Blog Archives

የወያኔን ሰላዮችን ከውጭ አለም ማጽዳት

ከእስከ ነጻነት

ኢትዮጵያ የነጻነት ቀንዲል ነች፡እንደ ስበሃት ነጋ ላሉ ባንዳ ወያኔዎች ግን ጣሊያንን አሸንፈን ለመላው የጥቁር ህዝብ የነጻነት ጎህ ቀዳጅ መሆናችን ኩራት ሳይሆን እፍረት ስለሚመስላቸው አገሪቷ ከነሰንደቅ አላማዋ ጥፍታ ማየት የዘወትር ጥረታቸው ነው፡ ሌት ተቅን የሚተጉትም ለዚህ ስለሆነ የኢትዮጵያዊነት ሰሜት ያላቸውን ሁሉ ማሰር፤ መግደል፤ ማጥፋት ዋና ትግባራቸው ነው፡ ይህም ተግባራቸው ከበረሃ እስከ አዲስ አበባ ከዛም ጎረቢት አገሮች ድረስ ዘልቆ አሁን ደግሞ ወደ ምእራብ ሐገራትም መጣሁ እያለ ነው።

ግን አገሪቷም ሆነ ባንዲራዋ ልትጠፋ አትችልም፡ ለጥቁር ህዝብ የነጻነት ጎህ የቀደደች መሆኗን ለማረጋገጥ በርካታ ሃገራት ከቅኝ ግዛት ነጻ ሲወጡ ባንዲራቸውን መሰረት ያደረጉት በኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ላይ ስለሆነ ባለም ዙሪያ ሲውለበለብ ይኖራል እንጂ ባንዳዎች እንደተመኙት ልትጠፋ አትችልም።

ባለፈው አበበ ገላው ላይ የተቃጣው የግድያ ሴራ ከወያኔ አድሎአዊ አገዛዝ፤ ሸሽተን በመጣነው ሁሉ ላይ የተቃጣ ዛቻ ነው በሚል አጠር ያለች ጽሑፍ በእንግሊዘኛ ቋንቋ አቅርቤ ነበር። በዛሬው ጽሁፌ ማተኮር የምፈልገው ወያኔ (ለኔ ወያኔ ማለት ለአላማም ይሁን ለጥቅም የዚህን አገዛዝ እድሜ የሚያራዝም ሁሉ ነው) እንዴት ተሰደን ባለንበት አገር ለማስፈራራት ብርታቱን አገኘ? እንዴትስ የወያኔ አባላት ሰላዮች እና እበላ ባዮች በውጭው አለም በዙ? እንዴትስ መመንጠር እንችላለን የሚሉትን ዝርዝር ጉዳዮች በተመለከተ ይሆናል።

ወደ ውጭ አገር መሰደጃ መንገዶች የታወቁ ናቸው፡ ከደርግ ጅምላ ፍጅት ሽሽት አገራቸውን ጥለው የተሰደዱ ብዙ ናቸው፡ በዘር የተደራጀው እና ዘር በማጥላላትና በማጥፋተ ላይ የተመሰረተው የወያኔ ቡድን ስርዓቱን በኢትዮጵያ ላይ ከጫነ ጀምሮ፡ ወያኔ በህዝቡ ላይ በሚያደርገው ጫና፤ ጭቆናና ግፍ አገራችንን ለቀን ተሰደናል፡ የተሳካልን ነጻው አለም ደርስናል ያልተሳካላቸው በበረሃ አሸዋ ተውጠው ቀርተዋል፡ ባህር ውጧቸዋል፡ ከቀይ ባህር እስከ ቬንዙዌላ የውሃ ጎርፍ ወስዷቸዋል፡ ከባህር እና ካሸዋ የተረፉት በየሀገራቱ እስር ቤቶች ተሰቃይተው ሞተዋል፡የውስጥ አካላቸው ተበልቶ ተወሰዷል፤ በእህቶቻችን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ግፍ እና ስቃይ መናገር አይቻልም፡ የሰው ህሊና ሊያስበውና ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ነው።

እኛስ በዚህ መልኩ ተሰደድን የወያኔ ደጋፊዎች፤ እና ሰላዮችስ እንዴት መጡ?

በስራ፤ በንግድ፤ ወይም በተለያየ መንገድ ከመጡት በተጨማሪ፡ እንደኛው ወያኔ ሊያኖረኝ አልቻለም፡ አሰረኝ፤ ገረፈኝ ብለው የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው ውጭ የሚኖሩ በጣም ብዙ ናቸው፡ በሌላም በኩል ኤርተራዊ ነኝ፡ ብለው በኤርትራውያን ስም፤ ሱማሌያዊ ነኝ ብለው በሱማሌ ስም ጥገኝነት ጠይቀው የተፈቀደላቸው እንዳሉም ይታወቃል፡ እንዳውም የኤርትራውያንን ስደተኞች ተቀብያለሁ እና ሶስተኛ አለም ተረከቡኝ ብሎ ሶስተኛ አገሮች ከተረከቧቸው አብዛኛዎቹ የወያኔ ደጋፊዎች እና የወያኔ ሰላይ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ስደተኞችን ተቀባይ አገሮች አይወቁት እንጂ የህን ጽሁፍ በማንበብ ላይ ያለኸው፤ ያለሽው፡ ጠንቅቀው ያውቁታል።

ለምን የወያኔ ደጋፊዎች፤ ወደ ነጻው አገር መጡ አደለም ጥያቄው፡ ይኸ መንግስት በድሎናል፤ ጨቁኖናል መኖር አልቻንም ብለው የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው፤ ጥያቄያቸው ተቀባይነት ካገኘ በሗላ ከዚሁ ጨቆነን ካሉት መንግስት ጋር አብሮ መስራት፤ የወያኔ ደጋፊዎች፤ ኢምባሲ ጭምር በሚያዘጋጁት ስብሰባ ላይ፤ የድጋፍ ሰልፍ ላይ እንዴት ሊገኙ ቻሉ?

ይህ ብቻ አደለም ከድጋፍ አልፈው የወያኔ አገዛዝ አስመርሯቸው የተሰደዱትን በኬንያ፤ በዩጋንዳ በሱዳን፤ በሶማሊያ፤ በጅቡቲ ሲገሉ እና ሲያሰገድሉ ኖረዋል፡ ያንን ተግበር አሜሪካ፤ ካናዳ እና አውሰትራሊያም ሊሞከሩ እንደሚችሉ፤ መገመት በቻ ሳይሆን አበበ ገላው ላይ የተጠነሰሰው ሴራና የአሜሪካው የፌዴራል ምርምራ ቢሮ (FBI) ማክሸፉ ያላቸውን ዕብሪት በግልጽ ያሳያል።

ይህ ደግሞ በአበበ ገላው ብቻ የሚቆም አደለም ለሌሎቻችንም የሚተርፍ የወያኔ ድግስ ነው ስለዚህ እንዴት ማስቆም አለብን የሚለው ነው ቁም ነገሩ።

ይህንን ለማሰቆም ወይም የወያኔ ሰላዮችን አጋልጦ ለፍርድ ለማቅረብ የፖለቲካ ድርጅቶች ወይም የሲቪክ ድርጅቶች አያስፈልጉም፡ እነሱ ወያኔን ከስሩ ለመንቀል ይንቀሳቀሱ፤ ለዚህ ተግባር ግን የሚያሰፈልገው፡ በወያኔ የዘረኛ አገዛዝ ተማረህ የተሰደድክ፡ ግፋዊ አሰተዳደሩን መቋቋም አቅቶሽ አገርሽን ጥለሽ የወጣሽ፡ በወያኔ የግፍ ቀንበር እህትህን ያጣህ፤ ወንድምሽ እህትሽ በስደት ላይ እያሉ ባህር የዋጠብሽ፡ አንተ ነህ፤ አንቺ ነሽ የምታስፈልጊው፤ የምታስፈልገው። በአንድ ከተማ ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ቁርጠኛ ኢትዮጵያዊ ካለ በቂ ነው፡ በኢትዮጵያ የህግ የበላይነት መከበር ጽኑ አላማ ያለውና በጥቅም ያማይገዛ ህሊና ያላቸው አንድ ወይም ሁለት ባንድ ከተማ ካሉ በጣምበቂ ነው፡ የሚጠበቀው መደባደብ ወይም መሰዳደብ አደለም የሚያሰፈልገው ወያኔ በድሎኛል ብሎ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ ሰው ከወያኔ ቡድን ጋር እየሰራ እና ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም ጥገኝነት የሰጠውን አገር አየስለለ መሆኑን ሪፖረት ማረግ ብቻ ነው።

ማንኛውም ሰው አንድ አገር የፖለቲካ ጥገኝነት ሲጠይቅ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በደለኝ ብሎ መኖር አልቻልኩም ካለና ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ በሗላ ያ መንግስት እስካልተቀየረ ድረስ ከዛ መንግሰት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሊኖረው አይችልም፡ በምንም መልኩ ከዛ መንግስት ጋር ግንኙነቱን ከቀጠለ ከመንግስቱ ጋር ችግር የለበትም ማለት ነው ስለዚህ ወዳገሩ መመለስ አለበት፡ የኽ የኔ አስተያየት ሳይሆን የየሃገራቱ የስደተኛ ህጎች ናቸው።

ስለሆነም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ የተፈቀደለት፡ ወይም ኤርትራዊ፤ ሶማሊያዊ ነኝ ብሎ ጥገኝነት የተፈቅደለት (ወንድ ይሆን ሴት፤ አማራ ይሁን ኦሮሞ፤ ትገሬ ይሆን አደሬ፤ ማንም ይሁን ማ) የወያኔው ኢምባሲ በሚያዘጋጀው ፕሮገራም ላይ የሚሳተፍ፤ የወያኔ ባለስልጣናት በሚጠሩት ስብሰባ ላይ የሚገኝ፤ የወያኔ ደጋፊዎች ወይም ካደሬዎች በሚያዘጋጁት የወያኔ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የሚገኘን፡ ከወያኔ ጋር የንግድ ስራ ጀምሮ ኢትዮጵያ የሚመላለስን ሁሉ ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ማደረግ ያስፈልጋል።

ባለፈው 21 አመት ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት አልተቀየረም ስለሆነም በነዚህ ጊዜያት የወያኔ መንግስት በድሎኛል፤ ሊያኖረኝ አለቻለም ብሎ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ ሰው ሁሉ በምንም መልኩ ከወያኔ ጋር የሚሰራ፡ ወያኔ በሚያዘጋጀው ዝግጅት ላይ የሚገኝ ሁሉ ሪፖርት መደረግ አለበት።

እዚህ ላይ አደራ የምለው እና ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባው ሪፖርት የሚደረገው ነገር እውነት ብቻ እንዲሆን፤ በግል ቂም በቀል፤ ወይም በተወሰነ ዘር ላይ ያነጣጠረ እንዳይሆን አደራ እላለሁ፡፡ ወያኔን ያጠናከረው፡ የተወሰነ ዘር ወይም የወያኔው አባላት ብቻ ሳይሆን እበላ ባይ አጃቢ ጭምር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡ ስለዚህ ሁሉም የወያኔን እድሜ እየለመነ የወያኔን ፍርፋሪ የሚለቃቅም ሁሉ ሪፖርት መደረግ አለበት።

ወያኔን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ከወያኔ ጋር መደባደብ መነታረክ ሳይሆን ሰማቸውን ቢቻል አድራሻና ፎቶገራፋቸውን መዝግቦ መያዝ ነው ከዛ ለሚመለከተው ረፖርት ማድረግ።

ሪፖርት ለማድረግ የግድ የግል ሰማችሁን መጠቀም አይኖርባችሁም፤ ሰሜ አይገለጽ ማለትም ትችላላችሁ፡ ከቤታችሁ ሪፖረት መላክ ካላመቻችሁ ወይም ካልፈለጋችሁ ከህዝብ መጻሕፍት ቤት ኮምፑተር ተጠቅማችሁ ሪፖርት ማድርግ ትችላላቸሁ፡ የህዝብ ቤተ መጻህፍት አባል ለመሆን ክፍያ አይጠይቅም ነጻ ነው፤ የሚጠይቀው መታወቂያ ወይም ባደራሻችሁ በስማችሁ የተላከ ደብዳቤ ብቻ በቂ ነው፡

መልክታችሁ አጭር ነው፡

“እገሌ የሚባል ሰው አዚህ አገር ሲገባ መንግስት ጨቆነኝ አላኖር አለኝ፤ ብሎ ነበር አሁን ግን ጨቆነኝ ከሚለው ከመንግስት ጋር በቀጥታ እየሰራ ስለሆነ ሰላይ ሊሆን ይችላል ወይም የጥገኝነት ጥያቄው የውነት አደለም ብዬ እጠራጠራለሁ ማጣራት ቢደረግ”

ማጣራቱ የናንተ ጉዳይ ሳይሆን የደህንነት ሰራተኞች ጉዳይ ይሆናል፡ ከማንም ሳትማከሩ፤ አዩኝ አላዩኝ ብላችሁ ሳትፈሩ፤ ሚስጥሬ ይባክናል የሚል ስጋት ሳይኖራችሁ ትክክለኛውን መረጃ ለሚመለከተው ክፍል መስጠት የህሊና ነጻነት መጎናጸፍ እና የዜግነት ድርሻን መወጣት ነው፡

ሪፖርት የምታደርጉባቸውም አድራሻዎች

1. በዩናይትድ ሰቴትስ FBI (Federal Bureau of Investigation)https://tips.fbi.gov 2. በካናዳ Canadian Security Intelligence Service:http://www.csis-scrs.gc.ca/cmmn/cntcts-eng.asp 3. በአውስትራሊያ Australian security Intelligence Organization:http://www.asio.gov.au/Contact-Us.html እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

Abbay Media.com

Advertisements

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ

tplf addis

June 23, 2013 12:19 pm By  Leave a Comment

ወደ ግንቦት 20ቀን, 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ትንሽ ወደ ኋላ መለስ በማለት የደርግ ስርዓትን በትንሹ እንቃኘው::

ደርግ

የካቲት ወር 1966 ዓ.ም. የዘውድ አገዛዙን ስርዓት በመቃወም በአርሶ አደሩ ፣ በተማሪው ፣ በአስተማሪው ፣ በመንግስት ሰራተኛው ፣ በወዛደሩ ፣ በነጋዴው እና በመለዮ ለባሹ ወዘተ ፣ ወዘተ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ጊዜ ሳይወስድበት በ6 ወራት ውስጥ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ግቡን መታ::

ህዝባዊ አመጹን የሚመራው የተደረጀ ፓርቲ ባለመኖሩ በር የተከፈተለት መለዮ ለባሽ አመቺ ሁኔታ በማግኘቱ በፍጥነት ተደራጅቶ ከተራ ወታደር ጀምሮ የተለያዩ ማእረግ ያላቸው አባላቱን አስመርጦ ወደ 120 የሚጠጉ ተወካዮቹን አዲስ አበባ በሚገኘው አራተኛ ክፍለጦር አሰባሰበ::

ከጦር ሃይሎች ፣ ከክቡር ዘበኛ እና ከፖሊስ የተውጣጡት እንኚሁ መለዮ ለባሾች በሰኔ ወር 1966 ዓ.ም. ተሰብስበው ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ መስርተው “ኢትዮጵያ ትቅደም ፣ አቆርቋዥ ይውደም” በሚል መርህ ስር ሰፊ ሊባል የሚችል የህዝብ ድጋፍም አግኝተው ነበር::

መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም. የተመሰረተው አስተባባሪ ኮሚቴ ንጉሱን ከስልጣን አውርዶ “ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ” የሚል ስም በመያዝ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ጀመረ:: ቀስ በቀስም ደርግ የስልጣን ወንበሩን በማመቻቸት የሃገሪቷ መንግስት ለመሆን ቻለ::

በወቅቱ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሃገራት ሶሻሊዝም ወይም ህብረተሰባዊነት በሚባል ርዕዮተ አለም እድገት እና ብልጽግና የማይገኝበት “ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ” ስርዓት በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት እና ቻይና ፕሮፖጋንዳ አለምን እንደማዕበል ሲወዘውዛት የነበረበው ሁኔታ ሆኖ በደርግ የተመሰረተው መንግስት ግራና ቀኙን ሳይመለከት ሶሻሊዝም በኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈጥረውን ቀውስ እና ችግር ሳያጤን እና ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን ሳያማክር በ1972 ዓ.ም. ኢሰፓአኮን(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን) መሰረተ:: ይህንን ምስረታ ተከትሎም ደርግ አንድ እግሩን ገደል ከተተው::

በዚህ ጽሁፍ ሁለት ነገሮችን ለያይቼ በማሳየት ለማለፍ እሞክራለሁኝ፤

  1. ደርግ እንደ ፖለቲካ ተቋም እና ስርዓት
  2. መለዮ ለባሹ እንደ አገር መከላከያ ሰራዊት

ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያዊ የሆነ እና በዘመናዊነቱ በአፍሪካ ጭምር ተወዳዳሪ ያልነበረው እንደነበር ነው:: የደርግ ስርዓት ከወታደሩ በወጡ ሰዎች ቢመሰረትም ሰራዊቱ ግን በየትኛውም መለኪያ የኢትዮጵያ ሰራዊት ለመሆኑ ከጥያቄ ውስጥ ሊያስግባው የሚችል አንዳችም መከራከሪያ ሊቀርብ አይችልም:: አገራችን ዘመናዊ ጦር ማደረጀት ከጀመረችበት ከሃያኛው ክፍለዘመን መባቻ ጀምሮ በስንት ወጪ እና ጥረት የገነባችውን ጦር የ “ደርግ ጦር” የሚል ቅጽል በመስጠት ከፍተኛ የሆነ የስም እና የሞራል ማጥፋት ዘመቻ የፈጸሙበት ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑት ወያኔ እና ሻዕቢያ ናቸው::

ይህ ጦር ደሙን አፍስሶ ፣ አጥንቱን ከስክሶ ፤ ራበኝ ፣ ደክመኝ ሳይል ወያኔ እና ሻዕቢያን እግር እግራቸውን እየተከታተለ ሲደመሥሳቸው እና ሲያጠፋቸው የነበረ የኢትዮጵያ ብርቅ ልጅ ነው:: የዛሬው የወያኔ ዘረኛ ሰራዊት ግን እንኳን ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሊከላከል ይቅርና ራሱ የወያኔ ሰራዊት ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ ህዝብ የአንድ ጎጠኛና ዘረኛ ታጣቂ ቡድን ነው:: አሁን ያለው በዘር የተደራጀው ቅጥረኛ እና ባንዳ ሰራዊት በየትኛውም መለኪያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተብሎ ሊወሰድ የሚችልበት ሁኔታ የለም::

የደርግ መንግስት በስልጣን በቆየበት 17 አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ቀይ ባህርን የጠበቀ ፤ ከገንጣይ እና አስገንጣዮች አገሪቷን እየተከላከለ ሉዓላዊነትን የጠበቀ የኢትዮጵያ ስርዓት ነበር::

በሚከተለው ርዕዮተ አለም ቀስ በቀስ እየተዳከመ በመሄድ እንደነበረው አገርና ህዝብ ለማዳን አልቻለም:: ደርግ በተዳከመ ጊዜም ሰራዊቱ ይዳከማል:: አንድ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከመንግስት የሚቀርብለት ነገሮች ብዙ ናቸው:: ይህ አልሆነም:: ሰራዊቱም መንግስት በመዳከሙ ምክንያት የነበረው አልበገር ባይነት ስሜቱ እና ጀግንነቱ የውጊያ ብቃቱ ተስፋ በመቁረጡ ችግር እየፈጠረለት ሄደ ቢሆንም ግን ወያኔም ሆነ ሻዕቢያ አሁንም ፈቀቅ ሊሉ አልቻሉም:: የማይበገር የኢትዮጵያ ሰራዊት መሆኑን ያውቁታል እና::

ይህ በዚሁ እንዳለ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት መንግስቱ ሃይለማሪያም ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ለቀው ዚምባብዌ ሃራሬ ገቡ:: እዛም ጥገኝነት ጠየቁ:: መሆን የማይገባውን ስራ ሰሩ:: በኢትዮጵያ ሃገራቸው ሰርተው ሂወታቸው ቢያልፍ ታላቅ ስምና ክብር ያገኙ ነበር:: ግን አላደረጉትም:: ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሰራዊት ተበተነ::

ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. በፕሬዚደንት መንግስቱ እግር የተተኩት ጀነራል ተስፋዬ ገብረኪዳን በዜና እወጃ የኢትዮጵያ ሰራዊት የነበርከው በያለህበት ቦታ መሳሪያህን ለህወሃት(ኢህአዴግ) እና ለሻዕቢያ እያስረከብክ ወደ ምትፈልግበት ሂድ፤ ሻዕቢያም ኤርትራን ህወሃትም ኢትዮጵያን እንዲቆጣጠሩ ፈቅደናል በማለት ፍጹም ክህደት በሆነ መንገድ ኢትዮጵያ እና ህዝብዋን ለደመኛ ጠላቶች አሳልፈው ሰጡ::

ያን በወታደራዊ ሳይንስ እና የጦር ውጊያ የተከማቸ እውቀት እና ችሎታ የነበረውን የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሰራዊት እልም ባለ ገደል ወረወሩት:: ለስንት አመታት የሃገሩን ዳር ድንበር ያስከበረ እና የጠበቀ ጦር ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. ካልምንም መተዳደሪያ እና የአገልግሎት ክፍያ በየበረሃው ተበተነ:: በስንት ሚሊዮን የሚቆጠሩ የምድር ጦር ፣ አየር ሃይል ፣ ባህር ሃይል ፣ አየር ወለድ እና አየር መቃወሚያ አባላት እና ቤተሰቦች ለመከራ እና ለችግር ተዳረጉ::

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ወያኔና ሻዕቢያ:: ሻዕቢያ ኤርትራን ሲቆጣጠር ወያኔ ህወሃት ደግሞ ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. በፈንደቀለት ጸሃይ አዲስ አበባን ግንቦት 20 ቀን 1983 ተቆጣጠረ:: ኢትዮጵያም ለፋሺስት መሪዎች ተዳረገች:: ሰራዊቱ እየጫነ ካለምንም ችግር ካለ ምንም ውጊያ ወያኔ ኢትዮጵያን ተቆጣጠረ:: ከግንቦት 20 ቀን ጀምሮ ወያኔ በከፊል የተቆጣጠረው ወሎ ፣ ጎንደር እና ጎጃም ብቻ ነበር:: ቀሪው የኢትዮጵያ ግዛቶች በተለይ ደቡብ ምስራቅ-ምዕራብ ወያኔ የገባው ከሶስት ወር በኋላ ነበር እንጂ:: ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ አልተቆጣጠረም:: ወደ አዳዲስ ክፍለ ሃገራት ሲሄድ ብዙ ገንዘብ በመክፈል በነዋሪዎች እየተመራ ነው:: ምክንያቱም ወያኔ ህወሃት ከትግራይ አይወጣም ነበር::

ስለሆነም ለኢትዮጵያ ነጻነትና ዲሞክራሲ ስል ብዙ መስዋትነት ከፍያለሁ የሚለው ከንቱ ውሃ የማይቋጥር መፈክሩ ይህ ትልቅ ምስክርነት የሚያሳየው ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን እንደማያውቃት ነው::

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ እና ህዝብዋ ምን ይዛ መጣች? በግንቦት 20 ኢትዮጵያ አገራችን በጨለማ ጉም ተሸፈነች:: አገርና ህዝብ ጥቁር የሃዘን ልብስ ለበሱ:: ሲጠሏት እና ታሪኳን እና ህዝቧን ሲያዋርዱን ሲያንቋሽሹ በነበሩት ወያኔ ህወሃት ለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ተዳረገች:: ዘረኛው እና ጎጠኛው ወያኔ ህወሃት በመለስ ዜናዊ የሚመራው የማፍያ ፋሺስት ግልገል እና ግብረ አበሮቹ ጸረ ሀገር እና ጸረ ህዝብ የሆኑትን ለዘመናት የተከበረው የምኒሊክ ቤተ መንግስት ተቆጣጥረው የግልገል ፋሺስቶች መንደላቀቂያ ሆነ:: እነሱም ስልጣን እንደጨበጡ ኤርትራን አስገንጥለው የቀይ ባህር ንግስት የነበረችው ኢትዮጵያ ወደብ ወይም የባህር በርዋን አጥታ አንገትዋ የተቆረጠ ዝግ አገር አደረጉዋት::

ወያኔ ህወሃት ከደደቢት ይዞት የመጣውን ህገ ደንቡን የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አደረገው:: ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት እና ኢትዮጵያዊነት አጠፋዋለሁ ብሎ ያመጣውን የዘረኝነት ህጉን በኢትዮጵያ ዘረጋ::

ይህ በዚህ እንዳለ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ እና ግንቦት 20 ምን ይዞለት መጣ? የኢትዮጵያ ህዝብስ ከግንቦት ሃያ ቀን ምን ተጠቀመ? ምን እድገት አገኘ? ፍትህና ነጻነቱ እንዲሁም ሰብዓዊ መብቱስ እንዴት ሆነ? የሃገሪቷ ሃብትስ በትክክል ለህዝብ ጥቅም ዋለ ወይስ ምን ሆነ? የትምህርት እድገቱስ? የዘመናዊ ቴክኖሎጂስ ለህዝብ ተስፋፋ ወይ? ሌላም ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል:: ለሰው ልጅ አደገኛ ጠንቅ ዕጽ መስፋፋት ለምን? ሽርሙጥና መስፋፋት ለምን? ስራ አጥነት ፣ የወንጀል ድርጊት መስፋፋት እንዴት እና ለምን? የህዝብ መፈናቀል ለምን? የዘር ማጥፋት በኢትዮጵያ ስለምን ተደረገ? ወዘተ ::

ወደ ግንቦት 20 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ከ17 አመታት በፊት ወያኔ ህወሃት እንደተፈጠረ የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. የትግራይ ህዝብ የአደረበትን ስሜት ባጭሩ ልዳሥ::

ወያኔ ህወሃት በዚሁ ቀንና ወር ደደቢት በረሃ ሲወጣ የትግራይ ህዝብ የዚሁ እኩይ ድርጅት ማንነቱን አያውቅም ነበር:: ቀስ በቀስም በየቦታው ብቅ ጥልቅ ሲል የትግራይ ህዝብ አልተቀበለውም::በህዝቡ ወያኔ ህወዋት ተቀባይነት በማጣቱ የተነሳ ምክንያት ጭንቀትን ንዴት የተነሳ በሰላማዊ የትግራይ ተወላጆች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረ:: አስገድዶ ንብረቱን መውረስ እና አስገድዶ እርዳታ እንዲሰጥ ተደረገ:: ምክንያቱም የሚከላከልለት ረዳት የሌለው ህዝብ ሻዕቢያ፣ ወያኔ እና ጀብሃ ሶስቱ በየፊናቸው አስቸገሩት:: የትግራይ ህዝብ ከየቦታው እየተለቀመ ተገደለ::

ከዚህም ቀጠል በማድረግ ወያኔ ህወሃት በሃይማኖት ጣልቃ በመግባት ክርስቲያን ጸረ ክርስትና እስላሙ ጸረ እስልምና ሃይማኖታቸውን እንዲያወግዙ የተቻለውን ቢሰራም አልሆነለትም::

ጸረ ህወሃት እና ጸረ ሻዕቢያ እየተባሉ ያልሆነ ያላሰቡት ብዙ ፣  ብዙ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች ሃለዋ ወያኔ (06) እየገቡ እሱም/እርሳውም ተገድለው ቤት ያፈራው ሃብታቸው ተወርሰው ህጻናት አልባሌ ቦታ ወድቀው ቀርተዋል::

በየከተማው ወያኔ ህወሃት ሽብርተኞች () በማሰማራት በጠራራ ጸሃይ ብዙ ሰው ገድለዋል:: ህወሃት የትግራይን ህዝብ እንደግሉ መሳሪያ አድርጎ የሚናገረው የትግራይ ህዝብ ከመጀመሪያ ትግሉ ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም. ለወደፊትም አልተቀበለውም:: አይቀበለውምም:: ህወሃት የሚቀልደው ያለ ጉልበቱ ተማምኖ ነው:: ለዚሁም ዋና ምስክር ምርጫ 97 ዓ.ም. ትግራይ ወያኔ አልመረጠውም:: ለወደፊቱም ወያኔን አይመርጥም:: ሁለቱ ሊታረቅ የማይችል ቂም አላቸውና::

ወያኔ ህወሃት የትግራይ ወጣት ሴት ፣ ወንድ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት በማያውቁት የኤርትራ በረሃዎች ሞተዋል:: እዛው አጥንታቸው ተበታትኖ መቅረቱ የትግራይ ህዝብ እስከ አሁን ደም እያለቀሰ ያለበት ጊዜ ነው::

በአጠቃላይ በትግሉ ወቅት በትግራይ ህዝብ ወያኔ ህወሃት የፈጸመው ግፍ በከፍተኛ ወንጀል የሚይስጠይቀው ነው:: የትግራይ ህዝብ ወያኔ የተፈጠረባት የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. በሚከበርበት ጊዜ በየቦታው የሚጠራበት ስም አለው:: በተምቤን አካባቢ “የተረገመች ቀን” ሲላት በአድዋና አክሱም አካባቢ “የጨለማ ቀን”” ሲለው በሽሬ አካባቢ ደግሞ “የእልቂት ዘመን” ይለዋል::

ወያኔ ህወሃት በለስ ቀንቶት አዲስ አበባን የተቆጣጠረበት ቀን ግንቦት 20,1983  ኢትዮጵያ እና ህዝቧ በደመኛ ጠላታቸው የወደቁበት እና በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ የመጣበት ቀን ነው::

ከዚሁ ቀን መነሻ በማድረግ ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ የነበረው ቂም በቀል በማያቋርጥ ሁኔታ በ22 አመት የወያኔ ህወሃት አገዛዝ የወረደበት ግፍና ሰቆቃ ቀጥለን ባጭር ባጭሩ እንመልከት::

ግንቦት 21 ቀን 1983 ዓ.ም. ወያኔ ኤርትራን አስገነጠለ:: ኢትዮጵያንም ካለ ባህር በር አስቀራት::

ወያኔ ህወሃት የኢትዮጵያ ዝነኛው ምድር ጦር ፣ አየር ሃይል ፣ ባህር ሃይል ፣ ፖሊስ ወዘተ የጠላይ ጦር በማለት ይደርግ ስርዓት በራሱ ሂደት ተመናምኖ በወደቀበት ለብዙ አመታት የሃገሩ ዳር ድንበር ሲያስከብር ከጠላት ሲከላከል የነበረው ካለምንም ጡረታና መተዳደሪያ የ”ጠላት ጦር” በማለት ለልመና እና ለችግር ዳረገው:: የሚይስተዳድራቸው ቤተሰቡ በሚልዮኖች የሚቆጠር ለረሃብ እና ችግር ተዳርገው ተበታትነው ቀሩ:: ከትግራይ ይዟቸው የመጣ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሃገር መከላከያ ሰራዊት አደረገ:: ቀሪዎቹን ታጋዮች ደግሞ ፖሊስ ፣ ደህንነት በማለት ዘረኛ ሰራዊት በኢትዮጵያ አቋቋመ:: ይህም በምንም አይነት ኢትዮጵያን የማይወክሉ ሁሉም ከላይ እስከ ታች ለነዚህ ተሰጠ:: እነዚህም በፊናቸው በኢትዮጵያ ህዝብ አስከፊ ሰቆቃና ግድያ በህዝቡ እየፈጸሙ ይገኛሉ::

ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ በዘር ማጥፋት ወንጀል ተሰማራ:: ዘር ማጥፋቱን ገና ከ1969 ዓ.ም. የጀመረው ሲሆን በበለጠ ደግሞ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ አማራው ከያለበት እየተፈለገ ዘሩን ማጥፋት ተጧጧፈ ቀጥሎም ኦሮሞ ፣ ጋምቤላ ፣ አፋር ፣ ቤኑሻንጉል ወዘተ :: በትግራይ ውስጥም አደገኛ ጠላት ናቸው የሚላቸውን በዘዴ አጠፋቸው::

ወያኔ ህወሃት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የአማራው ቋንቋ ስለሆነ ይህ ቋንቋ የትምህክተኛና የነፍጠኛው ቋንቋ በየትኛውም ክልል እንድይነገር በማለት የኢትዮጵያ ህዝብ መገናኛው እና ሃሳብ ለሃሳብ የሚለዋወጥበት ለስንት ሺህ አመታት ሲጠቀምበት የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ህወሃት እያጠፋው ይገኛል:: በየትኛውም ክልል አማርኛ መናገር በህጉ ከለከለው::

ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ሲያበቃ ለዘመናት ኢትዮጵያዊው ህዝብ በፈለገው ቦታ ሲኖርና በጋብቻ በደም የተዋሃደው ህዝብ ከየክልላችሁ ከሌላ ቦታ የመጣውን ተስፋፊ ህዝብ አስወጡ በማለት እርስ በርሱ በማጋጨት ብዙ ሂወት ጠፍቶ ንብረቱም ተዘርፎ በየበረሃው ተበትኖ ግንቦት 20 ቀን 1983 ይዞት የመጣውን መከራ ገፈት ቀማሽ ሆነ:: በተለይ አማራው::

ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጉ አልበቃ ብሎት በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሱዳን በእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ በምትደዳርበት ገዳሪፍ በተባለው የሱዳን ግዛት አስተዳዳሪ በነበረው ሻለቃ ጉዌን የወሰን መስመር ለጣልያኖች ይጠቅማል በማለት በ1903 እ.ኤ.አ በህገወጥ መንገድ የነደፈው የመስመር ክልል በአጼ ምኒልክ ኋላም በአጼ ሃይለስላሴ እና በደርግ መንግስት ውድቅ የተደረገው እና ተቀባይነት ያጣውን ወያኔ ህወሃት ከየት እንዳገኘው ሳይታወቅ የኢትዮጵያን የወሰን ድምበር በመጻረር ለወዳጁ ሱዳን ከሰቲት ሁመራ እስከ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ድረስ ወደውስጥ ከ40 እስከ 60 ኪ.ሜ. የሚዘልቅ እና 1,600ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ለሱዳን መንግስት የአንዲት ኢትዮጵያን ሰፊና ለም መሬት የሸጠ ወያኔ የሱዳን መንግስት ለውለታው ከገዳሪፍ እስከ መቀሌ የባቡር መንገድ እንደሚዘረጋ የሃገራችንን ሉአላዊነት በመድፈር ለግል ጥቅሙ ሃገራችን እያወደመ ያለ ስርዓት ነው:: የግንቦት 20 ቀን 1983 መዘዝ::

ወያኔ ህወሃት በተፈጥሮ ባህሪው አምባገነን እና ሽብርተኛ ድርጅት እሱን የሚቃወም እና የሚፈጽመው ግፍ እንዲነሳበት አይፈልግም:: ፍላጎቱ ተሳስተሃል አትበሉኝ:: ስለኔ አትናገሩ ከሚለው ፋሺስታዊ ባህሪው በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ እንዲኖር አይፈልግም:: የህዝቡ በነጻነት መናገር እና ሃሳቡን መግለጽ ለወያኔ እንደ እሳት የሚለበልበው ለመሆን የፕሬስ ነጻነት ያገደው:: ይህም እንደ ገዢ ፓርቲ ህወሃት የታገደ ነው:: በዚሁ ፖለቲካዊ ውሳኔ የነጻ ፕሬስ በማደን ፣ በማሰር ፣ በማንገላታት ሳያበቃ ብዙ የፕሬስ ጋዜጠኞች ሃገራቸውና ቤተሰቦቻቸው ለመከራን ስደት ተዳረጉ:: ነጻ ፕሬስ በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ::

ወያኔ ህወሃት የሽግግር መንግስት ብሎ ከሰኔ ወር 1983 ዓ.ም. እስከ ግንቦት ወር 1985 ዓ.ም.  በስልጣን በቆየበት ምርጫ በማለት በጸረ ዲሞክራሲያዊ መንገድ በ1987 ዓ.ም. , በ1992 ዓ.ም. , በ1997 ዓ.ም. እና በ2002 ዓ.ም. በማካሄድ በተለይ በ1997ዓ.ም. ቅንጅት በተለያዩ ፓርቲዎች ቀስተ ደመና ፣ መኢአድ ፣ ኢዴሊ ፣ ኢዴአፓ-መድህን ወዘተ በተጠናከረ ማዕከላዊ ፓርቲ “ቅንጅት” ተብሎ እንደተመሰረተ እምነቱ መሰረታዊ ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲና እድገት ፣ ብልጽግና ፣ ፍትህ ፣ ነጻነት ፣ ከዘረኝነት የጸዳ በምርጫው ለመወዳደር በቀረበበት ምርጫም ተካሂዶ መሉ በሙሉ አሽንፎ ሲወጣ በአንጻሩ ወያኔ -ህወሃት/ኢህአዴግ በዜሮ ተሸንፎ ከምርጫ የወጣው በጉልበቱ ምርጫውን በመንጠቅ ድምጻችን አይነጠቅም ብለው የወጣውን ሰላማዊ ዜጎች በአግአዚ ቅልብ የመለስ ዜናዊ ጦሮች ግደሉት ብሎ ትዕዛዝ በመስጠት ብዙ ኢትዮጵያውያንን ሲገደሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ በየወህኒ ቤት በማሰር ወያኔ ህዝብ ያጠፋበት ቀን የሌባው አይነ ደርቁ ወያኔ በ2002  ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ እንደልማዱ ኮረጆውን በመገልበጥ 99.6% አሸነፍኩ ብሎ ኢትዮጵያና ህዝብዋን ማውደሙን ቀጠለ:: ይህ ሁሉ ችግርን ግድያ ሰቆቃ የግንቦት 20ቀን 1983 ዓ.ም. ውጤት ነው::

ወያኔ ህወሃት በፕሮግራም እንዳስቀመጠው የኤርትራ ጥያቄ ያላንዳች ጥርጥር ሃቀኛና ታሪካዊ መሰረት ያለወ ጸረ ቅኝ አገዛዝ ትግል ነው በማለት ወያኔ ያመነበት ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የማያምንበት የኤርትራ ህዝብም ያላመነበት በኢትዮጳዊነታቸእው የማያምኑ መሆናቸው አንዳች ጥርጣሬ የለውም:: ድርጊቱ የወያኔ ብቻ ነው:: ይህ በዚህ እንዳለ አሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኤርትራ ግዛት አልነበረችም ሁሉ ተከታታይ ዘመናት በወሎ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ሆና ስትተዳደር እንደነበረች ሁሉ ኢትዮጵያ በትክክል የሚያውቀው ሃቅ ነው:: አሰብን በኤርትራ ካርታ ጨምሮ በ1967 ዓ.ም. ያወጣው ወያኔ ብቻ መሆኑን በግልጽ የሚታወቅ ሃቅ ነው:: ወያኔ ህወሃት ይህን የታሪክ እና የሃገር ክህደት የፈጸመው ሆን ተብሎ ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳይኖራት ያደረጉት ኢትዮጵያና ህዝብዋ ጠላት ብለው ስለአስቀመጡት የፈጸሙት ጥቃት ነው:: ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወሮ እንደተቆጣጠረ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የባህር በሯን አጣች::

