘፈቁ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተባባሪ የንግዱ ማሕበረሰብ አባላት ከሕግ አግባብ ውጪ የሚያገኙትን የኢትዮጵያ ብር በአዲስ አበባ ጥቁር ገበያ ውስጥ በዘረጉት ሰንሰለት ወደ አሜሪካ ዶላር ለውጠው ወደ ውጭ ሀገር እንዲወጣ በማድረግ ተጠቃሚ በመሆናቸው መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በተለይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በዚህ መልኩ የሰበሰቡትን የአሜሪካ ዶላር በተሰጣቸው ያለመፈተሸ መብት በመጠቀም እና በገቢዎችና ጉምሩክ በዘረጉት የኪራይ ሰብሳቢ ሰንሰለቶች አማካይ ወደ ውጭ ይዘውት የሚወጡበት አሰራር ሊኖር እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል። የሰበሰቡትን የአሜሪካ ዶላር በሳምሶናዊት ቦርሳቸው ውስጥ በመጨመር እና ቦርሳውን ላይ ያለመፈተሽ መብት የሚያጎናጽፋቸውን ልጣፍ በመለጠፍ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ዶላሩን ይዘው የሚወጡበት ዕድል ከፍተኛ በመሆኑ ሊጠቀሙበት ይችላሉ ሲሉ ግምታቸውን ተናግረዋል።

በአስረጅነት ግምታቸውን ሲያስቀምጡ የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ዋና ዳሬክተር የነበሩት አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት የተገኘው 26ሺ የአሜሪካ ዶላር እና 19ሺ ዩሮ የአውሮፓ ሕብረት የመገበያያ ገንዘብ በዚህ መልኩ የተሰበሰቡ ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን ግምት ገልፀዋል። አያይዘውም አንድ ግለሰብ ከ200 የአሜሪካ ዶለር ምንዛሪ ውጪ ይዞ መገኘት እንደማይችል በኢትዮጵያ ሕግ መስፈሩንም አስታውሰዋል። እንዲሁም በአቶ አስመላሽ ወ/ማሪያም መኖሪያ ቤት የተገኘውም አንድ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ወደ ዶላር ለመቀየር የተቀመጠ ገንዘብ ሊሆን እንደሚችል ከጥቁር ገበያ ያገኘነው ግምታዊ መረጃ ያሳያል።

ይህን መሰል ተግባር መፈጸም ትርጉሙ ብዙ ሊሆን ይችላል። በተለይ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን በሀገር ውስጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት መኖሩ እያወቀ የኢትዮጵያን ብር በዶላር እየመነዘረ ወደ ውጭ ሀገር በማስወጣት ተግባር ላይ ከተሰማራ እንደሀገር ትልቅ በደል መሆኑን መገንዘብ ሮኬት ሳይንስ አይሆንም። በዚህ መልኩ የተሰማሩ የመንግስት ባለስልጣናት በወፍ በረር ሲታይ፣ ዶላር ማሸሽ ቢመስልም በተግባር ግን ሲመነዘር የኢትዮጵያ መንግስትን እና ሥርዓቱን ቀስ በቀስ እየሸራረፉ ሊጨርሱት መዘጋጀታቸውን የሚያሳይ ነው። የፓርቲ ሹመኞቹን የመንግስትን ስርዓት ለዘረጋው ገዥ ፓርቲ ቢተውም፣ ተግባራቸው ግን ሕገ መንግስቱን በጠራራ ፀሐይ እየበጣጠሱት ስለመሆኑ አስረጂ አያስፈልገውም።

የገንዘብ ምንጩ ስትራቴጂ

እ.ኤ.አ. የሴፕቴምበር 11 ቀን 2001 የአሜሪካኑን የሽብር ጥቃት ተከትሎ ትንሹ ቡሽ ሴፕቴምበር 20 ቀን 2001 “WAR ON TERROR” በሚል መጠሪያ ዓለም ውስጥ የሚገኙ አሸባሪዎችን ለመደምሰስ ያስችላል በሚል አዲስ ስትራቴጂ ይዘው ብቅ አሉ። ቡሽ ቀጠል አድርገው በአሸባሪዎች ላይ የምንከፍተው ዘመቻ ‘የመስቀል ጦርነት’ ነው በማለት ለዓለም ሕዝብ በይፋ ተናገሩ።

ቡሽ ብዙም ሩቅ ሳይጓዙ በአደባባይ “የመስቀል ጦርነት” የሚለውን ቃል ተገቢ አይደለም፤ ከእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር አወዛጋቢ ፍቺ ያመጣል በማለት በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል። ጦርነቱን የምንጀምረው በአልቃይዳ እና በእሱ የሽብር መረብ ከተያያዙ አሸባሪዎች ጋር ነው ሲሉ አቋማቸውን በግልፅ አስቀመጡ። ዓለም ከአሜሪካ ጎን ቆመ። ቡሽም፣ ‘ወይ ከእኛ ወይም ከእነሱ’ ጋር መሆንን ምረጡ ብለው ለዓለም ዓቀፉ ሕብረተሰብ ጥሪ አቀረቡ። ዓለምም በወቅቱ በጐ ምላሽ ሰጣቸው። ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው። ኦሳማ ቢላደን ግን ከአስር ዓመት በኋላ ተገድሏል።

እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን ቁምነገር፤ እንደቡሽ የመጀመሪያ አቀራረብ ቢሆን የተቀደሰውን የእስልምና እምነት ከሽብር ተግባር ጋር ጨፍልቆ ለማየት ያለመ ነበር። ሆኖም ቡሽ ፈጥነው አባባላቸው ስህተት መሆኑን አርመው በይፋ ይቅርታ ጠየቁ። ስለዚህም ነገሮች ለያይቶ ማየት እንጂ በአንድ ቅርጫት ውስጥ ወርውሮ አንድ መለያ መስጠት ተገቢ አለመሆኑ ከዚህ መረዳት ይቻላል።

በተነፃፃሪነት ሲታይ ደግሞ ገቢዎችና ጉምሩክ በቀድሞ ከፍተኛ አመራሮቹ በኩል የኢትዮጵያ ነጋዴዎችን በተለይ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙትን ነጋዴዎች በግብር ስም ሁሉም ነጋዴ ግብር አጭበርባሪ ኪራይ ሰብሳቢ በማድረግ ሽብር “TERROR ON TAX” በነጋዴው ላይ ረጩ። ነጋዴውም ግብር መክፈሉን ሳይሆን ለኪራይ ሰብሳቢ ወይም ለግብር አጭበርባሪ ታፔላን ላለመጋለጥ በሚል ብቻ የገቢዎችና ጉምሩክ ከፍተኛ ሃላፊዎች ተገዢ መሆኑ አረጋገጠ። በመጨረሻም በተፈበረከው የሽበር ማዕቀፍ ውስጥ ነጋዴው ወደቀ። ፍርሃት፣ ስጋት መለያው ሆነ።

ከዚህ በኋላ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮቹ ጋር ተባብሮ መስራት የኪራይ ሰብሳቢዎች የህግ የበላይነትን ማረጋገጫ አድርጎ ተቀበለው። ለዚህ ማሳያ የሚሆነው መንግስት ከፍተኛውን የሙስና ወንጀል በራሱ መንገድ ደረሰበት እንጂ በአደባባይ በመውጣጥ ለማጋለጥ የደፈረ ታዋቂ ባለሃብት አንድም አልነበረም። በሕግ የማይነኩ በሚመስሉ የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣናት ጋር ሲራኮቱ የነበሩ ታዋቂ የከተማችን ባለሃብቶች ሕግ በራቸው ደጃፍ ሲመጣ ሌላ የፖለቲካ ዓላማ ያለው ተግባር እንጂ ሙስና አይመስለንም ሲሉ በአደባባይ በዘረጉት የኪራይ ሰብሳቢዎች የሙስና ሰንሰለት በመጠቀም ከተማውን እያሟሟቁ ይገኛሉ። እውነቱ ግን ሌላ ሆኖ ነው እየታየ ያለው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በባሕርዳር በተደረገ የኢሕአዴግ 9ኛው ጉባኤ ላይ ከተጋበዙ ባለሃብቶች መካከል አንዱ የከተማችን ባለሃብት ለጉባኤው ያቀረበው ጥያቄ አጠቃላይ መንፈሱ ሲታይ “የኪራይ ሰብሳቢ” መሰረታዊ ይዘት በመቀየር ወደ ‘ሽብር’ መለወጡን አመላካች ነው። ባለሃብቱ ጉባኤውን የጠየቀው እንዲህ ሲል ነበር፣ “የኪራይ ሰብሳቢ ፍቺው በጣም የተለጠጠ ነው። በትክክልም ምን እንደሆነ እንኳን ለመረዳት አዳጋች ነው። በጅምላ ሁሉም ነጋዴ በገባበት ቢሮ ውስጥ ኪራይ ሰብሳቢ እየተባለ ይሸማቀቃል። እኔ እራሴ አሁን ኪራይ ሰብሳቢ በሚባለው ፍቺ ኪራይ ሰብሳቢ ልሁን፣ አልሁን ማረጋገጥ እንኳን አልችልም” ሲል በነጋዴው ላይ የተለቀቀውን ሽብር ለጉባኤው አስረድቷል።

ቡሽም በጅምላ የሚካሄደው ጦርነት የመስቀል ጦርነት ነበር ያሉት። እሳቸው ግን በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስትም ከንግዱ ማሕበረሰብ ጋር የበለጠ በመቀራረብ ለኪራይ ሰብሳቢዎች የተጋለጠውን የንግዱን ሕብረተሰብ ከሌላው ጤነኛ የንግዱ ሕብረተሰብ መለየት አለበት። ሁሉም ነጋዴ የኪራይ ሰብሳቢዎች መጠቀሚያም ተባባሪም ሊሆን ስለማይችል ነው። ንግድም ዓለምን የለወጠ የተከበረ ተግባር ከመሆኑ አንፃር መንግስት ከዚህ በፊትም ሲያደርገው እንደነበረው አሁንም አጋርነቱን ማሳየት ይጠበቅበታል። ስለዚህም መሰረታዊ የመንግስትን የገቢዎችና ጉምሩክ ፖሊሲን “በሽብር”፣ “በፍርሃት” ቆፈን ቀይረው ለራሳቸው ጥቅም ያደሩ የመንግስት ባለስልጣናት በፈጠሩት የተሳሳተ የኪራይ ሰብሳቢ ፍቺም በተቻለ ፍጥነት ለንግዱ ማሕበረሰብ መሰረታዊ ዕሳቤውን ማቅረብ ያስፈልጋል። በአንድ ቅርጫት ውስጥ የተቀመጠው የንግዱ ማሕበረሰብ ስምም ተገቢውን ስፍራ ሊያገኝ ይገባል። በመንግስትም በበኩሉ ኪራይ ሰብሳቢዎችን መያዙ ምርጫው ሳይሆን ግዴታው መሆኑን ግንዛቤ መውሰዱም ይጠቅማል። በተረፈ መንግስትና ጤናማው የንግዱ ማሕበረሰብ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጸች መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር በመሆኑ ብዙ ማለት አይቻልም። (ፎቶ: Euroradio)

(ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 402 ረቡዕ ግንቦት 14/2005)

Golgul.com

ኢሳት ጋዜጠኞች ጆሮ ላይ ስልክ ለምትዘጉ ባለስልጣኖች ማሰጠንቀቂያ

እስከ ነጻነት

መረጃ የማግኘት መብት የስብዓዊ መብት ዋናው መሰረት ነው፡ መረጃ የማግኘት መብት ዋናው የሰብዓዊ መብት ምሰሶ መሆኑን የሃገራት ደርግ (League of Nations) የደነገገው በ1946 ዓ.ም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነበር፡ ያደጉ ሃገራት ይህንን መብት በሚገባ ይጠቀሙበታል፡ ገልብጦ መጻፍ እንጂ ማንበብ የማይችልው የወያኔ ዘረኛ ስርዓትም ይህንኑ መብት በህገመንግስቱ ላይ አሰቀምጦታል። ለነገሩ ያላሰቀመጠው ነገር የለም ግን ማን አንብቦት ተግባራዊ ያደርገዋል እንጂ። ተግባራዊ እየሆነ ያለው ዘርን ለማጥፋት የተወጠነው የጫካው ህጋቸው ብቻ ነው።

ይህን እዚሁ ላይ ላቁምና ወደተነሳሁበት ልመለስ፤ የውነትም ይሁን የውሸት ስልጣን ይዛችሁ መረጃ ስትጠየቁ ስልክን ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ የምትዘጋ፤ የምትዘጊ፤ የምትዘጉ ግለሰቦች ወንጀል መሆኑን ካልተገነዘባችሁ እንድትገነዘቡት ላስታውሳችሁ አወዳለሁ፡የእሳት ጋዜጠኛ መረጃ ሲጠይቃችሁ ጆሮው ላይ ስትዘጉ፡ የዘጋችሁበት መሳይ፤ ፋሲል፡ ሲሳይ ወይም፡አንድ የእሳት ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ ሳይሆን የ90 ሚሊየን የኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ ላይ መሆኑን ልብ ካላላችሁ ላስታውሳችሁ፡ ለያንዳንዷ ለዘጋችሗት ስልክ የምትጠየቁ መሆኑን ደግሜ ደጋግም ላስገነዝባችሁ እወዳለሁ።

በእርግጥ አማራ ነን ብላችሁ አማራ ህዝብን የምታስፈጁት፤ ኦሮሞ ነን ብላችሁ የኦሮሞን ደም የምታፈሱት፤ ኢሳ ሆናችሁ የኢሳን ህዝብ የምታስፈጁት ሌሎቻችሁም የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ካድሬ ከላይ ተጭኖ እንደሚያዛችሁ አለም የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡ ምናልባትም ለእሳት መረጃ ለመስጠት የፍርሃት ቆፈን ቀፍድዷችሁ ሊሆን ይችላል። ፈቃደኝነቱ ኖሮ ችግራችሁ ፍርሃት ከሆነ መረጃውን ለሌላ ለምታምኑት ሰው አቀብላችሁ መረጃ የሰጣችሁትን ስው ስልክ ቁጥር ለእሳት ጋዜጠኛ ልትነግሩ ትችላላችሁ፡ ሲሆን ሲሆን አንድ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ጨባጣ ካድሬ እንደ አውራ ዶሮ ሲንቀባረርባችሁ እንደ ሲካካ ዶሮ እኔ እኔ እያላችሁ ከመሽቀዳደም በጋራ ማሰወገድ ትችሉ ነበር፡ይህ ባይሆን እንኳ የወገናችሁን ሰቆቃ እና የወያኔን ሚስጥራዊ ወንጀል ማጋለጥ ከናንተ የሚጠበቅ ትንሹ ተግባር መሆን ሲገባው ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ ስልክ ትዘጋላችሁ።

እስኪ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ በተለይ አማራ ነን ያላችሁ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር መጋዣዎች፤ አማራን ለማጥፋት በተግባር እቅዱ ላይ ነድፎ የሚንቀሳቀስ ድርጅት እናንተን እንደማይበላችሁ ማረጋገጫችሁ ምንድነው? መረጃውን እዚህ ላይ አንብቡት አሁን በሙስና ተብለው የታሰሩት በርግጥ በሙስና ነው? እናነተስ ነገ ወደቃሊቲ ላለመላካችሁ ዋስትናችሁ ምንድነው? ስለዚህ ቀኑ ሳይመሽ ወደ ህሊናችሁ ተመልሳችሁ ወደ ወገናችሁ ተደባለቁ። ይህ ጥሪ ላማራ ብቻ አደለም፤ ለኦሮሞ፤ ለሲዳማ፤ ለኦጋዴን፤ ለአፋር፤ ለሲዳማ፤ በአጠቃላይ ወያኔ በየቦታው የወዘፋችሁ ባለስልጣናትን ሁሉ ይመለከታል፡ ይህ ሁሉ ሳይሆን ቀርቶ፤ ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ ስልክ እየዘጋችሁ የወያኔን ወንጀል ደብቃችሁ ቀኑ ከመሸ እያንዳንዳችሁ ከተጠያቂነት እንደማታመልጡ መረዳት አለባችሁ፡ ወያኔ እንኳን የናንተን ገመና ሊሸፍን የራሱን ገመና መሸፈን የማይችል የፍየል ጅራት መሆኑ አይናችሁን ካልጨፈናችሁ በስተቀር በግልጽ የሚታይ ጉዳይ ነው።

በህግ ስላላወቅሁ ነው የሚባል ነገር እንደሌለና ለሰራችሁት ወንጀል ሁሉ ተጠያቂ መሆናችሁን አስረግጬ እዚህ ላይ ላብቃ።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

 

 ECADF.COM

የህማማት ማሰታወሻ ‹‹ህዝቤን ልቀቅ!›› እስክንድር ነጋን ልቀቅ!…

ተመስገን ደሳለኝ

ይህ ሳምንት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ‹‹ሰሞነ ህማማት›› ተብሎ በፀሎትና በስግደት ይከበራል፡፡ ይህ የሆነው ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ በሀሰት ተወንጅሎ ለስቅላት ተላልፎ የተሰጠበት፣ በሰው ልጅ ከሚደርስ ስቃይ፣ መከራና ግርፋት ሁሉ የከፋውን የተቀበለበት ሳምንት በመሆኑ ነው፡፡

…የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የኦርቶዶክስ ክርስትና ሀይማኖት ጥብቅ አማኝ ነው፤ የሀይማኖቱን ትእዛዛቶች በጥብቅ ያከብራል፤ ሁሉንም አፅዋማትም ይፆማል፡፡ ዛሬ በግፍ ታስሮ በሚገኝበት የቃሊቲ ወህኒም ሆኖ እንኳ የኩዳዴን ፆም ከመፆም አልሰነፈም (በነገራችን ላይ እስክንድር የሚገኝበት ‹‹ዞን ሶስት›› ፈርሶ እንደገና ሊሰራ ስለሆነ እስረኞቹ ወደሌላ ቦታ ሊዘዋወሩ እንደሆነ ተነግሯቸዋል)
እስክንድር የተወለደው ጥቅምት 27 ነው፡፡ ይህ ዕለት ደግሞ ለእምነቱ ተከታዮች የ‹‹መድሐኒያለም ዕለት›› እየተባለ የሚከበረበት ቀን ነው፡፡ እርሱም ቢሆን ምንጊዜም ጠዋት ወይም ማታ ከስድስት ኪሎ ዩንቨርስቲ ከፍ ብሎ በሚገኘው ‹‹ምስኪያዙና መድሐኒያለም ቤተ-ክርስቲያ››ን የፈለገ አያጣውም፡፡የህማማት ማሰታወሻ ‹‹ህዝቤን ልቀቅ!›› እስክንድር ነጋን ልቀቅ!...

…የፊታችን ሀሙስ (ሚያዚያ 24 ቀን 2005 ዓ.ም) የእስክንድር ነጋ ይግባኝ ‹‹ለመጨረሻ ጊዜ›› ተብሎ ተቀጥሯል፡፡ ዕለቱ ለክርስትና እምነት ተከታዮች ‹‹ፀሎተ ሀሙስ›› ታስቦ የሚውልበት ቀን ነው (አይሁዳውያን ኢየሱስ ክርስቶስን አሳልፈው ሰጥተው ሲያበቁ ስለሁከት፣ ስለመግደል በወሀኒ ታስሮ የነበረውን በርባንን ‹‹ፍታልን!›› ያሉበትን እና የሐዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በትህትና ያጠበበትን ለማስታወስ ነው ቀኑ ‹‹ፀሎተ-ሀሙስ›› ተብሎ የተሰየመው)

…በድህረ ምርጫ 97 ለእስር ከተዳረጉ ጋዜጠኞች መካከል እስክንድር ነጋ አንዱ ነበር፡፡ የተፈታውም በ‹‹ይቅርታ›› ሳይሆን ፍርድ ቤቱ ‹‹ነፃ ነህ!›› ብሎ አሰናብቶት ነው፡፡ ቀኑም የ‹‹ፀሎተ-ሀሙስ›› ዕለት ነበር፡፡ …የከነገ በስቲያ ሚያዚያ 24 ግጥምጥሞሽስ ምን ያሰማን ይሆን?
የሆነ ሆኖ የመፅሀፍ ቅዱስ ቃል ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት እግዚአብሄር ሙሴን እንዲህ እንዳለው ይነግረናል፡-
‹‹እኔ እግዚአብሄር ነኝ፤ ከባርነት አወጣችኋላሁ፤ ከተገዥነታቸውም አድናችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም እታደጋቸኋለሁ፤ አምላክም እሆናቸኋለሁ፡፡›› (ኦሪት ዘጸአት ም.6 ቁ.6-7)
በወቅቱ ብዙ ሺህ ንፁሃን፣ ፈርኦን በተባለ ጨካኝ ንጉስ ስር ይሰቃዩ ነበር፡፡ እናም ከዕለታት አንድ ቀን እግዚአብሄር ሙሴን ወደ ፈርኦን ላከው፡፡ ሙሴም ቤተ-መንግስቱ ውስጥ ድረስ ዘልቆ በዙፋኑ ለተቀመጠው ፈርኦን እንዲህ ሲል የአምላኩን መልዕክት ነገረው፡-
‹‹እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡- በፊቴ ለመዋረድ እስከመቼ እምቢ ትላለህ? ያገለግለኝ ዘንድ ህዝቤን ልቀቅ!››
…በምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያም እስከዛሬ ድረስ ያየነው ስርዓቱና ምንደኞቹ ንፁሃንን በሀሰት ከሰው፣ በሀሰት ምስክርና በሀሰት ማስረጃ ወደ ጨለማ (ወህኒ) ሲወረውሩ ነው፡፡

በመላ ሀገሪቷ የነገሰውም የህግ የበላይነት አይደለም፤ የፈርኦን የበላይነት እንጂ፡፡ ፈርኦኖች ደግሞ ምን ጊዜም ከመከራ እንጂ ከታሪክ ተምረው አያውቁም፡፡ መልካሚቷን ምክርም ሊሰሙ አይወዱም፡፡ ስለዚህም ብቸኛው አማራጭ በአደባባይ ተሰባስበን፡-
‹‹በፊታችን ለመዋረድ እስከመቼ እምቢ ትላለችሁ? ሀገራቸውን ያገለግሉ ዘንድ ወንድምና እህቶቻችንን ልቀቅ!››
‹‹እስክንድር ነጋን ልቀቅ!
በቀለ ገርባን ልቀቅ!
አንዱአለም አራጌን ልቀቅ!
ርዕዮት አለሙን ልቀቅ!
ውብሸት ታዬን ልቀቅ!
የሱፍ ጌታቸውን ልቀቅ!
አቡበክር አህመድን ልቀቅ!
ብዙ… ብዙ ሺህ ንፁሃንን ልቀቅ!››
እያሉ መጮኹ ኢያሪኮን ለማፍረስ ያልተመለሰው የጭቁኖች ጩኸት መነቃነቅ የጀመረውን ስርዓት ለመፈረካከስ ብቸኛው ምርጫችን እንደሆነ ዛሬም ደግሜ እናገራለሁ፡፡
‹‹ልቀቅ! ልቀቅ! ልቀቅ!››

ECADF>COM

ምርጫ የለም እንጂ ምርጫማ ቢኖር …!

በፍቅር ለይኩን

የዛሬው ጽሑፌን በምርጫ ዙሪያ ካጋጠመኝ ትንሽ ቆየት ካለ ገጠመኜ ልጀምር፡፡ በደቡብ አፍሪካዊቷ ቢዝነስ ከተማ ጆሐንስበርግ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በትውልድ ደቡብ አፍሪካዊ የሆኑ ካህን፣ አባትና አገልጋይ የሆኑ በ60ዎቹ መጨረሻ ዕድሜ ላይ የሚገኙ አንድ አዛውንት አባት አሉ፡፡

እኚህ አዛውንት ካህን ስማቸው ፋዘር ዲሊዛ ኔልሰን ቫሊዛ ሲሆን፤ በኢትዮጵያውያን የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና ምእመናን ዘንድ ደግሞ በክህነት የማእረግ ስማቸው መልአከ ሰላም ዲሊዛ ቫሊዛ በመባል ይጠራሉ፡፡ ታዲያ ፋዘር ዲሊዛ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ፣ ስለ ኢትዮጵያውያንና ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አውርተው፣ ተናግረው የሚጠግቡ ሰው ዓይነት አይደሉም፡፡

ከኬፕታውን ከትምህርት ቤት በመዘጋቱ ለእረፍት ወደ ጆሐንስበርግ መጥቼ ነበር፡፡ በጆሐንስበርግ መድኃኔ ዓለም ካቴድራል በነበረኝ የመንፈሳዊ አገልግሎት ቆይታዬም ከእኚህ አዛውንት አባት ጋር ከመንፈሳዊና ከሃይማኖታዊ ጉዳዮች ባሻገርም በበርካታ በአገራችንና በደቡብ አፍሪካ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በተለያዩ አጋጣሚዎች አብዝተን እንወያይ ነበር፡፡

ፋዘር ዲሊዛ በየትኛው አጋጣሚ ለሚያገኟቸው ኢትዮጵያውያንም ሆነ የውጭ አገር ዜጎች ሁሉ አዘወትረው የሚናገሩት አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም ለዛሬው ነፃነታችን፣ ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ የዘረኝነት መድሎ ለሌለበት ፍትሐዊ ሥርዓት እውን መሆን እናንተ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ድርሻ አላችሁ በማለት በአድናቆትና በልዩ የደስታ መንፈስ ውስጥ ሆነው ምስክርነታቸውን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይሰጣሉ፡፡

በአንድ ወቅት ከፋዘር ዲሊዛ ጋር ባደረግነው ውይይት እኚህ አዛውንት አባት በአገራቸው ደቡብ አፍሪካ ለሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ (Local Government Election) ከጆሐንስበርግ ከ1000 ኪ.ሜ. በላይ ወደሚርቀው የውቅያኖስ ጠረፏ የትውልድ አገራቸው ፖርት ኤልዛቤት ለመሄድ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ አንዳች ጉጉት በሚንጸባረቅበት ልዩ ስሜት ውስጥ ሆነው አጫወቱኝ፡፡

እኔም በመገረም ሆኜ እንዴ …! ፋዘር እንዴት ለአካባቢ ምርጫ ሲሉ ይህን ያህል ርቀት፣ ይህን ያህል ብዙ ብር የትራንስፖርት ወጪ አውጥተው ይሄዳሉ?! ደግሞስ እርስዎ አሁን አርጅተዋል፣ ለምን እንዲህ በመንገድ ይደክማሉ፤ ባለቤትዎና ልጆችዎ ከመረጡ በቂ አይደለም እንዴ …?! አልኳቸው፡፡

አዛውንቱ ካህን ለምርጫ ወደ ትውልድ መንደራቸው ለመሄድ ጓዛቸውን እየሸከፉ መሆናቸውን መስማቴና እርሳቸውም የጉዞአቸውን ስላረጋገጡልኝ በጣሙን ግርምትም አድናቆትም አጭሮብኝ፡፡ ፋዘር ዲሊዛ ግርምት ለተሞላበት ጥያቄዬና አስተያየቴ ሲመልሱልኝም፡-

አይ ልጄ ይህ የመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብቴ በብዙ ዋጋ፣ በእልፎች ክቡር ደምና መሥዋዕትነት የተገኘ ልዩ መብት ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ከእናት ቤተ ክርስቲያናችን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ፈጽሞ እንዳንገናኝ ዘረኛው የአፓርታይድ መንግሥት የገነባው የመለያየት ግንብ የተናደው ፓርቲዬ ኤ.ኤን.ሲ፣ በበርካታ የደቡብ አፍሪካውያን የነፃነት ፋኖዎች እና ለሰው ልጆች ነፃነትና እኩልነት ቀናኢ በሆኑ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮችና ሌሎች አጋሮቻችን ጭምር ነው፡፡

እናም ልጄ በዚህ ምርጫ በመምረጥም ሆነ በመመረጥ ለመሳተፍም ሆነ ላለመሳተፍ አንተ እንደምትለው የዕድሜዬ መግፋት፣ በቦታ ርቀት፣ በገንዘብ ወጪ ፈጽሞ የሚተመን አይደለም፡፡ ይህ በምንም በማይተመን በብዙዎች የሕይወት መሥዋዕትነት የተገኘ ልዩና ክቡር መብት/መብቴ ነው፡፡ እናም መብቴን በሕይወት እሳካለሁ መጠቀም አለብኝ፡፡

አየህ አሉኝ ፋዘር ዲሊዛ ንግግራቸውን በመቀጠል በአትኩሮት እየተመለከቱኝ አየህ ልጄ የእኔ አንድ ድምፅ ለፓርቲዬ ድልም ሆነ ሽንፈት ወሳኝነት አለው፤ ስለሆነም ለዘመናት ለታገልንበትና የበርካታ አባቶቻችን ክቡር ሕይወት ተከፍሎበት አገሬ ደቡብ አፍሪካ ዛሬ ለደረሰችበት ሰላም፣ ብልጽግና፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደት እውን መሆን ማረጋገጫው በዚህ ያለማንም አስገዳጅነት በራሴ ፍላጎት፣ ወድጄና ፈቅጄ የምሳተፍበት ይህ ፍትሐዊ የሆነ የአካባቢ ምርጫ አንዱ ነው፡፡

እናም ልጄ ምንም ተአምር ቢፈጠር በሕይወትና በጤና እሳካለሁ ድረስ ለምርጫ ወደ ትውልድ መንደሬ ከመሄድ የሚያግደኝ ነገር አይኖርም በማለት ፈርጠም ብለው መለሱልኝ፡፡ አዛውንቱ ካህን በዚህ የዕድሜያቸው መጨረሻ እንኳን በስስት የሚያዩት የመምረጥና የመመረጥ መብታቸው ላይ ያላቸው ስሱነትና ፖለቲካዊ ንቃታቸው (Sensitivity and political consciousness) በእጅጉ አስገረመኝ፣ አስደመመኝም፡፡

በፋዘር ዲሊዛ ቫሊዛ መልስ የበዛ አድናቆትና ግርምት የተጫረብኝ ኢትዮጵያዊው እኔ ወደኋላ ዘወር ብዬ በበርካታ አፍሪካ አገሮችና በመላው ዓለም የነፃነት ሰንደቅ ተደርጋ በምትታየው ኢትዮጵያ፣ የአገሬን የምርጫ ታሪክና ዲሞክራሲዊ ግንባታ ሂደት ለመታዘብ ይህ ጥቂት የቆየ ገጠመኜ ዕድሉን ፈጠረልኝ፡፡ እናም ከዚህ ገጠመኜ በመነሳት ይህችን አጠር ያለች ትዝብት አዘል ጽሑፍ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተካሄዱት የአካባቢ፣ የቀበሌና የወረዳ ም/ቤቶች ምርጫ ዙሪያ በመመርኮዝ ጥቂት ነግሮችን ለማለት ወደድኩ፡፡

በዘመኔ የደረስኩበት፣ በሙሉ ልቤ የምመሰክርለትና በንቃትም የተከታተልኩት ምርጫ ቢኖር በአገር አቀፍ ደረጃ ተካሄደው የ1997ቱ ምርጫ ነው፡፡ ከዛን በፊት ስለ ምርጫ፣ ስለ መምረጥና ስለ መመረጥ መብት ለማወቅም ሆነ ለማገናዘብ የነበረኝ ፖለቲካዊ ንቃትና ዕድሜዬም ደረጃም ብዙም የሚፈቅድልኝ አልነበረም፡፡ እናም የትዝብቴ ዋና ትኩረት የሚሆነው ምርጫ 97ን ተመርኩዞ ከሰሞኑ በተካሄደው የአካባቢናና የወረዳ ምክር ቤት ምርጫ ላይ ነው፡፡

በዘንድሮው የአካባቢና የወረዳ ምክር ቤት ምርጫ ላይ በጥቂቱ ትዝብቴን ለማካፈል የ1997ቱን ምርጫ እንደ መነሻ ወይም መንደርደሪያ አድርጌ ለመውሰድ የተነሣሁበት የራሴ የሆነ ምክንያት ስላለኝ ነው፡፡ ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የ1997ቱ ምርጫ በእኔ ብቻ ሳይሆን በብዙ ኢትዮጵውያን ልብ ውስጥ የማይረሳ ውብም አስቀያሚም የሆነ መቼም ማይረሳን ትዝታ ትቶ አልፏል፡፡

1997ቱ ምርጫ ምንም እንኳን ፍጻሜው ባያምርም የምርጫው ጅማሬና ሂደት መላው ኢትዮጵያውያንን ከሊቅ አስከ ደቂቅ፣ ከአፈ ነቢብ እስከ ምሁር፣ አለቃን ከምንዝር ሳይለይ ሁሉንም ኅብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ ምድሪቱን ከዳር እስከ ዳር ያነቃነቀና መላውን ዓለም ጭምር ያሰደመመ ነበር፡፡

ሚንጋ ነጋሽ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ምሁር Ethiopia’s Post Election Crisis: Institutional Failure and The Role of Mediation በሚል አርዕስት በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ከተማ በሚገኘው Witwatersrand ዩኒቨርስቲ ባቀረቡት የጥናት ወረቀታቸው፣ ምርጫ 97 በአገራችን ምርጫ ታሪክ ውስጥ ትልቅና ጉልህ የሆነ ታሪካዊ ክስተት ሆኖ ማለፉን እንዲህ በማለት ነው በጥናታዊ ጽሑፋቸው የገለጹት፡-

The 1997 elections marked an historic event in the country, as Ethiopia witnessed its first genuinely competitive campaigns period with multiple parties fielding strong candidates.

በወቅቱ ምርጫውን የታዘበው ካርተር ምርጫ ታዛቢ ቡድን ማእክልም ባወጣው ባለ69 ገጽ ሪፖርቱ እንደገለጸው፣ በምርጫ 97 ወቅት ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይ የነበራቸውን ሁሉን አቀፍ ሕዝባዊ ተሳትፎና ትልቅ መነቃቃት በተመለከተ ሲገልጽ፡-

The May 2005 election was started against the backdrop of tensions and unprecented level of public political consciousness. … Voters had a genuine choice in Election Day and responded with enthusiasm and high turnout. 

1997ቱ ምርጫ አንፃር የዘንድሮውን ምርጫ ሂደት የታዘቡ ብዙዎች ዋ ምርጫ!፣ ዋ የምርጫ ፉክክርና ውድድር!፣ ወይ የምርጫ ነገር፣ ወይ ነዶ … በማለት ቁጭታቸውንና ብሶታቸውን የገለጹበትን አጋጣሚ ትቶ ነው ያለፈው፡፡ አንዳንዶችም በማኅበራዊ ድረ ገጾች ባሰነበቡት ምጸትን የተሞላ ሰም-ለበስ ግጥማቸው እንዲህ በማለት ነበር የዘንድሮውን የኢህአዴግን የምረጡኝ አማርጡኝ ደፋ ቀና የአካባቢና የወረዳ ምርጫ ግርግርን እንዲህ የተቀኙበት፡-

ምርጫ የለም እንጂ ምርጫ ቢኖር፣

ኑ ምረጡን የሚለን ‹‹ካድሬ›› ባላሻን ነበር፡፡

1997 ምርጫ በኋላ የተካሄደው የ2002ቱ ምርጫ ከ1997ቱ ምርጫ በሁሉ ነገር አንሶና ኮስሶ ነበር የታየው፡፡ በእርግጥ ኢህአዴግ ከ97ቱ ምርጫ ስህተት በወሰደው ትምህርት ራሱን በሚገባ አጠናክሮ፣ ከሕዝቡ ጋር ለመገናኘት ተከታታይ የሆኑ ሰፊ ዘመቻዎችን በማድረግ በፍቅርም በጉልበትም መጪው ዘመን የእርሱና የእርሱ ብቻ እንዲሆን የተለመው እቅዱን ፈጽሟል ማለት ይቻላል፡፡

ይሁን እንጂ በ2002ቱ ምርጫ ላይ የነበረው ሕዝባዊው ተሳትፎው በአብዛኛው የቀዘቀዘ፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከገዢው ፓርቲ የተለመደ ወከባና በትር ያላመለጡበት፣ በተሳትፎ ረገድም መሳሳት የታየበት፣ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግም99.6 በመቶ ምርጫውን ያሸነፈበትን ይህን መሬት አንቀጥቅጥ የሆነ ድሉን ለራሱና ለደጋፊዎቹ የዘከረበትና ያዘከረበት ምርጫ ሆኖ ነበር ያለፈው፡፡

በዘንድሮው 2005 የአዲስ አበባ የአካባቢ፣ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤት ምርጫ ኢህአዴግ በየቤቱ እየዞረና ኑ እባካችሁ ምረጡ እያለ በመቀስቀስ ሕዝቡን ለምርጫ ቢወተውትም የምርጫው ድባብ ከሂደቱ እስከ ፍፃሜው ድረስ ቀዝቃዛና ደብዛዛ ነበር፡፡

አንድ በአነስተኛ የሸቀጥ ሱቅ ውስጥ የሚሰራ ወጣት ስለ መምረጡ ስጠይቀው በሰጠኝ ምላሹ በግርምታ ሆኖ ‹‹እንዴ አዲስ መንግሥት መጥቷል እንዴ!? ትላንትና ዛሬስ ያለው ኢህአዴግ አይደል እንዴ!? ታዲያ የምን ምርጫ ነው የሚሉን እነዚህ ሰዎች በማለት ያስፈገገኝንም ያሳዘነኝንም መለስ ሰጥቶኛል፡፡

ብዙዎች ደግሞ አማራጭ ሲኖር እኮ ነው ምርጫ፣ ለመሆኑ ማንን ከማን ነው የምንመርጠው፣ በእውነት ኢህአዴግ አሁንስ ‹‹ከዝንጀሮ ቆንጆ …›› እንደሚባለው ተረት አደረገው እኮ ይሄን ምርጫ የሚለውን ነገር በማለት፤ ዋ…! ምርጫስ 97 ላይ ቀረ፣ አከተመ፡፡ ሲሉ በትዝታ ሰረገላ የ97ቱን የምርጫ ውድድር ብርቱ መንፈስና ሰፊ ሆነውን ሕዝባዊ ተሳትፎ በሐዘኔታ ውስጥ ሆነው እያስታወሱ፣ ወይ ነዶ፣ ዋ ምርጫ፣ የምርጫስ ነገርስ ይቅርብን ተዉን እባካችሁ … ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በእርግጥ ከ1997 ወዲህ ለተደረጉ አገር አቀፍም ሆነ የክልል ምርጫዎች እንዲህ መቀዛቀዝና ሕዝቡ ለመምረጥም ሆነ ለመመረጥ ያለው ፍላጎትና ስሜት እየወረደና እንደ በረዶ እየቀዘቀዘ መምጣት ገዢው ፓርቲ ብቻውን ተጠያቂ አይሆንም ባይ ነኝ፡፡

በአገራችን የሚገኙ አብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲዎችና አመራሮቻቸው ራእይ አልባነት፣ ቁርጠኝነት ማጣት፣ በሕዝብ ልብ ውስጥ ለመግባት የሚያስችላቸው ፕሮግራምና ፖሊሲ ለመቅረጽ መታከታቸውና ትግሉ የሚጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ያላቸው ዝግጁነት አናሳ መሆኑ አንዳንዶቹን ፓርቲዎችና አመራሮቻቸውን በበቃኝ ከትግሉ መድረክ እንዲያፈገፍጉ እያደረጋቸው እንዳለ እየታዘብን ነው፡፡

እንዲሁም በአገራችን የሚገኙ አብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲዎችና አመራሮቻቸው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደርስባቸውን ጫና መቋቋም አቅቷቸው፣ እንደ እሳት ሊፈትናቸው ያለውን መከራ በሩቅ ሸሽተውትና ቀቢጸ ተስፋ ተውጠው፣ ለገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ሜዳውም፣ ፈረሱም ይኸው በማለት ለብቻው ያለአንዳች ከልካይ በአገሪቱ የፖለቲካ ሜዳ ላይ እንደ ልቡና እንዳሻው ይጋልብበት ዘንድ በከፊል ቢሆን ዕድሉን አመቻችተውለታል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አለመጠናከርና በአመራሮቻቸው መካከል ያለው አምባገነንነት፣ የእርስ በርስ አለመግባባት፣ ሽኩቻ፣ መወጋገዝና መከፋፈል የራሱ ሆነ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ደግሞ ማንም የማይክደው ሐቅ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡

ከምርጫ 97 ማግስት በኋላ እርስ በርሳቸው መካሰስን፣ መወነጃጀልንና መወጋገዝን ሥራዬ ብለው የያዙት የተቀዋሚ ፓርቲ አመራሮች አንዱ የአንዱን ገበና ሳይቀር እንኳን በአደባባይ በማውጣት የገቡበት ቅሌትና የስነ ምግባር ውድቀት፣ አይወርዱ አወራረድ በብዙዎች ዘንድ ለመሆኑ እንደው የሆነስ ሆነና ኢህአዴግ ሥልጣኑን ቢያስረክባቸው ኖሮ ይህችን አገር ሊመሩ የነበሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ እንዴ እስኪሉ ብዙዎች በእፍረት እንዲሸማቀቁና እንዲያንሱ ያደረጉበትን በርካታ አጋጣሚዎችን ታዝበናል፡፡

በአገራችን ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎችና አመራሮቻቸው በሕዝብ ዘንድ አመኔታን በማጣታቸው የተነሳ አብዛኛው ሕዝብ ‹‹ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ምንትስ ይሻለናል፡፡››፤ ‹‹ትሻልን ትቼ ትብስን አመጣሁ፡፡›› እንዳይሆን በሚል ስጋት ወዶም ሆኖ ሳይወድ ኢህአዴግን የሙጥኝ እንዲል የተገደደ ነው የሚመስለው፡፡ እናም ዛሬም ድረስ ተቃዋሚ ነን በሚሉ የትላንትናዎቹ አንጋፋ ፓርቲዎች ውስጥ የተከሰተው ታላቅ የሆነ ስብራት ወይም ስንጥቃት የተጠገነ፣ ቁስሉም የተፈወሰ አይመስልም፡፡

የገዢው ፓርቲ የኢህአዴግ ግትርነት፣ ለሕዝቡ ከእኔ በላይ ለአሳር የሚለው አመለካከቱ፣ በአማራጭ መንገዶችን ለማየትና ከሌሎች ጋር ለመነጋገር ያለበት ችግርና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ያሉት ኁልቆ መሣፍርት የሌላቸው ችግሮች ተደራርበው አገራችን የምታልመውን የዲሞክራሲያ ሥርዓት ግንባታን ዕድገት እያጓተተው ነው፡፡

ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግና አጋሮቹ የ1997ቱ ዓይነት ሕዝብ አቀፍ የሆነ የዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ መንፈስና ቅናት ዳግም እንዲፈጠር ከመሥራት ይልቅ ዛሬም በለመደው ሸካራ መንገድ መጓዝን ነው የመረጠው፡፡ ኢህአዴግ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ተቀራርቦ ለመነጋገር፣ ለመወያየት የጠረቀመውን በሩን በጨዋ መንገድ ለመክፈት ዛሬም ተቸግሮ ያለ ነው የሚመስለው፡፡ እናም በጠላትነት የመተያየት፣ የጥላቻና የጽንፈኝነት ክፉ መንፈስ ዛሬም ድረስ በአገራችን የፖለቲካ ሰማይ ላይ የመጠፋፋትን፣ የመበላላትን ጥቁር ደመና እንዳዘለ ነው፡፡

በዚህ ሁኔታ ደግሞ በፊታችን የሚጠበቀው አገር አቀፉ ምርጫ 2007 የተለየ አንድምታ ሊኖረው አይችልም የሚለው ተስፋ አስቆራጭ የሚመስል ድምፆች ከዚህም ከዚያም እየተሰሙ ናቸው፡፡ ያው እንደተለመደው ምርጫ ሲደርስ ከተደበቁበት ጎሬ ወጥተው አለን አለን የሚሉት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ምርጫን ሰበብ አድርገው እንደ እንጉዳይ የሚፈሉትና እዚህም እዛም ብቅ ብቅ የሚሉት የአገራችን ፓርቲዎች እንደልማዳቸው በመጪው ምርጫ ግርግር መፍጠራቸው አይቀር ይሆናል፡፡

ግና ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውን የሚያስፈልጋቸው ፓርቲና ፖለቲከኛ የምርጫ ሰሞን አለሁ አለሁ የሚል የትርፍ ጊዜ ፓርቲና ፖለቲከኛ አይደለም፡፡ የአገሪቱን የፖለቲካ ታሪክ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቿን፣ የሕዝቦቿን ሃይማኖት፣ ታሪክ፣ ባህልና ቅርስ በሚገባና ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ በአገሪቱ ብሔራዊ እርቅ፣ መግባባትና አንድነት እንዲመጣ ጠንክሮ የሚሠራ፣ እንደ ማህተመ ጋንዲና እንደ አፍሪካዊው ኔልሰን ማንዴላ የፍቅርን፣ የወንድማማችነትንና የእርቅን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጎ የሚያውለበልብ፣ ቆራጥና የሕዝብ ወገንና አለኝታ የሆነ ፓርቲና ፖለቲከኛ ነው ብዙዎቻችን በእጅጉ የናፈቀን፣ የሚያስፈልገንም፡፡

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአገራችን የተከሰተው አብዮት ካመጣቸው መዘዞች አንዱ የፖለቲካ ፕሮፌሽናል ደረጃ እየወደቀ መሄድ ነው፡፡ የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ሺፈራው በቀለ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማኅበር ባዘጋጀውVision 2020 የሥራ ባልደረባቸው የሆኑት ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ ‹‹ምን አለምን? የት ደረስን? ወዴትስ እያመራን ይሆን?›› በሚል አርዕስት ባቀረቡት የጥናት ጽሑፍ ላይ ባቀረቡት ለውይይት ማጫሪያና ማዳበሪያ የሚሆን መነሻ ሐሳብ ላይ ሲገልጹ፡-

ፖለቲካ ማለት መቀላመድ፣ ለዘመድ አዝማድ፣ ለአምቻ ለጋብቻ፣ ለዘር፣ ለወገንና ለጎሳ ‹‹ጮማ መቁረጥ ጠጅ ማንቆርቆር›› (በዚህ ዘመን እንኳን ምናልባት ውስኪ ማውረድ ቢባል ይቀላል፡፡) ማለት ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያውያን አእምሮ ውስጥ በፖለቲካና በማፈያ መካከል ልዩነቱ እየደበዘዘ ሄዷል ማለት ይቻላል፡፡ በመሠረቱ ግን ፖለቲካ በምዕራቡ ዓለም እጅግ ተከበረ ፕሮፌሽን መሆኑን በመጠቆም የታሪክ ምሁሩ በአገራችንም በጥንት ጊዜ ፖለቲካና ፖለቲከኝነት እንዲሁ እንደነበር ያስረዳሉ፡፡

ፕሮፌሰር ሺፈራው ፖለቲካና ፖለቲሺያኖች የተከበሩ፣ ጨዋ፣ የጨዋ ጨዋ ካልሆኑ፣ የሚናገሩት ከመሬት ጠብ የማይል ካልሆነ ምንም ያህል ውብ ውብ ራእዮች ስንደቀድቅ ብንውል ራእዮቻችን ዋጋ አይኖራቸውም ሲሉ ነው የሚደመድሙት፡፡

በስነ ምግባር የታነጸ፣ ጨዋ፣ ለራሱ ሳይሆን ለሕዝቡ የተሰጠ፣ ልክ እንደ እስራኤላውያኑ መሪ ሙሴ ‹‹ይህን ሕዝብ ከምታጠፋው እኔን ከሕይወት መጽሐፍ ደምስሰኝ፡፡›› የሚል በሕዝብ ፍቅር የሰከረ፣ በሳል ፖለቲከኛ/መሪ፣ ከጽንፈኝነት፣ ከጥላቻና ከጎሰኝነት የጸዳ ጠንካራ ፓርቲና ፖለቲካኞች ለማየት አልናፈቃችሁም ወገኖቼ?!

በትንሹም በትልቁም ዛቻና ማስፈራሪያ እየበረገገ፣ መከራው ሲጸናበትና ቀንበር ሲከብድበት ለሕዝብ የገባውን ቃል አጥፎ፣ ‹‹ሞቴም መቃብሬም እዚሁ ነው፡፡›› ብሎ ምሎ እንዳልተገዘተ ሁሉ ‹‹በቦሌም በባሌም›› ብሎ እግሬ አውጪኝ በማለት ወደ አውሮፓና አሜሪካ የሚሰደድ ሳይሆን፣ እዚሁ በአገሩ ከሕዝቡ ጋር ደጉንም ክፉውንም ተቀብሎ በትዕግሥት፣ በጽናት እና በሰላማዊ መንገድ የሚታገል፣ በሕዝብ ፍቅር የወደቀና የነደደ እንደ ጋንዲ፣ እንደ ማርቲን ሉተር፣ እንደ አፍሪካዊው ኔልሰን ማንዴላ ያለ የሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነ ፓርቲና ፖለቲከኛ አልናፈቃችሁም ወገኖቼ!

እንዲህ ዓይነት ከሕዝብ ለሕዝብ የሆኑ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች ሲፈጠሩ ሕዝቦች ያለ ምንም ቀስቃሽና ወትዋች በነቂስ ወጥተው ያገለግለናል፣ ይጠቅመናል የሚሉትን ፓርቲም ሆነ እጩ ለመመረጥ የሌሊቱ ቁር፣ የቀኑ ፀሐይ ሳይበግራቸው መብታቸውን አውቀው ለመጠቀም ይተጋሉ፣ ይሰለፋሉ፡፡ ምርጫ 97 ደግሞ ይህን ሐቅ ለመንግሥት ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሕዝብ ሁሉ በይፋ አሳይቷል፣ አስመስክሯል፡፡

ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለመቀመጫ ወይም ለስልጣን ከመወዳደራቸው በፊት የሕዝብን ልብ አሸንፈው፣ በሕዝባቸው ልብ ዙፋን ላይ ሊቀመጡ የሚችሉበትን ፍቅርን፣ መፈራትን፣ መወደድንና መከበርን ያገኙ ዘንድ መትጋትና መሥራት ይኖርባቸዋል፡፡ የዛን ጊዜ ምርጫው ምርጫ ይሆናል፤ ሕዝብም ያለ ምንም ቀስቃሽ የመምረጥ መብቱን ለመጠቀም በነቂስ ተጠራርቶ ይወጣል፡፡

ሰላም! ሻሎም!

ECADF.COM

በሳንድያጎ የወያኔዎች ስብሰባ ሳይጀመር ተበተነ

በሳንዲያጎ የወያኔ አምባሳደር ይገኝበታል ተብሎ በአባይ ግድብ ስም ቦንድ ለመሸጥ የተጠራው ስብሰባ በኢትዮጵያውያን ተቃውሞ እንዲቋረጥ ሆንዋል።

Ethiopians in San Diego Protest April 28, 2013

በቁጥር ከሁለት መቶ በላይ የተቆጡና በርካታ መፈክሮችን ያነገቡ ኢትዮጵያውያን ስብሰባው በሚደረግበት አዳራሽ የተገኙት ቀደም ብለው ነበር።

TV channels covering Ethiopians demo. in San Diego

በርካታ ታዋቂ ሚድያዎች በቦታው ተገኝተው የተቃውሞዉን ትዕይንት የዘገቡ ሲሆን የቴሌቪዥን ጣብያዎች ዜናውን ማምሻው ላይ ለቀውታል።

ወያኔዎቹ በሌሎች ቦታዎች የገጠማቸውን ከግምት አስገብተው 3 ሰዎች በር ላይ አቁመው የራሳቸውን ሰዎች ብቻ መርጠው ለማስገባት ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም።

ስብሰባው ሲጀመር የወያኔዎቹ ቁጥር ከ20 በታች ሲሆን ኢትዮጵያውያኑ ከሁለት መቶ በላይ ነበሩ።

ነገር አሳምራለሁ ብሎ ስብሰባውን እንግሊዝኛ ቋንቋ በመናገር የጀመረው የወያኔ ተወካይ በጥዋቱ ነበር ተቃውሞ የገጠመው፣ ኢትዮጵያውያኑ “እኛ ኢትዮጵያውያን ነን በቋንቋችን ተናገር” ብለው አስቆሙት። ተወካዩ ንግግሩን በአማርኛ ቀጠለ “እኛና እናንተ…” ብሎ ሊቀጥል ሲል አሁንም ከባድ ተቃውሞ ገጠመው “እናንተ እነማን ናችሁ? እኛስ ማን ነን? አትከፋፍለን እኛ አንድ ነን” አሉት።

ECADF.COM

Rally in New York: Ban Ki-moon UN Secretary-General is Aware of the Crimes Against Humanity in Ethiopia

by Tedla Asfaw

Ethiopians Rally in New York: Demanding UN investigate Ethnic Cleansing

(NEW YORK) – The Monday April 29, 2013 cloudy sky with drizzle seems to remind the largest Ethiopian crowd in recent memory here in NYC the darkest time of our people under the minority regime of TPLF/Woyane. The cry of Amharas in Beni Shanguel Gumuz, Gura Ferda, Waldiba who were ethnically cleansed and dumped as landless and homeless by cruel and inhuman TPLF/Woyane thugs carrying the ID of “Nations and Nationalities” is indeed the turning point in our struggle.

It reminded us how it is uncomfortable just to stay few hours out in a rain knowing that it will be over and each one of us will go to our home in D.C., Maryland, Buffalo, Philadelphia, NJ and to all boroughs of New York City. We stood tall to be the voice of poor farmers and monks and challenge UN to condemn the Ethnic Cleansing underway in Ethiopia. We stared at the UN building where Tewodros Adhanom lectured just last week about TPLF/Woyane’s role on Somalia “security”. We call it “Kiraye Sebsaba Politica” or blackmailing politics.

Shame on him and his regime who snatched the “security” of thousands of Amharas from their home they built from scratch. Shame on him who Kicked out children from their school without warning. Shame on him who forced pregnant women to give birth in forests with no medical care.

The condemnation of the Woyane fascist and barbaric regime that started at 11am by fifty brave Ethiopians who came from NY Tri State area some driving seven hours from upstate New York started with a good news from NY organizers. By 10:30am the copy of the letter prepared for H.E. Ban Ki-Moon UN Secretary General was delivered to USA Ambassador to United Nations, Ambassador Susan Rice. We know pretty well that the content of this letter will soon reach to President Obama via John Carry, Secretary of State.

John Carry who is travelling to Addis Ababa on the 50th anniversary of OAU next month will be challenged to condemn Ethnic Cleansing and all human rights violations in Ethiopia in public. The USA Ambassadors to Ethiopia past and present were and are acting as “member” of TPLF. The State Department findings about Ethiopia is nothing more than empty gesture. We believe this time is different if they take note of the anger building in the diaspora community this month alone. We demand the Obama Administration to follow the recommendation of its own department without any excuse whatsoever.

The campaign to be heard by UN Secretary-General went on for a week by email and fax from the Ethiopian Diaspora all over the world. The fax and email flooded his office. When our five delegates went to deliver the letter asking UN to condemn Ethnic Cleansing and send an independent investigation team the positive reply we received was not surprising to most of us.

“The Secretary Genera was aware of what was going in Ethiopia ” especially the Ethnic Cleansing even before he received our letter. The Prime Worshipper/Minster Hailemariam was forced to admit in his own parliament about Ethnic Cleansing after his European tour of begging. He blamed the “locals” for carrying out the crime. Yes crime is committed locally but order was given from TPLF/Woyane who some were heard saying on VOA and ESAT Radio that they needed to clear the land for investment.

The Ethnic Cleansing of Amharas was to secure land for Woyane landlords. The list of the people who are directly connected to the crime against humanity was out to the public and UN . Omad Obang, Gambella, Shiferaw Shigute, Gura Ferda and South Omo Valley, Ahmed Nasir, Beni Shanguel Gumuz, Abdi Mohamud Omar, Ogaden, Abdi Maxamud Cumar, Ogaden, Abay Tsehai and Sibaht Nega , Waldiba was a short list for crimes against humanity present and past for which we demanded UN investigation.

The past crimes against Annuak, Mursi, Ogaden and Oromo people were executed under the direct order of late Meles Zenawi. The crowd condemned Hailemariam as a “leader” who is led by TPLF/Woyane thugs behind the curtain to finish the Job the late Meles Zenawi started more than 21 years ago. Bereket Simon and Shiferaw Tekelamriam the “director” of the Movie “Jihadwi Harkeat”, Christians VS Muslims anti Muslim propaganda were among the names accused as crimes against humanity.

The huge crowd from D.C. who came in two buses, vans and small cars joined the rally between 12pm and 1pm. Dag Hammarskjold Plaza ( UN Plaza ) was on fire. The big blast from the sound system should have awaken anyone from long distance. No wonder the Woyanes from the surrounding area were forced to come out and face the condemnation of the system they are defending.

The drizzle had no impact on the protesters at all. Bishop Filipose and Sheik Kalid short but direct call to all of us here and back home was emotional. Bishop Filippose compared our situation to the time of fascist occupation of Ethiopia where one patriot Dr. Melaku Beyan organized black Americans to stand with the Ethiopian people who were abandoned by League of Nations and USA..

However, at this very moment Ethiopia has thousands of Melaku Beyans thanks to the huge populations of Ethiopians in the Diaspora. Woyane’s “rent collection/Kiraye Sebsaba” project though succeeded back home using brute force and blackmail it failed miserably to be replicated here in the diaspora, “KeAbaye Befit Zeregnet Yegedeb” before building dam to collect water let us “build” a dam to check on a poison called racism is a rallying cry by Ethiopians.

Sheik Khalid reminded us what Woyane did in May 2005. Woyane played effectively Muslims VS Christians. ” If Kinijit captured power the Muslims were told the end of their fifteen years of religious freedom”. The Muslims though most of them voted for Kinijit did not stand with fellow Ethiopians to call for their vote to be counted. Woyane resurrected for vengeance !!!! Business who supported Kinijit lost their livelihood and now most retail and wholesale is under control of Woyanes.

Sheik Khalid did not hide his disappointment for fellow Ethiopian Christians not joining the Muslim struggle “Dimtsachen Yesema”, Let our Voice be Heard a more than 16 month peaceful struggle which shook Woyane’s foundation of ethnic division as was expected. He said our community need to come together and take back our country.

We compliment Sheik Khalid by calling Christians to take their Sunday as a day of prayer and a day to stand with those monks at Waldiba, fellow Christian farmers who are kicked from their land and fellow Muslims who have been struggling for Woyane to get out of Mosques and Islamic Institutions, for Abay Tsehai and Sibhat Nega to get out of our church affairs.

We the believers should take this matter into our own hands back home and here in Diaspora. Priests and church administrators who are on our way should be condemned as cowards who bow for the devil. Let us tell them that this is our Christian Obligation to stand with fellow Orthodox Christians and fellow Muslim brothers and sisters.

The poems, songs and slogans indeed made our rally a tourist attraction. Many posed to take picture with our beautiful people and flag. Young Ethiopian Muslims dressed in their Hijab, mothers with traditional cloth and many who came with yellow, green and red scarf gave beauty to our rally. When the good news of the Secretary General five staffs reviewing our letter for immediate tangible reply came to the public the roar was deafening. The NYC organizers will update fellow Ethiopians in Social Medias, diaspora radios and TV on the development at UN Secretary General Office.

At 3pm NYC organizers thanked all who came from long distance sacrificing a day to be the Voice for the Voiceless Victims of Ethnic Cleansing and Human Rights Violation. The energized crowd extended the rally for 45 minutes. The Woyane Council faced a huge angry crowd denouncing crimes against humanity perpetrated by TPLF/Woyane.Those who are associated with these crimes by collecting money in the name of “building a dam” can not escape responsibility. There is no place in NY, D.C, Oslo or wherever it maybe to hide and lie. Your time is up !!. We will follow you and expose you for the public. God is Great, Alah Wakiber !!!! Ethiopia Will Be Free !!!