ይህን በተመለከተ ወያኔ/ህወሃት እና ሻዕቢያ እንግሊዝ አገር ለንደን ከተማ ከግንቦት 5 ቀን እስከ ግንቦት 9 ቀን 1983 ዓ.ም. የቀድሞው የአሜሪካ  ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር የሻዕቢያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ እና የወያኔው መሪ መልስ ዜናዊ ባሉበት ስብሰባ ኢትዮጵያ 85 ሚሊዮን ህዝብ ስላለባት የባህር በር ያስፈልጋታል:: አሰብም ከኤርትራ ያልተካለለ በመሆኑ በአጼ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ ስርዓትም ከኤርትራ ውጭ ሆኖ በወሎ አፋር የተካለለ ስለነበር ቀደም ሲልም አሰብ ከኤርትራ ውጪ ሆኖ በጣሊያንም ብዙ ያልተደፈረች የኢትዮጵያ የባህር በር እንደነበረች ይታወቃል:: አሰብ የኢትዮጵያ የባርህ በር መሆን አለበት ብለው ሃሳባቸውን ሲያቀርቡ የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ በጣም ተናዶ ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ የወደቀች ሃገር የነበሩ አመራር አጼ ኃይለስላሴ ሆኑ ደርግ ያስቀመጡት ካርታ ህወሃት አይቀበልም:: አሰብ የኤርትራ መሬት ነው:: እኛ አሁን በኢትዮጵያ ስልጣን የምንቆጣጠረው የወደብ ችግር አይኖረንም:: ችግር አይፈጠርብንም:: ብንፈልግ ጂቡቲን አሊያም የሶማሊያ እና የኬኒያን ወደቦች እንጠቀማለን:: አሰብ የኤርትራ ስለሆነ እምነታችንም ይህ በመሆኑ አሰብ የኤርትራ እንጂ የኢትዮጵያ አይደለም::

ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር እና ሌሎች አደረዳሪዎች አቶ መለስ ዜናዊ አሰብን የኤርትራ ነው ፤ የወደብ ችግር የለብንም ብለው እኛንም ስለአሳመኑን አሰብ በኤርትራ ውስጥ መካተቱን ተቀብለናል በመለት ሲዘጉት ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ታሪካዊና ጥንታዊው የባህር በርዎችዋን አሳጥቶ ግንቦት 20 ቀን 1983ዓ.ም. አገራችን ኢትዮጵያን በጠላቶችዋ እጅ የወደቀችበት የኢትዮጵያ ህዝብም በድቅድቅ ጨለማ እና ጭቆና ፋሽስት ስርዓት ይዛ የመጣች ይህች ግንቦት የተረገመች ቀን ናት:: በምስራቅ-ምዕራብ-ሰሜን-ደቡብ የሚገኙ ኢትይጵያውያንም እየተረገመች ነው::

ወያኔ ህወሃት በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን በለስ ቀንቶት ወሮ በተቆጣጠረበት ወቅት የኢትዮጵያን ሃብት-ንብረት ወያኔና ሻዕቢያ ተባብረው ዘረፉት:: የወላድ መሃን የሆነችው ኢትዮጵያ ተከላካይ የሌላት ሁለት ከደደቢትን ከሳህል በረሃ የመጡት ሙሉ ሰራዊታቸውን በማሰማራት ሃብትዋን ንብረትዋን ዘርፈውታል:: የተለያዩ ተቋማት ተዘርፈዋል:: ጠቅላላ ጥሬ ገንዘብዋ ተዘርፏል:: ጥሬ ህብቶቿ ተዘርፏል:: የቀራት ነገር የለም:: ለውጪ ገበያ ለሺያጭ የሚመረት ቡና ፣ ሰሊጥ ፣ አደንጓሬ ወዘተ አይን ባወጣው ዝርፊያ ቀን እና ሌሊት ተፈጽሞባታል:: ዝርፊያው በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የጀመረው እስከ አሁን ቀጥለውበታል:: ኤርትራ የቡናና የቅባት ምግብ አምራች በመሆን በአለም ገበያ አቅራቢ ሆና ከዓለም 3ኛውን ደረጃ ያዘች:: ከኢትዮጵያ በተዘረፈው ጥሬ ሃብት ዋና ገንዘብ ወያኔ ህወሃት መሪዎች 1. መለስ ዜናዊ እና ባለቤቱ አዜብ መስፍን 2.ስብሃት ነጋ 3.አባይ ጸሃዬ 4.ስዩም መስፍን 5.አርከበ እቁባይ 6.አዲስ አለም ባሌማ 7. አባዲ ዘሙ 8.ጸጋይ በርሄ እና ባለቤቱ ቅዱሳን ነጋ 9.ተክለወይኒ አሰፍ 10.ብርሃነ ገብረክርስቶስ ወዘተ ሆነው ኢፈርተን አቋቁመው ስልጣኑንም ተቆጣጥረው የናጠጡ ባለብዙ ፋብሪካዎች ትልልቅ ተቋማት መስርተው ቱጃር በለሃብቶች ሆነዋል:: ወያኔ ህወሃት ወደ ስልጣን ባልበቃበት ጊዜ በአጼ ኃይለስላሴና በደርግ ስርዓት ነጻ ተቋም በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ሲያገለግሉ የነበሩትን ብሄራዊ ባንክን ፣ ንግድ ባንክን ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ፣ እርሻ ትራንስፖርት ፣ መአድናት ወዘተ ወያኔን ስልጣን እንደጨበጠ ሁሉን ከህዝብ በጉልበቱ ነጥቆ በመቆጣጠር የሃገርና የህዝብ ሃብት የህወሃት ተቋማት ሆኑ:: ይህም ወያኔ ህወሃት በከፍተኛ ወንጀል የሚጠየቅበት ከዋናዎቹ አንዱ ነው::

ወያኔ ከኢትዮጵያ የዘረፈው ገንዝብ እና ጥሬ ሃብት ኢፈርት በትግርኛ ት.እ.ም.ት የሚል ስያሜ በመስጠት በትግራይ ህዝብ ስም ሲያጭበረብር የትግራይ ህዝብ መነገጃ ማድረጉም ህወሃት በዚሁ ሌብነቱ በወንጀል የሚያስጠይቀው ነው:: በትግራይ ህዝብ ስም የወያኔ መሪዎች ነገዱበት እንጂ የትግራይ ህዝብ ከት.እ.ም.ት ተጠቃሚ አይደለም:: ህዝቡም ራሱ የሚናገረው ሃቅ ይህ ነው::

ወያኔ ህወሃት ድርጅት ነው ስንልም ህወሃት የተመሰረተውና እስከ አሁንም ያለው ህወሃት ግለሰቦች ተደራጅተው የፈጠሩት የማፍያ ስብስብ እንጂ በምንም ተአምር የትግራይ ህዝብን የማይወክል ነው:: በድርጅቱ የተሰባሰቡ ግለሰቦችን ያቀፈ:: ህዝብ ሌላ፤ ህወሃት ሌላ:: ህወሃትን የመሰረቱት ሰዎችም ጸረ ህዝብ እና ጸረኢትዮጵያ ናቸው:: ይህ ህወሃት ተብሎ የሚጠራ በሻዕቢያ የተመሰረተ ኤርትራን ነጻ ለማውጣትና ትግራይም የአማራው ቅኝ ግዛት በማለት የተነሳ ከጥዋቱ ኢትዮጵያዊነቱን የካደ የከሃዲዎች ስብስብ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች የገደለ ጸረ ህዝብ ነው:: በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ገና ከትግሉ መነሻ ጀምሮ ህወሃትን በእውቅና አልተቀበለውም::

ወያኔ ህወሃት ገና በ1968 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መሬት እጠቀማለሁ በማለቱ ከባድሜ እስከ አፋር ቡሬ የመሬት ቆዳ ስፋት 1.ታች አዲያቦ 2. ላይ አዲያቦ 3.ጭላ ወይም አንከረ ባሩካ 4. አሕሰኣ 5.እገላ 6.ዛላምበሳ  በዚሁ ውስጥ የሚጠቃለሉ ኢሮብ ፣ ጻልገዳ ፣ ዓውዳ ፣ አይጋ ፣ ሶቦያ ፣ ወዘተ 7.የአፋር መሬት  እስከ ቡሬ 8. አሰብ የኤርትራ መሆንዋን በዚሁ ፊርማቸው በ1969 ዓ.ም. አረጋግጠዋል:: 1. መለስ ዜናዊ 2.አባይ ጸሃዬ 3.ስብሃት ነጋ በዋናነት የሚጠቀሱ በትክክል የኤርትራን መሬት ነው በማለት ፈርመው የሰጡት ህዳር ወር 1969 ዓ.ም. ነው:: በዚሁ መሰረት የትግራይ ህዝብ 1.በሻዕቢያ 2.በጀብሃ 3.በህወሃት  በእነኚህ ሶስት ድርጅቶች ትተዳደራለህ ብለው በመወሰን ህዝቡም በእነኚህ ሶስት ድርጅቶች ቁም ስቃዩን በማየት ተገደለ:: ንብረት ሃብቱ ተዘረፈ:: አቤት የሚባልበት በማጣት በየስደቱ ተበታተነ:: ወያኔ ይህን ወንጀል እንደፈጸመ በአንጻሩ ከሰሜን ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ለም ወሬት ነጥቆ ወሰደ::

የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ዋና ጦሱ ከላይ እንደተጠቀሰው ነው:: የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት መንስኤ   ው በግልጽ የሚታወቅ ነው:: ወያኔ ህወሃት አመራር የሚያላክኩት በኢኮኖሚ ችግር የተፈጠረነው ሲሉ በተደጋጋሚ በተለይ የወያኔው መሪ ነበር መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማሳመን ለከት በሌለው ውሸቱ ሲለፋደድ ሃገር ሙሉ ያውቃል:: ቀሪዎቹ የሱ የአመራር አባላቱ ስብሃት ነጋ ፣ አባይ ጸሃየ ፣ ስዩም መስፍን ፣ አርከበ እቁባይ ወዘተ የመለስ ዜናዊን ሃሳብ በማስተጋባት በየውጪ ሃገሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማሳመን ብዙ ውጣ ውረድ ቢያደርጉም እስከ ዛሬ ተቀባይነት አላገኙም::

የጦርነቱ መንስዔ በኢኮኖሚ ሳይሆን በትክክለኛው አነጋገር በተጨባጭ ሁኔታው የመሬት ይገባኛል ነው:: ሻዕቢያ የኔ ግዛት ነው:: ከዚህ ቀደምም በ1969 ዓ.ም. ተስማምተን እናንተም የኤርትራ መሬት ነው በማለት ያመናችሁበትን አስረክቡን በማለት ወደ ጦርነቱ ሻዕቢያ እና ወያኔ ገቡ:: እውነቱ ይህ ነው:: ይህ በዚሁ እንዳለም የኢኮኖሚው ጉዳይም አስተዋስኦ ያደረገበት አለ:: ሁሉ ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው ከ1983 ዓ.ም. ግንቦት ወር ጀምሮ እስከ 1990ዓ.ም.  የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራ የግላችን የኢትዮጵያ ሃብት ደግሞ የጋራችን ተባብለው በህወሃት መሪዎች መጠነ ሰፊ ድጋፍ ሁለቱ ማለት ሻዕቢያና ወያኔ የሃገራችን ኢትዮጵያን ጥሬ ሃብትዋን መዓድኗን እና ሃገሪቱ ያፈራችውን የተለያዩ ፋብሪካዎቸ እና ባንኮችን አብረው ተባብረው ዘርፈዋል:: ኢትዮጵያ እና ህዝብዋ ለረሃብ እና ችግር ተዳርገው ኤርትራውያን ጤፍ በየአይነቱ ዳጉሳ ፣ ስንዴ ፣ ገብስ ወዘተ በርካሽ ዋጋ ኤርትራ ሲሸጥ የኢትዮጵያ ገበያ ባዶ ቀረ:: ስለዚህ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲነሳ ያ የለመዱት በሰው ሃገር ሃብት ሲንደላቀቁ የቆዩት አሁን ሲያጡት ለጦርነቱ አስተዋጽኦ ያደረገም ነበር:: በጣም ከሚገርሙ ነገሮች እና አሳዛኝ የሆነው ሁለቱ መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወርቂ በስልክ ጥብቅ ግንኙነት እንደነበራቸው ብዙ ሰዎች ተናግረዋል:: ስብሃት ነጋ ፣ አባይ ጸሃዬ እና ሌሎቹ የወያኔ መሪዎች በጣም የደመቀ ግንኙነት ከጦርነቱ ዋዜማ አንስቶ የወያኔ መሪዎች ይገናኙ እንደነበር ምስጢሩም የሚያውቁ ሰዎች ተናግረውታል::

ኢሳያስ አፈወርቂ ላቀረበው የአንድ ቢሊዮን ብር ላክልን መለስ ዜናዊ ሳያቅማማ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተፈቅዶ ገንዘቡ አስመራ እንደገባ በቀናት የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ መቀሌ ውስጥ(ሃይደር) የሚገኘው የመዋዕለ ህጻናት ትምህርት ቤት በሚግ አውሮፕላን ደበደበው:: ከተዋጊ አውሮፕላኖቹ የተጣለው ክላስተር ቦምብ ወድያውኑ 53 ህጻናትና አስተማሪዎች ሲሞቱ 185 ደግሞ ከባዱ ቁስል ደረሰባቸው:: ለዚሁም ተጠያቂው መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ ናቸው::

የሻዕቢያ ተዋጊ ጀቶች እንደገና ተመልሰው ቦምብ ጭነው 48 ሰላማዊ ሰዎችን 10 ህጻናትን ሲገድሉ 150 ሰዎች አቆሰሉ:: በማለት ቢ.ቢ.ሲ. እና ሲ.ኤን.ኤን. የዘገቡት ዋቢ ነው:: ይህ ጥቃት የደረሰው በግንቦት ወር መጨረሻ 1990 ዓ.ም. ሆኖ አስራት አብርሃም በአሳማኝ ሁኔታ ከ’ሃገር በስተጀርባ’ በሚል መጽሃፉ እንደገለጸው መለስ ዜናዊን ኢሳያስ አፈወርቂ እስከ ታህሳስ ወር 1991 ዓ.ም. ይገናኙ እንደነበሩም ያስረዳል:: መለስ ዜናዊን ግብረአበሮቹ እነ ስብሃት ነጋ ወዘተ ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ የባዕዳን ቅኝ ገዢዎች መሆናቸው በግልጽ የሚያሳይ እውነታ ነው::

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም ሆን ብሎ ያሰናከለው መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ እና አባይ ጸሃዬ መሆናቸው ሲታወቅ ምክንያቱም በ1969 ዓ.ም. ከላይ የተጠቀሰ መሬት የኤርትራ ነው ብሎ ወያኔ የፈረመበት በመሆኑ ይህም በአልጀርሱ ስምምነት ወያኔ መሪ መለስ ዜናዊ አሳልፎ ለኤርትራ መስጠቱ የ1969 ዓ.ም. ትልቁ ማሳያ ነው:: የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት እነማን መሩት? ይህን እንመልከት::

1. መለስ ዜናዊ የጦሩ ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስቴር …………………………………………ኤርትራዊ

2. ጻድቃን ገብረተንሳኤ የጦሩ ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ……………………………………………..ኤርትራዊ

3. ሳሞራ የኑስ…ከፍተኛ ጀነራል…………………………………………………………………………………….ኤርትራዊ (በናቱ ከርከበት በአባቱ ሱዳናዊ)

እነዚህ ሶስቱ አመራር በምንም ተአምር ለኢትዮጵያ ይሰራሉ?? ጦርነቱን በትክክል ይመራሉ ብሎ ማሰብ “ላም አለችኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ” አይነት ነው:: እነዚህ ትልቁ ምኞታቸው የኤርትራ ሰራዊትና ህዝብ እንዳይጎዳ ኢትዮጵያዊው ሰራዊት ቢያልቅ ምንም የማይሰማቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉም የውጊያና ጦርነት አመራር ብቃት የሌላቸው በአጋጣሚ የተገኘው ጠ/ሚኒስቴርነት እና ጀነራልነት ከንቱ ነው:: ጠቅላላ የወያኔ ህወሃት መሪዎች ጀነራሎች እና ወታደሮች ከወታደራዊ ሳይንስ ያላቸው ርቀት ሰማይና መሬት ነው:: በ1991 ዓ.ም. ያለቀው ሰራዊት ተጠያቂም ናቸው::

2ኛው በዚሁ ኢትዮ ኤርትራ ውጊያ ሲመሩ የነበሩ የመለስ ዜናዊ እና የስብሃት ነጋ ታዛዦች ናቸው:: አታድርጉ ከተባሉ አያደርጉም:: በዋናነት ጎልተው የሚጠቀሱም::

1. ሰዓረ መኮንን

2.ዮሃንስ ገ/መስቀል (ቦጅቦጅ)

3.ታደሰ ወረደ

4.አብርሃ ወ/ማሪያም(ኳርተር)

5.ብርሃነ ነጋሽ ወዘተ ሲሆኑ ሌሎችም አሉ::

ስለሆነም በ1991ዓ.ም የደረሰው ውድመት ከ100,000ሺ ሰራዊት የሞተበት ወደ 200,000 የሚጠጋ ሰራዊት አካለ ጎዶሎ የሆነበት ግምቱ አስቸጋሪ የሆነው የኢትዮጵያ ሃብት ንብረት የወደመበት ተጠያቂው ማነው??

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የተፈጠረበት ምክንያት እና ሰበቡ ምንድነው?? እነዚህ ሁልቱ ጥያቄዎች መልስ በግልጽ ለማስቀመጥ እፈልጋለሁኝ::

1. በኢትዮ-ኤርትራ ለደረሰው ግድያና በጦርነት የወደመው ሃብትና ንብረት ተጠያቂዎች::

1. መለስ ዜናዊ

2. ስብሃት ነጋ

3.አባይ ጸሃዬ

4. አርከበ እቁባይ

5. ጻድቃን ገ/ተንሳኤ

6. ሳሞራ የኑስ

7. ስዩም መስፍን

እነዚህ በሰው ህይወት ለደረሰው እልቂትና ጉዳት በሃገሪቱ የደረሰው ከፍተኛ ውድመት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናቸው::

በጦርነቱ የወደመው ሃብት እና ንብረት ተጠያቂውስ ማነው? ለሚለው::

1. መለስ ዜናዊ

2.ስብሃት ነጋ

3.ጻድቃን ገ/ተንሳኤ

4.አበበ ተክለሃይማኖት

5.ገዛኢ አበራ

6.ጀነራሉ በባለ ሌላ ማእረግ

7.ስዩም መስፍን

8.ብአዴን, ኦህዴድ እና የደቡብ ህዝብ ንቅናቄ

9. በወቅቱ የነበሩ የፓርላማ አባላት በሙሉ

10. የህወሃት ካድሬና ደጋፊዎች በሙሉ::

እነዚህም ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች ሲሆኑ፤

3. የጦርነቱ መንስኤ ለሚለው ጥያቄ የህወሃት አመራር በ1969 ዓ.ም. ሻዕቢያ ላቀረበው የመሬት ይገባኛል በወቅቱ አምነት ተቀብለው በፊርማቸው ባረጋገጡት መሰረት በትግራይ ህዝብ ተቀባይነት የሌለው የህወሃት ጥቂት የማፍያ ስብስብ በፈጸሙት ነገር ከሃዲዎች ከሻዕቢያ ጥቅም እናገኛለን ብለው የፈጸሙት ሚያዝያ ወር 1991 ዓ.ም. የፈነዳ ጦርነት ነው:: ተጠያቂዎቹም ህወሃቶች ናቸው::

በብዙ በርካታ ወንጀሎች የትግራይ ህዝብ ሊከሳቸው ዝግጅቱን አጠናቅቆ ቀኑን በመጠባበቅ ላይ ነው:: ህወሃት እና መሪዎቹ ይከሰሳሉ:: አዎን ለፍርድም ይቀርባሉ::

የአይደ መዋእለ ህጻናት የአየር ጥቃትም የትግራይ ህዝብ ካቀረባቸው ክሾች ውስጥ አንዱ ስለሆነ በዚሁም በዋናነት የሚጠቀሱ መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ መሆናቸው ነው::

ግንቦት 20 ቀን1983 ዓ.ም. ይህን አይነት አሰቃቂ ድርጊቶችን አስከትላ ነው ብቅ ያለችው:: የተረገመችው ይህቺ ቀን ኢትዮጵያ ለምለም አገራችንን ለከሃዲ ባንዳዎች አሳልፋ የሰጠች::

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ይዛው የመጣችው ሰቆቃ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በፈለገው የሃገሩ ግዛት የመኖር ለዘመናት ተጠብቆ የቆየውን መብቱን በህወሃት ከፋፍለህ ግዛ በሚመቸው ሃገራችን በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ጠባብ ብሄረተኛ በሆነው መንገድ የዘር ፌደራሊዝም መሰረት ይህ የእቅድ ሃሳቡም አማራውን ለማጥፋት እና ለማክሰም የተቀነባበረ ሴራ ነው:: ይባስ ብሎም ሸዋ ጠ/ግዛት ለሌሎች ብሄራት በመስጠት ጎጃም በጌምድር ጠ/ግዛት ወሎ ጠ/ግዛት በታትነው አማራው መኖሪያ አልባ ተደረገ:: በተለያዩ ጠ/ግዛት ይኖር የነበረው አማራ ውጣ እየተባለ በወያኔ ህወሃት ከህጻን እስክ ሽማግሌ እየተገደለ በየበረሃው ወድቆ የዘሩን ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል:: ቀስ በቀስም ኦሮሞ ጋምቤላ አፋር ወዘተ ተመሳሳይ እጣ ደረሰባቸው:: በጠቅላላው ከተወለደበት ካደገበት ኢትዮጵያዊ ከመሬቱ የተፈናቀለ 24 ሚሊዮን ሲሆን በወያኔ ህወሃት የተገደሉ ኢትዮጵያውያን አንዳንድ ጥናቶች የሚያመለክቱተ 7.9ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ወያኔ ህወሃት እንደገደላቸው ያሳያሉ::

ግንቦት 20ቀን 1983 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሁለቱ ሃይማኖቶች እስልምናእና ክርስትና በእጁ አስገብቶ ለመቆጣጠር እና ቀስ በቀስም ሃይማኖቶቹን ለማክሰም ተነሳ::

1. የኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖት ለብዙ ዘመናት ወግና ህግጋቱን ጠብቆ የመጣ በብዙ ሚሊዮን እስልምና ተከታይ ያለው የኢትዮጵያ ቅርስና የምንኮራበት ሃይማኖት ዛሬ በወያኔ ህወሃት ተደፍሮ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ሙሉ መብታቸውን ተነጥቀው በእስራት መከራ እየተሰቃዩ በገዛ ሃገራቸው ለክፉ ችግር ተዳርገዋል::

2.የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም በክፉ አደጋ ወድቃለች ቤተ ክርስቲያና እየተቃጠሉ ታሪካዊ ቅርሶችዋን በወያኔ ተዘረፉ::ወያኔ የሚቃወሙ ብጹአን አባቶች ለስደት ተዳርገዋል:: ብዙም ተገድለዋል:: ይህን ሁሉ የፈጸመው የወያኔ አባል የነበረው አባ ገብረመድህን ወይም አባ ጳውሎስ የሚባል በወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ፓትሪያርክ ካደረገው ብዙ ወንጀል በቤተ ክርስቲያናችን ፈጽመዋል::

ለመሆኑ አቡነ ጳውሎስ ማነው??

አቡነ ጳውሎስ ትውልዳቸው ትግራይ አድዋ ያደጉትም እንዳባገሪማ ገጠር ነው:: እንዳባገሪማ የተባለበት ምክንያት በአክሱም ዘመነ መንግስት በንጉስ አልአሜዳ ብ470ዓ.ም. ከመጡት ተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ አባ ገሪማ ሲሆኑ ከአድዋ በስተምስራቅ የ18 ኪሎ ሜትር ርቀት የምተገኘው ተራራማ ቦታ አባ ገሪማ በጣም አስደናቂ ሆኖ የተሰራው ቤተ ክርስቲያናቸው በማነጽ እዛው ሞተው እዛው ስለተቀበሩ በዚሁ ምክንያት እንዳባገሪማ ተብላ ትጠራለች::የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያዋረዱን የቤተ ክርስቲያኗን ህገ ደንብ እና ቀኖናውን የለወጡ እና ያፈረሱ ፣ ለስጋቸው ያደሩ: አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ሃይማኖት ለማጥፋት ጸረ ክርስትና የሆኑት ጳውሎስ የአድዋ ልጅ በመሆናቸው በኢትዮጵያ ህጋዊ ሊቀ ቅዱሳን ፓትሪያርክ በቤተ ክርስቲያኑ ህግና ደንብ የተሾሙት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ዘኢትዮጵያ ወያኔ በሃይል አስወግዶ አባ ጳውሎስን ሾመ:: ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሀይማኖት ወግና ስርዓቱን ለማጥፋት የታቀደ ነው:: የቤተ ክርስቲያኑን ህግና ደንብ የሚጻረርም ነው::

አቡነ ጳውሎስ የወያኔ ህወሃት በአባልነት የመለለመሉት በ1976 ዓ.ም. ነበር:: በወቅቱ የሚነገረው ዶ/ር አባ ገብረመድህን የተባሉ የኛ አባል ስለሆኑ ትግራይ ሃገራችን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነጻ በምትወጣበት እኚሁ የትግራይ ፓትሪያርክ ይሆናሉ በማለት ስብሃት ነጋ በለመደው ወሬ ማዛመት በታጋይ ውስጥ ተሰራጨ:: ቢሆንም ግን ታጋዩ ብዙ ስሜት አልሰጠውም:: ምክንያቱም ሃይማኖት የለሽ የወያኔ አመራር በትግሉ ወቅት እግዚያብሄር የሚባል አማልክት የሚባሉ በፍጹም የሉም:: ይህ ለአማራው አገዛዝ እንዲመችለት የፈጠረው ከንቱ ሃሳብ ነው:: በማለት ስለአስተማሩን የአባ ገብረመድህንም ይህን ድባብ የሸፈነው ነበር::

ንገሩ እንደገና በ1980 ዓ.ም. መጀመሪያ ታድሶ መጣ የህወሃት አባል አባ ገ/መድህን ከአሜሪካ ሱዳን ድርስ መጥተው ስብሃት ነጋ የወቅቱ የህወሃት ሊቀ መንበርና መለስ ዜናዊ ሱዳን ድረስ በመሄድ እንደተገናኙ በድጋፍ መልክም $15,000 የአሜሪካን ዶላር መስጠታቸውን የሄዱት ሁልቱ የወያኔ አመራሮች በድብቅ ሳይሆን በግልጽ የተናገሩት ነበር:: ከዚሁም በተጨማሪ ሱዳን ካርቱም ውስጥ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን አስቀድሰው በውስጡ የሚገኙ ቀሳውስት ካህናት ወደ ህወሃት አባልነት መልምለው በሶስተኛው ቀን ወደ መጡበት መመለሳቸም ተነገረ::ስብሃት ነጋ አቡነ ጳውሎስ የህወሃት መሪህ ባህታ(vanguard) ናቸው በማለት ይጠራቸዋል::

እንግዲህ የአቡነ ጳውሎስ ነገር ይህ ሆኖ ትግሬ በመሆናቸው ብቻም በደርግ መታሰራቸውን ብዙ ግፍ ተፈጸመብኝ የሚሉት አቡነ ጳውሎስ የኢትዮፕያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አባላት እውነት ይሁን አይሁን ለነሱ ልተው:: ከሆነም አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንዋ ላይ በቂም በቀል ማወካቸው ከአንድ መናኝ አባት መፈጸም የሌለበት ፈጽመዋል:: ነብሳቸውም ለሲዖል ተዳርጋለች::

አቡነ ጳውሎስ የፓትርያርኩ ስልጣን አግባብ በሌለው መንገድ የተረከቡት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያናት በምርጥ ካድሬነታቸው በዋልድባና በተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት ብዙ ግፍ ከመፈጸማቸው በላይ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ከየቤተ ክርስቲያኑ በማስወጣት ሸጠዋል::

ይህ ሁሉ በእስልምና ሃይማኖትና በክርስትና መዘዙ ይዞት የመጣው ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የተረገመች ቀን ናት::

ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያውያን እንደተቆጣጠረ ብዙ የዝርፊያ ተቋማት አመቻችቶ ነበር:: አገራችንን የተቆጣጠረው 1. ዋና ኢፈርት 2. ለም የኢትዮጵያ መሬት ለባዕዳን መሸጥ 3. ኢትዮጵያውያን ከተወለዱበትና ካደጉበት መሬት ማፈናቀል 4. ገዢ የሆኑት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ተቋማት በህወሃት ቁጥጥር ውስጥ መዋል 5. ኢትዮጵያዊው የሃገሩ ዳር ድንበር ጠባቂ አማራው ማጥፋት ከዚህም ጎን ለጎን አማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ማጥፋት እና ማክሰም:: 6.የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሀ.አየር ኃይል ለ. ምድር ጦር ሐ.ባህር ሃይል መ.ፖሊስ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ አስወግዶ የራሱን የህወሃትን ታጋዮች ከትግራይ የመጡ ሁሉ የኢትዮፕያ ምድር ጦርና አየር ኃይል ለማድረግ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ በራኡ መዳፍ ውስጥ ለማስገባትና ለመቆጣጠር ደህንነቱም ከላይ እስከ ታች በትግሬዎች ማዋቅር አላማው ነበር::

ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ የወያኔ አመራር መለስና ስብሃት ነጋ ባወጡት እቅድ ተግባራዊ ተደርገዋል::

የኢትዮጵያ ህዝብ በእርሻ የሚተዳደረው መሬቱን ተቀምቶ ለባዕዳን ሳውዲ አረቢያ ፣ ህንድ ፣ እና ለቻይና ወዘተ ህወሃቶች ሸጡት:: በሽያጭ የተገኘው ገንዘብም ሆነ በነ መለስ ዜንዊና ባለቤቱ ወ/ሮ አዜብ እጅ ሲገባ ከመሬቱ የተፈናቀለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በየበረሃው ወድቆ ለክፉ ችግርና መከራ ተዳርገዋል::

ወያኔ ህወሃት በዘር ማጥፋት ወንጀል ተሰማርቶ ህዝበ ኢትዮጵያዊ እያለቀ ነው:: አማርኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ጠላት ነው ብለው ወያኔዎቹ ፈረጁት:: ለመሆኑ የቋንቋ ጠላት አለን?? ይህ ሁሉ በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የመጣ የኢትዮጵያ ህልውና አጠያያቂም ሆነ:: ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ያፈረሰ ህዝብዋንም ለችግር እና ለመከራ የዳረገ በጥቁር ታሪክ የሚመዘገብ የፋሺስት ወያኔ ህወሃት አገዛዝ ስርዓትና የጨለማ ዘመን በማለት ታሪ ዘግቦታል::

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. አንቺ ጥቁር የታሪክ አተላ ቀን የስንቱን ኢትዮጵያዊያን ህይወት በላሽ?! ስንቱን ኢትዮጵያዊ ምሁራን የነጻ ፕሬስ እውቅ ጋዜጠኞች ለስደት ለመከራ ዳረግሽ?! ስንቱን ወጣት ሴት እና ወንድ ከሃገሩ ጠፍቶ የባህር ቀለብ ሆነ:: ስንቱስ በስደት ሂወቱ እየማቀቀ ለክፉ መከራ ተዳረገ:: ስንቱ ቤተ ሰብ አፈናቅለሽ የስንቱን ቤት አፈረሽው:: ወጣት የሴት ህጻናት ሽርሙጥና ዳረግሽ:: አደንዛዥ እጽ እና አሺሽ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ተራ የንግድ ገቢ ሆኖ ወጣቱ ትምህርት ተከልክሎ እቅቀት እና ስልጣኔ በኢትዮጵያ የጠፋበት ዛሬ በኢትዮጵያ ስራ አጥነት የተስፋፋበት የወንጀል ድርጊት በስፋት የሚፈጸምበት ህጻናት በየቆሻሻው የተጣሉ ምግብ አይነት ነክ እየለቀሙ የሚበሉበት የጎዳና ተዳዳሪ ጠዋሪ ማደሪትይ ያጡ ህጻናት ለአቀመ አዳም ያልደረሱ ልጆች ወንድ ሴት ማደሪያቸው በየመንገዱ ሆነ:: ህጻናት በርሃብ በየመንገዱ በየትምህርት ቤቱ አእምሮዋቸውን እየሳቱ የሚወድቁበ እርጉዝ ሴት መኖሪያ አልባ ሆና በየዱር ገደሉ እየወለደች ከተወለዱ ህጻናት ከ10 ህጻናት 6 በ3 እና በ 4 ወራቸው እየሞቱ ህክምና ጠፋ:: ውሃ ጠፋ:: መብራት ጠፋ:: አረ ስንት ጉድ ነው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የወረደው ግፍ::

የወያኔ ህወሃት አባል ድርጅቶች ህወሃት ራሱ የነዚህ ቤተሰብ ልጆች ውጭ አገር እየተንደላቀቁ ሲማሩ ሃገር ውስጥ ያሉ አመራሩ ደጋፊዎች በኑሮ ተንደላቀው በሙስና ተዘፍቀው የሃገር እና የህዝብ ሃብት እየዘረፉ ቀኑ ለነሱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ የችግር ጨለማ መብቱ የተረገጠ ባሪያ ጥዋት ማታ በወያኔ ስርዓት የሚሰቃይ ግዞተኛ ባዕድ ሆኖ ያለበት ዘመን ነው::

ይህ ክፉ አረመኔያዊ የህወሃት አገዛዝ በዚሁ መንገድ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይቀጥል ሁሉ ኢትዮጵያዊ በአንድነት ይነሳ በህዝባዊ ትግል ወያኔን ከስረ መሰረቱ ነቅለን እንጣለው::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

ገብረመድህን አርአያ

አውስትራሊያ

goolgule.com

ወያኔ የፈጠረዉ የፍርሀት ድባብ ሲሰበር . . .

በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚደርሰዉ በደልና መከራ ወለደን ብለዉ ለትግል ጫካ የገቡት ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዉ ከተደላደሉ በኋላ በህዝብ መብትና ነጻነት፤ በአገር አንድነትና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ብሄራዊ ጥቆሞች ላይ ይህ ነዉ ተብሎ ሊነገር የማይችልና ከእነሱ በፊት ከነበሩት መንግስታት ጋር ሲተያይ እጅግ በጣም የከፋ በደል ፈጽመዋል እየፈጸሙም ይገኛሉ። ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዉ የኢትዮጵያን መንበረ ስልጣን ከመቆጣጠራቸዉ በፊት ዕቅድ አዉጥተዉና ተዘጋጅተዉ የመጡት የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፤ በሐይማኖትና በክልል በመከፋፈል በጠመንጃ ኃይል የያዙት ስልጣን በግዜና በህገመንግስት ያልተገደበ መሆኑን ለማረጋገጥና የእኛ ነዉ ለሚሉት የህብረሰተብ ክፍልና ለሚተባበሯቸዉ ሆዳሞች ተቆጥሮ የማያልቅ ሀብት ማጋበስ የሚችሉበትን መንገድ ለመፍጠር ነዉ። የወያኔ መሪዎች ይህንን አገራዊ በደል ያለምንም ተቃዉሞ መፈጸም እንዲችሉ ከአገሩ ይልቅ የተወለደበትን ክልል ብቻ፤ ከብሔራዊ አንድነቱና አጋራዊ ጥቅሙ ይልቅ የራሱን ጥቅም ብቻ የሚመለከትና የእነሱን ኃይለኝነትና የተለየ ጀግንነት እየሰበከ የሚኖር በፍርሀት የተሸበበ ፈሪ ትዉልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

የወያኔ ክፋት፤ ዘረኝነትና “ልማት” በሚል ሽፋን የተደበቀ አገር የማፍረስ ሴራ ከወዲሁ የገባቸዉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ልጆች ከ1997ቱ ምርጫ በፊትም ሆነ በኋላ የወያኔን ገመና ለማጋለጥና የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ፤ ለነጻነቱና ለእኩልነቱ እንዲታገል ለማድረግ እንደሻማ እየቀለጡ ብርሀን ሆነዉ አልፈዋል። ይህ የዕልፍ አዕላፋት የትግል መስዋእትነትና ምሳሌነት ፍሬ እያፈራ መጥቶ በላፈዉ እሁድ ግንቦት 25 ቀን የተካሄደዉንና ወያኔ ከሃያ አመታት በላይ ሲቋጥር የከረመዉን የፍርሀት መቀነት የበጠሰ እጅግ በጣም የሚያበረታታ ትዕይንተ ህዝብ እንዲደረግ አስተዋጽኦ እድርጓል፡፡ ይህ ባለፈዉ እሁድ የተካሄደዉ ሰላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስተባብሩት፤ አቅጣጫ የሚያሳዩትና ጉያዉ ዉስጥ ገብተዉ እያበረታቱ የሚመሩት መሪዎችን ካገኘ እንኳን ምንም አይነት ህዝባዊ መሠረት የሌለዉን ወያኔን የመሰለ ፀረ ህዝብ ሃይል ቀርቶ ለማንም የማይበገር ህዝብ መሆኑን ያስመሰከረ ሰልፍ ነዉ።

በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራዉና የብዙ ኢትዮጵያዉያንን ይሁንታ ያገኘዉ የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ወያኔ ያስረናል ወይም ይገድለናል እየተባለ አላግባብ እየተፈራ በቀጠሮ ሲተላለፍ የቆየዉን ህዝባዊ ትግል ከፍርሀትና እንደ ገመድ ከረዘመ ቀጠሮ ዉስጥ በጣጥሶ ያወጣና የህዝብን የትግል መንፈስ ያነቃቃ ሰላማዊ ሰልፍ እንደነበር በሰልፉ ላይ የታየዉ የህዝብ ስሜትና ለኢትዮጵያ ህዝብ የተላለፉት መልዕክቶች በግልጽ ይናገራሉ። ባለፈዉ እሁድ በተደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የታየዉ ህዝብዊ መነሳሳት ሊበረታታ የሚገባዉና እንዲሁም በአገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵየዉያን የመብትና የነጻነት ትግላቸዉ አካል አድርገዉ ሊቀላቀሉት፤ ሊረዱት፤ሊተባሩትና ህዝባዊ ትግሉ የሚጠይቁዉን አመራር ሊሰጡት የሚገባ እጅግ በጣም አበራታች ጅምር ነዉ። ለትግልና ለመስዋዕትነት ዝግጁ የሆነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ያጣዉ መሪ ነዉ እያልን አግባብ የሌለዉ ጩከት ከመጮህ ይልቅ አገራችንን የምንወድ የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ መሪዎችን በትግል ሂደት ዉስጥ የምንፈጥረዉ እኛዉ እራሳችን መሆናችንን ተረድተን ይህንን የሚያበረታታ ተስፋ የሰጠንን ሰላማዊ ሰልፍ የምናጠናክርበትንና ተከታታይነት ኖሮት ብዙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያካትትበትን መንገድ ልንቀይስ ይገባል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ቢሆን ለመብቱ፤ለነጻነቱና ለአንድነቱ ማናቸውንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ባለፈዉ እሁድ በግልጽ አሳይቷል። አሁን የሚቀረዉ ህዝባዊ ትግሉን የመምራት ታሪካዊ ሀላፊነት የወደቀበት የህብረተሰብ ክፍል ጨርቄን ማቄን ማለቱን ትቶ ወቅቱ የሚፈልገዉን የትግል አመራር መስጠት ብቻ ነዉ።

ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ አንዴ የታጠቀዉን ጠመንጃ በመጠቀም ሌላ ግዜ ደግሞ ፓርላማዉንና የህግ ተቋሞችን ተጠቅሞ ተቃዋሚ ኃይሎችን የሚያጠፋ ህግ በማዉጣት የኢትዮጵያን ህዝብ የፍትህና የነጻነት ፍላጎት ለማፈን ብዙ ጥሯል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ እራሱን “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ” ትዉልድ ብሎ በመጥራት ህዘብ በፍርሃት ጨለማ ዉስጥ እንዲኖር ለማድረግ ብዙ ታግሏል። ቆራጡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ስድቡን፤ ንቀቱን፤ እስራቱን፤ግድያዉንና ስደቱን እንዳመጣጡ መክቶ በፍርሀት ዉስጥ የማይኖር ህዝብ መሆኑን ባለፈዉ እሁድ ለወዳጁም ለጠላቱም በግልጽ አሳይቷል። ይህ እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓም አዲስ አበባ ዉስጥ የታየዉ የትግል መነሳሳት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በማቀፍ ወያኔና በጠመንጃ ኃይል የመሰረተዉ ዘረኛ ስርአቱ እስከተወገዱና ኢትዮጵያ ፍትህ፤ ነጻነትን ዲሞክራሲ የነገሱባት ምድር እስክትሆን ድረስ መቀጠል ይኖርበታል፤ ይህንን ለማድረግ ደግሞ በአገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ እንደ አንድ ሰዉ ቆሞ መታገል ይኖርበታል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

 

የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ

“ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ”

ጎልጉል የድረ-ገጽ ጋዜጣ

በነበራቸው የስራ ሃላፊነት በድብቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ቆይተው ለመንግስት ካጋለጡ በኋላ ራሳቸውን ደብቀው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ ምሳ እየተመገቡ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ ተስፋዬ ሰኞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር።

Allegations of Corruption Emerge Against Federal Government Examiners

Former Gambella Regional President, Mr. Omot Obang Olom

በቅርቡ ወደ ፌደራል መንግስት የተዛወሩት የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኡሞት ኦባንግ፣ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር በማደራጀት ለኢህአዴግ ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ አሟሟታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን፤ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ መረጃዎች ናቸው። መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” በሚል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ በ (ጥቅምት 19፤2005/October 29, 2012) መዘገቡ ይታወሳል

ቀደም ሲል የጋምቤላ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ከላይ የተጠቀሰውን የሙስና ወንጀል በማጋለጣቸው ጋምቤላ መኖር ሳይችሉ ቀርተው ራሳቸውን ሸሽገው ለመኖር ተገደው እንደነበር የሚያውቋቸው ለጎልጉል አስረድተዋል።
“አቶ ተስፋዬ ሙስናን በማጋለጣቸው በፍርሃቻ ራሳቸውን ደብቀው ሊኖሩ አይገባም” በማለት ኢህአዴግ ከለላ እንደሚሰጣቸው ቃል በገባላቸው መሰረት ከተሸሸጉበት የወጡት አቶ ተስፋዬ ሰንጋተራ ትንሳዔ ሆቴል ከጋምቤላ ልጆች ጋር መገናኘት ይጀምራሉ።

ባለፈው ሳምንት ከፌዴራል የጸረ ሙስና ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ ከያዙ በኋላ ኮሚሽነሩ በድንገት ለለቅሶ ወደ ጎንደር በመሄዳቸው ቀጠሮው ለሳምንት ይራዘማል። ለሰኞ (ሰኔ10፤2005) አዲስ ቀጠሮ ይይዛሉ።

በስልክ ያነጋገርናቸው ትንሳዔ ሆቴል አካባቢ እንደነበሩና ለጉዳዩ ቅርበት እንዳላቸው የሚገልጹ የጋምቤላ ተወላጅ የስራ ሃላፊ እንዳሉት አቶ ኦሞት ኦባንግ ለአቶ ተስፋዬ ስልክ ደውለው ነበር። አቶ ተስፋዬ ህይወታቸው ከማለፉ ሁለት ቀን በፊት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኦሞት በስልክ ተማጽንዖ አቅርበው ነበር።

አቶ ኦሞት “እውነት ነው ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀጠሮ የያዝከው?” በማለት ይጠይቃሉ

“አዎ! እውነት ነው” በማለት አቶ ተስፋዬ መልስ ይሰጣሉ።

አቶ ኦሞት መልሰው “እንግዲያውስ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከመግባትህና ከማነጋገርህ በፊት ሁለታችን መገናኘት አለብን። የምንነጋገረው ነገር አለ” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። አቶ ተስፋዬ ስለ ስልክ ልውውጡ እንደነገሯቸው የተናገሩት እኚሁ ሰው፣ አቶ ኦሞት በስልክ ደጋግመው በመደወል ያቀረቡትን የ”እንነጋገር” ጥያቄ አቶ ተስፋዬ አልቀበልም ይላሉ።

ጋምቤላ ስራቸውን ለቀው ራሳቸውን ደብቀው የኖሩት በእርሳቸው ምክንያት መሆኑን፣ ፍትህ እንደሚፈልጉ፣ አሁን ለመነጋገር ጊዜው እንዳልሆነ፣ ዘርዝረው ለአቶ ኦሞት መናገራቸውን ያወሱት የጎልጉል ምንጭ፣ ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው አቶ ኦሞት በንዴት ተዛልፈው ነበር።

ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው እንግዲህ አቶ ተስፋዬ ትንሳዔ ሆቴል ሰዎችን በመላላክና በመታዘዝ ከሚኖር አንድ የጋምቤላ ሰው /አቶ ተስፋዬ የሚረዱት በምግባር ጉዳይ የሚታማና ጸበኛ የሚባል ሰው ነው/ አብረው ተቀምጠው ምሳ እየበሉ ሳለ አቶ ተስፋዬ አረፋ ይደፍቃቸዋል። ወዲያው ከተቀመጡበት ተንሸራተው መሬት ይወድቃሉ። ቀጥሎም ሰውነታቸው ይዝልና ኮማ ውስጥ ይገባሉ። ከአፋቸው እየተዝለገለገ የሚወጣው ፈሳሽ በመጨመሩና የተለያየ ርዳታ ቢደረግላቸውም ሊተርፉ ስላልቻሉ ሆስፒታል ተወስደው ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።

አቶ ተስፋዬ ሆስፒታል ከመድረሳቸው በፊት እንደሞቱ የሚናገሩት የጎልጉል ምንጭ አሟሟታቸው ከመርዝ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ በሙስና ወንጀል ላይ ያሰባሱትን መረጃ ለተለያዩ አካላት የበተኑ ስለሆነ እሳቸውን በመግደል ማድበስበስ እንደማይቻል አስታውቀዋል። አቶ ተስፋዬ ሙስና ካጋለጡ በኋላ መሰወራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው። በተያያዘ በጋምቤላ ኢንቨስትመንት ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ውስጥ ከ70በመቶ በላይ የሆኑት የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች የነበሩና የክልል አንድ ተወላጆች መሆናቸው የአቶ ተስፋዬን አሟሟት ይበልጥ ውስብስብ እንዳደረገው አስተያየት እየተሰጠ ነው፡፡

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ “የአቶ ተስፋዬ ሞት አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ” በማለት ስለ አቶ ተስፋዬ ሞትና አሟሟት መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።

“አቶ ተስፋዬ ለእውነት ሲል ሞቷል። ኢህአዴግ ውስጥ በርካታ የወንጀል መረጃ ያላቸው ወገኖች አሉ። እንዲህ ያሉ ዜጎች በየትኛውም ዘመን አይረሱም። የቀን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ስማቸውና ታሪካቸው ከጨዋነታቸው ጋር ተመልሶ ህያው ይሆናል። ሌቦችና ነፍሰገዳዮች ወደ ህግ ሲያመሩ፣ እንደ አቶ ተስፋዬ አይነቶቹ የመጪው ትውልድ ታላቅ ምሳሌ ሆነው እየተወደሱ ህያው ሆነው ይኖራሉ” የሚል አስተያየት የሰጡት አቶ ኦባንግ፤ አቶ ተስፋዬ ያሰባሰቧቸው የሙስናና ተመሳሳይ ወንጀሎች ማሳያ ሰነዶች እጃቸው ላይ ስላለ አቶ ተስፋዬን በመግደልና በማስገደል ወንጀል ማድበስበስ እንደማይቻል ተናግረዋል።

የአቶ ተስፋዬ የቀብር ስነስርዓት ጋምቤላ መፈጸሙን ለመረዳት ተችሏል። ቤተሰቦቻቸውን በማግኘት ሆስፒታሉ ስለ አሟሟታቸው የሰጠውን አስተያየት ጠይቀን ለመረዳት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም።

 

 ECADF.COM

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ (መንግስት ለሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥ አሁንም እንጠይቃለን!)

ሰማያዊ ፓርቲ

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በርካታ ሕዝብ በተገኘበት ደማቅ ሆኖ ተካሂዷል፡፡ ለዚህ ሰልፍ መሳካት ከፍተኛ ድጋፍና አስተዋፅኦ ላደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የመገናኛ ብዙኃንና በሰልፉ ለተሳተፉ ዜጎች እንዲሁም ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ለረዱ የፀጥታ ኃይሎች ፓርቲያችን ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡Blue Party Ethiopia

ከዚህ በተቃራኒ ግን ይህንን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የገዥው ፓርቲ ባለስልጣናትና የመንግስት ተወካዮች የተለመደውን ተልካሻ አስተያየቶች ሰጥተዋል፡፡ የገዥው ፓርቲ ተወካይ ሰልፉን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት “የሐይማኖት አክራሪነት አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ድብቅ አጀንዳው ገሃድ ወጣ” በማለት በሰጡት አስተያየት ፓርቲውን ለማንቋሸሽና ለማራከስ ሞክረዋል፡፡ ይህም ፓርቲውን በእጅጉ ያስቆጣ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ መሰረተ ቢስ ፍረጃ የገዥው ቡድን አባላት ለንግግራቸውና ለሚሰጡት አስተያየት ሚዛን የሌላቸው ከመሆኑ ውጭ በፓርቲው ፕሮግራምም ሆነ እንቅስቃሴ ከአሸባሪነት ጋር የሚያገናኘውን አንዳችም ነገር አልጠቀሱም፡፡ ፓርቲው በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ እና በሕገ መንግስቱ በተሰጠው መብት ተጠቅሞ በሕጋዊ ሥነስርዓት ያደራጀውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በእንዲህ አይነት መንገድ መፈረጅ ሰልፉ ከተጠራበት ዓላማና መንፈስ በእጅጉ የራቀ አስተያየት ሆኖ አግኝቶታል፡፡

ፓርቲው ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ በሰጣቸው መግለጫዎች በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነት መቃወሙ ይታወሳል፡፡ ይህንኑ ጥያቄ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ወደ አደባባይ ይዞ መውጣቱ ሕገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ መሆኑን ይገነዘባል፡፡ ከባለሥልጣኑ የተሰጠው አስተያየት ግን የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ዜጎች በሰላማዊ መንገድ የተቃውሞ ጥያቄ ማቅረባቸውን ገዥው ፓርቲ በበጎ ጎን አለማየቱንና የመብት ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ሁሉ ወደ ሽብርተኝነት ፍረጃ ለመክተት የሚያደርገውን ጥረት የሚያመላክት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በተጨማሪም ገዥው ፓርቲ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ኢትዮጵያውያን ዜጎች እንደሆኑ አድርጎ እንደማያያቸውም ሰማያዊ ፓርቲ ተገንዝቧል፡፡

የመንግስት ተወካይ የሆኑት ባለስልጣን በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት በሰላማዊ መንገድ ተጠይቆና ታውቆ መንግስት ራሱ ያመነውና እጅግ ሰላማዊ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲካሄድ ያደረገን ፓርቲ ውጭ የሚገኙ ኃይሎች ተላላኪ አድርጎ ማቅረብ የአብዬን ወደእምዬ እንደሚባለው መሆኑን እየገለፅን ይልቁንም በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀሰውን ፓርቲያችንን መንግስት ከልቡ ሊቀበለው እንዳልቻለ አስገንዝቦናል፡፡ በተጨማሪም ይህ አባባል ሰማያዊ ፓርቲን የማይመጥን፤ ፓርቲውም በተግባር እያሳየ ያለውን ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚጥስ በመሆኑ አጥብቀን እናወግዘዋለን፡፡ እኝሁ የመንግስት ባለስልጣን በሰላማዊ ሰልፉ የተላለፉት መልዕክቶች ህገ መንግስቱን የሚንዱ ናቸው በማለት በደፈናው ህዝብን ለማታለል ከመሞከራቸው በተለየ የትኛው ሃሳብ የትኛውን የሕገ መንግስት ድንጋጌ እንደሚፃረር ካለማመልከታቸውም በላይ ፓርቲው በፍርድ ቤት ጉዳይ ጣልቃ እንደገባ አድርጎ ለማሳየት መሞከር የመንግስትን ግብር ለሰማያዊ ፓርቲ መስጠት ከመሆኑም ሌላ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ያደርገዋል፡፡

በመጨረሻም የእስልምና እምነት ተከታይ ዜጎቻችን ማንኛውንም የመብት ጥያቄ ከሌሎች ወገኖቻቸው ጋር በሰላማዊ መንገድ የማቅረብ ሕገ መንግስታዊ መብታቸው መሆኑን መንግስትም ሆነ ገዥው ፓርቲ እንዲያውቀው እያሳሰብን፤ ሰማያዊ ፓርቲ ከመንግስትም ሆነ ከገዥው ፓርቲ በሚሰጥ ማንኛውም ማስፈራሪያ ከጀመረው የሰላማዊ ትግል ጉዞ ፍፁም ወደ ኋላ እንደማይል፤ ይልቁንም የተነሱትን የሕዝብ ጥያቄዎች መንግስት በሦስት ወራት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥ አሁንም በድጋሚ ማሳሰብ እንፈልጋለን፡፡

ግንቦት 29 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

 Ecadf.com

የአዲስ አበባ ልጆች አኮራችሁኝ!

እንደልቡ (ዳግም)

“ወጣቱ እንዲህ ሆንዋል እንዲያም ሆንዋል…” ወጣቱን ከማያውቁት ሰዎች የምሰማው የዘወትር መዝሙር ነበር። ወጣቱ ግን ማን እንደሆነ ባገኘው አጋጣሚ አስመሰከረ!!! ነጻነት የሌለው ህዝብ በበረት ዉስጥ እንደታጎረ እንስሳ ነው፣ ይህም ከፍተኛ የመዋረድ ስሜት ይፈጥርና አምሮን ይጎዳል፣ በሞራል ላይ ተመርኮዘን ማድረግ ከሚገቡን ነገሮች ሳናውቅ እንቆጠባለን፣ ውሸታም እና አስመሳይም እንሆናለን… ስለዚህ ነጻነታችንን ማስመለስና በራሳችን የምንተማመን ኩሩ ዜጋ መሆናችንን ማረጋገጥ እጅግ አስፈላጊ ነው።

ይህን የተገነዘቡት በካሊፎርኒያ የፖለቲካ ሳይንስ አስተማሪ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች ስለ ነጻነት፣ ክብርና ሞራል ሲያስተምሩ አይደክማቸውም… እነሆ ለነጻነታቸው ቀናኢ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ በህብረት ስለነጻነታቸው ሲዘምሩ የተመለከቱት ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም ብዕራቸውን አነሱ… እንዲህም አሉ፣

The long youth march to freedom and dignity has begun in Ethiopia. It is beautiful. It is beautiful because it is peaceful. It is beautiful because it is motivated by love of country and love of each other as children of one Mother Ethiopia. It is beautiful because Ethiopia’s youth in unison are shouting out loud, “We can’t take anymore! We need change!” History shall record that on Ginbot 25, 2005 Ethiopia rose from the pit she has fallen into on the wings of her youth.

የፕሮፌሰር አለማየሁን ሙሉ ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Over one hundred thousand young men and women marched in the streets of Addis Ababa

On Ginbot 25, 2005, over one hundred thousand young men and women marched in the streets of Addis Ababa demanding the release of political prisoners, religious freedom, respect for human rights and the Constitution and public accountability.

ECADF.COM

ኢሳት ጋዜጠኞች ጆሮ ላይ ስልክ ለምትዘጉ ባለስልጣኖች ማሰጠንቀቂያ

እስከ ነጻነት

መረጃ የማግኘት መብት የስብዓዊ መብት ዋናው መሰረት ነው፡ መረጃ የማግኘት መብት ዋናው የሰብዓዊ መብት ምሰሶ መሆኑን የሃገራት ደርግ (League of Nations) የደነገገው በ1946 ዓ.ም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነበር፡ ያደጉ ሃገራት ይህንን መብት በሚገባ ይጠቀሙበታል፡ ገልብጦ መጻፍ እንጂ ማንበብ የማይችልው የወያኔ ዘረኛ ስርዓትም ይህንኑ መብት በህገመንግስቱ ላይ አሰቀምጦታል። ለነገሩ ያላሰቀመጠው ነገር የለም ግን ማን አንብቦት ተግባራዊ ያደርገዋል እንጂ። ተግባራዊ እየሆነ ያለው ዘርን ለማጥፋት የተወጠነው የጫካው ህጋቸው ብቻ ነው።

ይህን እዚሁ ላይ ላቁምና ወደተነሳሁበት ልመለስ፤ የውነትም ይሁን የውሸት ስልጣን ይዛችሁ መረጃ ስትጠየቁ ስልክን ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ የምትዘጋ፤ የምትዘጊ፤ የምትዘጉ ግለሰቦች ወንጀል መሆኑን ካልተገነዘባችሁ እንድትገነዘቡት ላስታውሳችሁ አወዳለሁ፡የእሳት ጋዜጠኛ መረጃ ሲጠይቃችሁ ጆሮው ላይ ስትዘጉ፡ የዘጋችሁበት መሳይ፤ ፋሲል፡ ሲሳይ ወይም፡አንድ የእሳት ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ ሳይሆን የ90 ሚሊየን የኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ ላይ መሆኑን ልብ ካላላችሁ ላስታውሳችሁ፡ ለያንዳንዷ ለዘጋችሗት ስልክ የምትጠየቁ መሆኑን ደግሜ ደጋግም ላስገነዝባችሁ እወዳለሁ።

በእርግጥ አማራ ነን ብላችሁ አማራ ህዝብን የምታስፈጁት፤ ኦሮሞ ነን ብላችሁ የኦሮሞን ደም የምታፈሱት፤ ኢሳ ሆናችሁ የኢሳን ህዝብ የምታስፈጁት ሌሎቻችሁም የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ካድሬ ከላይ ተጭኖ እንደሚያዛችሁ አለም የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡ ምናልባትም ለእሳት መረጃ ለመስጠት የፍርሃት ቆፈን ቀፍድዷችሁ ሊሆን ይችላል። ፈቃደኝነቱ ኖሮ ችግራችሁ ፍርሃት ከሆነ መረጃውን ለሌላ ለምታምኑት ሰው አቀብላችሁ መረጃ የሰጣችሁትን ስው ስልክ ቁጥር ለእሳት ጋዜጠኛ ልትነግሩ ትችላላችሁ፡ ሲሆን ሲሆን አንድ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ጨባጣ ካድሬ እንደ አውራ ዶሮ ሲንቀባረርባችሁ እንደ ሲካካ ዶሮ እኔ እኔ እያላችሁ ከመሽቀዳደም በጋራ ማሰወገድ ትችሉ ነበር፡ይህ ባይሆን እንኳ የወገናችሁን ሰቆቃ እና የወያኔን ሚስጥራዊ ወንጀል ማጋለጥ ከናንተ የሚጠበቅ ትንሹ ተግባር መሆን ሲገባው ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ ስልክ ትዘጋላችሁ።

እስኪ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ በተለይ አማራ ነን ያላችሁ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር መጋዣዎች፤ አማራን ለማጥፋት በተግባር እቅዱ ላይ ነድፎ የሚንቀሳቀስ ድርጅት እናንተን እንደማይበላችሁ ማረጋገጫችሁ ምንድነው? መረጃውን እዚህ ላይ አንብቡት አሁን በሙስና ተብለው የታሰሩት በርግጥ በሙስና ነው? እናነተስ ነገ ወደቃሊቲ ላለመላካችሁ ዋስትናችሁ ምንድነው? ስለዚህ ቀኑ ሳይመሽ ወደ ህሊናችሁ ተመልሳችሁ ወደ ወገናችሁ ተደባለቁ። ይህ ጥሪ ላማራ ብቻ አደለም፤ ለኦሮሞ፤ ለሲዳማ፤ ለኦጋዴን፤ ለአፋር፤ ለሲዳማ፤ በአጠቃላይ ወያኔ በየቦታው የወዘፋችሁ ባለስልጣናትን ሁሉ ይመለከታል፡ ይህ ሁሉ ሳይሆን ቀርቶ፤ ጋዜጠኛ ጆሮ ላይ ስልክ እየዘጋችሁ የወያኔን ወንጀል ደብቃችሁ ቀኑ ከመሸ እያንዳንዳችሁ ከተጠያቂነት እንደማታመልጡ መረዳት አለባችሁ፡ ወያኔ እንኳን የናንተን ገመና ሊሸፍን የራሱን ገመና መሸፈን የማይችል የፍየል ጅራት መሆኑ አይናችሁን ካልጨፈናችሁ በስተቀር በግልጽ የሚታይ ጉዳይ ነው።

በህግ ስላላወቅሁ ነው የሚባል ነገር እንደሌለና ለሰራችሁት ወንጀል ሁሉ ተጠያቂ መሆናችሁን አስረግጬ እዚህ ላይ ላብቃ።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

 

 ECADF.COM

ምርጫ የለም እንጂ ምርጫማ ቢኖር …!

በፍቅር ለይኩን

የዛሬው ጽሑፌን በምርጫ ዙሪያ ካጋጠመኝ ትንሽ ቆየት ካለ ገጠመኜ ልጀምር፡፡ በደቡብ አፍሪካዊቷ ቢዝነስ ከተማ ጆሐንስበርግ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በትውልድ ደቡብ አፍሪካዊ የሆኑ ካህን፣ አባትና አገልጋይ የሆኑ በ60ዎቹ መጨረሻ ዕድሜ ላይ የሚገኙ አንድ አዛውንት አባት አሉ፡፡

እኚህ አዛውንት ካህን ስማቸው ፋዘር ዲሊዛ ኔልሰን ቫሊዛ ሲሆን፤ በኢትዮጵያውያን የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና ምእመናን ዘንድ ደግሞ በክህነት የማእረግ ስማቸው መልአከ ሰላም ዲሊዛ ቫሊዛ በመባል ይጠራሉ፡፡ ታዲያ ፋዘር ዲሊዛ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ፣ ስለ ኢትዮጵያውያንና ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አውርተው፣ ተናግረው የሚጠግቡ ሰው ዓይነት አይደሉም፡፡

ከኬፕታውን ከትምህርት ቤት በመዘጋቱ ለእረፍት ወደ ጆሐንስበርግ መጥቼ ነበር፡፡ በጆሐንስበርግ መድኃኔ ዓለም ካቴድራል በነበረኝ የመንፈሳዊ አገልግሎት ቆይታዬም ከእኚህ አዛውንት አባት ጋር ከመንፈሳዊና ከሃይማኖታዊ ጉዳዮች ባሻገርም በበርካታ በአገራችንና በደቡብ አፍሪካ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በተለያዩ አጋጣሚዎች አብዝተን እንወያይ ነበር፡፡

ፋዘር ዲሊዛ በየትኛው አጋጣሚ ለሚያገኟቸው ኢትዮጵያውያንም ሆነ የውጭ አገር ዜጎች ሁሉ አዘወትረው የሚናገሩት አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም ለዛሬው ነፃነታችን፣ ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ የዘረኝነት መድሎ ለሌለበት ፍትሐዊ ሥርዓት እውን መሆን እናንተ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ድርሻ አላችሁ በማለት በአድናቆትና በልዩ የደስታ መንፈስ ውስጥ ሆነው ምስክርነታቸውን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይሰጣሉ፡፡

በአንድ ወቅት ከፋዘር ዲሊዛ ጋር ባደረግነው ውይይት እኚህ አዛውንት አባት በአገራቸው ደቡብ አፍሪካ ለሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ (Local Government Election) ከጆሐንስበርግ ከ1000 ኪ.ሜ. በላይ ወደሚርቀው የውቅያኖስ ጠረፏ የትውልድ አገራቸው ፖርት ኤልዛቤት ለመሄድ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ አንዳች ጉጉት በሚንጸባረቅበት ልዩ ስሜት ውስጥ ሆነው አጫወቱኝ፡፡

እኔም በመገረም ሆኜ እንዴ …! ፋዘር እንዴት ለአካባቢ ምርጫ ሲሉ ይህን ያህል ርቀት፣ ይህን ያህል ብዙ ብር የትራንስፖርት ወጪ አውጥተው ይሄዳሉ?! ደግሞስ እርስዎ አሁን አርጅተዋል፣ ለምን እንዲህ በመንገድ ይደክማሉ፤ ባለቤትዎና ልጆችዎ ከመረጡ በቂ አይደለም እንዴ …?! አልኳቸው፡፡

አዛውንቱ ካህን ለምርጫ ወደ ትውልድ መንደራቸው ለመሄድ ጓዛቸውን እየሸከፉ መሆናቸውን መስማቴና እርሳቸውም የጉዞአቸውን ስላረጋገጡልኝ በጣሙን ግርምትም አድናቆትም አጭሮብኝ፡፡ ፋዘር ዲሊዛ ግርምት ለተሞላበት ጥያቄዬና አስተያየቴ ሲመልሱልኝም፡-

አይ ልጄ ይህ የመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብቴ በብዙ ዋጋ፣ በእልፎች ክቡር ደምና መሥዋዕትነት የተገኘ ልዩ መብት ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ከእናት ቤተ ክርስቲያናችን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ፈጽሞ እንዳንገናኝ ዘረኛው የአፓርታይድ መንግሥት የገነባው የመለያየት ግንብ የተናደው ፓርቲዬ ኤ.ኤን.ሲ፣ በበርካታ የደቡብ አፍሪካውያን የነፃነት ፋኖዎች እና ለሰው ልጆች ነፃነትና እኩልነት ቀናኢ በሆኑ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮችና ሌሎች አጋሮቻችን ጭምር ነው፡፡

እናም ልጄ በዚህ ምርጫ በመምረጥም ሆነ በመመረጥ ለመሳተፍም ሆነ ላለመሳተፍ አንተ እንደምትለው የዕድሜዬ መግፋት፣ በቦታ ርቀት፣ በገንዘብ ወጪ ፈጽሞ የሚተመን አይደለም፡፡ ይህ በምንም በማይተመን በብዙዎች የሕይወት መሥዋዕትነት የተገኘ ልዩና ክቡር መብት/መብቴ ነው፡፡ እናም መብቴን በሕይወት እሳካለሁ መጠቀም አለብኝ፡፡

አየህ አሉኝ ፋዘር ዲሊዛ ንግግራቸውን በመቀጠል በአትኩሮት እየተመለከቱኝ አየህ ልጄ የእኔ አንድ ድምፅ ለፓርቲዬ ድልም ሆነ ሽንፈት ወሳኝነት አለው፤ ስለሆነም ለዘመናት ለታገልንበትና የበርካታ አባቶቻችን ክቡር ሕይወት ተከፍሎበት አገሬ ደቡብ አፍሪካ ዛሬ ለደረሰችበት ሰላም፣ ብልጽግና፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደት እውን መሆን ማረጋገጫው በዚህ ያለማንም አስገዳጅነት በራሴ ፍላጎት፣ ወድጄና ፈቅጄ የምሳተፍበት ይህ ፍትሐዊ የሆነ የአካባቢ ምርጫ አንዱ ነው፡፡

እናም ልጄ ምንም ተአምር ቢፈጠር በሕይወትና በጤና እሳካለሁ ድረስ ለምርጫ ወደ ትውልድ መንደሬ ከመሄድ የሚያግደኝ ነገር አይኖርም በማለት ፈርጠም ብለው መለሱልኝ፡፡ አዛውንቱ ካህን በዚህ የዕድሜያቸው መጨረሻ እንኳን በስስት የሚያዩት የመምረጥና የመመረጥ መብታቸው ላይ ያላቸው ስሱነትና ፖለቲካዊ ንቃታቸው (Sensitivity and political consciousness) በእጅጉ አስገረመኝ፣ አስደመመኝም፡፡

በፋዘር ዲሊዛ ቫሊዛ መልስ የበዛ አድናቆትና ግርምት የተጫረብኝ ኢትዮጵያዊው እኔ ወደኋላ ዘወር ብዬ በበርካታ አፍሪካ አገሮችና በመላው ዓለም የነፃነት ሰንደቅ ተደርጋ በምትታየው ኢትዮጵያ፣ የአገሬን የምርጫ ታሪክና ዲሞክራሲዊ ግንባታ ሂደት ለመታዘብ ይህ ጥቂት የቆየ ገጠመኜ ዕድሉን ፈጠረልኝ፡፡ እናም ከዚህ ገጠመኜ በመነሳት ይህችን አጠር ያለች ትዝብት አዘል ጽሑፍ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተካሄዱት የአካባቢ፣ የቀበሌና የወረዳ ም/ቤቶች ምርጫ ዙሪያ በመመርኮዝ ጥቂት ነግሮችን ለማለት ወደድኩ፡፡

በዘመኔ የደረስኩበት፣ በሙሉ ልቤ የምመሰክርለትና በንቃትም የተከታተልኩት ምርጫ ቢኖር በአገር አቀፍ ደረጃ ተካሄደው የ1997ቱ ምርጫ ነው፡፡ ከዛን በፊት ስለ ምርጫ፣ ስለ መምረጥና ስለ መመረጥ መብት ለማወቅም ሆነ ለማገናዘብ የነበረኝ ፖለቲካዊ ንቃትና ዕድሜዬም ደረጃም ብዙም የሚፈቅድልኝ አልነበረም፡፡ እናም የትዝብቴ ዋና ትኩረት የሚሆነው ምርጫ 97ን ተመርኩዞ ከሰሞኑ በተካሄደው የአካባቢናና የወረዳ ምክር ቤት ምርጫ ላይ ነው፡፡

በዘንድሮው የአካባቢና የወረዳ ምክር ቤት ምርጫ ላይ በጥቂቱ ትዝብቴን ለማካፈል የ1997ቱን ምርጫ እንደ መነሻ ወይም መንደርደሪያ አድርጌ ለመውሰድ የተነሣሁበት የራሴ የሆነ ምክንያት ስላለኝ ነው፡፡ ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የ1997ቱ ምርጫ በእኔ ብቻ ሳይሆን በብዙ ኢትዮጵውያን ልብ ውስጥ የማይረሳ ውብም አስቀያሚም የሆነ መቼም ማይረሳን ትዝታ ትቶ አልፏል፡፡

1997ቱ ምርጫ ምንም እንኳን ፍጻሜው ባያምርም የምርጫው ጅማሬና ሂደት መላው ኢትዮጵያውያንን ከሊቅ አስከ ደቂቅ፣ ከአፈ ነቢብ እስከ ምሁር፣ አለቃን ከምንዝር ሳይለይ ሁሉንም ኅብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ ምድሪቱን ከዳር እስከ ዳር ያነቃነቀና መላውን ዓለም ጭምር ያሰደመመ ነበር፡፡

ሚንጋ ነጋሽ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ምሁር Ethiopia’s Post Election Crisis: Institutional Failure and The Role of Mediation በሚል አርዕስት በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ከተማ በሚገኘው Witwatersrand ዩኒቨርስቲ ባቀረቡት የጥናት ወረቀታቸው፣ ምርጫ 97 በአገራችን ምርጫ ታሪክ ውስጥ ትልቅና ጉልህ የሆነ ታሪካዊ ክስተት ሆኖ ማለፉን እንዲህ በማለት ነው በጥናታዊ ጽሑፋቸው የገለጹት፡-

The 1997 elections marked an historic event in the country, as Ethiopia witnessed its first genuinely competitive campaigns period with multiple parties fielding strong candidates.

በወቅቱ ምርጫውን የታዘበው ካርተር ምርጫ ታዛቢ ቡድን ማእክልም ባወጣው ባለ69 ገጽ ሪፖርቱ እንደገለጸው፣ በምርጫ 97 ወቅት ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይ የነበራቸውን ሁሉን አቀፍ ሕዝባዊ ተሳትፎና ትልቅ መነቃቃት በተመለከተ ሲገልጽ፡-

The May 2005 election was started against the backdrop of tensions and unprecented level of public political consciousness. … Voters had a genuine choice in Election Day and responded with enthusiasm and high turnout. 

1997ቱ ምርጫ አንፃር የዘንድሮውን ምርጫ ሂደት የታዘቡ ብዙዎች ዋ ምርጫ!፣ ዋ የምርጫ ፉክክርና ውድድር!፣ ወይ የምርጫ ነገር፣ ወይ ነዶ … በማለት ቁጭታቸውንና ብሶታቸውን የገለጹበትን አጋጣሚ ትቶ ነው ያለፈው፡፡ አንዳንዶችም በማኅበራዊ ድረ ገጾች ባሰነበቡት ምጸትን የተሞላ ሰም-ለበስ ግጥማቸው እንዲህ በማለት ነበር የዘንድሮውን የኢህአዴግን የምረጡኝ አማርጡኝ ደፋ ቀና የአካባቢና የወረዳ ምርጫ ግርግርን እንዲህ የተቀኙበት፡-

ምርጫ የለም እንጂ ምርጫ ቢኖር፣

ኑ ምረጡን የሚለን ‹‹ካድሬ›› ባላሻን ነበር፡፡

1997 ምርጫ በኋላ የተካሄደው የ2002ቱ ምርጫ ከ1997ቱ ምርጫ በሁሉ ነገር አንሶና ኮስሶ ነበር የታየው፡፡ በእርግጥ ኢህአዴግ ከ97ቱ ምርጫ ስህተት በወሰደው ትምህርት ራሱን በሚገባ አጠናክሮ፣ ከሕዝቡ ጋር ለመገናኘት ተከታታይ የሆኑ ሰፊ ዘመቻዎችን በማድረግ በፍቅርም በጉልበትም መጪው ዘመን የእርሱና የእርሱ ብቻ እንዲሆን የተለመው እቅዱን ፈጽሟል ማለት ይቻላል፡፡

ይሁን እንጂ በ2002ቱ ምርጫ ላይ የነበረው ሕዝባዊው ተሳትፎው በአብዛኛው የቀዘቀዘ፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከገዢው ፓርቲ የተለመደ ወከባና በትር ያላመለጡበት፣ በተሳትፎ ረገድም መሳሳት የታየበት፣ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግም99.6 በመቶ ምርጫውን ያሸነፈበትን ይህን መሬት አንቀጥቅጥ የሆነ ድሉን ለራሱና ለደጋፊዎቹ የዘከረበትና ያዘከረበት ምርጫ ሆኖ ነበር ያለፈው፡፡

በዘንድሮው 2005 የአዲስ አበባ የአካባቢ፣ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤት ምርጫ ኢህአዴግ በየቤቱ እየዞረና ኑ እባካችሁ ምረጡ እያለ በመቀስቀስ ሕዝቡን ለምርጫ ቢወተውትም የምርጫው ድባብ ከሂደቱ እስከ ፍፃሜው ድረስ ቀዝቃዛና ደብዛዛ ነበር፡፡

አንድ በአነስተኛ የሸቀጥ ሱቅ ውስጥ የሚሰራ ወጣት ስለ መምረጡ ስጠይቀው በሰጠኝ ምላሹ በግርምታ ሆኖ ‹‹እንዴ አዲስ መንግሥት መጥቷል እንዴ!? ትላንትና ዛሬስ ያለው ኢህአዴግ አይደል እንዴ!? ታዲያ የምን ምርጫ ነው የሚሉን እነዚህ ሰዎች በማለት ያስፈገገኝንም ያሳዘነኝንም መለስ ሰጥቶኛል፡፡

ብዙዎች ደግሞ አማራጭ ሲኖር እኮ ነው ምርጫ፣ ለመሆኑ ማንን ከማን ነው የምንመርጠው፣ በእውነት ኢህአዴግ አሁንስ ‹‹ከዝንጀሮ ቆንጆ …›› እንደሚባለው ተረት አደረገው እኮ ይሄን ምርጫ የሚለውን ነገር በማለት፤ ዋ…! ምርጫስ 97 ላይ ቀረ፣ አከተመ፡፡ ሲሉ በትዝታ ሰረገላ የ97ቱን የምርጫ ውድድር ብርቱ መንፈስና ሰፊ ሆነውን ሕዝባዊ ተሳትፎ በሐዘኔታ ውስጥ ሆነው እያስታወሱ፣ ወይ ነዶ፣ ዋ ምርጫ፣ የምርጫስ ነገርስ ይቅርብን ተዉን እባካችሁ … ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በእርግጥ ከ1997 ወዲህ ለተደረጉ አገር አቀፍም ሆነ የክልል ምርጫዎች እንዲህ መቀዛቀዝና ሕዝቡ ለመምረጥም ሆነ ለመመረጥ ያለው ፍላጎትና ስሜት እየወረደና እንደ በረዶ እየቀዘቀዘ መምጣት ገዢው ፓርቲ ብቻውን ተጠያቂ አይሆንም ባይ ነኝ፡፡

በአገራችን የሚገኙ አብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲዎችና አመራሮቻቸው ራእይ አልባነት፣ ቁርጠኝነት ማጣት፣ በሕዝብ ልብ ውስጥ ለመግባት የሚያስችላቸው ፕሮግራምና ፖሊሲ ለመቅረጽ መታከታቸውና ትግሉ የሚጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ያላቸው ዝግጁነት አናሳ መሆኑ አንዳንዶቹን ፓርቲዎችና አመራሮቻቸውን በበቃኝ ከትግሉ መድረክ እንዲያፈገፍጉ እያደረጋቸው እንዳለ እየታዘብን ነው፡፡

እንዲሁም በአገራችን የሚገኙ አብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲዎችና አመራሮቻቸው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደርስባቸውን ጫና መቋቋም አቅቷቸው፣ እንደ እሳት ሊፈትናቸው ያለውን መከራ በሩቅ ሸሽተውትና ቀቢጸ ተስፋ ተውጠው፣ ለገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ሜዳውም፣ ፈረሱም ይኸው በማለት ለብቻው ያለአንዳች ከልካይ በአገሪቱ የፖለቲካ ሜዳ ላይ እንደ ልቡና እንዳሻው ይጋልብበት ዘንድ በከፊል ቢሆን ዕድሉን አመቻችተውለታል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አለመጠናከርና በአመራሮቻቸው መካከል ያለው አምባገነንነት፣ የእርስ በርስ አለመግባባት፣ ሽኩቻ፣ መወጋገዝና መከፋፈል የራሱ ሆነ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ደግሞ ማንም የማይክደው ሐቅ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡

ከምርጫ 97 ማግስት በኋላ እርስ በርሳቸው መካሰስን፣ መወነጃጀልንና መወጋገዝን ሥራዬ ብለው የያዙት የተቀዋሚ ፓርቲ አመራሮች አንዱ የአንዱን ገበና ሳይቀር እንኳን በአደባባይ በማውጣት የገቡበት ቅሌትና የስነ ምግባር ውድቀት፣ አይወርዱ አወራረድ በብዙዎች ዘንድ ለመሆኑ እንደው የሆነስ ሆነና ኢህአዴግ ሥልጣኑን ቢያስረክባቸው ኖሮ ይህችን አገር ሊመሩ የነበሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ እንዴ እስኪሉ ብዙዎች በእፍረት እንዲሸማቀቁና እንዲያንሱ ያደረጉበትን በርካታ አጋጣሚዎችን ታዝበናል፡፡