 

በህዝብና በሀገር ላይ ቀልድ የለም (በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ስብስብ)

በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ስብስብ የተሰጠ የተቃዉሞ መግለጫ

ህዝባችን መስዋእትነት ከፍሎና ተንከባክቦ ባቆያትና እትብቱ በተቀበረባት ምድር የመኖር ነፃነቱን ከተነፈገ፣ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን በዘርና በቋንቋ እየተመነዘረ በገዛ ሀገሩ እንደ ባይታዋር ተቆጥሮ ከተባረረና ሜዳ ላይ ከተጣለ፡- ሀገር አለኝ ማለቱ ትርጉሙ ምንድን ነው?። የውጭ ባለሃብቶች ለም መሬታችንን ይዘው ኰርተውና ተንደላቅቀው ሲያርሱና ሲያለሙ በአንፃሩ የሀገሩን ባለቤት የሆነውን ህዝብ የበይ ተመልካችና ተመፅዋች ሆኖ እየተንከራተተ የሚኖረው እስከ መቼ ይሆን?። ይህ ዓይነቱ አሳፋሪ እርምጃ እየተደጋገመ ከሄደስ የሀገራችን የወደፊት ዕጣ ፋንታ ምን ሊሆን ይችላል? ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ ስርዓተ አልበኝነት ነግሶ ህዝቡ አቤት የሚልበት የፍትሕ ቦታ አጥቶ ሲተራመስ ስናይ ለመሆኑ በሀሪቱ ላይ መንግስት አለ ወይ? የሚለውን ጥያቄ እንድናነሳ አድርጎናል።

ሰሞኑን በቤንሻንጉል አካባቢ በሽዎች በሚቆጠሩት የአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው ከቤት ንብረታቸው የማፈናቀል ድርጊት በተለያዩ ሚዲያችና እንዲሁም ሜዳ ላይ ከወደቁት ተፈናቃዮች ከራሳቸው አንደበት ስንሰማ እጅጉን አሳዝኖናል። ይህ አረሜናዊ ድርጊት ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚል መንግስት ቀርቶ በባዕዳን ወረራ ጊዜም ቢሆን ያልተፈፀመና በኢትዮጵያ የመንግስታት ታሪክም ታይቶ የማይታወቅ አስነዋሪ ተግባር መሆኑን አሳይቶናል። ከዚህም አልፎ የሚያሳዝነውና የሚያስገርመው ደግሞ ድርጊቱን መፈፀሙ ብቻ ሳይሆን የህወሓት/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት እንደ ለመዱት ሁሉ ወንጀሉን ለመሸፋፈን ሲሉ የሰጡትን መግለጫ በህዝቡ ህይወት ላይ መቀለድና ማፌዝ መሆኑን በይፋ አሳይቶናል። ሰለሆነም ፡-

1. የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት በወገኖቻችን ላይ እየፈፀመ ያለው አረሜናዊ ድርጊት ኢትዮጵያዊነት ስነ ምግባር ያልተከተለ፣ የህዝባችን ሕገ መንግስታዊና ዜግነታዊ መብት የሚጥስ፣ ዓለም አቀፋዊ የሰብኣዊ ፍጡር አያያዝ የሚፃረር የወንጀል ድርጊት በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን። በዚሁ የወንጀል ድርጊት ላይ የተሳተፉ ሰዎችም በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን።

2. “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም” ነውና የዜጎች ህይወት የዶሮን ያህል ክብር ሳትሰጡ ሀገርንና ህዝብን በፍርፋሪ፣ በስልጣንና በጊዚያዊ ጥቅም በመለወጥና እንዲሁም የህዝቡን ትዕግስት፣ ጨዋነትና ዝምታ እንደ ሞኝነት በመቁጠር በየዋሁ ህዝባችን ላይ ወንጀል እየፈፀማችሁ የምትገኙ የስርዓቱን ካድሬዎችና ደጋፊዎች ሁሉ ትዕግስት ገደብ አለውና የዛሬ ዝምታ የነገ እሳተ ጎሞራ እንደሚሆን ተገንዝባችሁ ከእኩይ ድርጊት እጃችሁን እንድታነሱ እንጠይቃለን።

3. በህዝባችን ላይ እየተፈፀመ ያለው የወንጀል ድርጊት እንደ ተለመደው “የባሰ አታምጣ” ተብሎ በማድበስበስ፣ በዝምታና በማዳፈን የሚታለፍ ሳይሆን ጉዳዩን ገለልተኛ አካል እቦታው ድረስ ሂዶ እንዲያጠራ ዓለም አቀፍ ሰብኣዊ መብት ተሟጓች ድርጅቶችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

4. በሀገር ውስጥም ሆነ በዲያስፓራ የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ሁሉ በመካከላችን ሊኖር የሚችለው የአመለካከት ልዩነት እንደ ባላንጣነት ሳይሆን እንደ ውበት ተቀብለን ለጋራ ችግር በጋራ መቆም ጊዜው የግድ ይለናል። ካልሆነ ግን በተናጠል ተበታትነን በየተራ እየተደቆስን መኖር የማይቀር ነው። ስለዚህ “ጎርፍ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው” እንዲሉ የህወሓት/ኢሕአዴግ መሪዎች ቀለማቸውን እየቀያየሩ በልማት ስም የህልም እንጀራ ለማብላትና መርዝ በማር ጠቅልለው ለማጉረስ ሌት ተቀን እንቅልፍ አጥተው ሲንቀሳቀሱ እኛ ደግሞ የህልውናችን ሞሶሶና ዋስትና በፍቅር፣ በመከባበር፣ በመደማመጥና በመቻቻል ላይ የተመሰረተ አንድነት በተግባር ማሳየት ለነገ የማይባል የያንዳንዳችን አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን በፅኑ እናምናለን።

5. ኢሕአዴግ በተለይም ዕድሜ ልኩን ያንተ ነፃ አውጪ ነኝ እያለ በትግራይ ህዝብ ስምና ደም ሲነግድ የኖረው ህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) በተለመደው ባህሪው በወንድሞቻችን ላይ እየፈፀመ ያለው ጭካኔ የተሞላበት አረሜናዊ ድርጊት ሆን ተብሎ ወገን ከወገኑ ጋር ለማጋጨትና ጥርጣሬ ለመፍጠር የተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ከተገነዘበው ውሎ አድረዋል። ስለዚህ ህወሓት በኢትዮጵያውያን መካከል እየተከለ ያለው ልማት ሳይሆን ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ የጥፋት ፈንጅ መሆኑን በመገንዘብ የአንድነትና የሰላም ባላንጣ የሆነውን ድርጅት የሚፈፀመው ግፍ ከካድሬዎቹ በስተቀር ብዙሃኑን የማይወክል መሆኑን እየገለፅን ቡድናዊ አምባ ገነኖችን ከህዝብ ነጥሎ መታገል የፓለቲካ ብልህነት ብቻ ሳይሆን አማራጭ የሌለው የለውጥ መንገድም እሱ ብቻ መሆኑን እናምናለን።

6. እኛም ከማንም ከምንም በላይ ዘር፣ ቦታ፣ ሀይማኖት፣ ቋንቋ፣ የፓለቲካ እምነትና ስደት ሳይገድበን ከ80 ሚሊዮን በላይ የሆነውን ህዝብ እንደ ዓይን ብሌናችን በማየት ችግሩ ችግራችን፣ ደስታው ደስታችን፣ ሀዘኑም ሀዘናችን መሆኑን በማመን የጋራ ችግራችንን በጋራ ለመፍታት በሚደረገው የለውጥ እንቅስቃሴ ከጎኑ የምንቆም መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ እናረጋግጣለን።

ኢትዮጵያ ሀገራችን ለዘላለም ትኑር

 

 Zhabesha.com

በብአዴን ወለድ አግድ ስር ያለ የአማራ ህዝብ

እንግዳ ታደሰ – ከኖርዌይ

ሲፈልግ ሸክፎህ – ሲያሻውም መትሮህ

እንደዘንቢል ጭኖህ-እንደንፍሮ ዘግኖህ

እንደ አጋሰስ ጋልቦህ- እንደ አህያ ገርፎህ

ቀንበር አሸክሞህ – ፉርሽካውን ጭኖህ

ሆድህ ካሸነፈህ – ሰውነትክን ካጣህ

እዛው ማገዶ ሁን – መቸም ፋንድያ ነህ፡፡

አማራ ነን ብለው አማራውን ለሚያስጨፈጭፉ ብአዴኖች

የት እንደሆነ አላስታውስም ግን አንብቤአለሁ ፡፡ << አማራው እርስ በራሱ የሚጣፋ ፍራክሽን ነው >> የሚል ኃይለ ቃልን የያዘ ቁጭት ወይም ሹፈት ፡፡ ኃይለ ቃሉ ! ለሚቆጩት እራሳቸውን እንዲመረምሩ ፣ ለሚያላግጡበት ደግሞ ፣ሁኔታው ወደ አልተፈለገ ፍጥጫ ወስዶ ! የማን ቤት ለምቶ ! የማን ይጠፋ ? ወደሚል አደጋ ውስጥ እንዳይወስደን እሰጋለሁ ፡፡

በኢትዮጵያዊነት ፍቅርና ማተብ ላደገ ዜጋ ምናልባት አማራነቱን እንዲያውቅ በታሪክ የተገደደበት ዘመን ቢኖር በወያኔ የአገዛዝ ዘመን ብቻ ነው ፡፡ ወያኔ የከፋፍለህ ግዛ የአገዛዝ መዋቅሩን በአገሪቱ ካሰፈነበት ጊዜ ጀምሮ ፣ ኢትዮጵያዊ ነው ዜግነቴ ብሎ ፈርጥሞ የሚናገረውን ዜጋ ! በትምክህተኝነትና በነፍጠኝነት ድሪቶ በማስደረት አንገቱን እንዲደፋ ለማድረግ  የተኛበት ጊዜ አንድም ቀን አልነበረም ፡፡ ይህን እኩይ ሥራውን ለማካሄድ የአቶ መለስ መንግሥት ፣ ከቤተ መንግሥቱ ከሚደላ ፍራሽ ይልቅ ፣ የዛፍ ላይ እንቅልፍን መርጧል አሁንም ይመርጣል ፡፡

ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለ ዜጋ መታወቂያ እንዳይሰጠው አድርጓል ፡፡ በተለያዩ መንግሥታዊም ሆነ የግል ንግድ እንቅስቃሴ ላይ  የዜግነትን መብት የሚያጎናጽፈውን ብሄራዊ መብቱን እንዲያጣ ደንግጓል ፡፡ ይህን የብሄረሰብ ማንነትን የሚያሳይ መታወቂያ የያዘ ዜጋም ቢሆን በነርሱ አጠራር አምሀራ፟ ከሆነ ከመገፍተር አላዳነውም ፡፡ እንዲያውም ክፉ ዘመን ሲመጣ በቀላሉ ተነጥሎ እንዲመታ አድርጎታል ፡፡ በደኖን ፥ ዎተርን ፥ ጉርዳፈርዳን እንዲሁም በቅርቡ በቤኒሻንጉልና ጉሙዝ ክልል እያየን ነው ፡፡ መታወቂያው ላይ ያለው ብሄር- አማራ  የሚለው ታፔላ ከሌሎች ወገኖቹ ኢትዮጵያውያን በመልክና በቁመና ባይለይም ወያኔ ሠራሽ በሆነው መታወቂያ ተለይቷል ፡፡ የወያኔ ወንጭፍ ሳያንቀላፋ በየጊዜው እንደ አሜባ ቅርጹን እየለዋወጠ እንደ ተውሳክ አማራውን ማጥቃት ይችላል  ፡፡

አማራውን አሳጥቶ ለማስመታት ወያኔ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም ፡፡ ወደ ደቡብ ብንወርድ ፣ አማራና ፍየል እየተረገሙ ይረባሉ የሚል ብሂል ሞቅ ተደርጎ እንዲጮህ አድርጓል ፡፡ወደ ሱማሌ ክልል ብንሄድ ፣ ኢትዮጵያዊውን ሱማሌ የሂሳብ ትምህርት ሲሰጠው ፣ አምስት ፍየል ቢኖርህና ማታ ሲመሻሽ ወደጉሮኗቸው ሶስቱ ብቻ ቢመለሱ ሁለቱን ፍየሎች ማን የበላቸው ይመስልሃል ? ብሎ ሲጠይቅ ተማሪው ነብር ቢሆን መልሱ ተሳስታችኋል ፣ የበላቸው አምሃራ ነው ብሎ ያስተምራል ፡፡ በቅርቡም በዘመነኛው ፓልቶክ ተብሎ በሚጠራው የውይይት መድረክ ፣ እቶን የምትተፋው የገዛ ተጋሩ የትግራይ ሴት ካድሬ  የአማራውን ህዝብ ልሂቃን popcorn politician ብላቸዋለች ፡፡ የሚንጣጡ ፈንድሻዎች ! ጧጧ ብቻ በማለት ተሳልቃባችዋለች ፡፡

በቅርቡ ከወደ ትግራይ አንድ አርቆ አሳቢና መጪው ጊዜ አደገኛ እንደሆነ በተገኘው አጋጣሚ የሚጽፍልን ወጣት አብርሃ ደስታ ያለውን ማስተዋል ይገባል ፡፡ በትግራይ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በነበርንበት ወቅት ፣ የደርግን ክፉነት በጨቅላ ዓይምሮአችን እንዲቀረጽ ለማድረግ ፣ ደርግ አማራ ነው የሚል ትምህርት ተሰጥቶን ነው ያደግነው ብሏል፡፡ ቢያንስ ይህ ወጣት በትግራይ ህዝብ ስም የሚነግዱትን ወገኖቹን ክርስቶስ ለስጋው አደላ በሚለው ብሂል ቀባብቶ አላለፋቸውም ፡፡ ቢያንስ የትግራይ ህዝብ በአማራው ክልል ውስጥ ወልዶና ተዋልዶ ይገኛልና ነግ በኔ እንዳይሆን ብሎ በኢትዮጵያዊነት ጨዋነት ወያኔዎች አዙረው እንዲያዩ አድርጓል ፡፡

ሚሚ ስብሃቱ ! የአማራውን መባረር ከዛፍ ጨፍጫፊነቱ የተነሳ የተወሰደበት ርምጃ ነው ብላ ሰሞኑን እንደረገመችው ይህ ወጣት የትግራይ ልጅ በአምሃራ ጥላቻነት እንዲማር ቢገደድም – በአማራው ህዝብ ላይ አልተሳለቀበትም ፡፡ አይጋ በሰሞኑ የሆድ አደሩን የተስፋዬን ሃቢሶ የአማራውን መርገምት ጽሁፍ ለተባረሩት አማሮች ምክንያት ነው ብሎ እንደለጠፈው የዘረኝነት ዝብዝንኬ ጽሁፍ ፣ ይህ የትግራይ አርቆ አስተዋይ ወጣት ወርዶ የአማራውን ህዝብ   አልሰደበም ፡፡ ተዉ የትግራይ ህዝብ አማራው ውስጥ አለ እየኖረም ነው ብሎ ነው የመከረው ፡፡

ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ታሪካዊ ቦታዎች ጉዞ

ጡጦውን ላመጣ ከጓዳ ገብቼ

የወተቱን ሙቀት ስለካ ቆይቼ

ስመለስ ሳሎኑን ትበረብራለች

የመኪናውን ቁልፍ የት ነው ያደረግሽው ? ብላ ፊቴ ቆመች

ዓይኔ ዓይኗ ላይ ሆኖ ጊዜን ተሟገትኩት

በምንኛ ፍጥነት ከቅፌ ፈልቅቀህ ልጄን ወሰድክ አልኩት ፡፡

ግጥም ዝነኛዋ ጸሃፊ ዓለም ፀሃይ ወዳጆ

ከባለቤቴ ጋር በመሆን አገራችንን ሳናውቃት በስደት የተለየናትን የሰሜን ኢትዮጵያ ታሪካዊ ቦታ ለመጎብኝት የዛሬ 12 ዓመት ግድም ጉዟአችንን ከአክሱም ለመጀመር ፣ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተናል ፡፡ከተሰቀለው የጉዞ ማሳያ ሰሌዳው ላይ አክሱም የሚል ባለመለጠፉ ፣ ከባለቤቴ ጋር ስንጠያየቅ ፣ አንዲት ከጀርባዋ ላይ አንስተኛ ቦርሳ የሸከፈች ወጣት ሴት ልጅ ለካስ ታዳምጠን ኖሮ ! ወደ አክሱም ነው የምትሄዱት ብላ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ትጠይቀናለች ፡፡መልሳችን አዎ! ስለነበር ፣ እኔም ወደዚያ ስለሆነ ሰልፉ እዚህ ነው አብረን እንሄዳለን አለች ፡፡ ተረጋግተን ሰልፋችንን ይዘን ስንጠባበቅ የመብረሪያ ሰዓታችን ደረሰና ወደ ጢያራዋ ውስጥ ዘልቀን ገባን ፡፡ ይህች ወጣት ልጅ የመጣችው ከካናዳ እንደሆነ ፣ በትውልድ ቀዬዋ ከዛው አክሱም እንደሆነች ነግራን እኛም ከየትኛው የውጭ አገር እንደመጣን ጠየቀችን ፡፡ ከሰሜን አውሮፓ ከስካንድኔቪያ እንደመጣን አወጋናት ፡፡

አውሮፕላኗ ውስጥ አቀማመጣችን እርሷ ከፊት ፣ እኔና ባለቤቴ ደግሞ ከርሷ ኋላ የተቀመጥን ሲሆን ፣ ከኛ ኋላ ደግሞ ሁለት ሴቶችና አንድ ወንድ ሆነው በጋራ ሞቅ ያለ ወሬ ተያይዘው ነበር ፡፡ ብዙ ጊዜ ጭውውታቸው በአማርኛና እንግሊዘኛ ጉራማይሌ ቋንቋ ፥ አልፎ አልፎ ደግሞ በትግርኛ እያወሩ ጉዞአችንን ወደ አክሱም ተያይዘነዋል ፡፡ እነኝህ ከኋላችን የተቀመጡት ዲያስፖራዎች ፣ የመጡት ከእንግሊዝ አገር ነበር ፡፡በትግርኛ የሚያወሩትን ንግግር ምን እንደሆነ ባናውቀውም ፣ ከፊት ለፊታችን የተቀመጠችው ከካናዳ የመጣችውና የአክሱም ልጅ የሆነችው ልጅ ግን ታደምጣቸው ነበር ፡፡ አክሱም ደርሰን ከአውሮፕላኗ ስንወርድ፣ጭሥስ ያለችው የአክሱም ልጅ ፣ ከናንተ ኋላ የተቀመጡት ሶስት ሰዎች የሚያወሩትን አድምጣችኋል በማለት ትጠይቀናለች ? በአማርኛና በንግሊዘኛ የሚሉትን ሰምተናቸዋል ፡፡ በትግርኛ የተናገሩትን ግን አልገባንም ብለን መለስንላት ፡፡

ምናሉ መሰላችሁ ? የአውሮፕላኗ አፍንጫ ወደ አክሱም ስታዘቀዝቅ አረንጓዴ ምድር ሲያዩ ! እዪ አድዋን ! እዪ አድዋን እያሉ ይኩራራሉ ፡፡ አውሮፕላኗ እኮ የነበረቸው አክሱም ክልል ነው ብላ በመናደድ ትነግረናለች ፡፡ ግራ የተጋባነው እኔና ባለቤቴ ፣ አድዋ ከዚህ ምን ያህል ይርቃል ብለን ስንጠይቃት ወደ 20 ኪሎሜትር ግድም እንደሆነ ስትነግረን ትንሽ ግራ እንጋባለን ፡፡ እንዴት በሃያ ኪሎሜትር ርቀት የሰው አመለካከት ይለያያል ብለን ግራ ተጋባን ፡፡ ኧንዲያውም የሃያ ኪሎሜት ርቀት ላይ ካለንማ በትራንስፖርት ሄደን አድዋን ማየት አለብን ታሪካዊ አገራችን አይደለች ብዬ እንዳልኩ ፣ የተናደደቸው የአክሱም ወጣት ምን አለ ብላችሁ ነው ? ባዶ ተራራ ነው ብላ ሃሳቤን አጣጣለችው ፡፡

ይህ በዚህ እያለ ሆቴል የት እንደያዝን ትጠይቀናለች ? ገና ሆቴል እንዳልያዝን ግን ጥሩ ሆቴል የቱ እንደሆነ ብትጠቁምን ደስ እንደሚለን ስንነግራት ፣ ጥሩ ሆቴል አስይዛችኋለሁ ፣ ከዚያ በፊት ግን እቤት ገብታችሁ ፥ ምሳ በልታችሁና ቡና ጠጥታችሁ ዕረፍት ካደረጋችሁ በኋላ ነው በማለት በግድ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት ትወስደናለች ፡፡ የግቢውን በር እንደቆረቆረች ፣ የልጃቸውን መምጣት የሚጠባበቁት እናት የውጭው በር ድረስ መጥተው አብረው ስመው ተቀበሉን ፡፡ አማርኛ መናገር ትንሽ ቢያዳግታቸውም በልጃቸው አስተርጓሚነት ምሳ በልተን ፣ ቡና እየጠጣን ብዙ ወግ እናትየዋ አወጉን ፡፡አማርኛ ተናጋሪ በመሆናችን እኝህ አዛውንት እናት አልጎረበጣቸውም ፡፡ የሆዳቸውን አወጉን ፡፡

ወያኔ ወንዶች ልጆቻቸውን ልቅም አድርጋ ወስዳ በህይወት እንዳልተመለሱ ፣ አንድም የቀራቸውን ወንድ ልጅ ፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ሊወስዱት ሲሉ ፣ ወደ አዲስ አበባ አሽሽተው ከዚያም ኬንያ እንዳስገቡትና ካናዳ ያሉት እህቶቹ እየረዱት ኬንያ እንደሚገኝ በማዘን ነገሩን ፡፡ለወያኔ ያላቸውንም ጥላቻ ሳይደብቁ ነገሩን ፡፡ ጭውውታችን ሲያልቅ ፣ እባካችሁ በቂ መኖርያ ክፍል አለን ፥ ሻወርም አለን አትሂዱ እዚሁ እደሩ ብለው ተማጸኑን ፡፡ የለም ጠዋት ስለሆነ ወደ ቀጣዩ የላሊበላ ጉዞ የምናደርገው በጠዋት አንቀሰቅሳችሁም እግዜር ይስጥልን ብለን ፣ በእንግዳ ተቀባይነታቸው አክብረንና እጅ ነስተን ወደ መረጡልን ራሃዋ የሚባል ሆቴል ይመስለኛል ወደዚያ አመራን ፡፡

ላሊበላ አንድ ቀን ቆይተን ቀጣዩ ጉዟችን ጎንደር ነበር ፡፡ ላሊበላ ሳለን አንድ ወጣት ልጅ ያረፍንበት ሆቴል ውስጥ እንተዋወቃለን ፡፡ የተዋወቅነው ወጣት ዲያስፖራ ሳይሆን ላሜ ቦራ ነበርና ፣ ጎንደር ጥሩ ሆቴል የቱ እንደሆነ ስንጠይቀው ፣ ሰርክል የሚባል ሆቴል እጅግ ጥሩ ሆቴል ነው እዚያ ያዙ ይለናል ፡፡ ልጁ በነገረን መሰረት ጎንደር እንደደረስን አውሮፕላን ጣቢያ ያገኘነውን ታክሲ ይዘን ሰርክል ሆቴል አድርሰን እንለዋለን ፡፡

ባለታክሲው ምን እንደሆንን ሳያውቅ ፣ለምን ሰርክል ሆቴል ትይዛላችሁ ? ለናንተ ጥሩ ሆቴል እኔ አስይዛችኋለሁ ብሎ ያግባባናል፡፡   የለም እኛ እዚያ ነው መያዝ የምንፈልገው ብለን ድርቅ እንላለን ፡፡ እሽ ካላችሁ ነገ ግን አድራችሁ ሳገኛችሁ አዝናችሁ አገኛችኋለሁ ብሎን ሆቴል ከመግባታችሁ በፊት ጎንደር ከተማን አንዴ አዟዙሬ ላሳያችሁ በማለት ከተማዋን ሲያሳየን በመጀመርያ ወስዶ ያሳየን ፣ ዳሽን ቢራ ፋብሪካውን ነበር ፡፡ ይኽውላችሁ ይህ ፋብሪካ ሲሠራ አጥሩን የሚያጥር ግንበኛና ወዛደር የመጣው ልክ ቻይኖች የራሳቸውን ሰዎች እንደሚያመጡት ከትግራይ ነበር ፡፡ ጎንደር ባገሩ የቀን ሥራ እንኳ ተከልክሎ ከትግራይ ! እያለ ይቆጭ ጀመር ፡፡ ጭራሽ ስትዝናኑ ቡና ቤት ስትገቡ ዳሽን ቢራ እንዳትጠጡ ፡፡ ዳሽን ከጠጣችሁ የጎንደር ህዝብ የወያኔ ደጋፊዎች ናችሁ ብሎ ፣ ይጠረጥራችኋል ይለናል ፡፡ባለቤቴን ምንም አይነት አስተያየት እንዳትሰጥ ቆንጠጥ አድርጌያት ታክሲ ነጂውን መጠርጠር ያዝኩ ፡፡ አናግሮ አናጋሪ በሚል ፍራቻ ፡፡ ሆቴላችን አድርሶን የሚገኝበትን ስልክ ቁጥር ሰጥቶን ይሄዳል ፡፡

በማግስቱ በጠዋት ሆቴላችን ድረስ መጥቶ አዳራችን እንዴት እንደነበረ ይጠይቀናል ? ከፊታችን ላይ ደስታ እንዳልነበረን የተረዳው ታክሲ ነጂ አልነገርኳችሁም ?አልሰማ ብላችሁ እኮ ነው ይለናል ፡፡ በቂ እንቅልፍ እንዳልተኛን ሌሊቱን ሙሉ የትግርኛ ሙዚቃና ከበሮ ብቻ ሲዘፈን እንዳደረ እና እንደረበሸን ነገርነው ፡፡ ድሮስ ! አልሰማ ብላችሁኝ እኮ ነው ብሎ በወያኔ ላይ ያለውን ጥላቻ በግልጽ ነግሮን ወደ ኤርፖርት መልሶ አደረሰን ፡፡ በዚያች ምድር ወያኔ በሚሠራው የዘረኝነት መርዝ ምን ያህል የትግራይ ህዝብ እንደተጠላ ተረዳን ፡፡ ይህ ታክሲ ነጂ ፣ ሰሞኑን የአቶ በረከት ሰምኦን እናት በወታደራዊ ሠልፍና ማርሽ ጎንደር ጸጥ ብላ ሲቀበሩ ምን ተሰምቶት ይሆን ? በህይወት ካለ ፡፡

ባህር ዳር

ከጎንደር ባህርዳር ባደረግነው ቆይታ ብዙ ነገር ለመታዘብ ችያለሁ ፡፡ ቢያንስ ጎንደር ከተማዋ በነጻ ጋዜጦች ሽያጭ የማትታማ ፣ ሁሉኑም ጋዜጦች ማግኘት የሚቻልባት ፣ በአንጻራዊነትም የጎንደር ህዝብ በግልጽ ለወያኔ ያለውን ጥላቻ ከማሳየት የማይታቀብበት ከተማ ስትሆን ፣ የአማራው ክልል ዋና ከተማ የተባለው ባህርዳር ግን ዝም እርጭ ያለ፣ ምንም አይነት ነጻ ጋዜጣ የሚባል የማይታይበት ከተማ ነበር ፡፡ ባህርዳር ከተማ ውስጥ ያላየነውን የወያኔ ተቃውሞ ምልክቶች ማጣት ግን ጢስ አባይን ጎብኝተን በታንኳ ጎርጎራ የሚባለውን ጎንደርንና ጎጃምን የሚያውስነውን ወንዝ ለማየት ስንሄድ፣ የገጠመን አስደንጋጭ ንግግር ግን ይህች አገር ወዴት እንደምትሄድ የሚያሳይ ጠቋሚ አደጋ ነበረ ፡፡ ግፋ ቢል እድሜያቸው ከአስር እስከ አስራ ሁለት አመት የሚጠጋቸው ልጆች በአሽዋ ውስጥ የተቀበረ አንቧውሃ ይዘው ጋሽዬ ! ክኔ ግዙ ! ጋሽዬ ከኔ ግዙ፡! እያሉ ይሻማሉ ፡፡ ከሁሉም መግዛት ባንችልም እጃችን ወደ ወሰደን እና ቀደም ብሎ ከተማጸነን ካንደኛው  ልጅ ላይ ልንገዛ ስንል ! አንቱ ጋሽዬ ! ከሱ ልጅ አትግዙ ብለው ሁሉም ህጻናት ጮሁ ፡፡

ለምን እሱ ነው ከቅድም ጀምሮ ግዙኝ እያለ የለመነን አልኳቸው ፡፡ አይ ! የሱ አባት ትግሬ ስለሆነ አትግዙት ጋሽዬ አሉን አንድ ላይ በመጮህ ፡፡ ባለቤቴና እኔ ተያየን ፡፡ በአድማ እንዳይሸጥ የተጮኸበት ልጅ አንገቱን ደፋ ፡፡ አዘንን ፡፡ለማስተባበል ሞከረ በማዘን ፡፡ አይዞህ ምንም አይደል እንገዛሃለን አልነው ፡፡ የተሰበረ ልቡን ለመጠገን ስንል ፡፡ ይህ ልጅ መርጦ አልተወለደም ፡፡ የአቶ መለስ መንግሥት በዘራው የዘረኝነት መርዝ ይህ ጎንደርና ጎጃም ድንበር ላይ ጎርጎራ የተወለደው ልጅ የርሱ እኩዮች በሆኑ ልጆች ጥርስ ውስጥ ገብቷል ፡፡ ዘረኝነት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ እንኳን በአዋቂዎች በልጆች ውስጥም መዝምዞ እንደገባ ያሳየናል ፡፡ ዓለም ጸሃይ በግጥሟ እንዳለችው ፣

ጡጦዋን ላመጣ ከጓዳ ገብቼ

የወተቱን ሙቀት ስለካ ቆይቼ

በምንኛ ፍጥነት ከቅፌ ፈልቅቀህ ልጄን ውስድክ አሉት ? ማለት ይህ ነው ፡፡

ህወሃት በአማራው ህዝብ ላይ የጣለውን ዘር የማጥፋት ርምጃ ፣ እንዲያስፈጽሙለት ፣ የአማራውን ህዝብ በወልድ አግድ እንዲያስተዳድረው የመደበለት የአማርኛ ተናጋሪ የትግርኛ ክፍል ፣ የአማራውን ብሄር በቁጥር ከሁለት ሚልዮን ተኩል በላይ በህዝብ ቆጠራ ወቅት የት እንደደረሰ ጠፍቶ ባለበት ጊዜ እንኳ አለመጠየቁ ሲደንቀን ፣ አቶ መለስና የማፍያ ቡድናቸው ግን አየር በአየር ስለሸጡት ብዙ ሺህ ቶን ቡና ከፍተኛ ቦታ ተሰጥቶት ሲነገር ፣  አማራው ግን ከቁጥር ሳይገባ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ቡና ጠፋ ተብሎ ሪፖርት ሲደረግ፣ አማራ ግን ቁጥሩ ለምን እንዲቀንስ ተደረገ ብሎ የጠየቀ አካል አልነበረም ፡፡ ብአዴን የተባለው አማራውን በወልድ አገድ የያዘ የትግርኛ ተናጋሪ የአማራ ክፍል ከቤኒሻንጉልና ጉሙዝ ለተባረሩት አማሮች መብት ባይቆም የሚደንቀን ለምንድነው ?

አማራው አዲስ አበባ አካባቢ ከሌሎች ጎሳዎች በላይ በቁጥር በልጦ መታየቱ እንቅልፍ የነሳው ህወሃት፣ በዘዴና በኮንዶሚኒዬም ሰፈራ ዘዴ ጥንታዊውን ነዋሪ ከለመደው ቀዬ በማፈናቀል ፣ አንዱን ጉለሌ ፣ሌላውን ገርጂ በመበታተን እንዲሁም ጥንታዊዎቹን እድሮች በማፈራረስ ሰዉ ባይተዋር እንዲሆን በማድረግም ፋሽስታዊ አካሄዶችን ተግብሯል ፡፡ ብዙ ጊዜ እያጠቃን ያለው እና እንዳልዛይመር ህመም ሁሉን የመርሳት ችግር እየገጠመን ፣ በፎቅና መንገድ መሽቆጥቆጥ ጥንታዊው ነዋሪ የት ሰፈረ ? እድሮችስ የት ሰመጡ ? ብለን አለመጠየቃችን ፣ አራዳ ነኝ ለሚለው ወያኔ ! እኛ ወረዳ ሆነንለታል ፡፡ ወያኔ ብዙ የሚጫወትባቸውን ካርታዎች ገና ከእጁ አልጣለም፡፡ አሁንም አልዛይመር ካልያዘን የምርጫ 97 ን ምርጫ ወቅት አለመርሳት ነው ፡፡ ቅንጅት አዲስ አበባን አሸንፎ ዶክተር ብርሃኑ ከንቲባ ሆነ ሲባል ፣ አይንህን ከፊንፊኔ እንዳላየው ብሎ ናዝሬት ያባረረውን ኦህዴድን ወዲያው ከናዝሬት ጽህፈት ቤቱን አስነቅሎ ያስመጣውን መርሳት የለብንም ፡፡ ምን ግዜም በ 110 ካሬ ሜትር ቦታ እንደ ኤሳው በጭብጦ ምስር ቤት አለኝ ብሎ አንገቱን የሚደፋለት ዲያስፖራ ፣ ነገ ያንተ ክልል አይደለምና ውጣ ተብሎ እንደሚባረር አልገባውም ፡፡በተለይ ጥቁር ልብስና ወይባ የለበሱት እንዲሁም ዲያቆናት አስተማሪዎች ነን ብለው ከአዲስ አበባ ዋሽንግቶን ዲሲ በተጨማሪም አውሮፓ ለአገልግሎት ሲመጡ ከነሚስቶቻቸው የሚጋበዙት ሰባኪዎቻችን ፣ከሰማዩ ቤታቸው ይልቅ ወያኔ ለሚሰጣቸው 110 ካሬ ሜትር ቦታ ሲሉ ፥ ለሰማዩ ቤታቸው የመግቢያ ቪዛ ሳይሆን ፣ ወያኔ ለሚሰጣቸው የመግቢያ ቪዛ ሲሉ ፣ ተራው አማኝ የማያውቃቸውን አስፈሪ ጥቅሶች እየጠቀሱ ፣ ህዝቡን ፖለቲካ አትስማ በማለት እያስተኙ የሚያስጨፈጭፉንን ፈሪሳውያን ቀሳውስትና ዲያቆናት .. ህዝባችሁ ሲጋዝ ምነው ድምጻችሁ የት ጠፋ ? ካላልናቸው አብረው ከወያኔ ጋር እንደነገዱብን ይቀጥላሉ ፡፡

በውጭ ያለው አማኝ ይህ ሁሉ የአገሪቱ ዜጋ ሲፈናቀል ቤተክርስቲያኖቻችንን በተለይ ገለልተኛ ነን የሚሉትን ምነው የጸሎት ጊዜ አላወጃችሁም ብሎ መጠየቅ ይገባዋል ፡፡ ከአዲስ አበባ የውሃ መንገድ የሆነላቸውን ብልጣ ብልጥ ዲያቆናትን ከንግዲህ የአውሮፕላን ትኬት አንገዛም ፣ እዚያ አገራችን ያለውን የተፈናቀለ ህዝባችንን በጸሎትም ሆነ ከጎኑ ሆናችሁ አጽናኑ ማለት አለብን ፡፡ ቤተ ክህነት ውስጥ ሆነው ፣ ከስድስት ኪሎ አራት ኪሎ የተደረገውን አልሰማንም የሚሉ ጥቁር ለባሽ ጳጳሳትን እየሰማን ባለንበት አገር ቤንሻጉሉና ጉሙዝማ እጅግ ሩቅ ነው ፡፡  በብአዴን የተጠረነፉ ፈሪሳውያን ወንጌላውያንም ቢሆኑ አማራውን በወልድ አግድ በምድር ገዝተው ያሰሩት ጭምር ናቸው ፡፡

እግዚአብሄር የግፉሃንን እንባ ያብሳል !

ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር

 

 Zhabesha.com

ወያኔ በአማራ ተወላጆች ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንደቀጠለ ነው

ወያኔ ለአማራ ህዝብ፤ ባህልና ታሪክ ያለዉን ጥላቻ ከተራ ጥላቻ አልፎ በተግባር አማራዉን ወደ ማጥቃት ዘመቻ አደገ እንጂ ለአንድም ቀን ቀንሶ አያውቅም። አማራው እንደ ሰው ልጅ የመኖር መብቱ፣GINBOT 7 Movement ስብእናው ተገፎ ከቀየው፣ ከመንደሩ የአፈራውን ንብረትና ገንዘብ እየተቀማ መባረሩ፣ መሰደዱ፣ እንግልቱ ሁሉ የወያኔ የበቀል እርምጃ ነው።

በአሶሳ፤ በደኖና በአርባጉጉ ውስጥ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ህጻናት፤ሴቶችና አረጋዉያን በግፍ ተገድለዋል። ባለፈዉ አመት በደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጋር ተግባብተዉ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ብሄረሰብ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ለአመታት ያፈሩትን ንብረት ይዞ የመሄጃ ግዜ እንኳን ሳይሰጣቸዉ አከባቢዉን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለቅቀዉ እንዲወጡ እንዲፈናቀሉ ተደርጓል።

ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ ጀምሯል። በደቡቡ የአገራችን ክልል በጉራፈርዳ የጀመረዉን አማራውን ነጥሎ የማጥቃትና የማንገላታት ዘመቻ አሁን ደግሞ በሰሜን ምስራቅ የአገራችን ክፍል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀጥሏል።

የቅርብ ግዜው ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሜዳ ላይ ወድቀው የሚገኙት አማራ አርሶደአሮች የድረሱልን ጥሪ ማሰማታቸውና፤ ብሄረ አማራን እወክላለሁ ባዩ ብአዴን (የህወሃት ቡችላ) ጠበንጃ ደቅኖብን ወደ መጣችሁበት ተመለሱ ከዚህ ጥፉ ሲል አዋከበን፤ የወገን ያለህ ድረሱልን የት እንግባ ልጆቻችን የአውሬ ራት ሆኑ ሲሉ ስቃያቸውን አሰምተዋል። በርግጥ የህወሃት ተለጣፊው ብአዴን ሆዳቸው ስለሞላ ህሊናቸው ታውሮ ይህ በደል የሰው ልጅን የማጥፋት ሴራ መሆኑን እና በዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሚያስጠይቅ የተረዱ አይደሉም።

ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ አያሌ የአማራ ብሄረስብ ተወላጆች ያፈሩትን ንብረት ለመሰብሰብ እንኳን ግዜ ሳይሰጣቸዉ የኔ ብለው ከሚጠሩት የመኖሪያ ቦታቸዉ እንደባዳ እየተገፉ እንዲወጡ ሲደረጉ በአንጻሩ በባህርዳር ከተማ ብአዴን የቱባ ባለስልጣናቱን ከርስ ለመሙላት የክልሉን ህዝብ ጮኸት ጀሮ ዳባ ብሎ ሽርጉድ ሲል የነበረ መሆንን ያገናዘበ ኢትዮጵያዊ ቁጭት በርካታ ነው ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፡ እርግጥ ነው ይህን ዘረኛ ቡድን ለማስወገድ በሚደረገው መራራ ትግል ሂደት ውስጥ በደልና ሰቆቃው እየበዛ እንደሚሄድ ቢታወቅም ተባብረን ከታገልነው ግን ይህን ልናሳጥረው እንችላለን። አለበለዚያ ግን እስከ መቼ ነው ወገኖቻችን በትውልድ መንደራቸው የሀገር ውስጥ ጥገኛ ጠያቂ የሚሆኑት? የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ከቀያቸው የተባረሩት በኢትዮጵያዊ ዜግነታቸው ነው።

ግንቦት 7 ንቅናቄ ይህ የወያኔ ስርአት እስካልተወገደ ድረስ በአማራው የተጀመረው ጭፍጨፋ፣ እንግልት፣ ስደት፣ መከራና ግድያ፤ ህወሃት በሌሎችም አጠናክሮ ይቀጥልበታል ብሎ ያምናል። ስለዚህ ምን እንጠብቃለን በወያኔ ያልተበደለ፣ ያልታሰረ፣ ያልተደበደበ፣ ያልተሰደደ፣ ያልተፈናቀለ፣ ያልተራበ፣ ያልተዋረደ፣ ያልተገደለ ህዝብ የለም። የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ጨካኝ ስርአት አማካኝነት በጨለማ ሂዎት ውስጥ እየኖረ ነው።

የሀገራችን ወጣት ሆይ፡ ወጣትነት ሀገር ተረካቢ፣ ባላደራ፣ ለውጥ ፈላጊ፣ ሀገሩን ጠባቂ ነው። ወገንህ ሲገረፍ ሲንገላታ ሲሰደድ ማየት እና ከንፈር መምጠት እሰከ መቼ ይሆን? ሰቆቃቸው፣ ቁስላቸው የድረሱልን ዋይታቸው መቼ ይሆን ተሰምቶን እንባቸውን በአለንላችሁ የወገን ደራሽነት የምንደርስላቸው? የምንጠርግላቸው? ግንቦት 7 ትግሉን የማቀጣጠያ ሰአት ጊዜው አሁን ነው ይላል። ወጣት፣ አዋቂ፣ ጎልማሳ፣ ሽማግሌ፣ ዘር ጾታ ቋንቋ ሳይለየን ወያኔን ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ምላሽ ስጡ፣ ተቀላቀሉ። በኢትዮጵያ የጠቆረውን ጨለማ በብርሃን መተኪያ ጊዜ ዛሬ ነው። ይህ ትውልድ የታሪክ ባለእዳ አይሁን።

በወያኔ ውስጥ ያላችሁ ይህ በደል ና ሰቆቃ የሚሰማችሁ ወገኖቻችን የውስጥ አርበኛ የምትሆኑበት ሰአት ላይ ናችሁ። ራሳችሁን እና ወገናችሁን ከቀን ጅብ ስርአት አድኑ። ከነጻነት ማግስት በኋላ ከሚመጣባችሁ ከየት ነበራችሁ ክስ ለመጽዳት ከነጻነት ታጋዮች ጋር አብሩ። ወያኔ ለ21 አመታት ህዝቡን ለማጋጨትና ለማባላት የሚያደርገው ስልት መሆኑን ተረድታችሁ የውስጥ ታጋዮች መሆናችሁን ማሳያ ጊዜው አሁን ነው። አሊያ ግን በአማራው ህዝብና በሌላው ማህበረሰብ ላይ እየተፈጸመ ባለው እጅግ አስከፊ ወንጀል በግልም ሆነ በቡድን፣ የንጹሀንን ደም እያፈሰሳችሁ ያላችሁ ወንጀለኞችና ተባባሪዎች ተብላችሁ፣ ከያላችሁበት ታድናችሁ ለፍርድ እንድትቀርቡ ንቅናቂያችን የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት በግልጽ እንድታውቁት ይገባል።

የሀገራችን ህዝብ ሆይ፡ ዛሬ ኢትዮጵያን ከገባችበት ዘረኛ መቀመቅ ስርአት ውስጥ የሚያወጣት ብቸኛ መፍትሄ፣ ፍርሃታችንን በጥሰን በተባበረ ጉልበትና ድፍረት ወያኔን በሚገባው ቋንቋ ስናናግረው፣ ታግለን ስናስወግደው ብቻ ነው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ክብርን፣ ተሳስቦና ተፈቃቅሮ፣ ተከባብሮና ተቻችሎ የመኖር ጸጋን የምናመጣው። ስለሆነም በየትኛውም አቅጣጫ የሚደረገውን የነጻነት ጉዞ ትግል ትቀላቀሉ ዘንድ ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪውን በድጋሜ ያቀርባል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

 

 ECADF.Com

ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ

የአሜሪካዊው አስከሬንና አሟሟት ሊመረመር ነው

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (http://www.goolgule.com/)

የመከላከያ ሰራዊት በድንገተኛ ከበባ ከገደላቸው ንጹሃን ዜጎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን የአቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የሰራዊቱ አባላት አስከሬን አደባባይ በማውጣት ለህዝብ እያሳዩ ደስታቸውን ሲገልጹ የተመለከቱ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ክፉኛ መበሳጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በጋምቤላ የደረቁን ወቅት ወይም በጋውን በወንዞች ዳር ውሃ ተንተርሶ መኖር የተለመደ ነው። ከቋሚ የመኖሪያ ቀዬ ወደ ወንዝ ዳርቻ በመሄድ አድኖ መመገብና አሳ አስግሮ ዕለትን ማሳለፍ የባህል ያህል ነው። በአገሬው ልምድ መሰረት ከቋሚ መኖሪያቸው ወደ ውሃ ዳር የሚሄዱት ወንዶች ሲሆኑ ጉዞውም የሚደረገው በቡድን ነው።Gambella

በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ክልል የጎክዲፓች ነዋሪዎች የደረቁን ወቅት ለማሳለፍ በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን ያመራሉ። በቡድን ወደ አብሌን ያመሩት ሰዎች ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባቸው። ተኩስ ተከፈተ። ለጊዜው ስድስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና የቆሰሉ እንዳሉ ለተጎጂዎቹ ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ።

ሰዎቹ ከጋምቤላ ከተማ 120 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አብሌን ተቀምጠው ኑሯቸውን እየገፉ ሳለ በድንገት የተከበቡት በጥቆማ እንደሆነ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። “አቶ ኡሞት ኡዶል እና ሌሎች መሳሪያ የታጠቁ አብሌን ታይተዋል” የሚል ጥቆማ የደረሰው ኢህአዴግ፤ ሰራዊቱን ሰዎቹ በቋሚነት ወደሚኖሩበት ጎክዲፓች በመላክ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ፣ በማሰርና፣ በመግረፍ ሰዎቹ ያሉበትን ቦታ እንዲያሳዩ አስገደዱ።

አቶ ኡሞት በዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ የነበሩ ሲሆን የአሜሪካ ዜግነትም አላቸው። ኢህአዴግ ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ በክልሉ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ አጥብቀው በግልጽ የሚቃወሙ ሰው መሆናቸውን የሚያውቋቸው ይናገራሉ። አቶ ኡሞት ከመሬት ነጠቃ ጋር በተያያዘ ህዝብን የሚያስተባብሩና ለዓመጽ የሚያነሳሱ ናቸው በሚል ኢህአዴግ ቢወነጅላቸውም ውንጀላውን በማስረጃ ማቅረብ እንደማይችል እነዚሁ ክፍሎች ይገልጻሉ። ስለተፈጸመው ግፍ የተሞላበት ግድያና ከግድያው በኋላ ስለተከናወነው “አረመኔያዊ የእንስሳ ተግባር” ሲያስረዱ በቁጣ ነው።

በተጠቀሰው ቀን ቤተሰቦቻቸውን ቀበሌያቸው ድረስ በመሄድ በመግረፍና በማስፈራራት ወደ አብሌን ለከበባ በጠቋሚ የመጡት የመከላከያ አባላት ሰዎቹን እንደተመለከቱ ተኩስ ከፈቱ። በድንገት የተከበቡትና ዛፍ ሥር ተቀምጠው የነበሩት አንዳችም ጥያቄ ሳይቀርብላቸው በጥይት የተደበደቡት ሰዎች የአልሞት ባይ ተጋዳይ ትግል ቢያደርጉም አልሆነም። ተደራጅቶ በሶስት የወታደር ካሚዮን ከባድ መሳሪያ ታጥቆ የመጣው ሰራዊት ጨፈጨፋቸው። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እንደተናገሩት ወዲያው ህይወታቸው ካለፈው ስድስት ንጹሃን መካከል አቶ ኡሞት መሞታቸው ሲታወቅ የሰራዊቱ አባላት አውካኩ፤ በደስታ ጨፈሩ። አስከሬኑንን ጭነው ፉኙዶ ወደሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ በመሄድ ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ደስታቸውን አበሰሩ።

አስከሬን በመኪና በመጫን ከተማ እየዞሩ ደስታቸውን ገለጹ። በማግስቱ በጋምቤላ ከተማ ስታዲየም አስከሬኑን ህዝብ እንዲመለከተው ታዘዘ። ህዝብ ስታዲየም ተገኝቶ የአቶ ኡሞትን አስከሬን እንዲሳለም፣ ኢንቨስተሮችም ያለስጋት የመሬት ነጠቃቸውንና “ልማታቸውን እንዲቀጥሉ”፣ መሞታቸውን አይቶ ሕዝቡ እንዲያምንና ሞራሉ እንዲጎዳ የተላለፈው ውሳኔ ባልተጠበቀ ሁኔታ ተስተጓጎለ። ለጎልጉል መረጃውን ያስተላለፉ እንዳሉት አቶ ኡሞት አሜሪካዊ መሆናቸው ሲታወቅ ማዕከላዊ መንግስት ከአዲስ አበባ አስቸኳይ ትዕዛዝ አስተላለፈ። አስከሬኑን ባስቸኳይ እንዲቀብሩ መመሪያ ሰጡ። ሁሉም ነገር በመመሪያው መሰረት ተጠናቀቀ። የአቶ ኡሞት አስከሬን ባልታወቀ ቦታ ተቀበረ። አስከሬኑንን ለማየት በግዳጅ ተሰባሰበው ህዝብም ምንም ነገር ሳይመለከት ወደ ቤቱ ተመለሰ። ሁኔታውን ተከትሎ በተፈጠረ አለመረጋጋት የኢህአዴግ ሠራዊት በጎክ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የጋምቤላ ተወላጆች በተለይም ወንዶችን እያሠሩና እያሰቃዩ እንደሆነ ከሥፍራው የደረሰን ዜና ያረጋግጣል፡፡

የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት ጉዳዩን ለአሜሪካ መንግስት እንዳሳወቀና የአሜሪካ መንግስት ጉዳዩን ከስር መሰረቱ ጀምሮ እንደሚመረምረውና እስከ መጨረሻው የመንግሥት አካል እንደሚደርሱ ማረጋገጡ ታውቋል። ኢህአዴግ አቶ ኡሞትን የገደለበትን ምክንያት በማስረጃ ማቅረብ እንደሚጠበቅበትም አስታውቀዋል። አቶ ኡሞት የሚጠረጠሩበት ድርጊት እንኳን ቢኖር በቁጥጥር ስር አውሎ በህግ መጠየቅ እየተቻለ እንዲገደሉ መደረጋቸው ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ የሚከራከሩላቸውና ጉዳያቸውን ይፋ ያደረጉት ክፍሎች ይናገራሉ።

በወቅቱ ህይወታቸው ያለፈው ንጹሃንና የደረሱበት ያልታወቀው ሰዎች ስም ዝርዝር ከስፍራው የደረሰን ሲሆን እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

 1. ጎጎ ኦቻላ
 2. ቻም ኦቻላ
 3. ዑከች አቻው
 4. አኳይ ኦሞት
 5. ኦሞት ኦባንግ
 6. አጂባ አኳይ
 7. ኦሞት ኡጁሉ ኦጎታ
 8. አንበሳው ኡጁሉ
 9. ቱወል ኦሎክ
 10. ኦችዋል ኦባንግ
 11. ኦዋር ቻም
 12. ኒሙሉ አጎሌ
 13. አብራች ኒሙሉ
 14. አኩኔ ኦሞት
 15. አግዋ ቻም
 16. ኦዋር ኒግዎ አጋክ
 17. ኦሞት ኡዶል (አሜሪካዊው)                          Ecadf.com

የህወሃት መሪዎች “የኢትዮጵያ ታሪክ እንደገና መፃፍ አለበት!” ይላሉ:: ለምን?

ገብረመድህን አርአያ

Click here for PDF

ህወሃት ከጥንሥሱ ጀምሮ እንደተልዕኮ እና መመሪያው ለዘመናት ከብዙ የውጭ ወረራዎች እና ያልተሳኩ የቅኝ ግዛት ጥረቶች በአባቶቻችን ጽኑ ተጋድሎ የቆየውን ኢትዮጵያዊነት ለማፍረስ ፤ ህዝብን በአለም ታይቶ በማይታወቅ የቋንቋ እና የዘር ልዩነት ከፋፍሎ ለብቻው የትግራይን ሪፖብሊክ ለማቋቋም ፤ ኤርትራን መገንጠል ፤ ትግራይን ከአማራ ቅኝ ገዢዎች ነጻ ማውጣት ፤ ኢትዮጵያ የምትባል በአጼ ምኒሊክ የተፈጠረችን አገር ከአለም ካርታ ላይ ማጥፋት ፤ የሚሉ እና ሌሎች ዝርዝር ግቦችን እና አላማዎችን አንግቦ የተነሳ ድርጅት እንደነበር ባለፉት በርካታ አመታት እኔ በግሌ ስገልጽ እና ሳስረዳ ህወሃትም አንዳንድ ጊዜ በግልጽ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በግብር ይህንን እኩይ ምግባሩን ሲያሳየን ቆይቷል:: ይኸው ኢትዮጵያዊነትን ከፊት በመሆን ከውጪ ወራሪዎች በጽናት ተጋድሎ አቆይቷል ብሎ የሚወነጅለውን የአማራ ብሄርን የተመቸው ሲመስለው ከ1971 አንስቶ  በቀጥታ በሰሜን ጎንደር በወልቃይት ፣ በጠገዴ ፣ በጸለምት እንዲሁም በሚቆጣጠራቸው የትግራይ ቦታዎች እንዳደረገው በዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ፤ ሳይመቸው ሲቀር ደግሞ በተላላኪዎቹ አማካይነት በጉራ ፈርዳ እንዳደረገው ከአካባቢው አማራን የማጽዳት ስራ ሲያደርግ ይኸው ብዙ አመታት ተቆጠሩ::

ወያኔ ህወሃት የደርግ ስርዓት መዳከምን ጨምሮ ከሌሎች ጉዳዮች መገጣጠም ጋር ተያይዞ በተፈጠረለት እጅግ አሳዛኝ ታሪካዊ ኹነቶች ታግዞ በ1983 ዓ.ም. አዲስ አበባን

Gebremedhin Araya former TPLF

አቶ ገብረመድህን እርአያ

ሊቆጣጠር ቻለ:: በደደቢት ተቀፍቅፎ በሽምቅ ጥቃት የሚቆጣጠረውን ግዛት በተለያየ ጊዜ እያሰፋ የመጣው ህወሃት በገባባቸው እና አንድ ፣ አንድ ጊዜም ተቆጣጥሮ በሚቆይባቸው ቦታዎች በዋናነት ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የመንግስትን ካዝና ማራገፍ እና መዝረፍ ነበር:: የዚህ ዘረፋ ዋና አስተባባሪ እና ተቆጣጣሪም ስብሓት ነጋ ነበር:: ከስብሓት ጋርም ዘረፋውን ያቀናጁ የነበሩት አርከበ እቁባይ ፣ አባይ ፀሃየ እና ሟቹ ክንፈ ገብረመድህን የነበሩ ሲሆን ፤ ዘረፋውን ከላይ ሆኖ በስብሓት በኩል ያዝ እና ይቆጣጠር የነበረው ደግሞ መለስ ዜናዊ እንደነበር በበረሃ በነበርኩበት ወቅት በተለያዩ አጋጣሚዎች የማየት እና በቅርበት የመታዘብ የታሪክ አጋጣሚ ነበረኝ:: ህወሃት በወርሃ ግንቦት 1983 ዓ.ም. አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ ወታደራዊ ቁጥጥር እና የማረጋጋት ስራን ከመስራት ጎን ለጎን በገንዝብ ሚኒስቴር ጠቅላይ ግምጃ ቤት ፣ በንግድ ባንክ እና በብሄራዊ ባንክ  የነበረውን ገንዘብ በጠቅላላው በማጋዝ በሚኒሊክ ቤተመንግስት አስቀመጠ:: እንደወርቅ ያሉ በአይነት የተቀመጡ እና በገንዘብ ሊተመን የማይችል እጅግ ብዙ ዋጋ ሊያወጡ የሚችሉ ቅርሳ ቅርሶችንም ሰብስቦ በዚሁ በቤተመንግስት በጊዜያዊነት ባሰናዳው የዘረፋ ጣቢያ ላይ አከማቸ:: ከማዕከላዊው ባንክ ግምጃ ቤት ተጭኖ ወደዚሁ የዘረፋ ማከማቻ የተወሰደው ወደ 800 ኪ.ግ. የሚመዝን ወርቅ የዘረፋውን ትልቅነት እንደማሳያ ሊጠቀስ የሚችል ነው:: በግንቦት መጨረሻ ሳምንት አዲስ አበባን ተቆጣጥረው ለቀጣይ ሁለት ወራት የተደራጀ እና ከፍተኛ የዘረፋ ስራ ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ በቤተመንግስት ያስቀመጡትን እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብን ጨምሮ በአይነት የተደለደሉ እጅግ ብዙ ብር የሚያውጡ ብርቅ መአድናት እና ቅርሳቅሶችን በአውሮፕላን እና በመኪና በመጫን ወደ ትግራይ አጓጓዙ:: እንግዲህ ለድርቅ የተመደበ እርጥባንን ከደሃ ጉሮሮ በማህበረ ረድኤት ትግራይ — ማረት በኩል በመንጠቅ እና በተከታታይም የህወሃት ጦር በገባበት ከተማ እንደዚህ በተደራጀ የዘረፋ ስራ የአገር እና የመንግስትን ግምጃ ቤት በማራቆት በተገኘ ገንዘብ ነው በ እንግሊዘኛው ምጽአረ ቃል ኢፈርት(EFFORT) በትግሪኛ ደግሞ  ት.እ.ም.ት. ወይም ትካል እግሪ ምትኻል ትግራይን  ለቀጣይ የተደራጀ ዘረፋ እና የኢኮኖሚ የበላይነት ያቋቋሙት::

ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ የተቋቋሙት መሰቦ ሲሚንቶ ፣ አልመዳ ጨረቃጨርቅ ፣ መስፍን ኢንጂነሪንግ ፣ ሱር ኮንስትራክሽን ፣ አዲስ መድሃኒት ፋብሪካ ፣ ኢዛና ማይኒንግ ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ አፍሪካ ኢንሹራንስ ፣ ወጋገን ባንክ ጨምሮ እስከ ቱሪስት አስጎብኚ እና መጽሃፍ ችርቻሮ የደረሰ የንግድ እና የዘረፋ መዋቅር የተዘረጋው በጠራራ ጸሃይ በተደረገ ዘረፋ እና ኋላ ላይ ያለ ማስያዣ ከሃገሪቱ የመንግስት ባንኮች በብድር ስም በሚወጣ ገንዘብ እንደመሆኑ እነኚህ ኩባንያዎች የሁሉም ኢትዮጵያውያን ንብረቶች መሆናቸው በፍጹም ሊዘነጋ የማይገባው ሃቅ ነው:: ለነገሩ እነ ስብሓት ነጋ በተለይ በረሃ በነበሩበት ወቅት የተለያዩ ከተማዎችን ወርረው ሲቆጣጠሩ ይዘርፉ እና ያዘርፉ የነበረው የመንግስትን ንብረት ብቻም አልነበረም:: መጠኑ ይነስ እንጂ ድርጅቱ መሰሪ የሆነ አላማዬን አይደግፉም ፣ ኢትዮጵያዊ አገር ወዳድነት አላቸው ፣ በኤርትራ ጥያቄ ላይ ከህወሃት ሃሳብ ጋር አይስማሙም ብለው የመደቧቸውን ንጹሃን ዜጎችን የተለያየ ስም በመስጠት እና በመወንጀል በሃለዋ ወያኔ(ስውር እስር ቤቶች) በመወርወር ንብረታቸውን ይወርሱ ነበር:: እነኚህ ዜጎች መጨረሻቸው በተለያዩ ጊዜያት ከነኚህ እስር ቤቶች ውስጥ በመውጣት መረሸን ነበር:: ስብሓት ነጋ በተለያዩ አጋጣሚዎች ኢፈርት በኢትዮጵያ ሃብታሙ ድርጅት እንደሆነ እና ህወሃትም ያለ ምንም ማፈር ‘ኢፈርት መር ኢኮኖሚ’ እየገነባ እንደሆነ ነግሮናል:: በተለያየ ጊዜ በዘረፋ የሰበሰቡት እና ያከማቹት ሃብት መጠን ምን ያህል እንደሆነ አስበውት ይሁን አዳልጧቸው ከሚነግሩን ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ ሊል ይገባል::

እነሆ ላለፉት 22 አመታት ማዕከላዊ መንግስቱን ተቆጣጥሮ ያለው ይህ የአጥፊ ወሮበሎች ቡድን በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ሲፈጠር ጀምሮ አጠንጥኖ የመጣውን የጥፋት ተልዕኮ ለማስፈጸም ሲሰራ ሲመቸው በይፋ በህዝብ መገናኛ ብዙሃን ትዕቢት በተቀላቀለው ድንፋታ ሳይመቸው ሲቀር ደግሞ በተጠማዘዘ እና ግራ በገባው የፖለቲካ ፍልስፍና በማደንዘዝ እና ግራ በማጋባት ሲሰራ ኖሯል:: ዛሬ ፣ ዛሬ ደግሞ በበረሃ ጀምሮ በተጋነነ ፣ ተጠምዝዞ በተተረጎመ እና አንድ ፣ አንድ ጊዜም ከሜዳ ተጠፍጥፎ በተሰራ የሃሰት እና ክህደት ሸፍጥ ሲያጠቁት እና ሲያንኳስሱ የኖሩትን የኢትዮጵያ ታሪክ እንደ አዲስ እንጽፋለን ብለው በስብሓት ነጋ በኩል በይፋ ማወጅ ጀምረዋል:: የህወሃት መሪዎች አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ብቻ ሳይሆኑ በ1993ቱ ክፍፍል ከስልጣን የተባረሩትም ጭምር በተለያዩ ጊዜያት ይህን በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ያደባ የታሪክ ክለሳ እና እንደ አዲስ የመጻፍ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ሃሳባቸውን መስጠት ብቻ ሳይሆን ዋና አቀንቃኝም ሆነው ሰብከዋል:: እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ያቺ አገር እና በወቅቱ የነበሩ መንግስታት ብዙ አፍሪካዊያን በጭለማ በሚኖሩበት ዘመን እንደ ዜጋ በሰጧቸው በጎ እድል ተምረው ሰው መሆን የቻሉ የትግራይ ምሁራን ፍጹም ምሁራዊ እና የዜግነት ሃላፊነታቸውን በወያኔያዊ ዘረኝነት እና ሆዳቸው ለውጠው የዚሁ እኩይ ምግባር አይዞህ ባይ ፣ ምሁራዊ ድጋፍ ሰጪ እና አንዳንድ ጊዜም ፊታውራሪ ሆነው መገኛታቸው ነው:: ከሃገር ውጪ ሆነው አንዳንዶቹም ሃገር ቤት ገብተው ለዚህ እኩይ አላማ ከተሰለፉ ምሁር ተብዬ ዜጎች ውስጥ ዶ/ር ገብሩ ታረቀ ፣ ዶ/ር ሰለሞን እንቋይ ፣ ዶ/ር አሳየኸኝ ደስታ ፣ ጎርፉ ገብረመድህን ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኪሮስ ፣ ዶ/ር ክንደያ ገ/ሂወት ናቸው:: ዛሬ ፣ ዛሬ ካሸነፈ ጋር ያደሩ መስሎዋቸው ህሊናቸውን ሸጠው በክህደት ቢኖሩም ነገሮች ዞር ያሉ ለት ለትውልድም ሆነ ለህሊናቸው ምን መልስ ሊሰጡ እንደሚችሉ ያሰቡበትም አይመስልም::

የኢትዮጵያ ታሪክ ፍጹም ጥልቀት ያለው እና በአመዛኙ እምብዛም መከራከሪያ ሳይቀርብበት በግልጽ ባሉና በጽሁፍ ተመዝግበው በተቀመጡ ድራሳናት ፣ ቅርሳ ቅርሶች ፣ እና መዛግብት አስረጂነት ሊጠና የሚችል እና እስካሁንም በተለይ በውጪ የታሪክ አጥኚዎች በመጽህፋ መልክ በብዛት የተጻፈበት ነው:: ይህንን ታሪክ አጣሞ ለመተርጎም እና እነ ስብሓት ነጋ እንደሚሉት እንደ አዲስ ለመጻፍ መነሳት መሞከር ሊሳካ የማይችል ነገር ግን ብዙ ጉዳት ሊያመጣ የሚችል የመጨረሻው የጥቃት ሙከራ ነው::

በታሪክ ኹነቶች ላይ  በታሪክ ምሁራን በኩል ደረጃውን የጠበቀ እና ጥብቅ የሆኑ ሳይንሳዊ መንገዶችን በመከተል የትርጓሜ ክርክር ማንሳት ይቻላል:: የተከሰቱ የታሪክ እውነታዎችን በመካድ ታሪክን እንደፖለቲካ ማጥቂያ መሳሪያነት ለመጠቀም መሞከር ግን እጅግ ከፍተኛ መዘዝ አለው:: መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ መቶ አመት ነው ብሎ በይፋ በተናገረ ጥቂት አመታት ውስጥ ኢትዮጵያውያን በይፋ በምርጫ ካርዳቸው የሱን ዘረኛነት አንፈልግም ወግድ ባሉት የምርጫ 97 ማግስት አይኑን በጨው አጥቦ ኑና ሚሊኒየም እናክብር ያለው ክስተት መቼም የሚረሳ አይደለም:: የኢትዮጵያ ታሪክ የሶስት ሺህ አመት ታሪክ ነው ሲባል ዝም ብሎ በአፈታሪክ ወይም በዘልማድ የሚነገር ነገር ሆኖ አይደለም:: የግዛት ስፋቱ ይጥበብም ይስፋ የአገራችን ታሪክ 3000 አመት ለመሆኑ የሚያሳዩ የተለያዩ ማስረጃዎች በመኖራቸው ነው:: ይህንን ሃቅ ለመካድ መነሳት እንደነ መለስ እና ስብሓት እኩይ አላማ አርግዞ የመጣ ቡድን ወይንም ጭልጥ ብሎ አእምሮውን የሳተ ሰው መሆን አለበት:: በውጭ አገራት በፖርቹጋል ፣ ግብጽ ፣ እስራኤል ፣ ጣልያን ፣ እንግሊዝ ፣ ጀርመን ፣ እና ስፔይንን ጨምሮ በብዙ አገራት የአገራችንን የተለያዩ ዘመናት ታሪክ ሊያሳዩ እና ሊይስረዱ የሚችሉ የታሪክ መዛግብት እና ማስረጃዎች ይገኛሉ::