በአገራችን ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎችና አመራሮቻቸው በሕዝብ ዘንድ አመኔታን በማጣታቸው የተነሳ አብዛኛው ሕዝብ ‹‹ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ምንትስ ይሻለናል፡፡››፤ ‹‹ትሻልን ትቼ ትብስን አመጣሁ፡፡›› እንዳይሆን በሚል ስጋት ወዶም ሆኖ ሳይወድ ኢህአዴግን የሙጥኝ እንዲል የተገደደ ነው የሚመስለው፡፡ እናም ዛሬም ድረስ ተቃዋሚ ነን በሚሉ የትላንትናዎቹ አንጋፋ ፓርቲዎች ውስጥ የተከሰተው ታላቅ የሆነ ስብራት ወይም ስንጥቃት የተጠገነ፣ ቁስሉም የተፈወሰ አይመስልም፡፡

የገዢው ፓርቲ የኢህአዴግ ግትርነት፣ ለሕዝቡ ከእኔ በላይ ለአሳር የሚለው አመለካከቱ፣ በአማራጭ መንገዶችን ለማየትና ከሌሎች ጋር ለመነጋገር ያለበት ችግርና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ያሉት ኁልቆ መሣፍርት የሌላቸው ችግሮች ተደራርበው አገራችን የምታልመውን የዲሞክራሲያ ሥርዓት ግንባታን ዕድገት እያጓተተው ነው፡፡

ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግና አጋሮቹ የ1997ቱ ዓይነት ሕዝብ አቀፍ የሆነ የዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ መንፈስና ቅናት ዳግም እንዲፈጠር ከመሥራት ይልቅ ዛሬም በለመደው ሸካራ መንገድ መጓዝን ነው የመረጠው፡፡ ኢህአዴግ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ተቀራርቦ ለመነጋገር፣ ለመወያየት የጠረቀመውን በሩን በጨዋ መንገድ ለመክፈት ዛሬም ተቸግሮ ያለ ነው የሚመስለው፡፡ እናም በጠላትነት የመተያየት፣ የጥላቻና የጽንፈኝነት ክፉ መንፈስ ዛሬም ድረስ በአገራችን የፖለቲካ ሰማይ ላይ የመጠፋፋትን፣ የመበላላትን ጥቁር ደመና እንዳዘለ ነው፡፡

በዚህ ሁኔታ ደግሞ በፊታችን የሚጠበቀው አገር አቀፉ ምርጫ 2007 የተለየ አንድምታ ሊኖረው አይችልም የሚለው ተስፋ አስቆራጭ የሚመስል ድምፆች ከዚህም ከዚያም እየተሰሙ ናቸው፡፡ ያው እንደተለመደው ምርጫ ሲደርስ ከተደበቁበት ጎሬ ወጥተው አለን አለን የሚሉት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ምርጫን ሰበብ አድርገው እንደ እንጉዳይ የሚፈሉትና እዚህም እዛም ብቅ ብቅ የሚሉት የአገራችን ፓርቲዎች እንደልማዳቸው በመጪው ምርጫ ግርግር መፍጠራቸው አይቀር ይሆናል፡፡

ግና ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውን የሚያስፈልጋቸው ፓርቲና ፖለቲከኛ የምርጫ ሰሞን አለሁ አለሁ የሚል የትርፍ ጊዜ ፓርቲና ፖለቲከኛ አይደለም፡፡ የአገሪቱን የፖለቲካ ታሪክ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቿን፣ የሕዝቦቿን ሃይማኖት፣ ታሪክ፣ ባህልና ቅርስ በሚገባና ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ በአገሪቱ ብሔራዊ እርቅ፣ መግባባትና አንድነት እንዲመጣ ጠንክሮ የሚሠራ፣ እንደ ማህተመ ጋንዲና እንደ አፍሪካዊው ኔልሰን ማንዴላ የፍቅርን፣ የወንድማማችነትንና የእርቅን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጎ የሚያውለበልብ፣ ቆራጥና የሕዝብ ወገንና አለኝታ የሆነ ፓርቲና ፖለቲከኛ ነው ብዙዎቻችን በእጅጉ የናፈቀን፣ የሚያስፈልገንም፡፡

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአገራችን የተከሰተው አብዮት ካመጣቸው መዘዞች አንዱ የፖለቲካ ፕሮፌሽናል ደረጃ እየወደቀ መሄድ ነው፡፡ የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ሺፈራው በቀለ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማኅበር ባዘጋጀውVision 2020 የሥራ ባልደረባቸው የሆኑት ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ ‹‹ምን አለምን? የት ደረስን? ወዴትስ እያመራን ይሆን?›› በሚል አርዕስት ባቀረቡት የጥናት ጽሑፍ ላይ ባቀረቡት ለውይይት ማጫሪያና ማዳበሪያ የሚሆን መነሻ ሐሳብ ላይ ሲገልጹ፡-

ፖለቲካ ማለት መቀላመድ፣ ለዘመድ አዝማድ፣ ለአምቻ ለጋብቻ፣ ለዘር፣ ለወገንና ለጎሳ ‹‹ጮማ መቁረጥ ጠጅ ማንቆርቆር›› (በዚህ ዘመን እንኳን ምናልባት ውስኪ ማውረድ ቢባል ይቀላል፡፡) ማለት ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያውያን አእምሮ ውስጥ በፖለቲካና በማፈያ መካከል ልዩነቱ እየደበዘዘ ሄዷል ማለት ይቻላል፡፡ በመሠረቱ ግን ፖለቲካ በምዕራቡ ዓለም እጅግ ተከበረ ፕሮፌሽን መሆኑን በመጠቆም የታሪክ ምሁሩ በአገራችንም በጥንት ጊዜ ፖለቲካና ፖለቲከኝነት እንዲሁ እንደነበር ያስረዳሉ፡፡

ፕሮፌሰር ሺፈራው ፖለቲካና ፖለቲሺያኖች የተከበሩ፣ ጨዋ፣ የጨዋ ጨዋ ካልሆኑ፣ የሚናገሩት ከመሬት ጠብ የማይል ካልሆነ ምንም ያህል ውብ ውብ ራእዮች ስንደቀድቅ ብንውል ራእዮቻችን ዋጋ አይኖራቸውም ሲሉ ነው የሚደመድሙት፡፡

በስነ ምግባር የታነጸ፣ ጨዋ፣ ለራሱ ሳይሆን ለሕዝቡ የተሰጠ፣ ልክ እንደ እስራኤላውያኑ መሪ ሙሴ ‹‹ይህን ሕዝብ ከምታጠፋው እኔን ከሕይወት መጽሐፍ ደምስሰኝ፡፡›› የሚል በሕዝብ ፍቅር የሰከረ፣ በሳል ፖለቲከኛ/መሪ፣ ከጽንፈኝነት፣ ከጥላቻና ከጎሰኝነት የጸዳ ጠንካራ ፓርቲና ፖለቲካኞች ለማየት አልናፈቃችሁም ወገኖቼ?!

በትንሹም በትልቁም ዛቻና ማስፈራሪያ እየበረገገ፣ መከራው ሲጸናበትና ቀንበር ሲከብድበት ለሕዝብ የገባውን ቃል አጥፎ፣ ‹‹ሞቴም መቃብሬም እዚሁ ነው፡፡›› ብሎ ምሎ እንዳልተገዘተ ሁሉ ‹‹በቦሌም በባሌም›› ብሎ እግሬ አውጪኝ በማለት ወደ አውሮፓና አሜሪካ የሚሰደድ ሳይሆን፣ እዚሁ በአገሩ ከሕዝቡ ጋር ደጉንም ክፉውንም ተቀብሎ በትዕግሥት፣ በጽናት እና በሰላማዊ መንገድ የሚታገል፣ በሕዝብ ፍቅር የወደቀና የነደደ እንደ ጋንዲ፣ እንደ ማርቲን ሉተር፣ እንደ አፍሪካዊው ኔልሰን ማንዴላ ያለ የሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነ ፓርቲና ፖለቲከኛ አልናፈቃችሁም ወገኖቼ!

እንዲህ ዓይነት ከሕዝብ ለሕዝብ የሆኑ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች ሲፈጠሩ ሕዝቦች ያለ ምንም ቀስቃሽና ወትዋች በነቂስ ወጥተው ያገለግለናል፣ ይጠቅመናል የሚሉትን ፓርቲም ሆነ እጩ ለመመረጥ የሌሊቱ ቁር፣ የቀኑ ፀሐይ ሳይበግራቸው መብታቸውን አውቀው ለመጠቀም ይተጋሉ፣ ይሰለፋሉ፡፡ ምርጫ 97 ደግሞ ይህን ሐቅ ለመንግሥት ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሕዝብ ሁሉ በይፋ አሳይቷል፣ አስመስክሯል፡፡

ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለመቀመጫ ወይም ለስልጣን ከመወዳደራቸው በፊት የሕዝብን ልብ አሸንፈው፣ በሕዝባቸው ልብ ዙፋን ላይ ሊቀመጡ የሚችሉበትን ፍቅርን፣ መፈራትን፣ መወደድንና መከበርን ያገኙ ዘንድ መትጋትና መሥራት ይኖርባቸዋል፡፡ የዛን ጊዜ ምርጫው ምርጫ ይሆናል፤ ሕዝብም ያለ ምንም ቀስቃሽ የመምረጥ መብቱን ለመጠቀም በነቂስ ተጠራርቶ ይወጣል፡፡

ሰላም! ሻሎም!

ECADF.COM

ህዝቡ በወያኔ ላይ ያለውን ምሬትና ጥላቻ መግለጽ ጀምሯል!

April 25, 2013 | Filed underG7 Editorial,Slider Post | Posted by 

የኢትዮጵያ ህዝብ እውነተኛ ምርጫና የቀልድ ምርጫ ምን ማለት እንደ ሆነ ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑን በ1997 አም ባደረገው አለምን ባስደመመ ሂደት አስመስክርዋል::

ወያኔና ጀሌዎቹ ግን ዛሬም ሊማሩ አይችሉምና ደግመው ደጋግመው ህዝባችን ሊያሞኙት ይሻሉ በ2002 አ.ም ምርጫ ቦርድ ከሚባለው ሎሊያችው ጋር ሆነው ድምጹን ሰርቀውና አሰርቀው አሽንፍዋል አሽነፍን ብለው አይናቸውን በጨው አጠበው ጨፍር ብለው አደባባይ አስወጡት፤ በጥቃቅን ስም ባደራጁቸው እበላ ባዮች ታጅበውም በአደባባይ አላገጡ በህዝብ ቁስልም ላይ ጨው ነሰነሱ ህዝብም ታዝቦ ዝም አለ ዘንድሮስ?

ዘንድሮ የተለየው ነገር ተቃዋሚዎች ተባብረው 33 የሚሆኑት በአንድ ላይ ቆሙ ከምርጫው በፊት ጥያቄዎችን አንስተው እንደራደርም ብለው ጠየቁ ትእቢተኛው ወያኔም እንደልማዱ አሻፈርኝ የት ልትደርሱ አላቸው ትኩረታቸውን በሙሉ በየቤቱ እየዞሩ ካርድ እንዲወስድ ያስፈራሩት ጀመር የፈራ ወሰደ ያልፈራም ሳይወስድ ቀረ ይህንንም ህዝብ በትዝብት ተመለከተ ፤ካድሬዎቹም ሆነ አለቆቻቸው ወያኔዎች እሁንም ህዝቡን ንቀውታል ምን ያመጣል በሚል ትእቢት ከ99.6 % ወደ 100፥ በመለወጥ ለማሸነፍና ለመጨፈርና ለማስጨፈር ዝግጅታቸውን ማጠናቅቅ ላይ ብቻ አደረጉ።

ተቃዋሚዎችም በአንድ ድምጽ በመሆን የወያኔ የምርጫ አሻንጉሊት ሆነን ለእሱ ፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ አንሆንም ብለው በውሳኔያቸው በመጽናታቸው ወያኔን በእጅጉ አበሳጭቶታል፤ ይሁን እንጅ አጨብጫቢ የሆኑ ፓርቲዎችን መፈለጉ ግን አልቀረም ለምርጫ ጨዋታው አዳማቂነት። የምርጫ ዴሞክራሲያዊነት ከሚለካበት አንዱና ዋናው ፤ ህዝብ የሚፈልጋቸውን መሪዎቹ ያለማንም አስገዳጅነት መርጦ እንደሚሾሙና እንደሚሽር ማመን ሲጀምር መሆኑ ዛሬም ሊዋጥላቸው አልቻለም። ይሁን እንጅ ህዝብ ዛሬ ሳይሆን ከ97 ምርጫ ጀምሮ ወያኔን በህዝብ ድምጽ ተሸንፎ እንደማይወርድ የተገነዘበው አሁን ላይ ሆኖ ሳይሆን ትላንት መሆኑን ወያኔዎች አልተረዱትም ቢረዱትም ለህዝብ ድምጽ ደንታ አልሰጣቸውም።

ስለዚህም የህዝብ የበላይነት ማረጋገጫ የሆነውን ምርጫ ሂደት ወደ ልጆች መጫዎቻነትና ማላገጫ በመቀየር መሬት ላይ የሌለውን ምርጫ በቲቢ ምርጫ እንዳለ ለማስመሰል በኢቲቪ ተወዳድሮ የማሸነፍ ምኞታቸውን መራጭ በሌለበት ምርጫ ለማሳየት ሞክረዋል። ይህም የማስመሰል እና የማጭበርበር አመላቸው ሱስ ሆንባቸው የውድቀታቸውን፣ የሽንፈታቸውን ጽዋ እየተጋቱ እልል ሲሉ ያሳዩናል “በቀሎ እያረረ ይስቃል እንዲሉ”።

የሀገሪቱን ዜጎች በደልና ጥቃት የፍትህ ስርአት የነጻነት ጥያቄ በማፈን የአማራውን መፈናቀል ያልዘገበ ሚዲያና ጋዜጠኞቹ፤ እውን ምርጫ ስላልሆነ ተውኔት የአለቆቻቸውንና የስልጣን ጥመኞችን ውሸት እውነት አድርጎ በማቅረብ አለቆቻቸውን ሲደስቷቸው ሌሎችን ደግሞ አሳዝኗል።

ሚዲያ በታፈነባት ሀገረ-ኢትዮጵያ እንደ ኢቲቪ ያሉ ያዩትን ሳይሆን በወያኔ የተነገሩትን፣ የተዘጋጀላቸውን ሀተታዊ ድራማ በሚዘግቡ፤ እውነታን በማይናገሩ ቡችሎች ስለምርጫ ሲዘምሩ ይታያሉ። ካድሬዎቻቸው እንኳ ወጥተው ባልተሳተፉበት መራጭ የሌለውን፤ ውጤቱ የዜሮዎች ድምር ዜሮ የሆነውን የምርጫ ድራማ ተውኔትና ውርደታቸውን ሲያሳዩ በአንጻሩ ህዝብ እየተፈናቀለ እያዩ እንዳላዩ በመሆን ለማስመሰያ ጭዋታ የሀገሪቱን ንብረትና ሀብት ያባክናሉ።

ይህን ሁሉ ፈተና አልፎና ተገድዶ የሄደው ህዝብም ቢሆን ያገኘውን እድል በመጠቀም ወያኔዎችን ውረዱ፣ በቃችሁ፣ወንጀለኞች ናችሁ፣ የፖለቲካና የሃይማኖት እስረኞችን ፍቱ እና ሌሎችንም የወያኔ ባዶነትን ለመግለጽ ባዶ ወረቀቶችን በመስጠት ጥላቻቸውን በድጋሜ አረጋግጠውላቸዋል። ግንቦት 7 ህዝቡ ያሳየውን እምባይነት እያደነቀ ነገር ግን የወያኔዎችን ጭቆና ተቋቁሞ ትግሉን ከዚህም በላይ በመውሰድ በየአካባቢው በማፋፋም መቀጠልና ነጻ አውጪዎችን ሳይጠብቅ በራሱ ጎበዝ አለቃዎች በመደራጀት አልገዛም ባይነቱን እንዲቀጥል ጥሪውን በዚህ አጋጣሚ ማስተላለፍ ይወዳል።

ንቅናቂያችን ዛሬም ትክክለኛና ህዝብ በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ተሳትፎ የሚመርጠው አካል፣ እንዲሁም ለህዝብ ተጠያቂ የሆነና ህዝብን የሚፈራ መንግስት፣ በህዝብ የሚሾም፣ የሚሻር አካል ለመፍጠር በቅድሚያ ወያኔን በማስወገድ ብቻ ነው ብሎ ያምናል።

ነጻነትን ለማግኘት ዝም ብለን ስለተመኘነው የሚመጣ አይደለም፣ ዝም ብሎም በራሱ ታምር ሆኖ አይከሰትም፤ ሁሉም ዜጎች ከወያኔ የምርጫ ማጭበርበሪያ ካርድ ወጥተው ተደራጅተውና አደራጅተው በተናጥልም ሆነ በቡድን ወያኔን አስወግዶ በሀገራችን ሁሉም ዜጎች በእኩልነት ተከብረው የሁሉም መሰረታዊ መብቶች ባለቤት ሲሆኑ ነው።
ይህ የሚሆነው ደግሞ ወያኔ እንደ ምጽዋት እስጣችኋለሁ በሚለው መንገድ ሳይሆን ፣ ብቸኛው ምርጫ በሆነው ነጻነታችንን ለማስከበርና የሀገራችንን ህልውና ለመታደግ ማናቸውንም አይነት የትግል ስልቶችን ተጠቅመን ደማችንን አፍሰን አጥንታችንንም ከስክሰን በሚከፈል ዋጋ መሆኑን አምነን ትግሉን በማፋፋም በመሆኑ በተለይም ወጣቶች ትግሉን እንድትቀላቀሉን ጥሪያችን ይድረሳቹሁ እንላለን።

በዚህም አጋጣሚ ግንቦት 7 ለወያኔ አባላት የሚያስተላልፈው መልእክት በፍላጎታችሁ እና በምርጫችሁ የመስራትና የመኖር ሰብአዊ ነጻነታችሁ በወያኔ የፖለቲካ ፓርቲ አሽከር አደግዳጊና ጉዳይ ፈጻሚ በመሆን ብቻ የምታገኙት እርጥባን ሳይሆን በዜግነታችሁና በሰውነታችሁ የተሰጣችሁ መብት በመሆኑ ከፍርሃት ወጥታችሁ ንጹህ ህሊናን ተጥቅማችሁ ወያኔን በማስወገድ በሚደረገው ህዝባዊ ትግል ውስጥ ጊዜው ሳይይረፍድ ከታጋይ ሀይሎች ጋር በመቀላቀል የበኩላችሁን አስተዋጽኦ በማድረግ ኢትዮጵያዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

 

 GINBOT7

በሳንድያጎ የወያኔዎች ስብሰባ ሳይጀመር ተበተነ

በሳንዲያጎ የወያኔ አምባሳደር ይገኝበታል ተብሎ በአባይ ግድብ ስም ቦንድ ለመሸጥ የተጠራው ስብሰባ በኢትዮጵያውያን ተቃውሞ እንዲቋረጥ ሆንዋል።

Ethiopians in San Diego Protest April 28, 2013

በቁጥር ከሁለት መቶ በላይ የተቆጡና በርካታ መፈክሮችን ያነገቡ ኢትዮጵያውያን ስብሰባው በሚደረግበት አዳራሽ የተገኙት ቀደም ብለው ነበር።

TV channels covering Ethiopians demo. in San Diego

በርካታ ታዋቂ ሚድያዎች በቦታው ተገኝተው የተቃውሞዉን ትዕይንት የዘገቡ ሲሆን የቴሌቪዥን ጣብያዎች ዜናውን ማምሻው ላይ ለቀውታል።

ወያኔዎቹ በሌሎች ቦታዎች የገጠማቸውን ከግምት አስገብተው 3 ሰዎች በር ላይ አቁመው የራሳቸውን ሰዎች ብቻ መርጠው ለማስገባት ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም።

ስብሰባው ሲጀመር የወያኔዎቹ ቁጥር ከ20 በታች ሲሆን ኢትዮጵያውያኑ ከሁለት መቶ በላይ ነበሩ።

ነገር አሳምራለሁ ብሎ ስብሰባውን እንግሊዝኛ ቋንቋ በመናገር የጀመረው የወያኔ ተወካይ በጥዋቱ ነበር ተቃውሞ የገጠመው፣ ኢትዮጵያውያኑ “እኛ ኢትዮጵያውያን ነን በቋንቋችን ተናገር” ብለው አስቆሙት። ተወካዩ ንግግሩን በአማርኛ ቀጠለ “እኛና እናንተ…” ብሎ ሊቀጥል ሲል አሁንም ከባድ ተቃውሞ ገጠመው “እናንተ እነማን ናችሁ? እኛስ ማን ነን? አትከፋፍለን እኛ አንድ ነን” አሉት።

ECADF.COM

በህዝብና በሀገር ላይ ቀልድ የለም (በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ስብስብ)

በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ስብስብ የተሰጠ የተቃዉሞ መግለጫ

ህዝባችን መስዋእትነት ከፍሎና ተንከባክቦ ባቆያትና እትብቱ በተቀበረባት ምድር የመኖር ነፃነቱን ከተነፈገ፣ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን በዘርና በቋንቋ እየተመነዘረ በገዛ ሀገሩ እንደ ባይታዋር ተቆጥሮ ከተባረረና ሜዳ ላይ ከተጣለ፡- ሀገር አለኝ ማለቱ ትርጉሙ ምንድን ነው?። የውጭ ባለሃብቶች ለም መሬታችንን ይዘው ኰርተውና ተንደላቅቀው ሲያርሱና ሲያለሙ በአንፃሩ የሀገሩን ባለቤት የሆነውን ህዝብ የበይ ተመልካችና ተመፅዋች ሆኖ እየተንከራተተ የሚኖረው እስከ መቼ ይሆን?። ይህ ዓይነቱ አሳፋሪ እርምጃ እየተደጋገመ ከሄደስ የሀገራችን የወደፊት ዕጣ ፋንታ ምን ሊሆን ይችላል? ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ ስርዓተ አልበኝነት ነግሶ ህዝቡ አቤት የሚልበት የፍትሕ ቦታ አጥቶ ሲተራመስ ስናይ ለመሆኑ በሀሪቱ ላይ መንግስት አለ ወይ? የሚለውን ጥያቄ እንድናነሳ አድርጎናል።

ሰሞኑን በቤንሻንጉል አካባቢ በሽዎች በሚቆጠሩት የአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው ከቤት ንብረታቸው የማፈናቀል ድርጊት በተለያዩ ሚዲያችና እንዲሁም ሜዳ ላይ ከወደቁት ተፈናቃዮች ከራሳቸው አንደበት ስንሰማ እጅጉን አሳዝኖናል። ይህ አረሜናዊ ድርጊት ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚል መንግስት ቀርቶ በባዕዳን ወረራ ጊዜም ቢሆን ያልተፈፀመና በኢትዮጵያ የመንግስታት ታሪክም ታይቶ የማይታወቅ አስነዋሪ ተግባር መሆኑን አሳይቶናል። ከዚህም አልፎ የሚያሳዝነውና የሚያስገርመው ደግሞ ድርጊቱን መፈፀሙ ብቻ ሳይሆን የህወሓት/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት እንደ ለመዱት ሁሉ ወንጀሉን ለመሸፋፈን ሲሉ የሰጡትን መግለጫ በህዝቡ ህይወት ላይ መቀለድና ማፌዝ መሆኑን በይፋ አሳይቶናል። ሰለሆነም ፡-

1. የህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት በወገኖቻችን ላይ እየፈፀመ ያለው አረሜናዊ ድርጊት ኢትዮጵያዊነት ስነ ምግባር ያልተከተለ፣ የህዝባችን ሕገ መንግስታዊና ዜግነታዊ መብት የሚጥስ፣ ዓለም አቀፋዊ የሰብኣዊ ፍጡር አያያዝ የሚፃረር የወንጀል ድርጊት በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን። በዚሁ የወንጀል ድርጊት ላይ የተሳተፉ ሰዎችም በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን።

2. “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም” ነውና የዜጎች ህይወት የዶሮን ያህል ክብር ሳትሰጡ ሀገርንና ህዝብን በፍርፋሪ፣ በስልጣንና በጊዚያዊ ጥቅም በመለወጥና እንዲሁም የህዝቡን ትዕግስት፣ ጨዋነትና ዝምታ እንደ ሞኝነት በመቁጠር በየዋሁ ህዝባችን ላይ ወንጀል እየፈፀማችሁ የምትገኙ የስርዓቱን ካድሬዎችና ደጋፊዎች ሁሉ ትዕግስት ገደብ አለውና የዛሬ ዝምታ የነገ እሳተ ጎሞራ እንደሚሆን ተገንዝባችሁ ከእኩይ ድርጊት እጃችሁን እንድታነሱ እንጠይቃለን።

3. በህዝባችን ላይ እየተፈፀመ ያለው የወንጀል ድርጊት እንደ ተለመደው “የባሰ አታምጣ” ተብሎ በማድበስበስ፣ በዝምታና በማዳፈን የሚታለፍ ሳይሆን ጉዳዩን ገለልተኛ አካል እቦታው ድረስ ሂዶ እንዲያጠራ ዓለም አቀፍ ሰብኣዊ መብት ተሟጓች ድርጅቶችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

4. በሀገር ውስጥም ሆነ በዲያስፓራ የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ሁሉ በመካከላችን ሊኖር የሚችለው የአመለካከት ልዩነት እንደ ባላንጣነት ሳይሆን እንደ ውበት ተቀብለን ለጋራ ችግር በጋራ መቆም ጊዜው የግድ ይለናል። ካልሆነ ግን በተናጠል ተበታትነን በየተራ እየተደቆስን መኖር የማይቀር ነው። ስለዚህ “ጎርፍ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው” እንዲሉ የህወሓት/ኢሕአዴግ መሪዎች ቀለማቸውን እየቀያየሩ በልማት ስም የህልም እንጀራ ለማብላትና መርዝ በማር ጠቅልለው ለማጉረስ ሌት ተቀን እንቅልፍ አጥተው ሲንቀሳቀሱ እኛ ደግሞ የህልውናችን ሞሶሶና ዋስትና በፍቅር፣ በመከባበር፣ በመደማመጥና በመቻቻል ላይ የተመሰረተ አንድነት በተግባር ማሳየት ለነገ የማይባል የያንዳንዳችን አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን በፅኑ እናምናለን።

5. ኢሕአዴግ በተለይም ዕድሜ ልኩን ያንተ ነፃ አውጪ ነኝ እያለ በትግራይ ህዝብ ስምና ደም ሲነግድ የኖረው ህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) በተለመደው ባህሪው በወንድሞቻችን ላይ እየፈፀመ ያለው ጭካኔ የተሞላበት አረሜናዊ ድርጊት ሆን ተብሎ ወገን ከወገኑ ጋር ለማጋጨትና ጥርጣሬ ለመፍጠር የተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ከተገነዘበው ውሎ አድረዋል። ስለዚህ ህወሓት በኢትዮጵያውያን መካከል እየተከለ ያለው ልማት ሳይሆን ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ የጥፋት ፈንጅ መሆኑን በመገንዘብ የአንድነትና የሰላም ባላንጣ የሆነውን ድርጅት የሚፈፀመው ግፍ ከካድሬዎቹ በስተቀር ብዙሃኑን የማይወክል መሆኑን እየገለፅን ቡድናዊ አምባ ገነኖችን ከህዝብ ነጥሎ መታገል የፓለቲካ ብልህነት ብቻ ሳይሆን አማራጭ የሌለው የለውጥ መንገድም እሱ ብቻ መሆኑን እናምናለን።

6. እኛም ከማንም ከምንም በላይ ዘር፣ ቦታ፣ ሀይማኖት፣ ቋንቋ፣ የፓለቲካ እምነትና ስደት ሳይገድበን ከ80 ሚሊዮን በላይ የሆነውን ህዝብ እንደ ዓይን ብሌናችን በማየት ችግሩ ችግራችን፣ ደስታው ደስታችን፣ ሀዘኑም ሀዘናችን መሆኑን በማመን የጋራ ችግራችንን በጋራ ለመፍታት በሚደረገው የለውጥ እንቅስቃሴ ከጎኑ የምንቆም መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ እናረጋግጣለን።

ኢትዮጵያ ሀገራችን ለዘላለም ትኑር

 

 Zhabesha.com

ወያኔ በአማራ ተወላጆች ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንደቀጠለ ነው

ወያኔ ለአማራ ህዝብ፤ ባህልና ታሪክ ያለዉን ጥላቻ ከተራ ጥላቻ አልፎ በተግባር አማራዉን ወደ ማጥቃት ዘመቻ አደገ እንጂ ለአንድም ቀን ቀንሶ አያውቅም። አማራው እንደ ሰው ልጅ የመኖር መብቱ፣GINBOT 7 Movement ስብእናው ተገፎ ከቀየው፣ ከመንደሩ የአፈራውን ንብረትና ገንዘብ እየተቀማ መባረሩ፣ መሰደዱ፣ እንግልቱ ሁሉ የወያኔ የበቀል እርምጃ ነው።

በአሶሳ፤ በደኖና በአርባጉጉ ውስጥ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ህጻናት፤ሴቶችና አረጋዉያን በግፍ ተገድለዋል። ባለፈዉ አመት በደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጋር ተግባብተዉ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ብሄረሰብ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ለአመታት ያፈሩትን ንብረት ይዞ የመሄጃ ግዜ እንኳን ሳይሰጣቸዉ አከባቢዉን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለቅቀዉ እንዲወጡ እንዲፈናቀሉ ተደርጓል።

ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ ወያኔ በአማራዉ ህዝብ ላይ አዲስና ሰፋ ያለ የጥቃት ዘመቻ ጀምሯል። በደቡቡ የአገራችን ክልል በጉራፈርዳ የጀመረዉን አማራውን ነጥሎ የማጥቃትና የማንገላታት ዘመቻ አሁን ደግሞ በሰሜን ምስራቅ የአገራችን ክፍል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀጥሏል።

የቅርብ ግዜው ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሜዳ ላይ ወድቀው የሚገኙት አማራ አርሶደአሮች የድረሱልን ጥሪ ማሰማታቸውና፤ ብሄረ አማራን እወክላለሁ ባዩ ብአዴን (የህወሃት ቡችላ) ጠበንጃ ደቅኖብን ወደ መጣችሁበት ተመለሱ ከዚህ ጥፉ ሲል አዋከበን፤ የወገን ያለህ ድረሱልን የት እንግባ ልጆቻችን የአውሬ ራት ሆኑ ሲሉ ስቃያቸውን አሰምተዋል። በርግጥ የህወሃት ተለጣፊው ብአዴን ሆዳቸው ስለሞላ ህሊናቸው ታውሮ ይህ በደል የሰው ልጅን የማጥፋት ሴራ መሆኑን እና በዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሚያስጠይቅ የተረዱ አይደሉም።

ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለረጂም አመታት ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ አያሌ የአማራ ብሄረስብ ተወላጆች ያፈሩትን ንብረት ለመሰብሰብ እንኳን ግዜ ሳይሰጣቸዉ የኔ ብለው ከሚጠሩት የመኖሪያ ቦታቸዉ እንደባዳ እየተገፉ እንዲወጡ ሲደረጉ በአንጻሩ በባህርዳር ከተማ ብአዴን የቱባ ባለስልጣናቱን ከርስ ለመሙላት የክልሉን ህዝብ ጮኸት ጀሮ ዳባ ብሎ ሽርጉድ ሲል የነበረ መሆንን ያገናዘበ ኢትዮጵያዊ ቁጭት በርካታ ነው ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፡ እርግጥ ነው ይህን ዘረኛ ቡድን ለማስወገድ በሚደረገው መራራ ትግል ሂደት ውስጥ በደልና ሰቆቃው እየበዛ እንደሚሄድ ቢታወቅም ተባብረን ከታገልነው ግን ይህን ልናሳጥረው እንችላለን። አለበለዚያ ግን እስከ መቼ ነው ወገኖቻችን በትውልድ መንደራቸው የሀገር ውስጥ ጥገኛ ጠያቂ የሚሆኑት? የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ከቀያቸው የተባረሩት በኢትዮጵያዊ ዜግነታቸው ነው።

ግንቦት 7 ንቅናቄ ይህ የወያኔ ስርአት እስካልተወገደ ድረስ በአማራው የተጀመረው ጭፍጨፋ፣ እንግልት፣ ስደት፣ መከራና ግድያ፤ ህወሃት በሌሎችም አጠናክሮ ይቀጥልበታል ብሎ ያምናል። ስለዚህ ምን እንጠብቃለን በወያኔ ያልተበደለ፣ ያልታሰረ፣ ያልተደበደበ፣ ያልተሰደደ፣ ያልተፈናቀለ፣ ያልተራበ፣ ያልተዋረደ፣ ያልተገደለ ህዝብ የለም። የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ጨካኝ ስርአት አማካኝነት በጨለማ ሂዎት ውስጥ እየኖረ ነው።

የሀገራችን ወጣት ሆይ፡ ወጣትነት ሀገር ተረካቢ፣ ባላደራ፣ ለውጥ ፈላጊ፣ ሀገሩን ጠባቂ ነው። ወገንህ ሲገረፍ ሲንገላታ ሲሰደድ ማየት እና ከንፈር መምጠት እሰከ መቼ ይሆን? ሰቆቃቸው፣ ቁስላቸው የድረሱልን ዋይታቸው መቼ ይሆን ተሰምቶን እንባቸውን በአለንላችሁ የወገን ደራሽነት የምንደርስላቸው? የምንጠርግላቸው? ግንቦት 7 ትግሉን የማቀጣጠያ ሰአት ጊዜው አሁን ነው ይላል። ወጣት፣ አዋቂ፣ ጎልማሳ፣ ሽማግሌ፣ ዘር ጾታ ቋንቋ ሳይለየን ወያኔን ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ምላሽ ስጡ፣ ተቀላቀሉ። በኢትዮጵያ የጠቆረውን ጨለማ በብርሃን መተኪያ ጊዜ ዛሬ ነው። ይህ ትውልድ የታሪክ ባለእዳ አይሁን።

በወያኔ ውስጥ ያላችሁ ይህ በደል ና ሰቆቃ የሚሰማችሁ ወገኖቻችን የውስጥ አርበኛ የምትሆኑበት ሰአት ላይ ናችሁ። ራሳችሁን እና ወገናችሁን ከቀን ጅብ ስርአት አድኑ። ከነጻነት ማግስት በኋላ ከሚመጣባችሁ ከየት ነበራችሁ ክስ ለመጽዳት ከነጻነት ታጋዮች ጋር አብሩ። ወያኔ ለ21 አመታት ህዝቡን ለማጋጨትና ለማባላት የሚያደርገው ስልት መሆኑን ተረድታችሁ የውስጥ ታጋዮች መሆናችሁን ማሳያ ጊዜው አሁን ነው። አሊያ ግን በአማራው ህዝብና በሌላው ማህበረሰብ ላይ እየተፈጸመ ባለው እጅግ አስከፊ ወንጀል በግልም ሆነ በቡድን፣ የንጹሀንን ደም እያፈሰሳችሁ ያላችሁ ወንጀለኞችና ተባባሪዎች ተብላችሁ፣ ከያላችሁበት ታድናችሁ ለፍርድ እንድትቀርቡ ንቅናቂያችን የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት በግልጽ እንድታውቁት ይገባል።

የሀገራችን ህዝብ ሆይ፡ ዛሬ ኢትዮጵያን ከገባችበት ዘረኛ መቀመቅ ስርአት ውስጥ የሚያወጣት ብቸኛ መፍትሄ፣ ፍርሃታችንን በጥሰን በተባበረ ጉልበትና ድፍረት ወያኔን በሚገባው ቋንቋ ስናናግረው፣ ታግለን ስናስወግደው ብቻ ነው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ክብርን፣ ተሳስቦና ተፈቃቅሮ፣ ተከባብሮና ተቻችሎ የመኖር ጸጋን የምናመጣው። ስለሆነም በየትኛውም አቅጣጫ የሚደረገውን የነጻነት ጉዞ ትግል ትቀላቀሉ ዘንድ ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪውን በድጋሜ ያቀርባል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

 

 ECADF.Com

በሚዲያ መረሳት ያስፈራል

“ነጻ ፕሬስ ከሌለ አገር አደጋ ላይ ነው”

the meeting

March 15, 2013 07:20 am By  2 Comments

“ከምድር በታች ጨለማ ቤት ውስጥ የታሰሩትን በቀን ለ10 ደቂቃ እናያቸዋልን። ልብ የሚነካ ነው። የብርሃን ማነስ አይናቸውን እንደጎዳቸው ያስታውቃሉ … ሴቶችን በተገኘው ሰበብ ያስሯቸዋል። ምክንያት ፈልገው እስር ቤት ይከቷቸዋል። ከዚያም ይደፍሯቸዋል። በርካታ የተደፈሩ እህቶች አሉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና መንግሥት ያሰማራቸው ሚሊሻዎች ይህንን አሳዛኝ ድርጊት እንደፈጸሙ ተነግሮናል” ይህ ማዕከላዊ እስር ቤት ታስሮ፣ ችግሩ ባለበት ቦታ ተገኝቶ የነበረው ስዊድናዊ የፍሪላንሰር ጋዜጠኛ ማርቲን ካርል ሻቢዬ ቃል ነው።

ስለ ማዕከላዊ እስር ቤት መስማት ይጨንቃል። ሰዎች በሲቃ የሚያሰሙት የጣር ድምጽ ለጆሮ  የተለመደ ነው። ከመሬት በታች የጨለማ ክፍል አለ። በዚህ መታጎሪያ ውስጥ ሆነው ስቃይ የሚፈራረቅባቸው ወገኖች ጥቂት አይደሉም። ማዕከላዊ ብዙ ጉድ ያለበት ሲኦል ነው። የሰው ልጆች በግፍ ማቅቀውበታል። እየማቀቁበትም ነው። ለውጥ እስከሌለ ድረስ የሚቆም አይመስልም። በመሃላ የሚነገርለት ውርስና ይቀጥላል የሚባለው የመለስ ራዕይ አንዱ ክፍል ይህ ነው።

መጋቢት 3፤2005 (3/12/2013) በኖርዌይ ኦስሎ የሥነጽሁፍ ቤት (ሊትሬቸር ሀውስ) በተዘጋጀ የመወያያ መድረክ ላይ ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ተገኝተው ነበር። መድረኩን ያዘጋጀው ደግሞ NOAS በሚል ስያሜ የሚታወቀው የስደተኞች ተሟጋች ድርጅት ነው። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አን-ማግሬት ኦስቴና ሁለቱን እንግዶች ካስተዋወቁ በኋላ መድረኩን እየመሩ ውይይቱ ተካሄደ። በዚህ ውይይት ላይ ሁለቱ ጋዜጠኞች እየተፈራረቁ የደረሰባቸውንና በትክክል ያዩትን አስታወቁ።

ማርቲን ካርል ሻቢዬና ባልደረባው የፎቶ ጋዜጠኛ ጆሃን ካርል አበክረው የሚናገሩት ስለ ሙያቸው ነው። “ጋዜጠኛ ለመጻፍ ማየትና ማነጋገር አለበት። በተለያዩ አገራት ጋዜጠኞች ችግር ባለባቸው ቦታዎች ገብተው ለመዘገብ ድንበር ያቋርጣሉ። አሁን በሶሪያ፣ ቀደም ሲል በሊቢያ የሆነው ይህ ነው። በኢትዮጵያ ግን ሽብርተኛ ያሰኛል” ሲሉ ግርምታቸውን ይጀምራሉ።

የ19 ዓመት ወጣት ነው። ስራዉ ሹፍርና ሲሆን “ኦነግ ነህ” ተብሎ ነው የታሰረው። መርማሪዎች ባዶ ወረቀት እየሰጡ ስለ ኦነግ ጻፍ ይሉታል። ምንም የሚያውቀው ነገር ስላልነበር መጻፍ አልቻለም። በመጨረሻ ራሳቸው ጽፈው አዘጋጅተው በራስህ እጅ ጽሁፍ ገልብጥ አሉት። እናም የተባለውን ፈጸመ። ጋዜጠኞቹ ብዙ መረጃ አላቸው። እነሱንም ያልሆኑትንና ያላደረጉትን አድርገናል እንዲሉ መደረጋቸውን አስታውቀዋል። “በሶማሊያ አምስት ዓመት ተቀምጫለሁ እንድል አስገድደው አሳመኑኝ” በማለት ጆሃን ካርል ገለጸ።

ወ/ሮ ዙፋን አማረ

የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር በኖርዌይ ሊቀመንበር ወ/ሮ ዙፋን አማረ እንደሚሉት ሁለቱ ጋዜጠኞች ኖርዌይ እንዲመጡ ከላይ ከተጠቀሰው ድርጅት ጋር ከመነጋገር ጀምሮ ማህበራቸው የበኩሉን ስለማድረጉ ይናገራሉ። ይህ እንዲሆን የታሰበው ደግሞ ጋዜጠኞቹ በትክክል ያዩትንና የደረሰባቸውን ለኖርዌይ ባለስልጣናት በማስረዳት በኢትዮጵያ ላይ የያዙትን አቋም እንዲያስተካክሉ የሚደረገውን የቅንጅት ትግል ለማጠናከር እንደሆነ ወ/ሮ ዙፋን ያስረዳሉ።

ሁለቱ ጋዜጠኞችም ያሰመሩበት ጉዳይ ይህንኑ ነው። ኖርዌይ የመጡበት ዋናው ምክንያት ከተለያዩ ፖለቲከኞች፣ አግባብ ካላቸው መስሪያ ቤቶችና ከዋናው ፓርላማ በመገኘት ስለ ኢትዮጵያ ማስረዳታቸውን ተናግረዋል። በርግጠኛነት ባለስልጣናቱ ያገኙትን መረጃ ለመልካም ይጠቀሙበታል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

ዶ/ር ሙሉዓለም

ኢትዮጵያዊያን ባሉበትና የስደተኞች ጉዳይ በሚነሳበት ሁሉ የማይጠፉት ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም የኢትዮጵያ መንግስት ስለሚፈጽመው በደልና ግፍ ለማስረዳት ብዙ መደከሙን፣ እነሱም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት ምን አይነት መንግስት እንደሆነ እንደሚያውቁ፣ መንግስትም ራሱን ሊሰውር ቢል የሚፈጽመው ተግባሩ ከግብሩ ሊሰወር እንደማያስችለው በሚያስረዳ መልኩ አስተያየት ከሰጡ በኋላ “”እነዚህን ሰዎች እኮ አቁሙ የሚላቸው የለም። የምታውቁትን ያስረዳችኋቸው ባለስልጣናትና ፖለቲከኞች ምን ምላሽ ሰጡ?” የሚል ሁሉንም የሚወክል ጥያቄ አቀረቡ።

በተደራራቢ ስብሰባና በውይይት መዳከማቸውን የገለጹት ሁለቱ ጋዜጠኞች “የኖርዌይ ባለስልጣናትና ፖለቲከኞች ያገኙትን መረጃ ለበጎ ይጠቀሙበታል የሚል እምነት አለን” በማለት መልስ ሰጥተዋል። ስለ አውሮፓና አሜሪካ ዝምታ ለተጠየቁት የመለሱት አሸባሪነትን በመዋጋት ስም ከፍተኛ ገንዝብ እንደሚገኝ በመግለጽ ነው። በምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካው መልክ የተወሳሰበ በመሆኑ ኢህአዴግም ይህንኑ እንደሚጠቀምበት አመላክተዋል። አሜሪካንና እንግሊዝን ኮንነዋል።

ስለ ኢህአዴግ የስለላ መረብና በስደት ላይ በሚገኙ ወገኖች ላይ ስላሰማራቸው ጆሮ ጠቢዎች አስተያየት እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ አገር ቤት ያስተዋሉትንና ያላቸውን መረጃ በማጣቀስ አድማጮችን አስፈግገዋል። በካፌና ተራ መዝናኛ ቦታዎች ጆሮ ጠቢዎች እንደሚሰማሩ፣ ሰዎች ሻይ እየጠጡ የሚያወሩትን እንደሚለቅሙ፣ በመገረም ተናግረዋል። ስደተኞችን መሰለልና መቆጣጠር አደገኛ ወንጀል እንደሆነ በሃዘን ስሜት አስረድተዋል።

እስር ቤት “ግምገማ አለ” በማለት ግምገማ የምትለዋን የአማርኛ ቃል ተጠቅመው ማብራሪያ ሰጥተዋል። እስር ቤት ውስጥ ባለው ግምገማ 100 ነጥብ የሚያገኙ ይቅርታ እንደሚያገኙ፣ 10 ወይም ከዚያ በታች የሚያገኙ ደግሞ ተቃራኒው እንደሚተገበርባቸው እየሳቁ የኢህአዴግን የቆሸሸ አካሄድ ተናግረዋል።

የኖርዌይ PEN (ፔን) ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ኤሊሳቤጥ ኤዲ “በሽርክና ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ” ሲሉ የጠሩትን የአገራቸውንና የኢትዮጵያን ግንኙነት የገለጹት በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ እንደሚመላለሱ መግለጽ ነው። እርሳቸውን ተከትሎ አቶ ዳዊት መሰረታዊ ጉዳዮችን አንስተው ጥያቄ የሰነዘሩ ሲሆን፣ በማዕከላዊ ምርመራ እስር ቤት ውስጥ መርማሪዎቹ እርስ በርስ የሚነጋገሩበት ቋንቋ በኢትዮጵያ ከሚነገሩት ቋንቋዎች የትኛው እንደሆነ እንዲያስረዱ ያቀረቡት ጥያቄ ፖለቲካዊ ፋይዳ ያለውና አፈናውን የሚያካሂዱትን ቡድኖች የሚያጋልጥ በመሆኑ ከስብሰባው በኋላ መነጋገሪያም ነበር። የጎልጉል ዘጋቢ ያነጋገራቸው አንድ የኖርዌይ ተወላጅ በጥያቄው መነሳት መገረማቸውን አስረድተዋል። ጥያቄው የቀረበላቸው ጋዜጠኞች ግን በተለይ ቡድን ለይተው አልመለሱም። ይሁንና በቅርቡ በሚያሳትሙት መጽሃፍ ብዙ ጉዳዮች እንደሚነሱ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር በኖርዌይ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጌዲዮን ደሳለኝ ስለ እስክንድር ነጋ አንስተው ነበር። የማህበሩ ጸሐፊ አቶ ቢኒያም በውይይቱ ላይ ከተገኙት መካከል የሚጠቀሱ ሲሆኑ፣ ሊቀመንበሯ ወ/ሮ ዙፋን በማህበራቸው ስም ከፍተኛ ምስጋና በማቅረብ ከሰብአዊ መብት መጣስ ጋር በተያያዘ ጥያቄ አንስተው ነበር።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አስቀድሞ በመታሰሩ የመገናኘት እድል እንዳላገኙ ያስረዱት ሁለቱ ጋዜጠኞች፣ ርዕዮት ዓለሙን እንዳገኙዋት፣ መነጋገር ስለማይቻል በምልክት ለመግባባት ይሞክሩ እንደነበር አስታውሰዋል። ከዚሁ ጋር አያይዘውም “እነዚህ ጋዜጠኞች የታሰሩት በመጻፋቸው ነው። የተከሰሱት ስለጻፉ ነው። ጋዜጠኞቹ ሲጽፉ ይህ እንደሚደርስባቸው ያውቁ ነበር። ሃላፊነቱን ራሳቸው ወስደው ጻፉ። አገራቸውን ስለሚወዱ፣ ሙያቸውን ስለሚያከብሩ፣ ህዝባቸውን ስለሚያፈቅሩ አደረጉት። ለነሱ ልዩ ክብር አለን” ብለዋል፡፡

“እስር ቤት እያለን አንድ ስጋት ነበረን” አሉ የስዊድን ጋዜጠኞች “ፍርሃታችን የስዊድን ጋዜጦች ስለኛ መጻፍ እንዳያቆሙ ነበር። የስዊድን ሚዲያዎች ስለኛ መጻፍ ካቆሙ እንረሳለን። መወያያ አጀንዳ የምንሆነው ካልተረሳን ብቻ ነው … ” በማለት የሚዲያን የመቀስቀስ ኃይል አጉልተው አሳይተዋል። አሁን በእስር ላይ ያሉት ጋዜጠኞች “ከመቃብር በታች ናቸው” በማለት ሁሉም ሚዲያዎች ሊረሷቸው እንደማይገባ የሚያስገነዝብ ውድ መልዕክት አስተላልፈዋል። “ነጻ ፕሬስ ከሌለ ለአገር አደጋ ነው። ነጻ ፕሬስ የሌለበት አገር አስተማማኝ መረጋጋት አይኖርም” ሲሉ የነጻ ሚዲያን አስፈላጊነት አስምረውበታል።

ጋዜጠኞቹ መጽሃፋቸውን በቅርቡ ጽፈው ለህትመት አስኪያበቁ ድረስ ዝርዝር ጉዳዮች በሚዲያ ላለመስጠት መወሰናቸው አስቀድሞ በስብሰባው አዘጋጆች በመነገሩ የሪፖርቱ አቅራቢ በዚህ ሊገደብ ችሏል። ስለሃብት ስርጭትና ሞኖፖሊ በማስረጃ ተደግፎ የቀረበውን ጥያቄ ጨምሮ ሰፊ ጉዳዮች በስብሰባው ላይ ተነስተው ነበር።

ተጋባዦቹ ጋዜጠኞች ፊትለፊት አውጥተው ባይናገሩም እስር ቤት ሆነውና፣ ኦጋዴን በአካል የታዘቡትን፣ እንዲሁም በግል ባሰባሰቡት መረጃ መሰረት በቅርቡ የሚያሳትሙት መጽሃፍ ታላቅ ዋጋ ያላቸው መረጃዎች የተካተቱበት እንደሚሆን የብዙዎች ግምት ነው። መጽሃፉ የሚታተምበት ትክክለኛ ጊዜ ባይታወቅም መጽሃፉ ከመረጃ ሰጪነቱና ኢህአዴግን ከማጋለጡ በተጨማሪ መንታ አላማ ማንገቡ የተገለጸው ሰዎቹ ከእስር እንደተፈቱ ነበር።

“በርግጥ ከእስር በመለቀቃችን እድለኞች ነን። ሆኖም ግን አዕምሯችን እረፍት አላገኘም። ምክንያቱም ብዙ ባልደረቦቻችን አሁንም እዚያው እስር ቤት ናቸው። የእስር ቤት ባልደረቦቻችን ባብዛኛው በምን ዓይነት ሁኔታ እንዳሉ ራሴን እጠይቃለሁ። እስር ቤቱ ጥሩ ስፍራ አይደለም። እንዲህ ባለ እስር ቤት ውስጥ መሞት ቀላል ነው። እኛ ከመንግስታችን ባገኘነዉ ትልቅ ድጋፍ ነጻ ወጥተናል። በርካቶች ግን አልታደሉም። ባልደረቦቻችን እዚያው ናቸው። አሁንም እዚያው ናቸው” ይህ ቃል ከእስር በተፈቱ ማግስት የተናገሩት ነው። ይህ ብቻም አይደለም በስማቸው የርዳታ ድርጅት በማቋቋም የህግ፣ የመድሃኒት፣ የእስረኞቹን ቤተሰቦች በገንዘብ ለመርዳት ቃልም ገብተው ነበር።

አትረሱ! ሚዲያ አይርሳችሁ! በሚዲያ መረሳት ሞት ነው! ነጻ ሚዲያ የሌለበት አገር አደጋ ውስጥ ነው! ነጻ ክርክርና ነጻ ሚዲያ የሌለበት አገር ሰላምና መረጋጋቱ አስተማማኝ አይደለም። ነጻ ሃሳብና ነጻ ህዝብ መፈጠር አለበት። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩም ሆነ በማንነቱ ለነጻነት አዲስ አይደለም። በእስር ለሚማቅቁ መጮህና ደጋግሞ ያለመሰልቸት መከራከር የሚዲያዎች ሁሉ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል። እስረኞች ሲባሉ ደግሞ ሁሉንም ነው። በሚዲያ አትረሱ! ሚዲያ ያልደረሰላቸው ወገኖች የሚዲያ ያለህ የሚሉ ወገኖች አንደበትና ጠበቃ ከመሆን በላይ ታላቅ ስራ የለም። ብዙ የተረሱ አሉ።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

goolgule.com

ሰራዊታችን ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ፡ ብዛት ያላቸው ሴት ታጋዮችም ግንባሩን ተቀላቀሉ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ነበልባል ጦር ጥር 17-2005 ዓ.ም በወልቃይት ጎብለል በተሰኘ የወያኔው መከላከያ ካምፕ ላይ በወሰደው ድንገተኛ ማጥቃት በካምፑ የሚገኙ የመከላከያ አባላትን ደምስሷል። በውጤቱም 25 ሙት 36 ቁስለኛ እንዲሁም  20 ክላሽንኮፍ ጠብመንጃ ፣ 4 የእጅ ቦንብና 1 ስናይፕር ጠብመንጃ ከነ ሙሉ ትጥቁ በመማረክ በማግስቱ ማለትም በትናንተናው እለት በቀጠለው የነበልባል ሰራዊት ወታደራዊ ጥቃት በወልቃይት ጠበቆ በተባለ ቦታ 24 የአገዛዙ ታጣቂዎች ሙትና 29 ቁስለኛ ሆኗል። በድምሩ በሁለት ቀናት ውጊያ በጠቅላላው 49 ሙት 65 ቁስለኛ ሲሆን፦ የአምባገነኑ አገዛዝ ሰራዊት የአርበኛውን ጡጫ መቋቋም ተስኖት እግሬ አውጭኝ ብሎ ከመፈርጠጡም ባሻገር የውጊያ ሞራሉ ክፉኛ በመዳከሙ ምክንያት በአድጎሹ ፣ አደባይ፣ሁመራና እድሪስ አካባቢ የሚገኙ የጦር አመራሮች በመሰባሰብ የመልሶ መቋቋም እንቅስቃሴ ላይ እንደተወጠሩ ታውቋል።

ነበልባል በመባል የሚታወቀው ልዩ ኮማንዶ የኢህአግ ሰራዊት በአርማጭሆ፣ ጠገዴና ወልቃይት ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት በመፈፀምና ሕዝቡን በማንቃት እንዲሁም በማስታጠቅ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ሴት ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ያሉበት በርካታ ወጣቶችን ወደ ትግሉ ጎራ እንዲቀላቀሉ አስችሏል።

ግንባሩን በጥር 18-2005 ዓ.ም የተቀላቀሉ ሴት አርበኞች የወቅቱን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያም እኛ ሴቶች አገራችን ኢትዮጵያ አይታው በማታውቅ ሁኔታ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካው መስክ አዘቅት ውስጥ እንደምትገኝ አብራርተው የእነሱ የትጥቅ ትግልን የመጨረሻ አማራጭ አድርገው የደም፣ የአጥንት፣ የጊዜ፣ የጉልበት፣ የእውቀት ብሎም የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈለ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትን ለመቀላቀል ኢትዮጵያዊነት ስሜታቸውና ሕሊናቸው እንዳስገደዳቸው በመግለፅ መላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ዘር፣ ቋንቋ፣ ሐይማኖትና ፆታ ሳይለይ ከትግሉ ጎራ በመሰለፍ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ከጥፋት ሃይሉ የእብሪተኛ ቡድን የምናላቅቅበት ወቅት አሁን ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን በጥር 18-2005 ዓ.ም የተቀላቀሉ ሴት አርበኞች አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር

 ecadf.com

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ክፍያ ሳይፈጽም ጫወታ ማሰራጨቱ የሚዲያ ስነምግባርን የጣሰ ውንብድና ነው ተባለ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለ ኤል ሲ ቱ የተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ ክፍያ ሳይፈጽም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዛንቢያ ቡድን ጋር ያደረገውን ጫወታ ማሰራጨቱ የሚዲያ ስነምግባርን የጣሰ ውንብድና ነው ተባለ::

ምንጮቻችን ባደረሱን መረጃ መሰረት የአፍሪካ ዋንጫ የቴሌቪዥን ስርጭት ባለመብት ለሆነው ለ ኤል ሲ 2 ክፍያ ሳይፈጽም ስርጭቱን ማስተላለፉ ተመልክቶል::

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተፈጸመውና ውንብድና የተሰኘው ለስርጭቱ ባለመብት የ 18 ሚሊዮን ብር ሳይከፍል ጠልፎ በህገወጥ መንገድ ባስተላለፈው ጨዋታ ባለመብት የሆነው ድርጅት በህግ ይጠይቀው አይጠይቀው የተባለ ነገር የለም::

የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያና የዛምቢያ ጨዋታ ሲደረግ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ክፍያ ሳይፈጽም ጫወታውን በውንብድና በመውሰድ እያስተላለፈ መሆኑን ከደቡብ አፍርካ የስፓርት ተንታኞቹ እየተቹበት እንደነበር ያገኘነው መረጃ ያስረዳል::

ምንጮች እንዳመለከቱት የኢትዮጵያና የዛምቢያ ጨዋታ እየተካሄደ እያለ ያለክፍያ በመጥለፍ ኢቲቪ ሲያስተላልፍ የነበረው ስርጭት ሲቆረጥ በዲኤስ ቲ ቪ ጨዋታውን የሚከታተሉ ያለችግር ማየታቸውን ለመረዳት ተችሎል::

አሁን ዘግይቶ በደረሰንመረጃ መሰረት የተቀሩትን ጨዋታዎች ከባለመብቱ ድርጅት ተከራይቶ ለማሳየት የ ኢቲቪ ሰዎች እየተደራደሩ መሆኑ ተመልክቶል:

Esat news

ፓሊሶች በአራት ኪሎ የሚገኙ ቤቶችን በእሳት አቃጠሉ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ለረጅም አመታት በአራት ኪሎ አካባቢ የኖሩ  ሰዎች ቦታው ለሼራተን ሆቴል ማስፋፊያ ይፈለጋል በሚል ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ሲነገራቸው እንደቆየ የተናገሩት አይን እማኞች፣ ነዋሪዎቹ በበኩላቸው መንግስት ተተኪ ቤት እስካልሰጣቸው ድረስ አካባቢውን ለቀው እንደማይሄዱ ሲከራከሩ ቆይተዋል። ዛሬ ጧት ወደ አካባቢው ያቀኑት ፖሊሶች ነዋሪዎቹ እቃዎቻቸውን ሳያወጡ በቤታቸው ላይ እሳት በመልቀቅ ቤታቸውን አቃጥለውባቸዋል። ነዋሪዎቹ በጩሀት ወደ ፓርላማ በመሄድ አቤት ቢሉም ሶስት ሰዎችን በመወከል ችግራቸውን እንዲያቀረቡ ተነግሮአቸዋል። ፖሊሶች ወደ አካባቢው በመድረስ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ ነዋሪዎችን አባረዋቸዋል።

አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአይን ምስክር ለኢሳት እንደገለጡት፣ ተማሪዎች ደብተራቸውን እንኳን ሳያወጡ ቤታቸው እንደተቃጠለባቸው፣ ብዙዎችም በከፋ ችግር ላይ መውደቃቸውን ገልጸዋል።

በኢትጵያ ውስጥ በልማት ስም እየተበራከተ የመጣውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አለማቀፍ ሰብአዊ መብት ተማጓች ድርጅቶች ችላ እንዳሉት ተመልክቷል። በአላማጣ ላለፉት አንድ ወራት የከተማው ህዝብ በልዩ ፖሊሶች ሲዋከብ እንደነበርመዘገባችን ይታወሳል። በአዲስ አበባ ላፍቶ ክፍለከተማ ቤታቸው የፈረሰባቸው በርካታ ነዋሪዎች አሁንም በከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

 

 Esat news

ልማታዊው ኪስ አውላቂ (ክንፉ አሰፋ)

ማስታወሻ፡  ባለፉት ጊዚያት በጫጫርኳቸው አጫጭር ጽሁፎቼ፤ ገንቢ ትችቶች ለላካችሁልኝ አንባብያን ሁሉ ምስጋናዬ የላቀ ነው። በአንጻሩ አፍራሽ ትችቶች በስማችሁ ጽፋችሁ የላካችሁልኝ ወገኖችንም አደንቃለሁ። ነገር ግን በብእር ስም ራሳችሁን በመደበቅ፤ ነውር እና አሳፋሪ የሆነ የፈጠራ ስራ ለምትሰሩ ደግሞ፡ ልቦና ይስጣችሁ ከማለት ውጭ የምለው የለም። ሰውን ዘልፎ ለመጻፍ እንቅልፋቸውን የሚያጡ ሰዎችን ፈረንጆቹ ‘ባለ ትንሽ ጭንቅላቶች’ ይሏቸዋል። ችግሩ ከአስተዳደግ ጉድለት፣ ከአስተሳሰብ ድህነት እና በራስ ካለመተማመን የሚመጣ የስነልቦና በሽታ ነው።

ክንፉ አሰፋ

Click here for PDF

የ ‘ህዳሴው ቦንድ’ ግዢ ግርግር ሞቅ ብሎ በነበረበት ሰሞን ይነገር የነበረ አነድ ቀልድ አለ። የ‘ማረሚያ’ ቤት ፖሊሶች እና ታጋዮች 500 ብር በሰረቀ ሌባ ላይ ውይይት ያደርሉ። ተከሳሹ ብሩን ያላግባብ ይስረቅ እንጂ በገንዘቡ የህዳሴውን ቦንድ መግዛቱ ነው ጉዳዩን ለውይይት የዳረገው።  ይህ ሌባ መታሰር የለበትም የሚሉት ታጋዮች፡ ለፖሊሶቹ ያቀረቡት መከራከሪያ ነጥብ ልማታዊ ሃሳብ ነበር። እንዲህ ነበር ያሉት፡ ‘ይህ ልማታዊ ኪስ አውላቂ ነው። እንዲያውም እንደዚህ አይነቶቹን ሌቦች የበለጠ እንዲሰሩ ማበረታታት ነው ያለብን።…’  ሁሉም በዚህ ሃሳብ ተስማሙና ሌባውን በያዘው ልማታዊ ተግባር የበለጠ እንዲሰራበት መክረው ለቀቁት።

ይህ እነግዲህ ቀልድ ነው። ቀልድ ደግሞ በመጠኑም ቢሆን የእውነታ ነጸብራቅ እነጂ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ክስተት አይደለም። ‘ልማታዊ’ የሚለው ቃል ትርጉሙ ተዛብቶ ምን ያህል እየተቀለደበት መሆኑን ከዚህ ቀልድ ግንዛቤ እንወስዳለን። በዚህ ላይ ወደሗላ እመለስበታለሁ።

ቀልዱን በቀልድ እንለፈውና አንድ ምሽት በኢ.ቲ.ቪ. ያየሁትን እውነታ ላውጋችሁ። ኢ.ቲ.ቪ. በሚያዘጋጀው የትምህርት ቤቶች ጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ‘ቦንድ ማለት ምን ማለት ነው?’ የሚል የ500 ብር ጥያቄ ቀርቦ ነበር። ከተወዳዳሪዎቹ አንዱ መልስ ሰጠ። እነዲህ ሲል፣ “ቦንድ ማለት፡ መንግስት በህዝብ እጅ ያለውን ጥሬ ገንዘብ ለአንድ አላማ ወደ ባንክ እንዲገባ ለማድረግ የሚጠቀመበት ዘዴ ነው።”

“ጥያቄው በትክክል ተመልሷል!” የሚል መልስ ነበር ህዘብ ከጠያቂ ጋዜጠኛው ይጠብቅ የነበረው። ጠያቂው ግን ተወዳዳሪው ትክክል እንዳልመለሰ ተናግሮ፡ ጥያቄውን ተመልካቾች  እንዲመልሱለት ጋበዘ። አነዱ ‘ልማታዊ’ ተመልካች ከመሃል ተነስቶ “ትክክል” የተባለለትን መልስ ሰጠ። መልሱ ይህ ነበር፣  “ቦንድ ማለት ወለዱ ከግብር ነጻ የሆነ የቁጠባ ዘዴ ነው። ”

በዚህ ልማታዊ ጋዜጠኛ የተሳሳተ የቦንድ ትርጉም ተወዳዳሪ ተማሪው ብቻ ሳይሆን፤ የቴሌቭዥኑ ታዳሚዎችና ተመልካቾችም በሙሉ ቀልጠዋል። ይህ ጥያቄ በትምህርት ቤት ፈተና ላይ ቢመጣ ተመሳሳይ ‘ልማታዊ’ መልስ ያልሰጡ ተማሪዎች አያልፉም ማለት ነው።

በአጭር አነጋገር ቦንድ ማለት፤ ህዝቡ እንዲቆጥብ ታስቦ ሳይሆን መንግስት የገንዘብ እጥረት ሲኖርበት ከህዘብ ላይ በብድር መልክ የሚሰበስበው ገንዘብ ማለት ነው።  ቦንድ መሸጥ አዲስ ነገርም አይደለም። የምእራቡ አለም መንግስታትም በአንደኛው እና በሁለተኛው የአለም ጦርነቶች ወቅት የገንዘብ እጥረታቸውን ለመሸፈን ለሕዝብ ቦንድ ይሸጡ ነበር። ዩናይትድ ስቴትስ ለሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ገንዘብ ስላስፈለገ፤  ፕሬዚዳንት ሩዝቬልት የተጠቀሙት ዘዴ ‘የነጻነት ቦንድ’ ያሉትን ኩፖን በመሸጥ ነበር። ጀርመን፣ እንግሊዝና ካናዳም በተሳካለት የጦር ቦንድ ሽያጭ የሚጠቀሱ ሃገሮች ናቸው።

ወደ ዋናው ነጥብ ስንገባ ልማታዊ መንግስት የሚለው ጽንሰ-ሃሳብ የመነጨው በ20ኛው ክፍለዘመን መገባደጃ አካባቢ ከነበሩ የምስራቅ ኤሽያ ሃገሮች ነው። እነዚህ በወቅቱ እጀግ ደካማ የሚባሉ የኤሽያ ሀገሮች፡ በመንግስት የሚመራ የማክሮ ኢኮኖሚ እቀድ በማውጣት የሃገራቸውን ኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ስልጣን አጥብቀው በመያዝ ወደ ምጣኔ ሃብት እድገት ያመሩ ናቸው።

ልማታዊ ነን የሚሉ እነዚህ መንግስታት የብዙሃን ፓረቲ ዲሞክራሲን፣ የፕሬስ ነጻነትንና የመሳሰሉ መብቶቸን በመጠኑም ቢሆን ያፈኑ ቢሆኑም ‘ልማት ከሰብአዊ መብት ይቀድማል!’ ከሚሉት ከኛዎቹ ገዚዎች ፍጹም የተለዩ ናቸው። ልማታዊ መንግስታት  ከህዝባቸው ጋር ሆድና ጀረባ በመሆን ከህዝባቸው ጋር ጦርነት ሲገጥሙ አላየንም። እነዚህ ሃገሮች ትኩረታቸውን በሙሉ በኢኮኖሚ እድገት ላይ በማድረግ ህዝባቸው በምግብ ራሱን እንዲችል ከማድርግ አልፈው የአብላጫው ህዝብ የኑሮ ሁኔታ በእጀጉ እንዲሻሻል ረድተዋል።

ዛሬ የደቡብ ምስራቅ እሺያ ሀገሮች እና የቻይና ዜጎች የፖለቲካ ተሳትፏቸው እጅግ ዝቅተኛ ይሁን እነጂ የኑሮ ደረጃቸው በእጅጉ ተሻሽሎ እናያለን። በአንጻሩ በልማታዊው የኢህአዴግ ስርአት በግልጽ የማይታይ የሁለት አሃዝ እድገት መጠን ከማውራት ያላለፈ እድግት ባሻገር የህዝቡ የኑሮ ደረጃ ሲብስ እንጂ ሲሻሻል አይታይም። በልማታዊ መንግስት ስም 80 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዘብ ከነጻነቱም፣  ከኑሮውም ሳይሆን አሁንም በባሰ የኑሮ ጉስቁልና ውስጥ ይገኛል።

በቅርብ ከኢትዮጵያ የመጣ አንድ ሰው፡ የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ ከአንድ የእግር ኳስ ስታዲየም ጋር በማስመሰል ይገልጸዋል።  በአንድ የእግር ኳስ ስታዲየም ውስጥ ያሉ ሰዎች በሶስት ምድቦች ይከፈላሉ፤ ተጫዋቾች፣ አጫዋቾች እና ተመልካቾች።  የኢትዮጵያም ህዝብ እንደዚሁ በሶስት ምድብ ይከፈላል። ባለስልጣናቱ አጫዋቾች፣  አጫፋሪዎቹ (ለባለስልጣናቱ አየር ባየር ቢዝነስ የሚሰሩት) ተጫዋቾች – ሲሆኑ ህዝቡ ደግሞ የዚህ ጨዋታ ተመልካች ሆኗል።

ሕዝቡ የሃገር ሃብት ነው። ህዝብን ሳያሳትፉ ስለ እድገት ማውራት ከቶውንም የሚቻል አይሆንም። በተለይ ደግሞ ዲያስፖራውን። የምስራቅ ኤሸያ እድገት ሚስጥር ዲያስፖራው መጠነ ሰፊ ገንዘብ እና እውቀትቱን ይዞ በሃገሩ መስራት መቻሉ ነበር።

ህወሃቶች እንደሚሉት ‘ቶክሲክ’ (መርዘኛ) ዲያስፖራ እያሉ የሃገር ሀብት የሆነውን የዲያስፖራ ሃይል ቢሳደቡ ኖሮ እስያውያን እዚህ ደረጃ ባልደረሱ ነበር። በተማረ የሰው ሃይል፣ በቴክኖሎጂ እና የውጭ ምንዛሪ እጥረት ውስጥ ሆኖ ዲያስፖራውን በጅምላ ጠላት ማድረግ ከእብደት ውጭ ሌላ ትርጉም አይሰጠውም። የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የሰራው ወንጀል ቢኖር ‘ሰብአዊ መብት በሃገሪቱ ይከበር!’ ብሎ መጮሁ ብቻ ነው።

በአንድ ሃገር ኢኮኖሚ ላይ የዲያስፖራውን ሚና ለማሳየት ምሳሌ ሊሆነን የሚችለው የሲንጋፖር የእድገት ታሪክ ነው።  ሲንጋፖር ከታላቋ ብሪታንያ ቅኝ ግዛት ነጻ በወጣች ማግስት ህዝቧ በድህነት ውስጥ ነበር። ሲንጋፖር አንዳች የተፈጥሮ ሃብት የሌላት ፍጹም ድሃ የሆነች ደሴት ነበረች። ከዚህ ድህነቷ ለመላቀቅ የነበራት አማራጭ የተማረ የሰው ሃይሏን መጠቀም ብቻ ነበር።  አንድ የሲነጋፖር ዜጋ እነዲህ ብሎ ነበር ያጫወተኝ።

‘ሲንጋፖር በተፈጥሮ ሃብት ያልታደለች የትናንሸ ደሴቶች ክምችት ነች። ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻ እንደወጣች የመጠጥ ውሃ እንኳን አልነበራትም። በወቅቱ የተረፈን ጭንቅላታችን ብቻ ነበር – የተማረ የዲያስፖራ ሃይል። ከባዶ በመነሳት ሲንጋፖር አሁን ያለችበት ደረጃ እንድትደርስ ያደረጉት እውቅት እና ቴክኖሎጂ ይዘው የመጡ የዲያስፖራ ምሁራን ናቸው።’

‘የሲነጋፖር ምሁራን ከጎረቤት ሃገር ከማሌዢያ የሚፈሰውን ቆሻሻ ውሃ በቱቦ አማካይነት ወደ ሃገሪቱ እንዲገባ ካደረጉ በሗላ፡  ውሃውን እያጣሩ ለማሌዥያ መልሰው መሸጥ ጀመሩ።…’

የእውቀት ኢኮኖሚን የያዘ የዲያስፖራ ሃይልዋን ያልናቀችው ሲንጋፖር ዛሬ የኢንዱስተሪ ሃገር ናት። አንባገነንነቱ እና ሙስናው እነደተጠበቀ ሆኖ፡ ይህቺ ደሴት የበርካታ ሀገሮች የእድገት ምሳሌ (ሞዴል) ለመሆንም በቅታለች።

የኤርትራው ኢሳያስ አፈወረቂ እንኳን፤ በትረ ስልጣናቸውን የጨበጡ ሰሞን ‘ኤርትራን የአፍሪካ ሲንጋፖር እናደርጋታለን።’ ብለው ነበር። ይልቁንም ከ21 አመታት በሗላ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራን ሲን ጋፖር ሳይሆን ‘ሲንግል ኤንድ ፑር’ አደረጓት እያሉ ተቺዎች ይቀልዱባቸዋል። የኢትዮጵያም የእድገት ማነቆ ምስጢሩ በስብአዊ መብት አፈናው ሳቢያ ለተማረ የሰው ሃይል እና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ቦታ ካለመስጠቱ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ልማታዊ መንግስት ነን ይበሉ እነጂ፤ የልማታዊነት ትርጉሙ እንኳን የገባቸው አይመስልም። አሁን የተያዘው የኮብል ሰቶን ልማትን እንመልከት። የኮበልስቶን ስራን ሊሰራ የሚችል ያልሰለጠነ የሰው ሃይል በገፍ ባለበት ሃገር፤ በባችለር እና በማስተርስ ዲግሪ ከዩኒቨርሲቲ የሚመረቅ ዜጋ ሁሉ ድንጋይ መፍለጥ፣ መጥረብ እና መዘርጋት እንዲሰራ መደረጉ ለብዙዎች እንግዳ ነገር ነው። የተማረ እና የሰለጠነ የሰው ሃይልን በጉልበት ስራ የሚያሰማራ ልማታዊ መንግስት በኢትዮጵያ ብቻ ነው የታየው። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም በመገናኛ ብዙሃን ቀርበው በባችለር እና በማስተርስ ዲግሪ ከዩኒቨርሲቲ ለሚመረቁ ተማሪዎች የኮብል ሰቶን ስራ አዋጭ ስራ መሆኑን ሲናገሩ ተደምጠዋል።  አዋጪ ስራ መሆን አንድ ነገር ነው።  የሃገር እድገት ደግሞ ሌላ።  የሚያሳዝነው አማራጭ ያጡ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን የዚህ የተሳሳተ ልማታዊ አስተሳሰብ ሰለባ መሆናቸው ብቻ ነው።

የህንጻ  እን የከተማ መንገድ ግንባታ የከተማን ውበት ሊያሳምር ይችል ይሆናል። በህንጻ ግንባታ ከተማ ልትቀየር ትችልም ይሆናል። ይህ ግን ከሃገር እድገትና ከዜጎች የኑሮ መለወጥ ጋር ፈጽሞ ሊገናኝ አይችልም።  ምሁራኑ ድንጋይ ሲፈልጡ፣ ሲጠርቡ እና ሲያነጥፉ፡ የነሱን የሙያ ቦታ ያልተማሩ ካድሬዎች እነዲይዙት ማድረግ። ሃገር በዚህ አይነት ሂደት ታድጋለች የሚል የልማታዊ መንግስት ፍልስፍና የለም። ይህ እንዲያውም በልማት ስም የሚሰራ መንግስታዊ ወንጀል ነው። ኪስ አውልቆ ቦንድ ከመግዛት የማይተናነስ ወነጀል።

ecadf.com

መነቀል ያለበት ስር የሰደደ የወያኔ ዘረኝነት

የግንቦት 7 ንቅናቄ

ዘረኛዉ የወያኔ ስርአት የኢትዮጵያን ህዝብ ለጥቂት አመታት ኢትዮጵያዊያንን ባሰረና በገደለ ቁጥር ገንዘብ የሚሰጡትን አለም አቀፍ ድርጅቶችና አርዳታ ሰጪ አገሮች ደግሞ 21 አመት ሙሉ ካታለለበት መንገድ አንዱ የፌዴራል ስርአት መስርቼ ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር አደረኳት የሚለዉ ባዶ አባባሉ ነዉ። ይህንን ተጋልጦ እርቃኑን የቀረ አባባል የኢትዮጵያ ህዝብ ተገንዝቦ ወያኔን መታገል ከጀመረ ቆይቷል፤ ዋና ዋናዎቹ እርዳታ ለጋሾችም ቢሆኑ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ግድ የሌለዉ ወያኔ ወጣቶቻችንን እየገበረ ጥቅማቸዉን ስለሚያስከብርላቸዉ ነዉ እንጂ ወያኔ እንኳን እየደገፉ እርዳታ የሚሰጡት በአንድ ተርታም አብረዉ ለመቀመጥ የማይመች የእኩዮች ስብስብ እንደሆነ ካወቁ ቆይቷል።

ህወሀት በፌዴራል ስርአቱ ዉስጥ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት ነዉ ብሎ በሚጠራዉ ፓርላማ ዉስጥ ያለዉ መቀመጫ 8 ብቻ ነዉ። እዚህ ፓርላማ ዉስጥ የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ የሚለዉ ህወሀት ነዉ፤ ትግራይ ደግሞ ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ክልል ናት። የተቀሩት 8 ክልሎች በዚህ የእኩልነት ምልክት በሆነዉ ፓርላማ ዉስጥ ያላቸዉ የመቀመጫ ብዛት 569 ነዉ። ሆኖም በወያኔ መንደር የፖለቲካ ስልጣን ምንጭ ህዝብ ሳይሆን ጠመንጃ ነዉና ወያኔ ፓርላማዉ  ዉስጥ 8 ወንበር ብቻ ይዞ 569 ወንበር ያላቸዉን የኦሮሚያን፤ የአማራን፤ የደቡብ ክልልንና የተቀሩትን አምስት ክልሎች እንደ መኪና ይነዳቸዋል። የየክልሉን መሪ ይሾማል፤ ይሽራል ወይም የማይስማማዉን የክልል ባለስልጣን ያስራል። ፓርላማዉ ዉስጥ አንድ መቶ ሰባ ስምንት፤ አንድ መቶ ሰላሳ ስምንትና አንድ መቶ ሀያ ሦስት መቀመጫ ያላቸዉ የኦሮሚያ፤ የአማራና የደቡብ ክልል ፓርቲዎች በራሳቸዉ ጉልበትም ሆነ ህልዉና ስለሌላቸዉ አንዱ ከሌላዉ የበለጠ ስልጣን ወይም ሹመት ለማግኘት አንጋጥጠዉ ወደ ላይ የሚመለከቱት ህወሀትን ነዉ።

ለመሆኑ ወያኔ የፌዴራል ስርዐት መስርቼ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት አረጋገጥኩ ሲል ምን ማለቱ ነዉ? እኩልነቱ የፖለቲካ ነዉ  የኤኮኖሚ? ወይስ በየአመቱ ህዳር ወር ላይ የፌዴራልዝም ቀን ሲከበር እንደምናየዉ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠዉ በዘፈን ብቻ ነዉ? የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስርዐት ከላይና ከታች የሚቆጣጠረዉና ይህንኑ የፖለቲካ ስርአት የሚደግፍ የኤኮኖሚ መዋቅር ዘርግቶ የአገራችንን ኃብት የሚቦጠብጠዉ ህወሀት ብቻ ነዉና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ተረጋገጠ የሚባለዉ አባባል ከተራ የቃላት ድርደራ ዉጭ ሌላ ምንም ትርጉም የለዉም።