ዛሬ ፣ ዛሬ የኢትዮጵያ ማዕከሉን በዘር እና በሃይማኖት ከፋፍሎ ከመታ እና ካዳከመ በኋላ በዝርዝር ሌሎችን የህብረተሰብ ክፍሎች ወደማጥቃት በስፋት ተሰማርቷል:: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ፓትርያርክ አንስቶ ሌላ መሰየም:: የተሰየሙትም በእግዚያብሄር ቁጣ ሲወሰዱ ሌላ ለመሾም ድራማ መስራት ፣ ኢትዮጵያዊ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን የእምነት ትምህርት በካድሬዎች ለመጻፍ መሞከር አማኒያኑም እምቢ ሲሉም መግደል ፣ ማሰር እና ማንገላታት የዚሁ ታሪክን የማበላሸት እና እንደ አዲስ የመጻፍ ዘመቻ መገለጫ ኹነቶች ናቸው:: ዛሬ ላይ በዋልድባ ገዳማት ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ዝም ብሎ በአጋጣሚ የተከሰተ አይደለም ይልቁንስ ቀደም ብሎ ታቅዶበት በሂደት እየተተገበረ ያለው ታሪክን የማጥፋት እና የመደለዝ ዘመቻው አካል እንጂ::

ወያኔ ታሪክን ልክ እንደ አዲስ ከዜሮ ከሃዲው መለስ እና ሌሎች የወያኔ ጀሌዎችን ጀግና ነገር ግን ስለ እውነት እና ነጻነት ሲሉ የተዋደቁ እና የተሰዉ ሰማእት አባቶቻችንን ደግሞ ፈሪ እና ከሃዲ አድርጎ የመጻፍ ዘመቻውን ወያኔ ከሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን እና አሁን አሁን በብዛት እየተጻፉ ከሚወጡ እርባና ቢስ መጻህፍት መረዳት ይቻላል::

ወያኔ በኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰብ መብት አምጥቼያለሁ ይለናል:: ውሸት! የሆነው እና እየሆነ ያለው አገሪቷን በዘር ከፋፍሎ ሲያበቃ እነኚሁ መብት አምጥቼላችኋለሁ የሚላቸው ብሄሮች የዘር ማጥፋት ዘመቻውን እያካሄደባቸው ይገኛል::

ወያኔ ግዙፉን የደርግ ሰራዊት ደምስሼ ኢትዮጵያን ነጻ አውጥቻለሁ ይለናል::ቅጥፈት!! የሆነው እና እውነታው ሌላ ነው:: ትክክለኛ የታሪክ ተንታኝ ከአንድ ብሄር በተውጣጣ እና በአብዛኛው ዜጎችን የማይወክል ይልቁንም ታሪካቸውን የሚሰድብ እና የሚያንቋሽሽ ፖለቲካ ይዞ በመጣ የመርዘኞች ቡድን የኢትዮጵያ ጦር ተሸነፈ ብሎ መቀበል ፍጹም ስህተት ይሆናል:: ለኢትዮጵያ ጦር መሸነፍ በወቅቱ የነበረው የከሰረ የኮሚኒስት ስርዓት መላሸቅ እና የፖለቲካ ስርዓቱ ከቀዝቃዛው ጦርነት መዳከም ጋር ተባብሮ የእዝ ሰንሰለቱ በመላላቱ ያስከተለው የመዋጋት መንፈስ መቀዝቀዝ አይነተኛ እና ወሳኙን ሚና ተጫውቷል:: አንዳንዶች በወቅቱ በወያኔ መሪዎች የተሰጠውን ቃል አምነው ለጊዜውም ቢሆን እስቲ እንያቸው በሚል ካሳደሩት ዛሬ ላይ እንደ ታላቅ ስህተት ሊቆጠር የሚችል የፖለቲካ ስሌት ስህተት በቀር ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ወያኔን መጣብን እንጂ መጣልን ብሎትም አያውቅ::

ሌላው የወያኔ አይን ያወጣ የታሪክ ሽምጠጣ አንድ አንዶች ህገ አራዊት ብለው የሚጠሩት እና ሟቹ እኩይ መለስ ዜናዊ እንደ ማወናበጃ የሚጠቀምበት ህገመንግስት ነው:: ወያኔ ሲዘብት ለኢትዮጵያ ህዝብ አስደናቂ እና ነጻነቱን ያጎናጸፈ ህገመንግስት አመጣን ይለናል:: ሓሰት!! ህገ መንግስቱ በውስጥ ከያዛቸው አንቀጾች በመለስ አላማው ምን እንደሆነ እነሆ ከረቀቀበት የዘጠናዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ምን ማለት እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ እየኖረበት አይቶታል እና ዝርዝር ማብራሪያ ውስጥ መግባት አያሻኝም::

ሲመጻደቅ ደግሞ ኢትዮጵያን ከመበታተን አዳናት ይለናል:: ክህደት!! ስብሓት ነጋ ሲያዳልጠው ኢትዮጵያን አፍርሰን እንደ አዲስ እየሰራናት ነው ይልና ማን አፍራሽ እና በታኝ እንደሆነ ሳያውቀው ይነግረናል:: ወያኔ እንዳሰበው ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ ጽናት እና እምነት አገራችን እስካሁን በአንድነት ቆይታለች:: ይብላኝላቸው ለእነሱ እንጂ ከወያኔ ውድቀት እና ሞት በኋላም አንድነቷን ጠብቃ ትቀጥላለች::

ሲላቸው ደግሞ የአክሱም ታሪክ የጥቂት የትግራይ አካባቢዎች ታሪክ ነው ይሉናል:: ሙሉውን ትግራይ እንኳን አያጠቃልልም ሲሉም በድፍረት ይነግሩናል::ጉድ ነው!! ምን አይነት ማህጸን ይሆን እንደዚህ አይነት ከሃዲዎችን የወለደች?? በአንድ አገር ታሪክ ውስጥ አይነቱ ይለያይ እንጂ በታሪክ አጋጣሚ አሁን በማሊ እንደምናያቸው እና እንደአፍጋኒስታኑ ታሊባን አይነት ከተጠማዘዘ የሃይማኖት ፍልስፍና ተነስተው አገራዊ ጥፋት የሚያደርሱ ቡድኖች ስልጣን ሊይዙ ይችላሉ:: እንደ ወያኔ አይነት ግን ከአንድ አካባቢ ተቧድነው መጥተው በዚህ የመረጃ እና የእውቀት ዘመን ለክህደት እና ለጥፋት የሚተጉ ቡድን ግን አንብቤም  ሆነ ሰምቼ አላውቅም:: የአክሱም ታሪክ የመላው ኢትዮጵያውያን ታሪክ ነው:: እንደዘመኑ እና ጊዜው የተፈጸሙ ታሪኮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሁሉንም የአካባቢውን ማህበረሰቦች መንካታቸው እስካልቀረ ድረስ ታሪኩ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሊኮሩበት ሊወያዩበት እና ሊማሩበት የሚገባ የጋራ ታሪክ ነው::

ህዝባዊ ወያነ በኢትዮጵያ ላይ ያደረሰው ጥቃት እንደ ዮዲት ጉዲት እና አህመድ ግራኝ በአጭር ጊዜ ባይሆንም ላለፉት አርባ አመታት ገደማ ከበረሃ ጀምሮ በኢትዮጵያዊነት ስነ ልቦና እና ቅርስ ላይ ያደረገውን ጥቃት ስናይ ሁለቱ ካደረሱት መጠነ ሰፊ ጥቃት ጉዳቱ ይበልጥ እንጂ አያንስም::

የህወሃት ጥንሥሥ የጀመረው በ1964 በቀ.ኃ.ሥ ዩኒቨርሲቲ በሻዕቢያ “ጥሩምቡሌነት” (“ጥሩምቡሌ” ማለት በቀድሞ አነጋገር በገንዘብ የተገዛ ቅጥረኛ ባንዳ እንደ ማለት ነው::) በተሰባሰቡ የትግራይ ዘረኞች ነበር:: ሻዕቢያ ለራሱ እኩይ ተልዕኮ ማስፈጸሚያ ይረዳው ዘንድ ጥቂት ዘረኞችን ሰብስቦ ገንዘብ ፈሰስ በማድረግ ማህበረ ገስገስቲ ብሄረ ትግራይን ፈጠረ::  የድርጅቱን ከጥንስሡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት መነሳት የኔን ምስክርነት ማንበቡ ብቻ በቂ አይሆንም:: በአንድ አንድ ድረ ገጾች ላይ እና በኢንተርኔት በቀላሉ ሊገኝ የሚችለውን የድርጅቱን የ1968 ፕሮግራም ማየቱ ብቻ በቂ ነው::

ህወሃት በቀላሉ ሊደልዛቸው እና ሊያጠፋቸው የማይችላቸውን ከፍተኛ የአገር ክህደት እና የጅምላ ግድያ ወንጀሎችን የግል መዛግብቶቼን አመሳክሬ እዘረዝራለሁኝ:: አንባቢያን ዝርዝሩ ያለቅደም ተከተል መቀመጡን ልብ ይበሉ፤

1. ገና ከመመስረቱ ብዙም እድሜ ሳያስቆጥር በ1968 ንጹሃን የትግራይ ልጆችን ሲለው ኢዲዩ ሲያሰኘው ደግሞ በኢህአፓ እና በደርግነት እየወነጀለ በጅምላ ፈጃቸው:: አባወራ እና እማወራዎችን በመግደል ብቻም አላበቃም:: የብዙሃንንም ንብረት በመውረስ ቀሪ ቤተሰባቸውንም ጭምር ነው አይቀጡ ቅጣት የቀጣው:: ብዙሃን ህጻናትንም ያለወላጅ ፤አረጋዊያንንም ያለጧሪ እና ቀባሪ አስቀራቸው:: ይህ በትግራይ በስፋት የሚታወቅ ሃቅ በመሆኑ በዘመኑ የወያነ ጉጅሌ ጦር ይንቀሳቀስ በነበረባቸው ቦታዎች ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን በመጠየቅ ማንም ሊረዳው የሚችለው ሃቅ ነው::

2. በወርሃ ህዳር 1969 ዓ.ም. ከህወሃት አመራር ተወክለው መለስ ዜናዊ እና አባይ ጸሃየ ከሻዕቢያ ጋር አሁን አወዛጋቢ ተብለው የሚነገርላቸውን ከባድመ ጀምሮ እስከ የአፋር አካባቢዎች ድረስ ያሉ ቦታዎችን አሳልፈው የሰጡ መሆናቸው እና ከብዙ አመታት በኋላም ይህንኑ መዘዝ ተከትሎ በተነሳ ጦርነት ከመቶ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በጦርነት ያለቁበት ሁኔታ እና የጉዳዩም እስከአሁን ሳይቋጭ በእንጥልጥል መቆየት ማንም ሊዘነጋው የማይገባው ሃቅ ነው:: ህወሃት ይህንን አገር የመሸጥ ስራውን ይሰራ የነበረው ገና በደፈጣ ውጊያ ላይ በነበረበት ጊዜ እና በትግራይ ህዝብ ጭምር ምንም አይነት ተቀባይነትም ሆነ ውክልና ሳይኖረው መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል::

3. በ1968 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ህንፍሽፍሽ ተነሳ በማለት አመራሩ የተምቤን : እንደርታ : አዲግራት : ክልተ አውላሎ : ራያ : በትንሹም ቢሆን በአክሱም እና አድዋ ከነበሩ ታጋዮች ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ገድለዋል::  ለዚሁም ምስክር አሁን በህይወት ያሉ ታጋዮች እና ህዝቡ እማኝ ነው:: በየአካባቢውም ማስረጃ ሊሆኑ የሚችሉ የጅምላ መቃብሮችን ጭምር ማሳየት ይቻላል::

4. በ1969 በወርሃ ህዳር በወልቃይት ጠገዴ : ዳንሻ : ጠለምት : ሁመራ : እንዲሁም ከወሎ አካባቢውን ከተወላጆች በማጽዳት የትግራይ መሬት ነው በማለት በካርታ ቀላቅሎ አስታወቀ::

5. በ1971 ዓ.ም. የህወሃት አንደኛ ጉባዔ አንስቶ የድርጅቱ አመራር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የአማራው ገዢ መሳሪያ ነች በማለት የጥቃት በትሩን መዘርጋቱን ተያያዘው:: ይህ እኩይ ትንተናው ከኮሚኒስታዊ የፖለቲካ ፍልስፍናው ጋር ተጣምሮ በፈጠረው የተወላገደ ስነልቦና እየተመራ በብዙ አብያት ክርስቲያናት ላይ እና ገዳማት ላይ የዘረፋ እና የጥቃት እጁን ሰነዘረ:: ለዘመናት የኖሩ የሃይማኖቱን ትውፊት እና ባህላዊ እሴቶችን ማህበረሰቡን በማስገደድ ከለከለ:: ክርስትና ማንሳት እና ሰርግ ማድረግን ጭምር:: ቀሳውስትን በግልጽ ማጥቃት እና ቤተ እምነቶችንም ማርከስ እና መዝረፍ የሰርክ ግብሩ አደረገው::

6. በ1972 ጥቅምት ወር ጀምሮ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ የወያነ ህወሃት የዘር ማጽዳት ስራ አማራ ጸረ ትግራይ ነው በሚል ይፋዊ መፈክር ታጅቦ ከህጻን እስከ ሽማግሌ ድረስ ተፈጸመባቸው:: ቤተሰቦች መኖሪያ ቤታቸው በላያቸው ላይ እየተዘጋ እሳት ተለቀቀባቸው::

7. በ1970 ዓ.ም. ህወሃት በሚቆጣጠራቸው ነጻ መሬቶች ይኖሩ የነበሩ አማሮች ዘራቸው እየተቆጠሩ ተገደሉ:: ንብረታቸውም ተወረሰ:: አማራ በተገኘበት ቦታ ሁሉ እንዲገደል በይፋ አዋጅ ተላለፈ:: ብዙሃን አማራ ስለሆኑ ብቻ ተፈጁ::

8. በ1970 ዓ.ም. ኢህአፓ ከትግራይ ለቆ እንዲወጣ የህወሃት አመራር አዋጅ አስተላለፈ:: የኋላ፣ ኋላ ላይም ኢህአፓ በትግራይ ኢትዮጵያዊነት ላይና በኤርትራ ጥያቄ ላይ ያለውን አቋም እንዲለውጥ ለማስገደድ ቢሞክሩም አሻፈረኝ በማለቱ ሻዕቢያ እና ወያነ ግንባር ፈጥረው የኢህአፓን ጦር ደመሰሱ::

9. በ1970 ዓ.ም. መጀመሪያ አካባቢ በብስራት አማረ የሚመራ በቁጥር ወደ ሃምሳ ገደማ የሚሆኑ ታጋዮች ኤርትራ ውስጥ በሻዕቢያ አማካይነት የፈዳይነት ስልጠና ወስደው በተለያዩ የትግራይ አውራጃዎች ውስጥ ሰርገው በመግባት የህወሃትን እኩይ አላማ የማይደግፉ ንጹሃንን እና የመንግስት ሰራተኛ የሆኑ ሌሎች ዜጎችን በተደጋጋሚ ጥቃት ፈጁ::

10. በህዳር ወር 1968 ዓ.ም. የህወሃት አመራር ከነሰራዊታቸው የግንባር ገደሊ ሃርነት ትግራይ ታጋዮችን(ይህ ድርጅት በጊዜው በግብርም ሆነ በአላማ ከህወሃት እምብዛም የማይለያይ ድርጅት ሲሆን ብዙም በትግል ሳይቆይ በህወሃት የተደመሰሰ ድርጅት ነው::) በሙሉ በጸረ ዲሞክራሲያዊ ባህሪያቸው በአንዲት ለሊት ዘገልባ ጎጥ ውስጥ በጅምላ ፈጇቸው::

11. በ1977 በትግራይ የደረሰውን አስከፊ ድርቅ ተከትሎ በለጋሽ አገራት እና ህዝቦች ዘንድ ለነብስ አድንት ተብሎ የተላከውን እርጥባን የህወሃት አመራር በጥሬ ገንዘብ የመጣውን በቀጥታ ወደግል ካዝናቸው በአይነት የተለገሰውን ደግሞ በሱዳን ገበያ በመቸብቸብ ለትጥቅ መግዣ እና ለግል ሃብት አዋሉት:: እርዳታ ተላከለት የተባለው ምስኪን ህዝብም በየበረሃው ወድቆ ረገፈ:: ለመለመኛ ለታሰበ ድራማ ወደሱዳን እንዲሰደድ በህወሃት የታዘዘው ረሃብተኛም በየመንዱ ቀረ:: የትግራይ ህዝብም ታሪክ ሊረሳው የማይገባው ታላቅ ክህደት ከአብራኩ ወጣሁ በሚሉ ከሃዲዎች ተፈጸመበት::

12. በ1981 ዓ.ም. ደርግ ትግራይን ለቆ እንደወጣ ህወሃት ካለምንም ችግር በሩ የተከፈተ ቤት በማግኘቱ ሰተት ብሎ መሃል ትግራይ ገባ:: ገብቶም አላረፈም:: በየከተማው ይኖሩ የነበሩ መምህራንን እንዲሁም የመንግስት ተቀጣሪ ዜጎችን ጠላት ብሎ በደርግ ደጋፊነት በመወንጀል ለቅሞ ፈጃቸው:: ከየአውራጃው ብዙ ሰዎች መገደላቸውን በቀላሉ ማጣራት ይቻላል::

13. ህወሃት በበረሃ በነበረበት ወቅት ከሻዕቢያ ጋር በነበረው ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን የማጥቃት የጋራ ውል የትግራይ ወጣት ሴት እና ወንዶችን ሻዕቢያን ለማጠናከር በተለያዩ ጊዜያት በባርነት አሳልፎ ይሰጥ እንደነበር የሚታወቅ ሃቅ ነው:: ይህም የትግራይን ልጆች ወደማያውቁት ጦርነት አሳልፎ የመማገድ ዘመቻ ይፈጸም የነበረው በአስገዳጅነት እንደነበር እሙን ነው:: ከ1969-1970 ዓ.ም. ብቻ በቁጥር ወደ 29,000 የሚገመቱ የትግራይ ወጣቶችን ለሻዕቢያ አላማ ማስፈጸሚያ አሳልፎ ሰጥቷል:: የቀይ ኮከብ ዘመቻ እንደተጀመረ የህወሃት አመራር ከዚህ በፊት ያደረገው ሳይበቃው ከ1971-1974 ዓ.ም. ተጨማሪ በቁጥር ወደ 70,000 የሚደርሱ የትግራይ ልጆችን በደርግ ጥቃት የውድቀት ገደል ላይ የደረሰውን ሻዕቢያን ለማዳን በቀጥታ በሻዕቢያ እዝ ስር አዘመተ::ይህም ሳይበቃው ቀይ ኮከብ ዘመቻ በተፋፋመበት ወቅት በ8 ብርጌድ የተደራጁ በቁጥር 13,500 የሚደርሱ ተጨማሪ የትግራይ ወጣቶችን ለሻዕቢያ ህልውና ማስጠበቂያነት ለጭዳነት ላከ:: እነዚህ ሁሉ በማያውቁት እና ይልቁንም አገራቸውን ለሚጎዳ ጦርነት በባንዳነት ህወሃት አሰልፎ የላካቸው የትግራይ ወጣቶች ደም በየበረሃው መና ሆኖ ቀረ::  በጠቅላላው ህወሃት ለወሬ ነጋሪነት እንኳን ያልተመለሱ በቁጥር ከ112,500 በላይ የትግራይ ልጆችን ለሻዕቢያ ጦርነት ማጠናከሪያ እንደላከ ማስረጃ አለ:: አንዳንዶችም ቁጥሩ ከዚህ ሊልቅ እንደሚችል የሚናገሩ አሉ:: ይህ ነው እንግዲህ ትግራይን ነጻ አወጣለሁ የሚለን የነ ስብሓት እና መለስ ጉጅሌ የተሸከመው እና እንዲሰማ የማይፈልገው ጥቁር ታሪክ::

14. በ1981 ዓ.ም. የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች በየካቲት ወር በሱዳን ካርቱም መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወርቂን አነጋግረው እንደምን ስልጣን እና አገሪቷን ከደርግ ውድቀት በኋላ እንደሚያስተዳድሩ አደላድለው ሲያበቁ ለወያነ ከሃዲዎች ኢትዮጵያን አመቻቸተው አሳልፈው ሰጧት::

15. ከደርግ መዳከም ጋር ተያይዞ የአገሪቷ አራቱም ማዕዘናት ክፍት በመሆናቸው ህወሃት ከመቀሌ ተነስቶ ካለምንም ችግር አዲስ አበባ ሊገባ ቻለ:: ከሽሬ ተነስቶ በጎንደር: በባህርዳር በኩል አድርጎ አዲስ አበባን ተቆጣጠረ::

ህወሃት ኢትዮጵያን ወሮ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ የመንግስትን ስልጣን ተቆጣጥሮ የሰራውን ወንጀል በዝርዝር ለማቅረብ ይሄ ጽሁፍ ብቻ በቂ አይደለም:: ስፍር ቁጥር የሌለው የአገር ክህደት እና የዘር ማጥፋት ስራዎች በተለያዩ ቦታዎች በሚኖሩ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ፈጽሟል:: በተለያዩ ቦታዎች በአማራዎች ላይ ፣ በጋምቤላ በአኝዋኮች ላይ ፣ በአዋሳ በሲዳማዎች ፣ በኦጋዴን በኢትዮጵያ ሶማሌዎች ላይ እንዲሁም በመላ አገሪቱ ባሉ እስር ቤቶችን ታጉረው በሚማቅቁ በ10,000 የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ላይ እስከ ዘር ማጥፋት(genocide) ደረጃ የሚደርስ ወንጀል ፈጽሟል:: አሁንም እየፈጸመ ነው::

በተለያዩ የመረጃ ምንጮች እንደተገለጸው ህወሃት በበረሃ በነበረበት ወቅት በአሜሪካን መንግስት በሽብር ድርጊቱ እንደ አል ቃኢዳ አሸባሪ ድርጅት ተደርጎ ይታይ እንደነበር ወጣቱ ጋዜጠኛ አበበ ገላይ ከግሎባል ቴረሪዝም ዳታ ቤዝ(Global Terrorism Database) ላይ አሳይቶናል:: ይህንን መረጃ ማየት ለሚፈልግም ሰው ከኢንተርኔት ላይ ማግኘት ይችላል::

የህወሃት ጥቁር ታሪክ እንግዲህ ይህ ነው::  የእነ መለስ ዜናዊ ፖለቲካ እና አመራር በበረሃም ሆነ በከተማ ይህ ነበር:: ታሪክ ዳቦ ሆኖ አንበላውም ከሚል እጅግ አሳናፊ እና መሰሪ ትንተና ጀምሮ የኢትዮጵያን ታሪክ የማንቋሸሽ እና የማጨማለቅ ስራ የህወሃት ዋንኛ የፕሮፖጋንዳ ግብ እንደነበር እና አሁንም እንደሆነ ከአፋቸው የሚወጣውን ንግግር በመስማት መገንዘብ ይቻላል:: እነኚህ ናቸው እንግዲህ አማራን እና ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን እናጠፋለን ከሚል ጀምሮ ኢትዮጵያን አፍርሰን እንሰራለን እና ታሪኳንም እንደ አዲስ እንጽፋለን የሚሉን::

የስርዓቱ ዋና አንቀሳቃሽ መለስ ዜናዊ በሞት ተቀስፎ ከሄደ እነሆ ወራት ተቆጠሩ:: ሊታረቅ በማይችል የክህደት ቁልቁለት ውስጥ ያለው ህወሃትም ፍጹም ሊመልሳቸው በማይችላቸው ታሪካዊ ጥያቄዎች ተወጥሮ የውጪ ነብስ ፤ ግቢ ነብስ ግብግብ ላይ ይገኛል:: የድርጅቱ እኩይ አላማ እና ግቡ ዛሬ ፍንትው ብሎ በወጣበት ወቅት ላይ ኢትዮጵያውያን በመላ ኦሮሞ ፣ አማራ ፣ ትግሬ ፣ እስላም ፣ ክርስቲያን ሳይሉና አላስፈላጊ አተካራቸውን ወደጎን በማለት ይህንን የታሪክ አሽክላ የሆን ዘረኛ ቡድን ከስረ መሰረቱ ነቅለው መጣያ ጊዜው አሁን ነው:: በስቃይ ያሉ ወገኖቻችንን እና አገራችንን ከወያኔ መንጋጋ እናላቅ:: የሀገራችንን እና ህዝባችንን በጎ ታሪክ እና መጻኢ እድልም እናስመልስ::

ገብረመድህን አርአያ
የካቲት 2005

ECADF.Com

እራሷ ክርስትና አልተነሳች ልታቋቁም ወጣች

መቅደስ አበራ (ከጀርመን)

የወያኔ አንባገነኖች  በስልጣን ላይ በቆዩባቸው ያለፉት 21 ዓመታት እና በትጥቅ ትግል ወቅት የጠፋውን ህይወትና የወደመውን ንብረት ለኢትየጵያ ህዝብ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ነው፡፡ ለመሆኑ ሁሉም እድሉን አግኝቶ  ስላልተናገረው  ብእርና ወረቀት አዋህዶ ከትቦ በጽፈው ስንት መጽሐፍ እንደሚወጣው ቤት ይቁጠረው፡፡ ወይም ጽፈውት  ጊዜውን እየጠበቀ ይሆናል አንድ ቀን ያወጡታል፡፡ከሁሉ የሚከፋው ደግሞ የስልጣን ተቀናቃኞችን ብቻ ሳይሆን በጭፍን ትላቻ ተነድተው

በአንድ ብሄርና እምነት ላይ  ሌላውን በማነሳሳት ለጅምላ ግድያና በመቶ በሺዎች የሚቆጠሩን ለማፈናቀል የሚሰራውን ተንኮል ላየ እነዚህ ሰዎች እውነት ኢትጵያዊ ናቸው ብሎ እንዲጠይቅ ያደርገዋል፡፡ ሰው እንዴት ሀገርን እመራለሁ ብሎ የተቀመጠ ሀይል የራሱን ህዝብ በጅምላ ይጨፈጭፋል;ይግድላል ያፈናቅላል አላማቸውስ ምንድን ነው ብሎ ይጠይቃል

ይህ እንግዲህ ግር የሚለው ለባእዳን እና ነፍስ ላላወቁ ህፃናት ካለሆነ በስተቀር  የእድሜውን ግማሽ  የወያኔ/ኢህአዴግ የስቃይ ሰለባ ሁኖ ላሳለፈው ኢትዮጵያዊ አደለም፡፡ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት ይሏታል  እንደሚባለው ሲላቸው አስቀድመው በደንብ የተጠና ድራማ ይሰራና በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በኩል ህዝቡን ለማደናገር በተደጋጋሚ እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡ለምሳሌ ያህል አደስ አበባን እንደባገገዳድ አኬልዳማ ወዘተ የመሳሰሉትን ማሰታወስ ይቻላል፡፡  የመጀመሪያውን ትይንት አስጠልቶት  ህዝቡ ባያየውም በተመልካቾች አስተያየት ተደጋጋሚ ጥያቄ ስለቀረበልን  የተመልካቾችን ፍላጎት ለማርካት በሚል የንጹሀን ዜጎች ሀጢያት ተደርድሮ ይቀርባል፡፡ይኸኔ መገመት የሚቻለው እነዚህን ንጹሀን ወይ እድሜ ልክ እስራት ወይ ጸና ሲልም የሞት ፍረድ ሊያስፈርድ መዘጋጀቱን  ነው፡፡ ቀላል ሲባል ከ15-25 አመት ጽኑ እስራተና በርካታ የገንዘብ ቅጣት ይጠብቃቸዋል፡፡

ወያኔዎች ቀደም ሲል የጀመራቸው የስልጣን ጥማት ምኒልክ ቤተ ምንግስትን በመቆጣጠር  ሊረካ ባለመቻሉ ጵጵስናውም ፤ ሲኖዶሁም ፤መጅሊሱም መስጊዱም በወያኔ ቅጥጥር  ስል ውለዋል፡፡ በዚህም አይወሰኑም ለብዙ መቶ አመታት በፍቅር የኖሩትን የእስልምናና የክርስትና እምነት ተከታዮች እንደ እስራኤልና ፍልስጥኤም ታሪካዊ ወንድማማችነታቸውን  በታሪካዊ ጠላትነት ለመቀየር የጥላቻ ፖለቲካውን በዶክሜንታሪ ፊልም አስደግፎ ያቀርባል፡፡  ሰሞኑንም የእስልምና እምነት ተከታንና ለማዋጋት ከፍተኛ ዝግጅት እተደረገ እንዳለ በርካታ ምንጮች እየጠቆሙ ይገኛሉ፡፡አርቆ አስተዋዩ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉንም ችሎ ሆድ ካገር ይሰፋል በሚለው ሀገረኛ ፈሊጥ መሰረት ታገሰው እንጂ እንደወያኔ ተንኮልና ቴራ እስካሁን እስልምና እና ክርስትና እምነት ተከታየች አንድ ቤት ውስጥ ቀርቶ ባናድ ሀገር ውስጥ ከማይችሉበት ደረጃ ይደርሱ ነበር፡፡ወያኔዎች እስካሁን ያልገባቸው ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ ከጥላቻ ይልቅ ሰላምንና ፍቅርን እንደሚሻ አለማወቃቸው ነው፡፡ከሰላም እንጅ ከጦርነት ምንም እንደማይገኝ መረዳት አለመቻላቸው ነው፡፡”እራሷ ክርስትና አልተነሳች ልታቋቁም ወጣች “አሉ አበው ሲተርቱ የራሱን የውስጥ ሰላም የሌለው የወያኔ መንግስት ሱማሊያ፣ ኡጋንዳ እና ሱዳን ሰራዊት ከመላኩ በፊት፤ ከኤርትራ ጋር አስታርቁኝ እያለ ከመማጸኑ በፊት ምናለበት ከራሱ እና  ከራሱ ህዝብ ጋር ቢታረቅ፡፡ምናለበት በየአደባባዩ እየወጡ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ከማውራት ለነጻነትና ለእኩልነት መስፈን የተሰውትን የትግራ ይተወላጆች እና የሌሎችን ሰማእታት ደም የውሻ ደም ባያደርጉት፡፡

እነሆ እሳት እና ውሃን ፈጠርኩልህ እጅህን ወደፈለግህበት ጨምር ተብሎ በነጻነት የተፈጠረ ፍጡር ዛሬ በወያኔ በነጻነት እምነቱን እንዳያካሂድ ፤የፈለገውን የፖለቲካ አመለካከት እንዳይደግፍ ቢደረግም የኢትየጵያ ህዝብ ተባብሮ ነፃነቱን የሚያስመልስበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡የተለያዩ አፋኝ ሰው ሰራሽ ህጎች እና የስለላ መዋቅሮች አቋቁሞ በርካቶችን ለእስራትና ለሞት ቢዳርግም በፈጣሪያችን እገዛና በህዝቦች የጋራ ትግል ነጻ እንወጣለን፡፡

እግዚያብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን ይባክ!

Maleda Times

“ጂሃዳዊ ሀረካት”፡ ሳይተወን የከሸፈ የወያኔ ድራማ

ሕውሃት ከጥንስሱ ጀምሮ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎችን የዘር ታርጋ እየለጠፈ አንተ አማራ ነህ፤ ኦሮሞ እንዳያጠፋህ ቀድመህ አጥፋው፡ አንተ ስልጤ ነህ ጉራጌ እንዳያንሰራራ ቀጥቅጠው፡ አንተ ትግሬ ነህ አማራ ጠላትህ ስለሆነ ዘሩን አጥፋው በሚል አስተምሮት የተቃኘ እና ህዝብን በህዝብ ላይ በማነሳሳት፤ በማጋጨት እስካሁን ስልጣን ላይ መቆየቱን የማይረዳ ኢትዮጵያዊ ባሁኑ ሰዓት ሊኖር እንደማይችል አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ።“ጂሃዳዊ ሀረካት”፡ ሳይተወን የከሸፈ የወያኔ ድራማ

የትግሬ ነጻ አውጭ ድርጅት ፕሮግራም እንዳሰቀመጠው መጀመሪያ ጠላት አርጎ የወሰደው አማራን ነው፡ ከዚህም በመነሳት በሚሊየን የሚቆጠሩ አማርኛ ተናጋሪዎችን መፍጀቱ ይታወቃል። ከዘር ቀጥሎ የወያኔ የመከፋፈያ ስልት ሓይማኖት መሆኑን እና ለዚህም እንዲጠቅመው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በነታጋይ ጻውሎስ ተቆጣጥሮት እንደነበረና አሁንም ሌላ ካድሬ በመመልመል ላይ መሆኑን የማናውቅ የለንም። የክርስትና ሃይማኖትን እንደተቆጣጠረው ሁሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችንም ለመቆጣጠር ባዘጋጀው ሰፊ ዝግጅት የእስልምና እምነት ምን መሆን እንዳለበት እስልምና ተከታይ ወገኖቻችን ላይ ሊጭን ሲሞክር ሓይማኖቴን አንተ አትጭንብኝም በማለታቸው፤ ተገለዋል፤ ታስረዋል፤ ተሰደዋል፤ ተደብድበዋል፡ ይህ በግልጽ የምናውቀው ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው፡:

አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ በገሃድ የሚያወቀውን ሃቅ ወያኔ ከምን ተነስቶ ነው እስልምና ተከታዮች ክርስቲያኖችን ሊያጠፉ ነው የሚለውን ድራማ ይቀበሉኛል ብሎ ያሰበው?አማራንና ኦርቶዶክስ እስከወዲያኛው እንዳያንሰራሩ አጥፍተናቸዋል እያሉ በእብሪት የሚያናፉት እነ ሳሞራ ዩኑስ፤ ስበሃት ነጋ እና ሌሎችም ወያኔዎች አደሉም እንዴ? አሁን ከየት መተው ነው ለክርስትና እምነት ተከታዮች ጠበቃ ነን ለማለት የሚቃጣቸው? ነው ወይስ የኢትዮጵያ ህዝብ ያልነውን ሁሉ የመቀበል ግዴታ አለበት ከሚል ግልብ እብሪት የተነሳ ነው?

መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አገር ውስጥም ሆነ ውጭ ያለኸው፡ ወያኔ በበረከት ስምኦን ተደርሶ ማክሰኞ ባፈ ወያኔ ቴሌቪዥን ጣቢያው ሊያሰተላልፈው ያሰበውን “ጂሃዳዊ ሃረካት” የሚለውን ሰቆቃዊ ተውኔት ተከታተሉት ቀርጻችሁም አስቀምጡት፡ ለነገሩ ሚሰጥሩ ቀድሞ ህዝብ ጆሮ ስለደረስ ላያስተላልፈው ይችላል። ወያኔን ሰምታችሁ የሚለውን እንደማትቀበሉ በጣም እርግጠኛ ነኝ፡ ግን ከዚያች ቀን ጀምሮ የእስልምና ተከታይ ወገኖቻችሁ የሚያደርጉት ትግል እንድትቀላቀሉ አደራ እላለሁ።

እስልምናና ክርስትና እምነት ተከታዮች አትዮጵያ ውስጥ አብረው የኖሩት  ከአንድ ሺ ዘመን በላይ ነው፡ በነዚህ ዘመናት እስልምናና ክርስትና ባላቸው የመቻቻል እና የመከባበር ባህል ለአለም አርአያ ሲሆኑ እንጂ እርስ በርስ ሲተራረዱ አላየንም አልሰማንም፤ ታሪክም አልዘገበውም። ትናነት የመጣ ወያኔ ያውም የባንዳ ወንጀለኞች ጥርቅም ነው እስልምና ተከታዮች ክርስቲያኖችን ሊያርዱ ነው የሚለን? የወያኔ ፌዝ እዚህ ላይ ይቁምና ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን ይህንን ያገር ነቀርሳ ማሰወገድ
መቻል አለብን፡

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

እስከ ነጻነት

 

ፓሊሶች በአራት ኪሎ የሚገኙ ቤቶችን በእሳት አቃጠሉ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ለረጅም አመታት በአራት ኪሎ አካባቢ የኖሩ  ሰዎች ቦታው ለሼራተን ሆቴል ማስፋፊያ ይፈለጋል በሚል ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ሲነገራቸው እንደቆየ የተናገሩት አይን እማኞች፣ ነዋሪዎቹ በበኩላቸው መንግስት ተተኪ ቤት እስካልሰጣቸው ድረስ አካባቢውን ለቀው እንደማይሄዱ ሲከራከሩ ቆይተዋል። ዛሬ ጧት ወደ አካባቢው ያቀኑት ፖሊሶች ነዋሪዎቹ እቃዎቻቸውን ሳያወጡ በቤታቸው ላይ እሳት በመልቀቅ ቤታቸውን አቃጥለውባቸዋል። ነዋሪዎቹ በጩሀት ወደ ፓርላማ በመሄድ አቤት ቢሉም ሶስት ሰዎችን በመወከል ችግራቸውን እንዲያቀረቡ ተነግሮአቸዋል። ፖሊሶች ወደ አካባቢው በመድረስ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ ነዋሪዎችን አባረዋቸዋል።

አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአይን ምስክር ለኢሳት እንደገለጡት፣ ተማሪዎች ደብተራቸውን እንኳን ሳያወጡ ቤታቸው እንደተቃጠለባቸው፣ ብዙዎችም በከፋ ችግር ላይ መውደቃቸውን ገልጸዋል።

በኢትጵያ ውስጥ በልማት ስም እየተበራከተ የመጣውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አለማቀፍ ሰብአዊ መብት ተማጓች ድርጅቶች ችላ እንዳሉት ተመልክቷል። በአላማጣ ላለፉት አንድ ወራት የከተማው ህዝብ በልዩ ፖሊሶች ሲዋከብ እንደነበርመዘገባችን ይታወሳል። በአዲስ አበባ ላፍቶ ክፍለከተማ ቤታቸው የፈረሰባቸው በርካታ ነዋሪዎች አሁንም በከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

 

 Esat news

“አንድ ጥምቀት፣ አንድ ሃይማኖት” የሚል ጥቅስ የያዙ ወጣቶች ታሠሩ

(ደጀ ሰላም፤ ጥር 12/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 20/2013/ PDF)፦ ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በላከው መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ ያለውን “አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ጥምቀት” የሚል ጥቅስ ያለበት ቆብ ለሰንበት ት/ቤታቸው ገቢ ማስገኛነት በመሸጥ ላይ የነበሩ ወጣቶች በፖሊስ መታሠራቸው ታወቀ።
ጥር 11/2005 ዓ.ም ታቦተ ሕጉን ተከትለው በሞቀና በደመቀ ሃይማኖታዊ መንፈስ በማክበር ላይ እያሉ በፖሊስ የታሠሩት ስድስት ወጣቶች ሲሆኑ ጥቅሱ የተጻፈበትን ቆብ ይሸጡ የነበሩት ደግሞ ለብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ገቢ ለማስገኘት በሚል እንደሆነ ተገልጿል። መንግሥት የሃይማኖት አክራሪነትን እዋጋለኹ በሚለው ዕውቀት የጎደለው ተግባር ‘አንድ ሃይማኖት’ የሚል ቃል የሚናገሩ ክርስቲያኖችን በሙሉ በማሳደድ ላይ ይገኛል። የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይለ ቃል እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረተ እምነት የሆነውን ቃለ እግዚአብሔርን መናገር፣ ማስተማርም ሆነ በጽሑፍ መያዝ ሌሎች እምነቶችን እንደመዋጋት ተደርጎ እንዲቆጠር በመናገር በፖሊስ ጥብቅ ማዋከብና እንግልት የሚፈጽመው መንግሥት እነዚህን ስድስት ልጆች የያዘው በዚሁ ምክንያት መሆኑን በወቅቱ በቦታው የነበሩ እማኞች ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩ ቀደምት መንግሥታት ሁሉ በባሰና በከፋ መንገድ በቤተ ክርስቲያኒቱ የውስጥ ጉዳይ ረዥም እጁን አስገብቶ የሚያምሰው የፖለቲካው መዘውር በቅርቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤያት ላይ ሳይቀር ባለ ሥልጣኖቹን በመላክ የሲኖዶሱ ተሰብሳቢ ለመሆን በመሞከር ላይ መሆኑን ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል።
መንግሥት በአገሪቱ ቀደምት እምነቶች ላይ ያለውን አቋም ለካድሬዎቹ በተከታታይ ሥልጠኛ በመስጠት የሚያስጠናበት ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል። ለዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ድረስ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና በሌሎች ኃላፊዎች ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና እስልምና ላይ ያነጣጠረ ሲሆን በባለሥልጣናት ቁጥር ሰፊ ተሰሚነት ያገኙትን ፖሮቴስታንቶችን ግን ምንም አይነካም። መንግሥት በነባር አገራዊ ቤተ እምነቶች ላይ እያስፋፋ የመጣው ጣልቃ ገብነት ድንበሩን አልፎ የእስልምና መሪዎችን በማሰር፣ የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶስ በመዘወር መገለጡ ይታወቃል።
መንግሥት ለባለሥልጣኖቹ የሚሰጠውን ሥልጠና ለማወቅ ለምትፈልጉ ወደፊት እንዳስፈላጊነቱ ሙሉ ዶኩመንቱን ለማቅረብ እንሞክራለን።
ቸር ወሬ ያሰማን
dejeselam.org

ልማታዊው ኪስ አውላቂ (ክንፉ አሰፋ)

ማስታወሻ፡  ባለፉት ጊዚያት በጫጫርኳቸው አጫጭር ጽሁፎቼ፤ ገንቢ ትችቶች ለላካችሁልኝ አንባብያን ሁሉ ምስጋናዬ የላቀ ነው። በአንጻሩ አፍራሽ ትችቶች በስማችሁ ጽፋችሁ የላካችሁልኝ ወገኖችንም አደንቃለሁ። ነገር ግን በብእር ስም ራሳችሁን በመደበቅ፤ ነውር እና አሳፋሪ የሆነ የፈጠራ ስራ ለምትሰሩ ደግሞ፡ ልቦና ይስጣችሁ ከማለት ውጭ የምለው የለም። ሰውን ዘልፎ ለመጻፍ እንቅልፋቸውን የሚያጡ ሰዎችን ፈረንጆቹ ‘ባለ ትንሽ ጭንቅላቶች’ ይሏቸዋል። ችግሩ ከአስተዳደግ ጉድለት፣ ከአስተሳሰብ ድህነት እና በራስ ካለመተማመን የሚመጣ የስነልቦና በሽታ ነው።

ክንፉ አሰፋ

Click here for PDF

የ ‘ህዳሴው ቦንድ’ ግዢ ግርግር ሞቅ ብሎ በነበረበት ሰሞን ይነገር የነበረ አነድ ቀልድ አለ። የ‘ማረሚያ’ ቤት ፖሊሶች እና ታጋዮች 500 ብር በሰረቀ ሌባ ላይ ውይይት ያደርሉ። ተከሳሹ ብሩን ያላግባብ ይስረቅ እንጂ በገንዘቡ የህዳሴውን ቦንድ መግዛቱ ነው ጉዳዩን ለውይይት የዳረገው።  ይህ ሌባ መታሰር የለበትም የሚሉት ታጋዮች፡ ለፖሊሶቹ ያቀረቡት መከራከሪያ ነጥብ ልማታዊ ሃሳብ ነበር። እንዲህ ነበር ያሉት፡ ‘ይህ ልማታዊ ኪስ አውላቂ ነው። እንዲያውም እንደዚህ አይነቶቹን ሌቦች የበለጠ እንዲሰሩ ማበረታታት ነው ያለብን።…’  ሁሉም በዚህ ሃሳብ ተስማሙና ሌባውን በያዘው ልማታዊ ተግባር የበለጠ እንዲሰራበት መክረው ለቀቁት።

ይህ እነግዲህ ቀልድ ነው። ቀልድ ደግሞ በመጠኑም ቢሆን የእውነታ ነጸብራቅ እነጂ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ክስተት አይደለም። ‘ልማታዊ’ የሚለው ቃል ትርጉሙ ተዛብቶ ምን ያህል እየተቀለደበት መሆኑን ከዚህ ቀልድ ግንዛቤ እንወስዳለን። በዚህ ላይ ወደሗላ እመለስበታለሁ።

ቀልዱን በቀልድ እንለፈውና አንድ ምሽት በኢ.ቲ.ቪ. ያየሁትን እውነታ ላውጋችሁ። ኢ.ቲ.ቪ. በሚያዘጋጀው የትምህርት ቤቶች ጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ‘ቦንድ ማለት ምን ማለት ነው?’ የሚል የ500 ብር ጥያቄ ቀርቦ ነበር። ከተወዳዳሪዎቹ አንዱ መልስ ሰጠ። እነዲህ ሲል፣ “ቦንድ ማለት፡ መንግስት በህዝብ እጅ ያለውን ጥሬ ገንዘብ ለአንድ አላማ ወደ ባንክ እንዲገባ ለማድረግ የሚጠቀመበት ዘዴ ነው።”

“ጥያቄው በትክክል ተመልሷል!” የሚል መልስ ነበር ህዘብ ከጠያቂ ጋዜጠኛው ይጠብቅ የነበረው። ጠያቂው ግን ተወዳዳሪው ትክክል እንዳልመለሰ ተናግሮ፡ ጥያቄውን ተመልካቾች  እንዲመልሱለት ጋበዘ። አነዱ ‘ልማታዊ’ ተመልካች ከመሃል ተነስቶ “ትክክል” የተባለለትን መልስ ሰጠ። መልሱ ይህ ነበር፣  “ቦንድ ማለት ወለዱ ከግብር ነጻ የሆነ የቁጠባ ዘዴ ነው። ”

በዚህ ልማታዊ ጋዜጠኛ የተሳሳተ የቦንድ ትርጉም ተወዳዳሪ ተማሪው ብቻ ሳይሆን፤ የቴሌቭዥኑ ታዳሚዎችና ተመልካቾችም በሙሉ ቀልጠዋል። ይህ ጥያቄ በትምህርት ቤት ፈተና ላይ ቢመጣ ተመሳሳይ ‘ልማታዊ’ መልስ ያልሰጡ ተማሪዎች አያልፉም ማለት ነው።

በአጭር አነጋገር ቦንድ ማለት፤ ህዝቡ እንዲቆጥብ ታስቦ ሳይሆን መንግስት የገንዘብ እጥረት ሲኖርበት ከህዘብ ላይ በብድር መልክ የሚሰበስበው ገንዘብ ማለት ነው።  ቦንድ መሸጥ አዲስ ነገርም አይደለም። የምእራቡ አለም መንግስታትም በአንደኛው እና በሁለተኛው የአለም ጦርነቶች ወቅት የገንዘብ እጥረታቸውን ለመሸፈን ለሕዝብ ቦንድ ይሸጡ ነበር። ዩናይትድ ስቴትስ ለሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ገንዘብ ስላስፈለገ፤  ፕሬዚዳንት ሩዝቬልት የተጠቀሙት ዘዴ ‘የነጻነት ቦንድ’ ያሉትን ኩፖን በመሸጥ ነበር። ጀርመን፣ እንግሊዝና ካናዳም በተሳካለት የጦር ቦንድ ሽያጭ የሚጠቀሱ ሃገሮች ናቸው።

ወደ ዋናው ነጥብ ስንገባ ልማታዊ መንግስት የሚለው ጽንሰ-ሃሳብ የመነጨው በ20ኛው ክፍለዘመን መገባደጃ አካባቢ ከነበሩ የምስራቅ ኤሽያ ሃገሮች ነው። እነዚህ በወቅቱ እጀግ ደካማ የሚባሉ የኤሽያ ሀገሮች፡ በመንግስት የሚመራ የማክሮ ኢኮኖሚ እቀድ በማውጣት የሃገራቸውን ኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ስልጣን አጥብቀው በመያዝ ወደ ምጣኔ ሃብት እድገት ያመሩ ናቸው።

ልማታዊ ነን የሚሉ እነዚህ መንግስታት የብዙሃን ፓረቲ ዲሞክራሲን፣ የፕሬስ ነጻነትንና የመሳሰሉ መብቶቸን በመጠኑም ቢሆን ያፈኑ ቢሆኑም ‘ልማት ከሰብአዊ መብት ይቀድማል!’ ከሚሉት ከኛዎቹ ገዚዎች ፍጹም የተለዩ ናቸው። ልማታዊ መንግስታት  ከህዝባቸው ጋር ሆድና ጀረባ በመሆን ከህዝባቸው ጋር ጦርነት ሲገጥሙ አላየንም። እነዚህ ሃገሮች ትኩረታቸውን በሙሉ በኢኮኖሚ እድገት ላይ በማድረግ ህዝባቸው በምግብ ራሱን እንዲችል ከማድርግ አልፈው የአብላጫው ህዝብ የኑሮ ሁኔታ በእጀጉ እንዲሻሻል ረድተዋል።

ዛሬ የደቡብ ምስራቅ እሺያ ሀገሮች እና የቻይና ዜጎች የፖለቲካ ተሳትፏቸው እጅግ ዝቅተኛ ይሁን እነጂ የኑሮ ደረጃቸው በእጅጉ ተሻሽሎ እናያለን። በአንጻሩ በልማታዊው የኢህአዴግ ስርአት በግልጽ የማይታይ የሁለት አሃዝ እድገት መጠን ከማውራት ያላለፈ እድግት ባሻገር የህዝቡ የኑሮ ደረጃ ሲብስ እንጂ ሲሻሻል አይታይም። በልማታዊ መንግስት ስም 80 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዘብ ከነጻነቱም፣  ከኑሮውም ሳይሆን አሁንም በባሰ የኑሮ ጉስቁልና ውስጥ ይገኛል።

በቅርብ ከኢትዮጵያ የመጣ አንድ ሰው፡ የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ ከአንድ የእግር ኳስ ስታዲየም ጋር በማስመሰል ይገልጸዋል።  በአንድ የእግር ኳስ ስታዲየም ውስጥ ያሉ ሰዎች በሶስት ምድቦች ይከፈላሉ፤ ተጫዋቾች፣ አጫዋቾች እና ተመልካቾች።  የኢትዮጵያም ህዝብ እንደዚሁ በሶስት ምድብ ይከፈላል። ባለስልጣናቱ አጫዋቾች፣  አጫፋሪዎቹ (ለባለስልጣናቱ አየር ባየር ቢዝነስ የሚሰሩት) ተጫዋቾች – ሲሆኑ ህዝቡ ደግሞ የዚህ ጨዋታ ተመልካች ሆኗል።

ሕዝቡ የሃገር ሃብት ነው። ህዝብን ሳያሳትፉ ስለ እድገት ማውራት ከቶውንም የሚቻል አይሆንም። በተለይ ደግሞ ዲያስፖራውን። የምስራቅ ኤሸያ እድገት ሚስጥር ዲያስፖራው መጠነ ሰፊ ገንዘብ እና እውቀትቱን ይዞ በሃገሩ መስራት መቻሉ ነበር።

ህወሃቶች እንደሚሉት ‘ቶክሲክ’ (መርዘኛ) ዲያስፖራ እያሉ የሃገር ሀብት የሆነውን የዲያስፖራ ሃይል ቢሳደቡ ኖሮ እስያውያን እዚህ ደረጃ ባልደረሱ ነበር። በተማረ የሰው ሃይል፣ በቴክኖሎጂ እና የውጭ ምንዛሪ እጥረት ውስጥ ሆኖ ዲያስፖራውን በጅምላ ጠላት ማድረግ ከእብደት ውጭ ሌላ ትርጉም አይሰጠውም። የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የሰራው ወንጀል ቢኖር ‘ሰብአዊ መብት በሃገሪቱ ይከበር!’ ብሎ መጮሁ ብቻ ነው።

በአንድ ሃገር ኢኮኖሚ ላይ የዲያስፖራውን ሚና ለማሳየት ምሳሌ ሊሆነን የሚችለው የሲንጋፖር የእድገት ታሪክ ነው።  ሲንጋፖር ከታላቋ ብሪታንያ ቅኝ ግዛት ነጻ በወጣች ማግስት ህዝቧ በድህነት ውስጥ ነበር። ሲንጋፖር አንዳች የተፈጥሮ ሃብት የሌላት ፍጹም ድሃ የሆነች ደሴት ነበረች። ከዚህ ድህነቷ ለመላቀቅ የነበራት አማራጭ የተማረ የሰው ሃይሏን መጠቀም ብቻ ነበር።  አንድ የሲነጋፖር ዜጋ እነዲህ ብሎ ነበር ያጫወተኝ።

‘ሲንጋፖር በተፈጥሮ ሃብት ያልታደለች የትናንሸ ደሴቶች ክምችት ነች። ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻ እንደወጣች የመጠጥ ውሃ እንኳን አልነበራትም። በወቅቱ የተረፈን ጭንቅላታችን ብቻ ነበር – የተማረ የዲያስፖራ ሃይል። ከባዶ በመነሳት ሲንጋፖር አሁን ያለችበት ደረጃ እንድትደርስ ያደረጉት እውቅት እና ቴክኖሎጂ ይዘው የመጡ የዲያስፖራ ምሁራን ናቸው።’

‘የሲነጋፖር ምሁራን ከጎረቤት ሃገር ከማሌዢያ የሚፈሰውን ቆሻሻ ውሃ በቱቦ አማካይነት ወደ ሃገሪቱ እንዲገባ ካደረጉ በሗላ፡  ውሃውን እያጣሩ ለማሌዥያ መልሰው መሸጥ ጀመሩ።…’

የእውቀት ኢኮኖሚን የያዘ የዲያስፖራ ሃይልዋን ያልናቀችው ሲንጋፖር ዛሬ የኢንዱስተሪ ሃገር ናት። አንባገነንነቱ እና ሙስናው እነደተጠበቀ ሆኖ፡ ይህቺ ደሴት የበርካታ ሀገሮች የእድገት ምሳሌ (ሞዴል) ለመሆንም በቅታለች።

የኤርትራው ኢሳያስ አፈወረቂ እንኳን፤ በትረ ስልጣናቸውን የጨበጡ ሰሞን ‘ኤርትራን የአፍሪካ ሲንጋፖር እናደርጋታለን።’ ብለው ነበር። ይልቁንም ከ21 አመታት በሗላ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራን ሲን ጋፖር ሳይሆን ‘ሲንግል ኤንድ ፑር’ አደረጓት እያሉ ተቺዎች ይቀልዱባቸዋል። የኢትዮጵያም የእድገት ማነቆ ምስጢሩ በስብአዊ መብት አፈናው ሳቢያ ለተማረ የሰው ሃይል እና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ቦታ ካለመስጠቱ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ልማታዊ መንግስት ነን ይበሉ እነጂ፤ የልማታዊነት ትርጉሙ እንኳን የገባቸው አይመስልም። አሁን የተያዘው የኮብል ሰቶን ልማትን እንመልከት። የኮበልስቶን ስራን ሊሰራ የሚችል ያልሰለጠነ የሰው ሃይል በገፍ ባለበት ሃገር፤ በባችለር እና በማስተርስ ዲግሪ ከዩኒቨርሲቲ የሚመረቅ ዜጋ ሁሉ ድንጋይ መፍለጥ፣ መጥረብ እና መዘርጋት እንዲሰራ መደረጉ ለብዙዎች እንግዳ ነገር ነው። የተማረ እና የሰለጠነ የሰው ሃይልን በጉልበት ስራ የሚያሰማራ ልማታዊ መንግስት በኢትዮጵያ ብቻ ነው የታየው። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም በመገናኛ ብዙሃን ቀርበው በባችለር እና በማስተርስ ዲግሪ ከዩኒቨርሲቲ ለሚመረቁ ተማሪዎች የኮብል ሰቶን ስራ አዋጭ ስራ መሆኑን ሲናገሩ ተደምጠዋል።  አዋጪ ስራ መሆን አንድ ነገር ነው።  የሃገር እድገት ደግሞ ሌላ።  የሚያሳዝነው አማራጭ ያጡ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን የዚህ የተሳሳተ ልማታዊ አስተሳሰብ ሰለባ መሆናቸው ብቻ ነው።

የህንጻ  እን የከተማ መንገድ ግንባታ የከተማን ውበት ሊያሳምር ይችል ይሆናል። በህንጻ ግንባታ ከተማ ልትቀየር ትችልም ይሆናል። ይህ ግን ከሃገር እድገትና ከዜጎች የኑሮ መለወጥ ጋር ፈጽሞ ሊገናኝ አይችልም።  ምሁራኑ ድንጋይ ሲፈልጡ፣ ሲጠርቡ እና ሲያነጥፉ፡ የነሱን የሙያ ቦታ ያልተማሩ ካድሬዎች እነዲይዙት ማድረግ። ሃገር በዚህ አይነት ሂደት ታድጋለች የሚል የልማታዊ መንግስት ፍልስፍና የለም። ይህ እንዲያውም በልማት ስም የሚሰራ መንግስታዊ ወንጀል ነው። ኪስ አውልቆ ቦንድ ከመግዛት የማይተናነስ ወነጀል።

ecadf.com

የጥፋት ራእይ፤ የክህደት ሌጋሲ

ራእይም ይባል ሌጋሲ፤ህልምም ይባል ምኞት አንድ ነገር እውነት ነው። ሰውየው፤ከተጀመረ ጀምሮ በሰላም ኑሮ እንቅልፍ አግኝቶ ስለማያውቅ ህልም አለመ፤ራእይም ነበረው፤አስቦና መዝኖ ሠራ ለማለት አይቻልም። ከፊቱ ነገ አልነበረችም። ሊባል የሚቻለው፤ የነበረው የጥፋት፤ የማፍረስ፤ የመበተን፤ የክህደት ቅዠት ብቻ ነው።

የዛፉ ምንነት በሚያፈራው ፍሬ ይመዘናልና፤ የተዋቸውን እናስቀጥላለን ከሚባለው ራእይ ባዶ ኳኳታና ጩኸት ማካከል ጥቂቶችን እንመልከት። ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል እንዲሉ፤ያልነበረውን እንደነበረ፤ ባዶውን እንዳለ፤ የማይሆነውን እንደሚሆን ሲሰበክና ሲቅራራ ሲወሸከት ሕዝብ እንደታዘበ፤ ታሪክም እንደመዘገበና የፈጠጠው እውንታ የሚታይ መሆኑን መካድ አይቻልም። ሚዛኑ፤የሕዝቡ የእለት እለት ኑሮ፤ያለው ነጻነትና መብት፤ስነልቡናው፤የዓለምአቀፍ ሕብረተሰቡ የሚወተውተው ምን እደሆነ ማየት ነው።

ዓይናችሁን ጨፍሉ ላሞኛችሁ፤እንደሰጎን ራስን አፈር ውስጥ ቀብሮ አልታይም-የብልጣብልጥ ሞኝነት ሲዘበት ሁለት አስርተ አመታት እንደለፉ፤ በእነዚህ ወርቃማ አመታት መልካም አስተዳደር፤ ቅን አመለካከትን ጥረት ታክሎበት አገር ትመጥቅ ነበር ማለት ምኞት ብቻ ቢሆንል፤ በእድገቷ ከሌሎቹ ቀርቶ ከአአህጉር እህት አገሮች ጋር በተስተካከለች ነበር፤ ምን ያህል ብዙ በተሰራ ነበር ያሰኛል። በእርግጥም ብዙ ሕይወት ተገብሯል፤ ሕዝብ ተጎሳቁሏል፤ መብት አልባ ሖኗል፤ ታፍኗል፤ ታስሯል፤ ተሰዷል፤ አገር ተበትናለች፤ ንብረት ባክኗል፤ በአገር በሕዝብ ላይ ከመቸውም የበለጠ አደጋ አንዣቧል።

እውነቱ ሌላ፤የሚወራው ሌላ። ብዙ ጊዜ በማደናቆር፤በመዋሸት፤በማሳሳት፤በተንኮልና ሸፍጥ አልፏል።

ህልምና ቅዠት፤ እውነትና ውሸት፤ማታለል፤መደለልና እውነተኛ ሕዝባዊ አረማማድን ሌለውም ሌላውም ሕዝቡ በሚገባ ለይቶ ስለሚያውቅ፤ነገ እንደታሪክ እንደሚወራ ማዘንጋት አያሻም። ትላንት ዛሬ ነበረች፤ ዘሬም ነገ ትሆናለች፤ ባጭሩ እንደማንኛውም ስርአት፤ ይኸም ስርአት ይሻግታል፤ይበሰብሳል ያልፋል። እውነታው ግን ለትውልድ ፈጥጦ ይቀራል።
ከእንግዲህ የሚሞኝ ከተገኘ በራሱ ፈረደ። ወደድንም ጠላንም፤የመዋሸት፤የማታለል፤የክህደት፤የጥፋት ጊዜ፤አብቅቷል። ሁሉም እርምጃውን ጠብቆ፤ጊዜውን ቆጥሮ ይመጣል። የተሰጋጀም ተዘጋጀ፤ የባከነም በከነ፤ጊዜው ሲደርስ እንደበሰበሰም ሆነ እንደ እንተዘመመ እንዳልነበረ ሲሆን፤ዞር ብሎ ትላንትን በመልከምም በሌላም መቃኘት አይቀርም። በተለያየ መልኩ፤ብዙ ዝምታ መስማማት ቢመስልም፤ከምዙ ዝምታ በሗል አበይት ክስተቶች ይኖራል። የሕዝብም ዝምታ ከዚሁ አይለይም። ዝም አለ ከተባለ ማለት ነው።

ብዙ ሳንርቅ፡ይህ ራእይ እየተባ ሲነገርለትና እንቀጥለው የሚባለው ምኑ ነው? ዲሞክራሲ ቢባል ዲሞከራሲ የለም፤ ነፃነት ቢባል፤ ነጻነት የለም፤መብት ቢባል መብት የለም፤እድገት ቢባል እድገት የለም-የሕዝቡ ኖሮ ምስክር ነውና፤እንደተባለውም “ምንም የለም”፤ሁሉም የለም። ታድያ እንቀጥል የሚባለው ምኑን ነው? በነበረው በአስ ጉልበት እንቀጥል ከሆነ፤የሆነው ለመቀጠል አያበቃም፤ቢመኙትም ከሕዝብ ፍላጎት ውጪ ነው። ፊት በሐይል በጡንቻ ነበር፤የማያስኬድ መንገድም አይደለም። ሃይልም ቢባል፤ የሃይል ምንጭና ሃይል የት እንዳለ ማስተዋል ያስልጋል።

ነገርን ቢደጋግሙት መሰለቻቸት ነው። እስኪ አበይት ነጥቦችን እንወርውር።

1. ያገር ክህደት የአገር መሸጥ ሌጋሲ፤

አገርን ወደብ አልባ እንዳላደረገ፤ያዋሳኝ ለም መሪትን ለጎራባች አገር አሳልፎ እንዳልሰጠ፤የአገሪቱን ለም መሬት በማን አለብኝነትና ቅን አስተሳሰብ በጎደለው የግድ የለሽ ውሎች፤ድሀ ገበሬን ከመኖሪያው ፈንቅሎ በርካሽ መቸብቸብ እድገትንም ልማትንም እደማያመጠ፤ ጅማሬውም ፍጻሜውም ግልጽ የሆነው፤ የክህደት፤የቅዠት ጉዞ ሊዘነጋ አይገባም። ባለ ራእዩ ያተረፈን የተዘጋች፤ለአምሳና ከዚህም በላይ ዓመታት የተሸጠች አገር ነች።

2. የታሪክ ክህደትና ማጉደፍ ሌጋሲ፤

ጠለቅ ያለ ዝርዝር ከመስጠት አንጥቦ ለማለፍ፤የዘመናትን ታሪክ ሽሮ ሚሊኒየም እንዳላከበር፤የጀግኖች ልጆችዋን ታሪግ በባዶ እብሪትና ትምክህት እንዳላንኳሰሰ፤ እንዳላጎደፈ፤እንቀጥል የሚባለው የጥፋት መንገድ ይህ ነው-ታሪክን መካድ መሻር ማንኳሰስ።

3. የአገር ብተና ሌጋሲ፤

አገርን በዘር፤በቋንቓ ሽንሽኖ ለትውልድ የማይሽር የጥፋት መረብ የዘረጋ ያስተዳደር ስልተ፤ፈጠነብ ዘገየ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ የጥፋት ቀመር ለመሆሉ በየጊዜው የታየ አሁንም እንደሰደድ እሳት በየአራት ማእዘን እየጤሰ ያለ፤የሚአስቀጥል ራእይ ወይስ የጥፋት ቅዠት?

4. የዘረፋ ሌጋሲ፤

በእድገት ጭራ፤በዘረፋ ከአለም ቀደምት፤ ከድሃ አፍ ነጥቆ በውጭ ባንኮች ሀብትን ማድለብ፤ በሺ ብር ደሞዝ የሚሊዮን ብር ህንዳ መገንባት፤ ከመንግስት ተበድሮ ሰይከፍሉ መበልጸግ፤ ከመንግስት ካዝና ወርቅ ብር በሚሊዮን የሙቆጠር መዝረፍ፤ መጋዘኖችን ወዘተ ባዶ ማድረግ፤ ያገሪቱን ኢኮኖሚ መቆጣጠር፤ የዜጎችን እጅ ማሰር፤ ስንቱ ይነገራል። ይህ ነው እንግዲህ የሚያስቀጥል ራእይ። እራስን መታዘብ ቢያቅት፤ ሌሎች እንደሚታዘቡ መገመት ምንኛ ብልህነት ነው። የለመደበትን እጅ ለመሰብሰብ ይበጅ ነበር። በቀደምት ስርአቶች ያልታየ። የህን በዚህ እንተወው።

5. የአፈና ሌጋሲ፤

ሕዝቡ፤የሕዝቡ ልጆች፤ ወጣቱ፤ምሁራኑ አፋቸው እንዳይናገር፤ ዓይናቸው እናዳያይ፤ብእራቸው እንዳይፅፍ፤ እዳይሰበሰቡ፤እንዳይደራጁ፤ለአገር እንዳይመክሩ፤ ለመብት ለነጻነታቸው እንዳይቆሙ፤ይህንንም ካደረጉ፤ በህግ ከለላና ህግ ከሚፈቅድላቸው ውጪ የግፍ ግፍ ሲዘንብባቸው ለመኖሩ በየፈርጁ የተመዘገበ፤በቂ ማስረጃና ሕያው ዋቢ ያለው የሚያስጠይቅ እየቀጠለ ያለ ሂደት መሆኑ ባጽንኦ መጤን አለበት። በዚህ መስክ የጥፋቱ ራእይ እንደቀጠለ መሆኑ አይካድም።

6. የጥፍጠፋ (Cloning) ሌጋሲ፤

የፖለቲካ ድርጅቶችን፤የሲቪክ ማህበራትን፤ የሀይማኖት ድርጅቶችን በየፈርጁ እያሰላ በመጠፍጠፍ፤ሁሉንም በመልኩ ቀርጾ ሕዝብን በገዛ አገሩ፤በቤቱ፤በእምነቱና በባህሉ ባእድ ያደረገ የጥፋት መንገድ ከእርሱ ለእነነርሱ ራእይ እውነታው ግን የቅዠት መንገድ ነው።

7. የድምጽ መስረቅ ሌጋሲ፤

መዝግቦ ለማለፍ፤ለማስታወስ ካልሆነ በቀር፤ አይን ያወጣ የሕዝብ ድምጽ በቀትር ጠራራ ጸሀይ ሰለባ ሲካሄድ፤ደግሞ ተደጋግሞ ይባስ ብሉ በ99.6% ነጥብ አሸንፈናል ለማለት የበቃ፤እዚህ ላይ እየተሰረቀ ያለው የሕዝብ ድምጽ ሕዝብ ከነሕይወቱ መሆኑን ነው። ይህ ለእነርሱ የዲሞከራሲ ሌጋሲ ለእኛ ግን የሕዝብ ድምጽ በጠራራ ጸሀይ ሕዝብን ከነነፍሱ መዝረፍ ነው። ይህችም ፊደል በምትነጥብበት ወቅት እንኳ የሕዝም ድምጽ ለማፈን ለመዝረፍ ደባው እየቀጠለ ነው። ወይ ራእይ!

8. የአምባገነንንት ሌጋሲ፤

ከላይ በታያያዘ መልኩ፤ለሓያ አመታት፤አንድ ጊዜ ባለ ሙሉ ባለስልጣን ፕሬዘዳንት፤ በሚቀጥለው ጊዜ ባለ ሙኑ ስልጣን ጠቅናይ ሚኒስቴር፤ ሌለው እነዚህን የስልጣን እርከኖች ሲጨብጥ ባዶ እያደረገ የዘለቀ የሃያ አመት መሰሪ ላጠፋው ጥፋት ለፍርድ ሳይቀርብ ለማለፉ ለእነርሱ የመልካም አስተዳደር ራእይ፤ሌጋሲ ለታሪክ ግን አምባከነን የመሆኑን እውነታ ማሰቀመጥ ያስፍልጋል።

9. የውሸት የሀሰት የትእቢት ሌጋሲ፤

የሆነውን አልሆነም፤ያልሆነውን እንደሆኗል፤የነበረውን አልነበረም ያልነበረውን ነበር እይተባለ አይንን በጨው ያጠበ ነጭ ውሸት፤ፈሩን የሳተ የፐሮፐጋንዳ ዘመቻ ሲደለቅ አመታት ለማለፋቸው ሕዝቡ ከእነርሱ አንደበት የሚወጣው እንደማይጥመውና ጆሮውን እንደነፈጋቸው፤በልቡ ከእነርሱ እንደራቀ፤እንደካዳቸው፤ጊዜንና አጋጣሚን እየጠበቀ አንዳላ ከነርሱው አንደበት “የተቀመጥንብተ ወንበር የዛፍ ላይ እንቅልፍ” ሆነብን እስከሚሉ፤በእውነትም ራእይ ሳይሆን ቅዠት ላይ እንደጣላቸው፤ይህንንም ቅዘት ራእይ ብለው ሊመክሩ እደተነሱ አራሳቸውም አልዘነጉትም። ራእይና ቅዠት አንደ እይደሉም። ሲያንቀላፉ ከሳፉም መውደቅ። የውሸትና የትእቢተኝነት ሌጋሲ።

10. የዘር ማጥፋት ሌጋሲ፤

በአገሪቱ ለብዙ ጊዜ ባራቱም ማእዘናት፤ዘርን መሰረተ ያደረገ የጥፋት ዘመቻ የንጹሀን ደም በከንቱ ለጥቅም ለስልጣን ሲባል ሲፈስና ሲማገድ እንደነበር፤አሁንም በቅርቡ ድሀ ተገን የሌላቸው ዜጎች እየተማገዱ በየጥሻው እየተጣሉ እንዳሉ መዘንጋት አያሰፈልግም። የጥፋት ዘመቻው ለእነርሱ የሚቀጥል ራአይና ሌጋሲ ለዜጎች የሞት ሽረት ጉዳይ ሆኗል። ገበያ ባልወጣሽ የሚሉሽን ባልሰማሽ አሉ።

11. የትውልድ አፍራሽ፤የተበከለ ባህል ሌጋሲ፤

የዜሬው ትውልድ እዳለ ሆኖ የነገው ትውልድ የትምህርት፤የጤና፤የማህመራዊ ፤የእምለት ባጠቃላይ ተስፋው ጨልሞ፤ለአደገኛ ባህሎች፤ልምዶች ታጋልጦ፤በስራአጥነት ተጠምዶ በያለብት ወድቆ የወገን ያለህ፤የአገር ያለህ ሲል እንደሚታይ ሊደበቅ በማይይቻል መልኩ በያደባባዩ ተሰጥቶ ያለ እውለታ ነው። ካሁን በፊት የልነበሩ ያለተለመዱ የጥፋት ልምዶች፤ትውልድ አምካኝ ሂደቶች እንዳሽን እየፈሉ ለመሆናቸው እራሳቸው የማይክዱት፤ባለ ሌጋሲ የሚባለው መሰሪ ላገር ለትውልድ ያተረፈው የጥፋት ቅዠት ነው።

12. የአገርን ጥቅም አሳልፎ የመስጠት ሌጋሲ፤

ሞኝ እነደላኩት ነው ይሏል። እንዳዘዙት፤እንደሰደዱት፤የአገርን ሳይሆን የባእድን ጥቅም በማስቀደም፤ሲፈልግም በሪሞት ኮንትሮል የምንንቀሳቀስ የበናና ሪፑብሊክ አይደለንም እያለ፤ሲያሻው ሳንቲም ከእነርሱ አላገኘንም እያለ ሲሸመጥጥ በያለበት ወጣቱን እያስማገደ፤የወገንን ጉዳት ደብቆ፤ምስኪኑን በረሀ በልቶት እነደቀረ ለእነርሱ የሚቀጥል ሌጋሲ ለወገን ለአገር ግን የክህደት፤የአገርን ጥቅም መሸት ወንጀል ነው። ይህ ነው እንግዲህ እንቀጥል የሚባለው ቅዠት።

13. ኪራይ ሰብሳሚነትና የሞኖፖሊ ሌጋሲ፤

አገሪቱን በየፈርጁ -የፖለቲካ የኢኮኖሚ፤የመከላከያ፤የሰኩሪቲ፤የሲቪክና የእምንተ አውታሮችን ተቆጣጥሮ፤እኒህን በመመርኮስ ሊቃና ወደማይችል የኪራይ ሰብሳም የጥቅም ማጋበሻ ስርአት መስርቶ እንቀጥል፤በዚሁ ይቀጥል የሚለው ከንቱ ምኞት የሗላ ሗላ በእራስ ላይ መፍረድ መሆኑ ማታውቅ ይኖርበታል። ሕዝብ ኪራይ ሰብሳቢ ቢሉት፤ የቤት ኪራይ የመሬት ኪራይ እንዲመስለው በሚያሰለች መልኩ ሲደጋጋም ቢሰማም፤ሚስጥሩ የመንግስት ስልጣንን በመጠወም ሀብ ከማግበስብስ፤ሌላው ስርቶ እንዳይጠቀም በስልጣን ሀይል ማገድ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ስርአቱ የተመቻቸው ለምዝበራ-ሊቃናም የማይችል የጥፋት ራእይ-ቅዠት ነው።

14. የተዋረደ ኢኮኖሚ ሌጋሲ፤

በዚሁ ሂደት በእድገት ጭራ፤በዝርፊያ ቀዳሜ፤ባሳቻ ቀመር አንደኝነትን የያዘ ስርአት ለመሆኑ ብዙ መዘርዘር አያስፈልግም። ስንቱ ብለቶ ጠጥቶ የድራል፤የስንቱ መሰረታዊ ፍላጎቶች ተሟሉ፤አምራች ዜጋና ምርት የትና የት ናቸው፤ማን ምንነ ይቆጣጠራል፤ማን አደገ ተመነደገ፤ማንስ ድሃ ሆነ ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ እዛው ፈላ እዛው ሞላ፤ እኔን ከደላኝ እድገት ይህች ናት ነው። እነርሱ ሲበሉ ሕዝብ የጠገበ ይመስል፤ብዙሀኑ እንደትላንቱ መከራቸውን እየገፉ ነው።

ታዲያ፤ላገር ለወገን መልካም እንደሰራ፤እያፈነ፤እያደናቆረ በሕይወቱ በቁሙ በደነዘ ካራ አንገቱን ሲገዘግዘው የነበረን፤ይተደራረበ ወንጀለኛ፤መልከም እንዳደረገ፤የሕዝብ ገዳይ፤የአገር ሻጭ፤የታሪክ ነቀዝ፤በተንኮል መበመሰሪነት የተጠመደን መጥፎ ከሀዲ፤መዘዙ ለትውልድ የሚዘልቅን የጥፋት መልእክተኛ፤ባለራእይ፤ባለሌጋሲ አድርጎ በጥፋት መስመሩ እንቀጥል ማልት፤በቀላሉ፤ሰው የለንም፤ እስካሁን እርሱ ነበረ አበቃልን፤የተንኮል ምንጫችን ደረቀጭ መንገዳችንን እንፈልግ፤ ከእንግዲህ የሚሰማን የለም ቢሉ ይቀላል። በሌላ በኩል ደግሞ አስበው መሥራት አለመቻልን በራሰ የመተማመን ጉድለትን ያሳያል፤ዱሮስ።

የለፈውም አለፈ-ግልግል፤አዲሱም ታየ-ለውጥ የለውም። ሁሉም ለትምህርት ይሁን። መንገድ መንገድ መንገድ።

ቋያ ቋያ ጢሱ እየጢያጤሰብሽ፤
ዳሩ መሃል ሆኖ እሳቱ ሳይበላሽ፤
አገሬ ተነሼ ሌላም መንገድ የለሽ።

ቸር ያሰንብትልን!

ecadf.com

የ“ዝም በል ዳያስፖራ” – አዋጅ፦ ከቤተ መንግሥት እስከ ቤተ እምነት

ኤፍሬም እሸቴ/Adebabay

በዚህ ሰሞን መቼም ከእግር ኳስ ውጪ ማውራት በሕማማት ስለ ቁርጥና ጥብስ እንደማውራት ሳይቆጠር አይቀርም። እኔም ብሆን ስለ እግር ኳሱ ማውራቱን መች ጠልቼው። በርግጥ ይኼ ሁሉ ወፈ ሰማይ የስፖርት ተንታኝ በየኤፍ.ኤሙ ሲተችበት በሚውለው የተጫዋቾቻችን ብቃት፣ ጥራት፣ የኳስ ጥበብ፣ የሽልማት ዓይነት፤ የተጋጣሚዎቻችን ሁኔታ፣ የተጫዋቾቻቸው ዝና፣ ማን ከየትና ከየትኛው ክለብ እንደመጣ፣ አሰላለፋቸው እና ከኢትዮጵያ ጋር ሲገጥሙ ሊኖራቸው ስለሚችለው አያያዝ ለመተንተን ሙያውም መረጃውም የለኝም። (“ችሎታ የለኝም” አለማለቴ ይሰመርበት። ማን ይሞታል። መቸም “አልችልም” ማለት ጎጂ ባህል ሆኗል።) ቢያንስ የእንጀራ አገሮቻችን አሜሪካ እና ስዊዲን ስላፈሯቸው እና ለእናት አገራችን ኢትዮጵያ ስላበረከቷቸው ተጫዋቾቻችን መወያየት ይቻላል።ምን ይሆን ሚሰጥሩ ስንጥቅ የሚያረገኝ፡

ኢትዮጵያውያን እንደ ጨው በመላው ዓለም ተበትነዋል። በብዙ ቦታዎች አንድ ትውልድ አልፎ ሁለተኛ ትውልድ ላይ ደርሷል። በቅርብ ከሚገኙት ኬንያና ሱዳን እስከ አረብ አገሮች፣ ከምዕራብ አውሮፓና ስካንዲኔቪያን አገሮች እስከ አሜሪካና አውስትራሊያ ድረስ ብዙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ። ከእነርሱ መካከል የአሜሪካ ሜኔሶታው ፉአድ ኢብራሒም እና የስዊዲኑ ዩሱፍ ሳላህ ተገኝተዋል። ፉአድ ኢትዮጵያ ተወልዶ አሜሪካ ያደገ፤ ዩሱፍ ደግሞ እዛው ስዊዲን ተወልዶ እዛው ያደገ እግር ኳስ ተጫዋች ነው። የብዙ ኢትዮጵያውያን የኋላ ማንነት ማሳይ ሊሆኑ የሚችሉ ልጆች ናቸው። አድገውና ለቁም ነገር ደርሰው አገራቸውን ለመወከል መብቃታቸው ደስ ይላል። “አለ ገና፣ ገና፣ አለ ገና” እንላለን።

ጣዕመ-ኢትዮጵያ፣ ባህለ-ኢትዮጵያ በቀዘቀዘባቸው ባህሎች መካከል አድገው በመጨረሻ አገራቸውን ለመወከል መቻላቸው ትልቅ ነገር ነው። ስለ ፉአድ ያነበብኩት አንድ ጽሑፍ ይህ ወጣት ለአሜሪካ እግር ኳስ ቡድን (ከ17 ዓመት በታች እንዲሁም ከ21 ዓመት ላሉት) ቢጫወትም የማታ ማታ ግን አገሩን ለመወከልና የአገሩን ማሊያ ለመልበስ መወሰኑን ያትታል። ስዊዲን እነ ኢብራሒሞቪችን (በአባቱ ቦስንያዊ) እና ታዋቂው ሔንሪክ ላርሰንን (አባቱ ከኬፕቬርዴ ናቸው) የመሳሰሉ ተጫዋቾችን በማሰለፏ እናውቃታለን። ዩሱፍም ተመሳሳይ በሆነ መልክ ተመሳሳይ ዕድል ሊያገኝ እንደሚችል እገምታለኹ። ነገር ግን ያንን ትቶ የአገሩን መለያ ለብሷል።

ዳያስጶራው ለረዥም ዓመታት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ወደ አገሩ በመላክ አገሩን በቀጥታም በተዘዋዋሪም ሲደግፍ ቆይቷል። በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከዳያስጶራው የሚገኘው ገቢ አገሪቱ ከወጪ ንግድ ከምታገኘው በእጅጉ እንደሚበልጥ የዓለም ባንክ ጥናቶች በተደጋጋሚ አሳይተውናል። ከዚህ የቀጥታ ገንዘብ ርዳታ ባሻገር ትውልደ-ኢትዮጵያዊው በአገሪቱ አጠቃላይ ሕይወት ላይ በጎ ሱታፌ ማሳየቱ አገሩን ለሚወድ ወገን ሁሉ ትልቅ ተስፋ ነው። ዩሱፍና ፉአድ ለዚህ መልካም አብነቶች ይሆናሉ።

ዩሱፍና ፉአድ ወደ አገራቸው ሲመለሱ በዚያው መጠን ብዙ ኢትዮጵያውያን ወደ ዳያስጶራነት ጎራ እየተቀላቀሉ ነው። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በዋሺንግተን ዲሲ የተደረገ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ሐኪሞች ማኅበር ስብሰባ ተገልጿል እንደተባለው በአሁን ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ዶክተሮች ይልቅ በውጪ የሚገኙት ቁጥር ይበልጣል። አዝማሚያውን ስንመለከተው ይኸው የዕውቀትና የአዕምሮ ስደት እንደሚቀጥል እርግጥ ነው። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ዋስትና ማጣት እና ፖለቲካዊ ነጻነት አለመኖር ነው። ከኢኮኖሚው በበለጠ ፖለቲካዊ ጫናው ለብዙው ወገናችን መሰደድ ምክንያት ነው የሚለው የብዙዎች እምነት ነው። በፖለቲካዊ ምክንያቶች የተሰደዱት ደግሞ በየወጡበት አገር ባላቸው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን መንግሥት ዘወትር መክሰስ ቀጥለዋል። በቅርቡም ይቆማል ተብሎ አይጠበቅም። ይህም ፉአድንና ዩሱፍን የመሳሰሉ ትልውደ ኢትዮጵያውያን በየሙያቸው ትውልድ አገራቸውን እንዳያገለግሉ እንቅፋት ይሆናል። በአገሪቱ ያለው የሰብዓዊ መብት ገፈፋ ሲሻሻል ዳያስጶራውም ተጠቃሚ ይሆናል። ዳያስጶራውን በጥቅማጥቅም ማባበል መጠነኛ ደጋፊ ያስገኛል፤ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት መጠበቅና ሕገ መንግሥቱን ማክበር ግን ሙሉ ድጋፍ ያስገኛል።

ዳያስጶራው በየሚኖርበት አገር የሚተነፍሰው ፖለቲካዊ፣ ኅሊናዊ፣ አካላዊ እና ሰብዓዊ ነጻነት ይኸው ነጻነት በአገሩ እንዲኖር በጎ ምኞት ይቀሰቅስበታል። ስለዚህ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በአገሩ ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ይኮንናል፤ ተጽዕኖ ለመፍጠርም የማይወጣው ዳገት የማይወርደው ቁልቁለት የለም። ይህም የተለያየ አመለካከት መፍጠሩ አይቀርም። ዳጳስጶራው “አክራሪ ነው” ከሚለው ጀምሮ “የአገሩን ነባራዊ ሁኔታ የማያውቅ” እንዲሁም “50 ዶላር ልኮ አገር ውስጥ ያለው ወጣት እንዲማገድ ይፈልጋል” ወዘተ ተብሎ ይቀርባል።

ሐሳቡ ቀደም ብሎ በመንግሥት ብቻ ተደጋግሞ ሲገለጽ የቆየ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ተርታ ዜጎችም በማኅበራዊ ድረ ገጾቻቸው ሲያስተጋቡት ይስተዋላል። በአጭር አባባል ለማቅረብ “ዳያስጶራ ዝም በል” ወይም “ዝም እንዲል አድርጉት” የሚል አዋጅ የተነገረ ይመስላል።

በመጀመሪያ ደረጃ አንድን ዜጋ ከአገሩ ርቆ በመኖሩ ስለ አገሩ ያለውን ሐሳብ፣ በመንግሥቱ ላይ የሚኖረውን ቅዋሜ እና ለችግሮች የሚኖረውን መፍትሔ ከማቅረብ ሊከለክለው የሚችል ሕግ የለም። ስለ አገርህ ለመናገር በአገርህ መሬት መኖር አለብህ የሚል “የቀበሌ ትእዛዝ” የመሰለ ሐሳብ ውኃ አያነሣም። ነቢዩ ዳዊት ስለ ኢየሩሳሌም ሲናገር “ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” እንዳለው “እመሰ ረሳዕኩኪ ኢትዮጵያ  ለትርስዐኒ  የማንየ፣ ኢትዮጵያ ሆይ ብረሳኝ ቀኜ ትርሳኝ” የሚሉ ኢትዮጵያውያንን ‘እኮ ምን አግብቷችሁ’ ማለት ከስድብ ይልቅ ያማል።

ዛሬ ባንኖርባት ተወልደንባት አድገንባታል፤ ዘር ማንዘሮቻችን ኖረው አልፈውባታል። ክቡር አጥንታቸው ረግፎባታል። በየወቅቱ በሚመጣና በሚሄድ ሥልጣን የአንድ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱ አይገመገምም። ኢትዮጵያዊነትን ማንም ባለሥልጣን አልሰጠንም፣ ማንምም አይነፍገንም። ከደርቡሽና ቱርክ፣ ጣሊያንና ግብጽ፣ ከሌሎችም ድንበር ገፊዎች ሲታገሉ በወደቁ ወገኖቻችን የቆመ ዜግነት እንጂ እንጀራ ፍለጋ፣ ነጻነት ፍለጋ እንደምንኖርባቸው አገሮች በወረቀት ብቻ የሚረጋገጥ አይደለም። ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከወረቀት እና ከፖለቲካ ወገንተኝነት እንዲሁም ከየብሔረሰባዊ ማንነታችን በላይ ነው።

በሌላም በኩል ካየነው ስለ ሰብዓዊ መብት ለመናገር የግድ የዚያ አገር ዜጋ መሆን፣ በዚያ አገር መኖርም አይጠይቅም። ሰብዓዊ መብቱ እንዲጠበቅለት የሚፈልግ ማንም ሰው የሌላው ሰው መብት ሲጣስ አይደሰትም። ሌላው ሁሉ ታሪካዊ ሐተታ እንኳን ቢቀር በቅርቡ ዘመን የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት ከኛ ሚሊሻ ጋር አብረው የተዋደቁልንን ኩባውያንን  መስዋዕትነት እንደምናከብረው፣ ዕድሜ ዘመናቸውን በሴቶች (ፊስቱላ) ሕክምና ረገድ አገራችንን የጠቀሙትን ሐኪሞች እንደምናመሰግነው ሁሉ ለዜጎቻችን ሰብዓዊ መብት የሚከራከሩትንም በዚሁ መነጽር ልንመለከታቸው ይገባል።

በተጨማሪም የመንግሥትን አሠራር ማሔስ አገርን መተቸት አይደለም። መንግሥት የአገር መሪ እንጂ አገር አይደለም። ፓርቲና መንግሥትነት ከዘር ጋር በመቆራኘታቸው ፓርቲውን መተቸት የመጣበትን ዘር እንደመውቀስ ተደርጎ መቆጠሩም ትልቅ ስሕተት ነው። ፓርቲዎች በዓላማቸውና በአሠራራቸው መነቀስና መተቸት ግዴታቸው ስለሆነና በዘር ላይ የተመሠረተ የፓርቲ አወቃቀር እስካለ ድረስ ከፓርቲው ጀርባ ያለው ዘር ወቀሳው ለርሱ የተወረወረ አለመሆኑን ለመረዳት ብዙ ጥበብ አያስፈልገውም።

እንኳን የኢትዮጵያ መንግሥት በዲሞክራሲያዊነታቸው ወደር የማይገኝላቸው አገሮች የየጊዜው መንግሥታት ሳይቀሩ ከትችት አያመልጡም። ትችት መንግሥታቱን ከዓምባገነንነት የሚያተርፋቸው ፍቱን መድኃኒት ነው። ተቃዋሚዎችን፣ ፕሬሶችን፣ ጥቃቅን ስብስቦችን ሁሉ በመዋጥና በዓይነ ቁራኛ በመመልከት፣ ትችትን ሳይሆን ተቺውን በማፈን ጥሩ መንግሥት መሆን አይቻልም። “ልማት ላይ ነን አትንኩን” የሚል ፈሊጥ ወንዝ አያሻግርም። ጥያቄው ግድቡና ሕንጻው ላይ አይደለም። የዜጎችን ሰብዓዊ ሕንጻ እያፈረሱ የድንጋይ ሕንጻ እንሠራለን ማለት አይቻልም። ከግዑዝ ሕንጻ ሰብዓዊ ዜጋ ይቀድማል፤ከግድብ ግንባታም መብት ይቀድማል።

በውጪ የሚገኘው ዜጋ የአገሩን ሁኔታ በትኩረት ለመከታተል ቴክኖሎጂው ትልቅ ዕድል ይሰጠዋል። አራት ኪሎ የተፈጠረው አቃቂ፣ አንዱ ክፍለ ሀገር የተሠራው ሌላው ሳይረዳው ሳይሰማ፤ እረኛና አዝማሪ እንኳን ለዘፈኑና እንጉርጉሮው በራሱ ላይ ግላዊ-ሴንሰርሺፕ በጣለበት ዘመን፣ ከአንድ አፍ በሚወጣ ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚና ቁጥጥር የተደረገበት ወሬ አገር በሚተዳደርበት ጊዜ፣ አለመስማትን እና አለማወቅን (መንግሥታዊ የመረጃ ግርዶሽን) መታገል ሲገባ የሰማውንና ያወቀውን “እኮ ማን ስማ አለህ” ማለት አያዋጣም። ይህንን የሚለው አካል ነገሩ እንዳይሰማበት የፈለገው እንጂ ተጎጂው አለመሆኑም በቅጡ ይታወቃል።

ዳያስጶራውን አምርሮ የመጥላት እና በጅምላ ክፉ ስም የመስጠት ተደጋጋሚ ሙከራ ፍሬ ማፍራቱን ለማወቅ ተርታ ግለሰቦች እና ቤተ እምነቶች ሳይቀር ማንጸባረቅ የጀመሩትን ተመሳሳይ አመለካከት መመልከት ይገባል። የግለሰቦቹን እንኳን ለጊዜው ብናቆየው የአንዳንድ ቤተ እምነት አስተዳደሮችና መሪዎች ከውጪ የሚመጣላቸውን የአማኛቸውን ሐሳብ፣ ልክ እንደ መንግሥት፣ “አፍራሽ፣ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጥያቄ” አድርገው ሲመለከቱት ማየት እየተለመደ መጥቷል። ‘አጋጣሚ ነው ወይስ የተላለፈ አዋጅ አለ?’ የሚያሰኝ ነው። የቤተ እምነት መሪዎች ሰማያዊውን መንግሥት መጠበቅ ትተው ምድራዊውን መንግሥት ለመጠበቅ ደፋ ቀና ሲሉ እነርሱን የሚከተላቸው ምእመን እንደሚመለከታቸው እንኳን ይዘነጉታል። እነርሱም ከምድራዊው ባለ ጉልበት ጋር ተደርበው “ውጪ ያላችሁት ዝም በሉልን፣ እንደፈቀድን እንሁን” ሲሉ አዋጃቸውንም በደህና ጊዜ የሚናገሩትንም ሰማያዊ ቃል የሚሰማቸው ጆሮ ያጣሉ። በርግጠኝነት ግን ማንም ዝም አይልም።

መልካም ዕድል ለብሔራዊ ቡድናችን!!!!

 ይቆየን – ያቆየን

ecadf.com

መነቀል ያለበት ስር የሰደደ የወያኔ ዘረኝነት

የግንቦት 7 ንቅናቄ

ዘረኛዉ የወያኔ ስርአት የኢትዮጵያን ህዝብ ለጥቂት አመታት ኢትዮጵያዊያንን ባሰረና በገደለ ቁጥር ገንዘብ የሚሰጡትን አለም አቀፍ ድርጅቶችና አርዳታ ሰጪ አገሮች ደግሞ 21 አመት ሙሉ ካታለለበት መንገድ አንዱ የፌዴራል ስርአት መስርቼ ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር አደረኳት የሚለዉ ባዶ አባባሉ ነዉ። ይህንን ተጋልጦ እርቃኑን የቀረ አባባል የኢትዮጵያ ህዝብ ተገንዝቦ ወያኔን መታገል ከጀመረ ቆይቷል፤ ዋና ዋናዎቹ እርዳታ ለጋሾችም ቢሆኑ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ግድ የሌለዉ ወያኔ ወጣቶቻችንን እየገበረ ጥቅማቸዉን ስለሚያስከብርላቸዉ ነዉ እንጂ ወያኔ እንኳን እየደገፉ እርዳታ የሚሰጡት በአንድ ተርታም አብረዉ ለመቀመጥ የማይመች የእኩዮች ስብስብ እንደሆነ ካወቁ ቆይቷል።

ህወሀት በፌዴራል ስርአቱ ዉስጥ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት ነዉ ብሎ በሚጠራዉ ፓርላማ ዉስጥ ያለዉ መቀመጫ 8 ብቻ ነዉ። እዚህ ፓርላማ ዉስጥ የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ የሚለዉ ህወሀት ነዉ፤ ትግራይ ደግሞ ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ክልል ናት። የተቀሩት 8 ክልሎች በዚህ የእኩልነት ምልክት በሆነዉ ፓርላማ ዉስጥ ያላቸዉ የመቀመጫ ብዛት 569 ነዉ። ሆኖም በወያኔ መንደር የፖለቲካ ስልጣን ምንጭ ህዝብ ሳይሆን ጠመንጃ ነዉና ወያኔ ፓርላማዉ  ዉስጥ 8 ወንበር ብቻ ይዞ 569 ወንበር ያላቸዉን የኦሮሚያን፤ የአማራን፤ የደቡብ ክልልንና የተቀሩትን አምስት ክልሎች እንደ መኪና ይነዳቸዋል። የየክልሉን መሪ ይሾማል፤ ይሽራል ወይም የማይስማማዉን የክልል ባለስልጣን ያስራል። ፓርላማዉ ዉስጥ አንድ መቶ ሰባ ስምንት፤ አንድ መቶ ሰላሳ ስምንትና አንድ መቶ ሀያ ሦስት መቀመጫ ያላቸዉ የኦሮሚያ፤ የአማራና የደቡብ ክልል ፓርቲዎች በራሳቸዉ ጉልበትም ሆነ ህልዉና ስለሌላቸዉ አንዱ ከሌላዉ የበለጠ ስልጣን ወይም ሹመት ለማግኘት አንጋጥጠዉ ወደ ላይ የሚመለከቱት ህወሀትን ነዉ።

ለመሆኑ ወያኔ የፌዴራል ስርዐት መስርቼ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት አረጋገጥኩ ሲል ምን ማለቱ ነዉ? እኩልነቱ የፖለቲካ ነዉ  የኤኮኖሚ? ወይስ በየአመቱ ህዳር ወር ላይ የፌዴራልዝም ቀን ሲከበር እንደምናየዉ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠዉ በዘፈን ብቻ ነዉ? የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስርዐት ከላይና ከታች የሚቆጣጠረዉና ይህንኑ የፖለቲካ ስርአት የሚደግፍ የኤኮኖሚ መዋቅር ዘርግቶ የአገራችንን ኃብት የሚቦጠብጠዉ ህወሀት ብቻ ነዉና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ተረጋገጠ የሚባለዉ አባባል ከተራ የቃላት ድርደራ ዉጭ ሌላ ምንም ትርጉም የለዉም።

አፄ ቴዎድሮስን እንደ ልጅነት ሞዴሉ የሚመለከተዉ ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም የመጀመሪያዉን የኢትዮጰያ ዘመናዊ ወታደራዊ እንጂኔሪንግ ተቋም ሲመሰርት ስሙን “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ ነበር የሰየመዉ። ስያሜዉ የአፄ ቴዎድሮስ ስራና ስም ህያዉ ሆኖ እንዲኖር ለማድረግ የተደረገ ሙከራ እንደነበር ግልጽ ነዉ። የኢትዮጵያን የቀድሞ መሪዎች በጅምላ የሚዘልፈዉ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ከአንዲት የአገር ዉስጥ ጋዜጠኛ ጋር ባደረገዉ ቃለ ምልልስ አፄ ቴዎድሮስ ጋፋት ላይ ያሰሩትን መድፍና መንግስቱ ኃ/ማሪያም “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ  የሰየመዉን ወታራዊ ተቋም አስመልክቶ ሁለቱንም መሪዎች ሲያንቋሽሽ ተደምጧል። የሚገርመዉ ዛሬ ወያኔ የብረታብረት እንጂኔሪንግ ኮረፓሬሺን ብሎ የሚጠራዉ ግዙፍ የሲቪልና ወታደራዊ እንዱስትሪ ተቋምና በዚህ ተቋም ዉስጥ የሚገኙ ዋና ዋና ፋብሪካዎች ደርግ  “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ የጀመራቸዉ የከባድ እንዱስትሪ ጅምሮች ናቸዉ። በ1970ዎቹ አጋማሽ ላይ “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ስራዉን ሲጀምር የፋብሪካዉ ሀላፊዎች፤ እንጂኔሮች፤ የመምሪያ ሀላፊዎችና ቴክኒሺያኖች የስራ ዕድል የሚያኙት የትምህርት ደረጃቸዉ፤ ችሎታቸዉና የሰራ ልምዳቸዉ ብቻ እየታየ ነበር፤ ወይም ትግርኛ ስለተናገረ ስራ የሚከለከል አማርኛ፤ ኦሮምኛ ወይም ሌላ ቋንቋ ስለተናገረ አድሎ የሚደረግለት ዜጋ አልነበረም። ዛሬ ወያኔ ከደርግ ስርአት ተረክቦ የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ብሎ በሰየመዉ እንዱስትሪ ዉስጥ አብዛኛዉን የሀላፊነት ቦታ የያዙ ሰዎች ለቦታዉ የበቁት በስራ ልምዳቸዉና ችሎታቸዉ ሳይሆን የተወለዱበት ዘርና የሚናገሩት ቋንቋ እየታየ ነዉ። ወታራዊዉ አምባገነን ደርግም ሆነ  ወያኔ ይህንን እንዱስትሪ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ከባድ እንዱስትሪ ዘርፍ መሰረት ይሆናል የሚል ራዕይ ነበራቸዉ። ልዩነታቸዉ የእንዱስትሪዉ አስፈላጊነት ላይ ሳይሆን እንዱስትሪዉን ማን ይቆጣጠረዋል የሚለዉ ጥያቄ ላይ ነዉ። ደርግ በሱ መሪነት ለማንም ችሎታ ላለዉ ኢትዮጵያዊ የእንዱስትሪዉን በር የከፈተ ሲሆን ወያኔ ግን እንዱስትሪዉ እንዳለ በአንድ ዘር ቁጥጥር ስር እንዲገባ አድርጓል።  ደርግም ወያኔም አምባገነኖች ስለሆኑ አንዱስትሪዉን ከህዝብ ቁጥጥር ዉጭ አድርገዉታል፤ ወያኔ ግን ከአምባገነንም የጎሳ አምባገነን ስለሆነ ይህንን ትልቅ እንዱስትሪ ሙሉ በሙሉ በትግርኛ ተናጋሪዎች ቁጥጥር ስር አድርጎታል።

ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ባለለፉት ሦስት አመታት ይህንን ወያኔ ገነባሁ የሚለዉን የፌዴራል ስርአትና በስርአቱ ዉስጥ የተለያዪ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሚጫወቱትን ሚና በመረጃ አስደግፎ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ አቅርቧል። የዛሬ ሁለት አመት ግንቦት ሰባት በኢትዮጵያ መላከያ ሰራዊት ዉስጥ የተዘረጋዉን የወያኔ የዘረኝነት መረብ ከሰሞኑ ደግሞ የኢትዮቴሌኮምን የዘረኝነት አደረጃጀት በመረጃ በማስደገፍ ለህዝብ ማቅረቡ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮረፓሬሺንን የዘረኝነት አደረጃጀትና በዚህ አደረጃጀት ዉስጥ ማን ምን እንደሆነ ያጣናዉን የጥናት ዉጤት በመረጃ አስደግፎ ያቀርባል።  ግንቦት ሰባት ሃያ አራት ሰአት ሙሉ የሚከታተሉትን የወያኔ የደህንነት ሰራተኞች ከበባ ጥሶ የወያኔን ዘረኝነት የሚያጋልጡ መረጃዎችን ከራሱ ከወያኔ ጓዳ እየጎተተ አዉጥቶ ለህዝብ የሚያቀርበዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን ዘረኝነት አያውቀዉም በሚል አስተሳሰብ አይደለም። ግንቦት ሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ የፈጠረዉ ከፍተኛ የመረጃ ጉድለት አለ ብሎ ያምናል፤ስለሆነም ህዝቡ የወያኔን ዘረኝነት ቢረዳም መጠኑን፤ስፋቱንና ጥልቀቱን በሚገባ ላያዉቅ ይችላል ብለን እናምናለን። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በየቀኑ ደሙን እንደ መዥገር የሚመጠዉን ወያኔን የመሰለ የጀርባ ላይ አጥንት ተሸክሞ መኖር የለበትም ብለን ስለምናምን ህዝብን ለትግል ከምናዘጋጅበትና ከምናነሳሳባቸዉ መንዶች ዉስጥ አንዱ እንደዚህ ህዝብ በገዛ አገሩ “እኩል አደረግንህ” ብለዉ በሚነግሩት ከሀዲዎች ቅኝ አገዛዝ እየተገዛ መሆኑን በማሳወቅ ነዉ።

ባለፈዉ ሳምንት የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ዋና ዳይረክተር ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘዉ ፓርላማ ዉስጥ ተገኝቶ የኮርፓሬሺኑን የሁለት አመት የስራ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ኮርፓሬሺኑ የግል ባለኃብቶችን አያሳትፍም እንዳዉም እያቀጨጫቸዉ ነዉ፤ ለሙስና የተጋለጠ ነዉ፤ ደግሞም አብዛኛዉ የኮርፖሬሺኑ ሰራተኛ የመከላከያ ሰራዊት አባል ነዉና ይህ አሰራር  ሠራተኞችን ለማስተዳደር አስቸጋሪ አይሆንም ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዉለት ነበር። የግሉን ዘርፍ መቅጨጭ በተመለከተ ኢትዮጵያ ዉስጥ ቀድሞዉንም ቢሆን “የወያኔ ዘርፍ” እንጂ የግል ዘርፍ የሚባል ነገር የለምና ጥያቄዉ መቅረብም አልነበረበትም።  ሙስናም ቢሆን የወያኔ ስርዐት ዋናዉ መገለጫ ባህሪይ ስለሆነ ወያኔ እስካልተወገደ ድረስ ሙስና  “ሙስናን እናጠፋለን” ስለተባለ ብቻ የሚጠፋ ነገር አይደለም። ግንቦት ሰባትን እጅግ በጣም ያሳዘነዉና ያስገረመዉ ነገር ያንን ወያኔ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት ነዉ ብሎ የሚናገርለትን ፓርላማ ያስጨነቀዉ (ተጨንቆ ከሆነ) የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን በአንድ አናሳ ብሔረሰብ ሙሉ ቁጥጥር ስር መዉደቁ ሳይሆን አብዛኛዉ የኮርፖሬሺኑ ሰራተኞች የመከላከያ ሰራዊት አባላት መሆናቸዉ ነዉ። በእርግጥ የአንድ ትልቅ ኮርፖሬሺን ሰራተኞች በአብዛኛዉ  የጦር ሠራዊት አባላት ሲሆኑ የአሰራርና የአስተዳደር ችግር መፈጠሩ አይቀርም፤ ሆኖም የሠራዊቱ ታማኝነት  ለህዝብ ታዛዥነቱ ደግሞ ለህገ መንግሰስቱ ብቻ ቢሆን ኖሮ ይህ ችግር በቀላሉ የሚወገድ ችግር ይሆን ነበር።

ginbot 7 exposing woyane 1

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን በአምሰት አመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሺን ፕላን ዉስጥ የሚጫወተዉን ቁልፍ ሚና ፓርላማዉ በሚገባ የሚገነዘበዉ ይመስለናል፤ ታዲያ ይህ በአገር እድገት ዉስጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወተዉ ኮርፖሬሺን ሙሉ በሙሉ በአንድ ብሔር ቁጥጥር ስር ሲወድቅ ምነዉ የብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት የሆነዉ ፓርላማ አፉን ዘግቶ ተመለከተ? ፓርላማዉን ይበልጥ የሚገድደዉ የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በአንድ አናሳ ብሔረሰብ ሙሉ ቁጥጥር ስር ሆኖ ሌሎቹ ብሔረሰቦች ተመልካች ሲሆኑ ነዉ ወይስ የአንድ ኮርፖሬሺን ሰራተኞች  በአብዛኛዉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሲሆኑ ነዉ? ለመሆኑ የወያኔ ዘረኝነት በኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ዉስጥ ምን ያህል ዘልቆ ገብቷል? የኦሮሞ፤ የአማራ፤ የሶማሌ፤ የሲዳማና ሌሎቹም ብሔር ብሔረሰቦች በዚህ ለአገር እድገት ቁልፍ በሆነ ኮርፖሬሺን ዉስጥ የሚጫወትቱት ሚና ምን ይመስላል?

ginbot 7 exposing woyane 2

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን በአስራ አንድ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች የተዋቀረ ሲሆን በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎቸን ያስተዳድራል፤ ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀቀበት ቀን ድረስ ቁጥራቸዉ በዉል ተለይቶ ባይታወቅም አስራ ሦስቱ እንዱስትሪዎችም እያንዳንዳቸዉ በስራቸዉ ብዙ ፋብሪካዎችንና የማምረቻ ተቋሞችን ያቀፉ ናቸዉ። የኮርፖሬሺኑን  አስራ አንድ ትላልቅ መምሪያዎችና አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱሰትሪዎች በዋና ሀላፊነት፤ በዳይረክተርነተና በምክትል ዳይረክትርነት የሚመሩ 29 የከፍተኛ አመራር አባላት አሉ። ከእነዚህ 29 ከፍተኛ አመራር አባላት ዉስጥ 69 በመቶዉ ወይም ሃያዉ ህወሀት ሆን ብሎ ያስቀመጣቸዉ ትግርኛ ተናጋሪ የሆኑ ወታደራዊ መኮንኖች ናቸዉ።በዚህ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ያላቸዉ ቦታ 31 በመቶ ወይም ከእያንዳንዳቸዉ በቅደም ተከተል ሦስትና ስድስት ሰዎች ብቻ ሲሆን ከተቀሩት አምስት ክልሎች በዚህ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የተመደበ አንድም  ሰዉ የለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ እንዱስትሪ ለመገንባት በሚደረገዉ ጥረት ዉስጥ ከፍተኛዉን ሚና ይጫወታል የሚባለዉ የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን በሲቪልና ወታራዊ መምሪያዎች ተከፋፍሎ የተዳራጀ ሲሆን በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎች ይገኛሉ። እነዚህን እንዱስትሪዎች በማስተዳደሩ በኩል የብሔር ብሔረሰቦችን ድርሻ ወይም ኮታ ስንመለከት  ከአስራ ሦስቱ እንዱስትሪዎች ዘጠኙን የሚያስተዳድሩት የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። በኮርፖሬሺኑ ዉስጥ ከፍተኛ ስልጣን ከተሰጣቸዉ የትግራይ ተወላጆች ዉስጥ እነ ብረጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘዉ  የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን ዋና ዳይረክተር ፤ ኮ/ል ተከስተ ኃ/ማሪያም  በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ፕሮዳክሺን ግንባታ ሀላፊ ፤ ኮ/ል ፀጋሉ ኪሮስ በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ወታደራዊ ምርቶች ሀላፊ ፤ ኮ/ል ሙሉ ወ/ሰንበት በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ፕሮጀክቶች አስተደዳደር ሀላፊ፤ሻምበል ካህሳይ ክሽን የምርመራና ልማት ዳይረክተርና  ሻምበል ገ/ስላሴ ገ/ጊዮርጊስ የአቅም ግንባታና ስልጠና ማዕከል ዳይረክተርን የመሳሰሉ የህወሀት ታጋይ መኮንኖች ይገኙበታል።

ginbot 7 exposing woyane 3

ከትግራይ ዉጭ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔሰቦች በብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን እንዱስትሪዎች ዉስጥ ከፍተኛ የሀላፊነት ደረጃ ባለዉ የአመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ ዕድል ያገኙ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር አራት ብቻ ነዉ። ይህ ጥናት የተጠናዉ ከ2004 እስከ 2005 ዓም ባለዉ የአንድ አመት ግዜ ዉስጥ ነዉ። በ2004 ዓም የኢትዮጵያ ህዝብ 90 ሚሊዮን አንደሚሆን የተገመተ ሲሆን ከዚህ ቁጥር ዉስጥ በትግራይ ክልል  5.4 ሚሊዮን ህዝብ በተቀሩት ስምንት ክልሎች ደጎሞ 84.6 ሚሊዮን ሀዝብ ይኖራል ተብሎ ተገምቷል። ይህ ጥናት በዋናነት የሚያመለክተዉ በዋና ዋና የሀላፊነት ቦታ የተቀመጡትን ግለሰቦችና ግለሰቦቹ የመጡበትን ብሔር ስለሆነ ነዉ እንጂ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺንን የሰዉ ኃይል ምደባና የደረጃ እድገትን ጠለቅ ብለን ስንመለከት አብዛኛዎቹ እንጂኔሮችና ቴክኒሻኖች የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ፤ የደረጃ እድገትን በተመለከተም ከሌሎች ሰራተኞች ጋር ሲነፃፃር በፍጥነት የደረጃ እድገት የሚያገኙት እነዚሁ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። ይህ ደግሞ በአጋጣሚ የሆነ ነገር ሳይሆን ወያኔ በረሀ ዉስጥ እያለ አቅዶት ባለፉት ሃያ አመታት በስራ ላይ ያዋለዉ የረጂም ግዜ እቅድና ዝግጅት ዉጤት ነዉ።  ለምሳሌ ወያኔ ትግራይ ዉስጥ ኤም አይ ቲ  ወይም የመቀሌ ቴክኖሎጂ እንስቲቲዩት ብሎ የሚጠራዉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋም ተቀብሎ የሚያስተምረዉ የትግራይ ተወላጆችን ሲሆን ከዚህ ተቋም የሚመረቁ እንጂኔሮችና ተክኒሺያኖች ናቸዉ በኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን የሚሊታሪ ክንፍና በኢትዮቴሌኮም የስለላ ተቋሞች ዉስጥ ተመድበዉ ከፍተኛ የስለላ ስራ የሚሰሩት።

ginbot 7 movement exposing woyane 4

ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝና አገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚገኙ ቡችሎቹ የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ድርጅቶች በተለይ በዳያስፖራ ዉስጥ የሚገኘዉን ለእናት አገሩ ተቆርቋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጅምላ “የጥላቻ ፖለቲካ አራማጆች” እያሉ ለአመታት ሲዘልፉን ኖረዋል። የፖለተካ ትግላችን አላማና ግብ ከጥላቻ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለዉ ቢሆንም – ለመሆኑ ይህንን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተና አንዱን አለቃ ሌላዉን ተላላኪ፤ አንዱን የሚሾም ሌላዉን የሚሽር፤ አንዱን አብልቶ የሚያጠግብ ሌላዉን የበይ ተመልካች የሚያደርግ፤አንዱን የአገር መሪነት ቦታ ተረካቢ ሌላዉን ኮብልስቶን ድንጋይ ጠራቢ የሚያደርግ ስርዐት የሚወድ ማን አለ? ይህንን በንጹህ ዜጎች ደም እጁ የቆሸሰና ያደፈ ዘረኛ ስርአት ዉደዱ የሚለንስ ማነዉ? በምድርም በሰማይም የከሰሩ እነ ሚሚ ስብሀቱን የመሳሰሉ የፖለቲካ ሴሰኞች ሊነግሩን እንደሚፈልጉት ትግላችን የትግራይ ወንድሞቻችንንና እቶቻችንን በመጥላት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የትግላችን ብቸኛ አላማ ከትግራይ ወንድሞቻችን ጋር ሊያጋጩን የሚሞክሩትን የህወሀት ወንጀለኞች አስወግደን ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር ማድረግ ነዉ።

የግንቦት 7 ንቅናቄ

 

Austrian tourist killed in Ethiopia attack

Austrian tourist killed in Ethiopia attack

(AFP)

VIENNA — A 27-year-old Austrian tourist was killed in northern Ethiopia when his group was attacked during a whitewater rafting trip on the Nile, Austria’s foreign ministry said Monday.eth_bahir_dar_map

The attack occurred on Sunday near Bahir Dar, 550 kilometres (340 miles) northwest of the capital Addis Ababa, ministry spokesman Martin Weiss told AFP.

The victim was part of a group of 10 Austrians on an organised whitewater rafting trip in the region.

Four of the group had spent the night camping on the banks of the Nile when they were apparently attacked by robbers. The victim’s three companions were unharmed in the incident.

“There were gunshots,” Weiss told AFP.

One of the tourists “was mortally wounded, the three others managed to escape and called the Austrian embassy in Addis Ababa.

“The (local) authorities were later informed and we received information this morning that the three individuals were safe. Shocked but in safety,” he added.

“Technical equipment was stolen, the boats were damaged. It was probably a band of bandits.”

Weiss added the attack did not seem to have been political motivated, saying: “It was just a robbery.”

No arrests have been made, the ministry spokesman said.

In its latest travel advice on Ethiopia, published in November, the Austrian foreign ministry warned of “a heightened risk of terrorist attacks”.

In January 2012, five foreign tourists, including an Austrian, were killed on the slopes of the Erta Ale volcano in northern Ethiopia. Addis Ababa blamed the attack on groups trained and armed by neighbouring Eritrea, an accusation the Eritrean government denied.

 

 Abbaymedia.con

The original Ethiopian flag arrived in Johannesburg: Excitement and jubilation…

The Horn Times News
by Getahune Bekele, Pretoria-South Africa

“Sendekalamachin!”

Excitement and jubilation as Ethiopian refugees received delivery of the original national flag.

South-Africa-2013-Ethiopia

Shock, anxiety and bewilderment griped TPLF officials at the Ethiopian embassy in Pretoria as refugees totally rejected the satanic flag of the minority junta; a symbol of the brutal internal colonization of Ethiopia.

On Thursday morning the original Ethiopian flag arrived in Johannesburg directly from China, ahead of the black lions opening match against the copper bullets of Zambia in Nelspruit, much to the delight of thousands of patriotic fans. It was immediately distributed, all thanks to the sterling work of the Ethiopian community association in South Africa and the anti TPLF organization known as Bête-Ethiopia.

It will be proudly displayed on Monday at Mbonbela stadium.

“We have a big surprise for the enemy of our flag, our history and our tradition- the ruling junta. We are going to shame the dead tyrant Meles Zenawi who once called our flag ‘a piece of garment.’ In bringing this flag here, great gallantry has been displayed by great individuals here in South Africa. Long live the Ethiopian community association! Long live Bête- Ethiopia!” an elated refugee told the Horn Times.

With some of the flag stretching for up to 10m, it is now all systems go.
The Horn Times also watched some Ethiopians publicly dumping the TPLF flag they received earlier from embassy officials.

Meanwhile, despite the minority junta’s attempt to sabotage the national team’s arrival, we are all at Oliver Tambo international airport in Johannesburg to welcome the black lions of Ethiopia.

infohorntimes@gmail.com

 

 Abbaymedia.com

ሰበር ዜና፣ መንግስት በምስክር እጦት ጭንቅ ውስጥ ገብቷል፡፡

የብዙዎች ምላሽ ‹‹በሐሰት አንመሰክርም›› የሚል ሆኗል፡፡

በእስር ላይ የሚገኙ መሪዎቻችን እና ሌሎች ወንድሞቻችንን በአሸባሪነት ከስሶ ሲያንገላታ የቆየው መንግስት በምስክር እጦት ችግር ውስጥ መግባቱ ታወቀ፡፡ መንግስት ኮሚቴዎቻችን ላይ በመሰረተው ክስ በሐሰት ሊያስመሰክራቸው ያዘጋጃቸው 197 (አንድ መቶ ዘጠና ሰባት) ሰዎች መኖራቸውን ለፍርድ ቤት ቢያሳውቅም የተገለጸውን ቁጥር ያህል ምስክሮች ማግኘት አልቻለም፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ለምስክርነት የታሰቡት ብዙዎቹ ግለሰቦች ምስክር ለመሆን ፈጽሞ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ ነው፡፡ መሪዎቻችን ባልዋሉበት እና በማያውቁት ወንጀል የከሰሳቸው መንግስት በየአካባቢው ‹‹ድጋፍ ይሰጡኛል፤ እተማመንባቸዋለሁ›› የሚላቸውን ግለሰቦች ለምስክርነት ተደጋጋሚ ጥሪ ቢያደርግላቸውም በሐሰት አንመሰክርም የሚል ቆራጥ አቋም ማሳየታቸው ተሰምቷ፡ል፡ሰበር ዜና

ሙስሊሙ ህብረተሰብ ያነሳቸውን የመብት ጥያቄዎች ለመንግስት እንዲያደርሱለት በአስር ጣቱ አምኖባቸው የመረጣቸው ኮሚቴዎቻችን እና ሌሎች ዳኢዎች መንግስት እውቅና ሰጥቷቸውና ስለ ሰላማዊነታቸውም በመንግስት ብዙሀን መገናኛዎች መስክሮላቸው፤ ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ድርድር ሲያደርጉ እንደቆዩ ይታወሳል፡፡ ሆኖም መንግስት የቀረቡትን የመብት ጥያቄዎች ለመመለስ አለመፈለጉና እነሱም ጥያቄዎቹ እንዲመለሱ ተደጋጋሚ ጥያቄ በማቅረባቸው ‹‹አሸባሪ›› የሚል ታፔላ ተለጥፎባቸው ከሐምሌ 2004 ጀምሮ በእስር እና ስቃይ ላይ የሚገኙት መሪዎቻችን ንጹህ መሆናቸውን የተረዱ ብዙዎች በሀሰት እነሱ ላይ ለመመስከር ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በቀጥታ መግለጽ ችለዋል፡፡

መንግስት ይህን የመስካሪዎች እምቢታ ተከትሎ አዳዲስ ምስክሮችን ለመመልመል ቀን ከሌት እየሰራ እንደሚገኝ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ የመንግስት ደህንነቶች ቁጣና ንዴት በተሞላበት መልኩ ሰዎችን ምስክር እንዲሆኑ በአካልም ጨምር እየሄዱ በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ደህንነቶቹ በአዲስ አበባ አንድ አንድ መስጊዶች በመገኘት ግለሰቦችን በግድ በመያዝ ምስክር እንዲሆኑ እየጠየቁ ሲሆን፤ ፈቃደኛ አልሆንም ያሉ ሰዎችንም ‹‹የማትመሰክር ከሆነ አንተን ነው የምንከስህ›› በማለት በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ፡፡ የሀሰት ምስክርነትን (ሸሀደተ ዙር) አስከፊ ወንጀልነት የተረዱ በርካታ ሙስሊሞች አሁንም በእምቢታቸው የዘለቁ ሲሆን፤ አሁንም ግን ጥቂት የማይባሉ ‹‹ተገደን ነው የምንመሰክረው›› የሚል ምላሽ እየሰጡ ያሉ ግለሰቦች በመኖራቸው ከዚህ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡና ከአስከፊው የሀሰት ምስክርነት መዘዝ እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲጠብቁ አደራ እንላለን፡፡

አቡበከር ሲዲቅ (ረ.ዓ) የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ማለታቸውን ዘግበዋል፡- ‹‹የከባዶች ከባድ የሆነውን ሀጢአት አልነግራችሁንም›› እኛም ‹‹አዎ! የአላህ መልዕክተኛ እንዴታ!›› አልን፡፡ እሳቸውም ‹‹በአላህ ማጋራት (ሽርክ) እና ወላጅን ያለመታተዝ ናቸው›› አሉና ተደላድለው ከተቀመጡበት ድንገት ተነስተው እንዲህ አሉ ‹‹አዋጅ! ውሸት መናገር እና በሐሰት መመስከ›› እያሉ የሚያቆሙት አልመስልህ እስኪለኝ ድረስ ደጋገሙት ፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡

አላሁ አክበር!

 

አዲሱ መጅሊስ ሲጋለጥ ያንብቡት!!!