አፄ ቴዎድሮስን እንደ ልጅነት ሞዴሉ የሚመለከተዉ ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም የመጀመሪያዉን የኢትዮጰያ ዘመናዊ ወታደራዊ እንጂኔሪንግ ተቋም ሲመሰርት ስሙን “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ ነበር የሰየመዉ። ስያሜዉ የአፄ ቴዎድሮስ ስራና ስም ህያዉ ሆኖ እንዲኖር ለማድረግ የተደረገ ሙከራ እንደነበር ግልጽ ነዉ። የኢትዮጵያን የቀድሞ መሪዎች በጅምላ የሚዘልፈዉ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ከአንዲት የአገር ዉስጥ ጋዜጠኛ ጋር ባደረገዉ ቃለ ምልልስ አፄ ቴዎድሮስ ጋፋት ላይ ያሰሩትን መድፍና መንግስቱ ኃ/ማሪያም “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ  የሰየመዉን ወታራዊ ተቋም አስመልክቶ ሁለቱንም መሪዎች ሲያንቋሽሽ ተደምጧል። የሚገርመዉ ዛሬ ወያኔ የብረታብረት እንጂኔሪንግ ኮረፓሬሺን ብሎ የሚጠራዉ ግዙፍ የሲቪልና ወታደራዊ እንዱስትሪ ተቋምና በዚህ ተቋም ዉስጥ የሚገኙ ዋና ዋና ፋብሪካዎች ደርግ  “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ የጀመራቸዉ የከባድ እንዱስትሪ ጅምሮች ናቸዉ። በ1970ዎቹ አጋማሽ ላይ “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ስራዉን ሲጀምር የፋብሪካዉ ሀላፊዎች፤ እንጂኔሮች፤ የመምሪያ ሀላፊዎችና ቴክኒሺያኖች የስራ ዕድል የሚያኙት የትምህርት ደረጃቸዉ፤ ችሎታቸዉና የሰራ ልምዳቸዉ ብቻ እየታየ ነበር፤ ወይም ትግርኛ ስለተናገረ ስራ የሚከለከል አማርኛ፤ ኦሮምኛ ወይም ሌላ ቋንቋ ስለተናገረ አድሎ የሚደረግለት ዜጋ አልነበረም። ዛሬ ወያኔ ከደርግ ስርአት ተረክቦ የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ብሎ በሰየመዉ እንዱስትሪ ዉስጥ አብዛኛዉን የሀላፊነት ቦታ የያዙ ሰዎች ለቦታዉ የበቁት በስራ ልምዳቸዉና ችሎታቸዉ ሳይሆን የተወለዱበት ዘርና የሚናገሩት ቋንቋ እየታየ ነዉ። ወታራዊዉ አምባገነን ደርግም ሆነ  ወያኔ ይህንን እንዱስትሪ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ከባድ እንዱስትሪ ዘርፍ መሰረት ይሆናል የሚል ራዕይ ነበራቸዉ። ልዩነታቸዉ የእንዱስትሪዉ አስፈላጊነት ላይ ሳይሆን እንዱስትሪዉን ማን ይቆጣጠረዋል የሚለዉ ጥያቄ ላይ ነዉ። ደርግ በሱ መሪነት ለማንም ችሎታ ላለዉ ኢትዮጵያዊ የእንዱስትሪዉን በር የከፈተ ሲሆን ወያኔ ግን እንዱስትሪዉ እንዳለ በአንድ ዘር ቁጥጥር ስር እንዲገባ አድርጓል።  ደርግም ወያኔም አምባገነኖች ስለሆኑ አንዱስትሪዉን ከህዝብ ቁጥጥር ዉጭ አድርገዉታል፤ ወያኔ ግን ከአምባገነንም የጎሳ አምባገነን ስለሆነ ይህንን ትልቅ እንዱስትሪ ሙሉ በሙሉ በትግርኛ ተናጋሪዎች ቁጥጥር ስር አድርጎታል።

ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ባለለፉት ሦስት አመታት ይህንን ወያኔ ገነባሁ የሚለዉን የፌዴራል ስርአትና በስርአቱ ዉስጥ የተለያዪ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሚጫወቱትን ሚና በመረጃ አስደግፎ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ አቅርቧል። የዛሬ ሁለት አመት ግንቦት ሰባት በኢትዮጵያ መላከያ ሰራዊት ዉስጥ የተዘረጋዉን የወያኔ የዘረኝነት መረብ ከሰሞኑ ደግሞ የኢትዮቴሌኮምን የዘረኝነት አደረጃጀት በመረጃ በማስደገፍ ለህዝብ ማቅረቡ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮረፓሬሺንን የዘረኝነት አደረጃጀትና በዚህ አደረጃጀት ዉስጥ ማን ምን እንደሆነ ያጣናዉን የጥናት ዉጤት በመረጃ አስደግፎ ያቀርባል።  ግንቦት ሰባት ሃያ አራት ሰአት ሙሉ የሚከታተሉትን የወያኔ የደህንነት ሰራተኞች ከበባ ጥሶ የወያኔን ዘረኝነት የሚያጋልጡ መረጃዎችን ከራሱ ከወያኔ ጓዳ እየጎተተ አዉጥቶ ለህዝብ የሚያቀርበዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን ዘረኝነት አያውቀዉም በሚል አስተሳሰብ አይደለም። ግንቦት ሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ የፈጠረዉ ከፍተኛ የመረጃ ጉድለት አለ ብሎ ያምናል፤ስለሆነም ህዝቡ የወያኔን ዘረኝነት ቢረዳም መጠኑን፤ስፋቱንና ጥልቀቱን በሚገባ ላያዉቅ ይችላል ብለን እናምናለን። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በየቀኑ ደሙን እንደ መዥገር የሚመጠዉን ወያኔን የመሰለ የጀርባ ላይ አጥንት ተሸክሞ መኖር የለበትም ብለን ስለምናምን ህዝብን ለትግል ከምናዘጋጅበትና ከምናነሳሳባቸዉ መንዶች ዉስጥ አንዱ እንደዚህ ህዝብ በገዛ አገሩ “እኩል አደረግንህ” ብለዉ በሚነግሩት ከሀዲዎች ቅኝ አገዛዝ እየተገዛ መሆኑን በማሳወቅ ነዉ።

ባለፈዉ ሳምንት የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ዋና ዳይረክተር ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘዉ ፓርላማ ዉስጥ ተገኝቶ የኮርፓሬሺኑን የሁለት አመት የስራ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ኮርፓሬሺኑ የግል ባለኃብቶችን አያሳትፍም እንዳዉም እያቀጨጫቸዉ ነዉ፤ ለሙስና የተጋለጠ ነዉ፤ ደግሞም አብዛኛዉ የኮርፖሬሺኑ ሰራተኛ የመከላከያ ሰራዊት አባል ነዉና ይህ አሰራር  ሠራተኞችን ለማስተዳደር አስቸጋሪ አይሆንም ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዉለት ነበር። የግሉን ዘርፍ መቅጨጭ በተመለከተ ኢትዮጵያ ዉስጥ ቀድሞዉንም ቢሆን “የወያኔ ዘርፍ” እንጂ የግል ዘርፍ የሚባል ነገር የለምና ጥያቄዉ መቅረብም አልነበረበትም።  ሙስናም ቢሆን የወያኔ ስርዐት ዋናዉ መገለጫ ባህሪይ ስለሆነ ወያኔ እስካልተወገደ ድረስ ሙስና  “ሙስናን እናጠፋለን” ስለተባለ ብቻ የሚጠፋ ነገር አይደለም። ግንቦት ሰባትን እጅግ በጣም ያሳዘነዉና ያስገረመዉ ነገር ያንን ወያኔ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት ነዉ ብሎ የሚናገርለትን ፓርላማ ያስጨነቀዉ (ተጨንቆ ከሆነ) የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን በአንድ አናሳ ብሔረሰብ ሙሉ ቁጥጥር ስር መዉደቁ ሳይሆን አብዛኛዉ የኮርፖሬሺኑ ሰራተኞች የመከላከያ ሰራዊት አባላት መሆናቸዉ ነዉ። በእርግጥ የአንድ ትልቅ ኮርፖሬሺን ሰራተኞች በአብዛኛዉ  የጦር ሠራዊት አባላት ሲሆኑ የአሰራርና የአስተዳደር ችግር መፈጠሩ አይቀርም፤ ሆኖም የሠራዊቱ ታማኝነት  ለህዝብ ታዛዥነቱ ደግሞ ለህገ መንግሰስቱ ብቻ ቢሆን ኖሮ ይህ ችግር በቀላሉ የሚወገድ ችግር ይሆን ነበር።

ginbot 7 exposing woyane 1

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን በአምሰት አመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሺን ፕላን ዉስጥ የሚጫወተዉን ቁልፍ ሚና ፓርላማዉ በሚገባ የሚገነዘበዉ ይመስለናል፤ ታዲያ ይህ በአገር እድገት ዉስጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወተዉ ኮርፖሬሺን ሙሉ በሙሉ በአንድ ብሔር ቁጥጥር ስር ሲወድቅ ምነዉ የብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት የሆነዉ ፓርላማ አፉን ዘግቶ ተመለከተ? ፓርላማዉን ይበልጥ የሚገድደዉ የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በአንድ አናሳ ብሔረሰብ ሙሉ ቁጥጥር ስር ሆኖ ሌሎቹ ብሔረሰቦች ተመልካች ሲሆኑ ነዉ ወይስ የአንድ ኮርፖሬሺን ሰራተኞች  በአብዛኛዉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሲሆኑ ነዉ? ለመሆኑ የወያኔ ዘረኝነት በኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ዉስጥ ምን ያህል ዘልቆ ገብቷል? የኦሮሞ፤ የአማራ፤ የሶማሌ፤ የሲዳማና ሌሎቹም ብሔር ብሔረሰቦች በዚህ ለአገር እድገት ቁልፍ በሆነ ኮርፖሬሺን ዉስጥ የሚጫወትቱት ሚና ምን ይመስላል?

ginbot 7 exposing woyane 2

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን በአስራ አንድ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች የተዋቀረ ሲሆን በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎቸን ያስተዳድራል፤ ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀቀበት ቀን ድረስ ቁጥራቸዉ በዉል ተለይቶ ባይታወቅም አስራ ሦስቱ እንዱስትሪዎችም እያንዳንዳቸዉ በስራቸዉ ብዙ ፋብሪካዎችንና የማምረቻ ተቋሞችን ያቀፉ ናቸዉ። የኮርፖሬሺኑን  አስራ አንድ ትላልቅ መምሪያዎችና አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱሰትሪዎች በዋና ሀላፊነት፤ በዳይረክተርነተና በምክትል ዳይረክትርነት የሚመሩ 29 የከፍተኛ አመራር አባላት አሉ። ከእነዚህ 29 ከፍተኛ አመራር አባላት ዉስጥ 69 በመቶዉ ወይም ሃያዉ ህወሀት ሆን ብሎ ያስቀመጣቸዉ ትግርኛ ተናጋሪ የሆኑ ወታደራዊ መኮንኖች ናቸዉ።በዚህ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ያላቸዉ ቦታ 31 በመቶ ወይም ከእያንዳንዳቸዉ በቅደም ተከተል ሦስትና ስድስት ሰዎች ብቻ ሲሆን ከተቀሩት አምስት ክልሎች በዚህ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የተመደበ አንድም  ሰዉ የለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ እንዱስትሪ ለመገንባት በሚደረገዉ ጥረት ዉስጥ ከፍተኛዉን ሚና ይጫወታል የሚባለዉ የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን በሲቪልና ወታራዊ መምሪያዎች ተከፋፍሎ የተዳራጀ ሲሆን በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎች ይገኛሉ። እነዚህን እንዱስትሪዎች በማስተዳደሩ በኩል የብሔር ብሔረሰቦችን ድርሻ ወይም ኮታ ስንመለከት  ከአስራ ሦስቱ እንዱስትሪዎች ዘጠኙን የሚያስተዳድሩት የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። በኮርፖሬሺኑ ዉስጥ ከፍተኛ ስልጣን ከተሰጣቸዉ የትግራይ ተወላጆች ዉስጥ እነ ብረጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘዉ  የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን ዋና ዳይረክተር ፤ ኮ/ል ተከስተ ኃ/ማሪያም  በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ፕሮዳክሺን ግንባታ ሀላፊ ፤ ኮ/ል ፀጋሉ ኪሮስ በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ወታደራዊ ምርቶች ሀላፊ ፤ ኮ/ል ሙሉ ወ/ሰንበት በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ፕሮጀክቶች አስተደዳደር ሀላፊ፤ሻምበል ካህሳይ ክሽን የምርመራና ልማት ዳይረክተርና  ሻምበል ገ/ስላሴ ገ/ጊዮርጊስ የአቅም ግንባታና ስልጠና ማዕከል ዳይረክተርን የመሳሰሉ የህወሀት ታጋይ መኮንኖች ይገኙበታል።

ginbot 7 exposing woyane 3

ከትግራይ ዉጭ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔሰቦች በብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን እንዱስትሪዎች ዉስጥ ከፍተኛ የሀላፊነት ደረጃ ባለዉ የአመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ ዕድል ያገኙ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር አራት ብቻ ነዉ። ይህ ጥናት የተጠናዉ ከ2004 እስከ 2005 ዓም ባለዉ የአንድ አመት ግዜ ዉስጥ ነዉ። በ2004 ዓም የኢትዮጵያ ህዝብ 90 ሚሊዮን አንደሚሆን የተገመተ ሲሆን ከዚህ ቁጥር ዉስጥ በትግራይ ክልል  5.4 ሚሊዮን ህዝብ በተቀሩት ስምንት ክልሎች ደጎሞ 84.6 ሚሊዮን ሀዝብ ይኖራል ተብሎ ተገምቷል። ይህ ጥናት በዋናነት የሚያመለክተዉ በዋና ዋና የሀላፊነት ቦታ የተቀመጡትን ግለሰቦችና ግለሰቦቹ የመጡበትን ብሔር ስለሆነ ነዉ እንጂ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺንን የሰዉ ኃይል ምደባና የደረጃ እድገትን ጠለቅ ብለን ስንመለከት አብዛኛዎቹ እንጂኔሮችና ቴክኒሻኖች የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ፤ የደረጃ እድገትን በተመለከተም ከሌሎች ሰራተኞች ጋር ሲነፃፃር በፍጥነት የደረጃ እድገት የሚያገኙት እነዚሁ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። ይህ ደግሞ በአጋጣሚ የሆነ ነገር ሳይሆን ወያኔ በረሀ ዉስጥ እያለ አቅዶት ባለፉት ሃያ አመታት በስራ ላይ ያዋለዉ የረጂም ግዜ እቅድና ዝግጅት ዉጤት ነዉ።  ለምሳሌ ወያኔ ትግራይ ዉስጥ ኤም አይ ቲ  ወይም የመቀሌ ቴክኖሎጂ እንስቲቲዩት ብሎ የሚጠራዉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋም ተቀብሎ የሚያስተምረዉ የትግራይ ተወላጆችን ሲሆን ከዚህ ተቋም የሚመረቁ እንጂኔሮችና ተክኒሺያኖች ናቸዉ በኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን የሚሊታሪ ክንፍና በኢትዮቴሌኮም የስለላ ተቋሞች ዉስጥ ተመድበዉ ከፍተኛ የስለላ ስራ የሚሰሩት።

ginbot 7 movement exposing woyane 4

ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝና አገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚገኙ ቡችሎቹ የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ድርጅቶች በተለይ በዳያስፖራ ዉስጥ የሚገኘዉን ለእናት አገሩ ተቆርቋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጅምላ “የጥላቻ ፖለቲካ አራማጆች” እያሉ ለአመታት ሲዘልፉን ኖረዋል። የፖለተካ ትግላችን አላማና ግብ ከጥላቻ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለዉ ቢሆንም – ለመሆኑ ይህንን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተና አንዱን አለቃ ሌላዉን ተላላኪ፤ አንዱን የሚሾም ሌላዉን የሚሽር፤ አንዱን አብልቶ የሚያጠግብ ሌላዉን የበይ ተመልካች የሚያደርግ፤አንዱን የአገር መሪነት ቦታ ተረካቢ ሌላዉን ኮብልስቶን ድንጋይ ጠራቢ የሚያደርግ ስርዐት የሚወድ ማን አለ? ይህንን በንጹህ ዜጎች ደም እጁ የቆሸሰና ያደፈ ዘረኛ ስርአት ዉደዱ የሚለንስ ማነዉ? በምድርም በሰማይም የከሰሩ እነ ሚሚ ስብሀቱን የመሳሰሉ የፖለቲካ ሴሰኞች ሊነግሩን እንደሚፈልጉት ትግላችን የትግራይ ወንድሞቻችንንና እቶቻችንን በመጥላት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የትግላችን ብቸኛ አላማ ከትግራይ ወንድሞቻችን ጋር ሊያጋጩን የሚሞክሩትን የህወሀት ወንጀለኞች አስወግደን ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር ማድረግ ነዉ።

የግንቦት 7 ንቅናቄ

 

Austrian tourist killed in Ethiopia attack

Austrian tourist killed in Ethiopia attack

(AFP)

VIENNA — A 27-year-old Austrian tourist was killed in northern Ethiopia when his group was attacked during a whitewater rafting trip on the Nile, Austria’s foreign ministry said Monday.eth_bahir_dar_map

The attack occurred on Sunday near Bahir Dar, 550 kilometres (340 miles) northwest of the capital Addis Ababa, ministry spokesman Martin Weiss told AFP.

The victim was part of a group of 10 Austrians on an organised whitewater rafting trip in the region.

Four of the group had spent the night camping on the banks of the Nile when they were apparently attacked by robbers. The victim’s three companions were unharmed in the incident.

“There were gunshots,” Weiss told AFP.

One of the tourists “was mortally wounded, the three others managed to escape and called the Austrian embassy in Addis Ababa.

“The (local) authorities were later informed and we received information this morning that the three individuals were safe. Shocked but in safety,” he added.

“Technical equipment was stolen, the boats were damaged. It was probably a band of bandits.”

Weiss added the attack did not seem to have been political motivated, saying: “It was just a robbery.”

No arrests have been made, the ministry spokesman said.

In its latest travel advice on Ethiopia, published in November, the Austrian foreign ministry warned of “a heightened risk of terrorist attacks”.

In January 2012, five foreign tourists, including an Austrian, were killed on the slopes of the Erta Ale volcano in northern Ethiopia. Addis Ababa blamed the attack on groups trained and armed by neighbouring Eritrea, an accusation the Eritrean government denied.

 

 Abbaymedia.con

መገደብ የማይችል ሕዝባዊ እምቢተኛነት በኢትዮጵያ

ዳኛቸው ቢያድግልኝ

የትግራይ ተገንጣይ ቡድን እንደ መንግስት የመቆም አቅሙ ከእለት ወደ እለት እየተፍረከረከ መሄድም መዳህም አቅቶት ሲንገታገት እያየነው ነው። እንደ ፓርቲ ተሰነጣጥቆአል፣ እንደTigray People Front, TPLF መንግስት አርጅቶአል፣ እንደተገንጣይ ቡድንም ክህደቱን የትግራይ ሕዝብ አውቆበታል። የገንጣዩ ቡድን መሪዎችም አንዳንዶቹ ሞት ቀንሶአቸዋል፣ አንዳንዶቹ ጃጅተዋል፣ ጥቂቶቹም ታማሚ ሲሆኑ  ሌሎቹም ንቃት መለስ አድርጎአቸዋል። በአሮጌ ጨርቅ እንደተቋጠረ የበሶ ዱቄታቸው በየአቅጣጫው የሚያፈተልኩባቸው ጎጠኛ ሰራሽ ፓርቲዎቻቸውም አስተማማኝ አሽከር እንደማይሆኑ እያሳዩ ነው። ኦህዴድ ቀልዳችሁን አቁሙ ብሎ በድፍረት ሽቅብ ማየት ጀምሮአል። የበረከት ሰዎችም አማራነትን ለኛ ተውልን እያሉት ነው። እናም አደጋው ከምንጊዜውም የከፋ ይመስላል። ትግራይ በቀል ‘አረና ትግራይ’ በትግራይ ተገንጣዮች እየተደበደበ ነው። ዱላው እመንደሩ ድረስ ስለዘለቀ ክፋቱ ገፍቶ መጥቶአል።

ወይዘሮ አዜብ በመለስ ራዕይ ሊሸብቡት ባሌ ከመሰዋቱ በፊት የአምስት አመት ስትራቴጂ ለትግራይ እየሰራ ነበር የሚል ላሞኛችሁ አይነት ንግግር ለትግራይ ሕዝብ አሰምተዋል። መለስ የዋሸውን ያህል አሁን  የለም ብለው በስሙ ሁሉም ይዋሻሉ። መለስ ብቻውን የሚነድፈው የአምስት አመት ስትራቴጂ ሊኖር አይችልም። ካለ ደግሞ ጭፍን፣ ራሱን ብቻ አዋቂ የሚያደርግ በሌሎች ላይ እምነት ያልነበረው ብቸኛ ሰው ነበር ብለው መመስከራቸው ነው። ይህ አባባላቸው እንዲያውም ጥላቻን የሚያስፋፋና ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይበልጥ ይህንን ስርዓት እንዲታገለው ማበረታቻ ነው ያደረጉት። እሳቸው በተናገሩ መጠን የበለጠ ወያኔን ራቁቱን ያቆሙታል። ምክንያቱም በትግራይ ሕዝብ ስም የሚዘረፈው የሀገር ሀብት የአቶ መለስና ቤተሰባቸው እንዲሁም ጥቂት አጋሮቻቸው እንጂ የትግራይ ሕዝብ ሀብት ሆኖ አያውቅም። የሕዝብ ሀብት ከራሱ ከሕዝቡ ተደብቆ የሚከማች አይደለምና። ለዚሀም ነው አረና ትግራይና ሌሎች ተቃዋሚዎች በራሳቸው መንደር የጥቃት ሰለባ የሆኑት። ቢሮአቸው በቡልዶዘር እየፈረሰ አባላቶቻቸው እየታሰሩ ያሉትና በትግራይም ነጻነት ያለመኖሩን ያረጋግጣል። ይህ ማለት ለዘመናት የታፈነውና የተቀጠቀጠው ትግራይም የነርሱ ዋሻ ሊሆን እንደማይችል ነው። ስለዚህ መሰረታችን ነው በሚሉት ትግራይ ውስጥም ሕዝባዊ አመጽ ይነሳል። የፈለገውን አይነት ትጥቅና ስንቅ ትግራይን አስገንጥሎ ሀገር አያደርጋትም። እናም በትግራይ ተገንጣይ ቡድን የማይገደብ ሕዝባዊ አመጽ በግዱ ይነሳል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ ያሰሙን ዜና እጅግ የሚያስደስት ነው። ሀገራቸው የነርሱ ናትና ለነገው ቤታቸው ዛሬን የቤት ሥራቸውን መስራት አለባቸው። በመሆኑም ሀገር አቀፍ የሆነ በተማሪዎች እንቅስቃሴ ውስጥ የሚካተት ታጋይ ድርጅት መፍጠር መቻላቸውን ሲያበስሩ መስማት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው። አዎን ኢትዮጵያቸውን ዛሬ ካልታደጉ ነገ ሀገር አይኖራቸውም ወይም የሀብታም ጎጠኞች አገልጋይ ይሆናሉ ሰግደው እስከተገዙ ድረስ። ስለዚህ በተለያዩ ክፋላተሀገራት እንደመበተናቸው መጠን ግብታዊ ሳይሆን ሚዛናዊ፣ ስሜታዊ ብቻም ሳይሆን እውቀትና ብልህነትም የታከለበት ትግላቸውን ተጠናክረው ይቀጥሉበታል ብለን እናምናለን። የወያኔን የጎጥ ጸብ አጫሪነት ተሻግረው ኢትዮጵያን ለማዳን ይህ አይነቱ የወጣቶች ሀገራዊ መነሳሳት መገደብ የማይችል የሕዝባዊ አመጽ ምልክት ነውና አሸናፊነቱን መጠራጠር ከቶውን አይቻልም።

የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ሲያቀርቡ የነበረው ጥያቄ መልስ ሊያገኝ ያልቻለው ያለው መንግስት ለዚህ የተዘጋጀ ባለመሆኑና ያገኘው ሕዝባዊ ስብስብ ውስጥ የሀይማኖት ጓዳ ድረስ ዘልቆ አፈና ማኪያሄድ በመሆኑ ነው። ጥያቄያቸው አንድ ደረጃ ወደላይ አድጎ ማስተዳደር ያልቻለ መንግስት ይወገድ ወደሚለው ሀገራዊ መፈክር ማደጉም የሚያመለክተው የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ካፍንጫው ራቅ አድርጎ ማሰብ ባለመቻሉ የራሱን መቃብር በጥፍሩ ቆፍሮ የጨረሰ መሆኑን ነው። በወሎ የተደረገው ጭፍጭፋና ድብደባ፣ በአርሲ የተደረገው፣ በሐረር እየሆነ ያለው በሁሉም ሰው አይን ውስጥ ገብቶአልና ቁጣው ወደ ሕዝባዊ አመጽ ይቀየራል! ይህ አያጠራጥርም። ፌዴራል ፖሊሶች የጎጠኞች መሳርያ የመሆናቸውን ያህል አንድ ክፉ ቀን እንደ ደቡቡ አፍሪካ ነጭ ለባሾች ጎማ ባንገታቸው እያጠለቁ የሚያቃጥሉዋቸው ሰዎች እንዲነሱባቸው ማድረግ ይመጣልና ከወዲሁ ሊያስቡበት ይገባል። የቅንጅትን መሪዎችን በማሰር ትግሉን እንዳጨናገፉ ሁሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን መሪዎች በማሰር ስኬትን አገኛለሁ ማለት የሞኝ መንገድ መሆኑ እየተመሰከረ ነው።  ማወቅ የሚያስፈልገው ነገር ይህ ሁሉ በደል የበዛበት ሕዝብ ያለው ኃይል ታላቅ መሆኑንና ይህ ሕዝባዊ አመጽ ተጠናክሮ ሊቀጥልና አሳሪዎችን ታሳሪ ሊያደርግ የሚችል አቅም ላይ መድረሱን ነው። ይህንን ነው መገደብ የማይቻል ሕዝባዊ እምቢተኛነት ማለት የሚቻለው።

የክርስትና በተለይም የኦርቶዶክሱ ቤተክርስትያን የጎጠኞች ሰለባ ሆኖ በዚህም በዚያም ጥቃት ሲፈጸምበት መኖሩ ይታወቃል። አሁን ባለቀ ሰዓት እንኳን አስታራቂዎች ላይ የደረሰው በደልና ግፍ የሚያመለክተው ነገር ቢኖር ቤተክርስትያኑ በትግራይ ተገንጣይ ማፊያዎች እንደታገተ ነው። ስለዚህ ሕዝበ ክርስትያኑ ያለውን ሁኔታ በሚገባ ሊረዳው እንደሚችል ነው። ይልቁንም መረጃ በቀላሉ ወደ ሀገር ቤት እየገባ በመሆኑ ከማንም የተደበቀ አይደለምና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን ለማዳከም፣ ለመበታተን ይልቁንም ሀገር አቀፍ ጉልበት እንዳላቸው በማመን ያንን ለማፍረስ የሚደረገው ክፋት እየተጋለጠ ነው። ከእስልምና ተከታዮች የበለጠ በቤተክህነቱ ላይ ዘረፋ በመኪያሄዱ ያንን ለማፈን የሚደረገው ርብርቦሽ እየተዳከመና ለመዕመናኑ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። ይህም የግድ ሕዝባዊ አመጽ የሚያነሳሳ ነውና በየአቅጣጫው ቋጠሮ የሚፈታበት ቡድን ልብ ሊለው የቻለ አይመስልም። ቢልም የማቆም አንዳች ኃይል የለውም።

የወያኔ ሰራዊት እየተፈታ ነው። ሰራዊቱ እየካደ ጥሎ እየጠፋ ነው። ጠፍቶ ወዴት እንደሚሄድም ግልጽ ነው፣ በጣም ግልጽ ነው። ሕዝባዊ ኃይል መቀላቀል መጀመሩን ራሳቸው የጎጠኛው ጦር አዛዦች እየተናገሩ ነው። በሰራዊቱ መካከል ያለመግባባት መኖሩንም ግልጽ የሚያደርገው በቡሬ ግንባር የሆነው ነው። በተለያዩ አካባቢዎች እስረኞችን ማስፈታት፣ ፈንጂ መቅበርና የመሳሰሉት ሕዝባዊ ቁጣዎች የየቀን ዜና መሆን ጀምረዋል። ይህ በዚህ ከቀጠለ በሌሎችም ክፍላተ ሀገራት በቅርቡ የምንሰማው ጉዳይ ሊሆን ይችላል። ሕዝባዊ እምቢተኛነት ሲቀጣጠል መያዣ መጨበጫ ያጥራል።

ከሰሞኑ ግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ኃይል የሚል ድርጅት ራሱን ይፋ አድርጎአል። በሰራዊቱ ውስጥም በሚስጥር የተደራጀ ኃይል ስለመኖሩ ሰምተናል። ይህ የወያኔን ማፈኛ መንገድ እንደ አሮጌ መቋጠርያ በየቦታው የሚቀዳድደው ነውና ታላቅ ሕዝባዊ አመጽ መነሳቱ ያለ ጥርጥር እየታየ ነው። የአርበኞች ግንባር ብሎ ራሱን የሚጠራው ኃይልም እስረኞች ማስፈታትና በጎጠኞች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን እንደቀጠለ ነው።

ይህንን ሕዝባዊ አመጽ ማገትና ማቆም የሚቻል ነገር አይሆንም። የሚከተለውን አደጋና እልቂት ለመቀነስ ግን አሁንም ጊዜ አለ። ይህንን ዘረኛነት፣ ጎጠኛነትና እብሪት አጥፍቶ ለሁሉም እኩል የሆነች ሀገር ለመመስረት ለብሄራዊ እርቅ መዘጋጀት ከብዙ ጥፋት ያቅባል። እብሪት ላይ የተመሰረተ በራስ መተማመን ግን አምባገነኖችን ይዞ እንደሚጠፋ ሰደድ እሳት ነው። በአንድ ጀንበር የሚጠፋም ስልጣን መሆኑን ከታሪክ ያለመማር የውድቀትመደምደሚያ ነው። መገደብ የማይችል ሕዝባዊ እምቢተኛነት በኢትዮጵያ እየተቀጣጠለ ነው።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያንና ሕዝብዋን ይባርክ!!

biyadegelgne@hotmail.com

የFBI መርማሪዎች አበበ ገላውን ለመግደል የታቀደ ሴራ አከሸፉ – በሴራው የተሳተፉ የህወሃት ሰላዮች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው

ታህሳስ  ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን አንድ የአሜሪካ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ (FBI) ግበረሃል ባለፈው ወር መባቻ ላይ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ወደ ቦስተን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅትOne of TPLF spies who involved in Abebe Gellaw assassination attempt. በተጓዘበት ወቅት የግድያ ወንጀል ለመፈጸም በመዶለትና በማስተባበር ተግባር ላይ ተሰማርቶ የነበረና ለህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሰልል የሚጠረጠር ግለሰብ እና በግብረአበሮቹ ላይ ከፍተኛ ምርመራ መክፈቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጡ።

በአሜሪካ ሀገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ የሚኖረውና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ የዘር ድርጅት አባል እና ሰላይ እንደሆነ የሚታመነው ግኡሽ አበራ በመባል የሚጠራው ይሄው ግለሰብ ጋዜጠኛውን ለመግደል በማሴር ሶስት የወንጀሉ ተባባሪ የሚሆኑ ግለሰቦችን  መመልመሉ ንና ድርጊቱን ለመፈጸም መሰናዶ ማድረጉን የFBI መሪማሪዎች  ደርሰውበት ሴራውን በግዜ ማክሸፋቸው ተረጋግጧል።

ግለሰቡ ወንጀሉን ከመፈጸሙ በፊት የተለዋወጣቸው መልእክቶች የFBI ወንጀል መርማሪዎች እጅ በመግባታቸው ሳቢያ እርሱና አብረው የሚኖሩ ሌሎች አራት ግለሰቦች ላይ ክትትልና ምረመራ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል። ከተባባሪዎቹ ጋር  የተለዋወጣቸው መልእክቶች ጋዜጠኛ አበበ ገላው ወደቦስተን የመሄዱን አጋጣሚ በመጠቀም በመሳሪያ ተኩሶ የመግደል እቅድ አውጥቶ ድርጊቱን ለመፈጸም ወይንም ለማስፈጸም ይንቀሳቀስ እንደነበር በግልጽ እንደሚያሳዩ ታውቋል።

የቦስተን ቅርንጫፍ FBI ቃል አቀባይ እና ልዩ መርማሪ ( special agent) የሆኑት ግሬግ ኮምኮዊች በምርመራው ሂደት  ላይ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ቢቆጠቡም፣ FBI እንዲህ አይነት ወንጀሎችን በ ቸልታ እንደማያልፍ ገልጸው በውጭ መንግስታት ሰላዮችም ሆነ ተወካዮች የሌሎችን ሰብአዊ መብቶችን በሚገፍ ህገወጥ ወንጀል የተሰማሩ ካሉ ኢትዮጵያዊያን በቸልታ ማልፍ እንደማይገባቸው እና በአካባቢያቸው ለሚገኙ የFBI  ቅርንጫፎች ጥቆማ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበዋል። መርማሪው አክለውም FBI እንዲህ አይነቱን ጥቆማ በአግባቡ ትኩረት እንደሚሰጠው ገልጸዋል። “

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በመተቸት የሚታወቁት የጄኖሳይድ ወች ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ግሪጎሪ ስታንተን የግድያ ሴራውን ያከሸፉትን የFBI መርማሪዎች አድንቀው ፣ ህወሃት አሸባሪ ድርጅት መሆኑ ታውቆ ከኢትዮጵያ አልፎ በአሜሪካን ሀገር እንዲህ አይነት ወንጀል ሊፈጽም መንቀሳቀሱ በችልታ አይታይም ብለዋል።

በካምቦድያ በሰው ልጆች ላይ አስከፊ ሰቆቃና ጭፍጨፋ የፈጸሙ የካሜሩዥ ባለስልጣናትን ለፍርድ በማቅረብ አለማቀፍ እወቅና ያገኙት ፕሮፌሰር ስታንተን እንዲህ አይነቱ ወንጀል ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

ግኡሽ አበራን በቅርብ የሚያውቅ አንድ ኢትዮጵያዊ የቦስተን ነዋሪ፣ ግለሰቡ ከከፍተኛ የህወሃት ባልስልጣናት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለውና የቀድሞው አምባገነን መሪ የመለስ ዜናዊ አምላኪ እንደነበር፣ የእርሱ መዋረድና መሞት በጣም ካበሳጫቸው በአሜሪካ የሚኖሩ በርካታ የህወሃት ጀሌዎች አንዱ መሆኑን ገልጿል። በማከልም “ከሁሉ የከፋው ግለሰቡ በዘረኝነት ዛር የተለከፈ ስለሆነ ህወሃቶች እንዲህ አይነቱን ሰው ለእኩይ አላማቸው መጠቀማቸው የተለመደ ነው፣”  በማለት አስረድቷል::

ጋዜጠኛ አበበ ገላው “ህወሃት አሸባሪ የማፊያ ድርጅት መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት የነበሩብኝን የጽጥታ ስጋቶች ችላ ባለማለት ለሚመለከታቸው የህግ አስከባሪ አካላት ከማመልከት አልፌ የቤተሰቤንም ሆነ የራሴን ደህንነት ለማረጋገጥ ቀደም ብዬ እርምጃ ወስጃለሁ ወደ ፊትም እወስዳለሁ” ብሏል።

የFBI መርማሪዎች ወንጀሉ እንዳይፈጸም አስቀድመው እርምጃዎችን የወሰዱ ሲሆን ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ቦስተን ውስጥ ሮክስቤሪ በመባል በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን እና ግኡሽ አበራ ከሌሎች አራት ኢትዮጵያዊን ጋር በጋራ ይሚኖርበትን ቤት የበረበሩ ሲሆን፣  ወደ ሁለቱ የቤቱ ነዋሪዎች ስራ ቦታ ድረስ በመሄድ ምርመራ ማድረጋቸው ተረጋግጧል።

ኦህዴድ ውስጥ የማረጋጋትና የማጽዳት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው

ኢሳት ዜና:- የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት አቶ ሙክታር ከድር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ደረጃ ያለውን አመራር የማጠናከር፣ የማረጋጋትና የማጽዳት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ከፍተኛ ችግር በሚታይበት በምስራቅ ኦሮሚያ እና በሀረሪ ክልል የሚገኙ በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ የኦህዴድ አመራሮች ፣ መምህራንና ርእሰ መምህራን፣ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የድርጅት አባላቶች ከህዳር 27 ጀምሮ ስብሰባ ላይ ናቸው። በሀረሪ ክልል በአሚር አብዱላሂ አዳራሽ መጋቢት 28፣ ቀን 2005 ዓም በኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት በአቶ ረጋሳ ከፍያለው ሰብሳቢነት ስብሰባ ተካሂዷል። በመስራቅ ሀረርጌ ደግሞ መካከለኛ አመራር፣ ርእሰ መምህራንና የድርጅት አባላት የሚሳተፉበት ስብሰባ ዛሬ ተጀምሯል።

ከ700 በላይ የሚሆኑ የኦህዴድ አባላት በተሳተፉበት ስበሰባ ዋነኛ የመወያያ ጉዳዮች ሆነው ከቀረቡት መካከል በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠረው ልዩነት፣ የሙስሊሙ እንቅስቃሴና፣ ትምህርት ቤቶች የአንድ ለአምስት አደረጃጃትን ስለሚተገብሩበት ሁኔታ የሚሉት ይገኙበታል።

የኦሮሞ ህዝብ በብሄር ብሄረሰቦች ቀን ማንነቱን ያስከበረ መሆኑን፣ ኦነግ የሚያቀነቅነው ሀሳብ በአንቀጽ 39 የተከበረ መሆኑ፣ እንዲሁም በአመራሩ መካከል የታዩ ክፍተቶች የተዘጉ መሆኑን ሰብሳቢው ገልጸዋል።

ተሰብሳቢዎች በበኩላቸው “ ይህ በቂ አይደለም ፣ ምስራቅ ሀረርጌ በኦሮሚያ ክልል ስር መሆን ሲገባው በሀረሪ ክልል ሆኗል፣ ቋንቋችን ተግባራዊ ይሁን ከተባለ በሁዋላ እስካሁን ተግባራዊ አልሆንም።” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል።

ኦነግ አመለካከት ያላቸው ሰርጎ ገቦች በቂ የስልጣን ቦታ አላገኘንም በማለት የሚያስወሩት ሀሰት መሆኑንና ኦህዴድ የምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ስልጣን ማግኘቱን ሰብሰባዊው ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል በፕሬዝዳንቱ መታመም ምክንያት ያለፕሬዚዳንት ለ2 አመታት መመራቱና ኦህዴድም ራሱን ችሎ ሊቆም አለመቻሉ ጥያቄ ሆኖ ተነስቷል።

ድርጅቱ ራሱን የማጠናከርና የማረጋጋት ስራ እየወሰደ መሆኑን በስብሰባው የተካፈሉ ስማቸው እንዳይገለጥ የጠየቁ የኦህዴድ አባላት ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ዜናም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ለህክምና ተመልሰው ወደ ውጭ መውጣታቸው ታውቋል። ከአንድ አመት በፊት ጀምሮ በህክምና ላይ የሚገኙት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ህክምናቸውን ሳይጨርሱ ፣ ለአቶ መለስ ዜናዊ ቀብር ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ተደርጎ እንደነበር ይታወቃል። ከፍተኛ የሰውነት መጎሳቆል የሚታይባቸው አቶ አለማየሁ ከሀላፊነት እንዲነሱ በመርህ ደረጃ ውሳኔ ላይ ቢደረስም ፣ እርሳቸውን በሚተካቸው ሰው ላይ በካቢኔ አባላቱ መካካል ስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ ቦታው ክፍት እንዲሆን ተደርጓል።

ባለፈው ሳምንት በአዳማ በተካሄደው የምክር ቤት ስብሰባ ላይ ምክትሉ ሲገኙ ዋናው ፕሬዚዳንት አልተገኙም ነበር። የኦህዴድ መካካለኛ አመራሮችን በመሰብሰብ እያወያዩ ያሉትም ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ ረጋሳ ከፍያለው ናቸው። የኦህዴድ አመራር አባላት እንደገለጡት በድርጅቱ ውስጥ የሚታየው መከፋፋል ከፍተኛ ደረጃ በመድረሱ ስራ መስራት በማይቻልበት ደረጃ ተደርሷል።

ኢህአዴግ በድርጅቶቹ መካካል የተፈጠረውን መከፋፈል ለማስቀረት ከኦህዴድ እና ከብአዴንና ከህወሀት የተውጣጡ 3 ምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትሮችን መሾሙ ይታወሳል።

Admas
 
Posts: 40
Joined: 14 Jul 2007, 14:56

በደል የረሳል ወይስ ይለመዳል ወገን? (2)

አንዳንዶች ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ለማገልገል እድሜ ዘመናቸውን እንደጣሩ፣ እንደፈለጉ፣ እንደናፈቁ ሳይሳካላቸው ያልፋሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች ይህ ወረቃማ እድል ያለጊዜው እጃቸው ላይ ወድቆላቸው ያላግባብ ያለምንም ጥቅም ሲያሳልፉትና የወገንና የታሪክ ተጠያቂ ሲሆኑ እንመለከታለን። ከዚህም እጅግ በከፋ መልኩ ያገኙትን ሀገርንና ወገንን የመርዳት ወርቃማ እድል በተቃራኒው የሀገርን ሉአላዊነት ማስደፈሪያ፣ ወገንን ማስገረፊያ፣ ማሰቃያና ማሳደጂያ እንዲሁም ለራስ ምስል ግንባታ ብቻ በማዋል የሀገርም፣ የወገንም እንዲሁም የታሪክም ፍጹም ማፈሪያ ሆነው ሲያልፉ በተደጋጋሚ አስተውለናል።

በታላቁ መፅሐፍ መጽሐፈ አስቴር በምእራፍ 4 ቁጥር 13-14 አስቴር ስለምትባል አይሁዳዊት ሴት እንዲህ ተፅፏል መርዶክዮስም አክራቲዮስንድና ለአስቴር እንዲህ በላት አለው ”አንች በንጉስ ቤት ስለሆንሁ ከአይሁድ ሁሉ ይልቅ እድናለሁ ብለሽ በልብሽ አታስቢ። በዚህ ጊዜ ቸል ብትይ እረፍትና መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል፣ አንቺና ያባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ ወደ መንግስት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደሆነ ማን ያውቃል?”  ይህን ጥቅስ ስመለከት ላለፉት 21 ዓመታት የሀገራችን ቀዳማዊት እመቤት የነበረቺው አዜብ ጎላ ትዝ ትለኛለች ትውልዷ የዛሬ ቅኝቴ ከሆነው ከወልቃይት ጸገዴ ህዝብ ነውና። አሳዛኝ ግጥምጥሞሽ።

የዘሩት ሜዳ ሙሉ የሚያምር ፍሬ ያንዠረገገ ሰብል ከነማሳው በጠራራ ጸሐይ የተዘረፉ፣ እልፍኝ ካዳራሽ ቤታቸው ከነ ሙሉ ንብረቱ በህዝብ ፊት የተነጠቁ፣ የቤት እንሰሶቻቸው ከነ አይነቱ እነዲሁም ልጆች ወልጄ ኩየ ድሬ እኖርበታለሁ ሃብት ንብረት አፍርቼ አክብሬና ተከብሬ ለልጅ ልጆቼ አወርሰዋለሁ ካሉት ቀዬና ሸንተረር በግፍ በጉልበት በሃይል ተዋርደውና ተጎሳቁለው እንዲሰደዱ የተደረጉ ምስኪን ህዝቦች፤ የወልቃይትና ፀገዴ ወገኖቻችን። ሴቶቻቸው በወያኔ ኢህ አዴግ  በተደራጀና በተቀነባበረ መልኩ የራሳቸውን መሰል ወንዶች ሳይሆን አገዛዙ የመረጠላቸውን ወንዶች እንዲያገቡ ሆን ተብሎ የግፍ ግፍ የተሰራባቸው፤ ከስር ከመሰረቱ ነቅለው እንዲወጡና የአካባቢ፣ የመሬት ባለቤትነት እንዳያነሱ ተስፋ መሬታቸውን፣ ትዝታ ቀያቸውን የተወረሱ አሳዛኝ ህዝቦች፤ የወልቃይታ ፀገዴ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን። ታዲያ ይህ ይረሳል ወይስ ይለመዳል?