አዲሱ መጅሊስ ሲጋለጥ ያንብቡት!!!

ethiopian muslim new mejliss

በአንድ የግል ጋዜጣ የዘንድውን አወዛጋቢ የመጅሊስ ምርጫ አስመልክቶ የተመረጡትን ሰዎች ፕሮፋይል እየተመለከትኩ ነበር፡፡ ከጎኔ የነበረ ሰው የሙስሊም ኮፍያዬን ቀና ብሎ ተመልክቶ ከበፊቱ መጅሊስ የተሻለ ዓለማዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ዕውቀት እንዳላቸው ነገረኝ፡፡ በጋዜጣ መሸጫ ዙሪያ “ሲቪሎች” ስለሚበዙ እሱም መረጃ እየሰራ ይሆናል በሚል ግምት በአጭሩ ያለውን መስማማቴን በንቅናቄ ገልጬ ገጹን በመገልበጥ አባረርኩት (አባረረኝ)- ብቻ ያው ነው፡፡ ከዚህ ሰውዬ አስተያየት ጀምሮ እስከ ዛሬ ያማጥኩትን ለአንባቢያን ላበቃ ዘንድ እነሆ ብእሬን አነሳሁ፡ እኔ መሐመድ ካሊድ አዲሱ መጅሊስ  ባለስልጣናት /ፎቶ ምንሊክ ሳልሳዊ / ስለ ሰላማዊ ትግል በሚወራበትና ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለ 1 ዓመት ሙሉ ሕገ ወጡ መጅሊስ ይወገድ ከማለት ጀምሮ እስከ መሪዎቼ ይፈቱ ከዚያም ምርጫው ውድቅ ይደረግ ጥያቄ በአወሊያ ተጀምሮ እስከ ታላቁ አንዋር መስጂድ በዘለቀው የሰላማዊ ተቃውሞ የአንድ ዓመት ክብረ በዓል እየተከበረ ባለበት ወርሐ ታኅሳስ የመጨረሻ ሳምንት ስለ በግዱ መጅሊስ ማውራት ባይመስጥም ቢያንስ ውስጣዊ አሰራሩን ታነቡት ዘንድ ከትቤዋለሁ፡፡

አዲሱ መጅሊስ

በመጅሊሱ “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚለው ይሁን የእውነት አምነውበትና በአላማው ተመስጠው አሊያም ካድሬነት በሀይማኖት ተቋም ብዙ ተሰላፊ ስለሌለውና ሕወሓቶች ስለማይበዙበት በቀላሉ ትልቅ ካድሬ ሆኖ ለመገኘት ሲሉ አለያም የሀጅ ቢዝነስ አሪፍ ነው ሲባል ሰምተው አላውቅም ብቻ ወንድሞቻቸው አደባባይ እየጮሁ አልፈው ጥቂቶች የተወዳደሩበት በግዴታ ምርጫ ተካሂዶ እነሆ  እንደገና ተዋቅሯል፡፡ (አህመዲን አብዱላሂንም እንደስም ይጠራበት የነበረውንና ጨርቅ ከመሆኑ በቀር የአጼ ምኒሊክን ዘውድ የሚመስለውን ጥምጣሙን ተገላግሎ በኮፍያና በሸሚዝ መሀል ቦሌ ፈታ ብሎ ሲሄድ ልናየው ችለናል፡፡)

አዲሱ መጅሊስ የመጣበትን የምርጫ ሂደት ከቀበሌ መጀመሩ በታሪክ የመጀመሪያ ነው፡፡ ይህን ምርጫ ለማስተባበርም የተሰጠውም የመንግስት ሚዲያ ሽፋን ከመቼውም የተሻለ ነው፡፡ ተቃውሞውም እንዲሁ ታላቅ ነበር፡፡ ለዚህም ይመስላል በመጅሊሱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በድግሪና በማስተርስ ድግሪ ደረጃ የተማሩ ሰዎች ለስራ አስፈጻሚነት ደረጃ መድረሳቸው፡፡ ስለነዚህ ጉዶችም ብናወራ የመጅሊሱን ሁኔታ ለመረዳት የሚረዳ ይመስለኛል፡፡

አዲሱ መጅሊስ በሸህ ኪያር ሙሀመድ ፕሬዝዳንትነት ይመራል፡፡ በዋናው የመጅሊስ ስልጣን ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት እና ለስላሳው ለውሳኔ የሚቸገሩት ሙሀመድ አሊ እንደ ዋና ጸኀፊ ተወዝተዋል፡፡ በምክትል ፕሬዝዳንትነት የህዋሃት አባል የሆኑትና የቀድሞ የትግራይ ክልል የሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፣የክልሉ እስልምና ጉዳይ ፕሬዝዳንትነትና ሁሉንም ስራ አስፈጻሚ አባረው የሁሉም ዞኖች ተወካይ በመሆን ሁሉን ነገር የራሳቸው ጠቅለው በመያዝ ያላቸውን የአንባገነንነት አቅም ያስመሰከሩት ሼህ ከድር ማህሙድ ተሰይመዋል፡፡ ከዚህ ውጭ ሌሎቹን ስራ
አስፈጻሚዎች በሌላ ጊዜ አስተዋውቃለሁ፡፡

ይህ መጅሊስ በጎኑ እንዳይተኛ የሚያደርጉ ሀሳቦችን በመዳሰስ ትንሽ ልበል፡፡ መጅሊስ ማለት ሙስሊሙን ማህበረሰብ በሀይማኖታዊ ጉዳዩ የሚዎክል ተቋም እንደመሆኑ በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል እንዲሉ ብዙ ነገር አርፎ እንዳይተኛ ያደርገዋል፡፡ በዚህ ጽሁፍ የመጅሊሱን ፈተናዎች እና የፈተናውን ተዋናኞች ከዚህ በታች ባጭሩ እንዳስስ፡፡

1. የመጅሊሱ ቅቡልነት

መጅሊሱ ከድሮውም ለቅቡልነት አልታደለም፡፡ ይሁንና ያሁኑ ይባስ እንዲሉ ህዝበ ሙስሊሙ መጅሊሱን አንቅሮ ተፍቶታል፡፡በሙስሊሙ ማህበረሰብ አኳያ መጅሊሱ እመራዋለሁ የሚለው ህዝብ እየከሰሰውና እየገረመመው መኖሩ ጤናማ አይደለም፡፡  ይሁንና ያለፈው አልፏል እስኪ አንድ እድል እንስጣቸው ብሎ የሚነሳ ሙስሊም እንኳ ቢኖር በጥንቃቄ ካልተያዘ ያጡታል፡፡ ለዚህ ነው መጅሊሱ ለቅቡልነቱ የሚሰራውን ስራ ፈታኝ ነው የምለው፡፡ መጅሊሱ መልኩ ከፍቷል፡፡ ከሁሉ በፊት ፊቱ መዋብ አለበት፡፡ የመጅሊስን ክፉ ፊት ለማስዋብ ብዙ የመዋቢያ መሳሪያዎች (ኮስሜቲክሶች) የሚያስፈልጉት ሲሆን ምን ቢኳኳል ግን ፊቱ ላይ ያሉት ሁለት ቡጉንጆች ካልተወገዱ ሊዋብ አይችልም፡፡

እነዚህ ቡጉንጆች ኮማንደር ሙራድና ጀማል ሙሀመድ ሳሊህ ሲሆኑ እነዚህ እያሉ ገጽታን ማስተካከል የሚታሰብ አይደለም፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች የባለፈው ስራ አስፈጻሚ ይወገድልን ብሎ ህዝብ ሲጠይቅ አብሮ ፎቷቸው ተለጥፏል፡፡ ውሎ ማደሪያቸው ሳይቀር በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ተለቋል፡፡ ቀድሞም የመጅሊሱ ማንኛውም ውሳኔ የሚወሰነው በሰላም መምሪያ ጣልቃገብነት ነው፡፡ ትምህርት፣ቁርአን፣ልማት፣ሀጅ ወዘተ.. ብቻ ሁሉም ነገር ላይ የሰላም መምሪያ ጣልቃ ገብነት ያስፈልገዋል፡፡ ይህ ኃላፊነት የስራ አስፈጻሚ ሲልም በየክፍሉ ያሉ የስራ ሓላፊዎች መሆን ሲገባው እንዴት ጠቅሎ ወሰደው? ብዬ ስጠይቅ ያገኘሁት መልስ ቢኖር መንግስት ነው የሚል ነው፡፡ ብዙዎች እነደውም የሰላም መምሪያው ፕሬዘዳንቱን ማዘዙ የአደባባይ ሚስጥር እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

አዲሱ መጅሊስ በኮከብነት የሚመሩት ሙስሊሙን ሲያተረማምሱ የኖሩት እነ ጀማል ሙሀመድ ሳልህ ( የእውነት ስሙ ገብሬና ለትግል ሲባል ስሙ ከነአያቱ የተቀየረ ተብሎ የሚታማ) በዲሲፕሊን ከጉለሌ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ የተሰናበተው ኮማንደር ሙራድ ፎቷቸው ከሌሎች ጋር በመሆን ለህግ እንዲቀርቡ በዚህ ሳምንት ዓመቱን በሚያከብረው ድምጻችን ይሰማ የፊስ ቡክ ገጽ የለጠፋቸው ናቸው፡፡

ይታያችሁ ኮማንደር ሙራድ የመጅሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ ሲሾም ያለ ሀፍረት በሴትነታቸው የጠየቃቸው ሁለት ሴት ጓደኛሞች የመጅሊሱ ሰራተኞች ምን ይሰማቸዋል? ገብሬ እንደዱሮው ሁሉ ስራ አስፈጻሚውን አመራርና አመራር ያልሆነ ብሎ ከፍሎ ሀሳብ በማቅረብ የፈለገውን ስራ አስፈጻሚ ከስራ ሲያሳግድ ማየት እንዴት…..እንዴት….. እንዴት…ቅቡልነትን ያመጣል?

የፌደራል መጅሊስ 400 የሚሆን ሰራተኛ አለው፡፡ ይሄ ሰራተኛ ጉዳዬ ካማረው ለአደባባይ አሳልፎ ይሰጥሃል፡፡ በተለያዩ ጋዜጦች ላይ ካየናቸው የሂሳብ ሰነዶች ጀምሮ ለየመንግስት መስሪያ ቤቱ እስከገቡት ሰነዶች ድረስ ያለው ሚስጥር የወጣው በተለያዩ ሰራተኞች ነው፡፡  ባጭሩ የመጅሊሱ ሰራተኛ ማለት ወሳኝ ምስክር ማለት ነው፡፡ ምክር ቤቱ የስራ ባህሉ ክፉኛ የተጎዳ ከመሆኑ የተነሳ እድሜ ለነ እንቶኔ አብዛሀኛው ሰራተኛ ከስራ ይልቅ ወሬ ማቀበል እንደሚያሳድግ ገብቶት የነገር ማቀበል ሚና መጫወት ህሊናው የፈቀደ እያቀበለ ህሊናው ያልፈቀደው ደግሞ በስራ የሚመጣ ነገር እንደሌለ በመገንዘብ ቀኑ ሲመሽና ሲነጋ እየታዘበ ልጆቼን ላሳድግ የሚል ሆኗል፡፡

ከዚህ ባሻገር የአህሉሱና ወለወጀማአ እና ሱፊ ሰለፊ ጉዳይ ገና አነጋጋሪ ነው፡፡ የየእስልምና ምክር ቤቶቹ ምርጦች የመጡት በሱፊ መስፈርት ነው፡፡ ህዝቡ ደግሞ አንድነት እያለ ነው፡፡ የመጅሊሱ አመራሮች ቃለ መሃላ የፈፀሙትም በዚሁ መልኩ ነው፡፡ ሙስሊሙን ማህበረሰብ በአህሉሱና ወለወጀማዓ አስተምህሮ ለመምራት! ታዲያ የተመረጡበት መስፈርት ተቀይሮ አንድነትን ከግምት ውስጥ ያስገባ አካሄድ ቢሞከር ቅቡልነትን ለማግኘት ያግዝ ይሆናል፡፡

ሶስተኛው ጉዳይ የህዝብ ግንኙነት ስራ በአብዛሀኛው ቅቡልነትን ከመገንባት አኳያ ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡ ይሁንና መጅሊስ ገብታችሁ የህዝብ ግንኙነት ክፍሉን ብትመለከቱ በሰው ሃይል ረገድ በእጅጉ ተጎድቷል፡፡ ለዚህ ይመስላል አዳዲሶቹ ስራ አመራሮች ውሉ ጠፍቶባቸው ቢሮዎችን በመቀላቀል ትላልቅ ቢሮዎችን በመፍጠርና ቀለም በመቀባት ስራ ላይ የተጠመዱት፡፡ አዲሶቹ መጅሊሶች ከገቡ ሶስት ቢሮዎች ፈርሰው አንድ ትልቅ ቢሮ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ሁለት የትውውቅ መድረኮች ተከፍተዋል፡፡ ……ወዘተ፡፡

2. የመጅሊሱ የውስጥ መዋቅር

መጅሊስ በውስጡ የተለያዩ የልማት ተቋማት ያሉት ሲሆን የአወሊያ ተቋማት እና የልማት ኤጀንሲ እንዲሁም በመጅሊሱ የተለያዩ ዘርፎች ስር ያሉ ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ በነዚህ ተቋማት ስር ከ 400 በላይ ሰራተኞች ያሉ ሲሆን ከትምህርት ዝግጅትና ልምድ አኳያ ጥሩ ሊባል የሚችል አቅም ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡ በዚህ ተቋም ያለፈ የስራ ሂደት ታዲያ ይህን የሰው ሀይል በአግባቡ ስራ ሊያሰራ የሚችል አደረጃጀትም ሆነ ህግና ደንብ የሌለው በመሆኑ ሰራተኛው በማያውቀው ምክንያት በዙሪያው ሲከናወን ቆይቷል፡፡ ይህ በዚህ ሂደት የተዳከመና የተሰላቸ ሰራተኛ ስለመጅሊሱ ከስራ አስፈጻሚዎች በላይ ያውቃል፡፡ መጅሊሱ ሲቋቋም ጀምሮ አዲሱን በመቀበል እና ነባሩን በመሸኘት ከ 15 ዓመታት በላይ ከመጅሊሱ ጋር የቆዩ ሰራተኞች ከ1987 ጀምሮ የነበሩ መጅሊሶችን ተመልክተዋል፡፡ በንግግር የተካኑ የነበሩት መጅሊስ ስራ አስፈጻማች በባዶ ተስፋ ሲደልሉት ቆይተዋል፡፡ በመሆኑም የመጅሊሱ ሰራተኞች ተጨባጭ ለውጥ በተግባር ካላዩ ለመጅሊሱ የኔነት ስሜት ፈጽሞ ሊሰጡት አይችሉም፡፡

የመጅሊሱ ነባር ስራ መረጃ አያያዝም ደካማ በመሆኑ የመጅሊሱ ስራ አስፈጻሚዎች በቀጥታ ወደ ስራ ለመግባት የሚችሉበት ሁኔታም አይኖርም፡፡ መጅሊሱ ያለው የስራ መመሪያም ሆነ መዋቅር በሰኔ 1993 ዓ.ም የተዘጋጀ ሲሆን አሁን ካለው መዋቅር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለው እስከሚመስል ድረስ በሂደት ተቀያይሯል፡፡ የመዋቅሩን ማርጀት ተከትሎም በርካት መደቦች በተፈለገው ጊዜ ሊቀጠር በተፈለገው ሰው ልክ ሲፈጠሩ ቆይተዋል፡፡በዚህ ሂደት የተጠራቀሙ ሰራተኞች ቀን አሳላፊ ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ የስራ አስፈጻሚ ሚስት፣ልጅ፣እህት ባጠቃላይ ዘመድ አዝማድ ሆነው ግቢውን የረገጡና በዛው የቀሩትን ብዛት መጅሊሱ ይቁጠረው፡፡ ከእንግዲህ ይህን ሰራተኛ ነው ሁሉንም የሚመጥን የትምህት ዝግጅትና ልምድ ላይ ተመስርቶ ስራ ሰጥቶ ወደጤናማ ተቋም አካል መቀየር የሚቻለው፡፡

3. የውጭ እጆች

ሌላኛው የመጅሊስ ጣጣ ሆኖ የሚገኘው የውጭ እጆች  ልብ በሉልኝ ፡፡ ይህ ምክር ቤት በሀጅና ኡምራ ስራ ከብዙ ድርጅቶች ጋር ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በዚህ አወዛጋቢ የሀጅና ኡምራ ስራ የመስራት አበሳ ከተቋሙ ጋር ያነካካቸው ሰዎች ሁሉ ምንጌዜም ስራ አይፈቱም፡፡ ከመጪው ስራ አስፈጻሚ ጋር ሲስማሙ አብረው በመስራት ሳይስማሙ ይሄኛውን ጥለው ለነሱ የሚመቸውን ለማስመጣት ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ይሄ እጅ ምንጊዜም ስራ አይፈታም፡፡ ታዲያ ይህ እጅ አነዴ በጋዜጣ ሌላ ጊዜ በመጽሄት፤ ካልሆነም በተለያዩ የመንግስጥ የደህንነት መዋቅሮች ውስጥ አልፎ መምጣቱ ነው መከራው፡፡ አላሰርቅ ያለ ስራ አስፈጻሚ በሆነ ምክንያት አሸባሪ እንደማይባልና ከስራ እንደማይታገድ ምን ዋስትና አለን??

4. የመጅሊሱ የሰላም መምሪያ

ሌላኛው የመጅሊሱ ጣጣ የመጅሊሱ የሰላምና መረጃ መምሪያ ነው፡፡ የቀድሞ መጅሊስ አመራሮች መጅሊሱ በተለያየ ጊዜ ስልጣኑን ማቆየት ሲሳነው የዙፋኑ ጠባቂዎች እንዲሆኑ ለማድረግ ያመጣቸው የሚታወቅ ሙያም ሆነ ትምህርት የሌላቸው ሰዎችን ያቀፈ ክፍል ነው፡፡(ይህ ክፍል ከላይ የጠቀስኳቸውን ኮማንደር ሙራድን አቶ ገብሬ (ጀማል ሙሀመድ ሷሊህን) ጨምሮ 30 ሰራተኞችን የያዘ ነው፡፡ ይህ ቡድን በሀጅ ጉዞ 43434 ብር ተሸፍኖለትና ተጨማሪ 30000 ብር አበል ተሰጥቶት ሀጅን ሊቆጣጠር ሳይቀር ሳውዲ ይሄዳል፡፡ በመጅሊሱ ምርጫ ሂደትም በተለይም ዋና ጸኀፊ የነበረውን አቶ አልሙሀመድ ሲራጅን ለማስመረጥ እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ እንደነበረ በሰፊው ተወርቷል፡፡ ይህ ክፍል የመጅሊሱ ግል ማህደሩ ውስጥ የሁለተኛ ደረጃ መረጃ እንኳ የሌለው መሆኑን የሚያመለክተውን የመጅሊሱን ሰራተኛ በግጭት አፈታት ከአምስተርዳም ዩኒቨርስቲ ማስትሬት ድግሪ አለው ብሎ በኢትዮ ሙስሊም ጋዜጣ ሲያስነበበን ነው ተብሎም ይታማል፡፡

በአዲሱ የመጅሊስ ምርጫ የተመረጡት የመጅሊስ ፕሬዝዳንት የትምህርት ደረጃ ቀድሞ ተነግሮን ነበር፡፡ይህ በኋላ ላይ ሲጣራ ሃሰት ሆኖ የተገኘው ይህ የተመራጮች መረጃ የተቀነባበረው እና የሚነዛው በዚሁ ክፍል ስር ለዚህ ስራ በተሰማሩ ሰራተኞች መሆንም የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

የፕሬዝዳንቱ ቤተሰቦች የጉዞ ወኪል ቢዝነስ ያላቸው ሲሆን ከድፍን ኦሮሚያ ይህን አይነቱን ሰው ማምጣቱ በአንድ በኩል ለሀጅ ሙስና የተመቻቸና በልቶ የሚያበላ ነው የሚል ሃሜት በአዲሱ አመራር ላይ በሰፊው እየተወራ ቢሆንም የሰላም መምሪያው የግልና  ተቋማዊ ድጋፍ አዲሱም መጅሊስ ከቀድሞው የተለየ እንዳልሆነ ያመለክታል፡፡ አዲሱ ፕሬዝዳንት ግቢ ከገባ ጀምሮም ከሰላም መምሪያ ጋር ጠንካራ ግንኙት እንዳለው መገንዘብ ተችሏል፡፡

እንደመውጫ

የሕዝብ ተሳትፎ ለልማት ወሳኝ እንደሆነ ሁሉ ለሀይማኖትም ወሳኝ ነው፡፡ እና እስኪ ትንሽ ቢያንስ የተማረውን ሙስሊም አሳትፉ፡፡ አቅጣጭ ቀይሱ፡፡ ለሀገር ልማት አጋዥ የሁኑ አያሌ ነገሮች መስራት ይቻላል፡፡ አዲሱ ስራ አስፈጻሚ ላይ ተስፋ መጣል የመጡበትን መንገድ መርሳት ቢሆንም ከድሮው አሰራር እቅፍ ለመውጣት መሞከር ከቻሉ አሁንም የሙስሊሙ እውነተኛ ተወካይ ለመሆን መሞከር ይቻላል፡፡ ብዙ የሀይማኖት እውቀት ባይኖረኝም በሰማይ ቤት አካውንት እንዳለን አምናለሁ፡፡ ተስፋ አልቆርጥም፡፡ ታሪክና ፈጣሪ መዝግበው እንደሚይዙንም አለመርሳት ነው፡፡

ውድ አንባቢያን የመጅሊሱ የቅርብ ሰዎች ብዙ ሳይዘጋጁና ሳይጨነቁ ይህን ሁሉ መረጃ ሰጥተውኛል፡፡ ለግል ደህንነታቸው ሲሉም የተወሰነውንም ዝርዝር ነገር እንደማይነግሩኝ ገልጸውልኛል፡፡ ይሁንና በሂደቱ ያወቅኩት ነገር ቢኖር በመጅሊሱ የተማሩ ሰዎች በዙሪያው እንዳሉትና ያሉትን ሰራተኞች በአግባቡ ቢጠቀም ውጤታማ የመሆን እድል እንዳለው ነው፡፡

ይሁንና ሰራተኞቹ  የሰላም መምሪያ ግን ለሰራተኛውና ለስራ አስፈጻሚ አለመገናኘት ብዙ ሚናዎችን ከመጫወት አይቦዝንም ብለው ያሙታል፡፡ አዲሱ ስራ አስፈጻሚ ይህን ሰላም መምሪያ ካለው ሚና ለማቀብ ደፍሮ ሊያፈርሰው ይችላል የሚል ተስፋም እንደሌላቸው ነግረውኛል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ይህን ጽሁፍ ለሚያነብ ሙስሊምም ሆነ ሌላ ወገን የመጅሊስ ጉዳይ የሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን የሁላችንም በመሆኑ ለመስተካከሉ የቻልነውን ሁሉ ጥረት እንድናደርግ እላለሁ፡፡

—–
ጸሐፊውን ለማግኘት በኢሜይላቸው  (mkahlid9@gmail.com) ይጻፉላቸው፡፡
የዚህ ጽሑፍ ዋና ቅጂ በዞን ዘጠኝ እንዳይነበብ በታገደው የዞን ዘጠኝ ጦማር ላይ ይገኛል፡፡

 • facebook
 • twitter
 • rss
 • print
 • bookmark
 • email
 Abbay media.com

ጠ /ሚያችን ሃይለማርያም ራሳቸው እሰረኛ “እስረኛ የለም” ይላሉ

ጠ /ሚያችን ሃይለማርያም ራሳቸው እሰረኛ “እስረኛ የለም” ይላሉ

Hailemriam the puppetመቸም አገራችን ካለችበት ምስቅልቅል  የምትወጣ መስሎን  በትግሬ  ነጻ  አውጭ ግንባር  የሚመራው ኢህአዲግ  በጠመንጃ  ሃይል ስልጣን ከያዘበት ማግስት ጀምሮ “የዘመነ መሳፍንት” ጊዜ አስተሳሰቡን ትቶ አለም የደረሰበት ዲሞክራሲያዊና መልካም አስተዳደር  ደረጃ ላይ ባንደርስ እንኩዋ ጠጋ ብለን ለዘመናት ታፍኖና በችጋር ተቆራምዶ የኖረው ሕዝባችን የሚሰማውን አየተነፈሰ የለፋበት ሳይቀነስብት እየተቁኣደሰ ለመኖር የሚችልበት ስርእት እንዲዘረጋ ያልወተወትነው አልነበረም፡፡

ሰሚ ጠፋና አልሆነለንም፡፡ አምባገነኑ ወያኔ/ኢሀአዲግ እያድር ጥሬ እንጂ ሊበስል አልቻልም፡፡ ለውትወታችን  የስጠው ምላሽ ሲሻው በጡቻ፡ አላያም በጠመንጃ እንዲያም ሲል አይን ባወጣ ፍርደ-ገምድል ፍርድ ሕዝባችንን ማሰቃየት ብቻ ነው፡፡ ሕዝባችንንም ካለአንዳች እረፍት ሲያሰቃይ እነሆ ሁለት አሰርተ-አምታት አገባዶ ሶስተኛውን ተያይዞታል፡፡

መለስ በጌታ ፍርድ ከስልጣናቸው ሲወገዱ ግራ-ገቡን ሃይለማርያም ደሳልኝን ሳይወዱ ተክተው ሲሄዱ ነገሩ ሳይገባን ከእነበረከት ስምኦን ይልቅ ደስ ያለን እኛ ነበርን። የሁዋላ ሁዋላ “የምጣዱ እያለ የእንቅቡ በመንጣጣቱ”ፍዝዝ ብለን እያየን  መደነቅ ብቻ ሳይሆን የባሰ ግራ ተጋብትንም ነበር፡፡ ለካ  ነገሩ ወዲሀ ነው፡፡  እኛ ደስ ብሎን የነበር ሃይለማርያም ለዘመናት ተጨቁኖ ይኖር ከነበረው የደቡብ ክፍለ-አገራችን ከሆኑ ወገኖቻችን አብራክ ወጥተው ከፍተኛ የስልጣን እርክን  የደረሱ ስለመስለን ነበር፡፡ “ጉድ ወደ ሁዋላ ነው” እንዲሉ ሁዋላ ስንረዳው የእነ በረከት ደስታ ከኛ የተለየ ነው፡፡ እነርሱ የተደሰቱት ሙሽራው ሲወጣ ከተሻማው ዳቦ ባገኙት ጉራጅ ኖሮዋል። የተደበቀው በበለጠ የተከሰተልን ደግሞ ሃይለማርያም እራሳቸው በየመድርኩ እየወጡ የአምባገነኖቹ የእንግዴ ልጅ መሆናችውን  በጽናት ሲያረጋግጡ ነበር፡፡

ታዘው ይሆን ወይንም ወደው ባናውቅም   አንዴ ወጥተው የመለስ ተቀጥያ እንጂ ለኢትዮጵያ የራሳቸው ወጥ  የሆነ  የመልካም  አስተዳደር ራእይ እንደሌላቸው በገሀድ ነገሩን፡፡ አስተዳደራ ቸው የሚመራው በጀማ እንጂ እርሳቸው ከአፈ-ቀላጤነት በስተቀር ምንም ሚና እንደሌላቸው ሲያስታውቁን ደግሞ እንደዚሀ እራሱን ያዋረደ መሪ አይተን ስለማናወቅ  በጣም ደነገጥን፡፡  የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብለው የመጨረሻው የስልጣን ጣሪያ ላይ ሲቀመጡ ሚኒስትሮቻቸውን የማያስሾሙ የጦር መኮንንኖቻቸውን  የማያስመድቡ ከሆነ የእኝህ ሰው ጠቅላይ ሚኒስትርነት እምኑ ላይ ነው እያልን ተጨነቅን፡፡ ለመሆኑ አንድ ስህተት ቢፈጠር በህሊናችን ያሉበትን ሁኔታ እያወቅን በሃላፊነት ልንጠይቃቸው ነወይ?እያልን ዋለልን፡፡ በአጠቃላይ   በከፍተኛ የመንግስት አስተዳደር ደረጃ ለሚከስቱ ጉዳዮች ሁሉ በሃላፊነት የምንጠይቀው አሳጡን፡፡

የዚህ አይነቱ ክስተት ሲፈጠር በታሪካችን የመጀመሪያ ልዜ እይደለም፡፡ በቀዳማዊ ሃይለስላሴ  ካቢኔ ጠቅላይ ሚ/ር የነበሩት አክሊሉ  ሃብተወልድ የንጉሱ ልጅ የነበሩት ልእልት ተናኘ ወርቅ    የበላያቸው ድብቅ ጠቅላይ ሚ/ር እንደነበሩ የንጉስ ነገስቱ መንግስት በወሎ ሕዝባችን ላይ ባደረሰው ጥፋት የተነሳ  ሲጠየቁ በእየዬ ማጋለጣቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡  ያ እየዬ ጩኽታቸው ግን አምሽቶ የመጣ ስለነበር ከሞት አላዳናቸውም፡፡ ተረሽኑ፡፡ ችግራቸውን በወቅቱ ለሕዝብ አሳውቀው ዞር ብለው በነበር ምናልባት ከክሱ በዳኑ ነበር። አላደረጉትም። በዚህም የተነሳ እኛን የመሰል የነጻነት ታጋይና ያገር ባለውለታ ሳንቀብራቸው ቀረን፡፡ ታሪካችንም ተበላሽ፡፡ ጠቅላይ ሚ/ር እክሊሉ ችግራቸውን በወቅቱ ያልተጋፈጡት አንድም ከማን አለብኝነት እምበለ በለዚያም በስንት ርኩቻ ያገኙትን ሰልጣን ላለማጣት ይሆናል፡፡  ክቡር ልጅ ሚካኤል እምሩ ግን ይህን አላደረጉትም፡፡ ለአጭር ጊዜም ቢሆን በደርግ ካቢኔ ጠቅላይ ሚ/ር ሆነው ስርተዋል፡፡ ነገር ግን የደርግ አካሄድ አስቸጋሪና የማይታረም መሆኑን ሲረዱ በዘዴም ሆነ በልምምጥ ራሳቸውን አገለሉ፡፡ ስለሆነም ከሕረተስቡ ተቀላቅለው በክብር ኖሩ፡፡

እኛ ሃይለማርያምን ልናከብራቸው እንፈልጋለን። የጠቅላይ ሚ/ር አክሊሉ እድል እንዲገጥማቸው አንሻም። ልንቀብራቸው እንፈልጋለን። እርሳቸው ግን መንገዱን መምረጥ አለባቸው፡፡ የአክሊሉን ወይንም የሚካኤልን። የመለስን እመርጣለሁ ካሉ ግን ጠባቸው ከሕዝብም፡ ከእግዚአብሄርም ከራሳቸውም ጋር መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ስለ ፓለቲካ እሰረኛም ስናነሳ ቁጥሩን ከራሳቸው አንድ ብለው ቢጀምሩ መልካም ነው። ሃይለማርያም “እራሳቸው የፖለቲካ እስረኛ ሆነው “የፖለቲካ እስረኛ የለም ይላሉ፡፡ ይህ የተለመደ የመለስ አባባል ነው፡፡ እንዴት ራሳቸውን ማወቅ ይሳናቸዋል? ይልቁንስ እውነታውን ከመካድ እራሳቸውን ከእስር ቢያስፈቱ ይሻላቸዋል።

ጸሃፊው ዘነበ ታምራት በኢሜይል አድራሻቸው ztamira@yahoo.com ላይ ይገኛሉ

 Abbaymedia.com

የፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም አዲስ መጽሀፍ ግምገማ

መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ

ኢትዮጵያ ሀገሬ፣ ሞኝ ነሽ ተላላ፤ የሞተልሽ ቀርቶ፣ የገደለሽ በላ!

በሰሎሞን ተሰማ ጂ. (semnaworeq.blogspot.com)

በሐምሌ 1955ዓ.ም የወጣው መነን መጽሔት፣ (7ኛ ዓመት፣ ቁ.10 ዕትም፣ በገጽ 27) ላይ እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፤ “እኚህ የ33 ዓመት ወጣትProfessor Mesfin Woldemari is an Ethiopian peace activist and philosopher በአባታቸው ጎንደሬ፣ በእናታቸውም ይፋቴ ሲሆኑ፣ በአማርኛ የበሰሉ በመሆናቸው የመናገርና የማስረዳት ስጦታ ያላቸው ትሁት ወጣት ናቸው፤” ሲል ይገለጻቸዋል፡፡ ለጥቆም የወጣቱን መስፍን ወልደ ማርያም ሦስት ሐሳቦች እንደሚከተለው አስፍሮት ይገኛል፡፡ “ማናችንም በዘመኑ የምንገኝ ትውልዶች በምናውቀውና በተማርነው ችሎታችን ተሽለን ተገኝተን፣ የዚህ ዕድል ተሣታፊ ለመሆን የሚጓጉ ወንድሞቻችንን ለመርዳት የምንቦዝንበት ትርፍ ጊዜ እንዲኖረን አያሻም፡፡ …. እኔ ካወቅሁ ሌላው እንዲያውቅ መድከም የለብኝም ማለት፤ በዚህ ዓለም ላይ ብቻዬን በአንድ እግሬ ቆሜ እኖራለሁ ብሎ እንደማሰብ የሚቆጠር ነው፡፡….የሰው ሁሉ የተፈጥሮ ባሕርዩ ለየቅል መሆኑ ሲታመን፤ ይህን የየግል የነበረውን መንፈስ ሰብስቦ ለማስተማር ያለው የመምህሮች ድካም በቀላሉ የሚገመት ባይሆንም፣ ይህን ከመሰለው ጋር መሰለፍም ለመምህራኖች የታሪክ ክብር ነው፡፡” ልብ በሉ ይህ ንግግር የታተመው የዛሬ ሃምሳ ዓመት ገደማ ነው፡፡ ወጣቱ መስፍንም የገባውን ቃል ለመፈጸምና ለዕውቀት “የሚጓጉትን ወንድሞቻችንን ለመርዳትና ለማስተማር” በወሰነውም መሠረት፣ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ቃልና ተግባር ተስማምተው ሲገኙ ሁሌም ያስመሰግናሉ፤ ያስከብራሉም፡፡

ከመጋቢት 2002 ዓመተ ምህረት ጀምሮ፣ ይኼንን መጽሐፍ ሲያሳትሙ አራተኛ ሥራቸው/መጽሐፋቸው ነው፡፡ በሠላሳ ሦስት/አራት ወራት ውስጥ አራት ደህና-ደህና መጽሐፍትን ጽፎ ማሳተም ከባድ ተግባር ነው፡፡ በተለይም ሩጫው ከዕድሜና እርጅና ይዞት ከሚመጣው ጫና ጋር ሲታሰብ ከባድ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል፡፡ ኧረ ለመሆኑ፣ ሰማኒያ ሲደመር (80+)….ምናምን ሆኖ በሣምንታዊ ወይም በየሁለት ሳምንቱ የሚወጣ ጋዜጣና መጽሔት ላይ የሚጽፍ ኢትዮጵያዊ ማነው? ማነው ወቅታዊ ሁኔታዎችን ዕለት-በዕለት ተከታትሎ ከዕድሜና ከኑሮው/ከተሞክሮው እንዲሁም ከተማረው ትምህርት ጋር መርምሮና ፈትሾ ለሕዝብ እምነቱንና እውነቱን ባደባባይ የሚጽፈው? ማነውስ በጡረታ ዘመኑ፣ “አገዛዝን አልፈራም” ብሎ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጉባኤ/ድርጅት ከተባባሪዎቹ ጋር አቋቁሞ ገዢዎችን የሚሞግተው? ብዙዎች፣ ገዢዎችን ፈርተው፣ በፍርሐትም ተሸብበውና በተስፋ መቁረጥ ተሰንገው ዳር ቆመው ሲመለከቱ (ይሳካም-አይሳካም) ከሕዝብ ጎን/ጋር ተሰልፎ በሦስቱም ሥርዓቶች የተገኘው ሊቅ ማነው?(ያ ሰው በሚያዝያ 16 ቀን 1922ዓ.ም እዚሁ አዲስ አበባ ከተማ የተወለደው-ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ነው፡፡)

ፕሮፌሰር መስፍን ዋናው የጥናት መስካቸው ጂኦግራፊ ነው፡፡ በ1945ዓ.ም ወደ ሕንድ ሀገር ሔደው ከፑንጃብ ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍናና በጂኦግራፊ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡ በ1948ዓ.ም ወደኢትዮጵያ ተመልሰው በትምህርት ሚኒስቴር-በጆኦግራፊና በካርታ አነሣሥ ኢንስቲቱት ውስጥ ለጥቂት ወራት ሢሠሩ እንደቆዩ፤ በዚያው ዓመት አሜሪካን አገር በሚገኘው የክላርክ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ዓመታት ያህል በጂኦግራፊ ትምህርት የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡ በ1950ዓ.ም ወደኢትዮጵያም ተመልሰው፣ ወደአሜሪካን ከመሔዳቸው በፊት ይሠሩበት በነበሩበት መሥሪያ ቤት ተመድበው ለሁለት ዓመታት ያህል አገልግለዋል፡፡ ከዚያም፣ በ1952ዓ.ም ወደቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተዛውረው የጂኦግራፊና የካርታ አነሣሥ ትምህርን በማስተማርና በዚሁ ክፍል ኃላፊ በመሆንም እያገለገሉ ናቸው፤” ሲል ጅማሯቸውን ያትታል፡፡ በጣም ውሱን በሆነ አኳኋን የጻፉትንና መጠነኛ ማሳያ ተደርጎ ሊቆጠር የሚችለውን “አገቱኒ፡- ተምረን ወጣን (መጋቢት 2002ዓ.ም) የጻፉትን የራሳቸውን መጽሐፍ ማንበቡ የተሻለ መረጃ ስለሚሠጥ አንባቢያን እርሱን እንዲያነቡት ይመከራሉ፡፡

Mesfin Woldemariam (also spelled Mesfin Wolde Mariam; born 1930) is an Ethiopian peace activist and philosopher

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

ወደዋናው ጉዳያችን እንመለስ፤ ይኼኛው የፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም መጽሐፍ፣ “እንጉርጉሮ” ብለው (1967ዓ.ም) ያሳተሙትን የግጥም መጽሐፍ ሳይጨምር፣ በአማርኛ ከጻፏቸው መጽሐፍት ውስጥ ሰባተኛው ነው፡፡ በተመሳሳይም፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሰባት መጽሐፍትን በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ጽፈዋል፡፡ በተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ አገር ጥናታዊ መጽሔቶች ላይ የታተሙ ከሃያ በላይ ጥናቶችን አሳትመዋል፡፡ እጅግ ብርቱ፣ ከማጥናትና ከመመራመር የማይታቀቡ አዛውንት ናቸው፡፡ በቀጥታ፣ ለግምገማ ወደመረጥነው እርዕሰ ጉዳይ እንግባ፡፡ “መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ፤(ኢትዮጵያ ሀገሬ፣ ሞኝ ነሽ ተላላ፤ የሞተልሽ ቀርቶ፣ የገደለሽ በላ!) ይሰኛል፡፡ በታኅሣሥ 2005ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሟል፡፡ ጠይቄ እንደተረዳሁት ከሆነ፣ መጽሐፉ በደርግ ዘመን ተጀምሮ በርካታ ጥናቶችና ምርምሮች ሲደረጉበት የቆየ መጽሐፍ ነው፡፡ ዋጋው ብዙ አይደለም፤ በ45.00 የኢትዮጵያ ብር ገዝቶ ቁምነገር መዝረፍ ያጓጓል፡፡ መጽሐፉ-ካርታዎችን፣ ፎቶዎችንና አባሪዎችን አጠቃሎ 238 ገጾች አሉት፡፡ ገጽ በገጽ ሲገልጡት በአዳዲስ ሃተታዎች የታጨቀ ነው፡፡ የተለየ ጥልቀትም አለው፡፡ (ምናልባትም፣ ይህንን መጽሐፍ በአንድ ክፍል ብቻ መገምገሙ በቂ ላይሆን ይችላል፡፡ እንዲያውም “ንፉግነት ነው!” ቢባል አያስገርምም፡፡)

ያም ሆኖ፣ የምንገመግመው መጽሐፍ እጅግ ከፍ ያለ ዋጋ የሚሰጠው፤ የፖለቲካ-ጂኦግራፊ፣ የታሪክ፣ የትምህርት፣ የማህበራዊ ሳይንስና የባህል/ስነ-ሰብዕ ይዘት ያለው ሥራ ነው፡፡ስመ-ጥር የጂኦ-ፖለቲካ ሊቅነታቸው ብቻ ሳይሆን፣ በተደጋጋሚ ያሳዩት አገዛዞችን የመዳፈር ችሎታቸው በዚህም መጽሐፍ ውስጥ ተንፀባርቋል፡፡ ስም እየጠሩና ማስረጃ እያጣቀሱ ብዙዎቹን የታሪክ “ሊቃውንት” እና “ታሪክ ሠሪዎች” ተችተዋል፡፡ ከታሪክ ሊቃውንቱ መካከል፣ ከፕሮፌሰር ስርግው ሐብለ ሥላሴ በስተቀር ከሠላ ትችታቸው ያመለጠ የለም፡፡ ፕ/ር ስርግውን ግን፣ “የኢትዮጵያን ታሪክ በዘመናዊ መልክ በኢትዮጵያዊ መሠረት ላይ ለመትከል ብዙ የሠራና እጅግ የሚጥርም ሰው ነበር፤” ሲሉ ያመሰግኗቸዋል (ገጽ 89)፡፡

ከታሪክ ሠሪዎቹም ነገሥታት መካከል በተራ አፄ ቴዎድሮስ፣ አፄ ዮሐንስና አፄ ምኒልክ ሚዛን አንስተዋል፡፡ አፄ ቴዎድሮስን “መድፍ የሠራ” ብቸኛ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ ካሉ በኋላ፣ “ያንንም መድፍ መቅደላ ተራራ ላይ ማውጣቱም ራሱ ሌላ ትልቅ ሥራ ነው፤” ሲሉ ይገልጧቸዋል(ገጽ 165)፡፡ አፄ ዮሐንስንም በተመለተ፣ “የቴዎድሮስን ፈለግ ተከትለው፣ ከውስጥ አምባ-ገነኖችና ከውጭ ወራሪዎች ጋር የመረረ ትግል እያካሔዱ፣ ከአፄ ቴዎድሮስ የተሻለ ውጤት አሳይተዋል፤” ሲሉ ተገቢውን ክብር ይሠጧቸዋል(ገጽ 166)፡፡ ስለአፄ ምኒልክም ሲያወሱ፣ ቄሣራዊያን ኃይሎች ኢትዮጵያን ሊቃረጧት ባሰፈሰፉበት በዚያን የመከራ ወቅት፣ የኢትዮጵያን ሀገረ-መንግሥት ከመደምሰስ “የረዳው የአፄ ምኒልክ አመራርና የዘመኑ የኢትዮጰያ ሕዝብ የመንፈስ ወኔና አልበገር ባይነት የሰጣቸው ኃይል ነው” ብለዋል(ገጽ 168)፡፡ አክለውም፣ “አፄ ምኒልክ በንጉሠ ነገሥትነት ዘመናቸው ሁለት ጠባዮችን በጉልኅ አሳይተዋል፡፡ አንደኛ፣ ለጎበዝና ለጀግና ክብርን የሚሰጡ በመሆናቸው ሁልጊዜም በጀግኖችና በታላላቅ ሰዎች የተከበቡ” መሪ ነበሩ-ይሏቸዋል፡፡ “ሁለተኛም፣ ከመቅደላ ወደሸዋ ሰመለሡ ከወጋቸው ከአቶ በዛብህ ጀምሮ እስከ እምባቦ ጦርነት ላይ ለንጉሥ ተክለ ሃይማኖት እስካሳዩት” የመንፈስ ልዕልና ድረስ፣ “የወጋቸውንም እንኳን በክብር የመያዝና በእርሳቸው አመራር አምኖ ጠቃሚ የሚሆንበት ዕድል የመስጠት ችሎታ ነበራቸው፤” በማለት ከፍ-ያለ ዋጋ ይሠጧቸዋል(ገጽ 166-7)፡፡

“አፄ ምኒልክ አጠፏቸው የሚባሉት ነገሮች በብዛት፣ አፄ ዮሐንስ ንጉሠ ነገሥት ሳሉ በአፄ ዮሐንስ ትዕዛዝና አውቅና የተፈፀሙ እንጂ በአፄ ምኒሊክ ጉልበተኛነት ወይም ግፈኝነት የተፈፀሙ አይደሉም!” ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ “የደቡቡ፣ የምስራቁም ሆነ የምዕራቡ የአፄ ምኒሊክ ዘመቻዎች ያለአፄ ዮሐንስ እውቅናና ትዕዛዝ የተደረጉ አልነበሩም፡፡ ሆኖም ግን፣ ታሪክ ያላነበቡት ወያኔዎችና ሻዕቢያዎች፣ እንዲሁም የቄሣራዊያን የታሪክ ቅጥረኞች ሆን ብለው ታሪካችንን ለማክሸፍና ዋጋ ለማሳጣት ሲሉ፤ እየተቀባበሉ የደንቆሮ ለቅሷቸውንና ሙሾአቸውን ያወርወዳሉ፡፡” ይህንን የመሠለ መሰሪ የተቀነባበረ የፖለቲካ ቁማር የሚጫወቱ ሁሉም፣ ዞሮ-ዞሮ አንድ ዓላማና ግብ ያላቸው ኃይሎች ናቸው፤ እርነሱም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ለዘመናት የተገነባ የሕዝቦች ሕንፃ ለማፍረስ የሚፈልጉ-ከሐዲዎች ናቸው-ብለዋል (164-169)፡፡ ጀግናውን ራስ አሉላ አባነጋንም አውስተው፤ “የሥራቸውን ዋጋ ሳያገኙ ሞቱ፤” ሲሉ ይቆጫሉ(ገጽ 114)፡፡

ከነዚህ የታሪክ ሠሪዎችና ከፕ/ር ስርግው በስተቀር፣ ብዙዎቹን ኢትዮጵያዊያን በአራት ዓምዶች ስር ሰድረው ይተቿቸዋል፡፡ የመተቻ መስፈርቶቹንም ተጠቅመው የአንባቢያንን ሕሊና ለማንቃት ያደረጉት ጥረት የሚደነቅ ነው፡፡ እዚህም እዚያም ተሰባጥረው የሚገኙትን ነጥቦች “መክሸፍ፣” “ታሪክ”፣“ድንበርና-ወሰን”፣ እንዲሁም “ቄሣራዊ ኃይሎች” ባሏቸው አኃዞች አደላዳይነት “የኢትዮጵያን ታሪክና ደንቃራዎቹን”፣ በፈርጅ-በፈርጁ ሊያደራጁ ጥረት አድርገዋል፡፡ ሙከራቸውም ፈሩን ያለቀቀ ነበር፡፡…. የአንድ ትምህርት ዘርፍ ጥገኛ ለመሆን ስላልፈለጉም፤ ከታሪክም፣ ከፖለቲካም፣ ከስነ-ቃልና ከባሕላችንም ውስጥ ጠቃሚ የሆኑትን ሃሳቦችና ነጥቦች ተፈላልገው በማጠናቀር ከመጀመሪያው አስከ መጨረሻው የአንባቢን ቀልብ ለመግዛት ተፍጨርጭረዋል፡፡

ይሁንና፣ ምንም እንኳን የገለልተኛነት መንገድን ለመውሰድ ቢጥሩም፣ የስሜታቸው ተከታይ ከመሆን አላመለጡም፡፡ በገጽ-64 ላይ እንደጠቀሱትና ለስቬን ሩቢንሰን በ1969ዓ.ም እንደነገሩት፣ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው “ኢትዮጵያ ስትደማ አብሬ እየደማሁ፤ እንዴትስ ስሜት አይኖረኝም?” በማለት ራሳቸውን ያጋልጣሉ፡፡ “የኢትዮጵያ ታሪክና ቄሣራውያን ምሁራን” የሚለው ምዕራፍ ሥርም፣ የደራሲውን የሃሳብ አካሄድና የአስተሳሰብ ፈለግ በይበልጥ የሚመሰክር ነው፡፡ “ታሪክ የሁነቶች ድርደራ አይደለም፤ የተዋናዮቹን ‘አስተሳሰብና ስሜት፤ ጨዋነትና ብልግና’ የሚሉትን፤ ‘ክብርና ውርደት’ የሚሆንባቸውንም የጨምራል፤” ይላሉ(ገጽ-63)፡፡ አያይዘውም፣ ታሪክ የሁነቶች ገለፃ/Descriptive/ ብቻ አይደለም፤ ስነ-ሰብዕ/Ethnographic/ ጭምርም መሆን አለበት-የሚሉ ይመስላል፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ ከውጭ ሆነው የሚያጠኑት የውጭ አገር ዜጎችም ሆኑ በውጭ አገር ዩኒቨርሲቲዎች መሽገው የሚያጠኑት ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን የታሪክ “ሊቆች!” – “ስለኢትዮጵያ ምንም ስሜት የላቸውም፡፡ ስለሆነም፣ ኢትየጵያ ስትደማ አብረው አይደሙም፡፡” በተለይ-በተለይ፣ “በአውሮፓም ሆነ በአሜሪካን የሠለጠኑት የታሪክ ባለሙያዎች፣ ለኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያውያን ቋንቋ ከመጻፍ ይልቅ፣ በባዕዳን ቋንቋዎች ለባዕዳን ነው የሚጽፉት” ብለዋል(ገጽ-65)፡፡ በዚህም አተያይ፣ እንደፕ/ር “ባሕሩ ዘውዴ ያለው፣ አንድ አስተማሪው ያስታጠቀውን ጉዳይ” ይዞ “የማያውቀውን ነገር ይጽፋል” ሲሉ አብጠልጥለዋል(ገጽ-8/9)፡፡ ቀጥለውም፣ “ዱሮም ሆነ ዛሬ የታሪክ ጸሐፊዎቻችን ትኩረታቸው በእንጀራቸው ላይ ነው፤” ሲሉ ዜና መዋዕል ጸሐፊዎቹንም ሆነ ዘመናዊዎቹን የታሪክ “ጸሐፊዎች” ያለርሕራሔ ተችተዋል (ገጽ-76)፡፡

ዘመናዊዎቹ ታሪክ ጸሐፊዎችና አስተማሪዎቻቸው የፈለጉትን ያህል ቢሳሳቱም እንኳን፤ በገጽ 54 እና 56 ላይ እንደገለጹት፤ “የኢትዮጵያ ታሪክ እየተጠናከረ መሔድ የጀመረው፣ ዋናዎቹ የኢትዮጵያ ታሪክ ጸሐፊዎችና አስተማሪዎች የውጭ አገር ሰዎች” መሆን ከጀመሩ በኋላ ነው-በማለት እውቅና ይሰጣሉ፡፡ ሆኖም ይላሉ መስፍን፣ “ለምን ነጮቹ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርጉት ጥናት ስለዘር፣ ስለቋንቋና ስለባህል ብቻ ሊሆን ቻለ?” በማለት ይጠይቁና፣ ምክንያቱም ግልጽ ነው-ይላሉ፡፡ “እኛን እንደፈለጉ አድርገው ሊቀርጹን የሚያደርጉት” ቄሣራዊ ሙከራቸው አካል ነው፤ ሲሉ በአጽንዖት ይገልፃሉ፡፡ “እኛን እንደጥቁር ሰሌዳ፣ እነርሱንም እንደነጭ ጠመኔ ያለ ባሕርይ ሠጥተን መቀበላችንንም፤” በብርቱ ይቃወማሉ፡፡ ትልቆቹን ቄሣራውያን ምሁራን፣ ለምሳሌ እንደትሪንግሃምና ዶናልድ ሌቪን የመሳሱትን በስም ጠቅሰው፣ “ብዙ የመረጃ ምንጮቻቸውን ሳይመረምሩ፣ የፋሺስቶችን ትምህርትና ልዩ ቄሣራዊ ዓላማ አነግበው/ስላላቸው፤” የኢትዮጵያን ታሪክ አጎደፉ፤ ሲሉ አማረዋል(ገጽ-59-60)፡፡ በሶማልያና በቄሣራዊ ፓስፖርትና ቪዛ የሚምነሸነሹት እነበረከት-አብ ሀብተ ሥላሴም ኢትዮጵያን መካዳታቸው ሣያንስ፣ የሀሰት ታሪክ መጻፍን “የእንጀራቸው” መብያ አድርገውታል ሲሉ ይንገበገባሉ(ገጽ-179)፡፡

የፕ/ር ታደሰ ታምራትንና የፕ/ር መርድ ወልደ አረጋይንም ጥናቶች አንድ ባንድ አያወሱ፣ ከገጽ 90-103 ባሉት ሃተታዎች ውስጥ በእጅጉ ይሞግቷቸዋል፡፡ “ለኢትዮጵያ ልዩ ተፈጥሮና ባሕል፤ በተለይም የኢኮኖሚውና የኑሮው ሁኔታ የፈጠረውን የፖለቲካና የአስተዳደር ሥርዓት በመመርመር-ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ታሪክ የሚያገኙአቸውን የፖለቲካ ሁነቶች መሠረት አድርገው ባለመነሳታቸው፤ ስሕተት ላይ ወደቁ” ብለዋል(ገጽ-88)፡፡ በተለይም፣ ታደሰ ታምራት “ስቴትና ኢምፓየር (State and Empire) የሚሉትን ከአውሮፓ ባሕልና ታሪክ መድረክ የፈለቁ፣ ተለዋዋጭና የተወሳሰበ ታሪክ ያላቸው ሐሳቦች” ለኢትዮጵያ ተጠቅመው፣ ለቄሣራውያን አስተሳሰብ መሣሪያ ሆኑ-ብለው ተከራክረዋል(ገጽ-90)፡፡ በተጨማሪም፣ ፕ/ር ታደሰ መጽሐፍ “ከሣርና ከቅጠሉ በስተቀር፣ የኢትዮጵያን ሁኔታ ሁሉ በሃይማኖት ሚዛን ይለካል፤” ያም ስሕተት እንደሆነ አሳይተዋል(ገጽ-91)፡፡ ፕ/ር መርድንም አንስተው፣ ስለኢትዮጵያ ወሰንና ዳር-ድንበር ሲያጠና “አልቫሬዝ ስለደጋው የኢትዮጵያ ወሰን የጻፈውን “ተረት ነው” ብሎ አጣጥሎ፣ ለቆላማው ኢትዮጵያ ሲሆን ግን ያለማመንታት ይቀበለዋል፡፡ ያንንም የተዋሰው ከማርጀሪ ፐርሃም ሀሳብ ነው፡፡” በመሆኑም፣ ‘መርድ ሳያውቀው፣ ለቄሣራውያን ተንኮል የድምጽ ማጉያ ሆነ!’ ለማለት ይቃጣቸዋል(ገጽ-101/2)፡፡

ወደ“መክሸፍ”ና ስለኢትዮጵያ ታሪክ አከሻሸፍ ያወሱትን ለማጤን እንሞክር፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን “ከሻፋ” ነገሮች በሦስት ከፋፍለዋቸዋል፡፡ እነርሱም፤ ጨርሰው የከሸፉ(ገጽ-19)፣ በመክሸፍ ላይ-ያሉ(ገጽ 11-18)፣ እና እስከዘመናችን ድረስ ያለከሸፈ(ገጽ-10) በማለት፡፡ ያለከሸፈው “ለነፃነትና ለክብር በመስዋዕት” መሆኑ ብቻ ነው፡፡ በተረፈ፣ በገጽ-26 ላይ እንዲህ ይላሉ፤ “በኢትዮጵያ በኳስ ጨዋታው ሳይቀር መክሸፍ ጎልቶ ይታያል፤ በረጅም ርቀት ሩጫም ቁልቁለቱን የጀመርነው ይመስላል፡፡ ከባሕር ጠለል አካባቢ የሔደው ሶማሊያዊው ሞ ፋራህ፣ ደገኞቹን (ከደጋማው የኢትዮጵያ ክፍል የሔዱትን ሯጮች) ቀደማቸው፡፡ መክሸፍ ባህላችን መሆኑ ግዴታ ነው እንዴ?!” ለነገሩማ፣ “ከሸፈ ወይም እከሌ አከሸፈው እንላለን እንጂ፣ እኛ ራሳችን ከሽፈን-አከሸፍነው አንልም!” ሲሉ ይገሥፃሉ(ገጽ 29-31)፡፡

በመጨረሻም፣ ከበድ ያለና ተገቢ ማሳሰቢያ ለአንባቢያኑ ያቀርባሉ፡፡ በገጽ 104 ላይ ስለሦስቱ የቄሣራውያን ኃይሎች ግዛት ለማስፋፋት የሚጠቀሙባቸውን ዘዴዎች ተንትነው ሲያበቁ፤ በገጽ 145 ላይ ደግሞ ለምን ቄሣራውያን የኢትዮጵያን ለመግፋትና ወሰኗን ለመማጥበብም እንደፈለጉ የሚያሳዩ “ሦስት መሠረታዊ ጥቅሞቻቸውን” ከበቂ ማብራሪያና ማስረጃዎች ጋር ያቀርባሉ፡፡ እነዚህንም፣ የቄሣራውያንን ሴራዎችና ተንኮሎች ሳንረዳ የምንቀር ከሆነ፣ በውጫዊው የቄሣራውያን ግፊትና ሴራ መክሸፋችን እንደማይቀር ያስገነዝባሉ፡፡ “በመሆኑም፤” ይላሉ ፕ/ር መስፍን፣ “በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ መክሸፍ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት” ቦታ የያዘ መሆኑን ገልጸው(ገጽ-8)፤ “ከ1928ዓ.ም ወዲህ ግን፣ የክሽፈቱ ዓይነት የተለየ ሆኗል፡፡ ስለዚህም፣ ማኅበረሰባዊ ችግሮችንና ለሥልጣን የመስገብገብ ጉዳዩንም አስከፊ አድርጎታል”(ገጽ-12) ይላሉ፡፡ ስለሆነም፣ “የሥልጣን ምንጭ ሙሉ-ለሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆኖ፣ ሰው ለሰው የሚገዛበት ሥርዓት እስካልፈረሰና፣ ዜጎች በሕግ ፊት እኩል መብትና እኩል ግዴታ ያለባቸው መሆኑ በተግባር እስካልተረጋገጠ ድረስ” መክሸፋችን አይቀሬ መሆኑን ጠቁመዋል(ገጽ-201)፡፡

እስቲ ደግሞ ስለመጽሐፉ የቋንቋ አጠቃቀም ጥቂት ነጥቦችን እናንሳ! “መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ፤”፣ በቃላት አሰካክና አደራደሩ ስርዓትን የተከተለ ነው፡፡ ቃላቱ፣ ለአጫፋሪነትና ለአዳማቂነት ፈፅሞ ልሰፈሩም፡፡ ቀልብን ገዝተው መደመጽሐፉ ማብቂያ ያንደረድራሉ፡፡ ሆኖም፣ እዚህም-እዚያም የፊደል ግድፈቶች ታይተዋል፡፡ ለምሳሌም ያህል፣ በገጽ-53 ላይ “ሲጀምር” የሚለውን “ሺጀምር”፤ በገጽ-78 ላይ “ያተረፉ” የሚለውን “ያተረፋ”፤ በገጽ-88ም ላይ “ሁነቶች” የሚለውን “ሁነትች”፤ በገጽ-93 ላይም “አማርኛው” የሚለውን “አማራኛው”፤ በገጽ-127 ላይም “መሀከል” መሆን ሲገባው “በሀከል”፤ በገጽ-168ም ላይ “ኢትዮጵያ” የሚለውን “ኢጥዮጵያ”፤ እና በገጽ-194 ላይ ደግሞ “የሚተላለፍ” ለማለት “የሚታላለፍ” የሚሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ከሁሉም-ከሁሉም ግን፣ በገጽ-9 ላይ የወጣው ስም ስህተት ሊታለፍ አይገባውም፡፡ ፊታውራሪ “ተክለ ሐዋሪያት ተክለ ማርያም” መባል ሲገባው፣ ልጅየው “ግርማቸው” ያለቦታቸው ተተክተዋል፡፡ ከገጽ-12 እስከ 14 ባሉት አንቀጾችም ውስጥ፣ ዓ.ም(ዓመተ-ምህረት)ና ምዕተ-ዓመት(ም.ዓ – የሚባል አጠቃቀም ካለም ነው፣) ተዛንቀዋል፡፡ መጽሐፉ በድጋሚ ሲታተምም፣ እነዚህን የፊደልና የስም ግድፈቶች አርሞ እንደሚወጣም እምነቴ ነው፡፡

ማጠቃለያ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገራት ላሉት አንባቢያን፣ መጽሐፉ እንደልብ ገበያ ላይ ይገኛል፡፡ ዋጋ የሚፍቁና የሚደልዙ ወገኖች እንዳያጭበረብሯችሁ፣ ዋጋው አርባ አምስት/45/ ብር ብቻ መሆኑን በድጋሚ ልናስታውሳችሁ እንወዳለን፡፡ በውጭ አገራትም ያላችሁ፣ በሃያ/20/ ዶላር ገዝታችሁ ለማንበብ ወደ ኢሳት-ስቶር http://ethsat.com/store/ ጎራ በሉ፤ ታገኙታላችሁ፡፡ መጽሐፉን “ይፋ ባልሆነው ማተሚያ ቤት” ያሳተሙትን, ፕ/ር መስፍንና ተባባሪዎቻቸውን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን፡፡ እንዲሁም፣ መጽሐፉን በመተየብና የአርትኦቱም ስራ ያገዙትን ሁሉ፣ በአንባቢያኑ ስም “ክብረት ይስጥልን!” ልላቸው እመዳለሁ፡፡ (የሳምንት ሰዎች ይበለን!)

የFBI መርማሪዎች አበበ ገላውን ለመግደል የታቀደ ሴራ አከሸፉ – በሴራው የተሳተፉ የህወሃት ሰላዮች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው

ታህሳስ  ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን አንድ የአሜሪካ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ (FBI) ግበረሃል ባለፈው ወር መባቻ ላይ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ወደ ቦስተን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅትOne of TPLF spies who involved in Abebe Gellaw assassination attempt. በተጓዘበት ወቅት የግድያ ወንጀል ለመፈጸም በመዶለትና በማስተባበር ተግባር ላይ ተሰማርቶ የነበረና ለህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሰልል የሚጠረጠር ግለሰብ እና በግብረአበሮቹ ላይ ከፍተኛ ምርመራ መክፈቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጡ።

በአሜሪካ ሀገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ የሚኖረውና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ የዘር ድርጅት አባል እና ሰላይ እንደሆነ የሚታመነው ግኡሽ አበራ በመባል የሚጠራው ይሄው ግለሰብ ጋዜጠኛውን ለመግደል በማሴር ሶስት የወንጀሉ ተባባሪ የሚሆኑ ግለሰቦችን  መመልመሉ ንና ድርጊቱን ለመፈጸም መሰናዶ ማድረጉን የFBI መሪማሪዎች  ደርሰውበት ሴራውን በግዜ ማክሸፋቸው ተረጋግጧል።

ግለሰቡ ወንጀሉን ከመፈጸሙ በፊት የተለዋወጣቸው መልእክቶች የFBI ወንጀል መርማሪዎች እጅ በመግባታቸው ሳቢያ እርሱና አብረው የሚኖሩ ሌሎች አራት ግለሰቦች ላይ ክትትልና ምረመራ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል። ከተባባሪዎቹ ጋር  የተለዋወጣቸው መልእክቶች ጋዜጠኛ አበበ ገላው ወደቦስተን የመሄዱን አጋጣሚ በመጠቀም በመሳሪያ ተኩሶ የመግደል እቅድ አውጥቶ ድርጊቱን ለመፈጸም ወይንም ለማስፈጸም ይንቀሳቀስ እንደነበር በግልጽ እንደሚያሳዩ ታውቋል።

የቦስተን ቅርንጫፍ FBI ቃል አቀባይ እና ልዩ መርማሪ ( special agent) የሆኑት ግሬግ ኮምኮዊች በምርመራው ሂደት  ላይ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ቢቆጠቡም፣ FBI እንዲህ አይነት ወንጀሎችን በ ቸልታ እንደማያልፍ ገልጸው በውጭ መንግስታት ሰላዮችም ሆነ ተወካዮች የሌሎችን ሰብአዊ መብቶችን በሚገፍ ህገወጥ ወንጀል የተሰማሩ ካሉ ኢትዮጵያዊያን በቸልታ ማልፍ እንደማይገባቸው እና በአካባቢያቸው ለሚገኙ የFBI  ቅርንጫፎች ጥቆማ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበዋል። መርማሪው አክለውም FBI እንዲህ አይነቱን ጥቆማ በአግባቡ ትኩረት እንደሚሰጠው ገልጸዋል። “

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በመተቸት የሚታወቁት የጄኖሳይድ ወች ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ግሪጎሪ ስታንተን የግድያ ሴራውን ያከሸፉትን የFBI መርማሪዎች አድንቀው ፣ ህወሃት አሸባሪ ድርጅት መሆኑ ታውቆ ከኢትዮጵያ አልፎ በአሜሪካን ሀገር እንዲህ አይነት ወንጀል ሊፈጽም መንቀሳቀሱ በችልታ አይታይም ብለዋል።

በካምቦድያ በሰው ልጆች ላይ አስከፊ ሰቆቃና ጭፍጨፋ የፈጸሙ የካሜሩዥ ባለስልጣናትን ለፍርድ በማቅረብ አለማቀፍ እወቅና ያገኙት ፕሮፌሰር ስታንተን እንዲህ አይነቱ ወንጀል ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

ግኡሽ አበራን በቅርብ የሚያውቅ አንድ ኢትዮጵያዊ የቦስተን ነዋሪ፣ ግለሰቡ ከከፍተኛ የህወሃት ባልስልጣናት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለውና የቀድሞው አምባገነን መሪ የመለስ ዜናዊ አምላኪ እንደነበር፣ የእርሱ መዋረድና መሞት በጣም ካበሳጫቸው በአሜሪካ የሚኖሩ በርካታ የህወሃት ጀሌዎች አንዱ መሆኑን ገልጿል። በማከልም “ከሁሉ የከፋው ግለሰቡ በዘረኝነት ዛር የተለከፈ ስለሆነ ህወሃቶች እንዲህ አይነቱን ሰው ለእኩይ አላማቸው መጠቀማቸው የተለመደ ነው፣”  በማለት አስረድቷል::

ጋዜጠኛ አበበ ገላው “ህወሃት አሸባሪ የማፊያ ድርጅት መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት የነበሩብኝን የጽጥታ ስጋቶች ችላ ባለማለት ለሚመለከታቸው የህግ አስከባሪ አካላት ከማመልከት አልፌ የቤተሰቤንም ሆነ የራሴን ደህንነት ለማረጋገጥ ቀደም ብዬ እርምጃ ወስጃለሁ ወደ ፊትም እወስዳለሁ” ብሏል።

የFBI መርማሪዎች ወንጀሉ እንዳይፈጸም አስቀድመው እርምጃዎችን የወሰዱ ሲሆን ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ቦስተን ውስጥ ሮክስቤሪ በመባል በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን እና ግኡሽ አበራ ከሌሎች አራት ኢትዮጵያዊን ጋር በጋራ ይሚኖርበትን ቤት የበረበሩ ሲሆን፣  ወደ ሁለቱ የቤቱ ነዋሪዎች ስራ ቦታ ድረስ በመሄድ ምርመራ ማድረጋቸው ተረጋግጧል።

የዳዉሮ ህዝብ አመጽ እንደገና ሊያገረሽ ነው

“እውነትና ፍትህ በሌለበት ሀገር ኑር አትበሉኝ!”

ረ/ሳጅን ሽታዬ ወርቁ ሺበሺ
የዳውሮ ዞን ፖሊስ ባልደረባ
(ዋካ ከስዊድን)

መግቢያ

የዳውሮ ሕዝብ የደረሰበትን የመልካም አስተዳደር እጦት፤ በአቅራቢያው ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት አለመቻል፤ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ሕዝቡ ለሚያቀርበው የመብትA memorial service for Yenesew Gebre የፍትህና የዴሞክራሲ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ያለመስጠት፤  በየወቅቱ በሚፈራረቁ የሥልጣን ተረኛ በሆኑት የህወሐት/ ደኢህዴን ካድሬዎች የግል ፍላጎትና ውሳኔ ብቻ የወረዳ ማዕከል እየተወሰነ ከመንደር ወደ መንደር በመዘዋወሩ የተነሳ ማሕበራዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት አለመቻል አበሳጭቶት ወደ አምጽ ማምራቱን በመዘርዘር ከዚህ በፊት በሦስት ክፍሎች ያዘጋጀሁትን ጽሑፍ ማስነበቤ ይታወሳል።

አሁንም በሕወሃት/ ደህዴን ካድሬዎች ተንኳሽነት የተነሳ የሕዝቡ ቁጣ እንደገና እያገረሸ መጥቷል። እስሩ ማንገላታቱ ከሥራ ማባረሩ ተጀምሯል። የሕዝቡ ጥያቄ የሚታወቅና ግልጽ ነው። ከሚዲያና ከካድሬዎች የሚነገረውን የሀገሪቱን  የኢኮኖሚ የልማትና እድገት ፕሮፓጋንዳ ባሻገር ድርሻውን ማግኘት ቀርቶ በአይኑ ለማየት አለመቻል፤ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለማግኘት ያለመቻላቸውና የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየናረ መምጣት፤ አንድ አርሶ አደር ወደ ወረዳ ማዕከል ለመድረስ ከአንድ ቀን በላይ ለሚፈጅ ጊዜ በእግሩ መጓዝ የግድ እየሆነበት ስለመጣና ይህም ስላሰለቸው፤ ያላግባብ እንዲርቀው የተደረገው የወረዳ ማዕከል በሚፈልገውና ወደ ሚቀርበው ሥፍራ እንዲዛወርለት ያቀረበው ተደጋጋሚ አቤቱታ ሰሚ ሊያገኝ አለመቻሉ፤ ጥያቄውን ለመንግሥት በየደረጃው  በተደጋጋሚ አቅርቦ መፍትሄ አለማግኘቱ ሕዝቡን በጣም አሳዝታል። በዚህም የተነሳ የዳውሮ ዋካን ሕዝብ ጥያቄ ያነገበው ጀግናው ሰማዕት መምህር የኔሰው ገብሬ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን በደልና የመልካም አስተዳደር እጦት በመቃወምና ድርጊቱን በማውገዝ ራሱን በእሳት በማቃጠል መስዋዕትነት መክፈሉ ይታወቃል። ይህም ሆኖ የዳውሮ ሕዝብ በደል መፍትሄ እስካሁን ሊያገግኝ አልቻለም።

የተቃውሞው እንደገና መቀስቀስ ምክንያት

ህወሐት/ ደኢህዴን በደቡብ ክልል በአንዳንድ ዞኖች ውስጥ በተደጋጋሚ የሚነሳበትን የህዝብ ተቃውሞ መቀነስ ስለሚችልበት ሁኔታ ተወያይቶ ነበር። በዚህ ውይይት ላይ በዋናነት የተነሳውና የታመነበት ነጥብ የተጨማሪ ወረዳ ጥያቄና የወረዳ ማዕከል ጉዳይ ሆኖ በውይይቱ ጎልቶ ወጣ። በመቀጠልም እንዴት አድርገው የህዝቡን ቁጣ ማርገብ እንደሚቻልና ምንም ተጨማሪ ወረዳ ሳይሰጥ ሕዝቡን የማሳመን ሥራ መሥራት እንደሚገባ ታምኖበት ለአፈጻጸም ለሚመለከተው የፖለቲካ ኃላፊዎች እንዲያስፈጽሙት ስልጠና ተሰጥቶ ወደ ሕዝቡ እንዲወርዱ ተደርጓል።

በውይይቱ ላይ በአንክሮ የተነሳው የቀድሞው ሰሜን ኦሞ ዞን ሥር የነበሩት ዞኖች መካከል የጋሞጎፋና የዳውሮ ዞኖች ህዝብ ጉዳይ ነበር። በዚህ መነሻነት የዞን አመራሮች ሕዝባቸውን የማሳመን ሥራ እንዲሰሩ የሚያስገድድ መመሪያ ለዞኑ የፖለቲካ አመራርች ይወርዳል። አመራሮቸ እንዲያስፈጽሙ ታዘዙ። በዚህ መነሻነት ነው እንግዲህ   በእስርና በእንግልቱ ሳቢያ ዝም ያለና ጊዜ የሚጠብቅ፤ ግን ውስጥ ውስጡን እየፋመና እየጋመ የነበረን የህዝብ ብሶት እንደገና ቀሰቀሱት።

የዳውሮ ህዝብ ያቀረበው የፍትና የመብት ጥያቄ በመሆኑ ከዛሬ ነገ ይመለስልኛል ብሎ በሚጠበቅበት ወቅት  መንግሥትና ገዢው ፓርቲ ጥያቄውን ለማድበስበስና ከሕዝቡ የተሻለ ለሕዝቡ አሳቢ በመምሰል ወረዳ ምን ያደርግላችኋል? ልማት ነው የሚያስፈልጋችሁ! ከልማትና ከወረዳ ምረጡ! ተጨማሪ ወረዳ አይጠቅማችሁም! የወረዳ ርእሰ ከተማ ቢርቅባችሁም ራቀብን አትበሉ! ዝም በሉ! እንዲያውም ፍትህ ፍለጋ ስንቅ ተሸክማችሁ በእግራችሁ ረጅም ሰዓት በመጓዛችሁደስ ደስ ሊላችሁ ይገባል! የሚል ስሜት ያዘላ አድራቂ ፕሮፓጋንዳ ሕዝቡን ለማወናበድ እየተሞከረ ይገኛል። የመንግሥት ሠራተኛው የህዝብ ልጅ እንዳልሆነና የሕዝብ በደልን የማይረዳ በማስመሰል ከሕዝቡ ሓሳብ በተቃራኒው ከአመራሮች ጎን እንዲቆም ለማድረግ በየወረዳው ካድሬ ተመድቦ ተግቶ እንዲሰራ ይደረጋል።

ካድሬዎች በሕዝቡ መካከል እጅግ የሚገርምና ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው ሥራ ጀመሩ። የማረቃ ዋካ ወረዳ ዋና ከተማ ዋካ ይሁንልን የሚልን የህዝብ ጥያቄ ለማፈን የማይቻል መሆኑ ግልጽ ነው። በማሰር በማፈን በሐሰት በመክሰስና በመወንጀል በማስፈራራት ጥያቄውን ምላሽ እንዳያገኝ ማድረግ አምና ተችሏል። ይህ ማለት ግን ሕዝቡ ጥያቄውን ትቶታል ወይም መልስ አግኝቷል ማለት አይደለም። የወረዳው ማዕከል አያማክለንም የሚለውን የሕዝብ ጥያቄ ለማፈንና ምላሽ ላለመስጠት ሲባል ለዘመናት አብሮ የኖረንና ቤተሰብ የሆነውን የማሪና አካባቢውን ሕዝብ በመቀስቀስና በዋካ ከተማ ሕዝብ ላይ ለማነሳሳት መቀስቀስ ቀጠሉ።

የማረቃ ወረዳ ሕዝብ ከቆዳ ስፋቱና ከሕዝብ ቁጥር አንጻር እንዲሁም ጂኦግራፊያዊ አቀማመጡ የተነሳ ሁለት ወረዳ ሊሆን ይገባል የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢነት ያለው ነው። በዚህ የተነሳ ዋካና ማሪ ሁለት የተለያዩ ወረዳዎች መሆን ይገባቸዋል የሚል ሐሳብ ይዞ መነሳት ነው የተጨማሪ ወረዳ ጥያቄ ማለት። ነገር ግን ቀድሞ የነበረን ወረዳ የወረዳው ማዕከል ይርቀናል አያማክለንም የሚልን ጥያቄ ለማፈን ሌላ ተገቢ ያልሆነ ቅስቀሳ ሕዝብ ውስጥ መርጨት ተጀመረ።

በምንም ዓይነት ሁኔታየኢትዮጵያ ዋና ከተማ ኬንያ ጠረፍ የሚገኝ ቀበሌ ሊሆን አይችልም። የትግራይ ክልል ዋና ከተማ ደሴ አልተደረገም። ዳውሮ ውስጥ ብትመለከቱ ግን ሁኔታው የተለየ ነው። የሎማዲሳ ወረዳ  ዋና ከተማ ገሳ ጨሬ ይባላል። ይህ አዲስ የተቆረቆረ ከተማ ያለው በአጎራባቹ የጌና ቦሳ ወረዳ ውስጥ ነው። የሎማ ዲሳ ወረዳ ሕዝብ የጠየቀው የወረዳችን ዋና ከተማ ከአጎራባች ወረዳ ወጥቶ ቢያንስ እንደቀድሞው ወደ ወረዳችን መሐል አካባቢ ተመልሶ በሚያማክለን ሥፍራ ይደረግልን ነው። ይህንን ጥያቄ አይቶና ሰምቶ መፍትሔ የሚሰጥ አመራር የለም።

በመንግሥት ውሳኔ የተጣመሩ ወረዳዎች ዳግም በመንግሥት ውሳኔ ተለያይተው ቀድሞ ወደነበሩበት እንዲመለሱ ሲደረግ የወረዳው ማዕከል ጉዳይ ወደ ሕዝቡ ወርዶ ውይይት ተደርጎበት ሊወሰን ሲገባ ይህ ሳይሆን ቀርቷል። ታዲያ ይሄ ስህተት የማነው? የሕዝቡ ነው ወይስ የአመራሩ ነው? ከዲሳ አካባቢ ለምሳሌ ቃኢ ጌሬራና ከዚያ ርቆ የሚኖር አንድ አርሶ አደር የወረዳውን አስተዳደር ፍለጋ አንድ ቀንና ከዚያ በላይ መጓዝ አለበት የሚል የወረዳና የዞን አመራር እውነት ለህዝቡ የቆመ ነው? አመራሩ ለምንድነው የሚመራውን ሕዝብ  የማይሰማው? እውነት አሁን የዲሳ አካባቢ ህዝብ ወደ ገሳጨሬ እንዲመላለስ ተገቢ አይደለም ያለ የመንግሥት ሠራተኛ ሊዋከብ ሊታሰርና ከሥራ ሊታገድ ተገቢ ነው?

የዳውሮ ህዝብ የወረዳ ማዕከል ለአቤቱታ ሲሄድ እንደ ዘመነ ምንሊክ ከቤቱ ስንቅ ቋጥሮ በእግሩ ከአንድ ቀን በላይ በመጓዝ ላይ ይገኛል። በሎማ ወረዳ ዲሳ አካባቢ አገልግሎት ማለት ጋሞ ጎፋ ዞን አዋሳኝ አካባቢየሚገኝ ቀበሌ ማለት ነው። ከዚያ ተነስቶ አንድ አርሶ አደር የወረዳው ማዕከል ወደተሰደደበት ሌላ ወረዳ ማለትም ጌና ቦሳ ወረዳ ከአንድ ቀን በላይ መጓዝ ግድ ይለዋል። ከዚያ በኋላ ተጨማሪ የመኪና ጉዞ አድርጎ ነው ገሳ ጨሬ የሚደርሰው። ይህ ነው እንግዲህ እውነቱ። ልዩነቱ ጥቂት የእግር ጉዞ ሰዓታት ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ችግሩ በቶጫም ሆነ በማረቃ ወረዳዎች ተመሳሳይ ነው።

የሎማን ወረዳ ምሳሌ አነሳሁ እንጂ የቶጫ ወረዳም ቢሆን ተመሳሳይ ነው። ተርጫ አጠገብ ዋራ አካባቢ የሚኖርን አንድ አርሶ አደር ከጪ ድረስ ተጉዞ ፍትህ እንዲያገኝ ማስገደድ ምን ይባላል? ከጪ ኢሰራ ወረዳ አጠገብ ነው። ቀደም ሲል ኢሰራና ቶጫ ወረዳዎች እንዲጣመሩ በተደረገ ጊዜ ሁለቱን ወረዳዎች እንዲያማክል በሚል የተመሰረተ ከተማ ነው። ወረዳዎች ወደነበሩበት እንዲመለሱ ሲወሰን የኢሰራ ወረዳ ከተማ ወደ ቀድሞው ማዕከል ሲመለስ ቶጫ ወረዳ ግን ቀደም ሲል ወደ ነበረበት ሥፍራ ሳይመለስ እዚያው እንዲቀጥል ተደረገ።

ይህ የሕዝብ ጥያቄ ሕብረተሰቡን ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ያስተባበረና እያጠናከረው የመጣ ሲሆን በገዢው ፓርቲ  ላይ ያለው ጥላቻ እያደገና እየከረረ መጥቷል። ለዚህ አስተዋጽኦ ያደረጉት ካድሬዎች ናቸው። ጀግናው የነጻነት ታጋይና ሰማዕት የሆነው መምህር የኔሰው ገብሬም “ የወረዳና የልማት ጥያቄ በማቅረቡ ወህኒ ቤት ሲያስሩት ጤነኛ የነበረ፤ ሲፈቱት ያልታመመና በሳምንቱ ራሱን በብሶት በቤንዚን አቃጠለ። በተቃጠለ በሦስተኛው ቀን ሞተና ከሞተ በኋላ ደግሞ ፖለቲከኞቹ እንዲሉት ታዘውና ተገደው እብድ ነበር አሉት።  የከፈለው መስዋዕትነት የዚሁ ትግል አካል ነበር።  ሌሎችም ለሚዲያ ያልበቁ በየወረዳው ፍትህና መልካም አስተዳደር እጦት ለችግራቸው መፍትሄ የሚሰጥ አካል አጥተው በተለያየ መንገድ ራሳቸውን ያጠፉ ሰዎች ቁጥራቸው ጥቂት አይደለም። ጊዜና ወቅት ሲፈቅድ የሚታወሱበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል።

እኛ አመራሮቹ የምንፈልገውን አስተጋቡልንም? የወረዳ ጥያቄ ለህዝቡ አይጠቅምም እያላችሁ ሕዝቡን ቀስቅሱልን! የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን ከገዢው ፓርቲ ጋር ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ መተባበር ግዴታው ነው! ይህን ካላደረግህ ጥገኛ ነህ!  በሌላ አባባል ህዝቡን ለማፈን መብቱን ለመንፈግ ተነስተናልና የመንግሥት ሠራተኛውም ከእኛ ይተባበር የሚል አስገዳጅ ውሳኔ ወስነው ለመንግሥት ሰራተኛው ጥሪ አደረጉ። ለዚህ ያልተባበረውን የመንግሥት ሠራተኛ ከሥራ በማገድ በማባረር በማሰር ወዘተ ለማስገደድና አንገቱን ለማስቀርቀር ብሎም ዝም ለማሰኘት ይቻላል በሚል እርምጃ መውሰድ ጀመሩ።ይህም የሕዝቡን ቁጣ እየቀሰቀሰው ይታያል። ረዳት ሳጅን ሽታዬ ወርቁም ታህሳስ 17/ 2005 ዓ.ም በገሳ ጨሬ ከተማ የተደረገው የመንግሥት ሠራተኞች ስብሰባ ላይ አካሄዱን ያወገዘው። ሕዝቡን ማፈን ተገቢ አይደለም ያለው።

የረዳት ሳጅን ሽታዬ ወርቁ ጥያቄና ላቀረበው ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ የተሰጠው ምላሽም የዚሁ ውሳኔ አካል ነው። በደረሰበት ጫናና እስራት የተነሳ ነው ነጻነት በሌለበት ሁኔታ ለመኖር መቸገሩን ያስታወቀው። ይህንን የሚያደርጉ ካድሬዎች ነገ ከሕዝቡ ጋር የሚኖሩ ናቸው ወይስ አይደሉም? እያልኩ ራሴን ስጠይቅ ምላሽ አጣለሁ። መንግሥትም የዳውሮ ሕዝብ ችግርን በመናቅ ጉዳዩ ለስልጣኑ ምንም የሚያሰጋው ስላልሆነ ይመስላል እስከዛሬ እያስለቀሰው ይገኛል።

ይህንን የዳውሮን ሕዝብ በደል ለማስቆም ትልቁ ጉልበት ያለው በመንግሥት እጅ መሆኑ ግልጽ ነው። መንግሥት ግን ስለ ሕዝቡ መበደል አልተገነዘበም ወይም ንቆታል አሊያም ከአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና ዳውሮ ውስጥ ከፈጠራቸው አሽከሮቹ የሚቀርበውን የሐሰት መረጃ በመቀበል ሕዝቡን እንደጠላቱ ፈርጆታል ብዬ እገምታለሁ። በመሆኑም ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለመለወጥና የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ የሚመለከታችሁ የሕብረተሰቡ አካላት የየድርሻቸውን መወጣት እንደ አለባቸው በማመን መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

መልዕክት ለሕወሀት አመራሮች

የዳውሮ ሕዝብ በደል እጅግ ተባብሷል። ለመንግሥት ያቀረበው ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ያገኛል ብሎ ተስፋ ያደርግ ነበር። የሕዝቡ ጥያቄ በአጭሩ፤ የወረዳ ማዕከል ቦታ እንዲሆን የተመረጠው ሥፍራ የወረዳውን ሕዝብ አያማክልም፤ የወረዳ ዋና ከተማ ዝውውር የተወሰነውና የተከናወነው በአንድና ሁለት ካድሬዎች የግል ፍላጎትና መነሻነት ነው፤ ስለዚህ በሕዝቡ ፍላጎትና ሕዝቡን በሚያማክል ሥፍራ ይደረግልኝ ነው። ቅን መሪ ቢኖርና የመወሰን ኃላፊነት ከተመጣጣኝ ሥልጣን ጋር የተሰጠው ዜጋ ይህን ጥያቄ ለመመለስ እንደማይቸገር ግልጽ ነው። ይህ ባለመሆኑ ሕዝቡ ተበደለ።

የሕወሀት/ ደህዴን ኃላፊና የአሁኑ “ ጠቅላይ ሚንስትር ” የሆኑት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሰሩትና የሚያከናውኑት ድርጊት የዳውሮ ሕዝብ ጥላቻቸው እስካሁን እንዳልበረደላቸው ያሳያል። የዳውሮ ሕዝብ እምነት ያለውን ጠንካራ አመራር ጠራርገው አስወግደው፤ በቀጣይም ሌላ የተሻለ መሪ እንዳይፈጠር አምክነው በግል አሽከሮቻቸው ተክተውታል። እሳቸው በስልጣን እስካሉ ድረስ የዳውሮ ሕዝብ ለማንኛውም ፍትሐዊ ጥያቄው ምንም ምላሽ እንደማያገኝ እሳቸውም ያውቃሉ፤ አሽከሮሻሸውም ለዚሁ ሳይታክቱ ይሰራሉ፤ የዳውሮ ሕዝብም ይህንኑ በሚገባ ያውቃል። ይቃወሙናል በሚል የዳውሮ ከፍተኛ ባለሙያዎች በተለያየ ሰበብ ከሥራ ገበታቸው እየተወገዱ ይገኛሉ።

የእርሳቸው ዓላማ የዳውሮ ሕዝብን ጥቅም ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ነጥቀው የራሴ ነው ለሚሉት ብሔር አሳልፈው የመስጠትና የመጥቀም ራዕይ ነው። ለምሳሌ ያህል በዳውሮ ውስጥ የተካሄደውን የሰፈራ ፕሮግራም የሥራ ክንውን፤ በግልገል ግቤ ቁጥር ሦስት የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ ግንባታ ሥራ ከባለሙያና ከአስተዳደር ሠራተኞች ቅጥር ጀምሮ ከኃይል ማመንጫው ሥራ ጋር በተያያዘ የሚከናወኑ የተከላ ሥራ እንቅስቃሴዎች ድርጊቱን መመልከት በቂ ማስረጃ ነው። በወላይታ በኩል ብቻ ግንኙነት እንዲኖረው በማሰብ የዳውሮ ጠንባሮን የገጠር መንገድ ፕሮጀክት ሥራ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው አስዘግተውበታል። የዳውሮ ሕዝብ የወረዳ ጥያቄም እስከ አሁን መፍትሔ እንዳያገኝ ያደረጉ እሳቸው ለመሆናቸው የዳውሮ ሕዝብ ጥርጥር የለውም።አሽከሮቻቸውም ለሚቀርባቸው ሁሉ ይህችን ለሕዝቡ አረጋግጠዋል።አቶ ሺፈራው ሽጉጤ የደቡብ ክልል አስተዳዳሪ በዋናነት በዳውሮ የወረዳ ጥያቄ ጉዳይ አቶ ኃይለማርያም ያሳረፉትን በደል ጠንቅቀው ያውቃሉ። ለሕዝቡ ወረዳ በመስጠት ችግሩን ለመፍታት እንኳ እንዳይችሉ ተደርገዋል።

ህወሀቶች ከአቶ ኃይለማርያምና ከግል አሽከሮቻቸው ጡጫና በደል የዳውሮን ሕዝብ ታደጉ አላቅቁትም። ታግላችሁ የደማችሁት እናንተ ናችሁና እናንተው ብትበድሉት ይሻላል እሳቸው ከሚበድሉት። በደልን ማንም በደለ ያው ነው። ግን የእሳቸው በደል ባሰበትና ነው። እርሳቸው እንደሚሉት የዳውሮ ሕዝብ አሸባሪ፤ ጥገኛና ጸረ ልማት አይደለም። የሚጠቅመውንም የማያውቅ ሕዝብ አይደለም። የወረዳና የልማት ጥያቄን ልዩነትና አንድነት ጠንቅቆ ያውቃል። ለወላይታ ሕዝብ አምስት ተጨማሪ ወረዳ ሲሰጡት አቶ ኃይለማርያም የወላይታን ሕዝብ ጥገኛ ነው አላሉም። ጭቁን ሕዝብ ነው ብለው ነበር የሰጡት። ዛሬ የዳውሮ ሕዝብ የወረዳ ጥያቄ ከወላይታ ሕዝብ ቀድሞ ያቀረበ መሆኑን እያወቁ የተዛባ ሥም ሊሰጡት አይገባም። ይህንን ለምን ታደርጋለህ? የሚል ሰው የለም! እርሳቸውና የአሽከሮቻቸው የግፍ አገዛዝ ዘመን በዳውሮ ምድር ሊያበቃ ይገባልና የዳውሮን ሕዝብ ከእሳቸው ጡጫ አውጡት።

የወረዳ ጥያቄን ለማምከን ሲባል ወረዳውን በሁለትና በሦስት መንደር ከፋፍሎ የአንዱን መንደር ሕዝብ በሌላኛው ላይ ጥገኛ ሕዝብ ነው ታገሉት ብሎ መቀሰቀስ ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው አካሄድ ነው። ሕዝብ ሁልጊዜ አብሮ የሚኖር ነው። መንግሥት እንደነባራዊ ሁኔታው ሊቀያየር ግድ ነው። የሚቀየርና የሚያልፍ መንግሥትና ገዢ ፓርቲ ለዘመናት የኖረንና ወደፊትም አብሮ የሚቀጥል ሕዝብን ጥገኛ ነው፤ የጥገኛ ሐሳብ ተሸካሚ ነው፤ ጠላትህ ነው! ወዘተ በሚል ሕዝብን በጥላቻ እንዲተያይ ማድረግ አይጠቅምም። ይህንን ኃላፊነት ለጎደላቸው ከፍተኛ አመራሮች ንገሯቸው።

መልዕክት ለዳውሮ ዞንና ለየወረዳዎቹ ካድሬዎች

የዳውሮ ወረዳዎች የማዕከል ጥያቄ የተነሳው አሁን በእናንተ ዘመነ ሥልጣን አይደለም። አሁን በስልጣን ላይ ያሉት አመራሮችም ሆኑ ካድሬዎች ለችግሩ መነሻዎች እንዳይደላችሁ እረዳለሁ። የችግሩ ምንጭ ቀደም ሲል የወረዳዎች መታጠፍና እንደገና መዘርጋት ጥሎ ያለፈው ችግር እንደሆነም አስተውላለሁ። ችግሩን ለመፍታት ከጪ፤ ገሳ ጨሬና ተርጫ ቤት የሠሩና የንግድም ሆነ ሌሎች የግል ድርጅቶችን የመሰረቱ ከፍተኛ ካድሬዎች የሚያሳርፉት ቀጥተኛ ያልሆነ ግፊትና ጫናም እንዳለ ይሰማኛል። በየወረዳው ማዕከል የተሰሩ የአመራሮችና የካድሬዎች የግል መኖሪያ ቤቶች፤ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ለዚህ የወጣው ወጪ ወዘተ ቀላል እንዳይደለም አልዘነጋም። ይህ ሁሉ ግን ከምንመራው ህዝብ መብት የሚበልጥ አይደለም።ተጠቃሚው ሕዝብ አይመቸኝም ሲል ያለው አማራጭ መቀበልና በሕዝብ ውሳኔ መገዛት ይገባችኋል።

ይህንን የቤት ሥራና የዳውሮ የወረዳዎችን የማዕከል ጥያቄ በቀላሉ መመለስ ሲችል የሰሜን ኦሞ ዞን መዋቅር ፈርሶ በ1993 ዓ.ም መግቢያ አካባቢ ዳውሮ እንደ ዞን ሲዋቀር በወቅቱ የነበሩ የፖለቲካ አመራሮች ይህንን ችግር በሚገባ አስተውለው መወሰንና በቀላሉ ማስተካከል ሲገባቸው ይህንን ችግር ተክለው እንዳለፉ ይሰማኛል። ይህ የዛሬው የዳውሮ የአያማክለኝም ጥያቄና ችግር በሂደት ሊመጣ እንደሚችል አስቀድመው ማየት የቻሉ የዳውሮ ምሁራንና ባለሙያዎች ነበሩ። አስተያየታቸውን አቅርበው እንደነበር አውቃለሁ። ወረዳዎች እንዴት በአዲስ መልክ ቢካለሉ የተሻለ ሊሆን እንደሚችል አጥንተው ያቀረቡት ነገር ነበር። ይህንን ጥናት አስፍቶ ሕዝብን ማወያየትና የተሻለ መፍትሄ ማምጣት አልተቻለም። የዚያኔ  አስፈላጊ የነበረው ወረዳና የወረዳ ማዕከል ጉዳይ እንደተራ ነገር ታይቶ መፍትሄ ሳያገኝ ቀርቷል። ሕዝብ ተንቋል።

የቶጫ ወረዳ ሕዝብ የመኪና መንገድ በመቆፈር ግንኙነት መቁረጡን አትዘነጉትም። ይህን  ያደረገ ህዝብ አቅም ቢኖረው ኖሮ ለደረሰበት በደል የተሻለ እርምጃ አመራሩ ላይ ይወስድ እንሰነበር ለመገመት የሥነ ልቡና ትምህርት አይጠይቅም። ተቃውሞውን አሳይቷል። በተመሳሳይ የዋካንና አካባቢውን  ሕዝብ የወረዳ ማዕከል ጥያቄ ባለፈው ዓመት አይታችሁታል። የዲሳን ሕዝብ ብሶት ደግሞ ሰሞኑን እያያችሁት ነው።

ጋሞ ጎፋና ዳውሮ የተለያዩ ናቸው። አቶ ታገሰ ጫፎ ወደ ደጋማው የጋሞ አካባቢ ተንቀስቅቅሶ የሕዝብ ፍላጎት የነበረውን የተጨማሪ ወረዳ ጥያቄ ለማምከን ባደረገው ጥረት ውጤታማ ሥራ ሰርቷል በሚል ተሞክሮ ይህ ሂደት በዳውሮ ሕዝብም ላይ ይሞከር በሚል የዳውሮ ሕዝብ እንደላቮራቶሪ እንዲሞከርበት አሥራ አንድ ገጽ ወረቀት ለውይይት የቀረበ ሰነድ በሚል ተዘጋጅቶ ተሰጥቷችሁ የሕዝቡን ጥያቄ ለማፈን እየሰራችሁ ትገኛላችሁ። ለዚሁም አፈጻጸም እንዲመች አስተያየት እንዲሰጥ የመናገር ዕድል ለማን እድል መስጠት እንዳለባችሁ ጭምር ተነግሯችሁ በነጻነት መናገር ለሚችሉ አርሶ አደሮች የመናገርና ሀሳባቸውን መግለጽ እንዳይችሉ በሕዝብ ስብሰባው ላይ እድል በመከልከል፤ እንቢ ብለው ከተናገሩ አቅራቢያችሁ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ በማሰር ማፈን፤ የመንግሥት ሠራተኛ ከሆነ ደግሞ በተጨማሪ ማስፈራራት ከሥራ ማገድ እንዲሁም ከሥራ ማባረር ወዘተ ተግባራዊ በማድረግ የህዝብን ጥያቄ መቀልበስ እንደሚገባ ከሰነዱ ላይ ሰፍሯል። እየሰራችሁ ያላችሁትም ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ነው። በዋናነት የጋሞጎፋ ሕዝብ ጥያቄ የተጨማሪ ወረዳ ጭምር እንጂ በጉልህ የወረዳ ማዕከል ጥያቄ አልነበረም።

ባለሙያዎች የሆናችሁ አመራሮችና ካድሬዎች በሙያችሁ ሰርታችሁ በቀላሉ መኖር የምትችሉት ዜጎች ናችሁ። እውነትን ሰርቶ ማለፍ የህሊና ቁስል የለውም። እስቲ የሚከተሉትን ጥያዌዎች ልጠይቃችሁ። ሲዳማ ዘጠኝ፤ ወላይታ አምስት፤ ቤንች ማጂ ሦስት፤ ስልጢ ሁለት፤ ጎፋም እንደዚሁ አዳዲስ ወረዳዎች ለሕዝቡ ሲሰጥ ለምን የነዚህ ዞንና ወረዳዎች አመራሮች ህዝቡን ወረዳ አያስፈልገውም ልማት ይጠቅመዋል ብለው ወረዳውን ያላስከለከሉትና ሕዝባቸውን ያልቀሰቀሱት ለምንድነው? ምናልባት አመራሩ ጥገኛ ስለሆነ ነው ትሉኝ ይሆናል። ለሲዳማ አቶ ሺፈራው፤ ለወላይታ አቶ ኃይለማርያም፤ ለስልጢ አቶ ሬድዋን፤ ለቤንች ማጂ አቶ ጸጋዬ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የነበሩት ለሕዝባቸው አዳዲስ ወረዳዎችን ሰጧቸው። እርግጠኛ ነኝ እነዚህን አመራሮች ጥገኛ ናቸው እንደማትሉ! ታዲያ ዳውሮ ውስጥ ተጨማሪ ወረዳ መጠየቅ ይቅርና የወረዳ ማዕከል ይስተካከልልኝ ብሎ ማሰብ መናገርና መጠየቅ ምነው ጥገኝነት በሚል ፍረጃ ውስጥ የሚያስገባ ሆነ? የዳውሮ የወረዳ ማዕከል ጥያቄ ለምን ከልማት ጋር ይያያዛል? እናንተ ለህዝባቸው ወረዳ ከሰጡት ባለስልጣናት የምታንሱት ሕዝባችሁን ስለማትወዱና ራሳችሁንና የሥልጣን ዘመናችሁን ለማስረዘም ብላችሁ ነው የሚል ጥያቄ ቢነሳባችሁ መልሳችሁ ምን ይሆን? ቀድሞውኑ ማን ጠይቋችሁ!

በቀድሞዎቹ የንጉሡና የደርግ መንግሥታት ዘመን ያገለገሉትና ሕዝብን በድለዋል ተብለው ብዙ ባለስልጣናት ታስረዋል ተቀጥተዋል። እነዚህ ባለሥልጣናት አብዛኛዎቹ ያገለገሉበት መንንግሥት የሰጣቸውን ሥራ በሕዝቡ ላይ አስገድደው አስፈጽመዋል። ትልቁ በደላቸውና ስህተታቸው ይህ እንደሆነ ሲገለጽ ሰምተናል። የመንግስትን ዕቅድና ፍላጎት በጉልበት ማስፈጸም፤ የግለሰብን የመናገርና የማሰብ ነጻነት መንፈግ፤ ያለምንም ጥፋትና በደል ሰውን በመናገሩ ብቻ እንደወንጀለኛ ማሰር ማንገላታት ከሥራ ማባረር ወዘተ ማድረግ ከቻላችሁ ታዲያ እናንተ ከእነርሱ የምትለዩት በምንድነው? እናንተስ ነገ ተመሳሳይ ጥያቄ እንደማትጠይቁ እርግጠኞች ናችሁ?

አትቀበሉኝ ይሆናል ግን ልምከራችሁ።‘‘ጻድቃን ሥልጣን ሲይዙ ሕዝብ ሐሤት ያደርጋል፤ ክፉዎች ሲገዙ ግን ሕዝብ ያቃስታል፡፡’’ ምሳሌ 29፡2  እናንተንን ክፉዎች ናችሁ ለማለት ባልደፍርም የዳውሮ ሕዝብ እያለቀሰ ነው። እውነቱን ደግሞ ውስጣችሁ ያውቀዋል። እናንተም ነገ ታልፋላችሁ። ለሚያልፍ ሥልጣን ብላችሁ የማያልፈውን ወገናችሁን በዋናነት ዳውሮንና ሕዝባችሁን አትበድሉ። የመሰለውን ስለተናገረ ሰውን አላግባብ ጎትታችሁ አትሰሩ። የደርግ ባለሥልጣናት እንኳን እንደናንተ ለሕዝብ እንዲዋሽ ትብብር ጠይቀው እንቢ አልተባበርም ያላቸውን ግለሰብ ስለማሰራቸው እርግጠና አይደለሁም። የእናንተ ባስ እኮ!

የመንግሥት ሠራተኛ የግል ሠራተኛችሁ አይደለም። እንደእናንተ ሕዝብን አልዋሽም ስላለ ከሥራም አንዲባረር እንዲጎሳቆል አታድርጉ። ቢቻላችሁ የህዝቡን ጥያቄ በምትችሉት ሁሉ መልሳችሁ ምኑም ቀርቶባችሁ በሰላምና በፍቅር ከወገኖቻችሁ ጋር ብትኖሩ ይሻላችኋል። ነገ ከስልጣን ስትወርዱ የምትኖሩት ከዳውሮ ሕዝብ ጋር ነው። ብትሞቱ የሚቀብራችሁ ይህ ህዝብ ነው። ቃሉን አክብራችሁ ብትሰሩ ይጠቅማችኋል። ወደዳችሁም ጠላችሁ የህዝብ ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱ አይቀርም። አሁን በሥልጣን ያላችሁት ግለሰቦች የሕዝቡን ጥያቄ በተገቢው መልሳችሁ ምርቃቱ ቢቀርባችሁ እንኳ ሳትረገሙ ብታልፉ ይሻላችኋል። ነገ ከነገወዲያ እግዚአብሄር ሲፈቅድለት በእናንተ ማግስትም ቢሆን የህዝብ ጥያቄ በተገቢነት መመለሱ እንደማይቀር ለማየት ዕድሜ ያድላችሁ!

ለመንግሥት ሠራተኞች

ረዳት ሣጅን ሽታዬ ወርቁ በሎማ ዲሣ ወረዳ አካባቢ የዲሣ ከተማ ፖሊስ በመሆን ለዓመታት ማገልገሉንና በቅርቡ ወደ ሎማ ገሣ መዛወሩን፤  በዲሣ አካባቢ ቆይታዉ ወቅት የዲሣን ወረዳ ጥያቄ የሚያንቀሳቅሱ ሦስት ግለሰቦችን እንዲያስር ከዳዉሮ ዞን የፖለቲካ ጉዳዮች ሀላፊ መመሪያ ተሰጥቶት ያለ አንዳች በቂ ማስረጃና ጥፋት ሰዉ እንዲሁ ከሜዳ አላስርም በማለቱ በዞኑ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በሁኔታው አልተደሰቱም ነበር፡፡ የዲሣን ወረዳ ጥያቄ ያንቀሳቅሳሉና መታሰር አለባቸዉ ተብለዉ ከዞኑ ፖለቲካ ኃላፊ ትዕዛዝ የተላለፈባቸዉ ግለሰቦች አቶ አባቴ አሰፋ የትምህርት ባለሙያ፤ አቶ መስፍን ማሞ አርሶ አደር፤ እና አቶ ደስታ ቶልባ የግብርና ባለሙያ ነበሩ። አሁን እዚህ ላይ የፖለቲካ ኃላፊውንና ፖሊሱን አወዳድሩ። የትኛው ነው ለሕዝብ የቆመውና እውነተኛ የህዝብ ጥቅምና መብት የታገለው? ልዩነቱን ተመልከቱ።

ይህንን ያነሳሁት በየወረዳው እየተደረገ ያለው  የሕዝብን እውነተኛ የተጨማሪና የወረዳ ማዕከል ይስተካከልልኝ ጥያቄ የመንግሥት ሰራተኛው እንዳይደግፈው ለማድረግ እየተካሄደ ያለውን ሁኔታ ለማመላከት ነው። የመንግሥት ሠራተኛው የራሱም ሆነ የቤተሰቡ ህይወት መንግሥት በሚከፍለው የወር ደመወዙ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ካድሬዎች ይህችን እንጀራውን እንደማስያዣ ዕቃ ቆጥረው አንድን የመንግሥት ሠራተኛ እነርሱ የፈለጉትን እንደ ቴፕሪከርደር ሲዲ ያሻቸውን ሞልተው ለማናገር የወሰኑ ይመስላል።ልጅን በአባቱና በቤተሰቡ ላይ ለመቀስቀስ እየሰሩ ነው።

ኃላፊነት የጎደለው ሥራ እያተሰራ ይስተዋላል። የህዝብን ጥያቄ ለማፈን ለመንግሥት ከባድ አይደለም። እንደተለመደው ማሰር ማንገላታት ማስፈራራትና ጥያቄህን አንመልስም እንቢ ምን ታመጣለህ? በሚል በተለመደው መንገድ ማስቆምና መግታት ይቻላል። ተችሏልም። ነገር ግን አንድ ወረዳ ውስጥ ያለን የኖረንና የሚኖርን ሕዝብ እርስ በራሱ ለማጋጨት በአንድ ወረዳ ውስጥ የዋካንና ዙሪያውን ህዝብ ጥያቄ የማሪ ዙሪያ ህዝብ እንዲቃወመው ሕዝብን ማነሳሳትና መቀስቀስ፤ የዲሳን አካባቢ ሕዝብን የወረዳ ማዕከል ጥያቄን ለመቀልበስ የገሳጨሬ አካባቢ ሕዝብን መቀስቀስ፤ የቶጫ አካባቢን ሕዝብ ጥያቄ ለማፈን የከጪ አካባቢ ሕዝብን መቀስቀስ የዛሬን የሕዝብን የወረዳ ጥያቄ ለመግታት እየተሰራ ያለው ኃላፊነት የጎደለው ሥራ ለነገ አብሮነታቸው የሚያሳድረው የነገር ቁርሾ እንዳይኖር በተማሩትና አርቀው ማስተዋል የሚችሉት የሕብረተሰቡ ወገኖች ሊያስቡበትና ሊነቁበት ይገባል። ካድሬዎቻችን ምን እንደነካቸው አላውቅም። እኛ በስልጣን ላይ ዛሬን እንቆይ እንጂ የሕዝብ ጉዳይ የነገ ጉዳይ ወዘተ አያገባንም ያሉ ይመስላልና እንድናስብ አደራ እላለሁ። እነርሱ ለሕዝባቸውና ለዳውሮ ጥሩና የሚችሉትን አድርገው ለማለፍ የታደሉ አይደሉም።

በ1998 ዓ.ም እና በ1999 ዓ.ም የሌሎች አካባቢዎች የዞንና የክልል አመራሮች የነበሩ ለህዝባቸው ልማትና ዕድገት ሲሉ የራሳቸውን ጥቅም የማያስቀድሙ፤ ህዝባቸውን የሚወዱና የሚያከብሩ፤ በተሰጣቸው የስልጣን ክልል የህዝባቸውን የልማትና የወረዳ ጥያቄ አንግበው የታገሉና ጸንተው የቆሙ፤ የወከለኝ ህዝብ ጥያቄ የእኔም ጥያቄ ነው ያሉ አመራሮች በሌሎች ዞኖችና አካባቢዎች በተለያየ ቦታና ደረጃ አሉ። የሲዳማን የስልጢን የጎፋን የቤንችንና የወላይታ አመራሮችን የሥራ ተግባር ማየት እንችላለን። እነዚህ ህዝባቸውን ጠቅመዋል። የወከላቸውን ሕዝብ ጥያቄ በሆዳቸው አልለወጡትም። በዚህ የተነሳ ከፍተኛ የሞራል የበላይነት ሊሰማቸው ይገባቸዋል። ሕዝባቸውና አካባቢያቸው ሲዘክራቸው ይኖራል።

ለጊዚያዊ የግል ጥቅማቸው የቆሙ፤ ነገ ሳያውቁትና ሳይመሰገኑበት አሊያም ታስረው ወይም ተባርረው ለሚጥሉት ሥልጣን ትኩረት የሰጡ፤ ለጊዜው  የያዙትን ሥልጣን ማጣት የሚያስጨንቃቸው፤ ራስ ወዳዶች፤ ጥሩ ነገር ለህዝባቸው ሰርተው ለማለፍ ያልታደሉና አድርጉ የተባሉትን ለማድረግ ተሽቀዳድመው ከመሮጥ ባሻገር ቆም ብለው ይህ ሕዝባችንን አካባቢያችንን ይጠቅማል ወስ አይጠቅምም? ሕዝቡስ ምን ይላል ማለት የማይችሉ የህዝብ ተቃራኒዎች ደግሞ አሉ።። የዳውሮ ዞን አመራሮችን በዚህ ቡድን አስገብቶ መውቀስ ተገቢ ነው። ጠንካራ አመራሮች ለህዝባቸውና ለዞናቸው ተጨማሪ ወረዳ ታግለው አስገኙ። እኛ ለህዝብ የቆመ አመራር በዞን ደረጃ ስላልነበረን የዳውሮ ህዝብ እያነባ እያለቀሰ ይገኛል። ከእሱ የተሰበሰበው ግብርና ታክስ እየተከፈለው የሚሰራ አመራርና ካድሬ ህዝቡ ወረዳ አያስፈልገውም አልጠየቀም እያለ እየዋሸ እኛም የሱን ግጥምና ዜማ ተቀብለን እንድናዜም ሊያስገድደን ይታገለናል። አለመታደል እኮ ነው ወገኖቼ! በፍጹም እንቢ ልንል ግድ ይለናል። ተቃውሟችሁን በግልጽ አድርጋችሁ ጥቂቶችን ሰለባ ማድረግ ባያስፈልገንም የሕዝብ አጋርነታችንን በምንችለው ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተቃራኒ መግለጽ የሞራል ግዴታችን ነው።ይህ አመራር ጥቅሜ ከሚጓደልና የመኪና ጋቢና ከሚቀርብኝ ከዳውሮ ሕዝብ ምኑም ይቅርበት ብሎ የወሰነ ይመስላልና ያቅማችንን የማበርከት ግዴታ ይጠብቀናል።

ለዳውሮ አርሶአደሮች፤ ነጋዴዎችና ሌሎች የየከተማው ነዋሪዎች

ለዳውሮ ዞን ሕዝብ መንግሥት ተገቢውን  ምላሽ እንደሚሰጣችሁ በተስፋ ስትጠብቁ ቆይታችኋል። ነገሩ መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባ የሚታወቅ ቢሆንም የህዝቡ ጥያቄ ምላሽ ሊያገኝ ይገባል የሚል የፖለቲካ አመራር በየደረጃው ባለማኖሩ እስካሁን ተገቢውን ምላሽ ማግኘት አልተቻለም። እንዲያውም እያደር ጥያቄው የጥገኞች ነው፤ የጥቂቶች ነው፤ የብዙኋኑ የዳውሮ ሕዝብ ጥያቄ አይደለም፤ ሕዝቡ ልማት እንጂ ወረዳ አይጠቅመውም በሚል የሕዝቡን ጥያቄ ለመቀልበስና አቅጣጫውን ለማስቀየር ብሎም ህዝቡ ተጨማሪ ወረዳ እንዲያጣና የሚሻውን የወረዳ ማዕከል ወደሚቀርበው ሥፍራ የማዛወር መብት እንዳይኖረው ለማድረግ ተግተው እየሰሩ ይገኛሉ።

የገዛ ልጆችህ ናቸው ጥያቄህን ለመድፈቅ አሲረው አንተን ለማፈን ተግተው እየሰሩ የሚገኙት። የሚናገረውን ለማስፈራራትና እንዳይናገር በማድረግ እድል በመከልከልና በማሸማቀቅ፤ ለምን መብታችንን ትነኩብናላችሁ ብለው የሚጠይቁ ከተገኙ ለማስፈራሪያነት በማሰር ለማስፈራራት ዕቅድ ተሰጥቷቸው ይህንን ለመተግበር ይሰራሉ። በመንደርና በአገልግሎት በመከፋፈል ጥያቄህን ለማሳነስና የጋራ ጥያቄ አይደለም የጥቂቶች ነው ለማለት እየተባበሩ ነው። ስለዚህ በአገልግሎትና በመንደር መከፋፈል አያስፈልግህም። ልማትና ወረዳ አይነጣጠልም።

አንድ ምሳሌ ላንሳላችሁ። የወረዳ ማዕከል ጥያቄ የእኛ አይደለም የጥቂቶች ነው እኛ ወረዳ አንፈልግም በሉ፤ እንቢ ካላችሁ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቱን ከዚህ እናነሳለን፤ የጤና ጣቢያ ሥራ አይከናወንም ወዘተ የሚል ተራ ማስፈራሪያ አንድ ሆድ አደር ካድሬ ሲናገር ሰምተው ከተሰብሳቢዎቹ መካከል አንዱ አርሶ አደር (በማረቃ ወረዳ ጌንዶ አገልግሎት አካባቢ ውስጥ ነዋሪ ናቸው ) ካድሬውን በሚያሳዝን መልኩ ረግመውት አሁን የእኛን ወረዳ ጥያቄ ለማስጨንገፍ ብለህ ለሆድህ አድረህ ህሊናህን ሽጠህ በል የተባልከውን እያልክ ነው ብለዉት ይህንን ተራ ወሬ ይዞ ወደ መጣበት እንዲመለስና እሳቸውም ሆነ ሕዝቡ የሚሻለውን ጠንቅቀው የሚያውቁ መሆኑን አስተምረውት አሳፍረውት መልሰውታል።

ይህንን የተናገሩት አርሶ አደር በፖለቲካዊ ንቃተ ህሊና አንጻር ከካድሬው ጋር አነጻጽራችሁ የቱ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዳለ አስተውሉ። ማነው የህሊና ነጻነት ያለው? ልማትና ወረዳ አይነጣጠሉም። ወረዳ ሲመጣ ከወረዳው ጋር አብሮ ልማትም ይመጣል። ዳውሮ ዞን ባይሆን አሁን የደረሰበት የልማት ደረጃ ላይ ይደርስ ነበር የሚል ካድሬ ሊመጣ እንደሚችል አትጠራጠሩ ግን አትመኑት። የሰሞኑ ካድሬ ድንጋይ ዳቦ ነው ለማለት የሚታቀብ ስለመሆኑ ያጠራጥራል። እያከናወነ ያለው ክብሩን ህሊናውን ሞራሉን ሁሉ ትቶት ነው።

የዳውሮ ሕዝብን የወረዳና የልማት ጥያቄውን ለመቀልበስ የሚሰሩ ሁሉ የዳውሮ ልማትና የዳውሮ ህዝብ ጠላቶች ናቸው! ሕዝብ የሚበጀውንና የሚሻለውን ያውቃል። የካድሬ ሰበካና የሐሰት ቀላጤ አያስፈልገውም። የካድሬው ዓላማ የህዝብን ጥያቄ ወደ ጥቂቶች ጥያቄነት ለመቀየርና ጥያቄውን ለማምከን ነውና ሁላችንም በምንም ሳንከፋፈል አብረን ቆመን ጥያቄያችንን በጋራ በአንድ ድምፅ ማስተጋባት ይጠበቅብናል።

የዳውሮ ምሁራን የሆናችሁ በሙሉ!

ከላይ በዝርዝር ያስቀመጥኩትን እውነታ ተመልክታችኋል። የዳውሮ ዞን አመራሮች ከክልል አመራሮች ተጭነው የመጡትን የሕዝቡን የወረዳና የወረዳ ማዕከል ጥያቄ ለማምከን ምን ያህል ተግተው እየሰሩ እንዳለ ተመልከቱ። ከራሳቸው አልፈው የወረዳ አመራሮችንና ካድሬዎችን አስገድደው የተጫኑትን መልሰው ጭነውባቸው ከህዝቡ ጋር እያላተሟቸው ይገኛል። እኔ በግሌ የወረዳ አመራሮች ላይ ብዙ አልፈርድም። ለአብዛኛዎቹ የእንጀራ ጉዳይም ሆኖባቸው ሳይወዱ በግድ የተጫኑትን ማራገፊያ አጥተው እንደሚሰቃዩ ይሰማኛል። ከሕዝቡም እየደረሰባቸው ያለው ነገር እያሰቃያቸው ነው። በድርጊቱ ከዞን ጀምሮ ያለው አመራር በሕዝባችን ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም በደልና እንግልት ተጠያቂ መሆናቸውን ልብ ልንል ይገባል።

ምሁሩ የሕዝብ ወገን አመራሩ ለምንድነው እንዲህ የሚያደርጉት? ምን ይሻሻል? ከእኔ ምን ይጠበቃል? በሚል ማሰብ እንደሚገባችሁና እንቅስቃሴውንም በአንክሮ መከታተል እንደሚጠበቅባችሁ አሳስቤ ጽሁፌን በዚሁ እቋጫለሁ።

የማለዳ ወግ . . . አፋጣኝ ትኩረት የሚሻ የተፈናቃይ የኮንትራት ሰራተኞች ጥሪ . . .

ነቢዩ ሲራክ

አሮጌው የፈረንጆች አመት አልፎ በአዲስ አመት ከመግባቱ አስቀድሞ በዋዜማው ያየን የሰማነው በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩት የኮንትራት ሰራተኞች ውሎ አዳር ደስ አይልም ፡፡ በያዝነው ወርማ በተለያዩ የሳውዲ ጋዜጦች ሳይቀር የተዘመተብን ይመስላል ፡፡ የኮንትራት ሰራተኞች ተከላካይ ጠበቃ አጥተው ፤ በአሰሪዎች ሲባረሩ ፤ ሲደፈሩና አደጋው በርታ ሲል ተፍተው በኢንባሲና በቆንስል መስሪያ ቤቶች ጥገኝነት ይጠይቃሉ፡፡ ግፉአን ፍትህ ተነፍጓቸው ሲንገላቱ፤ ሲያብዱ ሲታመሙና በሃይል እርምጃ ነፍሳቸው ስትጠፋ ለመክረማቸው ምስክሮች ብዙ ነን ! እርግጥ ነው ለነፍስ ግድያ ተይዘውና ተወንጅለው ዘብጥያ የወረዱ እህቶችም አሉን ፡፡የማለዳ ወግ . . . አፋጣኝ ትኩረት የሚሻ የተፈናቃይ የኮንትራት ሰራተኞች ጥሪ

ወንጀሉና ግድያውን በምን ሰበብ አስባብ እንደፈጸሙት ግን ለእኛ የሚነግረን ፤ ለዜጎች ጠበቃ ሆኖ የሚሰማቸውና የሚከራከላቸው ያገኙ አይመስሉም፡፡ በእድሜ ያልበሰሉት እህቶች ነፍስ ለማጥፋት ያደረሳቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት ሳይሆን ለመረዳት በመጠለያ ያሉ እህቶች ማነጋገር ይበቃ ይመስለኛል፡፡ እህቶች ተፈጸመብን የሚሉትን ግፍና የመደፈር ጥቃት አሰቃቂ የግድያ ወንጀል ለመፈጸም የሚሰጥ ምክንያት ሊሆንና ወንጀልን መፈጸም አይገባም፡፡ ያም ሆኖ ሊገል የመጣን ገዳይ ለመከላከል አስበውትም ሆነ ሳያስቡት መግደል ራስን ከጥቃት ለመከላከል የሚደረግ እንቅስቃሴ እርምጃ መሆኑን ከህግ አንጻር የሚያስረዳ የመንግስት ተወካይ ያስፈልገናል፡፡

እንደ ዜጋ የተበዳዮችን ህመምና በደል ” እህ ” ብለን በማድመጥ ህግና ስርአትን ተከትለን መፍትሔ ልናፈላልግ ይገባል፡፡ ከምኖበት የቅርብ ርቀት ተፈጽሞ ግርግሩን በወቅቱ ዜናውን በጋዜጦች አንብቤያለሁ ! “ገደሉ” የሚባለውን ያህልም ባይሆን “ተገደሉ ” የሚለው አይነገርም ! ሲላቸው ራሳቸውን በራሳቸው አጠፉ ይሉና ” ሬሳቸውን ውሰዱ!” ይሉናል ! ለምን ራሳቸውን ገደሉ ብሎ ማን ይጠይቅልን ? !ራሳቸው ገደሉ እንኳ ቢባል ሌላን ሰው ከመግደል ራስን መግደል የመክበዱን ያህል ለዚህ ዜጎቻችን ለዚህ ያደረሳቸው ምክንያቱ ምን ይሆን ብሎ የሚያጠይቅልን አጥተናል ! ይህ ሁሉ እየሆነ አንድ የሳውዲ ጋዜጣ ባሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ ይፋ ያደረገው ሰነድ በጂዳ በሁለት የግድያ ወንጀል ፤ በያንቡ በግድያ ፤ በአልዘልፊ በደቡብ የሃገሪቱ ጠረፍ ፤ በአፈር አልበጠል ፤ በመካ በረፋዕና በተለያዩ የገጠርና ትላልቅ ከተሞች ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች በከባድ የግድያና የመሳሰሉት ወንጀሎች እንደተያዙ አልመዲና የተባለው ጋዜጣ አትቷል፡፡

እንደ ጋዜጠኛነቴ የዜጎችን ጉዳይ ለመከታተልና መረጃ ለማግኘት ወደ ቆንስሉ ብቅ ባሉኩበት አጋጣሚ ወደ ግቢው ለመግባት ስሞክር ቁም ስቅሌን የሚያሳዩኝ የቆንስሉ ዘበኛ በክብር ጎበስ ብሎ ያስገባቸው የሳውዲ አል መዲና ጋዜጠኞች የጅዳ ቆስንል ሃላፊዎችን አነጋግረው ያወጡትን መረጃ ማንበብ ሆድ አያሞላም፡፡ ልተወው . . .ብቻ የሳውዲ ጋዜጦች የሌለብንን እየለጠፉ ነፍስ ማጥፋታችን አግንነው የኮንትራት ስርራተኛ እህቶቻችንን ነፍስ በስነ ስርአት አልበኛነት እየኮነኑ የስራት አልበኛ ዜጎቻቸው ጥፋትና አሰቃቂ አያያዝ አኩስሰው ስለ መግደል ሙቅ ውሃ መቸለሳቸው ሰፊ ዘገባን እየሰሩ ይነግሩን ይዘዋል !

ከሁሉ በፊት ለዛሬው ድጋሜ የማለዳ ወጌ መነሻ ስለሆነኝ አፋጣኝ ትኩረት ወደ ሚሻው ጉዳይ ላምራ ! ከቆስንሉ አዲስ መጠለያ በቅርቡ እንዲገቡ ከተደረጉት ውጭ ያሉት 16 ተፈናቃዮች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ያገኘኋቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በቆንስሉና ከዚህ በፊት በርካታ ተፈናቃዮች በነበሩበት “መዲናተል ሃጃጅ” ከሚባለው መጠለያ አከራዮች መካከል በክፍያ የተነሳው ውዝግብ እልባት ባለማግኘቱ እዚያው ተጠልለው የነበሩ እህቶቻችን ለከፋ መከራ መዳረጋቸውን እውነትነት ከተለያዩ ምንጮች ማረጋገጥ ችያለሁ ፡፡

በመጠለያው የሚገኙ 6 የዓዕምሮ ህሙማንና ጨምሮ አስር ያህል እህቶች ከአስር ቀናት በላይ መብራትና ውሃ ተቆርጦባቸው በበራሪ ተባዮች እየተነደፉ እየገፉት ያለው የለት ተለት ኑሮ ሊናገሩት ይከብዳል ሲሉ ምንጮቸ ምስክረናተቸውን ሰጥተውኛል. . . የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ለእኒህን ተፈናቃይ ግፉአን ነፍስ አድን ጥያቄ መልስ ሲሰጡ መስማት ናፍቆኛል ! እኔ እጽፋለሁ ! እናንተ አንብቡ ! የመንግስት ሃላፊዎቻችን አፋጣኝ ትኩረት ለሚሻው የተፈናቃይ የኮንትራት ጥሪ ጀሮ ሊሰጡ ይገባል ! ጀሮ ያለው ይስማ . . .

የመሰንበቻውን የተፈናቃይ ኮንትራት ስራተኞች ውሎ ተጽፎ የሚገለጽ ብቻ አይደለምና ለህዝብ መብት ማስጠበቅና ለሰብ አዊ መብት ማስከበር የቆመ የመንግስትም ሆነ ገለልተኛ አካል ካለ በቃል ከመናገር ምስሎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎች ለሚያይ ለሚሰማ የችግሩን ክፋት ማሳየት ይችላሉና የጀመርኩትን እቀጥለዋለሁ ! በኮሚኒቲው አዳራሽ አጠገብ የተሰራችው ጠባብ መጠለያ የተጠለሉት ግፉአን እህቶች ቁጥር ወደ ሰላሳ ሲጠጋ አምስት ያህሉ ዓዕምሯቸው ተነክቷል ! . . .አንዷ ተረጋግጣ ጋዜጣ ስታነብና ከራሷ ጋር ስታወራ ፤ ሌላዋ ግቢውንና ካፍቴሪያውን እየገባች እየወጣች ትረብሻለች፤ ስላት ከግቢው መካከል ካለችው አደባባይ ቁጥጥ ብላ በመውጣት ትደንሳለች ፤ትጫወታለች . . .ከግቢው ወጥታ በአስፓልቱ መሃል ቆማ መኪና እንዲገጫት ስትታገልና ሲመልሷት ተመልክቻለሁ ! መናገር መጋገር የማትፈልገው ሌላዋ ዘርፈጥ ብላ ተቀምጣና ነሁልሳና በራሷ አለም የነጎደቸው እህት ልብን በሃዘን ትሰብራለች፡፡

በሌላኛው መጠለያ ያሉትን ጨምሮ ዓዕምሯቸው የተነካና ያበዱትን እህቶች ቁጥር ከአስር በላይ እየሆነ ሲመጣ ጤነኞችና ህሙማኑ በአንድ ላይ ባሉባት መጠለያ ያበዱት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ያላበዱት ለእብደት መዳረጋቸውንና እንባቸውን እያዘሩ የገለጹልኝ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ነው ፡፡ በሪያድ ያለውን ሁኔታ ያጫዎተኝ ወዳጀ ከጅዳው በከፋ ሁኔታ ዜጎች ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን ያመላክታል፡፡ እንዲያው በአጠቃላይ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች ስለ ዜጎች መብት ገፈፋ በመረጃ እየተደገፈ ሲነገር የሆነ ያልሆነውን መረጃ ከመስተት ተቆጥበው በትክክል በዜጎች ላይ ለሚደርሰውና በአስፈሪ ሁኔታ እየተጋረጥነው ያለውን ችግር ለመመከት ህዝብ ተጠርቶ የሚመክርበት መንገድ አለያም ማዕከላዊ መንግስት የጉዳዩን አሳሳቢነት እንዲረዳና በዚህ ረገድ እርምጃ እንዲወሰድ ጠንከር ያለ ትክክለኛ መረጃ ሊሰጥ ይገባል፡፡

አዲሱ አመት ነጋ ጠባ የምናነሳ የምንጥለው የኢዮጵያውያን መከራ የሚቀልበት ያደርገው ዘንድ ምኞቴ ደግሜ በመግለጽ የዛሬውን ወግ ላብቃ !

ቸር አሰማን !

ነቢዩ ሲራክ

ECADF.COM

የዘመኑ ፖለቲካ አስቂኝ –ብዙ ያልተነገረለት የኢህአዴግ ራዕይ

ምኒሊክ ሳልሳዊ

የዘመኑ ፖለቲካ አስቂኝ ነገር ይመስለኛል(ደንበኛ ኮሜዲ!) አስቂኝነቱ ግን ለፖለቲከኞቹ አይደለም፤እነሱማ ስራቸው ነው (ማን ነበር ንጉስነት እንጀራዬ ነው ያለው?) አስቂኝነቱ ለእኛ ነው- ለተደራሲያኑ!!(በጥበብ ቋንቋ መግለፄ እኮ ነው) ፖለቲካን እንደ ኮሜዲ ቲያትር አስባችሁት ታውቃላችሁ? (የምርም እኮ ኮሜዲ ነው!) መቼም የፖለቲካ ኮሜዲው ደራሲያንና ተዋንያን ማን እንደሆኑ አይጠፏችሁም ብዬ አስባለሁ፡፡ ፖለቲከኞቹ ናቸዋ! ተደራስያኑ ደግም ምስኪኑ ህዝብ! (“ልማታዊ ህዝብ” ይባላል እንዴ?) ለነገሩ “የበይ ተመልካች” ወይም ታዛቢ ብንባልም አይከፋንም (ሃቅ ነዋ!) እናላችሁ —- ፖለቲከኞቹ ይበላሉ፤ እኛ ኩራዝ እንይዛለን፡፡ ፖለቲከኞቹ ይወስናሉ፤ እኛ እንሰማለን፡፡ ምን ይደረግ … እጣ ፈንታችን እኮ ነው፡፡ (ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም!) ለነገሩ ተሰጥኦ ከሌለን ቀሽም ኮሜዲ ነው የምንሰራው (አያስቅ አያስለቅስ!) አያችሁ የፖለቲካ ኮሜዲ ችሎታ ይጠይቃል – ልዩ ተሰጥኦ!

እኔ መቼም የፖለቲካ ኮሜዲ ዘመን መሆኑ በጣም ነው ደስ ያለኝ (ምርጫ የለኝማ!) ግን እኮ በምናብ ባቡር (እውነተኛው ባቡር እስኪጀመር–) ወደ ኋላ ሸተት ብላችሁ የ60ዎቹን የፖለቲካ ተውኔቶች ብትመረምሩ የአሁኑን የፖለቲካ ኮሜዲ “ተመስገን!” ማለታችሁ አይቀርም፡፡ መቼም ከፖለቲካ ትራጄዲ የፖለቲካ ኮሜዲ ይሻላል፡፡ እኔ በበኩሌ ከምናዝን ቢቀለድብን እመርጣለሁ (Choosing the lesser evil እንደሚባለው!)