ከላይ እንዳየነው በታላቁ መፅሃፍ የተጠቀሰችው አስቴር አይገቡ ገብታ እና ንጉስ ባለቤቷን አሳምና የሞት ፍርድ የተፈረደባቸውን አይሁዳዊያን ወገኖቿን የቁርጥ ቀን ወገን ሁና ከሞት ስትታደጋቸው እናነባለን። ምስኪን የወልቃይትና የፀገዴ ህዝብ ግን  ዘሩ ሲመክን፣ ሃብቱ ሲራቆት፣ ከቅየው በባዶ እጁ ሲባረርና ተመልሶ የይገባኛል ጥያቄ እንዳይጠይቅ ባገሩ ስደተኛና ለማኝ ሲሆን ወልዶ ያሳደጋትና የኔ የሚላት ቀዳማዊት እመቤት አዜብ መስፍን እንደ አይሁዳዊቷ አስቴር በቤተ መንግስት ብትሆንም ወገኖቿን ለመርዳት ግን ጊዜ አላገኘችም። ውሃ የተራጨችባቸው የወልቃይት ወንዞች፣ ጭቃ አቡክታ የተሯሯጠችባቸው የፀገዴ ባድማዎች፣ አኩኩሉና ድብብዎሽ የተጫወተችባቸው የወልቃይት ፀገዴ ጫካዎች በግፍ ያለፍርድ ከታሪክ ምስክርነት ውጭ ወደ ታላቋ ትግራይ ሲካለልና ኗሪው ህዝብም አይሆኑ ሆኖ ሲባክን አዜብ ጎላ ግን ያለ ወገን የሚበላ፣ ያለ ዘመድ የሚደሰቱበት ያለ እህት ያለ ወንድም፣ ያለ አክስት ያለ አጎት የሚዝናኑበትን የቢዝነስ ኢምፓር እየገነባች ነበር። ታዲያ ይሄ እንዴት ይረሳል ወገን? እንዴትስ ይለመዳል?

ለወልቃይት ፀገዴ ህዝብ ተቆርቃሪና ደም መላሽ ወገን ከኛ ከኢትዮጵያዊያን ከወገኖቻቸው አለ። ጊዜው መቼም ይሁን መች ይህ በግፍ የተሰደደ ህዝብ ሃብቱን መሬቱን ሀገሩን ቅየውን ያገኛል። የተዋረደው ክብሩ የተንቋሸሸው ማንነቱ የተደፈረው እሱነቱ በወገኖቹ የማያቋርጥ ተጋድሎ ይመለሳል። ይህ ደግሞ አይቀርም። ወገኖቿ ሲሳደዱ ስትሳለቅ የነበረችው አዜብ ጎላ ግን የመከራ የስጋትና የጭንቀት ዘመኗ ጀምራል። ቤተመንግስቱን ለተመራጩ አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር  ለማስረከብ ስታንገራግር የነበረውም ከዚሁ ፍርሃትና ጭንቀት የተነሳ እንደሆነ ይተወቃል። ምስኪን የወልቃይትና የጸገዴ ወገኖቻችን ባካል እንደተሳደዱ ሁሉ አዜብ ጎላ ዛሬ ኮሽታ የሚያስበረግጋት የራሷ ጥላ የሚያስደነብራት ድንጉጥና  በመንፍስ ስደተኛ ሆናለች። በሰፈሩት ቁና መሰፈር ማለት ይህ ነው። ታዲያ ይህን ሁሉ የወገኖቻችንን ስቃይና መከራ ማን ይረሳል? እንዴትስ ተላምደን ልንኖር እንችላለን? ሁላችንም አንድ ሆነን የወያኔን ግብአተ መሬት ማፋጠን ይገባናል እንጂ።

ecadf.com

Nile fears turn toward south

Experts are wary of South Sudan, considering that it controls the White Nile, the other source of the Great Nile. That is problematic because the West and Israel could use their influence with South Sudan to put pressure on Egypt.

By Ibrahim Al-Jack

The African Research and Studies Centre at the International University of Africa held a forum last week titled “Ethiopian Renaissance Dam and Its Effects on Egypt and Sudan.”

The minister of electricity and irrigation, Dr. Tabitha Butrus; the Ethiopian irrigation minister; the Ethiopian ambassador to Sudan, Abadi Zemo; and many experts in agriculture, irrigation, and environment attended the forum.

Ethiopia denies any intention to block water from Egypt and Sudan.

The Ethiopian irrigation minister, Ilambo Timno, denied any intentions to block water saying that Ethiopia only wants to use the dam to generate electricity. He mentioned that late Ethiopian Prime Minister Meles Zinawi called on both Sudan and Egypt to take part in establishing the dam, but they have not.

He promised that Ethiopia has no hidden agenda. “The dam has many positive effects on the Nile Basin countries,” he claimed.

He continued, “Forums like these offer the chance to exchange points of view, opinions, and more research.”

He explained that the dam will help maintain the water level all year round and increase fishery production. Sudan will also benefit immensely, considering that there will be an abundance of water supply, especially in River Atbara, that can be used to improve agriculture and develop areas on the border between Sudan and Ethiopia. He called for partnerships to be built among Nile Basin countries to realise mutual benefits. Again, he denied that there is any reason for Egypt and Sudan to be wary of the dam.

Former Irrigation Minister Professor Saif Aldin Hamad said Ethiopia has 123 billion cubic metres of water, of which 97% is not used. He added that very little land is cultivated where water is scarce. The area surrounding the dam is not incapable of cultivation, he continued, but Sudan will benefit from the dam, considering it is dependent on the natural flow of the Nile and does not have and does not have the means to store its waters. That is where the Ethiopian dam comes in. It will help by storing up water, from which Sudan will benefit in more than way, such as: limited evaporation and doubled electricity production in Roseiris, Sinnar, and Meroe.

The benefits from the Ethiopian dam can be fairly imaginable, given that it stores up 74 billion cubic metres of water.

Advantages of the dam

The Ethiopian minister of energy and mining, Alfakki Ahmed Najash, said Ethiopia and Sudan will benefit immensely from this dam in irrigation and agriculture. But, he added, Nile Basin countries have different opinions on it.

Engineer Abdulhalim Alturabi said there are many benefits that can be reaped from this dam, but cooperation in establishing and running it is a prerequisite. He went on to say, “Ethiopia does not have vast land that can be farmed, and Sudan does. Ethiopia, therefore, cannot afford hostile relations with Sudan. The two countries must build their relations around being totally open with each other. They must exchange benefits because, in Sudan’s perspective, Ethiopia has a lot of potential and a work force that Sudan is in need of.”

Importance of Consensus on the Dam

A political analyst, Professor Hassan Alsaori, said it is important for the Nile Basin countries to have a consensus on the dam, especially as Ethiopia will control 86% of the Nile’s water after the dam is completed.

He said consensus is important, because without it, Ethiopia will have the upper hand and leverage in any dispute among Nile Basin countries because it will hold the “Nile water card.”
He said it is only fair that Egypt and Sudan take part in establishing and running the dam to be certain that their part of the Nile is safe.

Fears are steered south

Many experts argue that Ethiopia does not want to make a unilateral move regarding the dam to ensure it does not threaten regional security. In that regard, it is most careful to reassure Sudan and Egypt.

But the same experts were wary of South Sudan, considering that it controls the White Nile, the other source of the Great Nile. That is problematic because the West and Israel could use their influence with South Sudan to put pressure on Egypt. Sudan and Egypt have doubts that the newly founded and politically unstable country of South Sudan would take unilateral steps to decrease the portions of Nile water to which Sudan and Egypt are entitled. Such a step would jeopardise the regional and national security of Egypt and that of Sudan in the process.

Admas
 
ETHIOPIAN REVIEW

TPLF Manifesto, Amhara was labeled as #1 enemy of Tigray

The forgotten people” Why is the Ethiopians’ blood so thin?

TPLF Manifesto Amhara was labeled as number 1 enemy of Tigray

Mekonnen Workineh, Norway, Nov 2012

Writer from Norway, Mekonnen Workineh

Mekonnen Workineh

Analogously ,  the Nazi manifesto of 1920 was anti-Semiticanti-capitalistanti-democraticanti-Marxist, and anti-liberal.

Anti-Semitic was number one manifesto of Nazi Hitler and Anti-Amhara is number one manifesto of TPLF.

Hitler murdered 6 Million Jews. What happened 60 years ago is still fresh in the minds of Jews and is still haunting Germans, especially those whose family members were involved. Nazi criminals are still being hunted around the world and being brought to justice.

TPLF murdered more than 8 Million Ethiopians to date (G/Medhin TPLF Manifesto Amhara was labeled as enemy of TigrayAraya, former TPLF financial head). In the 2007/2008 senses 2.5 Million Amharas perished into the thin air;http://ethioskytv.com/view/570/25-million-amharas-missing-confirmed-in-parliament-part-1.html . Ethiopia has been under siege for the last 21 years by TPLF backed by the European Union, USA, and the United Kingdom. 1000s of Anuakes residences were red labeled and were massacred in a day light by this regime. Ogaden region was curtailed from international eye and mass murder, gang rape and  torture crime is being committed by this same regime( http://www.genocidewatch.org/ethiopia.html) , tens of thousands of Oromos,  the majority group of the country, are languishing in jail all over the country. Tens of thousands are being evicted even this time, TPLF regime is dehumanizing the Ethiopian people, torturing and committing savage crime against poor farmers, elders and children. Involved in human trafficking crime,

Hundreds of thousands are leaving the country every year, thousands dying in the desert, drawing in seas and rivers, facing abuse, prison and death in Middle East, queuing  in front of immigration offices around the world, crowding foreign prisons, the list of ordeal could go for days.  When will the international community open its eyes and see what is happening to Ethiopian people.

Why do Ethiopians go exile?  Because Ethiopia is poor?  Because Ethiopians are not hard working? Because Ethiopia does not have natural resources to feed its people?

The answer to all the above questions is NO

The reason for all this is administration problem. Billions of dollars is flying out of the country illegally 11.7 Billion until 2009 (, http://danielberhane.com/2011/12/22/ethiopia-the-illicit-financials-outflow-in-perspective/).

Fertile land of Ethiopia is being given away almost for nothing; Multinational corporate brag of feeding the world from Gambella region alone.

http://www.guardian.co.uk/world/2011/mar/21/ethiopia-centre-global-farmland-rush)

True Ethiopian people are weak at this time; True TPLF is strong with the help of the west in the name of stability. But how long will that last, why and how did Ruanda genocide happened?  What was the recipe for that? What is the guarantee that such thing would not be repeated in Ethiopia if pushed to the edge? How long does iron fist last?

I urge all international community specially the Obama administration, the Cameroun administration, the European Union, to stop propping minority ethno centric fascist regime to undermine Ethiopian people.

Victory for Ethiopians!

ECADF.COM

የአዜብ-በረከት የተንኮል እቅድ

(ከጋሻ ለኢትዮጵያውያን)
መለስ ዜናዊ የስልጣን እድሚያቸውን ለማራዘም ከተጠቀሙባቸው ዘዴዎች አንዱና ዋናው “የትግራይ ህዝብ የሥርዓቱ ልዩ
ተጠቃሚ”እንደሆነ አድረገው በካድሬዎቻችው በኩል ያለመሰልቸት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ማካሄድ ነበር። ይህ ዘዴ የትግራይ ህዝብ
ተጠቃሚ፤ የኢትዮጲያ ህዝብ ግን የበይ ተመልካች ሆኖ እንዲሰማው አድርጎታል። አቶ መለስ “ነፃ ሚድያ” ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚቻል
ሁኔታ ስላጠፉትና የኢትዮጵያ ህዝብም የሳቸው የፕሮፓጋንዳ ሰለባ ስላደረጉት እሳቸው የሚናገሩት እና የሚያወሩት እውነት ይሁን ውሸት
ለማወቅ ይቸገራል። ያ ውሸት ተደጋግሞ ሲነገረው ውሸቱን እውነት ነው ብሎ ይቀበለዋል። አቶ መለስ ኢኮኖሚህ 11 በመቶ አድጓል እያሉ
ነጋ ጠባ ሲወተውቱት፣ ከአመት ወደ አመት ኑሮው እየከፋ፣ ጉልበቱ በረሀብ እየደከመ የሄደው ወገን ውሸቱን እውነት አድርጎ ከመቀበልREAD MORE

የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሐውልት፣ የሚያለማውስ?

ከድሜጥሮስ ብርቁ -ቶሮንቶ

የዳግማዊ ምንሊክ አና የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሃውልቶችን ከስፍራቸው ለማንሳት ዝግጂቱ አንደተጠናቀቀ ስሰማ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት ቡድን በትክክልም የ”መለስንAbune Petros was born in 1892 in a farmer family in the city of Ficheራዕይ”ለማስፈጸም ደፋ ቀና አያለ አንደሆነ ተረዳሁኝ። ከዚህ በፊት በሌላ ፅሁፍ አንደገለጽኩት የ”መለስ  ራዕይ” የሚባል ነገር አንደሌለ እና የመለስ አየተባለ ለመሸጥ የሚሞክረው “ራዕይ” በትክክል የህወሃት ለመሆኑ አመላክቻለሁ። ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር የነበረው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ “ሃገሪቱን አሰለጥናለሁ” የሚል ነበር። አስቡት የኢትዮጵያ ስልጣኔ ጉዳይ ወዝውዞት ከጣልያን ሃገር ድረስ ጦር ሰብቆ ሲመጣ። አቡነ ጴጥሮስ በግፍ ሃውልታቸው የቆመበት ቦታ ላይ የተገደሉትም ዛሬ ህወሃት በሚጠቀመው ቋንቋ ሲመነዘር “ጸረ-ልማት” ናቸው በሚል ነበር።

ሲጀመር “ልማት” የሚለው ‘ዲስኩር’ ከጥርጣሬ ይልቅ የህዝብን አመኔታ አንዲገዛ ማድረግ ያስፈልጋል። መረጃ በማፈን፣ ውዢንብር አንዲነግስ በማድረግ ደሞ የህዝብን ትኩረት ለጊዜው በማስቀየር ሌላ የፓለቲካ ጥፋት ከበስከጀርባ መስራት ይቻል አንደሁ አንጂ የሕዝብን አምነት መግዛት አይቻልም። በዚሁ ሃውልት ጉዳይ አንኳን የሚወራው ዜና የተደበላለቀ ነው። መጀመሪያ ይፈርሳሉ የሚል መረጃ ተለቀቀ። ህዝቡ ሲጯጯህ ደሞ “የለም አይፈርሱም” የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ብቻ ነው ለጊዜው በባለሙያዎች “በክብር” ከቦታው የሚነሳው። ተመልሶም በባለሙያዎች በክብር የነበረበት ቦታ “በክብር” ይቀመጣል” የሚል መረጃ ተለቀቀ። የኋለኛውን መረጃ የምድር ባቡር “ባለስልጣን” (መሆኑ ነው) የተናገረው ተባለ።  የባለስልጣኑን ቃል አንደወረደ ማመን ከተሞክሮ አንጻር ስህተት  ሊሆን ይችላል። ማን ይሆን? ከየት ይሆን ብሎ -ለማወቅ ያህል- መጠየቁ ዘመኑ ከፈጠረው ፖለቲካ አስተሳሰብ ሳይሆን ካለው ነባራዊ የፓለቲካ የሃይል ሚዛን አና አሰላለፍ ነው መታየት ያለበት።  በ “ልማት” ስም መታሰቢያ ሀውልቱን በባለሙያ “በክብር ከማስነሳት” ይልቅ ሃውልቱ በማይነካበት ሁኔታ ባለሙያዎች መስራት የተፈለገውን ግንባታ አንዲሰሩ ስለመቻላቸው ወይንም ስላለመቻልቸው ስለመሞከሩ አና ስላለመሞከሩ የምናውቀው ነገር የለም። የራሳችንን ግምት ግን አንወስዳለን -የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ “ለህወሃት ምኑ ነው?” የሚል ጥያቄ ግምት ውስጥ በማስገባት። የህወህትን ተፈጥሮ አና ባህሪ ግምት ውስጥ በማስገባት!

“ልማት”ን የአስከፊ ጥፋት መጠቅለያ ‘ዲስኩር’  እያደረጉ (አንደጣሊያኖቹ) ዝርዝር መረጃ ሲታፈን አና ነገሮች ከህዝብ ጋር ያለምክክር ሲደረጉ ጥርጣሬ ፣ሁከት፣አና ተቃውሞ አንደሚነሳ መዘንጋት ምን ማለት አንደሆነ አይገባኝም። ዛሬ ወታደራዊ ጉልበት ስላለ አና  የፖለቲካ መዘውር በሃይል ስለተያዘ ብቻም  ህዝቡ አሉኝ የሚላቸውን ከቅርስንትም ያለፈ ትርጉም አና ዋጋ ያላቸውን ታሪካዊም መንፈሳዊም ማህበራዊም ሃብቶቹን አንደፈለጉ መነካካት አሁን ያለውን ትውልድ አና ህዝብ ኢትዮጵያዊ ስነ ልቦና በማድማት የሚያልቅ ጉዳይ አይደለም። የአለመረጋጋትን መሰረት አየጣሉ አንደመሄድ ነው። ተቃውሞው በሌላ መልኩ በሌላ ጊዜ  ሲከሰት  እንዳሁኑ በመጯጯህ አና በህዘን የሚያልቅ ጉዳይ ላይሆን ይችላል። ከ”ብሶት ተወለድኩ” የሚል ቡድን ብሶት ሊወልድ የሚችለውን ነገር መዘንጋት የለበትም።  የትውልዱ ማህበራዊ አስተሳሰብ  አና የሃገር ፍቅር ከጥቅም ውጪ ተደርጎአል፤ ስጋት የሚፈጥር ተቃውሞ ሊፈጠር አይችልም( “መቶ አመት አንገዛለን” አንደሚባለው”) የሚመስለው አስተሳሰብ ምናልባት ከትውልዱም የበለጠ የሚናገረው ስለገዢው ቡድን ትምክህትና አላዋቂነት ሊሆን ይችላል። በውጭም በውስጥም ያለውን የጥፋት ትስስር (nexus)ገብቶት አንደ አቡነ ጴጥሮስ ለሃገር ለመሞት የተዘጋጀ ትውልድ ቢነሳስ?

ሕዝቡ “አለማለሁ” የሚለውን ቡድን የሚጠራጠረው ባህሪውን ስለሚይውቅ ብቻ አይደለም።  አንዳንድ “ልማት” የሚባሉ ፕሮጀክቶች በእርግጥም የልማት መሆናቸው አጠራጣሪ ስለሆነም ነው። ገዢውም ፓርቲ ለማወናበድም ዝም ለማለትም የሚምክረው የኢትዮጵያን ሕዝብ ስለሚያውቀው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ከመሬት ተነስቶ አይጠራጠርም። ተሞክሮውን ተመርኩዞ አንጂ!  የበፊት የበፊቱን አንኳን ትተን የቅርቡን የጥርጣሬ ምንጭ ለማስታወስ ያህል – የአፍሪካ የውሃ ማማ ናት በምትባለው ፤ ሰፊ የቆዳ ስፋት ዓላቸው ከሚባሉ የአፍሪካ ሃገሮች በምትመደበው ሃገራችን ውሃ አና መሬት የጠፋ ይመስል የስኳር ልማት ዋልድባ ላይ እተክላለሁ ተባለ።  “ልማቱ” በትክክል የህወህት አጂ ብቻ ይሁን ወይንም የውጭ ሃይሎች አጂ ይኑርበት እስካሁን ድረስ የገባኝ ነገር የለም። በትክክል የማውቀው ነገር ቢኖር ግን ዋልድባ ድረስ የተሄደው የኢትዮጵይውያንን እምነት ለመዝረፍ አንጂ ለልማት  ጉዳይ  ብቻ አንዳልሆነ ከማንም ኢትዮጵያዊ አንደማይሰወር ነው።

የአቡነ ጴጥሮስ መታስቢያ በ “ክብር” የሚነሳበት ዓላማ በትክክል ልማት ከሆነ ሃውልቱ የሚያስተጋባው መልዕክት በራሱ ልማትም ለልማትም አስፈላጊ የሆነ መሰረታዊ ነገር አንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል። ሃውልቱ ካረፈበት ኩርማን መሬት ይልቅ ሃውልቱ የሚያስተጋባው መልዕክት ዘላቂነት ላለው የልማት ተሰሳሽነት አስፈላጊ ነው።  ልማት ለማጣደፍ የሃገር ፍቅር ያስፈልጋል። የዜጎችን ስብዕና አና ህሊና ማልማት ለልማት አንደ መሰረትም አንደ ቅድመ ሁኔታም መታየት አለበት። በስልጣን መባለጉ፣ በሙስና መዝቀጡ፣ የሃገር ጥቅም አሳልፎ መስጠቱ ፣ ሀገርን ለበላየ ሰቦች ጥሎ ወደ ሰው ሃገር ተሰዶ በሰው ሃገር መደላደሉ ሁሉ የሚመጡት ልማት ካላየው -ካልለማ- ስብዕና ነው። የራስን ዜጋ በሆነ ባልሆነው መጨፍጨፍ አና የመሳሰሉት ችግሮች መነሻቸው ያለማ ህሊና አና የሃገር ፍቅር አለመኖር ነው። ሃገሩን የሚውድ ዜጋ ሃገሩን የሚያገለግልበት ዕድል ሲያገኝ ሃገሩን አይዘርፍም። አያዘርፍምም። ህውልቱ  የሚያነበው አና ጩኽቱን የሚሰማው  የመንግስት አክል ባይኖርም  የሚናገረው አነዚህህ የሃገር ጠንቅ የሆኑ ማህበራዊ አና ፓለቲካዊ ተውሳኮች በመቃወም ነው። እንዴት “ባለ ራዕይ” የሚያመልክ ፓርቲ አና መንግስት ይሄን ማየት ተሳነው?

የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት መታሰቢያ  የጠንካራ ስብዕና ፣ የሃገር ፍቅር፣ የቁርጠኝነት አና የነጻነት ተምሳሌትነትን ነው ጧትና ማታ የሚያስተጋባው። በአስቸጋሪ ዘመን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አውነትን አንቆ ለእውነት ስለተሰዋ ክቡር ኢትዮጵያዊ ነው የሚናገረው። የአቡነ ጴጥሮስ የመንፈስ ጽናት ፤ መልዕክት አና መስዋዕትነት  የትግል ስንቅ ሆኗቸው ፋሺስትነትን በጽናት ታግለው ስለሞቱም ኢትዮጵያውያን የሚያስታውሰን መታሰቢያም ነው። ጎበዝ ኢትዮጵያ አኮ በፋሽስት ጦርነት አንድ ሚሊዮን ዜጎቾን አጥታለች። ስልሳ ሺ ታጋዮች ለትግራይ ተሰውላት ተብሎ ትግራይ ላይ ሃውልት የሚሰራ ቡድን በኢትዮጵያን ሃውልት ለምን ይቀለዳል??  በቅርቡ የተሰራው የአባ ጳውሎስ ሃውልትስ ሃይማኖታዊ አይደለም ይፍረስ ሲባል አይፈርሲም ሲባል አልነበረ አንዴ? ምነው አቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ላይ ተነቃ?! የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ “ለህወሃት ምኑ ነው?” ነዋ ነገሩ! ህወህት የተዋጋውን ኢትዮጵያዊነት ጧትና ማታ የሚያስተጋባ ነዝናዣቸው ነዋ!

የገዢው ቡድን በተለይም የህወህት ጽንፈኛ ደጋፊዎች  የሚመስሉኝን ሰዎች (አንዳንዶቹ በብዕር ስም የሚጽፉ የአመራር አባላትም ይመስሉኛል) በዌብሳይቶች ላይ የሚጽፉአቸውን ጽሁፎች እከታተላለሁ። በዋነኛነት ከማነባቸው ውስጥ የሳይበር ኢትዮጵያን የፓለቲካ አምድ(click here )አንዱ ነው። በኦፊሲየል ሲነገር የማይሰማውን የህወሃትን የፓለቲካ እሳቤ -በተለይም  ከትምክህትና የበላይነት ስለ ልቦና ግንባታ ጋር የተያያዙትን ህሳቦች ቡዙ ሳይነካኩ (አንዳንዴ ምንም ሳይነካኩም) አንደወረደ የሚያቀርቡ ግለሰቦች አይጠፉም።

አንደወረዱ የሚቀርቡትን ትቼ ትንሽ አየተነካኩ አንዳንዴ የስነ-ጽሁፍም ገጽታ እየተሰጣቸው የሚሰነዘሩ ሃሳቦችን ለአብነት አቀርባለሁ። አንደዚህ አይነት ሃሳቦችን ያንጸባርቃሉ ያልኳቸውን ጽሁፎች ለማየት በቅንፍ ውስጥ ያለውን ማጣቀሻ ይጫኑት( click here) ። ሃሳቡ የህወሃት ለመሆኑ ሁነኛ ማስረጃ ይሆናል ብየ ከማስበው ነገር እንዲህ ያለውን ጽሁፍ ብዙ ጊዜ የሚያሞካሿቸው (በዚያው መድረክ ላይ ማለቴ ነው) ህወሃት ባደረገው የትጥቅ ትግል ተሳትፈናል የሚሉ ስልጣን ከያዙ በኋላም ተምረው  በዲፕሎማሲ ስራ ላይ (ካያያዛቸው ይመስላል) የተመደቡ ይገኙበታል። ጉዳዩን አዚህ ያነሳሁብትም ምክንያት ህወሃት የሚከተላቸውን “የልማት” ይሁን ሌሎች የኢኮኖሚ ፓሊሲዎች  ዓላማቸው ህወሃት የበላይነት ስነ-ልቦን መገንባት አና የበላይነቱን ያስጠበቀበትን የስልጣን ተዋረድ ጠብቆ ለማቆየት የሚያስችለው ከመሆን ውጪ ሌላ ሊሆኑ አንደማይችሉ ለማመላከት ነው። አንዲህ አይነቶቹን ፓሊሲውች ህወሃት በቀጥታ የሚያስትላልፋቸው አይደሉም ማለት ህወህት የውሳኔው አድራጊ አና ፈጣሪ አይደለም ማለትም አይደለም (በነገራችን ላይ የህወህት አመራር ‘ሜንተሮችን’ አንማን ነበሩ? ናቸው?)።

ቅጥ ባጣ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እና የነጻው ፕሬስ ላይ የዘመተው ህወሃት መራሽ መንግስት ከዚሁ ጎን ለጎን በስፋት የተያያዘው ነገር የህዝብን ስነ-ልቦና የሚዘርፍበት ፣ ማህበራዊ አስተሳሰባችን ርባና ቢስ የሚያደርግበት ዘመቻ ነው (ለአስተሳሰቦቹ ሃውልት የተሰራላቸው አንገበዋቸው የኖሩ አና አንግበዋቸው የሞቱ ኢትዮጵያውያንን በመዘከር አንደሆነ አንዳይረሳ)። ማህብራዊ ስነ-ልብና የሚዘረፍብት ምክንያት በዘራፊነት አና በግፍ ላይ የተመሰረተ የስልጣን ተዋረድ የማይቀርለትን ተቃውሞ በመገንዘብ  የተቃውሞውን ምንጭ አና ለስልጣን የበላይነቱ ችግር ይፈጥሩብኛል የሚላቸውን ጉዳዮች ከምንጫቸው ለማድረቅ ከሚደረግ ጥረት አካል ሊሆን አንደሚችል አገምታለሁ።

የመሃል ሃገሩን ታሪካዊውን – ዓለም ጭምር ያወቀውን የነጻነት ትግል የሚያስታውሱ መታሰቢያዎችን በ “ልማት” ሰበብ  “መልስን በክብር አንደነበረ አናደርገዋለን” አየተባለ እየሰወርን በነበረው የርስ በርስ ጦርነት  “ተሰው” የሚባሉ የህወሃትን ታጋዮች የሚያስታውስ መታሰቢያ ትግራይ ላይ ለቱሪስት ማስጎብኘት  አና “በክልሉ” የሚያድጉ ህጻናትን ጭምር በዚህ መልክ ማነጹ አሁንም ትምክህት ክተሞላበት የፓለቲካ ስራ  ውጪ ከ”ልማት”ጋር የትያያዘ ነው ለማለት ያስቸግራል።  በነገራችን ትግራይ ላይ ያለው ሃውልት ስለ ርስበርስ ጦርነቱ ሙሉ ገጽታ ይሰጣል? ለትግራይ ህጻናት ከ”ትግራዋይነት” እኩል ኢትዮጵያዊነት ስሜት አንዲፈጥሩ ያግዛል? የመሃል ሃገሩስ ታዳጊ ወጣት በራሱ አንኳን አነሳሺነት (መንግስት አንደማያደርገው አርግጠኛ ስለሆነኩ ነው) የሃገሩን ታሪክ አንዲጠይቅ የሚያስታውሰው መታሰቢያ አንዳያይ የሚደረግበት ምክንያት ስልታዊ የስነ ልቦና ዘረፋ ካልሆነ በስተቀር ምን ሊሆን ይችላል??

ህወህት የአርበኛውን የአቡነ ጴጥሮስን መታሰቢያ ህውልት አነሳለሁ በሚልበት ሰዓት ጣሊያኖቹ በኢትዮጵያ ብዙ እልቂት ላደረሰው የጦር መኮንናቸው (ግራዚያኒ) የመታሰቢያ ሃውልት ሊያቆሙ ነው። የህወህት ድርጊት ሳይታሰብ በአጋጣሚ የተደረገ ነው ማለት ያስቸግራል። ምናልባትም የአማካሪ  ሃሳብም ያለበት ድርጊት ሳይሆንአይቀርም(ከላይ nexus ያልኩበትም የጥርጣሬ መሰረት ይሄው ነው)። የህዝብ ስነ-ልቦና ዘረፋ የመጨረሻው ደረጃ መሆኑ ነው። ይሄ ጉዳይ በቸልታ የታለፈ አንደሆነ አንድ ሰው ገስግሶ ዓይናችንን ሊያጠፋው ወደዓይናችን ሲጠጋ አይቶ አንዳላይ  አንደመሆን ነው። በድርጊቱ ቀጥሎበት ዓይናችን ከተዛቀ የሚደርሰው ነገር ከአካል ጉዳትኝነት  ያልፋል።

የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሃይማኖታዊ የሆነ  አና የነፍጠኞች ነው ተብሎ የሚታሰበው( በህወሃቶች ዘንድ) የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የሃይማኖት ቅርስ አይደለም። ክርስቲያን ላልሆነውም ኢትዮጵያዊ ቅርስ ነው። ታሪኩ የሃይማኖት ሳይሆን የነጻነት ትግል ታሪክ ነው።  ስለሆነም አሁን ባለው ነብራዊ ሁኔታ በተሻለ ሁኔታ ተደራጂተው እየታገሉ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም አንደ ኢትዮጵያዊነታቸው በጽናት ሊቃወሙት አና ሊያወግዙት  የሚገባ ድርጊት ነው።

የነጻነትን ትርጉም አየጠየቀ “ሊበራሊዝምን” ከእምነት በማይተናነስ መልኩ ተቀብሎ  ስለ ውጭ ሰዎች የነጻነት እሳቤ አና ትግል የሚነግሩን የፖለቲካ ሰዎች (“አደፍርሶች”) ፤ የአቡነ  ጴጥሮስ አይነት ክቡር ዜጋ  ስለ ነጻነት በተግባር የከፈለውን መስዋዕትነት የመነጋገሪያ ርዕስ አድርገው ቢያወሩን ኖሮ ዛሬ አንዲህ አይነት ነገር ሲሰማ የሚሰማው ቁጣ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል በሆነ። የነ አባ ጳውሎስ ሃውልት ተጎልቶ የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት በ”ክብር ከቦታው ይነሳል” አየተባለ ሲላገጥ ከመስማት የበለጠ ውርደት ለዚህ ትውልድ መቸም አይመጣም።

ECADF.COM

የኢሳት አድማጮች አስተያየት

የኢሳት አድማጮች አስተያየት

ከሥርጉተ ሥላሴ 24-11-2-12

ፍለጋ ገባሁ። እርአስ መረጣ … ግን አጣሁ። ስለዚህ ያው ልጠይቀው አሰብኩት አቅም ስላለኝ።  በምልክት እንግባባ ይሆን ብዬም ተግ አልኩ።  ከዘራውን ዘወር አድርጊ ፊቱን ዬ ና – ን ግልባጭ አደባባይ ላይ – ሰገነቱ ላይ – ቀዩን ጃኖ አዘናክቼለት „በላ ልበልኃ“ አልኩታ እኔ ሞኝ።

አዎን ትናንት ማምሻ ላይ ከኢሰአት የአድምጮች ክፈለ ጊዜ የተሰጡትን በሙሉ አዳማጥኳቸው። ያው ትችቱንም የሰማዕት ህጻናትንም ድምጽ የወከለ ለዛውም በሥነ -ግጥም … ተመላለስኩበት። ያቺው ይህቺን ሰባራያን እስኪ … እስኪ … ተዚህ ላይ ይደገም እያልኩ አጣጥምኩት። ያው ሃዘን ሲበዛ ማጣጣም … መራራውን እንደ ጣፋጭ … ዶሮ ማታ ብዬ አሳንጋለውን ዘመን … አዳመጥኩት።

አንድ ሁለት የሚሆኑ አምልኮዊ ፍቅረ ወያኔ የተጠናወታቸው „መጥታችሁ ከዚህ እውነት ካለበት ቦታ ለምን አትዘግቡም? የምተወሩት ያልሆነውን ነው“ የሚልም አዳመጥኩ። እስቲ ሌላው ሁሉ ቀርቶ „ጠቅላይ ሚኒስተሩ ከህማቸው አገግመዋል። በቂ እረፍት ስለሚያስፈልጋቸው ነው እንጂ  እስከ አዲሱ ዓመት ድረስ ሥራቸውን ይጀምራሉ“  ያሉት አቶ በረከት ስሞዖን፤ በረከት ገ/ሕይውት  በአባታቸው መጠራት ስላባቸው … ምላሳቸው ለእህል ለውሃ ሳይደረስ „አለፉ – ሞቱ – ተሰነባቱ“ ሲሉ የት ነበሩ? … ሌላው ሁሉ ይረሳላቸውና … አንድ ትልቅ የመንግሥት ባላሥልጣን በአንድ ሞት እንኳን ስንት ጊዜ ሲቀላመዱ ተሰሙ። እንዲያውም የረገጡት ህዝብ ምን ያህል ጨዋ እንደሆነ ቢያገናዝቡት መልካም ነው። እንጂ ውሸታም! ውሸታም! ውሸታም እያለ ቢና ጢናቸውን አውጥቶ በአደባባይ  ቀልባቸውን በገፈፈው ነበር …

ሌላው ደግሞ ፈሪዎች … ናችሁ እንጂ … እንኳንስ ቴሌቢዥን እስክርቢቶ ፈርታችሁ አይደል እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን፤ እነ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን ያሰራችሁ። መታሰር ብቻ ሳይሆን ድርብ ግፍ እዬተፈጸመባቸው ያለው። „ፍትህና ፍኖተስ“  ስለምን ከህትምት ታገዱ“ ፍትህ“ ስለምን ተቃጠላች… የውሸትም ዓይነት አለው፤ የቅጥፈትም ዓይነት አለው … የትችትም ወግ አለው … ጥጋባቸው በዛ። — እንዲያው እኮ የወያኔና የደጋፊዎቹ  አሰራማ ገፈቱ ምንም እኮ የይሉኝታ ላሂ የሚባል የሌለው መሃን ነው። በጣም ….. የሽብርተኛ ህጉስ … ? እንዲያው ተምን ላይ ይመድብላቸው …

አሁን ወደ ተነሳሁበት። እንዴት ነው ሚዲያና የፖለቲካ ድርጀት ወይንም ንቅናቄ ድብልቅ ያለበት ይመስለኛል ወገናችን። „ኢሰአት ድረስልን በተሎ !“ የሚል ብሄራዊ ጥሪ ጎልቶ አዳምጫለሁ። „ካለ እናንተ ማንም የለንም።“ የሚልም።  ሚዲያ አንደበት ነው። ሚዲያ ዜና ነው። ሚዲያ ወቅታዊ መረጃ ነው። ሚዲያ እውነትን ለባለቤቱ ያስረክባል። ሳይጨምር ሳይቀንስ እንጂ ተዋጊ የፓርቲ ሰራዊት ሊሆን አይችልም። ይህ ከሆነ ሚዲያው ነፃ መሆኑ ቀርቶ ልክ እንደ ኢትቪ የወያኔ ቧ ያለ የቅጥፈት አፍ ነው የሚሆነው።

? ? ? እስኪ ፍቷት የተከበራችሁ የኢሰአት አድምጮች። ስለ መራባችሁም፤ ስለ መታረዛችሁም፤ ስለ መጨቆናችሁም፤ ስለ መታፈናችሁም፤ ስለ መገደላችሁም፤ ፈጽሞ በማይቻልበት ሁኔታ ከቦታው እዬተገኘ ኢሰአት መረጃውን ማዕከላዊ በሆነ መልኩ በወገናዊነት ኃላፊነቱን እዬተወጣ ነው …. የቀረው ነገር … ? ? ?  ናት ወደ ራሳችሁ መመለስ። ራሳችሁን በማዬት – መጠዬቅ።

? ? ?  የተራበ፤ የታረዘ፤ የተጠማ፤ የተገፋ፤ የተረገጠ፤ የታሰረ፤ ጉሮሮው የተዘጋ፤ ሥራ አጣ፤ ቤቱ የፈረሰበት፤ ከኑሮ የተፈናቀለ፤ ህጻናት ልጁን ከ አንቀልባ ላይ የተገደለበት፤ አባወራውን የተቀማ፤ ጉልቻው የፈረሰበት፤ ልጆቹ ከትምህርት የተፈናቀሉበት፤ መሬቱን ተቀምቶ እሱ ባይታዋር ሆኖ ለውጪ ሀገር የተሰጠበት፤ አንጡራ እትብቱ ለባእድ በስጦታ የተሰጠበት፤  ክልሉ የተጣሰበት፤ በፍርድ አድሎ የተፈጸመበት፤ ማንነቱ የተቀጠቀጠበት፤ በትርፍነት የሚገኝ ዜጋ የወያኔ የፊት ለፊት ረድፈኛ ተጠቂ  ? ? ?  ውጪ ያለው ሚዲያ ወይንስ ? ? ? የማከብራችሁ ሀገር ቤት ያለችሁ ወገኖች ተቀራረቡ … ከውስጥ ረመጣችሁ ጋር ? ? ?