አንዳንዶች የቀድም ጠ/ሚኒስትር “ግልባጭ” የሚሏቸው (እሳቸውም የእሱ “ግርፍ” ነኝ ብለዋል እኮ) የኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ ከኢቴቪ ጋር የመጀመርያውን ቃለምልልስ ሲያደርጉ፤ አገራችን ከባለ ሁለት ዲጂት የኢኮኖሚ ዕድገት ባሻገር፣ በመንገድ ግንባታና ማስፋፊያ ሥራዎችም ከአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌላት ቀዳሚዋ አገር መሆኗን ሲገልፁ፤ (ሲያበስሩ በሚል ይተካልኝ!) ነፍሴ እንዴት በደስታ ጮቤ እንደረገጠች አልነግራችሁም፡፡ ከምሬ እኮ ነው! (ካልማልኩ አታምኑኝም?) ወዲያው ግን … አንድ “ነገረኛ ጥያቄ” ከአዕምሮዬ ጥግ ብቅ አለና ደስታዬን ነጠቀኝ። በቃ በጣፋጭ ህልም ከተሞላ የጥጋብ እንቅልፍ ላይ የተቀሰቀስኩ ነው የመሰለኝ፡፡ “በመንገድ ግንባታና ማስፋፊያስ ቀዳሚ ሆንን … በዲሞክራሲ ግንባታስ? በመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ምስረታስ? በነፃና ፍትሃዊ ምርጫስ? በፕሬስ ነፃነትስ? የህዝቦችን ሰብአዊ መብት በማክበርስ?–” ደህና የነበርኩት ሰውዬ የነፃነት ታጋይ ሆኜላችሁ ቁጭ አልኩ፡፡ አይገርማችሁም? ያለ ዕቅድና ያለ ፍላጐቴ እኮ ነው በእነዚህ ሁሉ የጥያቄዎች ጐርፍ የተጥለቀለቅሁት፡፡ ታዲያ ምን እንደቆጨኝ ታውቃላችሁ? ያንን ጠ/ሚኒስትሩን ኢንተርቪው ያደረገ የኢቴቪ ጋዜጠኛ ባገኝ ኖሮ “ጠይቅልኝ” ብዬ እማፀነው ነበር (ለእኛ እስኪገኙ ልማታዊ ጋዜጠኛ ልጠቀም ብዬ እኮ ነው!)

በነገራችሁ ላይ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ቶፕ 10 ውስጥ መግባቷን ሰምታችኋል አይደል? (ሪፖርቱ ኢህአዴግ አይልም – ኢትዮጵያ እንጂ!) ከዓለም ጋዜጠኞችን በብዛት በማሰር ቁጥር አንድ አገር ማን መሰለቻችሁ? ቱርክ ናት ይላል- ሪፖርቱ። 49 ጋዜጠኞቿ ቤታቸው ወህኒ ሆኗል፡፡ ኢራን 45 ጋዜጠኞችን አስራ በሁለተኛነት ትከተላለች፡፡ ቻይንዬ ደግሞ 32ቱን የፕሬስ ሰዎች ሸብ አድርጋ ሶስተኛ ደረጃ ይዛለች፡፡ አራተኛዋ አገር ዘመዳችን ኤርትራ ስትሆን 28 ጋዜጠኞችን ዘብጥያ አውርዳለች፡፡ ኢትዮጵያ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች – ጋዜጠኞቿን በማሰር፡፡ በነገራችሁ ላይ መንግስታት ምን እንደነካቸው አይታወቅም ጋዜጠኞችን እንደጦር መፍራት ጀምረዋል፡፡ እናም ዘንድሮ ከ1990 ዓ.ም ወዲህ በመላው ዓለም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች መታሰራቸውን ነው ሪፖርቱ ይፋ ያደረገው – በጠቅላላው በ27 አገራት ውስጥ 232 ሪፖርተሮች፣ የፎቶ ጋዜጠኞችና ኤዲተሮች ለእስር ተዳርገዋል (ስልጣን ሳይሆን መረጃ ጠይቀው!)

እኔ የምላችሁ ግን … ኢቴቪ የሚዲያ ዳሰሳ የሚለው ፕሮግራሙ ላይ የስያሜ ለውጥ አደረገ እንዴ? የሚዲያ ዳሰሳው ቀርቶ የኒዮሊበራል አቀንቃኝ አገራት የተራራቁበትን “ልማታዊ መፃህፍት” እያስኮመኮመን እኮ ነው፡፡ እኔ ግን አንድ ሃሳብ አለኝ – ስለ ፕሮግራሙ፡፡ ሃሳቤ በይዘቱ ወይም በአቀራረቡ ላይ አይደለም፡፡ በፕሮግራሙ ርዕስ ወይም ስያሜ ላይ ብቻ ነው! እንደኔ እንደኔ የሚዲያ ዳሰሳም ሆነ የመፃህፍት ዳሰሳ የሚለው ስያሜ ፈፅሞ ፕሮግራሙን አይመጥንም፡፡ እውነቴን እኮ ነው … ጋዜጠኞቹ የሚያቀርቡልን እኮ ዳሰሳ ሳይሆን የስብከትና የፕሮፓጋንዳ ቅይጥ ነገር ነው (ሚስቶ እንደሚሉት) ስለዚህ ለምን በኢቴቪ የፕሮፓጋንዳና የቅስቀሳ ዲፓርትመንት ሥር “የልማታዊ አስተሳሰብ ማስፋፊያ ፕሮግራም” አይባልም? የሚል ሃሳብ አለኝ (ዲፓርትመንቱ ከሌለ ይቋቋማ!) ልብ አድርጉ! እንዲህ ያሻኝን የምናገረው ኢቴቪ የእኛ የሰፊው ህዝብ ሃብትና ንብረት ነው ብዬ ነው (ለግል ባለሃብት ተሸጠ እንዳትሉኝ?)

አንዳንዴ ተቃዋሚዎች፤ “ኢህአዴግ ሚዲያውን በሞኖፖል ተቆጣጥሮታል” ሲሉ እሰማና እኛ ሳናውቅ ንብረታችን ተሸጠ? ብዬ እደነግጣለሁ (ኢህአዴግ ገዝቶት እንዳይሆን ብዬ እኮ ነው!) አለዚያማ ማን የማንን ንብረት ይቆጣጠራል? ወይም ደግሞ እንደ መሬት “የህዝብና የመንግስት” ነው ይበሉንና አርፈን እንቀመጥ፡፡ እኔ የምለው ግን —- የፖለቲካ ምህዳር የማን ንብረት ነው? “የህዝብና የመንግስት” ነው እንዳትሉኝና እንዳታስቁኝ (የዘመኑ ፖለቲካ ኮሜዲ ነው አልተባባልንም?) ኢህአዴግ ግን አንዳንዴ ያበዛዋል፡፡ ምናለ እቺን እንኳ ለተቃዋሚዎች ቢለቅላቸው (የፖለቲካ ምህዳር መሬት መሰለው እንዴ?)

በነገራችሁ ላይ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ምስጉን ሠራተኞች ሰሞኑን መሸለማቸውን ስሰማ እንዴት ደስ እንዳለኝ አታውቁም፡፡ የህዝብ ሽልማት ቢቀርባቸው የድርጅቱን እንኳን ያግኙ እንጂ! (ከሁለት ያጣ ሆኑ እኮ) ይሄን ደስታዬን ለአንዱ “ሟርተኛ” ወዳጄ ሳጋራው ምን እንዳለኝ ታውቃላችሁ? (“ደርግም እኮ “ኮከብ ሠራተኞች” እያለ ይሸልም ነበር!”) ምኑ ጨለምተኛ ነው ባካችሁ?

እናንተ— ሰሞኑን የሰማኋት አንዲት ዜና እንዴት ያለች የፖለቲካ ኮሜዲ መሰለቻችሁ! የዜናዋን ፍሬ ነገር ልንገራችኋ — ባለፈው ሳምንት ወደ ሩዋንዳ የተጓዙት ጠ/ሚኒስትራችን፤ ከሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ጋር መወያየታቸውን የዘገበው ኢቴቪ፤ ፓርቲያቸው ኢህአዴግ ከሩዋንዳዉ ገዢ ፓርቲና ከሌሎች ተራማጅ አስተሳሰብ ያላቸው የአፍሪካ ፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ጠቁሟል (ዘይገርም ነገር!) የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን የህይወት ታሪክ በሚተርከው “የነጋሶ መንገድ” የተሰኘ መፅሃፍ ላይ ያነበብኩትን አንድ መረጃ ካልነገርኳችሁ የዚህን ዜና አንደምታ ልታገኙት አትችሉም፡፡ ኢህአዴግ ገና ድሮ በትግል ላይ ሳለ (ከስልጣን ጋር ሳይተዋወቅ ማለት ነው) ስለነበረው ራዕይ ነጋሶ ሲናገሩ፤ “ኢህአዴግ በአፍሪካ ግዙፍና ተፅዕኖ ፈጣሪ ገናና ፓርቲ የመሆን ራዕይ” እንደነበረው ገልፀዋል፡፡ አሁን ትንሽ ተገለጠላችሁ? እኔ ሳስበው ኢህአዴግ ሩዋንዳ ድረስ ሄዶ ከባዕድ ፓርቲ ጋር ተስማምቶ የተመለሰው እቺን የጥንት ራዕይ ለማሳካት ይመስለኛል፡፡ አንዳንዶች “እዚህ መዲናዋ እምብርት ላይ 34 ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደራደር እያሉ ሲማጠኑት ሩዋንዳ ተሻግሮ መደራደር ምን ዓይነት ንቀት ነው?” ሊሉት ይችላሉ (ሲሰማቸው አይደል!)

አያችሁ — ኢህአዴግ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር መስራትን በተመለከተ ሁለት ራዕዮች እንዳሉት የደረስኩበት ሰሞኑን ነው – አገራዊና አህጉራዊ ይባላል። ቅድም እንደነገርኳችሁ አህጉራዊ ራዕዩ በአፍሪካ ገናና ፓርቲ መሆን ነው – ተፅዕኖ ፈጣሪ ግዙፍ ፓርቲ! አገራዊ ራዕዩስ? እንግዲህ ራዕይ ይሁን አይሁን አላውቅሁም እንጂ ከ2002 ምርጫ በኋላ “አዲስ ራዕይ” በተሰኘው የራሱ ልሳን ላይ እንዳሰፈረው ተቃዋሚዎች እንዳያንሰራሩ ለማድረግ በርትቶ እንደሚታትር ጠቁሟል (ጨለምተኛ ራዕይ ይሏል ይኼ ነው!)
አህጉራዊ ራዕዩን በተመለከተ ትንሽ የሚያሰጋኝ ምን መሰላችሁ? ኢህአዴግ ከአፍሪካ ልማታዊ ፓርቲዎች ጋር ጥምረት ወይም ግንባር ከመሰረተ በኋላ እዚህ አገር እንዳደረገው “ገናና ፓርቲ ነኝ” ብሎ ሸብ ለማድረግ እንዳይሞክር ነው (እነሱስ በእጃቸው ሙቅ ይዘዋል እንዴ?) ለነገሩ ኢህአዴግም ቢሆን አብዛኞቹ የአፍሪካ ገዢ ፓርቲዎች እንደሱው የነፃነት ታጋዮች እንደነበሩ የሚዘነጋው አይመስለኝም (ሁሉም በልቡ ገናና ነኝ ባይ እኮ ነው!) ምናልባት ዘንግቶት ችግር ላይ ከወደቀም የሚያዝንለት የለም፡፡ “የአገሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጡር ነው” እየተባለ መሳለቂያ ነው የሚሆነው፡፡

እኔ የምለው ግን— ከአገሩ አልፎ በአህጉር ደረጃ ገናና የመሆን ህልም ያለው ፓርቲ እንዴት የኮሙኒኬሽን አቅምና ብቃት አይኖረውም? ኢህአዴግ እኮ በኮሙኒኬሽን “Poor” ነው (ድክም ያለ!) አንዴም እንኳ የመግባባት ብልሃቱን ሳያሳየን ይኸው 21 ዓመት ሞላው። እንኳንስ “ጠላቴ” ብሎ ከፈረጃቸው ተቃዋሚዎች ጋር ቀርቶ ከእኛ ከህዝቦቹ ጋር እንኳ ሁሌ አይደል የሚላተመው? (ደግነቱ አጥፍቻለሁ ማለት ይወዳል!) እውነቴን ነው የምላችሁ —- ኢህአዴግ ከአገር በቀሎቹ ፓርቲዎች ጋር እንዲህ ዓይንና ናጫ ሆኖ አህጉራዊ ራዕዩን ለማሳካት ቢነሳ ፈፅሞ አይሳካለትም፡፡ ለማንኛውም ግን ያስብበት ለማለት ያህል ነው፡፡

መንግሥትና ቤተ ክህነቱ፣ በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል የቀጠለው ድርድር፣ የፓትርያሪክ ምርጫ ውዝግቡ ወዴየት እያመራ ይሆን!?

 

Abuna Merkorios Patriarch of the Ethiopian Orthodox Church

እሁድ ታህሳስ 21 ቀን በቶሮንቶ በተከበረው አመታዊው የታህሳስ ገብርኤል በዓለ ንግስ ላይ ፓትሪያርክ መርቆሬዎስ ለህዝቡ ቡራኬ ሲሰጡ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በብዙ ሚሊዮን ሚቆጠር ምእመናን እንዳላት ይታመናል፡፡ ይህች አንጋፋና ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ታሪክ፣ ታላቅ ሥልጣኔ፣ ባህልና ቅርስ መሠረት ለመሆን የቻለች የሃይማኖት ተቋም ናት፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ ለኢትዮጵያ ነፃነት፣ ሉዓላዊነትና አንድነት የነበራት ሚና እጅግ የጎላ ነው፡፡ ይኸው ሚናዋ ከአፍሪካ እስከ አሜሪካ፣ ጃማይካና ካረቢያ ድረስ ተሻግሮ ለብዙ ሚሊዮን የምድራችን ጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ትግል ፋና ወጊ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሆና ለመቆጠር የበቃችበትን ልዩ ታሪካዊ ክብርና ሥፍራን ለመጎናጸፍ አስችሏታል፡፡

ይህን ቤተ ክርስቲያኒቱ ለነፃነት፣ ለፍትህ እና ለሰው ልጆች እኩልነት መስፈን የነበራትን ታላቅ የሆነ መንፈሳዊና ታሪካዊ የሆነ ጉልህ ሚና በተለይ በደቡብ አፍሪካውያን የጸረ-ባርነትና የጸረ-አፓርታይድ ትግል ወቅት ለጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የነፃነት ፋኖዎች እንደ ትልቅ ስንቅና ወኔ ሆኖ አገልግሏል፡፡

ይህን ታሪካዊ እውነታ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ታቦ ኢምቤኪ እ.ኤ.አ በ2010 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ የክብር ዶክትሬት በሰጣቸው ወቅት ባደረጉት ታሪካዊ ንግግራቸው እንዲህ በማለት ነበር በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ ራሳቸውን ጨምሮ፣ አፍሪካውያንና መላው ጥቁር ሕዝብ የሚሰማውን ክብርና ኩራት በእንዲህ መልኩ የገለጹት፡-

…Thus would the authentic African Church serve as a repository of the aspirations of all Africans for freedom and respect for their cultures, their identity and their dignity.

The African National Congress of South Africa, the oldest modern national liberation movement on our continent, was born out of our country’s Ethiopian Churches. Indeed the African nationalism which drove our national liberation movement was described as Ethiopianism.

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ጥንታዊ የሆነ እምነቷ፣ ሥርዓቶቿና ትውፊቶቿ እንደ ሌሎች አፍሪካ አገራት የምዕራባውያን ቀኝ ገዢዎች አሻራ ያለረፈበት በመሆኑ Reconciliation within the Ethiopian Orthodox Tewahedo Churchአፍሪካዊት እናት ቤተ ክርስቲያን (An Independent African Mother Church, African Indigenous Church)የሚል ክብርና ቅጽል እንድትጎናጸፍ አድረጓታል፡፡

የክርስትና ሃይማኖት ወደ ኢትዮጵያ በገባበት ወቅት ኢትዮጵያውያኑ ነገሥታትና ሊቃውንት ክርስትናውን ከሕዝባቸው ታሪክ፣ ባህል፣ ቅርስ፣ ልማድና ትውፊት ጋር በማጣመር ውብና ማራኪ እንዲሆን አድርገው እንዳቆዩት በርካታ መርጃዎችን መዘርዘር ይቻላል፡፡

ዛሬ በሌላው ክርስቲያን ዓለም የማናየውን ይህን ጥንታዊና ሐዋርያዊ የሆነ ክርስቲያናዊ ባህልና አምልኮ ምዕራባውያኑ ቱሪስቶችና ተጓዦች ብዙ ሺህ ዶላራቸውን ከስክሰው ሊያዩት በየዓመቱ ወደ ኢትዮጵያ ይጎርፋሉ፡፡ ይህ ልዩ የሆነው የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊው ሥርዓቷ፣ የወንጌል መሰረት ያለው ክርስቲያናዊ ባሕሏ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ምእመኖቿ እና ተከታዮቿ የኢትዮጵያዊ ማንነትና ብሔራዊ ኩራት መገለጫ ሆኖ የመዝለቁ ምስጢር ይኸው ይመስለኛል፡፡

በተመሳሳይም የእስልምና ሃይማኖትም ብንመለከት ምንም እንኳን ከሌሎች አገራት ቀድሞ ወደ አገራችን የመጣ ቢሆንም ሃይማኖቱ ልክ እንደ ክርስትናው ሁሉ በኢትዮጵያዊ ታሪክ፣ ባህል፣ ቅርስ፣ ወግና ትውፊት ላይ ውብ የሆነ ጥምረትን ፈጥሮ ነው እዚህ የደረሰው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ ‹‹የሃይማኖቶች መቻቻል ምድር›› ተብላ እንድትጠራ ያደረገውም እነዚህ ሁለት አንጋፋ ሃይማኖቶች በማይበጠስ የኢትዮጵያዊነት ፍቅር፣ አንድነት፣ የጋራ ታሪክ፣ ባሕልና ቅርስ ላይ የተሳሰሩ በመሆናቸው ይመስለኛል፡፡

ከዚህም የተነሳ ኢትዮጵያያን ሙስሊሞች እንደ ሌላው ዓለም ወይም በታሪክ በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ መልኩ ልዩ ትስስርና ቅርበት ካለን ግብፅም ሆኑ ሌሎች ጎረቤቶቻችን አፍሪካውያን አገሮች የእስልምና ሃይማኖቱን ብቻ እንጂ የዐረባዊነትን ቋንቋና ባህል ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሊለብሱትና ሊወርሱት አልፈቀዱም፡፡ ይኽም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን የተለዩ ያደርጋቸዋል፡፡

እንደ እስልምና ሃይማኖት ምሁራን አገላለፅ (Ethiopians only Islamized but not Arabized) በማለት በአጭር ቃል ታሪካዊ እውነታውን ይገልጹታል፡፡ ይህም ሕዝባችን ስላለው ጠንካራ ብሔራዊ ማንነትና ኩራት እንዲሁም ዘመናት ያላደበዘዙት የጋራ ታሪክና ቅርስ ያለው ኩሩ ሕዝብ እንደሆነ ትልቅ ማሳያ እንደሆነ እገምታለሁ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ዓይነት ሃይማኖት ቢኖረው ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅርና በእግዚአብሔርም ላይ ያለው እምነት ጠንካራ ነው። የበርካታ ተጓዦችና አጥኚዎች በጥናታቸው ‹‹ኢትዮጵያውያን ሃይማኖተኛ ሕዝቦች የሚበዛባት አገር ናት፡፡›› ወደሚለው ድምዳሜ የሚያደላ ነው፡፡

ይህ ሕዝብም በታሪኩ ሃይማኖቱን የራሱና የግሉ አድርጎ በአንድ ኢትዮጵያዊነት ጥላ ሥር ተዋዶና ተከባብሮ የኖረ ሕዝብ ነው፡፡ በዚህም ከራሱ አልፎ ለሌላው ዓለም ተምሳሌት የሆነበትን እርስ በርስ ተዋዶና ተከባብሮ የመኖርን አንጸባራቂ ታሪክ የፃፈ ሕዝብ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ይህ የምንኮራበት የሁለቱ አንጋፋ የሃይማኖት ተቋማት ታሪክ ሙሉ በሙሉ አልጋ በአልጋ ነበር ብለን እንዳንደፍር የሚያደርጉ በተለያዩ ዘመናት በሁለቱ ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ የተከሰቱ መለያየቶች፣ ግጭቶችና ጦርነቶች በአገራችን ታሪክ መዛግብት ውስጥ ተመዝግቦ አለ፡፡

በሃይማኖትና በፖለቲካ አላቻ ጋብቻ፣ የተፈጥሮ ሀብትና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ምክንያት ያደረጉ በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖቶች ሕዝቦች መካከል የተነሱ ጦርነቶችና ግጭቶችም እንደነበሩ ማስታወስም ግድ ይለናል፡፡ እነዚህን በአገራችን ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው የተነሱ ግጭቶችንና ጦርነቶችን መንስዔያቸውን፣ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ውጤታቸው ለመተንተን የሚሞከር አይሆንም፡፡

አነሳሴም በኢትዮጵያ ውስጥ አንጋፋ ስለሆኑት ስለ ክርስትና እና እስልምና ሃይማኖት የአብሮነት ታሪክና ግጭት ለመተንተን አይደለም፡፡ ለመግቢያ ያህል ስለእነዚህ ሁለት አንጋፋ ሃይማኖቶች የጠቀስኩት ለጽሑፌ ጥሩ መንደርደሪያ፣ ግልፅና መጠነኛ የሆነ ታሪካዊ እይታን ይሰጠናል በሚል ቅን ግምት ነው፡፡

የዛሬው ጽሑፌ ዋና ማጠንጠኛ አሳብ የሚከተሉት ናቸው፡-

 • የመንግሥትና የቤተ ክህነቱ ጋብቻና ፍቺ ምን መልክ ነበረው፣ አሁንስ የሁለቱ ተቋማት ግንኙነት ምን ይመስላል? የነገይቱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ቤተ ክርስቲያን የመምራት ኃላፊነት የማን ይሆናል?
 • ለቤተ ክርስቲያኒቱ ለሁለት መከፈል ምክንያት ናቸው የተባሉት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን እልፈት ተከትሎ በስደት ከሚገኙት አባቶች ጋር የተጀመረውን ድርድር ወደ ፍፃሜ ለማድረስ እየተደረጉ ያሉ ውይይቶችስ ምን ፋይዳ ሊኖራቸው ይችላል?
 • እንዲሁም የቀድሞው ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ፣ ወይስ ሌላ ፓትርያሪክ ይመረጥ በሚሉትና፤ በአጠቃላይ በቤተ ክርስቲያኒቱ የነገ ዕጣ ፈንታ ዙሪያ እየተናፈሱ ያሉ ስጋቶችና ፍርሃቶች መነሻቸው ምን ሊሆን ይችላል?
 • በፓትርያሪክ ምርጫው ላይ አንዳንዶች ስውር የሆነ የመንግሥት ጣልቃ ገብነትና ጫና አለ በሚል እየተንሸራሸሩ ባሉ አሳቦችና ስጋቶች ዙሪያ እኔም የበኩሌን ከቤተ ክርስቲያኒቱ የትናንት በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ መልኩ ከሚጠቀሱ ታሪኮቿ በመነሳት በቅን መንፈስ ላይ የተመረኮዘ ጥቂት የውይይት አሳቦችን ለማጫር ነው፡፡

የቤተ መንግስቱና የቤተ ክህነቱ ጋብቻና ፍቺ ከትናት እስከ ዛሬ

የክርስትና ሃይማኖት ወደ አክሱም ግዛት ከገባ በኋላ በወቅቱ ከነበረው የክርስትና መስፋፋት ባህርይ ጋር በተቃራኒው መልኩ የመንግሥት ሃይማኖት የመሆን ዕጣ ፈንታ ነበር የገጠመው፡፡ በአራተኛው መቶ ክ/ዘመን መባቻ ጀምሮ የተጀመረው የቤተ መንግሥትና የቤተ ክህነት ታሪካዊ ግንኙነትና ዝምድና ውሉ የሚመዘዘውም ከዚሁ ታሪካዊ ክስተት ጀምሮ ነው፡፡

ከዛን ጊዜ ጀምሮ በቤተ መንግሥትና በቤተ ክህነት መካከል የነበረውን ግንኙነት ለመተረክ የሚቻል አይደለም፡፡ ስለዚህም በተቻለኝ መጠን ወደ ተነሳሁበት ዋና የጽሑፌ አሳብ የሚያደረሰኝን የቅርቡን ዘመን ብቻ ታሪክ በማንሳት ጽሑፌን ልቀጥል፡፡

የመንግሥትና የሃይማኖት ጋብቻ እስከ 1966ት የደርግ ወደ ሥልጣን መምጣት ድረስ መሪዎች/ነገሥታቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባል መሆን እንዳለባቸው በሕገ መንግሥት ጭምር የተደነገገ ነበር፡፡

ይህ የቤተ ክህነቱና የቤተ መንግሥቱ ጋብቻ በደርግ ዘመን መንግሥት በግልፅ መፍረሱ ቢገልፅም፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በአገሪቱ ሕዝቦች ታሪክ፣ ባሕል፣ ሥልጣኔና ቅርስ እንዲሁም የዕለት ተዕለት የማኅበራዊ ኑሮ መስተጋብር ውስጥ ካላት ሰፊ ድርሻና አሻራ የተነሣ መንግሥትና ቤተ ክህነቱ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ በሆነ መንገድ የመሳሳቡ ነገር መጠኑ ቀነሰ እንጂ ሊጠፋ አልቻለም ነበር፡፡

ደርጉ ‹‹መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው፡፡›› ባለ ማግስት በወቅቱ የሚያራምደውን እግዚአብሔር የለሽ ሶሻሊስታዊ ሥርዓት በመደገፍ ረገድ የቤተ ክርስቲያኒቱን አባቶች እንዳሻው ለማሽከርክር በፈለገበት ወቅት፣ የአንተ ወሰን እስከዚህ ድረስ ነው በሚል በተነሳ አለመግባባት የተነሣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለተኛ ፓትሪያሪክ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ለእስር፣ ለአንግልትና ለሞት እንዲዳረጉ ሆነዋል፡፡

ይህ ለሺህ ዘመናት ቤተ ክህነቱና ቤተ መንግሥቱ የተቆራኙበት ታሪካዊ እትብት በአንድ ጀምበር ቆርጦ በመጣል ወደፊት ለመራመድ የማይቻል መሆኑን የእዚህ የደረግ ድፍረት የተሞላበት እርምጃ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ በተጨማሪም በሕዝቡ ፖለቲካዊ ስነ ልቦና ላይ የራስዋ የሆነ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ አሻራ ያላትን ቤተ ክርስቲያን ከዳር አውጥቶ መንግስትን መምራት አዳጋች መሆኑን ይህ የደርጉ አብዮታዊ እርምጃ በግልፅ እውነታውን የሳየ እንደሆነ አስባለሁ፡፡

በሕዝብ የዕለት ተዕለት ኑሮ፣ ኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ስነ ልቦና ውስጥ የራሷ የሆነ ትልቅ ተጽእኖ ያላትን ይህችን ተቋም በተዘዋዋሪ መንገድ በእጁ ለማስገባት ደርግ ፈርጣማ ክንዱን ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ አሳረፈ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱን በመቆጣጠር በእርሷም በኩል ሕዝቡን ተገዢው ለማድረግ መሪዋን አሰረ፣ ገደለ፡፡ ውጤቱም ዘግናኝ የሆነ የትውልድ እልቂትና ፍጅትን ነበር ያስከተለው፡፡

ይህ የደርጉ እርምጃ በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊው መልኩ የቆየው የቤተ መንግሥቱና የቤተ ክህነቱ የግንኙነት ሰንሰለት  በቀላሉ በአንድ ጀምበር ሊቆረጥ አለመቻሉን ሊያሳዩን ከሚችሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ አንዱና ተጠቃሹ ነው፡፡

የቤተ መንግሥቱና የቤተ ክህነቱ ተቋማት እርስ በርሳቸው እንደ ተቃራኒ የማግኔት ዋልታዎች የሚሳሳቡበት ምክንያቱ ቤተ ክርስቲያኒቱ በኢትዮጵያ ታሪክ፣ ኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ ሕይወትና ፖለቲካ ውስጥ ከነበራትና አሁንም ካላት ተጽእኖ የተነሳ እንደሆነ ብዙዎች የቤ/ቱ ምሁራንና ታሪክ አጢኚዎች ይስማማሉ፡፡

በዚህና በአያሌ ተዛማጅ ምክንያቶች ቤተ ክርስቲያኒቱ በአገሪቱ የሚከሰቱ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ ተጽእኖ እንዳላት ሁሉ እርሷም ከተለያዩ አቅጣጫዎችና ከመንግሥት በሚመጡ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ኩነቶች ተጽእኖ ስር መሆኗ ግን አልቀረም፡፡ እናም መንግሥትና የቤተ ክህነት ግንኙነት አዎንታዊና አሉታዊ ውጤቱን እያስመዘገበ ዘመናትን ተሻግሮ  አሁን የሚገኝበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ የሚያጠኑ የታሪክ ምሁርና ተመራማሪ የሆኑ የአንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቋም ባልደረባ እንደሚሉት፣ ‹‹ቤተ ክርስቲያኒቷ ራሷን ቻለች በተባለችባቸው ሃምሳ ዓመታት ከግብፅ ጥገኝነት ብትላቀቅም በመንግሥት ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ ወደ መሆን መሸጋገሯን፡፡›› በጥናታቸው ይገልፃሉ፡፡

እኚሁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር እንደሚያስረዱት የቤተ ክርስቲያኒቱን የሃምሳ ዓመታት እራሷን የመስተዳደር ጉዞ ‹‹ፍፁማዊው ከነበረው የውጭ ጥገኝነት፣ ፍፁማዊው ወደሆነው የውስጥ ጥገኝነት የተሸጋገረበት ነው፡፡›› በማለት በአጭር ቃል ይገልጹታል፡፡

‹‹ቤተ ክርስቲያኒቱ ከግብፃውያን ቅኝ ግዛት ተላቃ በንጉሡም ሆነ በደርግ ዘመነ መንግሥት አንፃራዊ በሆነ መልኩ ውስጣዊ አስተዳደሯን በተመለከተ ራሷን ችላ በነፃነት ማከናወን የምትችልበት ዕድል ማግኘቷን ያሰምሩበታል፡፡ ይህን አንፃራዊ በሆነ መንገድ ራሷን በነፃነት የማስተዳድር ዕድል ከ1983ቱ የመንግሥት ለውጥ ጋራ ሲመጣ ግን ብቻውን አልመጣም፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቷ ራሷን ሙሉ በሙሉ የማስተዳደር አቅሟን በሚገባ ሳታዳብርና በቂ ዝግጅት ሳታደርግ ነበር ነፃነቱ የደረሰባት ይላሉ፡፡›› እኚሁ ምሁር፡፡

የታሪክ ተመራማሪው እንደሚሉት በደርግ እጅ የተገደሉት አቡነ ቴዎፍሎስ የጀመሯቸው የተቋማዊ አሰራር ውጥኖች ቢኖሩም ራስን በነፃነትና በውጤታማነት ለማስተዳደር በሚያስችል ደረጃ ሳይዳብሩ ቀርተዋል፡፡

የተቋማዊ አሰራሩ ድክመት ባልተቀረፈበት በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ ለረጅም ዓመታት በመንበሩ ላይ የቆዩት ፓትሪያሪክ አቡነ ጳውሎስ ከትምህርታቸውና ከውጭ ዓለም ልምዳቸው በመነሳት ስር ነቀል የሆነ ለውጥ ያመጣሉ ተብለው ቢታሰቡም ከበርካታ በመልካም እርምጃ ከሚጠቀሱባቸው ሥራዎቻቸው ባሻገር የተጠበቁትን ያህል የቤተ ክህነቱን ተቋማዊ አሠራርና አሥተዳደር ከመሠረቱ ለመለወጥ ሳይችሉ ቀርተዋል ሲሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ምሁራንና የቅርብ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡

ፓትርያሪኩ ይላሉ የአዲስ አበባው ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር ‹‹ከመንግሥት ጋር አላቸው የሚባለው የጠበቀ ግንኙነት መንግሥት በበኩሉ ጣልቃ እንደማይገባ ለማሳየት የቤተ ክርስቲያኒቱን ውስጣዊ ጉዳዮች በሙሉ ለራሷ የተወ በመምሰል በቅኝ አዙር አገዛዝ ‹አስተዳዳራዊ ድክመት ወደ አስተዳዳራዊ ቀውስ እንዲሸጋገር መንገዱን አመቻችቷል› በማለት ይደመድማሉ፡፡

ኢህአዴግ መንግሥትና ሃይማኖትም የተለያዩ ናቸው፡፡ አንዳቸው በአንዳቸው ጉዳይ ጣልቃ አይገቡም በሚል በግልፅ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ አስፍሯል፡፡ እናም የዘመነ ኢህአዲጓ ኢትዮጵያ ለሁሉም ሃይማኖቶች ክፍት መሆኗን በቃልም በተግባርም ያሳየች አገር ሆና ነው ላለፉት ሃያ ዓመታት የተጓዘችው፡፡

ይሁን እንጂ ይህን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ለመተርጎም ግን ገና ብዙ የሚቀረው ቢሆንም፣ የሃይማኖት ነፃነትን በግልፅ የተቀበለችና መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸውን በሕገ መንግሥቷ ያጸደቀች አገር ግን አለችን፡፡

የኢፌድሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 11 ላይ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ፣ ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንደማይገባ ቢገልፅም አልፎ አልፎ በተግባር እየታየ ያለው እውነታ ግን በተቃራኒው እንደሆነ ታዛቢዎችና በርካታ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ጥናት ያደረጉ የምሁራን የጥናት ወረቀቶች የሚጠቁሙት፡፡

በሕገ መንግስት ደረጃ ሃይማኖትና መንግሥት የተለያዩ ናቸው አንዱ በአንዱ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ አይገቡም ቢባልም፤ በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በተመለከተ ግን የኢህአዴግ መንግሥት ትናትናም ሆነ ዛሬ ነፃ ነኝ የሚልበት ድፍረትና ወኔ  ይኖረዋል ብዬ ለማሰብ ግን ፈፅሜ አልደፍርም፡፡ ለዚህም ሙግቴ አንዳንድ አሳማኝ ማስረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

ኢህአዴግ በሕገ መንግሥቱ ‹‹ኢትዮጵያ ለሁሉም ሃይማኖቶች እኩል ናት፣ የመንግሥት ሃይማኖት የሚባል ነገር የለም፣ መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው፡፡›› ቢልም ወደ ሥልጣን በመጣ ማግስት ወደ ቤተ ክህነቱ ተቋም በድፍረት ዘልቆ በመግባት ያለፈለገውን አውርዶ ያሻውን ለማስቀምጥ የሄደበት መንገድ በወረቀት ላይ ከደነገገው ሕግ ጋር የሚፃረር እንደሆነ ተደጋግሞ የተነሳ ጉዳይ ነው፡፡

እናም አሁንም ድረስ ለእኔና እኔን ለሚመስሉ ለበርካታዎች ቤተ መንግሥቱና ቤተ ክህነቱ ተለያይተዋል የሚባልበት መሰመሩ የቱ ላይ እንደሆነ በግልጽ ለመጠቆም እየተቸገረን እዚህ ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡

የኢህአዴግ መንግሥት ‹‹ህመምተኛ ነኝ፣ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመምራት አልችልም፣ በገዛ ፈቃዴ ሥልጣኔን ለቅቄያለሁ…፡፡›› ብለዋል በሚል ሰበብ ከመንበራቸው እንዲሰደዱ የተደረጉት አቡነ መርቆሪዮስ በሂደት ይኸው እስከ ዛሬይቱ ቀን ድረስ በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ ውስጥ ትልቅ የታሪክ ስብራትና ጠባሳ የሆነ አሳፋሪ ክስተትን ጥሎ አልፏል፡፡

ይህ ክስተት የወለደው መለያየትና መከፋፈልም የሃይማኖት አባቶችን በአብዛኛው የጥላቻ፣ የጠላትነትና የጽንፈኝነት የፍረጃ ፖለቲካ በሚንጠው የአገራችን ፖለቲካ ጎራ አሰልፎ ከቃላት ጦርነት ባለፈ በግልፅ ፖለቲካዊ አቋም እንዲያራምዱ ትልቅ በርን ከፈተ፡፡

ሰሞኑን በተለያዩ መረቦችና በማኅበራዊ ድረ ገጾች ተለቀው ያየናቸው አንድ በአሜሪካ የሚገኙ የሃይማኖት አባት፣ ‹‹በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ስርዓት፣ ፍትህ፣ የሕግ የበላይነትና ብልጽግና መስፈን አማራጩ መንገድ ጦርነት ነው፣ ሌላ የወንድማማቾች እልቂት፣ ሌላ የአንድ እናት ማኅፀን ልጆች ዳግማዊ ፍጅት ነው፡፡›› ብለው ዱር ቤቴ ካሉ ነፍጥ አንጋች ወገኖቻችንን ጋር በረሃ ድረስ ወርደው የተነሱት ፎቶ የሃይማኖት መሪዎቻችን ላሉበት የአቋም መዋዠቅና ኢ-መንፈሳዊ አካሄድ ትልቅ መሳያ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

ለፍቅር፣ ለሰላም፣ ለምሕረትና ለእርቅ ይቆማሉ የምንላቸው አባቶቻችን አድራሻቸው የጦር ግንባር፣ የእልቂት አውድማ ከሆነ እንግዲህ ምን እንላለን!?

ለእውነትና ለፍትህ ጠበቃ ይሆናሉ የምንላቸው አባቶች እርሰ በርሳቸው ተለያይተውና ተከፋፍለው በቃላት ጦርነት የሚሞሻለቁ ከሆነ ፍፃሜያቸው ምንድን ነው!?

የምሕረትና የእውነት አደባባይ በተባለች በቤተ ክርስቲያኒቱ ዐውደ ምሕረት ላይ ሐሰት ነግሶ፣ ጥላቻ ድል ነስቶ የሚወጣ ከሆነ ምን ማለት ይቻለን ይሆን!?

ቤተ ክህነቱ አሁን ላለበት ቀውስ ተጠያቂው ማነው፡- ራሱ የቤተ ክህነቱ ተቋምና መሪዎቹ ወይስ…?

ዛሬ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላለችበት ዘርፈ ብዙ አስተዳዳራዊ ቀውሶች፣ ሙስና፣ ዝርፊያ፣ ጎሰኝነት፣ ሥርዓተ አልበኝነት፣ የሞራል ውድቀትና ዝቅጠት፣ የመንፈሳዊነት ሕይወት መጥፋት… ወዘተ ተጠያቂው ማነው? ይህ ጽሑፌ ቤተ ክርስቲያኒቱንና የሚመሯትን አባቶች ክብርና ልእልና ዝቅ ለማድረግ ያለመ አድርገው እንዳያዩብኝ አባቶችን፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ተከታዮችንም ጭምር በትህትና ልገልጽላቸው እወዳለሁ፡፡

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ በቅንነት መንፈስ ቤተ ክርስቲያኒቱ ባሉባት ችግሮች ዙሪያ በቅንነትና በግልፅ ለመወያየት መድረክ ለመክፈት ነው፡፡ በዚህም ከትናንት ታሪካዊ ስህተቶቻችንና ውድቀቶቻችን ተምረን በጋራ ለመፍትሔው ለመመካር እንጂ የማንንም ሰብአዊ ክብርና ማንነት ለመንካት ብዬ አይደለም ይህን ጽሑፍ ያዘጋጀሁት፡፡

ወደ ተነሳሁበት ርዕሰ ጉዳይ ስመለስ የቤተ ክህነቱ ተቋም አሁን ላለበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ዋናው መንስኤ ራሱ ነው፡፡ መፍትሔውም የሚመነጨው ከራሱ ከቤተ ክህነቱ ተቋምና መሪዎቹ እንደሆነ አጥብቄ አምናለሁ፡፡ እስቲ በቅርብ ዘመን ቤተ ክህነቱና መሪዎች የተፈተኑበትን የታሪክ አጋጣሚዎች ከቅርብ የአገራችንና የቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ በመነሳት ለማሳየት ልሞክር፡፡

ቤተ ክህነቱ የራሱን መንፈሳዊ ክብር፣ ኃይል፣ ሥልጣንና ልእልና በመጠበቅ ረገድ ጉልበቴን ያለበትን በርካታ አጋጣሚዎችን እኔና ትውልዴ በተደጋጋሚ ለመታዘብ የቻልንባቸው ወቅቶች ትናንትና ነበሩ፤ ዛሬም ተደቅነውብን አሉ፡፡

የቤተ ክህነቱ ተቋም የሚመሩ አባቶች ይላሉ እውቁ ምሁርና ጸሐፊ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ክህደት ቁልቁለት በሚለው መጽሐፋቸው፡-«ሥጋቸውንየበደሉ፤ ለነፍሳቸውያደሩ» ናቸው ተብሎ ነው በብዙዎቻችን ምእመናን ዘንድ የሚታመነው፡፡የሃይማኖትመሪዎችለጽድቅማለትለእውነትእንዲሁምለፍትሕናለእኩልነትየቆሙናቸውተብሎይታመናል፡፡ ለሀብትናለሥልጣንግድስለሌላቸውከዚህዓለምጣጣውጭናቸውም ተብለው ነው የሚቆጠሩት፡፡

የሃይማኖት መሪዎች ለፍትህ፣ ለስው ልጆች ነፃነትና እኩልነትም ድምፃቸውን የሚያሰሙ የእውነት ጠበቃዎች ናቸው፡፡ ልዩ ክብር በሚያሰጣቸው በመንፈሳዊ ሰብእናቸውና ሥልጣናቸው የተነሣም በእውነትና በፈትህ ተቃራኒ የሚቆሙ መንግስታትን፣ መሪዎችንና ክፉዎችን ሁሉ የመገሰጽና ፊት ለፊት የመቃወም መለኮታዊ ሥልጣን ከላይ ከአርያም የተቸራቸው እንደሆኑ ነው በአብዛኛው ምእመኖቻቸው ዘንድ የሚታሰበው፣ የሚታመነውም፡፡››

ይሁን እንጂ በቤተ ክህነቱ ተቋምና ቤተ ክህነቱን በሚመሩት አባቶች ዙሪያ በእኔ እና በትውልዴ ዘመን እንኳን የታዘብነው እውነታ ግን ከዚህ ተቃራኒ የሆነ ነበር ወይንም ነው፡፡ ደርግ ወደ ሥልጣን በመጣ ማግስት የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪ የነበሩትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ሲያግዝና በግፍ ሲያስገድል ድርጊቱን በመቃወም ስለ እውነትና ፍትህ ድምፃቸውን ያሰሙ አባቶች እንደነበሩን አልሰማንም፡፡

እንደውም በተቃራኒው አሁን አሁን እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ስለ ቅዱስነታቸው ከመንበራቸው መወገድና መገደል ‹‹የክብር ፊርማቸውን በማኖር ሙሉ ስምምነታቸውን የገለጹ የሲኖዶሱ አባላት አባቶች እንደነበሩ ነው፡፡››

የግድያ እርምጃው ማንንም ከማንም ያለየበት ደርግ በእግዚአብሔር የለሽ አቋሙ ትውልዱን በኮሚኒሰት ማኒፌስቶ ጸበል እያጠመቀ ከሃዲ ሲያደርገውና አብያተ ክርስቲያናትም እንዲዘጉ ሲያደርግ፣ የሃይማኖት ሰባኪያን ወደ ወህኒ ሲወረወሩና ሲረሸኑ ትንፍሽ ያለ አባት ነበር እንዴ!?

በሀገሪቱ የሺህ ዘመን ታሪክ የደመቀ አሻራ የነበራት ቤተ ክርስቲያን ሀገሪቱ በጥፋት ገደል ጫፍ ላይ ቆማ በነበረችበት ጊዜ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ድምፃቸው ያለመሰማቱ ጉዳይ ምክንያቱ ምን እንደነበር አባቶቻችን አልነገሩንም፤ እኛም ደፍረን አልጠየቅንም፡፡

በተቃራኒው አባቶቻችን በዘመኑ የፖሊቲካ መሪዎች ጋር እጅና ጓንት በመሆን ከወንጌል እውነት ተቃራኒ ለፍትህ፣ ለእውነት፣ በወንድማማቾች መካከል ፍቅርና ሰላም እንዲሰፍን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያሰማሉ ሲባል ድምፃቸውን አጥፍተው በፍርሃት ድባብ አፋቸው ተሸብቦ ያን የመከራ ዘመን ከሕዝባቸው ጋር ለመቆም አልደፈሩም፡፡

አባቶቻችን የግፍንና የጭቆናን ቀምበር ለመስበር ሕዝቡን ከጎናቸው አሰልፈው ግንባር ቀደም በመሆን ለእርቅ፣ ለፍትህ እና ለሰላም መቆም አለመቻላቸውን ትላንትናም ሆነ ዛሬ አይተናል፣ ታዝበናል፡፡

የአንድ እናት ማኅፀን ልጆች እርስ በርሳቸው ሲተራረዱ፣ በቀይ ሽብርና በነጭ ሽብር የራሺያ የተውሶ አብዮት ምድሪቱ በደም አበላ ተመትታ አኬል ዳማ ስትሆን፣ ወንድማማቾች በርዕዮተ ዓለም ልዩነት አንጃ ፈጥረውና እርስ በርሳቸው ተቧድነው ሲተላለቁ መንግሥትን ተው ያለ፣ ወጣቶቹንስ ከልባቸው እንዲሆኑ የመከረና የዘከረ፣ ስለ ሰላምና እርቅ ድምፁን ከፍ አድርጎ ያሰማ የሃይማኖት መሪ ነበር እንዴ!?

ይህን የዘመኑን አሰቃቂ ክስተትና የሃይማኖት አባቶች ዝምታን የመረጡበትን እንቆቅልሽ ‹‹ያለመቻቻል ፖለቲካ ሰማዕትነት፡- መቼም እንዳይደገም›› በሚል ሦስት የአገራችን ምሁራን ባቀረቡት የጥናት መጽሔት ላይ የታሪክ ምሁሩ ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ ‹‹ቀይ ሽብር በኢትዮጵያ፡- ታሪካዊ ይዘትና አንድምታ›› በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጥናታዊ ወረቀታቸው፡-

‹‹በዘመነ ቀይ ሽብር አገሪቷ አስፈሪ የሆነ የሞት መልአክ ባንዣበባት ወቅት ካህናቱና የሃይማኖት መሪዎች እንደ ጥንቱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ባህል ታቦት ተሸክመውና መስቀል ይዘው በመውጣት ስለ ሰላምና ስለ እርቅ ሊሰብኩ ቀርቶ፣ ለራሳቸው ፈርተው ተሸሽገው ነበር፡፡›› በማለት ትዘብታቸውን በመግለፅ በወቅቱ የነበሩትንና አሁንም ድረስ በሕይወት ያሉትን አንጋፋ የቤተ ክርስቲያኒቱን አባቶች የዛን ቀውጢ ጊዜ የት እንደነበሩ የጠየቁት፡፡

በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት የሰው ደም በከንቱ ሲፈስ፣ ምርጫ 97ትንተከትሎ እንዲያ አገሪቱ ስትታመስ፣ ሮጠው ያልጠገቡ ሕጻናት በአልሞ ተኳሾች ግንባራቸው በጠራራ ጸሐይ እየተመቱ ሲወድቁ፣ የኢትዮጵያውያን ምስኪን ራሄሎች/እናቶች ዋይታና ፣ ኤሎሄታ፣ የፍርድ ያለህ፣ እያሉ እንባቸውን ወደ ጸባዖት ሲረጩ፣ ስለ ሰላም፣ እርቅና እውነት ይቆሙ ዘንድ የተገባቸው አባቶቻችን ለመሆኑ በዛች ቀውጢ ሰዓት ድምፃቸው ምነዋ አልተሰማ?!

ዛሬ ስለ ፍትህ፣ እውነትና ሰላም ይቆማሉ የምንላቸው አባቶቻችን በተቃራኒው መቆማቸውን ስናይ እኛ መንፈሳዊ ልጆቻቸው በእፍረት እንሸማቀቃለን፡፡ ከዛም አልፎ ዛሬ በግልጽ እያየንና እየሰማን ያለነው የሞራል ውድቀቱ፣ ዘረኝነቱ፣ ሙስናው፣ የመንፈሳዊ ሕይወት መጣቱ ጉዳይ ሌላ ትልቅ ቀውስ ሆነ ብቅ ብሏል፡፡ እናም የነገ የቤተ ክርስቲያኒቱ ህልውና ክብርስ ምን ሊሆን ይችላል በሚል በዋይታና በለቅሶ እንደ ነቢዩ ኤርምያስ ዓይኖቻችንን ወደ አርያም ለማንሳት እንገደዳለን፡፡

አሁን በመሪነት ያሉ አንዳንድ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች በከፍተኛ የአመራር ስነ ምግባር ብልሹነት ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ መናገር እንደ ዜና እንኳን የሚቆጠርበትን ደረጃ ካለፍን ሰንብቷል፡፡ በእነዚህ የሃይማኖት መሪዎችና አባቶች ነን በሚሉ ሰዎች እየተፈጸመ ያለው ድርጊት የእነርሱን ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የማኅበረሰባችንን የሞራል ድቀት፣ የአመራር ዝቅጠትና ራእይ አልባነት የሚያረጋግጥልን ነው፡፡

እንዲህ ዓይነቶቹን የሃይማኖት መሪዎች ማጋለጥ በአንዳንዶች የዋኻን ዘንድ የሃይማኖቱን ወይም ተቋማቱን እንደ ማዋረድ ተደርጎ ይሰበካል ወይም ይቆጠራል፡፡

በሌላ በኩል ይህን አመለካከት ተቋቁሜ ድርጊቱ እንዲታረም እታገላለሁ የሚል የሃይማኖት አባትም ሆነ ምእመን ቢገኝ እንኳን አቤቱታውን የሚያሰማበት መድረክም ሆነ አካል የለም፡፡ ‹‹የሃይማኖት መሪ ቢያጠፋ እንኳን ልንጸልይለት እንጂ እንደ ሥጋውያን ልንጠይቀው አይገባም፡፡›› የሚል እውነት ቀመስ የሐሰት ምሽጋቸውን ይቆፍራሉ፣ ያስቆፍራሉ፡፡

ታዲያ ይህን መሰል ማኅበረሰባዊ ክብራቸውን የሕገ ወጥነትና የኢ-ሞራላዊነት መደበቂያ ያደረጉ የሃይማኖት አባትና መሪዎች ነን የሚሉ እስከ መቼ እንዲህ ይቀጥላሉ፡፡ በዚህ ሁሉ ድቀት፣ ቀውስና ዝቅጠት ውስጥ ያለችው ቤተ ክርስቲየን በአንፃሩ ደግሞ ለትንሳኤዋ የሚተጉ እንደ ንጉሥ ዳዊት ባለ መንፈሳዊነት ‹‹የቤትህ ቅናት በላኝ›› በሚል መንፈሳዊ እልኽና ቁጭት የሚተጉ አባቶችና መሪዎች እንዳሉም አልዘነጋም፡፡

እንደ ነቢዩ ኤልያስም ስለ ቅዱስ መቅደሱና ስለ አምልኮተ እግዚአብሔር በፍፁም ነፍሳቸው የሚቀኑ፣ ከበዓል ነቢያትና በሃይማኖት ካባ ስር ተሸሽገው ካሉ አስመሳዮች ጋር ፊት ለፊት በመግጠም ስለ እውነትና ፍትህ የሚከራከሩ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች ትላንትና እንደነበሩና ዛሬም እንዳሉ ቅንጣት ያህል አልጠራጠርም፡፡ እንደ ነቢዩ ኤርምያስም እንባቸውን እያፈሰሱ ‹‹አቤቱ እባክህ የሆነብንን አስብ…!›› የሚሉ አባቶችና ምእመናን በመቅደሱ አደባባይና በጓዳ ውስጥ ዛሬም እንዳልጠፉ አምናለሁ፡፡

የተነሳሁበትን የቤተ ክህነቱን ጉዳይ በአንድ ክፍል ለመጨረስ የሚቻል አልሆነም፡፡ ስለዚህም በቀጣይ ጽሑፌ በተለይ በኢትዮጵያውና በአሜሪካው ሲኖዶስ መካከል ሰላማዊ ድርድሩ ወዴየት ያመራ ይሆን፣ የቀድሞው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ በሚሉና በፓትርያሪክ ምርጫ ዙሪያ የሚነሱትን አስተያየቶችና ውዝግቦች፣ የመንግስትን ስውር እጅና ጫና በተመለከተ በቤተ ክርስቲያኒቱ የቅርብ ታሪክ ላይ በመንተራስ ለመተንተን የሚሞክረውን ጽሑፌን በቀጣይ ሳምንት ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡

ሰላም! ሻሎም!

ፓትሪያርክ መርቆሬዎስ ቡራኬ ሰጡ፤ ሊቀካህናት ምሳሌ እንግዳ ታሪካዊ ስህተት እንዳይሰራ አስጠነቀቁ

ተክለሚካኤል አበበ

Abuna Merkorios (Patriarch and Catholicos of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church)

ትናንት እሁድ ታህሳስ 21 ቀን በቶሮንቶ በተከበረው አመታዊው የታህሳስ ገብርኤል በዓለ ንግስ ላይ ፓትሪያርክ መርቆሬዎስ ለህዝቡ ቡራኬ የሰጡ ሲሆን፤ ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ ከሰላምና አንድነት ሂደቱ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ አሳዛኝ አቅጣጫ እየያዘ መሆኑን ገልጸው፤ ታሪካዊ ስህተት እንዳይሰራ ህዝቡ በንቃት እንዲጠባበቅ አሳስበዋል።

በትናንትናው እለት በተከበረውን የታህሳስ ገብርኤል በኣል ላይ ለህዝቡ ባሰሙት አጭር የመግቢያ ንግግር፤ የውጪው ሲኖዶስ አባላት የቤተክርስቲያን አንድነት እንዲከበር ጥረት ቢያደርጉም፤ ከሰላምና አንድነት ጉባኤው አዘጋጆቹ አንዱና የኢትዮጵያውን ቅዱስ ሲኖዶስ ሊያናግሩ ሄደው የነበሩት ሊቀካህናት ሀይለስላሴ አለማየሁ ከቤታቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተጠርተው በአጃቢ ወደአሜሪካ በግድ እንዲመለሱ እንደተደረጉ ተናግረዋል።

ሌላኛው ሸምጋይ ዲያቆን አንዱአለም የደረሰበት እንደማይታወቅም ተናግረው ዝርዝሩን በመጪው ሳምንት ለህዝቡ እንደሚገልጹና ህዝቡም በንቃት እንዲከታተል አሳስበዋል።
በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ በዚህ ሳምንት የጉዳዩን መጨረሻ ተመልከተው ስለሰላምና አንድነት ሂደቱና በሸምጋዮቹ ላይ ስለደረሰው ችግር መግለጫ እንደሚሰጡም ጠቁመዋል።

በትናንትናው እለት በተከበረው በዓል ላይ ባለፈው ወር የቶሮንቶ ቅድስት ማርያም ካቴድራልን መርቀው የከፈቱት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትሪያርክ ርእሰ ልቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የተገኙ ሲሆን፤ የአቋቀም ሊቅ የሆኑት ፓትሪያርክ በእለቱ በቅዳሴና በዝማሬ፤ በብርቱ መንፈስ ሲያገለግሉ ውለዋል።
የፓትሪያርኩ ጤናም በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።

Abuna Merkorios (Patriarch and Catholicos of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church) 2012

Abuna Merkorios Patriarch and of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church)

Abuna Merkorios Patriarch of the Ethiopian Orthodox Church

ECADF.COM

ሰብአዊ መብት ለሰብአዊያን (ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

በዓለም ዙርያ ያሉትን አንባቢዎቼን 2013 የደስታና የብልጽጋና ዓመት ይሁንላችሁ በማለት መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

ላለፉት ያልተቋረጡ 300 ሳምንታት ያህል ጦማሮቼን ለተከታተሉ ሁሉ፤ከልብ የመነጨ አክብሮቴንና ምስጋናዬን እገልጻለሁ፡፡ ከኢትዮጵያና ከዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ለተቸረኝEvery human has rights prof. Alemayehu G. Mariam ማበረታታት ምስጋናዬ ይድረስልኝ፡፡

አንባቢዎቼን፤ በኢትዮጵያና በዓለም ላይ ሁሉ የተደፈሩ ሰብአዊ መብቶችን ለሁሉም ሰብአዊ ፍጡራን እንዲዳረሱና እንዲከበሩ የመጠራሪያና የማንቂያ ደወል በአፍሪካና በዓለማቱ ሁሉ እንደውል እላለሁ፡፡ ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ አንዳሉት “በማይበጠስ የአንድነት ሰባዊ ሰንሰለት ተሳስረናል፡፡ በአንድ አይነት እጣ ፈንታ ተያይዘናል:: አንዱን በቀጥታ የሚያጠቃው ሌላውንም በተዘዋዋሪ ደግሞ አይተወውም፡፡

አንባቢዎቼን፤ በሎርድ አልፍሬድ ቴኒሰን የረቀቀ ለዛ ባለው ግጥም (“እንጠራራ፤ ለሰብአዊ ፍጡር ሁሉ”) አሮጌውን ዓመት በመሰናበት አዲሱን እንቀበል በማለት አጠይቃለሁ::

እንጠራራ፤ አሮጌውን አመት ለመሸኘት አዲሱን ለመቀበል

እንጠራራ፤ ሃሰትን ተገላግለን አውነትን ለማስገባት

እንጠራራ፤ ሃዘንና ትካዜን ከሕሊናችንን ለማስወገድ

እንጠራራ፤ በደሃና በሃብታም መሃል ያለዉን ቅራኔ ለመፍታት::

እንጠራራ፤ ለሰብአዊፍጡርሁሉአዲስስብእናእንተካለት::

እንጠራራ፤ የወደቀ ስራትን ለመሸኘት

ለመለወጥ ዘመን የሻረውን የፓርቲዎችን መናቆር

እንጠራራ የሕይወትን  ክቡርነት እናስመስክር

በጣፋጭ ባህል በንጹህ ሕግጋት::

 

እንጠራራ፤  አጉል ትምክህትን ለማጥፋት

በዜግነት ላይ ሀሜት ክፋትና እልህ እንዲወገድ

እንጠራራ፤  ፍቅርን ሃቅና እውነትን ለማስገባት

እንጠራራ፤ መልክምን ለመተግበር ለሁሉም በሚሆን መንገድ::

እንጠራራ፤ ያለፉትን ሺህ እልቂቶች ላለመድገም

እንጠራራ፤ ለቀጣዮቹ ሺህ ዓመታት ሰላም አንዲሰፍን

እንጠራራ፤ለነጻነት ወደሚያበቃን ጀግንነት

ለሩህሩህ ልብ፤ ለለጋሽ እጆች

እንጠራራ ጨለማ የዋጣትን ምድር ለማዳን::

2012ን ስንሸኘው: ባለፈው አመት ካቀረብክዋቸው ሳሚንታዊ  ጽሁፎቼ  ትንሽ  ቅንጣቢ በመውሰድ ነው::

በጃንዋሪ 2012 የአፍሪካ ስፕሪንግ አለያም ‹‹የኢትዮጵያ ጸደይ›› ይመጣ እንደሆነ በማለት አግራሞቴን ጎላ አድርጌ አሰምቼ ነበር፡፡

የራሴን ጥያቄ በአልበርት ካሙስ ‹‹ዘ ሪቤል›› (ተቃዋሚ) በተባለው መጽሃፍ ሚስጥራዊ ትርጉም ውስጥ ሆኜ  መልሼ ነበር፡፡ ተቃዋሚ ምንድን ነው? ሲል ጠየቀ ካሙስ………… ‹‹እምቢ የሚል ሰው ………ዕድሜውን ሙል እሺ ጌቶቼ፤ እሺ እመቤቶቼ ሲል የኖረ ሰው በድንገት ያንገሸግሸውና ዳግም ትእዛዝ አልቀበልም ብሎ እምቢ ይላል፡፡ እምቢ ሲልስ ምን ማለቱ ነው? የሚለውማ፤ ለምሳሌ ‹‹ይሄ ትእዛዝ በዛ፤ እስካሁን ድረስ እሺ ከእንግዲህ ግን አሻፈረኝ፤ መጠናችሁን አጣችሁ፤›› ወይም  ‹‹እሺ ለማለትና ለመቀበል በቃ ለማለትም ገደብ አለው:: እምቢተኛው የራሱን ድምጸ ውሳኔ ካገኘበት ጊዜ አንስቶ……. ከአሻፈረኝ ሌላ ቃል ባይወጣውም፤ መመኘትና መዳኘት ይጀምራል፡፡ እምቢተኛው የሚሰጠውን ትእዛዝ በመጋተር ሊቋቋመው ከሚችለው በላይ የሚጫንበትን ትእዛዝ ላለመቀበል ይወስናል፡፡›› የአፍሪካ ስፐሪንግ አፍሪካውያን ኢትዮጵያንም ጨምሮ፤ከተጫነባቸው የግፍ ጫና እንቅልፋቸው ነቅተው በብሩሁ ጸደይ  ተነቃቅተው ‹‹አሻፈረኝ! በቃ ማለት በቃ ነው!›› ማለት ሲችሉ ነው፡፡

በማርች 2012 ኢትዮጵያ ከዲክታተርሺፕ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ትሸጋገራለች ብዬ በድፍረት ተንብዬ ነበር፡፡. ከዚሁ ጋርም   የዲክተተርሺፕ ማብቃት፤ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲን መወለድ አያረጋግጥም ብዬም ነበር፡፡ከሚገረሰሰው የበሰበሰ ዲክታተርሺፕ ሊፈለፈል የሚችል የዴሞክራሲ ዕውነታ ሊኖር አይችልም፡፡ ዴሞክራሲን ለማምጣት በርካታ የሕብረት አድካሚ ስራዎች ያስፈልጉታል፡፡ኢትዮጵያን ከተጫነባት የፈላጭ ቆራጭ ዲክታተርሺፕ አገዛዝ ለማላቀቅና ከግፈኞችን በደል ከማይጠግቡ የዓመጻ ልጆች ለማላቀቅ ብዙ ጉልበትና አንድነት መስማማት ይጠይቃል፡፡ይህን ለማድረግ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ተቋማት፤ተግባራዊነትን የሚያረጋግጥ የፖለቲካ ድርጅት፤የሲቪል ማሕበረሰብ ስርአት እና የብራሀን ፋና ወጊ የሆነ የነጻው ዴሞክራቲክ ፕሬስ ትንሳኤ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡

በኤፕሪል 2012 ለጀግናዬና አልበገር ባዩ የፔን በነጻነት የመጻፍ ሽልማት አሸናፊ ለሆነው እስክንድር ነጋ አንድ ልዩ አክብሮት መግለጫ ጽፌ ነበር፡፡ እስክንድር ነጋ (ለኔ አይበገሬው እስክንድር ነጋ)ሽብርተኛ ተብሎ በኢትዮጵያ አለሁ በሚለው ገዢ መንግስት ለእስር ተዳርጓል፡፡ እስክንድር ግን የጀግኖች ጀግና ነው፡፡ የእስክንድር ለእስር መዳረግ በበርካታ ያገባናል በሚሉ ታዋቂ ጋዜጠኞች፤ በተመሳሳይ ስቃዩ በያሉበት የደረሰባቸው ኬነዝ ቤስት፤(የላይቤርያው ኢንድፔንዳንት ዴይሊ ጋዜጣ መስራች) ሊዲያ ካቾ፤ዝነኛው የሜክሲኮ ጋዜጠኛ፤ የኢራኩ እውቅ ተቃዋሚ፤አክባር ጋንጂ: ፋራጂ ሳርኮሂ፤በሕንዱ ታዋቂ አሩን ሹውሪ፤እና በበርካታ ሌሎች የእስሩ ተቃዋሚዎች ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ለኔ እስክንድር ልዩ ጀግናዬ ነው፤ ምክንያቱም፤ከሃሳብና ከእውነት ውጪ መሳርያ የሌለው ተሟጋች ነውና፡፡ ቅጥፈትን: በእውነት ስለት ብዕሩ ብቻ ሰየፈው:: ተስፋ መቁረጥን በተስፋ፤ፍርሃትን በድፍረት፤ ቁጣን በምክንያታዊነት፤ዕብሪትን በትህትና፤መሃይምነትን በዕውቀት፤አለመቻቻልን በትዕግስት፤ጥርጣሬን በዕምነት፤ ጭካኔን ደግሞ በርህራሄ እስክንድር ተዋጋው›፡፡ እስክንድር አልበገሬው!

በሜይ 2012  ላይ የጂ 8 የምግብ ዋስትና ስብሰባ በሚካሄድበት በዋሽንግቶን ዲ ሲ ወጣቱ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ድምጹን ከፍ አድርጎ ነጻነት! እስክንድር ነጋ ይፈታ!  በማለት ድምጹን ከፍ አድርጎ ተናገረ!  ያለፈው መለስ ዜናዊ በዚያ በነበረበት ቦታ ላይ እንደተደገመባት ድመት አንገቱን ሰብሮ በዝምታ ወጣቱ ጋዜጠኛ፤ መለስ ዜናዊ ዲክታተር ነው ሲል ሰማው!  እስክንድር ነጋ ይፈታ! የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ! አንተ ዲክታተር ነህ መለስ! በማለት አበበ የተቃውሞ ጥሪውን አሰማ፡፡ አንተ በሰብአዊ ፍጡሮች ላይ ወንጀል ፈጽመሃል፤ ያለ ነጻነት ምግብ ዋጋ ቢስ ነው፤ የፖለቲካ እስረኞችን ልቀቅ! ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት ያስፈልገናል! አለው፡፡ ለአሜሪካን ሕብረተሰብ የ‹‹ሄክለር ቬቶ›› በእጅጉ ክብር የሚያስገኝ መብት ነው፡፡ ሃሳቡ በጣም ቀላል ነው፡፡ምንግዜም መንግስታት ናቸው በሃሳባቸው የማይስማሙትንና ተቃዋሚዎቻቸውን ዝም ለማሰኘት ማፈኛ የሚያበጁ፡፡ ‹‹በሄክለር ቬቶ›› ደግሞ ግለሰቦች ጉልበተኛንና መንገስትን ዝም ጸጥ ማሰኘት ይችላሉ፡፡ ጠረጴዛው የግልብጥ ሆነ፡፡ መለስ ዜናዊ በአበበ ገላው ተለጉሞ ጸጥ እንዲል ተደረገ፡፡ አበበ ድሕረ  ገጽ መጠርያ ስሙ አዲስ ድምጽ ትርጉሙን በአግባቡ  አሳወቀበት ‹‹ድምጻቸው የታፈነባቸው ድምጽ››::

በጁን 2012 በሙስሊሙና በክርስቲያኑ የሃይሞነት መሪዎች ሊከፋፍሏቸው ባለሙት ላይ ባሳዩት ሕብረት ተገርሜ ነበር፡፡ በቶሮንቶ በስደት ላይ የሚገኙት፤ታዋቂው የሙስሊሙ እምነት ተከታዮች መሪ፤ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት የሚሆን መልዕክት አስተላለፉ፡፡‹‹ እንደምታውቁት ኢትዮጵያ ብዙ እምነቶች የሚከበሩባት ሃገር ናት፡፡ኢትዮጵያ ፣ሙሊሙና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ክርስቲያኖች በፍቅር ተከባብረው የኖሩባት ሃገር ለመሆኗ ታሪክ ይመሰክራል፡፡ አሁን እንኳነ 50ና 60 ዓመታት ጊዜ ውስጥ በኛው ዘመን፤አንዳችም ሁከትና አለመግባባት በመሃላቸው አይተን አናውቅም፡፡ ማንኛውንም ነገር የምናገኘው ሃገር ሲኖረን ነው፡፡ ሃይመኖት የግል ምርጫ ነው፡፡ ሃገር ደግሞ የጋራችን ነው:: ሃገር ከሌለ ሃይማኖትም አይኖርም፡፡……..እነሱ…ገዢዎቹ የገሃሪቱን መሬት ለውጭ ሰዎች ለባዕዳን እየሸጡት ነው፡፡ ተራፊውን ለም መሬትም ለራሳቸው ይዘውታል፡፡ ከሽያጩም የተገኘው ገንዘብ በሃገራችን አይቀመጥም፤ በግል ኪሳቸውና በሌላም ቦታ ባላቸው ኪሳቸው ነው፡፡ለመሆኑ አሁን የተረፈ ኢትዮጵያዊ ትውልድ አለ? በዩኒቬርሲቲ ለመማር የሚመዘገቡትም ቢሆኑ ሞራላቸው በተስፋ ማጣት ተዳክሟል፤በጫት ተለክፏል፤በሲጋራ ሱስ ተበክለዋል፤፡ ገዢው መንግስት ትውልዱን አጥፍተውታል፡፡

በጁላይ 2012 የፕሬዜዳንት ማንዴላን 94ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን በግሌ የአከባበር ስርአት አድርጌ ነበር፡፡ በጤንነትና በደስታ ረጂም ተጨማሪ ዓመታት እመኝላቸዋለሁ፡፡ ማዲባ ልክ እንደጋንዲ ለኔ ዋነኛ መኩሪያ የመንፈሴ አነሳሥ ናቸው፡፡ ማዲባና ጋንዲ ካለአንዳች ፍርሃት ዕውነትን ለባለስልጣናት ሲያውጁ ነበር፡፡ ለማዲባ፤ ጋንዲ፤ ማርቲን ሉተር ኪነግ: እውነተኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች፤ የፖለቲካ ፍላጎት ጨርሶ የሌለበት ነው:: የሰብአዊ መብት ፖለቲካ የሰብአዊ ክብር ነው እንጂ የፖለቲካ ዘይቤ፤የፖለቲካ መጎዳኘትም፤አለያም የፖለቲካ ስልጣን ፍቅር አይደለም፡፡ ቁርጠኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጠበቃ፤ለተሸለ ተስፋና ሕልም እውነታ የቆመ ነው፡፡እኔ ለብዙ ዓመታት በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉዳይና በፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ላይ በርካታ መሟገቻ ጦማሮች አቅርቤያለሁ:: ይህ ጥረቴ ደግሞ አፋጣኝ ፖለቲካዊ ለውጥ ወይም አፋጣኝ መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚያስገኙ እገምተለሁ፡፡ ይህንንም ለረጂም ጊዜ በማድረግ የቆየሁበት ሰበብ፤ስለሰብአዊ መብት መሟገት፤ መከራከር፤ ጥብቅና መቆም የገዢዎችን ድክመት ይፋ ማውጣት ልክ ስለሆነና ጥሩና የሞርል ጉዳይም ስለሆነ ነው፡፡

በኦገስት 2012 ይፋ ባልሆነና ባልታወቀ ሕመም በሞት ለተለየን መለስ ዜናዊ ስንብት አደረኩ፡፡ ስንብት ለመፃፍ በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ ለሁለት መቶ ሰባ አምስት ሳምንታት፤አንድም ሳምንት ሳይታለፍ፤ለሁለት አሰርት ዓመታት ኢትዮጵያን ሲገዛ በነበረው ሰው ላይ ያደረሰውን በደልና የፈጸመውን ግፍ በተመለከተ በማጋለጥ በርካታ ጦማሮች አቅርቤያለሁ፡፡ በ2005 ያ ሁሉ የዜጎች ጭፍጨፋ ባይፈጸምና 200 ንጹሃን ዜጎች በጠራራ ጠሃይ በጎዳና ላይ ለሞት ባይዳረጉ፤ ከ800 በላይ ቁስለኛ ባይደረጉ፤መለስ ዜናዊንና እኔን የሚያገናኘን ጉዳይ አይኖረም ነበር::  ዕጣ ፈንታ መለስ በኢትዮጵያ ውስጥ ታሪካዊ ሚና እንዲጫወት መርጦት ነበር፡፡ ለ17 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ዲክቴተር ሆኖ ሲገዛ የነበረ ውን ወታደራዊ ጁንታ አሸንፎ ከገቡት የቡድኑ መሪዎች አንዱ ነበር፡፡ በድል ወቅት መለስ ስለ ዴሞክራሲያዊ ተግባራዊነት ምሎ ተገዝቶ፤ ልማትን ለማፋጠንምና ሃገርን ለመገንባት ቃሉን ሰጥቶ ነበር፡፡ ግና ዓመታቱ እየጨመሩና እያለፉ ሲሄዱ ቁጥር መለስ ጨቋኝ እየሆነ፤ትዕግስቱ ቅጥ እያጣ፤ አምባገነናዊ ትምከተኛ እየሆነ፤ከተካው ገዢ የበለጠ ጨካኝና ጨቁአኝ እየሆነ መጣ፡፡ በመጨረሻዎቹ ዘመኑ ላይ ብዙ የደህንነት አባላት ካድሬዎች የሚታገዝ የፖለስ ስርአተ መንግስት ፈጠረ፡፡ ዜጎች እንዳይነቃነቁና በነጻ እንዳያስቡ ቁጥጥሩን አጠናከረ፡፡ የሲቪሉን ማህበረሰብ ተቋማትንና የነጻውን ፕሬስ አባላት መወንጀል ያዘ፡፡ በሃገሪቱ የሩቅ ገጠር ሳይቀር ዘልቀው በመግባት ሕዘቡ ላይ  የግፍ ጫናቸውን አራገፉበት፡፡ ከ21 ዓመታት በላይ መለስ ስልጣኑን የሙጢኝ ብሎ ከጫካው ይዞት የመጣውን የፍትሕን ሰይፍ በግሉና ለራሱ ብቻ ጨብጦ፤ለመበታተኛነት እያዋለው፤ ሃሳቡን የሚሞግቱትንና ተቃዋሚዎችን በማስፈራራትና በደጋፊዎቻቸው ላይ ውንጀላና መጉላላትን እያካሄደ ፍጹም አምባገነናዊ በመሆነ ኖረ፡፡ ስልጣንን ከምንም በላይ አድርጎ በማየት ዕድል ሰጥቶት የነበረውን ቀጠሮ ስቶ በኢትዮጵያ አቻ የሌለው መሪ ሊባል የሚችልበትን ቀጠሮ አፋለሰ፡፡

በሴፕቴምበር 2012 የፕሬዜዳንት ኦባማን ዳግም ምርጫ ለምን እንደደገፍኩት አስረዳሁ፡፡ በመጀመርያ የምርጫ ዐመታቸው በአፍሪክ ውስጥ ስለነበራቸው አመለካከትና እንቅስቃሴ የሰብአዊ መብት መደፈር ቅሬታ ቢኖረኝም፤የፕሬዜዳንቱን ድጋሚ ምርጫ የመደገፌን መነሾ በሚገባ ገልጫለሁ፡፡ ፕሬዜዳንት ኦባማ በገቡት ቃል መሰረት ለአፍሪካ መልካም አስተዳደር የሰብአዊ መብት መከበርን፤ ዴሞክራሲያዊ ሁኔታን አስገኝተዋል? በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት መከበርን አረጋግጠዋል? በጭራሽ! ፕሬዜዳንት ኦባማ በአክራ ጋና በገቡት ቃል መሰረት ምንም ባለማድረጋቸውና ቃላቸውን ባለመጠበቃቸው ኢትዮጵያዊያን አሜርካዊያን ቅር ተሰኝተዋል:: አስተዳደራቸውስ በኢትዮጵያ ላለው ዲክታተራዊ ገዢዎች ስለሚያደርገው ድጋፍስ፤ አዎን እናስታውሳለን ፕሬዜዳንት ኦባማ ያን የመሰለ ንግግር በማድረግ በአፍሪካ ውስጥ ጠንካራና ጤናማ አስተዳደር እንደሚያስፈልግ አድርገው እንደነበር፡፡ ሁላችንም ይህን አስመልክተው ምን እንዳሉ የምናስታውሰው ነው፡፡ ‹‹አፍሪካ ጡንቻማ መሪዎች አይደሉም የሚያስፈልጓት፤ የፈረጠመና መልካም አስተዳደራዊ ተቋም እንጂ›› ‹‹ልማት መሰረቱ መልካም አስተዳደር ነው›› ገዢዎች ኤኮኖሚውን የሚበዘብዙት ሃገር ጨርሶ ሊለማ አይችልም›› እነዚህን ቃላቶች ለይስሙላ ያሉዋቸው ናቸው ወይስ ከምር አምነውባቸው? ዕውነቱ መውጣት አለበት፤ ፕሬዜዳንቱ ያደረጉት አለያም ያላደረጉት መልካም አስተዳደርን፤ዴሞክራሲያዊ ስርአትን፤የሰብአዊ መብት መከበርን በኢትዮጵያ አለማስገኘቱ፤ እኛ እራሳችን ባለጉዳዮቹ በርካታ ቁጥር ያለን ኢትዮጵያዊያን አሜሪካውያን ያደረግነው አለያም ያላደረግነው ጋር የተለያየ አይደለም፡፡ ይሄ ነው የሚጎመዝዘው እውነትና መቀበልና ማመን ያለብን፡፡

በኦክቶበር 2012 ስለሴቶችና ጡት ካንሰር ጥንቃቄ በኢትዮጵያ አንድ ጦማር አቅርቤ ነበር፡፡ በሃገር ውስጥም ሆነ በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊያን መሃል ስለ አንዳንድ በሽታዎች ሚስጥራዊነት ጎጂ ባሕል አለን፡፡ ሁለቱ በድብቅ የተከተቱ በሽታዎች ካንሰርና ኤች አይ ቪ ኤይድስ ናቸው፡፡ባህሉም በሽታዎቹን እስከመጨረሻው ድረስ: ከሞትም በኋላ ደመደብቅ ነው፡፡ ይህን አስከፊና አሳዛኝ ባህል በቅርቡ በመለስ ዜናዊ ሞት መስክረነዋል፡፡ የመለስ በሽታና የሞቱ መንስኤ ሚስጥራዊነቱ በጥብቅ የሚጠበቅ የሃገር ሚስጢር ሆኗል፡፡ በስፋት እንደሚታመነው የሞተው በአእምሮ ካንሰር ነው ይባላል፡፡ ይህ በሚስጢር የመያዝ ባህላችን በርካታ ኢትዮጵያዊያኖችን ለሕልፈተ ሞት ዳርጓል፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካን ሃገር በጉልህ የሚታወቅና የታይ የሕመም መደበቅ ባህላችን በርካታ ወገኖቻችንን ለሞት ዳርጓል፤ በዚህም ሳቢያ ብዙዎች ቅድመ ምርመራ በማድረግ በጊዜው ሊደርሱበት የሚችሉትን በሽታቸውን በሚስጢር በመያዝና ቅድመ ምርመራውም የሚያስከትለውን ውጤት ለማወቅ ካለመፈለግና በመፈራት በርካቶች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ ካንሰርን በተመለከተ ሚስጥር ማድረግን ቅድመ ምርመራን አለማድረግ በራስ ላይ የሞት ደረሰኝ እንደመቁረጥ ያለ ነው፡፡

በኖቬምበር 2012 ማስታወሻዬ፡፡ በጁን 6-8 እና በኖቬምበር 1-4 በመለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትእዛዝና ቁጥጥር በዚያው ዓመት በሜይ የተካሄደውን ፓርላማዊ ምርጫ አስመልክቶ መብትና ሕገመንግስት ይከበርልን በማለት ባዶ እጃቸውን አደባባይ የወጡትን ንጹሃን ዜጎች ጭፍጨፋና ግፋዊ ግድያ አስታወስኩ፡፡ ሕጋዊ ሆኖ የተመረጠው አጣሪ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው ዘገባ ባቀረበው መሰረት ከሰላማዊ ሰልፈኞቹ መሃል የመንግስት ሚዲያ እንዳለው አንድም ሰው ጠመንጃም/ሽጉጥ አለያም የእጅ ቦንብ የያዘ አልነበረም፡፡ በመንግስት ወታደሮችና የደህንነት ሰዎች የተተኮሱት ጥይቶች ሰልፈኛውን ለመበተን ተብለው የታለሙ ሳይሆኑ ደረትና ጭንቅላት ላይ ለመግደል ተብለው የተተኮሱ ነበሩ፡፡ ‹‹በወቅቱ የ29 ዓመቱን ኢትዮጵያዊ መምህርና የሰብአዊ መብት ተሟጋችና በደቡብ ኢትዮጵያ በ11/11/11 እራሱን በእሳት አቃጥሎ የተሰዋውን የዳውሮ ዞን ነዋሪውን የኔሰው ገብሬንም አስታውሻለሁ፡፡ የኔ ሰው በደረሰበት ቃጠሎ ከሶስት ቀናት በኋላ በሆስፒታል ሕይወቱ አልፏል፡፡ በስብሰባው አዳራሽ በራፍ ላይ ለነበሩትም ያስተላለፈው መልዕክት ‹‹መልካም አስተዳደርና ፍትሕ በሌለበት ሃገር፤ ሰብአዊ መብት በማይከበርበት ሃገር፤ እነዚህ ወጣቶች ነጻ እንዲሆኑ እኔ እራሴን አቃጥላለሁ›› ነበር፡፡

በዲሴምበር 2012 የሱዛን ራይስን የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሹመትን በጥብቅ ተቃዉሜ ነበር፡፡ የወቅቱ የአሜሪካ የተባበሩት መንግስታት አምባሳደር፤ ከዘመነኞቹ የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ጋር በሚፈጥሙት ግፍና በደል ሙዚቃ አብራቸው እስክስታዋን ሱዛን ራይስ ታቀልጠው ነበር፡፡ በኤፕሪል 6 በሩዋንዳ ተቀስቅሶ ያለውንና በሚሊሺያዎች የተነሳሳውን ኢንተርሃምዌ: ራይስና ሌሎችም የአሜሪካን ባለስልጣናት አስቀድመው አውቀውት ነበር፡፡ በሩዋንዳ ከሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ቢሮ ስለ ጉዳዩ የእለት ተእለት መግለጫ ይደርሳቸው ነበር፡፡ በዚህም ባለስልጣኖቹ የዘር ማጥፋት ሂደት መጸነሱን አውቀውታል፡፡ በአዲስ አበባ በሴፕቴምበር 2 እና በኒውዮርክ በተካሄደው የመለስ ዜናዊ ሞት መታሰቢያ ስንብት ያቀረበችው  ከንቱ ውደሴ በእጅጉ አሳፋሪና ከአንድ የመንግስት ተወካይ ከፍተኛ ባለስልጣን የማይጠበቅ ነበር፡፡ ራይስ በመለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትእዛዝ ለሞት የተዳረጉትን ንጹሃን ዜጎች ከምንም አልቆጠረቻቸውም፡፡ በመለስ ትእዛዝ በወህኒ ሃሳባቸውን ስለገለጹና ሕዝብ ማወቅ ያለበትን ስላሳወቁ፤ የመንግስትን ሕጸጽ ይፋ ስላወጡ ብቻ ሕገመንግስታዊና ሰብአዊ መብታቸው ተገፎ ለወህኒ የተዳረጉትን ሁሉ ችላ ከማለት ባለፈ ትታቸዋለች፡፡ራይስ በሩዋንዳ የተፈጸመውን ግድያና ጭፍጨፋ ሆን ብላ ላለማየት አሁንም ካለፈ በኋላ ላለማስታወስ አይኗን ጨፍናለች፡፡ በኢትዮጵያም የተካሄደውንና እሁንም በመካሄድ ላይ ያለውን ጭፍጨፋ ግፍና በደል ግድያ እስራት እያወቀችና እየተረዳች አይኔን ግንባር ያድርገው ብላ ክዳለች፡፡ አሜሪካ ‹‹እያየሁ አላየሁም;; ‹‹እየሰማሁ አልሰማሁም›› ‹‹ብናገርም አልተነፈስኩም›› የሚል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አያስፈልጋትም፡፡ አሜሪካ የሚያስፈልጋት የሃገር እስተዳዳር፤ በሰብአዊ መብትና በመንግስት ሕገወጥነት መሃል ያለውን ልዩነት የሚመለከትና የሚያውቅ የዉጭ ጉዳይ አስተዳዳሪ ነው የሚያስፈልጋት፡፡

እንጠራራ! ለሁሉም ሰብአዊ ፍጡራን ሰላምና ደህንነት በ2013፡፡ ሁላችንም ስለሰብአዊ መብት መከበርና የመንግስታትን እኩይ ተግባር በማጋለጥ ረገድ አብረን እንንቀሳቀስ!

ፕሮፌስር ዓለማየሁ ገብረማርያም በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሳን በርናርዲኆ የፖሊቲካ ሳይንስ መምሀርና የህግ ጠበቃ ናችው።

*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):  http://open.salon.com/blog/almariam/2012/12/29/ring_in_redress_to_all_humankind

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

ECADF.COM

ሦስቱ ባዶ ወንበሮች

ወንበር እና ዙፋን ብዙ መገለጫ አለው። ወንበር ሲባል ሁላችን ራሳችንን የምናሳርፍበት ማንኛውም መቀመጫ ማለት መሆኑ እንዳለ ሆኖ “ወንበር” ብዙ አንድምታ እንዳለው እናውቃለን።

ለምሳሌ ፍርድ ቤት ገብተን “የግራ ወንበር፤ የቀኝ ወንበር” ሲባል ብንሰማ ትርጉሙ “የግራ ዳኛ፣ የቀኝ ዳኛ” መሆኑ ይከሰትልናል። ምናልባት ወደ አብነት ት/ቤት (ቆሎ ት/ቤት) ጎራ ብለን “ወንበር ተዘርግቷል፤ ወንበር ታጥፏል” ሲባል ብንሰማ “ትምህርት ተጀምሯል፣ ትምህርቱ ተጠናቋል” ማለት ነው። “እገሌ ወንበር ተከለ” ከተባለ ደግሞ “መምህር ሆነ፣ አንድ የትምህርት ዘረፍ ለማስተማር ጀመረ” ማለት ይሆናል። ሥልጣን ባለበት አካባቢ “እገሌ የእገሌን ወንበር ይፈልጋል” ከተባለ …. ያው … ሥልጣንም ከሆነች፣ ኃላፊነትም ከሆነች … ሊቀማ የተዘጋጀ አለ ማለት ነው።

አንድ ታሪክ

እዚህ በአሜሪካ የምርጫ ፉክክር ሰሞን ሁለት ታላላቅ የፓርቲዎቹ ጉባዔያት ተካሂደው ነበር። የሁለቱም ፓርቲዎች ዓመታዊና ፕሬዚዳንታዊ እጩዎቻቸውን የሚያጸድቁባቸው ወሳኝ Ethiopian PM Hailemariam Desalegn and the empty chairጉባዔዎች። ታዲያ፣ ከሁለቱ በአንዱ፣ በሪፐብሊካን ዓመታዊ ጉባዔ ላይ “ራምኒን ለማስተዋወቅ፣ ተመራጭ ለማድረግ” የቀረቡት ዝነኛው የሆሊውድ ኮከብክሊንት ኢስትዉድ (Clint Eastwood) ንግግራቸውን ሆሊዉዳዊ ድራማ አስመስለው ቀርበዋል። ሰውየው በንግግራቸው ጣልቃ፣ ከፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጋር ክርክር ቢጤ ያደረጉበት ትዕይንት አስደማሚ ነው። በርግጥ ኦባማ በቦታው አልነበሩም። እርሳቸውን እንዲተካ የተደረገው ገጸባሕርይ “ባዶ ወንበር” ነበር። ኢስትዉድ ሲያወሩ ወደ ወንበሩ እየዞሩ “እንደ ሰው” እያናገሩት ነበር። እናም በትዕይንቱ የተሳለቁ ሰዎች “Obamachair” የሚል ቃል ፈጥረው (ObamaCare የሚለውን ለውጠው) ሲዘባበቱባቸው ሰንብተዋል። “ካረጁ አይበጁ” እያሉም አሹፈውባቸዋል። ወደ ኢንተርኔት ገባ ብላችሁ “ኦባማቼር” ብትሉ ጉዱን ታዩታላችሁ።

ሌላ ታሪክ

እንዲህ በዐቢይና ታላቅ ጉባኤ ላይ በክብር የሚቀመጥ “ባዶ ወንበር” የማውቀው በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ ነው። ጉባዔው በፓትርያርኩ መሪነት የሚስተናበር ቢሆንም መሪውና ወሳኙ መንፈስ ቅዱስ ነው ከሚለው አስተምሮ በመነሣት በጉባዔው ውስጥ በመጎናጸፊያ የከበረ አንድ ባዶ “ዙፋን” እንደሚቀመጥ አባቶች ይናገራሉ። ወንበሩ ከርዕሰ ጉባኤው፣ ከጉባዔው ሊቀ መንበር፣ ከፓትርያርኩ ጀርባ ይቀመጣል። ማንም ሰው አይቀመጥበትም። መንፈስ ቅዱስ የጉባዔው አካልና መሪ መሆኑን ያጠይቃል። “ባዶው ወንበር” ተምሳሌታዊ ብቻ ሳይሆን አማናዊ ትርጉም ያለው ሐሳብ ነው። በሌሎቹ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትም ይሁን ሲኖዶሳውያን በሆኑ ካቶሊክን በመሳሰሉ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህ ትውፊት ይኑር አይኑር አላወቅኹም።

የአቶ ኢስትዉድ ባዶ ወንበር እና ሃይማኖታዊ ትርጓሜ ያለው የቤተ ክርስቲያን “ባዶ ዙፋን” በይዘትም፣ በተምሳሌትም ይለያያሉ። የመጀመሪያው “ወንበር” ለጊዜው በዚያ ቦታ ያልተገኘ ሰውን ወክሎ እንዲጫወት የተደረገ ገጸ ባሕርይ ሲሆን ሁለተኛው ግን በርግጥም “እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በመካከላችን አለ፤ ይመራናል” ብሎ በማመን የሚደረግ ነው።

ሦስተኛ ታሪክ

ታዲያ የባዶ ወንበር ነገር ለሦስተኛ ጊዜ ራሴን “ቂው” ያደረገኝ አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ም/ቤት ተገኝተው መልስ ሲሰጡ የተቀመጡበትን ቦታ ባየኹ ጊዜ ነው። “ምናልባት አቀራረጹ ይሆን?” ብዬ አተኩሬ ለማየት ሞከርኩ። በርግጥም አቶ ኃ/ማርያም የተቀመጡበት ቦታ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር በሚቀመጡበት ቦታ አልነበረም። የአቶ መለስ “ወንበር” (ሁለተኛው ተርታ ቁጥር አንድ) ባዶዋን ቁጭ ብላለች። ደርሶ ተቺ፣ ደርሶ ነቃፊ ላለመሆን ለራሴ ሁሉንም ሎጂካዊ አመክንዮዎች ለማየት ሞከርኩ። በዚህም ብል በዚያ ያቺ “ወንበር” ባዶ የሆነችበት ምክንያት ግልጽ አልሆነልኝም። መቸም እንደ አቶ ኢስትዉድም፣ እንደ ቅ/ሲኖዶሱም እንዳልሆነ እናውቀዋለን። ታዲያ ለምን ባዶ አደረጓት?

በየትኛውም የሥልጣን ወንበር ላይ ለሚቀመጥ ሰው፣ እርሱ በሚያልፍበት ጊዜ ተተኪው በርሱ ቦታ እንደሚቀመጥ፣ እንኳን ዛሬ “ዲሞክራሲያውያን” ነን ብለን ቀርቶ በነገሥታቱም የተለመደ ነው። “ተቀመጥ በወንበሬ፣ ተናገር በከንፈሬ” እንዲል “መተካካቱ” ሲመጣ ከነሙሉ ክብሩና ግዴታው ሁሉ እንጂ በግማሹ አይደለም። ጠቅላይ ሚኒስትር የመተካት ልምድ የሌላት አገራችን እርሟን ከዚያ ሰዓት ስትደርስ የትኛውን ጥላ የትኛውን እንደምታንጠለጥል የቸገራት ይመስላል። በሌሎች ጉዳዮች ሲሆን “በሕንድ እንዲህ ሲደርግ ዓይተን ነው፣ ጎረቤታችን ኬኒያ እንኳን እንዲህ ነው የምታደርገው፣ ብዙ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ስዊዘርላንድ እንዲህ ናት” እንደሚባለው በዚህ ጉዳይ ማጣቀሻ ለመፈለግ የተሞከረ አይመስልም።

በመጀመሪያ። የጠ/ሚኒስትሩ ቤተሰቦች ቤተ መንግሥቱን ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ላለማስረከብ “ግብግብ” መግጠማቸውን “ጠላት የሚባለው ዳያስጶራው” ብቻ ሳይሆን “የታመኑ የውጪ አገር ፈረንጅ ጋዜጠኞች” ሳይቀሩ ሲተቹ ሰንብተዋል። እንደ መንግሥት ሳይሆን እንደ ግለሰብ ሳስበው እንኳን 20 ዓመት 2 ዓመት ከምኖርበት አፓርታማ ስቀይር እንዴት እንደሚከብድ አውቀዋለኹ። “ይኼ ሁሉ ዕቃ መቼ የሰበሰብኩት ነው?” ማለት የተለመደ ነው “ልሸክፍህ” ሲሉት። የሆነው ሆኖ የቤት ርክክቡ “ሰላማዊ” በሆነ መንገድ መጠናቀቁ ተገቢም፣ የሚጠበቅም ነው።

ቤቱ ይለቀቅ እንጂ፣ እንደማንኛውም የመሪ ቤት “የሚነቃነቁ” እና “የማይነቃነቁ” ነገሮች መኖራቸው ይታወቃል። መተካካት ስለተባለ ብቻ ኋላ የመጣው የፊተኛውን ጫማና ኮት አድርግ አይባልም። የፊተኛው ሲጠቀምባቸው ከነበሩት ዕቃዎች መካከል ለመታሰቢያነት በሙዚየም ሊቀመጡ የሚገባቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። አገሪቱን 20 ዓመት ያስተዳደሩት ጠ/ሚኒስትር (እንደተባለው በስማቸው ሙዚየም የሚቆም ከሆነ) ይጠቀሙባቸው የነበሩት የቢሮ ዕቃዎች ወዘተ ወዘተ መሰብሰባቸው አይቀር ይሆናል።

ይሁን እንጂ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር መንግሥታዊ ኃላፊነትን በሚረከቡበት ወቅት ከነሙሉ ክብሩ እንጂ በጎዶሎነት መሆን አይገባውም። በፓርቲ ሥርዓታቸው ለቀድሞ የፓርቲ ሊቀመንበራቸው ክብር ሲሉ የፓርቲያቸውን “ወንበር ባዶ” ማድረግ ይችላሉ። የመንግሥት ሥልጣን ግን አገራዊ እንደመሆኑ ለግለሰቡ የሚሰጠው ክብር የሰውየውን ማንነት ከግምት ውስጥ ሳያስገባ መሆን አለበት።

እውነቱን ለመናገር የፓርላማው ባዶ ወንበር ከቀጥተኛ ትርጉሙ ይልቅ ተምሳሌታዊነቱ (Symbolism) የበለጠ ትርጉም ይሰጠኛል። አቶ ኃ/ማርያም በመለስ ወንበር አለመቀመጣቸው ብቻ ሳይሆን ያልተረከቡት ሌላም ብዙ ነገር እንዳለ ማሳያ ይመስላል። ቢሯቸውስ “ግዴለም የድሮው ቢሮዬ ሆኜ እሠራለዅ” ወይም “አንዲት ወንበር በጎን በኩል አስቀምጡልኝ” ብለው በደባልነት ገብተው ይሆን?

“ከልት”/Cult መፍጠር

ሳስበው ሳስበው መለስን “ኢትዮጵያዊው ኪም ኤል ሱንግ” ለማድረግ እየተሠራ ይመስለኛል። ኪም ኤል-ሱንግ እ.ኤአ. ከ1948-1994 ድረስ የአገሪቱን አመራር ጨብጠው የዘለቁ መሪ ነበሩ። ከ1948-1972 ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ከ1972-94 ደግሞ ፕሬዚዳንት ነበሩ። እርሳቸው በሥልጣን ላይ ብቻቸውን በተቀመጡባቸው ዓመታት አሜሪካ 10 ፕሬዚዳንቶችን፣ እንግሊዝ 14 ጠ/ሚኒስትሮችን፣ ሶቪየት ኅብረት ሰባት መሪዎችን፣ ጃፓን 21 ጠቅ/ሚኒስትሮችን፣ ጎረቤቷ ደ/ኮሪያ 6 ፕሬዚዳንቶችን አስተናግደዋል።

ሞት አይቀርምና ሲሞቱ ልጃቸውን ለልጃቸው አሸጋግረው አልፈዋል። እርሳቸው በበኩላቸው “ታላቁ መሪ”፤”The Great Leader” (በኮሪያኛ Suryong) የሚል ቅጽል ተቀጽሎላቸዋል። ከዚያም ባሻገር በሕገ መንግሥት ደረጃ የተቀመጠ የአገሪቱ “ዘላለማዊ ፕሬዚዳንት” ተብለው ተሰይመዋል። የልደት ቀናቸውም ከዓመታዊ አገሪቱ በዓላት እንደ አንዱ በይፋ እንዲከበር ተሰይሟል።

በየአደባባዩ፣ በየታላላቅ ሕንጻዎች፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ በምክር ቤት ወዘተ ወዘተ ፎቶግራፋቸውን ከመደበኛ ይዘት እጅግ ከፍ ባለ መጠን እያሳተሙ መስቀል የገጽ ግንባታ ሳይሆን “ከልት”/Cult መፍጠር ነው። አሁን ባለው ይዘት መለስ ዜናዊን ኪም ኤል-ሱንግ ማድረግ ለገዢው ፓርቲም ሆነ ለቤተሰባቸው ክብር አይሆንም።

“የመለስ ራእይ” ከሚለው ጀርባም የሚኖረው ይኸው “ዘላለማዊነት” የተመኙለት መሪ እና ኢትዮጵያዊ-ኪም አል ሱንግ የመፍጠር ሐሳብ ነው። ፓርቲው “ራእዩ” በትክክል የገባቸው እና ያልገባቸው፣ ራእዩን የተቀበሉና ያልተቀበሉ፣ የራእዩ ተቃዋሚዎችና ደጋፊዎች በሚል ፍረጃ ውስጥ ለመግባት አፋፍ ላይ ይመስላል። ነገ ማንም ሰው ያለምንም አመክንዮ “ራእዩን ባለመደገፉ ብቻ” ወንጀለኛ ሊባል ይችላል። ኢሕአዴግ የታገለው የፓርቲ ዓላማ ነበረው። መለስም ያንን አይተው ነው የፓርቲው አባል የሆኑት። አሁን ግን መመሪያቸው የመለስ ራእይን መቀበል እና አለመቀበል “ማስቀጠልና አለማስቀጠል” ሆነ ማለት ነው?

በነገራችን ላይ “ማስቀጠል” የሚለው ቃል ሁሌም ያስፈግገኛል። ቋንቋ ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ይሞታል በሚለው የሥነ-ቋንቋ ሀ-ሁ እንዳምን ከሚያደርጉኝ ነገሮች አንዱ እንዲህ ያሉት ቃላት ናቸው። “ማስቀጠል” የሚል ግስ ተፈጠረ ማለት ነው? ለነገሩ ሁሉም “አስቀጣይ” ከሆነ ማን “ቀጣይ” ሊሆን ነው? ቃሉን “መገደብ” በሚል ብትተረጉሙት ሁሉም “አስገዳቢ” ከሆነ ማን “ገዳቢ” ሊሆን ነው። ሁሉ ከሆነ ቃልቻ ማን ይሸከማል ስልቻ አለ ያገራችን ሰው።

ይቆየን – ያቆየን።

ECADF.COM

ከአገር አቀፍ ንግግር ወደ አገር አቀፍ ተግባር

በሀብተጊዮርጊስ ለገሰ – ኖርዌይ ኦስሎ

“ሁሉም የሚችለዉን ያህል ጠጠር  ይወርዉር” ይህ መልዕክት የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይል ምስረታን በተመለከተ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከእሳት ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስGinbot 7 Popular Force - GPF formed ወቅት ያስተላለፉት ነዉ፣ ፣ በእርግጥ የእሳት ቴሌቪዥን የጋዜጠኛ ሲሳይ ዓላማ ህዝባዊ ሀይሉን በተመለከተ በተለያዩ  ግለሰቦች ለሚነሱት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ነበር፣ ፣

የህዝባዊ ሀይሉ መሪ ማነዉ? ህዝባዊ ሀይሉ የየትኛዉ ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ ነዉ? የዉጊያዉን እንቅስቃሴ የሚያደርገዉ የት አካባቢ ነዉ? የሚሉና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ከአንዳንድ ግለሰቦች የሚነሱ ቢሆንም የወታደራዊ ስትራቴጂ ጥያቄዎች በመሆናቸዉ ወቅታዊ ጥያቄዎች አይደሉም፣ ከዶ/ር ብርሀኑም አገላለጽ የምንረዳዉ ወቅታዊ ጥያቄ መሆን ያለበት የህዝባዊ ሀይሉ ዓላማ ምንድነዉ? ትግሉን  ያነጣጠረዉ በማን ላይ ነዉ? የሚሉት ናቸዉ፣ ፣ከመልስም አንጻር መረጋገጥ ያለበት ወያኔ ላይ ያተኮረ ትግል በማድረግ ዘረኛዉን መንግስት በማስወገድ ሉአላዊነቷ የተከበረ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መመስረት ነዉ፣ ፣

በመንደርደሪያነት የተጠቀምኩት የዶ/ር ብርሃኑ መልዕክት አንድ ዓረፍተ ነገር ቢመስልም በዉስጡ ያዘላቸዉ ሀሳቦች ግን ብዙ ናቸዉ፣ ፣ይህ መልዕክት ዓላማን መሰረት ያደረገ ትግል እንድናደርግ የሚያሳስበን ነዉ፣ ፣ትግላችን ከአንድ ብሄር በተዉጣጣ ቡድን የተጫነብንን የዉስጥ የቅኝ አገዛዝ ለማስወገድ የሚደረግ የነጻነት ትግል በመሆኑ ያለንን መለስተኛ የሀሳብ ልዩነታችንን ነጻ ከወጣን በሗላ በእኩልነት የምንዳኝበትን ስርዐት ፈጥረን ለኢትዮጵያ ህዝብ ማቅረብ ያለብን መሆኑን የሚጠቁም መልክት ነዉ፣ ፣

ቅኝ አገዛዝ(colonialism) በ19ኛዉና በ20ኛዉ ክፍለ ዘመን  የዉጭ ሀይሎች በተለይ አዉሮፓዉያን የሌላን ሀገር ህዝብ በማግለልና የፖለቲካ የበላይነትን በመቆጣጠር ለእናት ሀገራቸዉ የሌላን ሀገር ሀብት መመዝበር ላይ ያተኮረ ፖሊሲ ያራመዱበትን የሚገልጽ ቃል ነዉ፣ ፣በቅርጹ ከቅኝ አገዛዝና ከእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ( Colonialism and Neo-colomialism) የተለየዉና በይዘት አንድ የሆነዉ የዘመኑ የዉስጥ ቅኝ አገዛዝ ( Internal colonialism) በጥልቀት መታየት እንዳለበት በተለያዩ ምሁራን እየተገለጸ ይገኛል፣ ፣

ባሬራ (Barera) የተባሉት ምሁር የዉስጥ ቅኝ አገዛዝን ሲገልጹ ”Internal colonialism is a structured relationship of domination and subordination which are defined along ethnic or racial lines where the relation is established or maintained the interests of all or part of the dominant group in which the dominant and the subordinate populations intermingle.” ይላሉ ፣ ፣

በተጠናከረ መዋቅርና በረቀቀ ስልት  በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ሀብት ከአንድ ዘር የተዉጣጣዉን ቡድን ኪስ እያሳበጠና እያደለበ ስናይ፣ የመከላከያና የደህንነት ሀይሉ ከአንድ ዘር በተዉጣጣ ቡድን ፈላጭና ቆራጭነትን ሲገለጽ፣ የፖለቲካ ሀይሉ በአንድ ዘር የበላይነት ሲመራ፣ ቢሮክራሲዉ በአንድ ዘር ተተብትቦ ሰራተኛዉን መግቢያና መዉጪያ ሲያሳጣዉ ስናይ የባሬራ (Barera) የዉስጥ ቅኝ አገዛዝ(Internal colonialism) አገላለጽ የሀገራችን የዘረኛዉ መንግስት መገለጫ መሆኑን ሳንጠራጠር እንድንቀበል ያስገድደናል;;

ቅኝ አገዛዝና ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የማይለያዩ ሀሳቦች ናቸዉ;; የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ አንድ ሀይል ሌላዉን ትልቅ ሀይል በትንንሽ ክፍሎች በታትኖ እነዚህን ትንንሽ ሀይሎች አንድ በአንድ የመቆጣጠር ስልት ነዉ;; በእርግጥ ትልቁን ሀይል ትንንሽ ቦታዎች መከፋፈል ከባድ በመሆኑ አሸናፊዉ ክፍል ፖለቲካዉን፣ ሚሊታሪና ደህንነቱን፣ እንዲሁም ኢኮኖሚ ዘርፉን መጨበጥና የህዝብ አንድነት እንዳይፈጠር መከላከል የህልዉናዉ መሰረት ነዉ;; በመሆኑም የከፋፍለህ ግዛ መሪዎች በጎሳዎች፣ በብሔሮችና በአጠቃላይ በሕዝቡ መካከል የእርስ በርስ ጥላቻ መርዝ መርጨትና ማራገብ (encouraging blood feuds) የየዕለት ተግባራቸዉ ነዉ;; ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የእያንዳንዱን ጎሳና ብሔረሰብ ስስ ብልትና ደካማ ጎን አጥንቶ ማጋጨትና ማጣላትን ይጠይቃል;;በአገራችንም በትልልቆቹ ብሔረሰቦች በአማራና በኦሮሞ እንዲሁም በተለያዩ ጎሳዎች መካከል የተፈጠረዉ የመረረ ጥላቻና በጠላትነት እንዲተያዩ የማድርግ ሴራ በወያኔ ተግባራዊ የተደረገ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ዉጤት ነዉ;;

ይህ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በዓለማችን በሰፊዉ ስራ ላይ ዉሏል ;; ሮማዎችና እነግሊዞች ግዛታቸዉን ለማስፋትና ለመቆጣጠር ጎሳዎችን እርስ በርስ በማጋጨት ፖሊሲዉን ለሀብት ምዝበራ ተጠቅመዉበታል;;እንግሊዞች ህንድን፣ አንግሎ ኖርማን አየርላነድን ለመቆጣጠር የተጠቀሙበት ዘዴ ነዉ;; በአገራችንም ኢጣሊያን በአምስት ዓመት ቆይታዉ አገሪቷን በቋንቋ ከፋፍሎ ለመግዛት ያደረገዉ ሙከራ የሚረሳ አይደለም;;

በመሆኑም ለ21 ዓመታት የተዘራዉ የጎሰኝነት ወይም የዘረኝነት መርዝ ለነጻነት የሚደረገዉን ትግል ዉስበስብና ከባድ ያደርገዋል;;እዚህ ላይ ተጨምሮ የመቃወም ትርጉምና የተቃዋሚዎች ስራ እርስ በርስ በመብላላት ላይ የተመሰረተ ከሆነ ትግሉን ከማዳከምና የስርአቱን ዕድሜ ከማራዘም ዉጭ የሚፈየደዉ እንደሌሌ በቃለምልልሱ ላይ በጉልህ መገለጹ አግባብ ነዉ;; ሁሉም የአቅሙን ያህል፣ የችሎታዉን ያህል ለትግሉ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ ሲቀርብ ከልባችን ዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ እንዲመጣ እንደምንፈልግና እንደማንፈልግ የሚለይበት በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቶች በጉልህ ተለይተዉ የሚታወቁበት ወቅት ላይ የደረስን መሆኑን ከመልዕክታቸዉ መረዳት ይቻላል;;

የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት አስከፊ የሆነ ጭቆና ስር ወድቋል;;የአንድ አገር ምሶሶዎች ተደርገዉ የሚታዩት ኢኮኖሚ፣ ቢሮክራሲ፣መከላከያ፣ ደህንነትና ፖሊስ ከአንድ ብሔር በተዉጣጣ ቡድን እጅ የተያዘ በመሆኑ አብዛኛዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የበይ ተመልካች  የሆነበት ወቅት ላይ ደርሰናል;;በእሳት ቴሌቪዥን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቡድን አሳይመንት መስራት ጥያቄ እንደሚያስከትል መግለጻቸዉ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚጠቁም ነዉ፡፡ የልቅ-ግብረስጋ ግንኙነት(pornography) ድህረገጾች እየተለቀቁ ስለ አገራችን ችግሮች መረጃ ልናገኝባቸዉ  የምንችልባቸዉን ድህረገጾች ይዘጉበናል በማለት ተማሪዎቹ አሰደምመዉናል;;ይህን ሰምቶ ምን አገባኝ ብሎ መቀመጥ ከህሊና ወቀሳ አያድነንም;;

መረጃን ማራቅ፣ ያለመተማመን ስሜት በእያንዳንዱ ግለሰብ ዉስጥ እንዲፈጠር ማድረግ፣ የርስ በርሰ ጠላትነት ስሜት መፍጠር፣ ሁሉም በአይነቁራኛ እንዲተያይ ማድረግ የዘረኛዉ መንግስት የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማጠናከሪያ ዘዴዎች ናቸዉ;;

ስለዚህ ይህን ፀረ ሕዝብ የሆነ ከፋፋይ ዘረኛ ቡድን ለማስወገድ በሚደረገዉ ትግል ለመሳትፍ አምርረዉ የተነሱት;;አገራዊ አጀንዳ ያላቸዉ እንደ ግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይልና የመሳሰሉ ድርጅቶች ሙሉ ድጋፍ ሊሰጣቸዉ ይገባል;; በተለይ ህዝባዊ ሀይሉ ሀገራዊ አጀንዳ ካላቸዉ ከሌሎች በጎሳ/በብሔር ከተደራጁት ጋር ተባብሮ ለመታገል መወሰኑ በአንዳንድ ግለሰቦች የሚነሳዉን ስጋት ከማስወገዱም በላይ ድሉን የሚያፋጥነዉ በመሆኑ የሚደገፍ አቋም ነዉ;;

በአጠቃላይ ከጠባቂነት ተላቀን የእያንዳንዳችን ሀላፊነት መሆኑን በመረዳት ሁላችንም ለትግሉ የችሎታችንን ያህል ጠጠር በመወረዉር ከአገር አቀፍ ንግግር  ወደ አገር አቀፍ ተግባር  መሸጋገር እንዳለብን የሚጠቁም መለልዕክት የተላለፈ ስለሆነ በአዎንታ መቀበል ይኖርብናል;;

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች !!!

ፀሐፊዉን ለማግኘት ከፈለጉ –

tgiorgis2005@yahoo.com

ECADF.COM

በቡሬ ግንባር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት እርስ በርሱ ተዋጋ

ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጡት በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት እስከ እኩለቀን ዘልቆ እንደነበርና አሁንም ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

የእርስ በርስ ጦርነቱ እንደተጀመረ የአካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ጀመሩ በሚል ቀየውን ለቆ የተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር እየተንቀሳቀሱ ጦርነቱን ለማስቆም ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል።

40 ወታደሮች መሞታቸውን እንዲሁም ከ39 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን ከማንዳ ሆስፒታል የተገኘ መረጃ ያመለካተ ሲሆን፣ ሆስፒታል ሳይደረሱ የሞቱ፣ ወደ መቀሌ ሆስፒታል በሄሊኮፕተር የተወሰዱ ወታደራዊ አዛዦች መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።

ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ 15 ወታደሮች ወዲያውኑ መሞታቸውን ፣ 12ቱ ደግሞ ለሞት ሲያጣጥሩ በአይናቸው ማየታቸውን አንድ ስማቸውም ድምጻቸውም እንዳይተላለፍ የጠየቁ በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰሩ ነርስ ተናግረዋል።

የግጭቱን መንስኤ በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። አንዳንድ ወገኖች ግጭቱ በህወሀት ወታደራዊ ባለስልጣናት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ነው ሲሉ ሌሎች ወገኖች ደግሞ በህወሀት ደጋፊ ወታደሮችና በተቀረው ሰራዊት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነው ይላሉ። ኢሳት የግጭቱን ትክክለኛ ምንጭ ለማወቅ ጥረት እያደረገ ነው።

ማንዳ ከቡሬ ግንባር 21 ኪሎሜትር የሚርቅ ሲሆን፣ ግጭቱ በትክክል የተነሰባት ቦታ አሊ ፉኑ ዳባ እየተባለ በሚጠራው የጎሳ መሪ ስም በተሰየመ አሊ ፉኒ አካባቢ ነው። ግጭቱ በዚሁ ስፍራ ይጀመር እንጅ ወደ አራት አጎራባች አካባቢዎች ተሰራጭቶ እንደነበር ምንጮች አመልከተዋል።

ከትናንት በስቲያ እና ትናንት ውጥረቱ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን፣ ምናልባትም ግጭቱ እንደገና ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት የአካባቢው ሰዎች ቀያቸውን እየለቀቁ ነው።

የቡሬ ግንባር ዋና እዝ መቀሌ የሚገኝ ሲሆን፣ በሰሜን እዝ አዛዥ ጄነራል ሳእረ መኮንን እንደሚመራ ይታወቃል።

ቡሬ ግንባር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከባድመ ቀጥሎ ሀይሉን በብዛት ያሰማራበት ቦታ መሆኑ ይታወቃል። ኢሳት በቅርቡ በሰሜን ግንባር የተመደበን አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል በማናገር በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ችግር መዘገቡ ይታወሳል።

በሌላ ዜና ደግሞ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሰው የአፋር ጋድሌ ሚሊሺያ ሀይል ወጣቶችን ትመለምላላችሁ የተባሉ የሚሊሺያው ወታዳራዊ አዛዥ የሆኑት የኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ 4 የቅርብ ዘመዶች ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መንገሱንና መንግስትም ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ በርካታ ወታደሮችን ማስፈሩን መዘገባችን ይታወሳል።

 

 ESAT News

መንግስት የለም ወይ? መንግስት የለም ወይ? (ህዝብ)

ዘረኛው ህወሃት የኢትዮጵያ መንግስት እኔ  ነኝ ይላል። ህዝቡ ግን መንግስት የለም ወይ እያለ መጠየቁን አላቆመም። ህወሃት የመንግስት ቅርፅና መልክ የሌለው ቡድን ስለሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት አለ ለማለት አይቻልም። ህወሃት መንግስት መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ ብርቱ የሆነ የአቅም ችግር አለበት። ይሄን ደካማነቱን የተመለከተ ህዝብ ነው ድምጹን ከፍ አድርጎ መንግስት የለም ወይ ? መንግስት የለም ወይ? ብሎ የጠየቀው።ህወሃት የመንግስትነት ባህሪይ ቢኖረው ኑሮ ይሄን ድምጽ ማድመጥ በቻለ ነበር። እንዲህ ያለውን ድምጽ አሁን በዚህ ዘመን ያለ ይቅርና በዚያ በጨለማ ዘመን እግዚአብሄር ሾመን የሚሉ ነገስታት እንኳ ቢሆኑ ያደምጡት ነበር።ህወሃት ከጨለማው ዘመን ነግስታት እንኳ የማይሻል እጅግ ኋላ ቀር መሆኑን ከሚያሳዩን ድርጊቶቹ መካከል አንዱ ይሄው የህዝቡን ድምጽ መስማት አለመቻሉ ነው።

አንዳንድ ሰዎች ህወሃት የህዝቡን ድምፅ ለመስማት ፍላጎት እንዳይኖረው ያደረገው ምንድ ነው ብለው ይጠይቃሉ። መልሱ ተፈጥሮው ነው የሚል ነው። የህወሃት ተፈጥሮው የሚገለፀው በትእቢት እና በወንጀል ነው። ትዕቢቱና ሲፈፀመው የኖረው ወንጀሉ ደግሞ ከህዝብ ጋር አብሮ እንዳይኖር አድርገውታል። ህወሃት ራሱን “እኔ አውራ ነኝ ፤እኔ ከሌለው አገሪቷ ትፈርሳለች” እያለ በአደባባይ ሲፎክር መኖሩን እናውቃለን። ”እኔ ከሌለው አገር ትፈርሳለች” የሚለው አባባል አንደኛ የትዕቢቱ ማሳያ ሁለተኛ ደግሞ ለአገሪቷም ሆነ ለህዝቧ ምንም ኃላፊነት እንደማይሰማው የሚያስረግጥ አባባል ነው። በአጠቃላይ ህወሃት ራሱን አለማወቁና ወሰን ያጣው ትዕቢቱ የህዝብን ድምፅ እንዳይሰማ አግደውታል። ከዚህ ትዕቢቱ መላቀቅ ባለመቻሉም የህዝብድ ድምጽ አድምጦ ከህዝብ ጋር የመኖርን ጥበብ ሊያገኛት አልቻለም።

“እኛ አውራዎች ነኝ፤እኛ ከሌለን አገሪቷ ትፈርሳለች” የምትለዋ አባባል ያላዋቂዎች እንቶ ፈንቶ ብትሆንም እንዲህ እንላችኋለን፤

ህወሃቶች እውነት እውነት እንላችኋለን እናንተ ትሄዳላችሁ አገራችንም በሠላም ትኖራለች።የእናንተ አለመኖር አገራችንን አያፈርሳትም። እንዲያውም በተቃራኒው የእናንተ መኖር አገራችንን ከጎሬቤቶቿ ጋናንና ከኬኒያን ከመሳሰሉ አገራት በሁሉም ዘርፍ አንሳ እንድትታይ አደረጋት እንጂ የተሻለች አላደረጋትም።በእናንተ መኖር ምክንያት ዜጎች በተገኘው መንገድ ሁሉ መሰደድን መረጡ እንጂ ተረጋግተው በአገራቸው መኖርን አልመረጡም። ህወሃቶች አሁንም ስሙን እናንተ ባትኖሩ ኑሮ አገራችን ሠላሟ በዝቶ፤ ህዝቡ ተፋቅሮና ተከባብሮ፤ ብሄራዊ ስሜቱ በሚገባው ደረጃ ላይ ሁኖ፤ ሁሉም ኢትዮጵያ በአገሩ እኩል ከህግ በታች ሁኖ የሚኖርባት አገር በሆነች ነበር። ህወሃቶች አሁንም ስሙ የእናንተ መኖር አገሪቷን አፈርሳት እንጂ አልገነባትም።በእናንተ መኖር ምክንያት ህዝቡ “በአገራችን ሠላም አጣን”” ብሎ እንዲማረር ሆነ እንጂ ደስ ብሎት እንዲኖር አልሆነም።

ህወሃቶች የዚያች አገር መንግስት ለመሆን የሞራልም ሆነ የእውቀት ብቃት እንደሌላቸው ባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት በአገራችን ላይ የፈፀሟቸው በደሎች ህያዋን ምስክሮች ናቸው። አዲስ አበባ ውስጥ መንግስት የለም ወይ ? መንግስት የለም ወይ ? የሚለው ጥያቄ የመጠየቁ መነሻም ትግሬን ነፃ አወጣለሁ ብሎ የተነሳው ይሄ ዘረኛ ቡድን ያችን አገር ለመምራት የሚያስችል ስነ-ባህሪይ ማሳየት ባለመቻሉ ነው።ይህ ቡድን ራሱን ከጋረደበት ጥላቻ አላቆ እንደ ሰው ልጅ አስቦ ከሰው ልጆች ጋር አብሮ ለመኖር የሚያስችለውን ባህሪይ በሙሉ መልሶ ላያገኘው አጥቶታል። ይሄ ቡድን የሠላምን ዋጋ አያውቃትም።ይሄ ቡድን ነፃነት ማለት ምን ማለት እንደሆነም ገና አልገባውም።ህወሃት ከሌሎች ጋር አብሮ መኖርንም አያውቅም። ከጎጠኛ አስተሳሰቡ ለመላቀቅም የአዕምሮ ብስለት የለውም። ይህ የጎጠኞች እና የትዕቢተኞች ስብሰብ የሆነው ማፊያ ቡድን ሳይፈለግ ከተቆናጠጠበት የስልጣን ኮርቻ ላይ መውረድ አለበት። ኢትዮጵያን እንዲህ ያሉ ዘረኞችና ወንበዴዎች ሊመሯት አይገባም።

ህወሃት የሚመራት ኢትዮጵያ ህዝቧ ቀንና ማታ የሚያለቅስባት፤ልቅሶውን የሚያደምጥ መንግስት የሌለባት አገር ነች። ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በሃና ማሪያም መንደር ነዋሪ የሆኑ ዜጎች ጥረውና ግረው የሠሩት ቤት ፈርሶ ህፃናት፤ እመጫቶች፤ በእድሜ የገፉ አዛውንት አባቶችና እናቶች ወደ ምትሄዱበት ሂዱ ተብለዋል።የት እንሄዳለን ብለው፤ የአገሪቷን ባንዲራ ይዘው የምንሄድበትን ቦታ ንገሩን ብለው ቢማፀኑም የያዙትን ባንዲራ ተነጥቀውከዚህሂዱየኢትዮጵያህዝብድሮምየሚኖረውመንገድላይነው ተብለው በህወሃት ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች አማካኝነት እንዲባረሩ ተደርጓል።

እናንተ ህወሃቶችና  ከጎናቸው የቆማችሁ ሌሎች ሆይ ነውር ነገር ታውቁ እንደሆነ ያደረጋችሁት እና የተናገራችሁት ነውር ነው።እናንተ ግን ነውር ነገርን ታውቃላችሁ ለማለት በጣም እንቸገራለን። ለማንኛውም እንዲህ እንላችኋለን፤

የኢትዮጵያ ህዝብ ጎዳና ላይ መኖር የጀመረው ህወሃት አገሪቷን መቆጣጠር ከጀመረ ወዲህ ነው።ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ እንዲኖሩ የሆነው ህወሃቶች የአገሪቷን ሃብት ዘርፈው ለራሳቸው ብቻ በማድረጋቸው ነው።ዛሬ በውጭ አገራት ባንኮች ከኢትዮጵያ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ወጥቶ የተቀመጠው ብዙ ቢሊዮን ዶላር ዜጎች ጎዳና ላይ እንዲኖሩ ተደርጎ መሆኑን አበክረን ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።ይሄ ዝሪፊያችሁ ነው የኢትዮጵያ ህዝብን ጎዳና ተዳዳሪ እንዲሆን ያደረገው እንጂ ሌላ አይደለም።

እናንተ ጎጠኛ ህወሃቶች ስሙ!!!

ዛሬ እናንተ ልጆቻችሁን በአሜሪካና በአውሮፓ እንዲሁም በቻይና ልካችሁ የምታስተምሩት ከድሃው ኢትዮጵያዊ ዘርፋችሁ መሆኑን እኛ እንድንነግራችሁ ትፈልጋላችሁን? የእናንተ ልጆች ተንደላቀው ሲማሩ ሌላው ኢትዮጵያዊ ግን ጎዳና ተዳዳሪ ሁኖ በድንቁርና ውስጥ እንዲኖር የፈረዳችሁበት መሆኑንስ አትገነዘቡምን? የዘመኑ ባለስልጣናት ለራሳችሁ ባለ ብዙ ፎቅ ቤቶችን  ሠርታችሁ ተንደላቃችሁ ስትኖሩ ከራሳችሁ የተረፈውንም በብዙ ሺህ ብር እያከራያችሁ ደስ ብሏችሁ ስትኖሩ ድሆች በላባቸው ጥረውና ግረው የሰሩትን ቤቶች አፍርሳችሁ ሜዳ ላይ መጣላችሁን ህዝቡ የማያይ ይመስላችኋልን ?እኛም ሆንን ሌሎች ሁሉንም እያየን እና እየሰማን ነው።ከህዝብ ተሰውሮ የሚቀር አንዳችም ነገር የለም።

እናንተ “እኔ” ብቻ ማለትን የምታውቁ ህወሃቶች ስሙ !!!

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንዲህ እንደ እናንተ ዘመን ጎዳና ላይ የሚኖር ዜጋ ታይቶ አይታወቅም። እንዲህ አይነት ሁኔታ በጎሬቤት አገሮችም አልታየም። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአገሪቷ ዋና ከተማ ጎዳና ላይ የሚኖሩት እናንተ እንመራታለን በምትሏት ኢትዮጵያ ብቻ ነው። ጭካኔያችሁ ወደር የሌለው በመሆኑና አገራዊ ስሜት በማጣታችሁ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በሺዎች በሚቆጠሩ ጎዳና ተዳዳሪዎች ሊሞሉ ችለዋል ።

“ኢትዮጵያን የምንስበር እኛ፤ የምንጠግንም እኛ” ብላችሁ በቅዥት የምትኖሩ ህወሃቶች አሁንም ስሙ!!!

መተማመኛችሁ ጠመንጃችሁ መሆኑን እናውቃለን። እናንተ ከጠመንጃ ወዲያ ማሰቢያ አካል እንደሌላችሁም ደህና አድርገን እንገነዘባለን። እኛ ግን እንዲህ እንላችኋለን ያ ስትግድሉት አልቅሶ ዝም ያላችሁ ህዝብ ሞትን የሚንቅበት ግዜ እሩቅ አይሆንም። ካሁን ወዲያ ምን ሊመጣ የሚልበት ግዜም እየመጣ ነው። ለዲኑ፤ ለሃይማኖቱ፤ ለነፃነቱ መሞት ክብርና ጀግንነት መሆኑን አምኖ የሚቀበልበት ግዜ ደርሷል።ያን ግዜ ያ የተሞረኮዛችሁት ጠመንጃ የሸንበቆ ምርኩዝ ሆኖ ተሰብሮ የሚወጋችሁ መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን። ያ ከመሆኑ በፊት ግን ከህዝብ ጎራ እንድትቀላቀሉ ሳንመክራችሁ አናልፍም።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

ግንቦት 7

 

 ABBAY MEDIA.COM