ራህብን የሚያወቅው የተራበው ነው። እርግጥ ውጪ ያለው አይሰማውም ማለት አይደለም። ግን ማን እንደ ባለቤቱ። ውጪ ያለው ተራቡ ከሚልና እናንተ ተራብን ብላችሁ በጋራ ብትጮኹ ማነው የሚደመጠው ? ? ? በመዳህኒትዓለም ፊትም ሆነ እንዲሁም ብድርና እርዳታ በገፍ አያጎረፉ ወያኔን ጉልበታም ያደረጉት ኃያላን  ሁሉ የቀረቀሩትን ጆራቸውን ይከፍታሉ። ውጪ ያለው አብሶ አውሮፓ፤ አሜሪካ፤ አውስትራልያ፤ እንዲሁም ኒዊዝላንድ ያለው ወገን በልቶ ያድራል፤ መጠጊያም አለው፤ ነፃነትም አለው። የ እኔ ጌጦች … ውጪ ያለው ጩኽት ተጫማሪ እንጂ ወሳኝ ሚና ሊጫወት የሚቸለው የውስጡ ግፊት ነው። ፍውሰት የሚገኘው የታመመው በሽታውን ሲናገር ብቻ ነው። አፍናችሁ – እቅፍ ድግፍ አድርጋችሁ –  አሽኮኮ አድርጋችሁ ያዛችሁት እኮ የከረፋውን ግፍ … እና እናንተ  እስከ መቼ ? ? ?

የባዛው እሳት ከእራሳችሁ ላይ ነዶ ከእናንተው ዓናት ላይ ነው አመድ የሚሆነው …። በሁሉም ነገር እዬተንገበገባችሁ ያላችሁት እዬተቀጣችሁ ያለችሁት እናንተ ናችሁ። አይደለምን ? ? ? ። ስለሆነም በቃ! ማለት ያለባችሁ እናንተው ናችሁ። ብዙ ናችሁ። ዕልፍ ናችሁ። ዕልፍነታችሁን በተግባር ዕልፍ አድርጉትና ውጤቱን ለኩት። እርግጥ አላስፈላጊ መስዋዕተነት ክፈሉ ማለቴ አይደለም። ግን ለማናቸውም ነገር መንሹ ያለ ከእናንተ እንጂ ከኢሰአት አይመስለኝም።

…. እጅግ የምታናፍቁኝ፤ የምሳሳላችሁም ወገኖቼ እራሳችሁን ጠይቁ። ቁረጡ። ተመካከሩ። ከኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ተከታዮችም የተግባር ምርት ለመማር ተሰናዱ። በተቃዋሚ ፓርቲ የተደራጃችሁትም ምሩን … ለድል አብቁን ብላችሁ አፋጣችሁ ያዟቸው – መሪዎቻችሁን። እናንተም ቢሆን ግዴታችሁን በብቃት ተወጡ —  እነሱን ለመጠዬቅ በቂ መብት እንዲኖራችሁ።

ገፍተው የታገሉት እኮ ብቻቸውን ታሰሩ። አሁን ጋዜጠኛ እስክንድር ስንት ጊዜ ታሰረ? አቶ አንዱአለምስ? 21 ዓመት ሙሉ ተቃዋሚ ነን ብለው ለዘዝ ብለው ስለታገሉ — ለወያኔ የንግድ ፍጆታ ኮረጆውን በመሙላት ብቻ ቀዮዋን በር የማያውቋትም አሉ። ለማንኛውም ተጠ ያዬቁ  – ከፍላጎታችሁ ጋር። ተጠያዬቁ – ከራዕዮቻችሁ ጋር። ተጠያዬቁ – ከነፃነት ምኞታችሁ ጋር። ወያኔ ሚሊዎኖችን ማሰር ስላማይቻል በአንድነት ብትንቀሳቀሱ „ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ነው።“

ሰው ለራሱ ጉሮሮ እራሱ ብቻ ነው። ሲርባችሁ እንጀራን ሁል ጊዜ እራሳችሁ ነው በወጥ አጣቅሳችሁ የምትጎርሱት። የነፃነት ራህብ ከሁሉ የሚልቅ ነው። በቤታችሁ ውስጥ እንኳን ያለውን ነፃነት የምታውቁት እናንተ እንጂ እኔ ወይንም ሌላው አይደለም። ነፃነት – በነፃ ወይንም በርካሽ ዋጋ አይገኝም። የታሰሩትም እንደ እናንተ ትዳር፤ ኑሮ፤ ንጹሕ አዬር እንደ ሰው ያስፈልጋቸዋል። ለእነሱ የወር ማህያቸው በቂ ባይሆንም የጉሮሮ ማርጠቢያ ይሆናል። ግን ለማን ? ? ?  ስትሉ ከመልሱ ጋር ትታረቃላችሁ። ከሰማይ የሚገኝ መና የለም። ካለምንም ጥገኝነት። ወንድ ሴት፤ ሽማግሌ፤ አዛውንት ሳትሉ ከከፋችሁ ቀን ጋር ለመፈታት ድፈሩ።  በቃህን፤  አሁንማ አበዛኽው በሉት – ጎጠኛውን ሙጃ።

ትጠበቃላችሁ! …  ሶስቱ ሚስጢራት ተቆላልፈው — ተያይዘው — ተስማምተው እናንተኑ ይጠብቃሉ።  …  እንዚሁላችሁ አንድነት – በፍቅር፤ ቁርጠኝነት – በፍቅር፤ ድፍረት – በማስተዋል!  ቁልፉን —- ለመፋትት ተሰናዳችሁን  ? ? ?

እግዚአብሄር አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ። ህዝቧንም በበረከት ያጥግብ!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ECADF.COM

Likely war over the Blue Nile River?

Likely war over the Blue Nile River?

by Robele Ababya, 23 November 2012

The Nile water is the sole lifeline for Egypt to which the Blue Nile River contributes 85%. The Blue Nile River is a vital indispensable resource of Ethiopia for irrigation farming in view of her increasing population, source of hydraulic power, and a deterrent weapon of last resort for self-defense. The two countries are naturally bound by the Blue Nile on which they are dependent for survival. This is a top priority agenda like no others for both Ethiopia and Egypt to take extreme care in order to stop radicals on both sides bent on souring relations.

The writing of this piece is prompted by the uncertainty in the fate of multi-party democracy in Egypt and the intransigence of the TPLF-controlled EPRDF government to make an all-inclusive change conducive to robust internal harmony and unity to respond to any external threat to national interests. The matter is so serious that I gave it a rather scary title after a lot of soul-searching, but the arrogant stance of prominent Egyptian leaders begged for it as mentioned in the paragraph below – notwithstanding my long held dream that democratic Ethiopia and Egypt will one day emerge as powerful allies working together as keepers of stability and engines of economic growth in the region and beyond in the African continent.

But the new Egyptian regime appears to have dimmed any hope of engendering a secular democratic state given that liberal democratic political forces that have spearheaded the Egyptian revolution have withdrawn from drafting the constitution. It seems the government is bent on following in the footsteps of its predecessors. For example: in 1970, Egyptian President Anwar Sadat threatened war with Ethiopia over the proposed construction of a dam on LakeTana on the Blue Nile (El-Khodary, 1995: 1); the Egyptian former Secretary General of the United Nations, Boutros-Ghali, is reported to have talked of war over the Nile waters (Butts, 1997: 1); in October 1991, the Defense Minister of Egypt “remarked in al Ahram that his country would not hesitate to use force to defend its control of the Nile River, and predicted that future Middle East wars could result from water scarcity issues (Postel, 1992: 4) adding “I do not actually expect an impending control of the Nile River by a foreign country, but we consider it a possibility and are planning our military strategy accordingly” (Postel, 1992: 5).It is to be recalled that the Minister, Field Mohamed Hussein Tantawi Soliman, took over power from President Mubarak relinquishing it later to President Mohamed Morsi of the Moslem Brotherhood Party (FJP).  My emphasis

This recent setback for democracy in Egypt has considerably curbed my earlier hope that democratic Egypt and Ethiopia will play key roles in stabilizing the region and promoting development thus becoming formidable political forces to contend with; will be partners in the development of the Nile Basin – a key factor of regional policy to avoid war.

There is nothing more serious than asserting Ethiopia’s right to control the source of the Blue Nile, but this requires the unity of her citizens and competent leadership with Ethiopia’s interest at heart. But the EPRDF as it now stands is so weakened by internal wrangles of its own creation rendering it unable to defend vital national interests in the face of endless threat by Egypt to control the Blue Nile River.

Diminishing per capita quota of Nile water

The table below provides a frightening data of rapidly diminishing quota per capita of water available to riparian states for the period 1995 to 2025 vindicating the predicted fear that future wars would be over water more than anything else. Note that Ethiopia would incur a loss of 1365 cubic meters by 2025 remaining with only 842 cubic meters per capita quota in almost 12 years from now.

Diminishing per capita quota of Nile water

Source: Water politics in the Nile Basin: From Wikipedia, the free encyclopedia, (December 2007)

Suggestion to split riparian states in two groups

There are ten (10) riparian states entitled to the utilization of the Nile water of which Ethiopia is the source for 85% of it. With Egypt at the receiving end, Sudan in the middle and Ethiopia as the source, the relationship among these three countries is of paramount importance to the rational development of the Blue Nile Basin for the proportionate benefit of all parties.

It is interesting to note that the seven riparian states in the Great Lake Region are a cohesive group in the East African community with only Uganda having dams built or planned project on the White Nile River. This is unlike the other three lacking the knack for political cooperation due to their history of conflicts for centuries; the two of them are members of the Arab League traditionally inimical to vital strategic interests of Ethiopia.

The Nile water should therefore be resolved in two parts comprising White Nile riparian states on the one hand and those of the Blue Nile on the other so that issues unique to each can be much less cumbersome to handle and more effective to define and resolve to the satisfaction of parties to the issue. The approach in handling the matter at the two distinct regional blocs is further justified by the fact that the need for the Nile water greatly varies among the ten riparian states. But cooperation is encouraged under the umbrella of all riparian states of the Nile and African Union where the interests of the two blocs converge.

It can be argued that Ethiopia as provider of the lion’s portion  is entitled to have veto power in any bilateral agreement with Sudan involving the sharing, conservation and development of the Blue Nile water; similarly, Sudan should have a veto power over its agreement with Egypt. However it would be best if the three enter into a viable single agreement and forge a regional community emulating the countries of the Great Lake Region. This is in line with my recommendation made three decades ago in a friendly discussion with Egyptian experts at the reception held at their Embassy in Addis Ababa. It was appreciated that: cooperation would open the door for regional economic block involving Egypt, Sudan, and Ethiopia; the trio would become a powerful block in bolstering and expediting the African Union to realize continental integration; the saving of resources from such arrangement would be enormous.

The Blue Nile River is a natural bond of indispensable significance to Egypt and Sudan. Ibrahim Nasreddin of Cairo University’s Institute for African Studies said that “a 20-year-old feasibility study, a cooperative venture between some of the Nile’s source countries and donor states, to build 50 dams on the River Nile over 50 years has not seen any headway due to the high cost of these dams”.  He added that “the projects would cost in excess of $40 billion. According to Nasredin, “none of the African states can afford this. They won’t be able to repay loans of such an amount.” Source: Article by Reem Leila, Al-Ahram Weekly January 5, 2011.

Incidentally, the Imperial regime had participated in the abovementioned study, which I had the opportunity to see several volumes shelved in the study room of the Monarch at His Bahr Dar Palace. I was reverently surprised by His interest to read about the study of the dam projects.

Water expert Diaa El-Qousi stresses that “Egypt’s cooperation with other Nile Basin countries is based on a sense of neighborhood and an understanding of mutual interests and is likely to be an ongoing process that will encompass educational, irrigation, electricity, agriculture and industry-based projects. He goes on to state that “Egypt’s immediate focus will be on issues deriving from the ecology of the Nile Basin and on prospects for economic integration among the riparian countries that provide Nile water in a way that will ensure the maximum utilization of resources. Egypt is taking steps towards implementing joint projects with Nile Basin countries and is seeking agreement on future plans. Within this context, economic and trade relations between Egypt and Ethiopia are developing rapidly. The volume of Egyptian investments in Ethiopia is expected to increase to more than $1.1 billion.”

I was upbeat about the Egyptian uprising as written in some of my articles. However with the reported stance of President Morsi behaving like ‘the new Pharaoh’, entirely exclusive of secular liberal political parties that spearheaded the uprising, I should confess that my enthusiasm is considerably subdued. So should the optimism of Nasredin and Diaa El-Qousi, I would think. Egypt should propose scaling down of the DAM instead of pushing to scrape it altogether taking advantage of the weakness of the EPRDF at this time.

The Renaissance Dam

At all times and at this time of uncertainty in regional politics particularly I reiterate my stand that robust defense force and internal harmony are quintessential to preserve and protect national values; however the repressive government in power must change its ethnic-based policy and open the political space for very serious consultations with all political opposition parties, civic organizations, and above all the Ethiopian people as the ultimate and supreme source of power and owners of the country’s resources. I would like to underline that it would be foolhardy to construct the so-called “Renaissance Dam” at a location within artillery range from Sudan – a situation that will require missile defense against in-coming Egyptian air strike. My hunch is however that Egypt will send a commando force at some critical stage to destroy the Dam, which action would inflame political turmoil in Ethiopia and entail hefty loss of capital expenditure – a highly probable grave scenario indeed.

My suggestion is therefore to scale down the size of the Dam at its present location considerably and build as many other dams as required in the Amhara, Oromia and Gambella regions on rivers tributaries of the Blue Nile.

Conclusion

It is irresponsible to weaken internal harmony and strength by pursuing the familiar cheap politics of divide-and-rule along religious and ethnic lines thereby playing into the hands of hawkish Egyptian leaders to exploit any weak point in our midst to destabilize us. Therefore EPRDF government should release all political prisoners, preserve the unity of the 1682-yeay-old Ethiopian Orthodox Tewahido Church, and acquiesce to all constitutional demands of the Ethiopian Muslims so that unity and strength is achieved to effectively defend national interest.

The riparian states of the Nile should be split into two blocs, namely, Ethiopia, Sudan and Egypt on the one hand and the rest on the other. Ethiopia is legitimately the one to control the Blue Nile River in her territory and use it as a deterrent weapon of last resort in self-defense. To that effect, there has to be unity, internal peace and strength.

LONG LIVE ETHIOPIA!!!

ABBAYMIDIA.COM 

ፈተናን ረቶ የተፈጠረ ሚስጢር

ከሥርጉተ ሥላሴ 21.11.2012

አንዳንድ ጊዜ በዬትኛውም ሁኔታ በራዲዮ፤ በቴሌቪዢን፤ በስብሰባ፤ ወይንም በማህበራዊ ኑሮ የሚኖሩ አገላለጾችን በትርጉም ማቃናት የተገባ ነው። አብሶ በዘበኝነት የተሰማሩ ብዕሮች ይህንን ኃላፊትነት ተግተው መወጣት ይኖርባቸዋል።

ብቁ – ንቁ – ሞራል፤ – ትእግስታዊ – ሰላማዊ – ትዕይንት። – መምህራዊ – ማህበራዊ — ዕምነታዊ ሞገድ። ምን ቀረኝ ይሆን? …  የሰለጠነ … ዓላማውን ጠንቅቆ ያወቀ – ፍላጎቱን የተረዳ – ያደገ – አህታዊነት የተከተበበት ድንቅ የነፃነት እንቅስቀሴ ነው የኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ተከታዮች ተጋድሎ።

የእንቅስቃሴው ተመክሮ ማሳ ግን የንጋት ወጤት አይደለም። ከ40 ዓመት በላይ ዕድሜን ያስቆጠረ  የኢትዮጵውያን የወል እንቅቃሴ ልምድ ተጨባጭ ወጤት ነው። የኢትዮጵያ እስልምና እምነት ተከታዮችን የእንቅስቃሴ ድንቅነት ጉልበታም የሚያደርገው መሰረታዊ ነገር፤ በነበሩ ድክመቶች ላይ አልተመለሰባቸውም። ይልቁንም አዳዲስ የፈጣራ ቅኔዎችንም ተግባር ላይ አውሏል። ሂደቶቹ በሙሉ ሙሉዑና የታቀዱ መሪም ያላቸው ናቸው። በሌላ በኩል ሰላማዊ ትግል ብቁ፤ ደፋር፤ መሪ ካገኘ ካሰቡት የሚያድርስ ሰጋር ስለመሆኑም ትዕይነቱ ተግባራዊ ታሪክ ሰርቷል። ትልቁ ነገር ወያኔ በግፍ የጫነውን ፍርኃትንና ስጋትን ገርስሷል። ይህ በራሱ ድርብ ድል ነው።

ሰላማዊ ትግል ሰላማዊ ነው። ሰላማዊነቱ ሙት መሬት ላይ ሆኖ ገዢ መሬት ላይ ያለውን በሁሉም ዘርፍ የተሟላ የሎጅስቲክስ ድጋፍ ያለውን መንግስታዊ ተቋም በእውነትን መዳፍነት፤ ግፍን ለመጣል በጀግንነት ፊት ለፊት መጋፈጡ ነው።

ሰላማዊ ትግል ህጋዊ መብቶች የታፈኑባቸውን የአፈጻጻም ሥርዓቶችን ጥሶ በመጓዝ በተለያዬ ሁኔታ ተቃውሞውን በመግለጽ ነፃነቱን ከጨቋኞች መንጋጋ በሰላማዊ ኃያል ማስላቀቅ ነው። እኩልነቱን በሰላማዊ አመጽ አስገድዶ ማምጣት መቻሉ ነው። መስዋዕትነቱ ግን ሰፊ ነው። ባዶ እጅ ነውና። የነፃነት አምላክን ግን በመንፈሱ ሰንቆ  የሚንቀሳቀስ በመሆኑ ጥበቃው ሰማያዊ ነው።

ሰላማዊ ትግል ትዕቢተኞችን በሞራል ድቅቅ አድርጎ የሚያስተንፈስ ጉልበቱም ነው።  ኃይሉ ወደር የለውም። ታዳሚዎች ወደውና ፈቅደው ስለሚሰማሩበት ምንም የመንፈስ ሃብት – ንብረት ሳይባክን ለታሰበው ዓላማ ስኬታምነት በተዋህደ ቅንብር መንፈሳዊ ሃብቱን በአግባቡ መዋል ይችላል። አብሶ መሰረቱ የበሰበሰ ሥርዓት ከሆነ ተጨባጭ ሁኔታዎች እራሳቸው ገዢ መሬቱን ደልድለው ይጠብቁታልና።

ሰላማዊ ትግል ላይ ሁሉንም በእኩልነት መሬት ላይ በስፋት ስለሚያሳትፍ የዕድሜ፤ የጾታ፤ የብሄረሰብ፤ የእውቀት፤ የዕምነት ተዋፆውም ሙሉዑ ሰለሚሆን ተመክሮው ሆነ ልምዱ፤ መንፈሳዊ ሃብቱን ጨምሮ ጥሪተ – ዲታ ያደርገዋል።  ለሰላማዊ ትግል አርበኛ መቋጠሪያም አለው። መሰብሰቢያም አለው እሱም ድንግሉ ቅንነት ነው።

ቅንነት እንደ ቃሉ የአራት ፊደላት ቅመረት አይደለም። ቅንነት ለማናቸውም ዘርፍ ነፍሱ እስትንፋሱ ቅምጥ ሃብት ነው። ቅንነት ካለ ድል አለ። ቅንነት ካለ ፍቅር አለ። ቅንንት ካለ መደማመጥ አለ። ቅንነት ካለ ከበዱ ሸክም ቀላል ነው። ጨለማማው ጉዞ  – ብርሃናማ፤ ኮረኮንቹ – ደልዳላ፤ ወጣገቡ  – ሰጥና ለጥ ያለ ይሆናል።  የማናቸውንም ትግል ቀመስ  ፈተና ትብትብ የመፍታት አቅሙ ያለው ከቅንነት ዘንድ ብቻ ነው። ለእኔ ከፍቅር ይልቅ ቅንነት ይበልጥብኛል። ቅንነት ሲኖር ነው ፍቅርን እንደ ተፈጥሮ መተርጎም – ተጠቃሚ መሆንም የሚቻለው።

በዘመናችን ያየናቸው ህዝባዊ እንቅስቀሴዎች በቅነነት ሲመሩ ጉዟቸው ወደፊት፤ ውጤታቸው ሰብላማ ይሆናሉ። ቅንነት ሲያነክስ ደግሞ  ጉዞው ወደ ኋላ ይጎተታል። ልፋቱም ብላሽ። ስለሆነም ለህዝባዊ የነፃነት እንቅስቃሴ ሁለገብ መፍቻ ያለው ከቅንነት ነው። እኔ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንቅስቃሴ አብዝቼ ታዳሚ የሆንኩበት መሰረታዊ ምክንያት ቅንነትን ሰንቀው ለዓላማቸው በመነሳታቸው። ከአንዱ ደረጃ ወደ ሌላው ደረጃ የሚያደርጉት ሽግግር ሁሉ ማራኪ፤ ልብ አንጠጠልጣይ ኪኖ ሆኖ ነው ያገኘሁት  – እኔ በግሌ። ለነፃነት እንቅስቃሴም አዲስ ፊኖሚናም ነው … ሥነ ጥበባዊም ውበት አለው። እንቅስቃሴው አሁን ደግሞ በአደገ ደረጃ ላይ በመገኘቱ እስረኞችን በታሰሩበት ቦታ ጸጥ ብሎ ተሞ የልቡን አድርሶ በጸጥታ ተምልሷል። ወሸኔ!

በዕለቱ ህዝባዊው ሞገድ በወያኔ መራሹ የፀጥታ አስከባሪዎች ቆስቋሽነት የደረሰበትን ጥቃት በትእግስት ተቋቁሞ ተልዕኮውን በጀግንነት ፈጽሟል። ሀገር ቤት ለሚገኙት ለሰላማዊ የተቃዋሚ ኃይሎች ታጋዮች ሰላማዊ ነው መንገዳችን፤ ስትራቴጃችን፤ ስልታችን ነው ለሚሉትም …. በእውነት መምህር ነው። የጀግንነት ውሎው በራሱ አንድ የተግባር የትምህርት ተቋም ነው።

አዎን በቃሊትው የኢትዮጵያ እስልምና አምነት ተካታዮች ትዕይነት ላይ ኢትዮጵውያን ወገኖቻችን ሁለገብ ተሳትፎና እገዛም እንዳደረጉ በሪፖርቱ ተደመጧል። ወሸኔ ነው። ይህ የኢትዮጵዊነትን ግብረ ገበ ነብዬ መሀመድም ገልጸውታል። ኢትዮጵያ የክፉ ቀን ዋሳቸው እንደነበረች መስከረዋል። ይህ ማለት ኢትዮጵዊነት በሁሉም መሰክ የነጠረ ሁለገብ የተግባር መስክ መሆኑን ቀደምቱን በቅኝት መፈተሽ ያስችልናል።

ኢትዮጵያዊነት በማናቸውም ፈተና ውስጥ ነጥሮ የሚወጣ የስምረት ማተብ ነው። ኢትዮጵያዊነት ለፈተና ሽንፈት ድርድር የሚያድርግ አይደለም። እደግመዋለሁ ኢትዮጵዊነት ለፈተና ሽንፈት  ድርድር የሚያደርግ አይደለም። ስለምን? ኢትዮጵዊነት ሲፈጠር ፈተናን ድል አድርጎ የተፈጠረ ነውና። አንድ ጽንስ በሁኔታዎች አለመስማማት ሊያሰወርደው ይችላል። እድገቱ ተጨንገፎ ከቀናቱ ቀድሞ ሊወለድም ነፍሱ ሳትቀጥልም ሊሞትም ይችላል …

ኢትዮጰያዊነት ግን ፍጥረተ – ነገሩ ይህ አይደለም። በሙሉ ቀን በአማላካችን በመዳህኒታችን ፈቃድ የተፈጠረ። አማኑኤል ለመንፈሱ ማረፊያነት – ጥግነት የፈጠረው ሚስጢር ነው። አሁን መጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ቦታ ላይ ስለ ኃያሏ አሜሪካ፤ ስለ ኃያሉ ጀርመን ተጠቅሷልን? ስንት ጊዜ ነው የዓለምን የክርስትና ዕምነት በማዕከልነት ከሚመራው አንደበተ እግዚአብሄር፤ አካል ከሌለው ትጉኽ አገልጋይ ቃለ ወንጌል ላይ ኢትዮጵያ የተጠቀሰቸው? የኢትዮጵውያነት እናት ደግሞ ኢትዮጵያ ሀገራችን ናት።

… በምንም መስፈርት ኢትዮጵያዊነት ፈተናውና ያለፈው ሲፈጠር ነው! ኢትዮጵያዊነት ፈተናን ቀድሞ የተፈጠረ ድንግል መንፈስ ነው!  ኢትዮጵያዊነት ዛሬ ወይንም ትናንት የተፈጠረ አይደለም። ዓለምን ከነመሰረቱ የፈጠረ ረቂቅ መንፈሳዊ መክሊት ነው። ስለሆነም ፈተና ስለበዛ የሚያዳልጠው ወይንም የሚላጥ፤ ወይንም የሚፋቅ ወይንም የሚተረተር፤ ወይንም የሚሰነጠቅ አይደለም። ወጀብ አውሎ  በመጣ ቁጥር ወገቤን ያዙኝም የሚል አይደለም። ሊሆንም አይችልም።

አይደለም እኛን ዓለምን የፈጠረ ዕንቁ  – ቅዱስ – ድንግል  -ንጹህ መንፈስ ነውና …ገና ብዙ ተፈልፍለው የሚያበሩ ነገረ አልማዛት አሉት።

ከዚህ ጋር ልናያውና ልናስተውለው የሚገባው ትልቁ ቁም ነገር … ኢትዮጵያዊነት አብክሮ ///  በተደሞ፤ በአጽህኖት፤ ጨዋ፤ አድማጭ ፤ትዕግስተኛና የእውነት አርበኛ መሆኑን ማስተዋል አለብን። ኢትዮጵያዊነት ማለት ሐዋርያነትም ነው። ሐዋርያነቱ መሰረቱ ይሁን ጉልላቱ ማስተዋል ስለሆነ ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች በተደሞ፤ በቀስታና በእርጋታ ይመረምራል፤ የሚጠፋው ምንም ነገርም የለም። እንዲያውም ቀድሞ የሚታሰቡትን ሁሉ አስቀድሞ የመተንበይ ብቃቱ ሙሉዑ ነው።

ይህ የኢትዮጵያ እስልምና ተከታዮች እንቅስቃሴ — እኛ የነጻነት፤ የእኩልነት፤ የመብት ጥያቄ ነው እንላላን። ከዚህም ሌላ

  1. 1.    ዓለም የሚታመስበት እጅግ የሚሰጋበት፤ የሚፈራበትና የሚረበሽበትም ጉዳይ አለ።  ጽንፈኛው የእስልምና ዕምነት እንቅስቃሴ።
  2. 2.   እንዲሁም የኢትዮ ጂኦ ፖለቲካዊ አቀማማጥና ለአካባቢው ያላት ሁለገብ መስህብነት።
  3. 3.   ከአካባቢው አጎራባች ሀገሮች ተለይታ ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታይ መሆኗ …።
  4. 4.   እስካሁን በነበሩት የሌሎች ሃይማኖቶች ጭቆናዎች፤ ግፎች  የዕንባ ዘመኖች ሁሉና ሂደቶችም  የእስልምና እምነት ተከታዮችን ነበር አጋርነት፤ ታዳሚነት በተጨባጭ መፈተሽ የሚፈልጉ ወገኖችም መኖር …
  5. 5.   በአመዛኙም የኢትዮጵያ የእስልምና እምነት በወያኔ ተከብሮና ተደምጦ የቆዬ ነው የሚሉም ቀላል ያልሆኑ ወገኖች ሀሳባቸውን ሲሰነዝሩ መደመጡ

ባጠቃላይ እነዚህ ነገሮች በአግባቡ ጊዜ ተስጥቷቸው ወጥ የሆነ አስተሰሰብና እገዛ ለማድረግ ጊዜ ይጠይቃል። ይህ የማስተዋል ጊዜ ደግሞ የኢትዮጵያዊነት ሥነ -ምግባር የተቀመመበት መንፈስ ነው። በጥሞናም የተቀመቀመበትም ጥልፍ ነው። ታዲያ ይህ የማስተዋል ጊዜ፤ ይህ የዳኝነት ጊዜ  ኢትዮጵያዊነትን ተጠያቂም ሊያደርገው ፈተና ላይም ሊያስቀምጠው በፍጹም አይገባም። ይህም ብቻ አይደለም ፈተናውን ማለፉንም ለመመስከር እኛ አቅም ያለን አይመስለኝም። ኢትዮጵያዊነትን ለመገምግም። ኢትዮጵያዊነት እኮ ጥልቅና ዝልቅ ነው ሚስጢራቱ።

ኢትዮጵያን አንድ ጀርመናዊ ጸሐፊ ሲጽፈው “ እኛ ከመፈጠራችን የቀደመችው ሀገር“ ሲል ነው የቀደሳት።  እኔ እንደማስበው በተለምዶ እንጂ የሶስት ሺህ ዘመነት ብቻ አይደለም ታሪካችን ከዚህም ያልፋል ዬኢትዮጵያ የግዛት ወሰን እስከ ማዳጋስካር … ነበር ይህም ብቻም አይደለም በ21 ምዕተ ዓመት የዓለም ህዝብ መፈጠሪያ መሆኗስ … ? ወደ ኋላ ስንት ዘመን በምልሰት እንደንፈትሽ ይጋብዝናል?

እንደ ማሳረጊያ …. ከሀገራችን ማንነት ጋር ያሉ ጉዳዮችን ስናነሳ ተያያዥ፤ ተወራራሽ የሆኑትን ተጨባጭ እውነታዎችን ትራስ ማደረግ ይኖርብናል። ኢትዮጵያዊነት በቀላል የሂሳብ ስሌት የሚደመርና የሚቀነስ፤ ወይንም የሚተረጎም አይደልም። ቅዱስ መንፈስ ነው። ለቅድስናው ለንጽህናው እጅግ ጥልቅ መረጃዎችን፤ ማመሳካሪያዎችን ማቅረብ ይችላል። ስለ ምንድ ነው 24 ሰዓት ሙሉ ግርማ ሌሊት ሳይፈሩ በዱር በገደል ቅጠል እዬበሉ ደናግል የሚጸልዩት … ሚስጢሩ ያለው ከዚያ ላይ ነው … የፈለቀ ጸበል የሚፈውሰውስ? በመጠነ ሰፊ ፈተናና ወጀብ የእናት ሀገር ህልውና መቀጠሉስ? የሰለጠነ  የአውሮፓን ጦር መክታ የነፃነትን ፋና ወጊ መሆኗስ? ፊደላችንስ … የውስጥ ውበታችን ጠረንና ከሩቅ ጠሪነትስ? ተፈሪነትስ? ፈተናን ሁሉ ረቶ የተፈጠረ ሚስጢር – ኢትዮጵያዊነት።

እግዚአብሄር አምላክ ትርጉም ያለውን ነፃነትን በሁሉም ዘርፍ በሀገራችን እናይ ዘንድ ይርዳን። አሜን!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ECADF.COM

የፌድራል ፖሊሶች ህፃን በናትዋ ጀርባ ላይ እንዳለች በዱላ መተው መግደላቸው ተዘገበ

ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- በሀና ማሪያም አካባቢ መንግስት የሚያደርገውን መኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ አስፈፃሚ የሆኑ የፌድራል ፖሊሶች ህፃን በናትዋ ጀርባ ላይ እንዳለች በዱላ መተው መግደላቸው ተዘገበ።

ከ30.000 ሺህ በላይ አባ ወራ በተፈናቀለበት የንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 መኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ ትላንት በናትዋ ጀርባ እንዳለች በፌድራል ፖሊስ ተመታ ከሞተችው ህፃን ጋር የሞቱት ቁጥር አራት ደርሰዋል።

መጠለያም ሆነ ተለዋጭ ቤት ሳያገኙ ቤታቸውን ከነንብረታቸው በግሬደር እየተደረመሰ ያለው የወረዳ 01 ነዋሪዎች ለብርድና ለሀሩር ከመዳረጋችን አልፎ በፌድራል ፖሊሶች የሚደርስባቸው ድብደባ ፣ እስራትና ግድያ ባስቸኮይ እንዲቆምላቸው ጥሪ አድርገዋል ።

በፌድራል ፖሊስ ወደ ተገደለችው ህፃን መጠለያ ለቅሶ ለመድረስ እንኮን አልተፈቀደልንም ያሉ ነዋሪዎች መንግስት የበደል በደል እየፈፀመብን ነው ሲሉ ምሬታቸውን ገልፀዋል።

በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ከሳምንት በላይ በዘለቀው ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ ከ30 ሺህ በላይ ቤቶች ፈርሰው ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሜዳ ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ካአካባቢው ሰዎች የሚደርሰን መረጃ ያመለክታል።

በዚህ የማፍረስ ዘመቻ ቤተክርስቲያንና መስኪድ ሳይቀር መፍረሳቸውንም መዘገባችን ይታወሳል።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ዛሬ ፍ/ቤት ቀረቡ

ኢሳት ዜና:-በእነ አንዷለም ዓራጌ መዝገብ በተከሰሱት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ንብረት እንዲወረስ ዓቃቤ ሕግ በጠየቀው መሠረት ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ በዛሬው እለት ፍ/ቤት መቅረባቸው ታውቋል።

በንብረቱ የዕግድ ትዕዛዝ ላይ አስተያየቱን እንዲሰጥ የተጠየቀው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ መንግስት ይውሰደው አልከራከርም ባለቤቴም ድርሻዋን እትጠይቅም በማለት ልፍርድ ቤቱ ምላሽ መስጠቱን ከአዲስ አበባ የመጣው ዜና ያስረዳል። ፍ/ቤቱም ሥለራስህ እንጂ ባለቤትህን ወክለህ መናገር አትችልም በማለት ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሠርክዓለም ፋሲል ራስዋ ቀርባ እንድታስረዳ አዟል በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሕዳር 28/2005 ቀጠሮ ሠጥቶ ችሎቱ መነሳቱም ታውቋል።

ዓቃቤ ሕግ እንዲወረስ የጠየቀው የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቤት ባለ ሁለት ፎቅ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት እንዲሁም የወላጅ እናቱ ቤትና መኪና መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲሁም ወጣቱ ፖለቲከኛና የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አንዷለም አራጌ የአንድነት ማዕከላዊ ምክር ቤት አባል ናትናኤል መኮንን እንዲሁም የመኢዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወጣት ክንፈሚካኤል ደበበ በአሸባሪነት ተከሰው ከታሰሩ አንድ አመት ያለፋቸው ሲሆን እስከ እድሜ ልክ የደረሰ ቅጣት እንደተወሰነባቸውም ይታወቃል።